Saturday, May 28, 2016

ሰበር ዜና፡- የማኅበረ ቅዱሳን ዋና የአመራር አካል የሆነው ከፍያለው አያሌው በመግደል ሙከራ ወንጀል 10 ዓመት ተፈረደበት


 Read in PDF
,እስመ አልቦ ክዱን ዘኢይትከሠት ወኅቡእ ዘኢይትዐወቅ.(ማቴ.10:26) 

               
የሃይማኖት ጨለምተኝነትን ካባን ለብሶ ለበትረ ሥልጣንና ለንዋይ ክምችት ሲንቀሳቀስ የኖረውና እየተንቀሳቀሰ ያለው ማቅ ይህንን ነገር ለማሳካት ከሚጠቀምባቸው ነገሮች አንዱ ነፍሰ ገዳይነት   መሆኑ  የሚካድ አይደለም። ፖሊስ ያልደረሰላቸው፤ ሕግ ያልያዘላቸው ብዙዎች ንጹሕ ደማቸው በከንቱ ፈሷል። ሕይወታቸው አልፏል። በፖሊስ ተመርምረው በገንዘብ ኃይል ለፍርድ ሳይበቁ ደብዛቸው የጠፋ ወንጀሎችም መኖራቸው የሚታወቅ ነው። እነዚህ በአካል ደብድቦና አቊስሎ የገደላቸው  ሲሆኑ  ከሥራ  አፈናቅሎ፤  ሞራላቸውን  ነክቶ፤  ከቤተ  ክርስቲያን  አባሮ፤  በረሀብና በችግር የገደላቸውም  ብዙዎች  ናቸው።  ማቅ  በአካሔዱም  ሆነ  በዓላማው  የእርሱ  ያልሆነውን  ማጥፋት የተነሣበት ግቡ ስለሆነ ከወንጀል የራቀበት ጊዜ የለም። 

  የመግደል ሙከራ ለማድረግ ከተራ አባል እስከ ዋና አመራር ድረስ የማያመኑት እና ይህን ክፋታቸውንና ጭካኔያቸውን ሃይማኖታዊ ምክንያት በመስጠት ለራሳቸው ልዩ ወንጌል የፈጠሩት የማቅ ሰዎች የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ሁሌ ሊሳካ እንደማይችልና ለዘለቄታው ከህግ ተሰውሮ መኖር እንደማይቻሉ ትናንት ግንቦት 19 ቀን 2008 ዓ/ም የተሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ ማረጋገጫ ነው። የማህበረ ቅዱሳን ዋና አመራር የሆነው ከፍያለው አያሌው በፈጸመው የመግደል ሙከራ ወንጀል በአሥር ዓመት ጽኑ  እሥራት  ተፈርዶበታል። ከፍያለው አያሌው  የመግደል  ሙከራውን  ያደረገው የቤተ ክርስቲያን  አባት  በሆኑት በመልአከ  ገነት  አባ  ዮሐንስ  አፈወርቅ  የኮልፌ  ክፍለ  ከተማ  ሥራ  አስኪያጅ ላይ ነበረ።  ይህ ግለሰብ ያደረገው የመግደል ሙከራ በበቂ ማስረጃ ስለተረጋገጠበትትናንትና ዓርብ ከጠዋቱ በ4 ሰዓት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በአሥር ዓመት ጽኑዕ እሥራትና ለአምስት አመት ከማንኛውም የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዲታገድ ተፈርዶበታል። 

