Tuesday, May 3, 2016

የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት አለቆች በማቅ ላይ ተፈራረሙለረጅም አመታት ብዙ አባቶች እና ወንጌላውያን ከ1986 ጀምሮ የተሳደዱበት የተንገላቱበት እንዲሁም የተገደሉበት የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት አሁን ያበቃለት እንዲሁም ከማህበረ ቅዱሳን ነጻ የወጣ ይመስላል። የሁልጊዜውን መዝሙር እየደረሰ የሚያቀርበው ማቅ አሉቧልታውን ሳይቀይር ያው ተሃድሶ እያለ ግጥሙንም ዜማውንም ሳይቀይር አመት አመት የሚጮኸውን ተሃድሶ እየዘፈነ ሲመጣ አኳኋኑ የገባቸው የገዳማት እና የአድባራት አለቆች ሁልጊዜ ተሃድሶ ምንድነው? አስኪ አንድ ቀን መልካም አስተዳደር ስነ ምግባር ብላችሁ ቀይሩት ቢሏቸው የነሱን ሃሳብ ወደ ጎን በመተው ንጹሀንን የቤተክርስቲያን ልጆችን ለማሳደድ አሁንም ተሃድሶ ብለው ተነሱ በዚህም ምክንያት ይመስላል የኔ የሚሏቸው አለቆች እንኳን ሳይቀሩ ተፈራርመው ለድሬዳዋ  ሀገረ ስብከት በማቅ ላይ አንድ እርምጃ ይወሰድልን በማለት አመልክተዋል በዚም መነሻ በማድረግ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በወጣቶች እና በወንጌላውያን የተዋቀረ እንደመሆኑ መጠን አራት ጉዳዮችን አሟልቶ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዳንኤልን እየጠበቀ ይገኛል፡፡
1.     በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙትን ለምስራቅ ኢትዮጵያ ውንጌል መስፋፋት ትልቅ ድርሻ ያበረከቱትን እና የድሬዳዋ ልጆች የሆኑ ወጣት ሰባኪያንን ሲያሳድዱ የነበሩትን የማህበሩ አባላትን ቀሲስ ሀድስ ኪዳን ማርያምንና ማቲያስ በቀለ ላይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተወስኖ ሊቀ ጳጳሱን እየጠበቀ ይገኛል
2.    እነዚሁ አለቆች ባደረጉት ማጣራት የማይጾመው የማይቀድሰው የማያስቀድሰው የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጂ መጋቢ ሰናያት ሀይለማርያም ሁልጊዜ ወገናዊነቱን ለማህበረ ቅዱሳን እያሳየ የቤተክርስተያን ልጆችን እየበደለ ስለማይዘልቅ እንደሁም ሊቀ ጳጳሱ የሚሰጡትን መመሪያ ተግባራዊ ስለማያደርግ ብቻ ሊቀ ጳጳሱም በተደጋጋሚ ቢመክሩት ቢመክሩት እንደውም አንድ ቀን ከነዚህ ከማህበረ እኩያን እየዶለትክ አትምጣብኝ አስተዳደሬን አትረበሽብኝ ቢሉት አልሰማ በማለቱ ሊቀ ጳጳሱ ሲመጡ ሀገረ ስብከቱን የሚመጥን ሰው እሳቸው ባይኖሩም ሊተካቸው የሚችል ሰው ይተካል ተብሎ ይታሰባል
3.    የማቅ አባለት የድሬዳዋ ወጣቶች ነን በማለት ለመንግስት አካላት አስገብተውት የነበረው የክስ ደብዳቤ በሀገረ ስብከቱ በታማኝነታቸው እና በትልቅነታቸው የተመሰከረላቸው የሀገረ ስብከቱ የስራ ሀላፊዎች ወደ መንግስት በማቅናት መተማመን ላይ ተደርሷል እንደውም ማህበሩ በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ተቀብሯል 

