Tuesday, May 31, 2016

ሰበር ዜና - የሲኖዶሱ ስብሰባ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በተገኙበት ቀጠለየማኅበረ ቅዱሳን ልሳን የሆነው ሐራ ሰሞኑን ባናፈሰው ወሬ የማቅ ተላላኪዎች ቅዱስ ፓትርያርኩን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር መሥራትዎ ግድ ነው፤ ሕዝብ ይግባ፤ መንግሥት ይግባ ማለት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ሕገ መንግሥቱን አለማወቅ ነው፤ ማንም በማንም መግባት አይችልም፤ እኛም አንፈልግም፤ ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ መካከል ኾና ኹሉንም በአንድነት የምትጠብቅ ችግር ፈቺና አስታራቂ ተቋም ናት፤ እነእገሌ ይግቡ፤ እነእገሌ ይምጡ የሚለው አስተሳሰብ የመከፋፈል አጀንዳ ያላቸው ሰዎች ከውጭ የሚረጩት ነው፤” ማለቷ የሚታወስ ነው፡፡ እንዲህ ሲሉ የነበሩት የእንደራሴ አጀንዳ አቀንቃኞች በፓትርያርኩ አቋመ ጽኑነት ሐሳባቸውን ለውጠው መንግሥት ጣልቃ ይግባ ማለታቸውን ተከትሎ ለዛሬ ከሰዓት በኋላ ተላልፎ የነበረው እንደራሴን የተመለከተው አጀንዳ የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በተገኙበት ተካሄደ፡፡

ሚኒስትሩ በሚገኙበት የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት መሠረት ያደረገው ውይይት ኪሳራ ላይ የሚጥላቸው መሆኑን የተረዱት የማቅ ሰዎች በሐራ በኩል አሠራጭተውት የነበረው ወሬ አቅጣጫውን በመቀየሩ “ለምን መንግሥት ጣልቃ ይግባ አላችሁ? መንግሥት ጣልቃ ከገባ አቅጣጫው ይቀየራል” በማለት፣ አጀንዳ መሸከማቸውን እንጂ ጥቅምና ጉዳቱን በሚገባ ላላጤኑት ተላላኪዎቹ መልእክት ስላስተላለፈ ወዲያው አባ ሳዊሮስና አባ ሉቃስ ወደፓትርያርኩ ሄደው “እኛው በስምምነት እንጨርሰዋለን የመንግሥት ሹም አይምጣ” ብለው ለማግባባት ሞክረው የነበረ ቢሆንም፣ ፕትርያርኩ ግን “እንድ ጊዜ ጥራ ብላችሁኛል በ9 ሰዓት ሚንስትሩ ይመጣሉ” ባሉት መሠረት ስብሰባው በ9 ሰዓት ተጀምሮ እስከ 12 ሰዓት መቀጠሉ ታውቋል፡፡

ሰበር ዜና - በእንደራሴ ዙሪያ የተራዘመው ውይይት የመንግሥት አካላት በሚገኙበት እንዲካሄድ ተወሰነለቤተ ክርስቲያን በማሰብ ሳይሆን ለግል ጥቅምና ለማቅ ጥቅም ሲባል የተቀረጸውና ሌሎች አጀንዳዎችን እስከ መሸፈን የደረሰው እንደራሴን የተመለከተው አጀንዳ እስከ ዛሬ ረፋዱ ድረስ መስማማት ላይ ሳይደረስ ስብሰባው የተቋረጠ ሲሆን፣ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በተገኙበት ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና የመጨረሻ ዓመታት ወዲህ የሲኖዶስ ስብሰባ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጁ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት ሳይሆን አባቶችን የሚከፋፍሉ ጊዜን ገንዘብንና ጉልበትን የሚጨርሱ አንድን ቡድን ወይም ጥቂት ለቦታው የማይገቡ የሥልጣን ጥመኞችን ፍላጎት የተከተሉ አጀንዳዎች የሚስተናገዱበት የጭቅጭቅ መድረክ ሆኗል፡፡ ይህን መጥፎ ባህል የሲኖዶሱ ባህል እያደረገ ያለው በዋናነት ከጀርባ ሆኖ ሴራውን የሚጠነስሰውና የራሱን ጥቅም ለማስከበር ከፍተኛ በጀት መድቦ የሚንቀሳቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ 

Monday, May 30, 2016

እንደራሴ ይሾም የሚለው አጀንዳ መቋጫ ሳያገኝ የትናንትናው ስብሰባ ተጠናቀቀ

Read in PDF

በትናንትናው የሲኖዶስ ስብሰባ ውሎ እንደራሴ ይሾም በሚለው አጀንዳ ላይ ጳጳሳቱ ተካረው የዋሉ መሆናቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ አጀንዳውን ያቀረቡት ጳጳሳት ማለትም አባ ቀውስጦስ፣ አባ ሳዊሮስ፣ አባ አብርሃም፣ አባ ዲዮስቆሮስና የመሳሰሉት አጀንዳው ፍጻሜ ካላገኘ ሌላ አጀንዳ አናይም ማለታቸው የተሰማ ሲሆን፣ እንደራሴ ያስፈልጋል አያስፈልግም በሚሉት መካከልም ዝምታን የመረጡ ጳጳሳት መኖራቸው ታውቋል፡፡
የእንደራሴው ጉዳይ አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኋላ እየተረቀቀ በነበረው ሕገ ቤተ ክርስቲያን  ይካተት አይካተት የሚል ረቂቅ ሐሳብ ቀርቦ የነበረ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ ያን ጊዜ ሐሳቡን በጽኑ ከተቃወሙት መካከል ዛሬ በአጀንዳነት እንዲያዝ ያደረጉትና ሽንጣቸውን ገትረው እየተከራከሩለት ያሉት አባ ቀውስጦስ፣ አባ ሳዊሮስ፣ አባ አብርሃም፣ አባ ዲዮስቆሮስ፣ አባ ማቴዎስ፣ አባ ዮሴፍ፣ አባ ኤልሳእ ነበሩ፡፡ 

አርባ ሦስተኛው የስደተኛው ሲኖዶስ ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት።በስያትል ክብረ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ከረቡዕ 25/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው ቅዱስ ሲኖዶስ ከሁሉም ስብሰባዎች በሰላም እና በአንድነት የተከናወነ እንደነበር የደረሰን ሪፖርት ያመለክታል። ቅዱስ ሲኖዶስ በዋናነት በሚከተሉት አጀንዳዎች ተዋያይቷል። በኢየሩሳሌም ስለተቋቋመው የሁለቱ ሲኖዶሶች የእርቅ ኮሚቴ ተዋያይቶ የሰላሙ በር ክፍት መሆኑን አጽድቆ የሚደራደሩ ሰዎችን ለመምረጥ ወስኗል። በሲኖዶሱ ስር ያሉ ካህናት የሚያካሂዱት የስድስት ወር ጉባኤ ደካማ ጎኑ ተገምግሟል እርሱም ተመሳሳይ መምህራንና ተደጋጋሚ ትምህርት መሰጠቱ ሲሆን ጠንካራ ጎኑ ደግሞ ካህናት መገናኘታቸውና በሃይማኖት ጉዳይ ላይ መወያየታቸው አንዳንድ ርምጃዎችን በጋራ ለመውሰድ የሚያስችል መሆኑ ነው። በዚህ የካህናት ጉባኤ ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ይዛ የቆየችውና መታረም ወይም መቀጠል ያለባቸው ልማዶችና የስሕተት ትምህርቶች የሚገመገሙበት ታላቅ የትምህርት ጊዜ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ይህ ጉባኤ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ወስኗል።