 ማቅ መልአከ ገነት አባ ዮሐንስ አፈወርቅን ለመግደል ለምን ፈለገ? ይኽ የመግደል ሙከራው ከአሁንበፊት የተሞከረ ሲሆን ይኽ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።መልአከ ገነት አባ አፈወርቅ ዮሐንስ በማቅ የግድያ ሊስት  ውስጥ  እንዴት  ገቡ? 
አባ  አፈወርቅ  ጽኑዕ  አቋም  ያላቸው  እውነተኛ  ታማኝ  መነኲሴ ናቸው።  እኝህ  ሰው  የማቅ  አባል  ካለመሆናቸውም  ሌላ የማቅን  ገበና  አጋልጠዋል። ማቅ ሃይማኖትን ለፖለቲካ፤  ቤተ  ክርስቲያንን  ለመበልፀጊያ  የሚጠቀምበትን  የአሠራር  ሥልቱን  አባ  አፈወርቅ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት በማጋለጣቸው በማቅ ዘንድ ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ ተወስኖባቸዋል። ማቅ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን  መዋቅራዊ  አሠራር  ያፈነገጠበትንና  የቤተ  ክርስቲያንዋን  ሀብት  የሚዘርፍበትን  አካሔድ በአጋለጡበት ዕለት ባያብል በሚባለው የማኅበሩ ዋና ሰው በመኪና የመግደል ሙከራ ተደርጎባቸዋል። የመግደል  ሙከራው  አልሳካ  ሲል  በስም  አጥፊነት  ወንጀል  ለማስቀጣት  ፍርድ  ቤት አቆሙአቸው። ፍርድ ቤት  ክሱ የሀሰት መሆኑን ከአረጋገጠ በኋላ አባ አፈወርቅ በነጻ እንዲለቀቁ አድርጓል። ይኽም  የክሱ  ጉዳይ  አልሳካ  ሲለው  ማኅበሩ  አባ  አፈወርቅን  የመበቀል  ሥራውን ቀጥሎ ከሥራቸው እንዲፈናቀሉ አደረገ።  ይኽንን ለማሳካት አባ አፈወርቅ የወሊሶ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ስለነበሩ የወሊሶውን  ሊቀ  ጳጳስ  አባ  ሳዊሮስን  ጠምዞና  በነውራቸው አስፈራርቶ ወደ ራሳቸው ማስገባት ነበረ። ፊታቸውን ወደ ማኅበሩ ያዞሩት አባ ሳዊሮስ እውነትን ለመመሥከር በአደባባይ አብረው የቆሙትን አባ አፈወርቅን ከዱ።ከሥራቸው በማፈናቀልም አሳልፈው ሰጡአቸው። ቂም በቀሉ በዚህምአላበቃም። በማኅበሩ ዓላማ አንድ ከሆኑት አቡነ ማቴዎስ ጋር በመመካከር አባ አፈወርቅ ወደ ወሊሶ ሀገረ ስብከት ይዘው የመጡት በጀታቸው እንዲቆረጥባቸው፤ አባ አፈወርቅ እንዳይቆሙም እንዳይኖሩም በማድረግ ለረሀብና ለሥቃይ ዳረጉአቸው። አባ አፈወርቅ ግን ከእውነት ጋር ተጣብቀው በማያወላውል  አቋማቸው  ረሀቡንና  ሥቃዩን  ተጋፈጡት።  በዚህን  ጊዜ  የድኆች  እንባ  የሚገዳቸው፤ለእውነትና በእውነት የቆሙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከራሳቸው ኪስእየከፈሉ አባ አፈወርቅን ታደጉአቸው። ከብዙ ቆይታ በኋላም አባ አፈወርቅ የኮልፌ ክ/ከተማ ሥራ አስኪያጅ ሆኑ።
   
ማቅ አሁንም እረፍት አላገኘም። እርሱ የተበቀለው ሰው ሥራ በማግኘቱና እንዲሁም በብዙ መድረኮች የማቅን እኩይ አሠራር በማጋለጡ ማቅ የወጠነውን የመግደል ውሳኔ እየቀጠለበት መጣ።በመሆኑምአባ አፈወርቅ ከሚማሩበት ሰዋስወብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ድረስ በመሔድ መኪናውን ትምህርት ቤቱ መግቢያው ላይ አቁሞ ሲጠባበቅ ውሏል። በመኪና አደጋ የመግደል ሙከራ ወንጀል የፈጸመው ከፍያለው  አያሌው  አባ  አፈወርቅ  ከት/ቤት  ሲወጡ  ጠብቆ  መኪናውን  በኃይል  በማብረር  ገጭቶ ለመግደል ሲሞክር አባ አፈወርቅ በኃይል ተፈናጥረው የቱቦ ጉድጓድ ውስጥ በመግባት በእግዚአብሔር ቸርነት  አምልጠዋል።  በቱቦ  ጉድጓድ  ውስጥ  የአካል  ጉዳት  ቢደርስባቸውም  ከሞት ግን ተርፈዋል። 
ከአባ  አፈወርቅ  ጋር  ይጓዝ  በነበረው  ሰው  ጠቋሚነት  በትራፊክ ፖሊስ ክትትል ከፍያለው ለማምለጥሲሞክር ተይዞ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋለ። ወንጀለኛው ሲያዝ በመኪናው ውስጥ የነበረው የማኅበሩ ኮምፒዩተር፤  ልዩ  ልዩ  ሰነዶች  ተገኝተው  ለምርመራ  መያዛቸው  ታውቋል።  ማቅ  የአባቶችን  ስምጥላሸት ለመቀባት፤ በእግዚአብሔር ጸጋ የከበሩትን ለማዋረድ እየጻፈ በሐራ ተዋሕዶ የሚለጥፋቸው ወረቀቶች ሁሉ  መገኘታቸውን  ለመረዳት  ችለናል። ሰነዶቹ  በባለሞያዎቹ  በኩል  እንቨስትጌት እንደሚደረጉ ምንጮች ይገልጣሉ። በሰነዶቹ ብዙ ምሥጢር እንደሚጋለጥና የማኅበሩ ወንጀሎችም ይፋ እንደሚሆኑ ተጠቍሟል። 