4.    አንዳንድ አዋቂ ነን ባዮች ምንም ግን የማያውቁ ሁልጊዜም እነሱ ከሚሉት ዝባዝንኪ ውጭ ወንጌል የተሰበከ የማይመስላቸው የመጸሃፍት መምህራን ነን የሚሉ እንዳንድ ግለሰቦች ከማህበሩ እየተደጎሙ ሀገረ ስብከቱን ለመበጥበጥ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውዳሴ ማርያም ያልደገሙ እያሉ የሀገረ ስብከቱን የስራ ሃላፊዎች መተቸታቸው ስለተደረሰበት መረጃ በማጠናከር ለሊቀ ጳጳሱ ለማቅረብ ተዘጋጅቶ ይገኛል የሰንበት ት/ት ቤት አባላትን በመከፋፈል አላማን ለመሳካት የተደረገው ሙከራ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል በተለይ በዚህ ረገድ የሀገረ ስብከቱ የህግ ክፍል ያደረጉት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነበረ ለዚህ ሁሉ ዘመቻ መክሸፍ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የድሬዳዋ አድባራት እና ገዳማት አለቆች ታሪክ የማያልፈው ትልቅ ድርሻ ተወጥተዋል ከነዚህም ውስጥ ደግሞ ትልቁን ድርሻ የሚይዙት ጀግናው የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል አለቃ የመጀመሪያው ሲሆኑ ከመቸውም ጊዜ በላይ ደግሞ ለወትሮው ለማቅ ቁርጠኛ የነበሩት የድሬዳዋ ማርያም አለቃ መላከ ገነት አባ ሀይለ መስቀል  ደግሞ ከሁሉም የበለጠ ነበር እንደውም አንዳንድ ግለሰቦች ማቅ አለቀለት ቁርጠኛ አባላቱንም አጣ ነበር ብለዋል።
 እኛም እንዲህ ነው ለእውነት መቆም እንላለን አሁንም ደግመን የምናገረው አባቶች እንዳስቡበት የምንለው ማቅን የመታገሉ ሒደት ተጀመረ እንጂ አላለቀም እንዳትዘናጉ ነው ማቅ የሚያንቀላፋ ይመስላል እንጂ አይሞትም  ይህ በዚህ እንዳለ ኪሳራ ውስጥ የገባው ማቅ እንደተለመደው ዘመቻውን ይዞል አዋሳ ላይ አድርጎት የነበረውን በሚካኤሉ አለቃና አንዳንድ ወጣት ሰባኪያን ላይ የሀሰት ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት ቅጥረኞቹን ሰብስቦ ሲወያይ እንደነበረ ተሰምቷል  በዚህ እንዳትሸማቀቁ የበለጠ ለትግል ተነሱበት እያልን በመጨረሻም ለብፁእ አቡነ ዳንኤል የምናሳስበው ይህ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ለዛሬው ድል የበቃው በብዙ አባቶች መስዋዕትነት እንደሆነ አውቀው አባቶች የሚሉትን በማስተማር ተትሉን እንዳያዳክሙት እንዲሁም እየቀደሙ እንዲያስተካክሉት እና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲሰጡት ነው የምንመክረው እራሱን እያራባ ወንጌል እንዳይሰበክ እንቅፋት ሲሆን የነበረውን እንደውም አቡነ ማቲያስ እንዳሉት ቤተክርሰቲያንን ቅኝ ሲገዛ የነበረውን ማቅን በማስወገድ ታሪክ እንዲሰሩ ነው የምንመክረው ይህንን ለማስተካከል በሚያደርጉት ትግል ደግሞ እኛ የድሬዳዋን ነጻነት ናፋቂዎች ከጎንዎ መሆናችንነ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው ፡፡
                                          እንግዳ ነኝ ከድሬዳዋ

18 comments:

 1. deskuram zore bel woregna

  ReplyDelete
 2. እነዚሁ አለቆች ባደረጉት ማጣራት የማይጾመው የማይቀድሰው የማያስቀድሰው የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጂ መጋቢ ሰናያት ሀይለማርያም ሁልጊዜ ወገናዊነቱን ለማህበረ ቅዱሳን እያሳየ የቤተክርስተያን ልጆችን እየበደለ ስለማይዘልቅ እንደሁም ሊቀ ጳጳሱ የሚሰጡትን መመሪያ ተግባራዊ ስለማያደርግ ብቻ ሊቀ ጳጳሱም በተደጋጋሚ ቢመክሩት ቢመክሩት እንደውም አንድ ቀን ከነዚህ ከማህበረ እኩያን እየዶለትክ አትምጣብኝ አስተዳደሬን አትረበሽብኝ ቢሉት አልሰማ በማለቱ ሊቀ ጳጳሱ ሲመጡ ሀገረ ስብከቱን የሚመጥን ሰው እሳቸው ባይኖሩም ሊተካቸው የሚችል ሰው ይተካል ተብሎ ይታሰባል....... tsome endete new enanete ayasefelegeme eyalacho endete new lela sew yetsomale ahyetsome mahletene min ametawe aba leboche

  ReplyDelete
 3. ሰላም የሌላችሁ ሰላምን የማታወሩ ከሃዲዎች ናችሁ አባሰላማ የሚለው ስም ለእናንተ የሚገባ አይደለም መናፍቃን እና ግን ከማህበሩ ከማህበረ ቅዱሳን ጎን ነን