   የሊቃውንት ጉባኤው ባቀረበው ሪፖርት መነሻነት ዘመኑን የዋጀ ወጥ የሆነ የትምህርተ ሃይማኖት የሥርዓት  መጻሕፍት እንዲዘጋጅ ተወስኗል። አንድ ሊቀ ጳጳስ መጻሕፍት በተጻፉ ቁጥር ጴንጤ እና ተሃድሶ እየተባልን መግቢያና መውጫ አተናልና አርፈን እንቀመጥ ሲሉ ተማጽነዋል። ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ግን በጣም ተገርመው መጻሕፍት ይጻፉ አዲስ ነገርም ካለ እንወቀው የተሠወረ ካለም ይገለጥ በማለት የተለመደ ማበረታታቸውን አሳይተዋል። አቡነ መልከ ጼዴቅ በቤተ ክርስቲያን መወሰድ ያለባቸውን መንፈሳዊ እርምጃዎች ሁሉ ያለ ፍርሐት እውነትነቱን ሳይለቅ መወሰድ እንዳለበት ገልጠዋል። 

Sunday, May 29, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ፓትርያርኩን በደብዳቤ ይቅርታ ጠየቀለብዙ ዓመታት አንገቱን አደንድኖ የኖረውና በተደጋጋሚ የይቅርታ ጠይቅ ደብዳቤ ቢጎርፍለትም የይቅርታ ልብም ሆነ አፍ ኖሮት የማያውቀው ማኅበረ ቅዱሳን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል በሚችል መልኩ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ኢግዚብሽኑ ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማለትም ግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ እርሱ “ከልብ” ያለውን ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሌሎች የበደላቸውን አካላትም ውይይት ካደረገ በኋላ ይቅርታ እንደሚጠይቅ ገልጿል፡፡  

በጉዳዩ ላይ “ይቅርታ ስለመጠየቅ” የሚል ርእስ የተሰጠው ደብዳቤው እንደሚለው “ባለፉት ጊዜያት ቤተ ክርስቲያናችንን በልጅነት መንፈስ ለማገልገል በምንላላክበት መጠነኛ የአገልግሎት ሂደት በተፈጠሩ ክፍተቶች ምክንያት ሐሳቦቻችንን ያስረዳን መስሎን በጻፍናቸው ደብዳቤዎች እና በአንዳንድ ሥራዎቻችን ቅዱስነትዎ ቅር እንደ ተሰኙብን ተረድተናል፡፡ ስለዚህም እኛ ልጆችዎ ሆነ ብለን ቅዱስነትዎን ለማሳዘን ያላደረግነው መሆኑን ተረድተውልን ይቅርታ እንዲያደርጉልን ከልብ እንጠይቃለን፡፡” ይላል፡፡


የይቅርታ ደብዳቤው ከመጻፉ በፊት መሪዎቹ ግንቦት 10/2008 ዓ.ም ፓትርያርኩ ዘንድ ቀርበው ከፓትርያርኩ መመሪያ እንደ ተቀበሉና በተቀበሉት መመሪያ መሠረት ይህ ደብዳቤ እንደ ተጻፈ ከደብዳቤው መረዳት የተቻለ ሲሆን፣ በቅዱስነታቸው መመሪያ መሠረት “የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ወይይቶች ከተደረጉ በኋላ አግባቡን ጠብቀን ይቅርታ ለሚጠየቅባቸው ጉዳዮች ሁሉ ይቅርታ” እንጠይቃለን ይላል፡፡ የማቅ አመራሮች ከፓትርያርኩ ጋር እንዲነጋገሩ ያደረጉት የፈደራል ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ሲሆኑ፣ በንግግሩ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ መሆኑን እንደገለጹና ይቅርታም እንዲጠይቅ ማድረጋቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ይቅርታውን ለመጠየቅ ግን ግፊቱ ከውጪ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ የማኅበሩ አንዳንድ አመራሮችና አባላት “ጥፋት ተፈጽሟልና ይቅርታ ልንጠይቅ ይገባል” ሲሉ ሐሳብ ማቅረባቸውና በዚህ የተነሣም ክፍፍል ተፈጥሮ የነበረ መሆኑን ምንጮች ያስታውሳሉ፡፡  

Saturday, May 28, 2016

ሰበር ዜና፡- የማኅበረ ቅዱሳን ዋና የአመራር አካል የሆነው ከፍያለው አያሌው በመግደል ሙከራ ወንጀል 10 ዓመት ተፈረደበት


 Read in PDF
,እስመ አልቦ ክዱን ዘኢይትከሠት ወኅቡእ ዘኢይትዐወቅ.(ማቴ.10:26) 

               
የሃይማኖት ጨለምተኝነትን ካባን ለብሶ ለበትረ ሥልጣንና ለንዋይ ክምችት ሲንቀሳቀስ የኖረውና እየተንቀሳቀሰ ያለው ማቅ ይህንን ነገር ለማሳካት ከሚጠቀምባቸው ነገሮች አንዱ ነፍሰ ገዳይነት   መሆኑ  የሚካድ አይደለም። ፖሊስ ያልደረሰላቸው፤ ሕግ ያልያዘላቸው ብዙዎች ንጹሕ ደማቸው በከንቱ ፈሷል። ሕይወታቸው አልፏል። በፖሊስ ተመርምረው በገንዘብ ኃይል ለፍርድ ሳይበቁ ደብዛቸው የጠፋ ወንጀሎችም መኖራቸው የሚታወቅ ነው። እነዚህ በአካል ደብድቦና አቊስሎ የገደላቸው  ሲሆኑ  ከሥራ  አፈናቅሎ፤  ሞራላቸውን  ነክቶ፤  ከቤተ  ክርስቲያን  አባሮ፤  በረሀብና በችግር የገደላቸውም  ብዙዎች  ናቸው።  ማቅ  በአካሔዱም  ሆነ  በዓላማው  የእርሱ  ያልሆነውን  ማጥፋት የተነሣበት ግቡ ስለሆነ ከወንጀል የራቀበት ጊዜ የለም። 