ነፍሰ  ገዳዩ  ማቅ  እኔ  ብቻ  ሃይማኖተኛ  ነኝ  ማለቱ  በሃይማኖት  ስም  ግድያን  በመፈጸም  ብቸኛ መሆኑ በዚህ ታውቋል። ማቅ በዚህ ግብሩ የቤተ ክርስቲያንን አባቶች ስም በማጥፋት፤ ክብራቸውን በማዋረድ ቤተ  ክርስቲያንዋን  እጅግ  ጎድቶአታል።  ነፍሰ  በላ  ማኅበር መሆኑንም ያስመሠከረ ድርጅት ነው። 
በኦርቶዶክስ  ስም  የኦርቶዶክስ  ቤተ  ክርስቲያንን  የበዘበዛትና  በታሪኳ  ውስጥ ጥቁር አሻራ ያስቀመጠ ብቸኛ  ማኅበር  ነው።  ቤተ  ክርስቲያን  በዚህ  ማኅበር  የደረሰባት  የታሪክ  ውድመት  በእነ  ጉዲት፤ መሐመድና ሉቱራንም አልደረሰባትም።  

መልካም ንባብ!!!

34 comments:

 1. kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
 2. ይህ ምን ደንቃል የማቅ ዋናው ባህሪ እኮ ነው።

  ReplyDelete
 3. This is maybe the beginning of the end! We are looking forward to the Orthodox Church without the evil Mahibere Satan and its victim bishops that have sold their soul to the devil. In God's time everything happens and no one but no one can stop it. Psalm 37:12-15, 20, 32, 35-36.
  New International Version (NIV)

  12 The wicked plot against the righteous
  and gnash their teeth at them;
  13 but the Lord laughs at the wicked,
  for he knows their day is coming.
  14 The wicked draw the sword
  and bend the bow
  to bring down the poor and needy,
  to slay those whose ways are upright.
  15 But their swords will pierce their own hearts,
  and their bows will be broken.
  20 But the wicked will perish:
  Though the Lord’s enemies are like the flowers of the field, they will be consumed, they will go up in smoke.
  32 The wicked lie in wait for the righteous,
  intent on putting them to death;
  35 I have seen a wicked and ruthless man
  flourishing like a luxuriant native tree,
  36 but he soon passed away and was no more;
  though I looked for him, he could not be found.
  Your days are numbered!Time to ask God's forgiveness or land in the lake of fire! The choice is yours, take it or leave it!

  ReplyDelete
 4. Ere eferu midre grissa hula.

  ReplyDelete
 5. ውድ አባችታን አባ አፈወርቅን እግዚአብሔር ይሁናቸው ጠላቶችቻቸውን ከእግራውቸ በታች ይጣልላቸው

  ReplyDelete
 6. አይሰማ የለም ለመሆኑ በመግደል ሥልጣን ይገኛል
  ቢገኝስ እንዴት ይፀናል

  ReplyDelete
 7. የብላቴ ማሰልጠኛ ምሩቃን ማህበር በጥይት ቢያቅታችሁ በመኪና ህይወት ለማጥፋት? ሆይ ሆይ

  ReplyDelete
 8. ኤረ ጉድ ጉድ ጉድ ነው ዘንድሮ የአመጽ መጨረሻው ይህ ሆነ። እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ያውጣን ከመዓቱ እንበል እንጅ። ለአቡነ ጳውሎስ መርዝ ያቀበለው የእባብ ልጅ ለሌው ካህን ይተኛል ብሎ ማስብ ሞኝነት ነው። ገና የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የማቅ መሪዎችን ስውር ደባ ያጋልጣቸዋል። አውሬ ገና በክርስቶ መስቀል ድል ይደረጋል ። ገና ነው ጉዱ!!! እልልልል በል እልልል በይ የእነተኛው የተዋህዶ ልጅ ገና እግዚአብሄር በሐተኛው ማቅ ሰፉን መዞዋል። እርሱ ተዋግ አምላክ ነው ማን ይቃወመዋል። የማቅ በእመቤታችንና በቅዱሳን ስም መነገዱን በሰማይ በጌታ ዙፋን ፊት ደረሰ። ግዜው ደረሳ የማቅ መሪዎች ሞት።በንዋይ መንገድ ለይሁዳም አልበጀውም ለሞት ዳረው እጅ።ስብሐት ለእግዚአብሔር እውነቱ ይህ ነው። የነፍሰ ገዳይ ቡድን። እጅ ከፍንጅ ተያዘ።እልልልልል በሉ ጌታን አመስግኑ

