Friday, April 8, 2016

በመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችና በምሩቃን አገልጋዮች ላይ ማቅ የከፈተው የጥፋት ዘመቻ እንደ ዐውደ ርእዩ ይከሽፍ ይሆን? ማኅበረ ቅዱሳን በአደባባይ የሚያዜመው ለቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ተቆርቋሪና የቤተ ክርስቲያን የቊርጥ ቀን ልጆች የእርሱ አባላትና ማኅበሩ እንደሆኑ ነው፡፡ ሆኖም የማቅን ግብር እና አካሄድ ስንመለከት፣ የምናረጋግጠው እውነት ማህበሩ ለቤተ ክርስቲያን ከሚጠቅመው ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ መምጣቱን ነው፡፡ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያኒቱን በቁጥጥሩ ሥር ለማስገባትና  በራሱ ሌላ ሲኖዶስ የመተካት የራሱን ፓትርያርክ የማሾም ስውር ዓላማ እንዳለው የሚሠራው ሥራ በግልጥ እያሳየ መጥቷል፡፡

በተለይ በማይመለከተው በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥራ ውስጥ እጁን ማስገባቱና ማተራመሱ እንዲሁም ነገሮች እርሱ እንደፈለገው ካልሄዱ አባቶችን ሳይቀር መዝለፉ ባሕርዩ ሆኗል፡፡ አደረጃጀቱም ቤተ ክርስቲያኒቱን ተክቶ እርሷ የምትሠራውን ሁሉ እየሠራ እንደሆነ የሚያሳይ እንጂ ለቤተ ክርስቲያን መጠናከር የራሱን ድርሻ በተሰጠው የሥራ ክልል እየፈጸመ የሚንቀሳቀስ ድጋፍ ሰጪ ማኅበር አለመሆኑ ለሁሉም ግልጥ ይመስለናል፡፡

        ቤተ ክርስቲያን ዘግይታም ቢሆን ማኅበሩንና የሚሠራውን ሥራ አካሄዱንም ስትመለከት በተሳሳተ አቅጣጫ እየሄደ በመሆኑ ሥርዐት ለማስያዝ እንቅስቃሴ ጀምራለች፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሁሉም የጋራ መግባባት ላይ ባይደርሱም ርምጃ ተጀምሯል፡፡ እንደሚታወቀው እየተወሰደ ያለው ርምጃ በቤተ ክርስቲያኒቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ውስጥ ማቅ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነቱንና የማተራመስ ሥራውን እንዲያቆም፤ ማኅበሩም ተጠያቂነት ባለበትና ቤተ ክርስቲያንን ሊጠቅም በሚችል መንገድ ሥራውን መሥራት እንዲችል ለማድረግ ነው፡፡

        ይህ የቤተ ክርስቲያን ርምጃ ደግሞ ማቅን ከስውር ዓላማውና ቤተ ክርስቲያኒቱን በቁጥጥሩ ስር እንድትገባ የሚደርገውን ግስጋሴ እየገደበውና እያገደው መጥቷል፡፡ በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና መሪዎች ዘንድ የነበረውን ሥፍራ እያሳጣው ከመምጣቱም በላይ ሕዝባዊ መሠረት እንዳይኖረው በመከላከል ረገድ ርምጃው ውጤት ማስገኘት ችሏል፡፡ ሥርዐት ለማስያዝ እየተወሰደ ያለው ርምጃና አካሄድ ያላማረው ማቅ ጉዳዩን አጥንቶ እየደረሰበት ላለው ኪሳራና ለማቅ  የቤተ ክርስቲያን በሮች ዝግ የሆኑበትን ምክንያት ራሱን ተመልክቶ ከጥፋት ጎዳናው ከመመለስ ይልቅ በሌሎች ላይ አሳቦ እንቅፋት ሆነውብኛል ብሎ የፈረጃቸውን ለማስወገድ ቆርጦ ተነሥቷል፡፡ ለማቅ ተቀባይነት ማጣት እንቅፋቶቹ (ተቃዋሚዎቼ) ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል በአንደኛ ደረጃ የተቀመጡት የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችና ተመርቀው የወጡ በሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ እያገለገሉ ያሉ ምሩቃን ናቸው፡፡