  የመግደል ሙከራ ለማድረግ ከተራ አባል እስከ ዋና አመራር ድረስ የማያመኑት እና ይህን ክፋታቸውንና ጭካኔያቸውን ሃይማኖታዊ ምክንያት በመስጠት ለራሳቸው ልዩ ወንጌል የፈጠሩት የማቅ ሰዎች የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ሁሌ ሊሳካ እንደማይችልና ለዘለቄታው ከህግ ተሰውሮ መኖር እንደማይቻሉ ትናንት ግንቦት 19 ቀን 2008 ዓ/ም የተሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ ማረጋገጫ ነው። የማህበረ ቅዱሳን ዋና አመራር የሆነው ከፍያለው አያሌው በፈጸመው የመግደል ሙከራ ወንጀል በአሥር ዓመት ጽኑ  እሥራት  ተፈርዶበታል። ከፍያለው አያሌው  የመግደል  ሙከራውን  ያደረገው የቤተ ክርስቲያን  አባት  በሆኑት በመልአከ  ገነት  አባ  ዮሐንስ  አፈወርቅ  የኮልፌ  ክፍለ  ከተማ  ሥራ  አስኪያጅ ላይ ነበረ።  ይህ ግለሰብ ያደረገው የመግደል ሙከራ በበቂ ማስረጃ ስለተረጋገጠበትትናንትና ዓርብ ከጠዋቱ በ4 ሰዓት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በአሥር ዓመት ጽኑዕ እሥራትና ለአምስት አመት ከማንኛውም የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዲታገድ ተፈርዶበታል። 

Friday, May 27, 2016

እንደራሴ ይሾም የሚለው አጀንዳ በፓትርያርኩ በሌሎችም ጳጳሳት ተቀባይነት አጣሲኖዶስ ከያዛቸውና አጀንዳው እንዲያዝ ባደረገው ክፍል በኩል ዋና አጀንዳ ተደርጎ የተወሰደው “ለፓትርያርኩ እንደራሴ ይሾም” የሚለው አጀንዳ ለጳጳሳቱ መከፋፈል ምክንያት ሆኖ መዋሉንና ከስምምነት ላይ አለመደረሱን መረዳት ተችሏል፡፡ ወደ ሥልጣን ከመጡ 3 ዓመታትን ያስቆጠሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመልካም ጤንነትና በጥሩ አመራር ላይ እንዳሉና የቤተ ክርስቲያን “ነቀርሳ” የሆነውን ማቅን አደብ ለማስገዛት በጀመሩት ጥረት ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ እንደራሴ ይሾም የሚል አጀንዳ እንዲቀረጽ የመደረጉ ምስጢር ሌላ ሳይሆን ማቅ ለምን ተነካ በሚል እንደሆነ ከጉዳዩ አካሄድ መረዳት ይቻላል፡፡ ከሲኖዶሱ ስብሰባ በፊት የማቅ ሰዎች በዚህ ላይ ሲሰሩና ለደጋፊ ጳጳሳት ከፍተኛ በጀት መድበው ሲንቀሳቀሱና አጀንዳውን በአጀንዳነት ለማስያዝ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበርና ያንንም ማሳካት እንደቻሉ ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ አጀንዳው ምክንያታዊ ባለመሆኑ ማቅ እንደ አእዱግ እየቀረቀበ አጀንዳውን የጫናቸው ጳጳሳት ድል አልቀናቸውም፡፡
በማቅ በኩል የማቅን ይህን አጀንዳ ይዘው የተነሡትና እንደራሴ ይመረጥ ያሉት ጳጳሳት አባ ቀውስ ጦስ፣ አባ ማቴዎስ፣ አባ ዮሴፍ፣ አባ አብርሃም፣ አባ ዲዮስቆሮስ፣ አባ ኤልሳዕ፣ አባ እንድርያስ፣ አባ ቀሌምንጦስና በቅርቡ ማቅን የተቀላቀሉት አባ ሳዊሮስ ናቸው፡፡ ይህን በምክንያት ላይ ያልተመሠረተ የማቅን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የቀረበውን አጀንዳ የተቃወሙትና እንደራሴ አያስፈልጋቸውም በራሳቸው ቤተክርስቲያንን እየመሩ ነው ያሉት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ ብፁዕ አቡነ ሙሴ፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ናቸው ተብሏል፡፡ 

Thursday, May 26, 2016

እየተካሄደ ባለው የሲኖዶስ ስብሰባ የፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል

Read in PDF 
ቅዱስነታቸው ከአንድ መሪ የሚጠበቅና ብስለት ያለው ንግግር ያሰሙበት የግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በቀረጻቸው አጀንዳዎች መወያየቱን ቀጥሏል፡፡ ቅዱስነታቸው እንደ ከዚህ በፊቱ በተገኙባቸው መድረኮች ደጋግመው ሲገልጹት እንደነበረው አሁንም ወደ ውስጣችን መመልከት አለብን እያሉ ነው፡፡ ገደብ ለሌለው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንነሣ በማለት የቤተ ክርስቲያኒቱ የአሁንና የወደፊት እርምጃ የተስተካከለ እንዲሆን የቃለ እግዚአብሔር ትጥቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ንግግራቸው ፓትርያርኩ የውስጥ ተጽዕኖው እንደ ተጠበቀ ሆኖ የውጪው ጫና ማለትም ሴኪዩራሊዝም ግሎባላይዜሽን አክራሪነት እጅግ የወረደ ሥነምግባር በምድር ላይ ያለችውን ቤተክርስቲያን እየተጫናት፣ ተፅእኖ እያመጣባት ይገኛል ብለዋል፡፡
የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት እውነት ነው ዛሬ ባህር ላይ እንደወደቀ ኩበት ቤተክርስቲያን ወዲያ ወዲህ እያለች፣ ሞገስዋ ቀንሶ፣ ልእልናዋ ቀጭጮ፣ “የአባትህ ቤት ሲወረር አብረህ ውረር” በሚል ልማድ የሚመራ የሚመስለው የቤተክርስቲያን ኃላፊና ሠራተኛ ምዝበራውን፣ ዝርፊያውን የቤት፣ የመኪና ግዢውን አጧጡፎታል፡፡ አንድ ደብዳቤ ለማብረር ያለ ገንዘብ የማይሠሩ የቤተክርስቲያን ሠራተኞች፣ ጳጳሳት (ጥቂቶች ካልሆኑ በቀር) የደብር አለቆች ሁኔታ ሲታይ በቤተክርቲያን ላይ ያንዣበበው አደጋ በመጨረሻው ፍልሰተ ምእመናንን እያባባሰው ይገኛል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደከዚህ በፊቱ ችግሮቹን ሁሉ በሌሎች ላይ በማሳበብ ጊዜውን ከሚያጠፋ “ውስጥን ማየት” ለበሽታው ፍቱን መድኃኒት ነው።