  ReplyDelete
 9. ጉድ ጉድ ጉድ........100% ሃሰትና የሃሰት ወሬ። ከፍያለው አያሌው የሚባል አመራር ተራ አባል በማቅ መንደር የለም። አንባቢያን በማንኛውም መንገድ አጣሩና ታዘቧቸው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እረ ባክህ ልክዱት ነው ለአባል ችግር የለውም ቀረ ጎሽ እንዲ ነው

   Delete
  2. why you always say MK???

   Delete
  3. እሱማ ዳንኤል ክብረት የሚባልም አባል የላቸውም እኮ በጭራሽ 100%. ማጅራት መቺ ሁሉ ተሰብስቦ በነጠላ ይታነቅና ክርስቲያን ነኝ፤ ቅዱስ ነኝ፤ አይኔን ግንባር ያርገው እኔ ቤተክህነትን አልዘርፍኩም እንሱ እየሰጡኝ ነው ከሚል ኪስ አውላቂ ጋር ምን አከራከረህ ወንድሜ። ከመርካቶ ያመለጠው የቤተክርስቲያን ጊቢ አይቶ የማያውቀው ሌባ ሁሉ ነው ቀሚሱን እያጠለቀ ሰባኪና የማቅ አባል የሆነው። ማንቁርቱን ሲያዝ ወላሂ ያለ ዛሬ አላየሁትም ይላል።

   Delete
 10. የማህበረ ቅዱሳን አባላትን አላማና ተልእኮ በደንብ ለተረዳ ሰዉ ይሄ አያስደንቀዉም፡፡ በማቅ ቤት እንደ እነ እንትና ሰዉ መግደል ያጸድቃል የሚል አስተምሮ ሳይኖር አይቀርም፡፡ አንድ አዛዉንት በመግደል ምን ሊጠቀሙ ነዉ?

  ReplyDelete
 11. ሰሞኑን በዐውደ ርእዩ ሕዝ እየጎረፈ ሥራቸውን እያየው ስለሆነ ሰላ አጣችሁና ይህንን ፈጠራችሁ.... ስም አጥፊ ቦዘኔ ሁላ፡፡ ማቅ እያለ እናንተ ቤተ ክርስቲያንን ለመናፍቃን ማስረከብ... ሲያምራችሁ ይቅር፡፡ ሌላ ሥራ ስታጡ ወሬ ፍጠሩ... ማኅበሩ ግን የሠራውንና እየሠራ ያለውን ሕዝቤ ያውቃል አይቷልም፡፡

  ReplyDelete
 12. I enante mat awurawoch nefs megidel ewun kenante yebelete leba molacha, eminetyelesh, mena, bado =wona, tesadabi, sim atify, melkam neger yemayiwetawetawu, hule abatochin miyatilala, chifun eyita yalew man alen? nigerugn enji enaya jibo realy ke amagn sew yih AYINET ANEGAGER yITEBEKAL? nIGERUGN ENJI MIDERE TEHADISO HULA? EGNA EKO TEMELESU KETIFATACHIHU ENJI BEZAW ENDETEFACHIHU ENTIKERU HASABIM FILAGOTIM YELENIM .YENISIHA EDIMIE YISTACHIHU. YEMATIMELESU/MATASIBU KEHONE GIN LEBETECHRISTIAN KIBIR SIBAL EDIMIYACHIHUN BIYASATIRILIN YISHALAL

  ReplyDelete
 13. እናንተ አባ ሰላማዎች ከፍያለው አያሌው የሚባል ሰው በማኅበረ ቅዱሳን አመራር ውስጥ ለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡ ምክንያቱም በአመራር ደረጃ ያሉትን በሙሉ ስማቸውንና ሥራ ድርሻቸውን ለማጣራት ስሞክር እናንተ ጠቀሳችሁትን ሰው ስም ስላላገኘሁት ነው፡፡ ይሄ ነገር እውነት ለመሆኑ በጣም ያጠራጥረኛልና እስቲ የሰውዬውን ፍቶግራፍ፣ በማህበሩ አመራር ያለውን ቦታ፣ የመኖሪያና የሥራ አድራሻውን በግልጽ አስቀምጡልን፡፡ ካልሆነ ግን እውነትነቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