        እነዚህን ቤተ ክርስቲያን አስተምራ  ያሰማራቻቸው  አገልጋዮችን ከቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ከሕዝብ ለማለያየት ቊርጥ አቋም ወስዶ መጠነ ሰፊ ዘመቻ በኮሌጆቹና በምሩቃኑ ላይ መክፈቱ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ እነዚህን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለመምታት ማቅ እንደ ስልት የተጠቀመውና ከቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ሆነ ከሕዝብ ዘንድ ትርፍ ያስገኝልኛል ብሎ ያሰበው ተሐድሶ ናቸው በሚል ስማቸውን ማጥፋትና መክሰስ እነርሱን በተሐድሶነት ፈርጆ ማሳደድ ነው፡፡

        ይህንን የሚፈጽምበትን ስልቶች ነድፏል፣ እቅድ አቅዷል፣ ከፍተኛ በጀት መድቧል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የሰዎችንና የተቋማትን ስምና መልካም ዝና በሚያጠለሽበት ጋዜጣው መንፈሳዊ ተቋማቱን የተሐድሶ መፈልፈያ በማለት በየአህጉረ ስብከቱ የሚገኙ ምሩቃንን የተሐድሶ አራማጆች እንደሆኑ በማስመስል ከፍተኛ ዘመቻ ከፍቷል፡፡ በዚህም ከመንፈሳውያን ኮሌጆቹ በደረሰበት ተቃውሞ ክስ ተመሥርቶበት በሕግ እየታየ ከመሆኑም በላይ ፓትርያርኩን በደብዳቤው ለመስደብም ያበቃው ምክንያት ይኸው እንደ ነበር ይታወሳል፡፡

        በኮሌጆችና በምሩቃን ላይ የጥፋት ዘመቻ ከከፈተባቸው መንገዶች ሌላው ጉዳዩን በሲኖዶስ አጀንዳ እንዲሆንና ተሐድሶ በኮሌጅና በምሩቃን ነው እየተስፋፋ ያለው ትልቅም ስጋት ሆኗል በሚል በኮሚቴ እንዲጠናና ውሳኔ እንዲሰጠው እየሄደበት ያለው መንገድ ነው፡፡ ይህን ለማሳመን ለጳጳሳቱ አጠናሁ ብሎ ያቀረበውና አባቶች በትምህርት ተቋማቱና በአገልጋዮቿ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸውና ጉዳዩን አግዝፎ በማሳየት ትኩረታቸውን ስለሳበ የጥቅምቱ ሲኖዶስ አጀንዳ እንዲሆንና ማቅ በሚፈልገው መንገድ እንዲወሰን አድርጎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ማቅ የመለመላቸው በኮሌጆችና በአህጉረ ስብከቶች ባሉ ምሩቃን ላይ ጥናት እንዲያደርጉ የተሰየመው ኮሚቴ አባላት እምነት አልባ፣ እውቀት አልባ፣ ሥነ ምግባር አልባ በመሆናቸውና የተሰጣቸው ሥራ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ጥናቱ ሳይሠራ ቀርቷል፡፡ (በወቅቱ አባ ሰላማ በጉዳዩ ላይ ጽፎ እንደነበር አይዘነጋም) ማቅ አጀንዳውን እንደገና በቋሚ ሲኖዶስ እንዲታይ አቡነ አብርሃምን ተጠቅሞ አጀንዳው ተነሥቶ ሌላ አጥኚ ኮሚቴ እንዲሰየምና ጥናቱ እንዲካሄድ ሥራ አስጀምሯል፡፡