  ReplyDelete
 4. bizu anawora ewonet ena chis mewecha ayatam

  ReplyDelete
 5. Tulutula...... nachih

  ReplyDelete
 6. አይ ሃራጥቃ አዳሜ ትታወቂያለሽ እኮ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የምትሰሪው ሥራ አሁን ሞኝ የለም አዎ እናውቃለን ድሬዳዋ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ቤ/ክንን አሳልፈው ለመስጠት ከተዘጋጁ ሆዳቸው አምላካቸው ከሆነ የደብር ዐለቆች ጀምሮ እስከ ሰ/ትቤት ውስጥ የተለየ ተልዕኮ ኖራችሁ የምትሰሩ ማንነታችሁ እስከ ሥራቸሁ ይታወቃል አይዞን ቀኑ ደርሳል የምትለዩበት

  ReplyDelete
 7. አንቺን ማን ነው የቀጠረሽ 100000 ኩንታል ውሸት እንድትዘባርቂ????

  ReplyDelete
 8. Why always do you mention MK? I am really tired of this.

  ReplyDelete
 9. Mk bertu,yemenafekan qitregna ena musegna,lebete kirstian yemaytekim selehone ayzoachihu bertu, telat yewedkal. Egziabhere Hailachin newe!

  ReplyDelete
 10. Yebete kirstian telatoch ywedikalu,mk bertu!
  Egziabher Hailachin newe!

  ReplyDelete
 11. ebakachihu endihu sera sanisera geta endaymeta ayselchenim wei menakoru min yitekimal eski wongelin enanibib.Mahibere kidusan tehadiso... minamin eyetebabalin keminibala hulachinim ye Orthodox lijoch kehon metalat metemamat ayasefeligim.atifim kale yene abal new sanil erimija eniwused. Bergit tehadiso hono Orthodox negn malet tegebi adelem tehadiso kehone wede gibir abatih wede Pente mahiber betekirstyanachinin lekeh hid atinetarek. Mahibere Kidusan bizu eniken binorewum biyanis be eminet aytamam selezih ketehadiso gar menetsatser aychilim.

  ReplyDelete
 12. ይሄ ታዲያ ምን ይደንቃል? አይሁዶችም እኮ በኢየሱስ ላይ ተፈራርመው ነበር።

  ReplyDelete
 13. በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረግ ሴራን እያየን የምናልፈው ሆኖ አልተገኘም። ዝም አንልም። እውነተኛ አባቶች፥ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች፥ ምዕመናን እና ማኅበረ ቅዱሳን አባላት ባሉበት ዘመን አይሳካላችሁም ተስፋ ቁረጡ።

  ReplyDelete
 14. የድሬዳዋ ከተማ ለሃይማኖታቸው ቀናኢ ለአምላካቸው ታማኝ የሆኑ ምዕመናን ያሉባት ከተማ ናት። የተሃድሶ ምንጩ ምሥራቁ መሆኑ ሳይዘነጋ ስራ በመስራት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቤተ ክ/ን ሰላም ለማምጣት ምዕመናን ከእውነተኛ የቤተ ክ/ን ልጆች ጎን ልትቆሙ ይገባል። የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋ አይለወጥም ፥ አናንተ ተሃድሶዎች እንዳላችሁት ካቴድራሎች የናንተ አይሆኑም!አትወርሱም!ክፉ አሳብ ክጠላት እንደሆነ እናውቃለን። የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ከክፉ የሆነውን ሃሳባችሁን ይበትንባችሁ!

  ReplyDelete
 15. ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን
  ጥንታዊት ሐዋርያዊት ናመሲሀዊት ዓለምአቀፋዊት
  የሆነች ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ትጽልናን
  ዘመን የወለዳቸው ሁሉ ያጥልፋን

  ReplyDelete
 16. ከንቱ ድካማችሁ አሳዘነኝ ምክንያቱም አንድ የሚደግፋችሁ comment አላማየቴ

  ReplyDelete
 17. ስራስኪያጁን ማነው የቤተክርስቲያን ሰው ያደረጋው የደረገው እሱ አይበልጥም እንደ ቤተክርስቲያንን በማጥፋት የማህበረ ቅዱሳን አባል ለማድረግ አትሞክር እንደውም ተሃድሶዎቹ የታወቀ ነው ሀሳባቸው እሱ ገን ምኑም የማይታወቀወ ድንጋይ ነው እራሱን መግለጥ እንኮን የማይችል መሀይም ነው እሱ በማህበረ ቅዱሳን መታሰብ የለበትም እንድሁ ልታስወግዱት ካሰባችሁ በሉት እሱ ለናንተም ለማህበረ ቀረዱሳንም አይመጥንም

  ReplyDelete
 18. MK's days are numbered. EPRDF WILL BREAK MK's BACKBONE ONCE AND FOR ALL. OUR CHURCH WILL BE FREE FROM MK's TUGS.

  ReplyDelete