  ReplyDelete
 14. አየ ጉደ የአቡነ መርሃክርስቶስ ገዳይስ መቼ ነው የሚያዠው ማሀበረ ቅዱሳን አፍኖ ወስዱ በመርዝ መርፌ ወግቶ የገደላቸው የቀለሙን ቀንደ የደፋቸው

  ReplyDelete
 15. ከፍያለው አያሌው የሚባል አመራር የለም

  ReplyDelete
 16. nefese gedayun ye mk menfes geta yigesesew

  ReplyDelete
 17. nefese gedayun ye mk menfes geta yigesesew

  ReplyDelete
 18. እኔ በበኩሌ በእርግጠኝነት አያረገውም ብዬ አላምንም ምክንያቱ ነገሩ ሁላ ፓለቲካ ነው ለምን ስሙን እንደማይቀይር¡

  ReplyDelete
 19. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ የፍርድ ታሪኮች አንዱ የሶስና ፍርድ ነው፡፡ እሥራኤል ወደ ባቢሎን ተማርከው በነበሩ ጊዜ ኢዮአቄም እና ሶስና የተባሉ ባልና ሚስቶችም ተማርከው ነበር፡፡ የባቢሎን ሥርዓተ መንግሥት ከየሀገሩ የተማረኩ ፈላስያን የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ፈቅዶ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ የራሳቸውን ፍርድ ቤቶች አቋቁመው የራሳቸውን ጉዳዮች ይዳኙ ነበር፡፡ በዚህ የእሥራኤል ዳኝነት አንድ ጉዳይ ቀረበ፡፡
  ሶስና የምትባል በመልኳ ይህ ቀረሽ የማትባለው የኢዮአቄም ባለቤት በሞት በሚያስቀጣው የአመንዝራነት ወንጀል ተከሰሰች፡፡ በዚያ ዘመን በሀብት ሻል ያሉ የባቢሎን ሰዎች ቤታቸውን በኤፍራጥስ ወንዝ አቅራቢያ ሠርተው በወንዙ ዳር በሚገኙት የአትክልት ሥፍራዎች ውስጥ የገላ መታጠቢያዎችንና የመዋኛ ገንዳዎችን ያዘጋጁ ነበር፡፡ እነዚህ የመናፈሻ ሥፍራዎች በአጥር የታጠሩ ሆነው የራሳቸው በር ነበራቸው፡፡
  ኢዮአቄምና ሶስና ከፈላስያኑ ወገን በሀብትም በክብርም ላቅ ያሉ ስለነበሩ ይህ ሀብት ነበራቸው፡፡ ሀብት ክብር ብቻ ሳይሆን መዘዝም ያመጣል፡፡ በኢዮአቄም ቤት ለችሮታም፣ ለመጠለልም፣ ከባቢሎን ባለ ሥልጣናት ለመገናኘትም እያሉ የሚሰበሰቡ ብዙ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ መካከል ሁለቱ የተከበሩ የሕዝብ መምህራን ናቸው፡፡ ሕዝቡ በዐዋቂነታቸውና በወንበራቸው ያውቃቸዋል፣ ያከብራቸዋል፡፡ ‹በካባ ውስጥ ያለን ኃጢአት፣ በኮት ውስጥ ያለን ጽድቅ እግዜር ብቻ ነው የሚያውቀው› እንዲሉ እነዚህ ሁለት የተከበሩ ባለ ካባዎች ጠባያቸው እንደ ካባቸው አልነበረም፡፡ የኢዮአቄምን ሚስት ሶስናን ለመኝታ ይፈልጓት ነበር፡፡ ነገር ግን አመቺ ጊዜ አላገኙም፡፡