        ስለ አዲሱ የኮሚቴው አባላት በሌላ ጊዜ ዝርዝር እናቀርባለን፡፡ ሆኖም መንፈሳዊ ኮሌጆችን፣ መምህራኑን፣ የትምህርት ካሪኩለሙን፣ ተማሪዎችንና ምሩቃኑን ለማጥናት አጥኚዎቹ ምእመናንና ምእመናት መሆን የለባቸውም፡፡ በእነዚህ ተቋማት ያላለፉ፣ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሌላቸው የኮሚቴ አባላት በምን መመዘኛ በጥናታቸው የታመነ አቋም ይዘው መቅረብ ይችላሉ፡፡ በርግጥ ማቅ ያሰበው እርሱ አጥንቼዋለሁ ብሎ ያዘጋጀውን፣ የክስ ዶሴ ገልብጠው እንዲያቀርቡ በመሆኑ ጉዳዩ በቀላሉ እንዲታለፍ ሆኗል፡፡ በሁለተኛው ዙር ያቀረባቸው የኮሚቴ አባላት ለማቅ ምቹ ሰዎች ናቸው፡፡

        በዚህ ጉዳይ ቋሚ ሲኖዶስ ቆም ብሎ እንደገና ማሰብ ይገባዋል፡፡ የሚያስከትለው መዘዝና ጥፋት ከፍተኛ የሕዝብ ፍልሰት ሊያመጣ የሚችል ከመሆኑ ባሻገር ለማቅ በቤተ ክርስቲያን ያለከልካይ እጁን እያስገባ የማተራመስና ሕዝቡንም በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና መሪዎች ላይ በጥፋት እንዲቀሳቀስ የሚረዳው በመሆኑ ጉዳዩ እንደገና ታይቶ እንደ ዐውደ ርእዩ የሚከሽፍበት መንገድ መፈጠር አለበት፡፡

የኮሌጆቹና የምሩቃኑ አገልግሎት መፈተሹ አግባብ መሆኑን ብናምንም የተሰየመው የኮሚቴ አባላት የማቅ ጉዳይ አስፈጻሚ ከመሆናቸውም ባሻገር ለተሰየሙበት ትልቅ ሃይማኖታዊ ጉዳይ የሚመጥን እውቀት ስለሌላቸው በአፋጣኝ ኮሚቴው ሥራውን እንዲያቆም ተደርጎ ለማጥናት የሚመጥኑ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መመደብ ይኖርባቸዋል፡፡

        የተሰየመው ኮሚቴ በሰዋሰወ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ  የማተራመስ ሥራ እየሠራ ሲሆን ለኮሌጁ አመራር ማቅ ጉቦ በመስጠት ጭምር ተማሪዎችን ለመከፋፈልና ተቋሙ የተሐድሶ መፈልፈያ ነው እንዲባል እየተሠራ ያለው ሥራ ሊጤን ይገባል፡፡ የተማሪዎችን የመማር፣ የመጠየቅ የመመራመር፣ አሳባቸውን የማቅረብ፣ የመወያየት፣ የመተናነጽ፣ የመማማር ነጻነትን የሚገድብ ሴራ የያዘ ነው፡፡ ሌሎቹም ኮሌጆች ጭምር ኮሚቴው ለተሰጠው ሥራ የማይመጥን መሆኑን ለበላይ አካል በደብዳቤ ማሳወቅ ይገባቸዋል፡፡ በአቡነ ማቴዎስ ፊርማ ወደየአህጉረ ስብከቱ በተላከ ደብዳቤም ምሩቃኑን አጥንታችሁ አምጡ በተባለው መሠረት የሚሠራውን ሥራ ማኅበሩ እንደፈለገው ለማድረግ በንዑስ ጽ/ቤቶቹ አማካይነት ምሩቃኑን ለመክሰስና ያለ ስማቸው ስም ለመስጠት፣ ማቅ ስርዐት እንዲይዝ የሚታገሉና የእርሱ ደጋፊ ያልሆኑትን ሁሉ ተሐድሶ በሚል ለመክሰስና ለማሸማቀቅ እየተሯሯጠ የተሳሳተ መረጃ ለኮሚቴው ለማቅረብ የሚያደርገውን ሙከራ ቤተ ክርስቲያን ማወቅና በንቃት ልጆቹን በማቅ ሰላባ ከመሆን እንድትጠብቅ እናሳስባለን፡፡