Wednesday, May 25, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ኦርቶዶክሳዊነትን ዝቅ ያደረገ ማኅበርማኅበረ ቅዱሳን “ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል ርእስ ያዘጋጀው 5ኛ ዐውደ ርእይ ትልቅ ርእስ የተሰጠው ቢሆንም፣ ማኅበሩ ኦርቶዶክሳዊነትን እርሱ ጠንቅቆ ሌላውም እንዲጠነቅቅ የሚያደርግ ብቃት አለው ወይ የሚለው ግን አጠራጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ኦርቶዶክስ የሚለውን ስመ ሃይማኖት እርሱ ተጠራበት እንጂ ራሱ ጠንቅቆ እንዳላወቀውና ለሌላውም የማሳወቅ ብቃት እንደሌለው ከዐውደ ርእዩ ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠና ኦርቶዶክስን ኦርቶዶክስ ካሰኘበት መሠረታዊ ነገር እየራቀ ከመጣ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይበልጥ የዘቀጠውና ከስሙ በቀር አስተምህሮው በሌላ አስተምህሮ ተተክቶ የሚገኘው ግን ማኅበረ ቅዱሳን በተነሣበትና ቀጥሎ ባበት በዚህ ዘመን ነው ቢባል ትክክል እንጂ ስሕተት አይሆንም፡፡ ለምሳሌ በዛሬው ዕለት የሚቀርበው አንዱ መርሐ ግብር “ንባብ፣ ቅዳሴ እና ሰዓታት” በሚል ርእስ የንባብ ይዘት የቅዳሴ ምንነት ይዘትና አገልግሎትና ሥርዓቱ ንባቡንና ቅዳሴ አቀራረቡን በመድረክ በአብነት ተማሪዎች ማቅረብ እንደሆነ የወጣው መርሐ ግብር ያስረዳል፡፡ እውን ይህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን “አስተምህሮ” ተብሎ የሚቀርብ ጉዳይ ነወይ? ማኅበረ ቅዱሳን ኦርቶዶክሳዊነትን ዝቅ ያደረገ ማኅበር ነው ለማለት የደፈርኩትም ከዚህ በመነሣት ነው፡፡
  ኦርቶዶክስ ርቱዕ ሃይማኖት (የቀናች ሃይማኖት) ማለት ሲሆን በኒቅያ ጉባኤ ውሳኔ ላይ ተመሥርቶ የወጣ ስመ ሃይማኖት ነው፡፡ ይኸውም “ወልድ ፍጡር” ያለውን የአርዮስን ክሕደት መርምሮና እሱን ረትቶ ወልድ ፍጡር ሳይሆን ፈጣሪ መሆኑን በማስረዳት ለወሰነው ውሳኔ የተሰጠው ስም ነው፡፡ ተዋሕዶም በኤፌሶን ጉባኤ የንስጥሮስን ኑፋቄ በእግዚአብሔር ቃል መርምረውና ስሕተትነቱን በማወጅ አንዱ ጌታችን ኢየሱ ክርስቶስ መቀላቀልና መለያየት በሌለበት ተዋሕዶ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነበት ምስጢር መሆኑን ለመግለጥ የተጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ ስለዚህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ብሎ ማመንና በክርስቶስ ፍጹም አምላክነትና ፍጹም ሰውነት በአዳኝነቱም ማመን ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ሲል ግን ከዚህ መሠረተ እምነት በእጅጉ የራቁና እንደ አስተምህሮ የማይቆጠሩ ጉዳዮችን “አስተምህሮ” በማለት ሰይሞ ኦርቶዶክሳዊነትን ዝቅ ያደረገ ማኅበር ሆኖ ይገኛል፡፡
በሁለቱ ዓለም ዐቀፍ ጉባኤዎች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስያሜ ሊሰጥ የቻለው በክርስቶስ ማንነት ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ ስለዚህ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለው ስያሜ ከክርስቶስ ተለይቶ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ያለ ክርስቶስ ከሆነ ግን ስሙ ትርጉም አልባ ይሆናል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ውስጥ የክርስቶስ አምላክነትና ጌትነት፣ ክርስቶስ ብቻ አዳኝ መሆኑ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን የተቋቋመው ስላንቀላፉ ቅዱሳን እና ስለትውፊት እንጂ ስለ ክርስቶስ አይደለምና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለውን ስም ሳይገባው የሚጠራበት ስም ሆኗል፡፡ ስለዚህ ዛሬ በኦርቶዶክስ ስም ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ የማይመጥን ጉዳይ ላይ ብዙ ነገር እያባከነ ይገኛል፡፡   
እስቲ አንዳንድ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ላቅርብ፣ “ንባብ፣ ቅዳሴ እና ሰዓታት” በሚል ርእስ የንባብ ይዘት የቅዳሴ ምንነት ይዘት፣ አገልግሎትና ሥርዓቱ ንባቡና ቅዳሴ አቀራረቡ በመጀመሪያ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ነወይ? ሁለተኛ አሁን ያለው አንገብጋቢ ጉዳይ ይህ ነወይ? በተለይም ሕዝቡ በስፋት እየፈለሰ ያለው ማኅበሩ ርእሰ ጉዳይ አድርጎ የያዘውን “ንባብ ቅዳሴና ሰዓታት” ስላላወቀ ነወይ? ይህን ማሳወቅ ከተቻለ የሕዝብን ፍልሰት ማቆም ይቻላል ወይ? እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉት ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ይዞት የተነሣውን ይህ ርእሰ ጉዳይና ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ግን የሚገናኙ አይመስለኝም፡፡

Tuesday, May 24, 2016

የማቅ ኤግዚቢሽን በግንቦቱ ሲኖዶስ መክፈቻ ዕለት መከፈቱ ለምን ይሆን?

በዘንድሮው ዐቢይ ጾም ውስጥ ሊደረግ ታስቦ የከሸፈውና የነፈሰበት የማቅ ኤግዚቢሽን በነገው ዕለት ሊከፈት መሆኑን ማቅ ፈራ ተባ እያለ በመግለጽ ላይ ነው፡፡ ኤግዚቢሽኑ ባልጠፋ ቀን በዚህ ዕለት መዘጋጀቱ በኤግዚቢሽን ማእከል የነበረው ክፍት ጊዜ ይህ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎና ከሲኖዶሱ ስብሰባ ጋር እንዲያያዝ ተፈልጎ እንደ ተዘጋጀ የሚናገሩ አሉ፡፡ ማኅበሩ ኤግዚቢሽኑ ተፈቀደልኝ ካለ በኋላ ሊያሳይ የቀጠረው በሲኖዶስ ስብሰባ የመጀመሪያ ቀን ላይ መሆኑ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ጥላውን ለማጥላት አስቦ ያደረገው መሆኑን ብዙዎች ይገነዘባሉ፡፡
ይህን ኤግዚቢሽን ከዚህ በፊት እንደ ተደረገው እንደ አብነት መምህራኑ የግዮኑ ጉባኤ የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን የፈቃድ ደብዳቤ ፓትርያርኩ ባላቸው ሥልጣን ድንገት ያግዱታል ብሎ እስከ አሁን እየተኛና እየባነነ እንዳዘጋጀው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡

Sunday, May 22, 2016

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሕግ መምሪያ ሃላፊ በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን የቤት ሽያጭ ላይ የተወሰነውን ውሳኔ ለመቀልበስ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ የተሰየመው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ ከዚህ ቀደም በማስረጃ ተደግፎ በቀረበው የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ንብረት የሆነ ቤት ሕገወጥ ሽያጭ ላይ ተወስኖ የነበረው ውሳኔ እንዲቀለበስ በመደረጉ የአስተዳደር ጉባኤው አባላት ለሁለት መከፈላቸው ተሰማ፡፡ አዲሱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ የተወሰኑት አባላት ለጉዳዩ አዳዲስ ቢሆኑም ከነባሮቹ ጥቂቶቹ ከዚህ ቀደም የተወሰነው ውሳኔ እንዲቀለበስ ለማድረግ ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡ በተለይም የተወሰነውን ውሳኔ ወደፊት እንዲሄድና ተገቢውን የውሳኔ አፈጻጸም እንዲኖረው ማድረግ የሚገባው የሕግ መምሪያ ኃላፊው መ/ር ባሕሩ ተፈራ እና ታጋይ የተሳሳተና፣ የተጣመመ ሐሳብ በማንሳታቸውና በበሉበት እንዲጮኹ ያደረገ ሙግት ማድረጋቸውን ምንጮች ይናገራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የተወሰነው ውሣኔ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይሄድ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ባሕሩ ተፈራ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ባሕሩ ተፈራ (በቅጽል ስሙ ወ/ወ/ሩ - ወጣቱ ወልደ ሩፋኤል ይሉታል አለባበሱንና ሕይወቱን ከግምት በማስገባት) ከመጀመሪያው አንስቶ ውሳኔውን ላለመቀበል የራሱን እርምጃ ሲወስድ እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም የአስተዳደር ጉባኤው የውሳኔ ቃለ ጉባኤ ላይ ሳይፈርም ቆይቷል፡፡ ያቀረበው ምክንያት ክፍለ ሀገር ሄጇለሁ የሚል እንደነበር ምንጮች ጠቅሰው፣ በሙሉ ድምፅ የተወሰነውና በህገወጥ መንገድ የተሸጠውን ቤት የተዋዋለውና የሸጠው የደብሩ ምክትል ህንፃ አሠሪ ኮሚቴ እስጢፋኖስ ሀይሉ ይከሰስ ሲባል፣ ፋይሉ ላይ መተኛትንና እንዳይንቀሳቀስ ማድረግን ነው የመረጠው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ  ባሕሩ ተፈራ በተደጋጋሚ ከእነ ዮናስ መኮንን፣ የትናየት ሀይሉ፣ እስጢፋኖስ እስኪሰለቸው ድረስ ጽዮን ሆቴል፣ ሶራንባ ሆቴል፣ ኤፍሬም ውስኪ ቤት በተደጋጋሚ ሲጋብዙትና ለጉቦ የሚሆን ብርም ሲሰጡት እንደቆዩ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ለዚህም እነእስጢፋኖስ ነሸጥ ሲያደርጋቸው “አይዞን ነገሩን ባሕሩ ይዞልናል” ሲሉ መደመጣቸውን እንደ ማስረጃ ያቀርባሉ፡፡

ሌላው ተማጋች አሁንም አላርፍም ያለው ቄስ ታጋይ ነው፡፡ ቄስ ታጋይ በቀድሞው ሥራ አስኪያጅ አስተዳደር ጉባኤ ላይ መከሰስ አለባቸው ብሎ የተስማማና በቃለ ጉባኤውም ላይ የፈረመ ቢሆንም እርሱም ያን ቃል አጥፎ ምንም ጥፋት አልተፈጸመም ሲል መሟገትን የመረጠው ከግብዣውና ከጉቦው ተቋዳሽ ስለሆነ እንጂ የመጀመሪያው ውሳኔ ውሸት ስለሆነ አይደለም፡፡

Friday, May 20, 2016

የደቡብ ውሎ ሀገረ ስብከት በማኅበረ ቅዱሳን መዳፍ ውስጥ ወደቀማኅበረ ቅዱሳን በሚል ስያሜ የሚታወቀው ድርጅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በልዩ ልዩ ስልትና በከፍተኛ የገንዘብ አቅም እየታገለ ለዓመታት ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
    ቤተ ክርስቲያኒቱ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ድረስ ያላትን አደረጃጀት በሙሉ ለመቆጣጠር በሚያመች ሁኔታ ተመሳሳይ አደረጃጀትና መዋቅር በመዘርጋት ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትሠራውን ሁሉ ተክቶና በሁሉም ጉዳይ ጣልቃ እየገባ የማይገባውን ሁሉ ያለ ከልካይ በማከናወን የሚንቀሳቀሰው ማኅበር ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በዚህ ወቅት ስውር አሠራሩና ዓላማው የአደባባይ ምስጢር እየሆነ ሲመጣ ሥርዐት እንዲይዝና ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊጠቅም በሚቻልና ተጠያቂነት ባለበት ሥርዐትንና ሕግን በተከተለ መንገድ እንዲሠራ የማስተካከያ ርምጃ እየተወሰደ መሆኑም ይታወቃል፡፡
    ማቅን ሥርዓት የማስያዝ ርምጃ እንዲወስድብት የጠቅላይ ቤተ ክህነት 18ቱ መምሪያዎች በአንድ ድምጽ የተስማሙ ሲሆን የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችም ጭምር ማቅን ሥርዐት የማስያዝ እርምጃ የሚመለከተው ክፍል በአፋጣኝ እንዲወስድ በተደራጀ መንገድ አቋም ይዘው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
    ከጠቅላይ ቤተ ክህነት 18ቱ መምሪያዎች የተጀመረው ማኅበሩን በሕግና በሥርዐት እንዲሄድ የሚጠይቅ እንቅስቃሴ በቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት ማግኘቱንና የሚደግፉት የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት እየጨመሩ መምጣታቸውን ተመልክቶ የደነገጠው ማቅ እንቅስቃሴውን ለማስቀልበስና ለቤተ ክርስቲያን ሌላ ስጋት የሆነ አካል አለ በማለት ‹‹የግንዛቤ ማስጨበጫ›› በሚል ከአዲስ አበባ ውጪ በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ፀረ-ተሐድሶ በሚል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መረጋጋት እንዳይኖር፣ ምእመናን አገልጋይ ካህናቱንና መምህራኑን እንዲጠራጠሩና እንዲታወኩ በከፍተኛ በጀት ባለፉት ጥቂት ወራት በሙሉ ኃይሉ እየሠራ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
    ለቤተ ክርስቲያን የሚቆረቆሩ አባቶች የማቅን ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር ውድቅ ያደረጉ ሊሆን እንደነአቡነ ገብርኤል ያሉ አባቶች ደግሞ ፈቅደው የማኅበሩን ዲስኩር ካዩ በኋላ እውነትን ካለማወቅ የመነጨ የቤተ ክርስቲያን መሠረት ጉልላት የሆነው ኢየሱስን እንዳይሰብክ የሚከላከል በስውር የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ የሚሠራበት እንደሆነና “መጽሐፍ አንብቡ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የሚሠራ ካለ እንጂ ኢየሱስን የሚስብክ ተሐድሶና አፍራሽ ነው ማለት አላዋቂነት ነው” ብለው በተግሳጽ የማኅበሩን ዓላማ ከንቱና ለቤተ ክርስቲያን የማይጠቅም እንደሆነ አሳስበዋል፡፡
በአንዳንድ አህጉረ ስብከቶች በተለይም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት እየታየ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ከዚህ የተለየ ሲሆን ማቅ ሙሉ ለሙሉ ሀገረ ስብከቱን ተቆጣጥሮ የሚፈልገውን ለማድረግ እየሠራ ይገኛል፡፡