  ReplyDelete
 20. የሕዝቡ ሸንጎ በማግሥቱ ተሰብስቦ ጉዳዩን አየው፡፡ እነዚያ ሁለት መምህራን አይተናል ያሉትን ተናገሩ፡፡ ሰዎቹ የሚከበሩ በመሆናቸው ቃላቸውም ተከበረና በሶስና ላይ የሞት ፍርድ ተፈረደባት፡፡ ወደ ፍርድ መፈጸሚያው ሥፍራ ልትሄድ ስትል ግን ፍርዱን እንደገና ለማየት የሚያስገድድ ነገር ተፈጠረ፡፡ ነቢዩ ዳንኤል ‹እኔ በዚህ ፍርድ አልስማማም› አለ፡፡ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ያደረገውን ያውቁ ስለነበር ሕዝቡ ሁሉ ሊሰሙት ፈለጉ፡፡ ዳንኤል አንዱ ያንዱን ቃል ሊሰማ በማይችልበት ቦታ ሁለቱን ሰዎች ለየብቻ አቁሞ የትኛው ዛፍ ሥር ተኝታ እንዳዩዋት ጠየቃቸው፡፡ አንዱ በኮክ ዛፍ ሥር ሲል ሌላው በሮማን ዛፍ ሥር ነው አለ፡፡ ይህንን ሲመለከቱ የሕዝቡ ሸንጎ የሞት ፍርዱን እንዲከልስ ተገደደ፡፡ ሶስናን በነጻ አሰናብቶ በምስክሮቹ ላይ የቅጣት ውሳኔን አስተላለፈ፡፡
  ሶስና ኢትዮጵያዊት ሆና፣ ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ቢሆን ኖሮ ግን የመትረፍ ዕድል አልነበራትም፡፡ ምንም ንጹሕ ብትሆን፣ ምንም ምስክሮቹ የሐሰት ምስክሮች መሆናቸው በኋላ ቢረጋገጥ፣ ምንም እንኳን ከፍርዱ ውሳኔ በኋላ የፍርዱን ውሳኔ የሚያስገለብጥ ማስረጃ ቢገኝ ሶስና ከመሞት ውጭ አማራጭ አልነበራትም፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ በወንጀል ጉዳይ የተሰጠ ውሳኔ እንደገና የሚከለስበትን ዕድል ስለማይሰጥ፡፡ በታች ፍርድ ቤት የታየ ጉዳይ በይግባኝ በላይኛው ፍርድ ቤት ይታይ ይሆናል እንጂ አንድ የወንጀል ፍርድ ከተሰጠ በኋላ የቀረበው ማስረጃ ስሕተት ነበረ፣ የተፈረደበት ሰው በስመ ሞክሼ ነው፤ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት አለመፈጸሙ ተረጋገጠ፣ የወንጀሉን ፍርድ ሊያስገለብጥ የሚችል ሌላ ማስረጃ ተገኘ ቢባል እንኳን የሀገራችን የወንጀል ፍርድ ‹ከፈሰሰ የማይታፈስ› ነው፡፡

  ReplyDelete
 21. ወም የሚከራከሩ ወገኖች የሚያነሡት ሁለት ጉዳይ ነው፡፡ አንደኛው የወንጀል ፍርድ እንዴትና በማን ነው ሊከለስ የሚችለው? ሁሉም የወንጀል ችሎቶች ይህ ሥልጣን ከተሰጣቸው ላልተገባ ተግባር የመዋል ዕድል አይኖረውም ወይ? የሚል ነው፡፡ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ጉዳዩ መጀመሪያ ለቀረበበት ችሎት ነው የሚቀርበው፡፡ የወንጀል ጉዳዮች ሀገርንና ማኅበረሰብን የሚመለከቱ ስለሆኑ ይህንን ነገር ሊያዩ የሚችሉ ችሎቶችን መመደብ ወይም ከፍ ያለ ሥልጣን ለተሰጠው የፍርድ አካል መስጠት ይቻላል፡፡ በሌላም በኩል አንድ ንጹሕ በስሕተት ከሚታሠር ዐሥር ወንጀለኞች ቢለቀቁ ይሻላል የሚለውን የሕግ ምክር ተግባራዊ አድርጎ መጠቀም ነው፡፡
  ሌላው የሚነሣው ጉዳይ ደግሞ የካሣ ጉዳይ ነው፡፡ ‹በስሕተት ነው የታሠርከው› የተባለ ሰው ለተፈጸመበት ነገር ምን ሊደረግለት ይችላል? መንግሥትስ ለእነዚህ ሰዎች ካሣ ለመክፈል ኢኮኖሚያዊ ዐቅም አለው ወይ? የሚለውን የሚያነሡ አሉ፡፡ በስሕተት የተፈረደበት ሰው ኢኮኖሚያዊ፣ ሞራላዊና ማኅበራዊ ኪሣራ ያገኘዋል፡፡ ከሥራው ይወጣል፣ ንግዱ ይበላሻል፣ በሞያው ያፈራቸውን ደንበኞች ያጣል፡፡ ወንጀለኛ ተብሎ ስለተፈረደበት በማኅበረሰቡ ዘንድ ይገለላል፣ ስሙ ይጠፋል፣ ክብሩ ይቀንሳል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምክንያቶችም ሞራሉ ይነካል፡፡ የፍርዱ ዘመን ረዥም ከሆነም የማይተካው እድሜው ይወሰድበታል፡፡
  መንግሥት ለእነዚህ ነገሮች ሦስት ካሣዎችን ማዘጋጀት ይችላል፡፡ የሞራል፣ የማረሚያና የገንዘብ፡፡ የሞራል ካሣው ሰውዬው በስሕተት እንደታሠረ የሚገልጥ ማስረጃ(የምስክር ወረቀት) በመስጠት፣ አመቺ በሆነው ሚዲያ ወይም በአካባቢው ሊለጠፍ በሚችል ማስታወቂያ በስሕተት የታሠረ ንጹሕ ሰው መሆኑን በመግለጥ መካስ ይቻላል፡፡ የማረሚያ ካሣ ደግሞ ወደ ሥራው እንዲመለስ፣ በመታሠሩ ምክንያት ያጣቸው ጥቅሞች