        ምሩቃን አገልጋዮች ኅብረታችሁን እንድታጠናክሩና የአንዱ ወንድማችሁ መነካት የሁላችሁም መደፈር እንደሆነ በመቁጠር ጉዳዩን ጉዳያችሁ እንድታደርጉ፣ ለቤተ ክርስቲያናችሁ ሕልውና በመከራ በመጽናት እንድትታገሉ እንመክራለን፡፡

        ቤተ ክርስቲያን ያስተማረቻችሁ ሕዝቡን እንድታስተምሩ ነውና ወንጌልን ከማስተማር እንዳትቆጠቡ፡፡ ከማቅ ተጽዕኖ የተነሣ ፈርታችሁ ከአገልግሎት ድርሻችሁና ሓላፊነታችሁ ንቅንቅ አትበሉ፡፡ ከቤተ ክርስቲያንና ከሥራ እንፈናቀላለን ብላችሁ አትፍሩ የተባረሩት ማንም ምንም አልሆነም፤ እየኖሩ ነው ያውም በተሻለ ሁኔታ፡፡ ከእናንተ ይልቅ የቤተ ክርስቲያን መደፈር ያሳስባችሁ፡፡

ወንጌልን የሚጠላ ሰይጣን ነው፡፡ በጸሎት እየተጋደላችሁ ወንጌልን ስትሰብኩ እናንተን ለመፈተንና መከራ ላይ ለመጣል የመጣው ሰይጣን ይሸነፋል፡፡ ማቅ ከሕግ ውጪ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት ልትገድቡና ሥርዐት እንዲይዝ የተጀመረውን ሥራ ከግቡ ለማድረስ መልክ ያለው ሥራ መፈጸም ይጠብቅባችኋል፡፡ ማቅ ጩኸት ብቻ ነው እንጂ አሁን ኃይሉ ተመቷል፡፡ ኢየሱስን፣ የጌታን ቅዱስ ወንጌል፣ ሰባክያነ ወንጌልንና ለቤተ ክርስቲያን ሕልውናና ክብር የሚቆረቆሩትን ሁሉ ስለሚቃወምና ስለሚጠላ እግዚአብሔር ከማቅ ጋር ሊሆን አይችልም፡፡ መንፈሳዊ ኃይል የለውም አልን እንጂ ሥጋዊ የሆነ ኃይሉ ብዙ ነው፤ ለወንጀል የማይመለስ ስለሆነም መጠንቀቁ አይከፋም፡፡

        እናንተ እግዚአብሔርን ለማክበር ለቤተ ክርስቲያን ሕልውናና ክብር መጠበቅ አቋም ይዛችሁ በጸሎትና በወንጌል አገልግሎታችሁ ከጸናችሁ እንደ ዐውደ ርእዩ በእናንተ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በእግዚአብሔር እጅ ይከሽፋል፡፡

ክብር ለክርስቶስ ሰላም አካሉ ለሆነች ለቤተ ክርስቲያን ይሁን!!


18 comments:

 1. Ke Egziabhare yehone Yashenefal.MK ke Egziabhare kehone yashinefal,Enantem ke Egziabhare kehonachihu tashenifakachihu.Aticheneku Gin Ke Amlak gar Atimeslugnim.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Haratikan (tehadiso) yemedan ken zare new. Pls choose the best Life/ death or repentance/leave the church.

   Delete
  2. Your member in EOTC "Aba Kaletsidik" His under ground
   work was exposed in 1995 EC by Sewasew brhan Committed Students the he left to USA and joind the so called sidetegna Senod served as secretary with Melaku baweke & luelekal. Before 8 month came back & posisioned as EOTC forein affair officer.with the Support of Dr (fake) Mussie Haregewoin jointly fly togather for the sake of changing the Tewahido church to protistant.but it is impossible. God's the eye always on the church.no slip.

   Delete
 2. yetehadiso MegagnaApril 8, 2016 at 11:40 PM

  Haratikan just ur strategy on theology colleges are failed. The the colleges students stand up all togather with unity by them selves with out others support.& start aggressively to fight & eradicate the so called tehadiso from thier campas. Sewasew brhan is example. By this single event you the Haratikan are shocked. At the same time the Theology graduates association support these unti-atehadiso movement to protect thier church. The senod fathers are one by the issue.there fore no loophole for you to penetrate.now confusions are cleared. That is why our fathers took action.it is the agenda of all tewahido stockholders. This is the current & extiningt reality. Now you have only two choices Nisiha/dula.