Wednesday, May 18, 2016

ሦስቱ የዓለም ፈተናዎች፤   Read in PDF                                      
ፈተና ከሰው ልጅ ሕይወት ጋር የተያያዘ ነው። ፈተናን አልፎ ውጤታማ ደረጃ ላይ መድረስ፣ በፈተና ወድቆ ከወደቁበት ምክንያት ተምሮ እንደገና ፈተናውን ማለፍ ፈተናውን ሳያልፉ እንደወደቁ መቅረት የሰው ልጅ በሕይወቱ ውስጥ የሚገጥሙት የማያቋርጥ ሰንሰለታዊ አዙሪት ነው።  አስታውሱ! ከመጀመሪያው የጌታ ፍርድ በኋላ ፈተናዎቹ በበቂ ምጣኔ ሲሆኑ መሠረታዊ የሰው ልጅ የሕይዎት ፍላጎቶች መሆናቸውን በመዘንጋት የቀረበ አይደለም። ሆኖም አመጣጣቸውና ከመጠን በላይ በሆነ ፍላጎት የሰውን ልጅ ሲያጠምድና ሲያሰክሩ የሚያሳድሩት ተጽዕና የሚያስከትሊት አደጋ ምን ይመስላል የሚለውን ለማጠየቅ የቀረበ ነው።
መጽሐፍ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተጠንቀቁ እያለ ሲመክር እኛም ወደ ፈተና አታግባን እያልን ስንጸልይ ፈተና እና የሰው ልጅ በማገናኘት እንደሚፈልጉት ብዙ አጋጣሚዎች እንዳለ ወይም የሰው ልጅ በሚሄድበት የሕይወት መንገድ አጋጣሚ ሁለ ፈተና እንደሚያገኘው እንደሚከተለውና አብሮትም እንደሚሄድ አውቆ ከፈተና ለመዳን ዘወትር እንዲጸልይ የታዘዘበትን ስንመለከት ብቸኛ መፍትሔው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቆ ማለፍ እንደሚገባ ያስተምረናል ማለት ነው።
በመሆኑም በፍጥረታት የመጀመሪያው ዘመን /ኦሪት ዘፍጥረት/ ጀምሮ እስከ አለንበት የዓመተ ምሕረት ዘመን/ሐዲስ ኪዳን/ ድረስ የሰው ልጅ ከፈተና ገጠመኝ ውጪ ሆኖ የኖረበት ዘመን የለም። ብዙዎች በፈተና አልፈዋል፤ ብዙዎች ከፈተና ወድቀው ከወደቁበት የፈተና ሁኔታ ተምረው እንደገና ፈተናውን ወስደው አልፈዋል፤ ብዙዎችም በፈተና ተረተውና ተሸንፈው ወድቀው ቀርተዋል።
በዘመነ ኦሪት የመጀመሪዎቹ የሰው ልጆች እግዚአብሔር ከዚህ አትብላ ብሎ ወይም ወደ ፈተና እንዳትገቡ ብል የከለከላቸውን ፈተና ማለፍና ማሳለፍ አቅቷቸው የተከለከሊትን ምግብ በሊ፤ በመብላታቸውም ምክንያት በፍርድ አደባባይ ቀረቡ፤ በተድላ በደስታ፣ ያለድካም ያለኅማም፣ ያለሀፍረት ያለሰቀቀን፣ ያለፀብ ያለሙግት ከሚኖሩበት የገነት ሕይወት ተሰደው እንደወጡና ለፈተና የዳረጋቸውን ምግብ በውጣ ውረድ በድካም በጣርና በጋር እንዲበሊ ተፈረደባቸው። እዚህ ላይ የምናስተውለው ነገር ምግብ እራሱ ፈተና ሆኖ የማይሻር ይግባኝ የማይጠየቅበት በምድር ላይ የዘላለም የማይቀረውን የሞት ፍርድ ቅጣትን በሰው ዘር ሁለ እንዳመጣብን መረዳት ይገባናል።
የእግዚአብሔርን መንበረ ዙፋን ከበው ሌት ተቀን ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ! እያለ እንዲያመሰግኑ ከተመረጡት ቅዱሳን መላእክት መካከል ሳጥናኤል የመላእክት አለቃ ሆኖ እንዲያገለግል የተሰጠው ቅድስና አልበቃው ብሎ፤ በፈጣሪው የመፍጠር የማይመረመር ሥልጣን ውስጥ ቅናት አገረሸበትና  እኔ ፈጣሪ ነኝ! ብሎ በፈጣሪው ላይ አመጸ።  መንግሥት በመንግስቱ፤ ጎልማሳ በሚስቱ ፤እግዚአብሔር በመለኮቱ  ቀናኢ ነውእኔ ቀናተኛ  አምላክ  ነኝ ፤ ከእኔ  ከፈጣሪህ በስተቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ተብሎ እንደ ተጻፈ በሊቃውንትም እንደተሰበከ፤ ፈጣሪ በሳጥናኤል ላይ የማያዳግም ፍርድን ወሰደ። ከማኅበረ መላእክት አንድነት ለይቶ ጣለው። ለሕይወት ሳይሆን የጥፋት መንገድ አለቃ ሆኖ ቀረ። ሳጥናኤል ከተመረጠበት ከፍተኛ የማዕረግ ልዕልና ተልዕኮ ተለይቶ የተሰናበተበት ምክንያት ከተሰጠው ሥልጣን በላይ ሌላ የማይገባው ከመጠን ያለፈ የሥልጣን ባለቤት ነኝ በማለቱ ነው።
እዚህ ላይ የምንረዳው ከመላእክት መካከል እንኳን የፈጣሪን የመፍጠር ሥልጣን ለመቀማት የሥልጣን ጥመኝነት ተግባር ሲያንጸባርቁ ያመጣባቸው ፈተና ለከፋ ዘላለማዊ የጥፋት አደጋ የሚዳርግ መሆኑን ነው።
የዓለም መድኅኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋለ ሥጋዌው በዚህ ዓለም ሲመላለስ ቅዱስ ቃሊን ለዓለም እንዲያስተምሩ ሂዱና ዓለምን አስተምሩ ተብለው ከታዘዙ የአገልግሎት መመሪያ ከተሰጣቸው አሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት መካከል፤ ይሁዳ በመሆን ለድሆች መርጃ የሚሆን ገንዘብ የሚሰበሰብበትን የሳጥን ቁልፍ እንዲይዝ የተመረጠ የታመነ ነበር። ገንዘብ የሚሰጠውን ጊዚያዊ ጥቅም ቀስ በቀስ ከተለማመደ በኋላ ለከፍተኛ ፈተና ተዳርጎ፤ ለሐዋርያዊ ተልዕኮ የመረጠውን ጌታውን ለሰላሳ ብር አሳልፎ ለአላዊያን ነገሥታት ለካሀዲያን የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ጉንጩን ስሞ ሸጠው። 