  ReplyDelete
 22. እንዲከበሩለት፣ የተወሰደበት እንዲመለስለት፣ ያለፉት ነገሮች ካሉ እንዲሟሉለት ማድረግ ይችላል፡፡ የሀገሪቱ ዐቅም በሚፈቅደው መጠንም የገንዘብ ካሣ መስጠት ነው፡፡ መንግሥት በፍርድ ሂደት የሚያገኛቸው ገቢዎች አሉ፡፡ ከገንዘብ መቀጮዎች፣ ከውርሶች፣ ወዘተ፡፡ ከእነዚህ ሸረፍ አድርገው ሙሰኞቹ ከሚወስዱ ንጹሐኑ ቢካፈሉ ምን አለ?
  አንዳንድ ልሂቃን ‹የተወሰኑ የሕግ አካላት በሠሩት ስሕተት እንዴት መንግሥት ይቀጣል?› የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡ መንግሥት ድሮውንም በሰዎች የሚመራ መዋቅር ነው፡፡ መንግሥት የሾማቸው ሰዎች ለሚሠሩት ስሕተት አንዱ ተጠያቂም ራሱ መንግሥት ነው፡፡ ለዚህም ነው በሌሎች ሀገሮች የበታች አካላት ለሠሩት ስሕተት ከፍተኛ ኃላፊዎች ሥልጣን እስከ መልቀቅ የሚደርሱት፡፡
  ይህ በር እንደተዘጋ ከቀጠለ ግን ከባድ ማኅበራዊ ኪሣራ ያመጣል፡፡ ሰዎች ንጽሕናን እንዲጠየፉ ያደርጋል፡፡ ዘመኑ በተራቀቀበት በዚህ ወቅት ማስረጃዎችን መፈብረክ ቀላል ነውና አያሌ ንጹሐን ለዚህ በተዘጋጁ ማስረጃ ፈብራኪዎች እጅ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል፡፡ ያለ ሥራቸው ወንጀል ሠርታችኋል የተባሉትንም ለበቀል ያነሣሣል፡፡
  ሁለተኛውን ታሪክ እዚህ ላይ ላውጋችሁ፡፡ ሰውዬው በነፍስ ግድያ ተከሰሰ፡፡ በርግጥ ተኩሶ ሰው መትቷል፡፡ ሲተኩስም ሰዎች አይተውታል፡፡ በተኮሰበት ቦታም ደም ፈስሷል፡፡ ይህንን ሰውዬውም አልካደም፡፡ ምስክሮችም መስክረዋል፡፡ የሟች አስከሬን ግን ሊገኝ አልቻለም፡፡ ከተኩሱ ቦታ በታች ዝንጀሮ ብቻ የሚወርደው ገደል አለ፡፡ እዚያ ውስጥ ስለገባ ሊገኝ አልቻለም ተባለ፡፡ ተኳሹ ግን ‹በርግጥ ተኩሻለሁ ግን አልገደልኩትም› ብሎ ተከራከረ፡፡ ፍርድ ቤቱ የምስክሮችንና የማስረጃውን ነገር መዝኖ አምስት ዓመት ፈረደበት፡፡ ከዓመታት በኋላ ሞቷል የተባለው ሰው ሌላ መንደር እንደሚኖር ተሰማ፡፡ የታሣሪው ዘመዶችም ሄደው አረጋገጡ፡፡ ሰውዬው በጥይት ተመትቶ ነበር፡፡ ሲመታ ቢያውቀው ገደል ተንከባልሎ ገባ፡፡ በጋቢው ቁስሉን አሥሮ ገደል ለገደል ተንኳቶ ሌላ ሀገር ተደበቀ፡፡ እዚያ ጥይቱን አስወጥቶ ታክሞ ዳነ፡፡ ወደ መንደሩ ለመመለስ ስለፈራ ሌላ ቦታ ጎጆ ቀልሶ ተቀመጠ፡፡ ታሪኩ ይሄ ነው፡፡
  ታሣሪው ሰው ይህንን ሲሰማ አልተናደደም፡፡ እንዲያውም ደስ አለው፡፡ ‹ለማንም አትናገሩ› ብሎ ዘመዶቹን አስጠነቀቀ፡፡ አምስት ዓመቱን ጨረሰና ከወኅኒ ቤት ወጣ፡፡ ጠመንጃውን ወለወለ፣ ጥይቱን አቀባበለ፡፡ ‹ሟች› ይኖርበታል ወደተባለው ሥፍራ ሄደና ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ተኩሶ ገደለው፡፡ ሲገድለው ሰው አይቷል፡፡ እርሱም አልተደበቀም፣ ቤቱ ነው የተቀመጠው፡፡ ፖሊስ ግን እንዴት ይክሰሰው፡፡ አንድ ሰው ሁለት ጊዜ ሊሞት አይችልምና፡፡ በፍርድ ቤት ውሳኔ አሁን የተገደለው ሰው ከሞተ አምስት ዓመት አልፎታል፡፡ ይፈረድበት ቢባልም በአንድ ወንጀል ሁለት ጊዜ ፍርድ የለም፡፡ የተዘጋ የፍትሕ በር ዕዳው ይኼ ነው፡፡