  ReplyDelete
 3. Ewirane lib Ewirane ayimiro yemelkam neger tekarani seytan new(nachihu). Yetignawan betekiristyan new yemitilun? kibir lekiristos? Mech kiristosin tawkutalachihu? Meren yadegachihu silehone cristyanawi sireat yelachihum.

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር ይመስገን ስሙ ሲነሳ የመናፍቃንን መንደር የሚያርበደብድ ማህበረ ቅዱሳንን በነ ቄርሎስ እግር የተካ ።

  ReplyDelete
 5. Weregnoch Yeseytan lijotch silehonachihu hulgize kifat tasibalachihu yetetsafewin alaweta tilalachihu gebenachihu silemitawekibachihu esti yemyastemir tsihuf and ken tsafu alelewoch kenante min yitebekal.

  ReplyDelete
 6. 'Aba selama's are always anti Mahibere kidusan b/s they assume that they were rejected from Ethiopian orthodox Tewahido church by the holy synod (During 2004E.c synod assembly) due to Mahibere kiduan. So, they are doing a kind of revenge for that matter.Please please please be orthodox first to talk about mahibere kidusan.Don't you know that your preaching is the same to that of protestants? We know that you are supporters 'tehadiso' heresy thereby you are illegal but mahibere kidusan is legal . God bless Mahibere kidusan!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do you mean LUCIFER their Master hail and bless Mahibere Kidusan!! There's nothing wrong with Aba Selama's stand and what they write is the truth, but truth means Jesus and MK is allergic and totally against Jesus. One thing that is hidden from you all is that Jesus said His sheep know him and he knows his sheep. He doesn't know Orthodox, catholic, Pentecostal, Protestant, etc. He only knows his sheep (Christians) nobody and nothing else. If you don't know Jesus and don't accept him, how is it that you claim to be a Christian?? It's about time you should take this up with your master Beelzebub before he disown you and throw you in the lake of fire, the only thing he could offer!!

   Delete
 7. አይ አርዮሳውያን በቅርብ ትነቀላላችሁ እድሜ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች ማህበረ ቅዱሳን።

