Thursday, April 7, 2016

ደቀ መዝሙር ከፍያለው ቱፋ ከኮሌጁ የተሰናበተበትን ደብዳቤ በፍርድ ቤት በማሳገድ ወደኮሌጁ ተመለሰተሐድሶ ሆኗል ተብሎ ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተጻፈ ደብዳቤ የተሰናበተው ደቀ መዝሙር ከፍያለው ቱፋ በፍርድ ቤት ትእዛዝ የስንብት ደብዳቤው እንዲነሣለት አደረገ፡፡ ወንጌልን መስበክና ስለ እውነት መዘመር ትክክለኛ አቋም እንጂ ስሕተት ባይሆንም እውነትን ሐሰት፣ ሐሰትን እውነት፣ ብርሃኑን ጨለማ ጨለማውን ብርሃን ማለትን ሥራዬ ብሎ የያዘው ማኅበረ ቅዱሳን፣ የከፍያለውን ስንብት መነሻ በማድረግ ደስታውን በሐራ ብሎጉ “ሰበር ዜና” ብሎ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ነበር፡፡ እርሱ “ትክክለኛ” ከሚለው መንገድ የወጣውንና በእርሱ አስተሳሰብ “የጠፋውን” ሰው ከመመለስና ስለእርሱ ከማዘን ይልቅ "በመጥፋቱ" ደስታውን የገለጠበት መንገድም አሳፋሪ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ደቀ መዝሙር ከፍያለው መብቱን ለማስከበር ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞ በመሄድ የስንብቱ ደብዳቤ በሌላ ደብዳቤ እንዲሻር ትእዛዝ በማጻፍ ትምህርቱን እንዲቀጥል አድርጓል፡፡ ኮሌጁም የፍ/ቤቱን ውሳኔ ተቀብሎ የመጀመሪያውን ደብዳቤ የሚሽር ሌላ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ ይህም ኮሌጁ የወሰደው እርምጃ ሕግንና ሰብአዊ መብትን የሚጋፋ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ደቀመዝሙር ከፍያለው መብቱን ለማስከበር የሄደበት መንገድ በሕገወጥ መንገድ እየተባረሩ ላሉ መብታቸውን በሕግ ለማስከበር ትልቅ ማበረታቻ ሲሆን፣ ሰውን ከቤተክርስቲያን በማባረር ሃይማኖትን የሚያስጠብቁ እግዚአብሔርንም የሚያገለግሉ ለሚመስላቸው ክፍሎችም ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ማኅበረ ቅዱሳንን ለማስደሰት በሚል በአንዳንድ አድር ባዮች እየተሄደበት ያለው እንዲህ ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ከሕግና ከሥርዓት ወጪ ከቤተ ክርስቲያን የማባረር እስትራቴጂ ፈጽሞ መቀየር ያለበት ነው፡፡ አንድን ሰው ከማባረር በፊት ያን ሰው አቅርቦ ማነጋገር፣ የንስሐ እድል መስጠት ይገባል፡፡ ገና ከመነሻው መመለስን ሳይሆን ማባረርን ግብ አድርጎ መሥራት ግን መንፈሳዊነት አይደለም፡፡ በዓለም እንኳን እንዲህ አይደረግም፡፡ አንድ ሰው አጥፍቶ ቢገኝ በየደረጃው ምክር ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እንዲታረም እንጂ ፈጽሞ እንዲጠፋ አይደረግም፡፡ ይልቁንም ቤተክርስቲያን እንዲህ ያለውን ጉዳይ በልበ ሰፊነትና በትእግስት መያዝ፣ ሰውን ለማጥፋት ሳይሆን ለማቅናት መሥራት አለባት፡፡  

ይህን የኖረ ትክክለኛና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቤተክርስቲያን ሥርዓት በተለይ ማህበረ ቅዱሳን ከተነሳ ወዲህ ፈጽሞ በመለወጥ እርሱ ተሐድሶ ብሎ የጠረጠረውን ሰው አቅንቶ መመለስ ሳይሆን ከቤተ ክርሰቲያን ማባረርን ግብ አድርጎ በመንቀሳቀስ ኢክርስቲያናዊ ባህል እንዲሰርጽ አድርጓል፡፡ በመሆኑም ዛሬ ተሐድሶ ተብሎ የተጠረጠረ ሁሉ ተመክሮ ተዘክሮ ይመለሳል የሚል አመለካከት የለም፡፡ ዕጣ ፈንታው መባረር ብቻ ሆኗል፡፡ እንዲህ ባለው መንገድ ቤተክርስቲያን ብዙ ሊቃውንትን አጥታለች፡፡ ስለዚህ አሁንም እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች በትክክለኛው መንፈሳዊ መንገድ ካልታዩና ማኅበረ ቅዱሰን በቀየሰው የ “አባረህ በለው” መንገድ ከተሄደ ቤተክርስቲያን ገና ብዙ ሰዎችን ታጣለች፡፡ እረኛ በማጣት ወደሌላው በረት የሚሄደውን ሕዝብ ያክል በዚህ የማኅበረ ቅዱሳን ሰይጣናዊ መንገድ እየተባረሩ በሚወጡ ቤተክርስቲያን በብዙ ትጎዳለች፡፡ ስለዚህ ፍልሰትን ለመግታት ይህን የማኅበረ ቅዱሳን ሰይጣናዊ መንገድ መቀየር አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡    

  

18 comments:

 1. aye enante negeru heg menede hone selmataweku ayeferedebachum

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yetehadido MegagnawApril 8, 2016 at 5:41 AM

   CONGRADULATION kebero chikolachihu. Kend nekashinetachihun asayachihun .kefyalew wode college temese bilachihu manafatachihun saticherisu be tewahido ye collegu kurit lijoch bewulude kerlosochi destachi gereta, kisimachihu trsebere. Beke yeskezare yibekal.bitifelig nisiha giba batifelige timenetrsleh.