  ReplyDelete
 23. Are these guys ISIS members or the followers of Jesus Christ?

  ReplyDelete
 24. Are these guys ISIS members or the followers of Jesus Christ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. it is clear that you are working to destroy our church; that is why you always blindly talk false information about MK, the backbone of church. If you have real information why do not you tell us his position in mk and other information rather that categorizing every person who commit crime as MK member.You know what we , the son of tewahedo, will fight you, devils, till end of our life. no one stops us from chasing you where ever you are.

   Delete
 25. "Selamawoch" we are waiting the photo of the said guy.

  ReplyDelete
 26. ለመሆኑ ከነፍስ ማጥፋት ሌላ ምን ቁም ነገር ሊሠሩ ትጠብቃለህ ከማቅ ቁምነገር አይገኝምና አትድከሙ። ጀግናው አባ አፈወርቅ የእግዚአብሔር ባርያ ስለሆኑ ፈተና ይመጣል ፈተናውን ያልፋሉ። የሚያሳዝነው ድስቱን ጭኖ አምላኩን እና ወዳጆቹን ክዶ የማቅ ባርያ የሆነው ሳዊሮስ የሚባል ከሀዲ ነው። የአቡነ ሳዊሮስ ጉድ በቅርብ ቀን አደባባይ ይወጣል። ጠብቁ። በቅርብ ቀን የሳዊሮስ እና እንዲሁም የአቡነ ዲስቆሮስ እና የቅምጣቸው የወይዘሮ ፅጌረዳ ጉዳይ በቅርብ ቀን። ፅጌረዳ ቤተክህነት ሂሳብ ሰራተኛ። አባ ሳዊሮስ የኦሮሞ ሲኖዶስ አቁቁማለሁ እያሉ የተናገሩት በድምፅ ማስረጃ ይሰሙታል። እስከዚያው ቸር ይግጠመን።።።።።።

  ReplyDelete
 27. ለመሆኑ ከነፍስ ማጥፋት ሌላ ምን ቁም ነገር ሊሠሩ ትጠብቃለህ ከማቅ ቁምነገር አይገኝምና አትድከሙ። ጀግናው አባ አፈወርቅ የእግዚአብሔር ባርያ ስለሆኑ ፈተና ይመጣል ፈተናውን ያልፋሉ። የሚያሳዝነው ድስቱን ጭኖ አምላኩን እና ወዳጆቹን ክዶ የማቅ ባርያ የሆነው ሳዊሮስ የሚባል ከሀዲ ነው። የአቡነ ሳዊሮስ ጉድ በቅርብ ቀን አደባባይ ይወጣል። ጠብቁ። በቅርብ ቀን የሳዊሮስ እና እንዲሁም የአቡነ ዲስቆሮስ እና የቅምጣቸው የወይዘሮ ፅጌረዳ ጉዳይ በቅርብ ቀን። ፅጌረዳ ቤተክህነት ሂሳብ ሰራተኛ። አባ ሳዊሮስ የኦሮሞ ሲኖዶስ አቁቁማለሁ እያሉ የተናገሩት በድምፅ ማስረጃ ይሰሙታል። እስከዚያው ቸር ይግጠመን።።።።።።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Abune Sawirosen Jegena belachehu sitawedesu alnebere ende? Tadia "Harateka Menafekanen" siletekawemu aselalefachehun keyerachehu?

   Delete
 28. geleba becha!!!!!!

  ReplyDelete
 29. እባካችሁ ስራችሁን እወቁ ይህ ነው ስራችሁ በቅርብ ጊዜ ነበር ድረ ገፃችሁን ያየሁት

  ReplyDelete