  ReplyDelete
 8. በዘፍጥረት 3:15 ላይ "በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።" የሚል የእግዚአብሄር ቃል እናገኛለን:: በምዕራፍ 4:8 ላይ ደግሞ " ቃየንም ወንድሙን አቤልን፦ ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።" የሚል ቃል እናገኛለን እንግዲ ከዚህ ጀምሮ ነዉ ሁለቱ ዘሮች ማለትም የሴቷ ዘር እና የእባቡ ዘር ጠላትነት "ሀ" ብሎ የጀመረው:: በዚህ መልኩ ክርስቶስ ( አማናዊው ዘር) እስኪመጣ ድረስ ይሄ ጠላትነት እንደቀጠለ የእባቡ ዘር የሴቷ ዘር ማለትም ኢየሱስ የሚመጣበትን የዘር ግንድ እያሳደደ እየገደለ ከቆየ ቡሃላ ፤ ትንቢቱ በክርስቶስ መስቀል ተፈጽሞ የእባቡ ዘር (የሰይጣን) በክርስቶስ የመስቀል ሞት ተሸነፈ!:: ነገር ግን ሰይጣን ተሸነፈ እንጂ ገና ለዘላለም አልተወገደም:: ለዛም ነው ከክርስቶስ ቡሃላም በክርስቶስ ተከታዮች በእምነት የአብርሃም ልጆች በሆኑት ላይ ዘመቻዉን ያላቋረጠዉ:: ለምሳሌ:- ሁለት ግዛቶች ጦርነት ቢገጥሙ አንድኛዉ ግዛት ሌላኛዉን አሸንፎ ያለዉን ግዛት ሁሉ ይቀማዋል ነገር ግን ንጉሱን እና ሰራዊቱን ግን በምርኮኝነት እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል:: ነገር ግን እነዚህ በምርኮኝነት መኖር የጀመሩ ግዛቶች ዉስጥ ለዉስጥ ግዛታቸዉን አስፋፍተዉ ድጋሚ ጦርነት ሲያስነሱ ፤ በምርኮኝነት እንዲኖሩ ፈቅዶላቸዉ የነበረዉ ንጉስ በአሁኑ ሁሉንም ያጠፋቸዋል::" ልክ እንደዚሁ የሰይጣንን ግዛት ያሸነፈዉ ክርቶስ : ሰይጣን ተሸንፎ እንዲኖር ፈቅዶለታል ነገር ግን ተሸንፎም ለማሸነፍ ሲታገል ግን ከነድራሹ ያጠፋዋል:: በጌታ የተወደዳችሁ ዎዳጆቼ መጽሃፍ ቅዱስ በራእይ ዩሃንስ 20:10 ላይ እንደምናነበዉ " ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ።" በማለት ለዘላለም የሚጠፋበትን ግዜ ይጠቁመናል:: ስለዚህ አሁን ሃሳቡን በሚያስተገብርበት ማህበር ቢሯሯጥ ለግዜዉ ነው እና እንበርታ:: ጌታ ወደ ወንጌል ልባቸዉን እንዲመልስ የዳቢሎስን ስራ በማፍረስ እንጸልይ:: በማህበረ ቅዱሳን ስም የሚሰራ የወንጌል ተቃዋሚ በጌታ በኢየሱስ ስም የፈረሰ ይሁን!!!!! አሜን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Jesus is Lord!!! MK is a cult that that had recruited and mislead hundreds of thousands of college educated youngsters into blindly following its evil teachings. Once indcoctrinated they forcefully implement MK's plans into action regardless of consequences. When the late Abune Gorgorios Mistakenly started this group, his idea was to create a Bible educated youth who in turn will go out and apply the great commission to defend the Church from the enemy, but he did not foresee that the devil was hidden in the details and when the time came he raised his ugly head and started biting the heads of those that were teaching the Bible. The Orthodox Church was taken by surprise when its own disciples start destroying the Church, teaching falsehood, persecuting its clergy, selling its historical treasurers and ultimately taking it over as stated in the following quote.

   "ሆኖም የማቅን ግብር እና አካሄድ ስንመለከት፣ የምናረጋግጠው እውነት ማህበሩ ለቤተ ክርስቲያን ከሚጠቅመው ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ መምጣቱን ነው፡፡ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያኒቱን በቁጥጥሩ ሥር ለማስገባትና በራሱ ሌላ ሲኖዶስ የመተካት የራሱን ፓትርያርክ የማሾም ስውር ዓላማ እንዳለው የሚሠራው ሥራ በግልጥ እያሳየ መጥቷል፡፡"
   MK has nothing to do with Christianity, it hates to hear the name of Jesus. They claim to be Christians without Christ. There is no Christian without Jesus Christ!! period end of story!!

   "ወንጌልን የሚጠላ ሰይጣን ነው፡፡ በጸሎት እየተጋደላችሁ ወንጌልን ስትሰብኩ እናንተን ለመፈተንና መከራ ላይ ለመጣል የመጣው ሰይጣን ይሸነፋል፡፡ ማቅ ከሕግ ውጪ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት ልትገድቡና ሥርዐት እንዲይዝ የተጀመረውን ሥራ ከግቡ ለማድረስ መልክ ያለው ሥራ መፈጸም ይጠብቅባችኋል፡፡ ማቅ ጩኸት ብቻ ነው እንጂ አሁን ኃይሉ ተመቷል፡፡ ኢየሱስን፣ የጌታን ቅዱስ ወንጌል፣ ሰባክያነ ወንጌልንና ለቤተ ክርስቲያን ሕልውናና ክብር የሚቆረቆሩትን ሁሉ ስለሚቃወምና ስለሚጠላ እግዚአብሔር ከማቅ ጋር ሊሆን አይችልም፡፡ መንፈሳዊ ኃይል የለውም አልን እንጂ ሥጋዊ የሆነ ኃይሉ ብዙ ነው፤ ለወንጀል የማይመለስ ስለሆነም መጠንቀቁ አይከፋም፡፡"

   They seem to have sold their soul to the devil. They are always an obnoxious, negative, combative and loud and foul mouth caustic bunch that would not pass a chance from committing a crime if and when they can.
   በቅዱሳን ስም የሚሰራ የወንጌል ተቃዋሚ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የፈረሰና የተደመሰሰ ይሁን!!!!! አሜን!