   Delete
 2. yetekol balebet yehonachu hulu endih bemadenagere yemifeter neger ende lele maweke alebchehu

  ReplyDelete
 3. yetehadiso MegagnaApril 7, 2016 at 9:26 PM

  Alemawi fird bet bebetkiristian ayagebawim yenant post yaderegachihut debdabe wishet bew aynebebim.kefialew tebarual yihe lemachibrber new. Enante ebaboch. Gena timeneteraleh. Ye chika wisit eshoh lebetekirstian ayhonim.ke gna silalineberachihu ye gna atihonum.menafik enji eske ahun yetebarere liki yelem.azagn kibe anguachi.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Amel, leba & menafik andim Sositim (1/3) nachew.yemiwogedut betebel/belimena ayidelem bemagalet kalhunem bichal bedula neber. Ahunm edenante lale woslata misu yihew new.yediablos melikitegna kuba.

   Delete
  2. It is amazing to see a so called christian pouring out a venomous poison against another christian. Your name "Megagna" gives a peep into your soul and your caustic vile language explains that you are a lost soul. Please go back and read your Bible and follow Christ whose name you are wearing in vain. By persecuting christians you are condemning Christ Jesus and putting him back on the cross again. Let Almighty God rest your soul.

   Delete
 4. Dingayoch yikirta dingay sira alew guadegnachihu teneka betekiristyan sitineka minim almeselachihu emnetina fird bet yeteleyayu mehonachewin neg tayutalachihu.

  ReplyDelete
 5. እናንተ የዲያቢሎስ የግብር ልጆች እስከመቼ ነው ግን በቤተክርስቲያን ላይ የምትቀልዱት ሆዳቸው አምላካቸው ክብራቸው በነውራቸው ተብሎ ትንቢት የተነገረው ለእናንተ እንደሆነ አሁን በእውነት አወቅሁ ራሳችሁን ገለጣችሁ አሳያችሁኝ ምድረ ከሀዲያን የቅዱሳን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሄር ልቦና ይስጣችሁ፡፡ እኔ በግሌ ግን አፍሬባችሁአለሁ፡፡ አሳፈሪዎች....

  ReplyDelete
 6. የተሰጡት አስተያየቶች በሙሉ ከንቱ እና በግብዝነት የተጻፉ ናቸዉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Including Yours? It must be

   Delete
 7. Besemaym ,,bemidrm le tehadisona lewushet bota aynnorewum...iyetekebatere yinoral ... Kidist Betekirstiyanachin lezelalem tsenta tinoralechi...Awaj lehulum .............

  ReplyDelete
 8. Out colrge is not a secular college. Since this can not fall under jurisdiction of the secular court. The case has to be presented to the holy synods if they guy refuses to repent and as forgiveness he will be excommunicated. Then his dissimisalary shall automatic. The court cannot force us to train a protestant preacher.

  ReplyDelete
 9. Yetefawin lij yemitilut abrachihu new yetefachihut lukas 15 yetefaw lij abatun yikir belegn bilo new erasu yemetaw enantem esum end wengelu lij befekadachihu tefitachihual yikirta teykachehu yetewahedo lij hunu. Daru enante lay yaderew seytan wedegedel saychemirachihu aymelesim.Niseha gibu

  ReplyDelete
 10. If you are a real Believers, you would have advised him to go to Sinodos instead of Court.

  ReplyDelete
 11. አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ የሆነ ወሬ ይዛችሁ ታናፍሳላችሁ እውነት መውጣቱ ላይቀር በእግዚአብሔር
  ከሳሽ ደቀምዙሙር ከፍያለው ቱፋ
  ዳኛ ፈይሳ በዳዳ አሁን በናንተ ቤት የእግዚአብሔር ፍረድ መስሎአችሁ ታራግባላችሁ የማይገባን መስሎአችሁ ድንቄም!!!!

  ReplyDelete
 12. To Anonymous April 8,2016 at 3:40am
  Who is the Holy Synods?Following the True Gospel is not a wrong thing. God only knows if the Synods knows about GOD.

  ReplyDelete
 13. It is amazing to see a so called christian pouring out a venomous poison against another christian. Your name "Megagna" gives a peep into your soul and your caustic vile language explains that you are a lost soul. Please go back and read your Bible and follow Christ whose name you are wearing in vain. By persecuting christians you are condemning Christ Jesus and putting him back on the cross again. Let Almighty God rest your soul.

  ReplyDelete