Sunday, May 15, 2016

“አትታደስም” በሚል ርእስ የተዘጋጀ ፀረ ወንጌል “መዝሙር” እንዳይመረቅ ታገደ


 Read in PDF
በማኅበረ ቅዱሳንና በተከታዮቹ ቤተክርስቲያንን ከእውነተኛው የወንጌል ትምህርት በማንሸራተት ወደ ተረት ለመውሰድ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ፣ “አትታደስም” የሚል ስያሜ የተሰጠውና ወንጌልን ለመቃወም የተዘጋጀውና ግንቦት 4/2008 ዓ.ም ሊመረቅ የነበረው መዝሙር የምረቃ ሥነሥርዓት ታገደ፡፡ ታታ ዘየካ ለተባለ ግለሰብ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደርጎ የተሠራው ይህ መዝሙር ግለሰቡን ሽፋን አድርጎ ወንጌልን የመቃወም የተለየ ዓላማ የያዘ ሲሆን የምረቃ ሥነሥርዓቱ ሕገወጥና ከቤተክርስቲያን ፈቃድ ያልተሰጠው በመሆኑ በ11ኛው ሰዓት ላይ ታግዷል፡፡

 ምረቃው እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የወጣቶች ማእከል አዳራሽ ውስጥ ሊደረግ ታስቦ የነበረ ሲሆን  ምርቃቱ ገና ከመጀመሪያው ግልጽነት የጎደለው ነበርና አዘጋጆቹ የአዳራሽ ኪራይ የከፈሉት ራሳቸውን ደብቀው የማይታወቅ ሰው በመላክ ነበር፡፡ የቀበሌው ሥራ አስፈጻሚ ምንም የሚያውቀው እንደሌለ ሲገልጽ የተዋዋለው ሲጠራ የቀረቡት እነታታ ሳይሆኑ ስለጉዳዩ ምንም የማያውቀው ግለሰብ ነበር፡፡ እርሱም ተጠይቆ “ልከውኝ ክፈልና ና ብለውኝ ነው” በማለቱ ፈቃድ ከቤተ ክርስቲያን እንዲያመጡ ተጠይቀዋል፡፡ ያን ማድረግ ባለመቻላቸው ምረቃውን ማካሄድ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ታዛቢዎች ሕጋዊ ቢሆኑና ድብቅ ዓላማ ባይኖራቸው ኖሮ ራሳቸው ቀርበው መዋዋል ይችሉ ነበር ይላሉ፡፡

Thursday, May 12, 2016

“ቅድስና” እንደ “ማኅበረ ቅዱሳን” እና እንደ መሪው “ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ይሁንልን!አንድን ጉዳይ ደጋግሞ በፉለት ቁጥር ዕውቅና እንዲያገኝ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ግል ነው።  ስለ ዳንኤል በመፍ ጊዜ ማባከን ለምን አስፈለገ? ቢባልም በርግጥ ሳያውቁት “ዲያቆን” በሚል ተቀጥላ ስሙ የሚታለሉ የዋሃን ቁጥር  ብዙ ነውና እውነቱን መግለጡ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም። ለመሆኑ ዳንኤል ክብረት ማን ነው? የሚመራውስ ማኅበር (ማቅ) ዓላማው ምንድን ንው?    

በመሠረቱ ዳንኤል ክብረት አንድ ተራ ግለሰብ ሲሆን እታይ እታይ፤ እታወቅ እታወቅ በሚል በተጠናወተው አባዜው  የተነሣ ባልዋለበት ሊቅ መስሎ በየሄደበት የሚጮኸውና በምን ልታወቅ  ሁፎቹ መንገድ ዳር በበቀሉት ዕዋት በሚመሰሉት የዋሃን ምእመናንን ማደናገሪያ ከንቱ ድካሙ ያለ አቅሙ በዘመናዊውም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት  ስንት የደከሙ ሊቃውንትን የሚዘልፍ ከኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ዲፕሎማ ተነሥቶ በ advanced standing admission ከአማርኛ የመጀመሪያ ዲግሪ የማትዘል ዕውቀቱ በአንድ በኩል የሥነ መለኮት ተመራማሪ፤ በሌላው መለኩ ደግሞ የታሪክ ተመራማሪ በመምሰል የሚፈጨረጨር በውዳሴ ከንቱ ካባ ተጀቡኖ የሚኖር እሳት የላሰ ባዶ ናስ ነው።  በመሆኑም  በእግዚአብሔር ጋ የከበሩ  አባቶች ሊቃውንትንም ሆነ በዘመናዊ ትምህርትና ሥነ ምርምር  የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የደረሱ ምሁራንን ሲዘልፍ ይሉኝታ፣ ልጓምና ለከት ያጣው የዕውቀቱ ልክ ግድ ስለሚለው ነው። ምክንያቱም ሰው ባለው ልክ ነውና ለሌላው የሚተርፈው። ባዶ በርሜል/ገረወይና ትንሽ ቢነኩት ጩኸቱ መከራ ነው፤ ቢሞላ ግን ድም አልባ ነው።  ቢማር/ቢያውቅ ኖሮ የዐዋቂዎች/ የምሁራን/ የሊቃውንት ጥቅማቸው ይገባውና ይቆረቆርላቸው ነበር።  ወርቅን ለሚያውቀው ነው ወርቅነቱ፤ ለማያውቀው ግን ተራ ብረት ነውና።

ዳንኤል ከዚህች ከተጠቀሰችው ትምህርቱ በስተቀር ሌላ የሚያወላዳ ዕውቀት የለውም ከጥራዝ ነጠቅ መንፈሳዊ ከሚመስሉ የተኮረጁ ቃላቶቹ በስተቀር። በባህር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት አባል (የሰንበት ት/ቤቱ የትያትርና ሥነ ጽሁፍ ክፍል ቋሚ አባል) ሆኖ እየተወነና መነባንብ ለሰ/ት/ቤቱ ጉባኤ እያቀረበ እንደ ማንኛውም የሰ/ት/ቤት አባል በቤተ ክርስቲያን ከመቆየቱ በስተቀር የአብነት ትምህርት ከማንም መሪጌታ/አስተማሪ ጋር፤ አይደለም ዓመታትና ወራት፣ አንዲት ሳምንት ብሎም አንዲት ነጠላ ቀን ቁጭ ብሎ ፊደል የቆጠረበት ጊዜ የለም። ዛሬ “ዲያቆን” የምትለውን ማዕረግ ከስሙ በፊት ለጥፎ ሲታይ ላላወቀው በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ያለፈና ግዕዝ/ቅኔ የቆጠረ፣ መጽሐፍ የተማረ ይመስላል። ደግነቱ  በመድረክ ላይ ጩኸቱ ተውሶም ቢሆን የግዕዝ ቃላትም ሆነ ምስጢር ያለው ቅኔ ወርወር አድርጎም አያውቅም፤ ከቃላት አጠቃቀሙ የተነሣ ጨዋነቱ እንዳይገለጥበት።
 ያም ሆኖ በጨዋ ስብከቱ ማንነቱ አልተነቃበትም ማለት አይደለም። ይህችንም “ዲያቆን” የምትል ተቀጥላ ያገኘው ኮተቤ በሚማርበት ወቅት ክረምት ክረምት ኮሌጁ ሲዘጋ በወቅቱ የነበሩት የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጎርጎርዮስ ከነበራቸው ቅን አመለካከት የተነሣ ዳንኤልና መሰሎቹ በሰ/ት/ቤት የነበራቸውን ተሳትፎና አፈ ቀላጤነታቸውን በማየት ለወደፊቱ የወንጌል አገልግሎት ይጠቅሙ ይሆናል በሚልና ይህንንም አገልግሎት ለማከናወን አቶ ተብለው ሕዝብ ፊት ከሚቆሙ ዲ/ን ቢባሉ አገልግሎታቸው ተቀባይነት ይኖረዋል በሚል እሳቤ በዝዋይ የካህናት ማሰልጠኛ በሁለት በሁለት ወር የክረምት ኮርስ ስልጠና ለተልእኮ ይህችን ማዕረግ ስለሰጧቸው ዛሬ በውዳሴ ከንቱ መጠለፊያ ሆኖበታል/ሆኖባቸዋል። “ዲያቆን” ነኝ ይበል እንጂ ግባና ቀድስ ቢባል ግብረ ዲቁናውን አልሞከራትምና “ተንሥኡ”ን የሚያዜምባት ቅንጣት ታክል ችሎታና አቅም የለውም። በንባብ ካልሆነም በስተቀር አይደለም መልክአ ኢየሱስና መልክአ ማርያምን የዕለት ውዳሴ ማርያምን በቃሉ ቢዘልቅ ከምላሴ ፀጉር። 