   Delete
 9. በማህበረ ቅዱሳን ስም የሚሰራ የወንጌል ተቃዋሚ በጌታ በኢየሱስ ስም የፈረሰ ይሁን!!!!! አሜን!

  ReplyDelete
 10. Are you afraid that your cell in the colleges will be disclosed.
  As this is the wish of the college students who said they do not need Mk assistance to lean their college from 5th column tehadiso infiliterators.

  ReplyDelete
 11. ወንጌልን የሚጠላ ሰይጣን ነው፡፡ በጸሎት እየተጋደላችሁ ወንጌልን ስትሰብኩ እናንተን ለመፈተንና መከራ ላይ ለመጣል የመጣው ሰይጣን ይሸነፋል፡፡ ማቅ ከሕግ ውጪ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት ልትገድቡና ሥርዐት እንዲይዝ የተጀመረውን ሥራ ከግቡ ለማድረስ መልክ ያለው ሥራ መፈጸም ይጠብቅባችኋል፡፡ ማቅ ጩኸት ብቻ ነው እንጂ አሁን ኃይሉ ተመቷል፡፡ ኢየሱስን፣ የጌታን ቅዱስ ወንጌል፣ ሰባክያነ ወንጌልንና ለቤተ ክርስቲያን ሕልውናና ክብር የሚቆረቆሩትን ሁሉ ስለሚቃወምና ስለሚጠላ እግዚአብሔር ከማቅ ጋር ሊሆን አይችልም፡፡ መንፈሳዊ ኃይል የለውም አልን እንጂ ሥጋዊ የሆነ ኃይሉ ብዙ ነው፤ ለወንጀል የማይመለስ ስለሆነም መጠንቀቁ አይከፋም፡፡"

  ReplyDelete
 12. They seem to have sold their soul to the devil. They are always an obnoxious, negative, combative and loud and foul mouth caustic bunch that would not pass a chance from committing a crime if and when they can.
  በቅዱሳን ስም የሚሰራ የወንጌል ተቃዋሚ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የፈረሰና የተደመሰሰ ይሁን!!!!! አሜን!

  Delete

  ReplyDelete
 13. ሆኖም የማቅን ግብር እና አካሄድ ስንመለከት፣ የምናረጋግጠው እውነት ማህበሩ ለቤተ ክርስቲያን ከሚጠቅመው ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ መምጣቱን ነው፡፡ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያኒቱን በቁጥጥሩ ሥር ለማስገባትና በራሱ ሌላ ሲኖዶስ የመተካት የራሱን ፓትርያርክ የማሾም ስውር ዓላማ እንዳለው የሚሠራው ሥራ በግልጥ እያሳየ መጥቷል፡፡"
  MK has nothing to do with Christianity, it hates to hear the name of Jesus. They claim to be Christians without Christ. There is no Christian without Jesus Christ!! period end of story!!

  ReplyDelete
 14. Jesus is Lord!!! MK is a cult that that had recruited and mislead hundreds of thousands of college educated youngsters into blindly following its evil teachings. Once indcoctrinated they forcefully implement MK's plans into action regardless of consequences. When the late Abune Gorgorios Mistakenly started this group, his idea was to create a Bible educated youth who in turn will go out and apply the great commission to defend the Church from the enemy, but he did not foresee that the devil was hidden in the details and when the time came he raised his ugly head and started biting the heads of those that were teaching the Bible. The Orthodox Church was taken by surprise when its own disciples start destroying the Church, teaching falsehood, persecuting its clergy, selling its historical treasurers

  ReplyDelete