Tuesday, May 10, 2016

መሪው ተመሪ ተመሪው መሪ የሆነባት ቤተክርስቲያን መጨረሻዋ ጥፋት ነውቤተ ክርስቲያን ሁሉም ድርሻውን አውቆ ግዴታውንና ኃላፊነቱን የሚወጣባት የሥርዓት ቤት ናት፡፡ በዚሁ መሠረት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ቀሳውስትና ዲያቆናት ለምእመናን ሃይማኖትን ሊያስተምሩ በትክክለኛው መንገድ ሊመሩ፣ ምእመናን ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነውን ትምህርታቸውን ሊቀበሉና ለአመራራቸው ራሳቸውን ሊያስገዙ፣ በሌላውም እነርሱን በሚመለከተው ጉዳይ ላይ ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው፡፡ ይህን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዛሬ ግን አንዳንዶች ይህን አምላካዊ ሥርዓት ለመለወጥ ባለ በሌለ ኃይላቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት ግን ይህ አምላካዊ ሥርዓት እየተጣሰ መሪው ተመሪ ተመሪው ደግሞ መሪ እየሆነ ሥርዓት አልባነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰፈነ ይገኛል፡፡ የዚህ ውጤትም ውሎ አድሮ እውነተኛው የሃይማኖት ትምህርት በሌላ የስሕተት ትምህርት እንዲለወጥ፣ አምላካዊው ሥርዓትም ፈርሶ በስፍራው የሰው ሥርዓት ምናልባትም ሥርዓት አልበኛነት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትና እርሱን የሚያስተምሩ መምህራን የሚሉት ሳይሆን ምእመናን ከቃሉ ውጪ ለሃይማኖት ባላቸው ቅንዓት በተሳሳተ መንገድ የተቀበሉትና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲሆንላቸው የሚፈልጉት እንግዳ ትምህርት ተቀባይነት እንዲኖረው በር ይከፍታል፡፡
ይህ አካሄድ በተለይ ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በደንብ ሲሠራበት የኖረና ውጤቱ አሁን በመታየት ላይ የሚገኝ አደገኛ አካሄድ ሆኗል፡፡ ቀድሞ በእግዚአብሔር መሠረትነት እውነተኛ የተባሉት ትምህርቶች ዛሬ እንደ ኑፋቄ እየታዩና ብዙዎችን እያስወገዙ ናቸው፡፡ በሊቃውንቱ ዘንድ በኑፋቄነት ተፈርጀው የነበሩት የስሕተት ትምህርቶች ደግሞ ዛሬ ላይ እንደ ትክክለኛ ትምህርት እንዲታዩ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ወደየት እያመራች እንደሆነ መገመት ቀላል ነው፡፡

Friday, May 6, 2016

መፍትሔ ላጣው ደብር መፍትሔ የሚሰጥ ማነው?የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን መፍትሔ አጥቶ ሰላም ከራቀው ይኸው ከነችግሩ አንድ ዓመት አስቆጠረ፡፡ አሁን ያለው የደብሩ ችግር በካህናት ኑሮ ላይ አፍጦ እየታየ ነው፡፡ የበዓል ቦነስ ቀርቶ ደመወዛቸው ተረጋግቶ ሊከፈላቸው አልቻለም፡፡ የባለፈው ወር ደሞዝ ሌሎቹ አድባራትና ገዳማት ከተቀበሉ ከ15 ቀን በኋላ ነበር የተከፈላቸው፡፡ ለገንዘቡ መጥፋት ተጠያቂው ደግሞ የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው አባላት ሲሆኑ በተራዘመ የሕንጻ አሠራር ስልት ገቢውን ለግላቸው እየከበሩበት ካህናቱ ግን እየተራቡ ያለው የደብሩን ገቢ ሙልጭ አድርገው በመውሰዳቸው ነው፡፡ ተከታዮቻቸውንም ለሕንጻው እንጂ ለደብሩ ሙዳየ ምጽዋት አታስገቡ በማሰኘት ለበለጠ ዝርፊያ ሁኔታውን አመቻችተውላቸዋል፡፡
የዚህ ደብር ባለቤት ማነው? ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነት? ወይስ ሀገረ ስብከት? ወይስ የአካባቢው የጎበዝ አለቆች? ማን እያስተዳደረው እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ካህናቱም ጠዋት ኪዳን አድርሰው ቀን በየሰፈሩ ቀብር አስፈጽመው ቀድሰው ለበዓል የሚውሉበትን ገንዘብ በልምምጥ መልክ ምንም የማይመለከታው የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴዎችን ገንዘብ ስጡኝ ብለው መጠየቅ ውስጥ መግባታቸው ለእነርሱ ትልቅ ውርደት ነው፡፡ ካህናቱ በማገልገላቸው የሚገባውን ገንዘብ ህንጻ አሠሪዎቹ በተራዘመና በሰለቸ የሕንጻ አሰራር ስልት በእጅጉ እየተቀራመቱት ነው፡፡
·        ባለሲኖትራኩ አቶ ታረቀኝ፣
·        ባለ 5 ፎቁ አቶ ጉዳ ወይም በለጠ፣
·        ባለብዙ ቤት አከራዩ አቶ ብርሃኑ ድረሴ
·        በየጊዜው 55 ሺ ብር እየከፈሉ ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዙት አቶ ካሣ
·        ፎርማን የነበረውና 8 ሺህ እየተከፈለው ዛሬ የሕንጻ መሣሪያ ሱቅ ባለቤት የሆነው ባይሳ
·        የሕንጻውን ፎቶ በአሜሪካ ስቴቶች በመቶ ዶላር እየሸጡ ያሉት አቶ ዳንኤል ተገኑ ወዘተ እየተጫወቱበት ነገ የማይኖሩበትን ቤት እየገነቡበት ይገኛሉ፡፡
·        የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እስጢፋኖስ ሀይሉ ደግሞ ፒያሳና አትክልት ተራ ላሉት የኤሌክትሪክ ሱቆቹ ያለ ጨረታ ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ በበለጠ ወይም በጉዳ አማካይነት የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አቅርቦበታል፡፡