Tuesday, May 10, 2016

መሪው ተመሪ ተመሪው መሪ የሆነባት ቤተክርስቲያን መጨረሻዋ ጥፋት ነውቤተ ክርስቲያን ሁሉም ድርሻውን አውቆ ግዴታውንና ኃላፊነቱን የሚወጣባት የሥርዓት ቤት ናት፡፡ በዚሁ መሠረት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ቀሳውስትና ዲያቆናት ለምእመናን ሃይማኖትን ሊያስተምሩ በትክክለኛው መንገድ ሊመሩ፣ ምእመናን ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነውን ትምህርታቸውን ሊቀበሉና ለአመራራቸው ራሳቸውን ሊያስገዙ፣ በሌላውም እነርሱን በሚመለከተው ጉዳይ ላይ ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው፡፡ ይህን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዛሬ ግን አንዳንዶች ይህን አምላካዊ ሥርዓት ለመለወጥ ባለ በሌለ ኃይላቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት ግን ይህ አምላካዊ ሥርዓት እየተጣሰ መሪው ተመሪ ተመሪው ደግሞ መሪ እየሆነ ሥርዓት አልባነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰፈነ ይገኛል፡፡ የዚህ ውጤትም ውሎ አድሮ እውነተኛው የሃይማኖት ትምህርት በሌላ የስሕተት ትምህርት እንዲለወጥ፣ አምላካዊው ሥርዓትም ፈርሶ በስፍራው የሰው ሥርዓት ምናልባትም ሥርዓት አልበኛነት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትና እርሱን የሚያስተምሩ መምህራን የሚሉት ሳይሆን ምእመናን ከቃሉ ውጪ ለሃይማኖት ባላቸው ቅንዓት በተሳሳተ መንገድ የተቀበሉትና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲሆንላቸው የሚፈልጉት እንግዳ ትምህርት ተቀባይነት እንዲኖረው በር ይከፍታል፡፡
ይህ አካሄድ በተለይ ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በደንብ ሲሠራበት የኖረና ውጤቱ አሁን በመታየት ላይ የሚገኝ አደገኛ አካሄድ ሆኗል፡፡ ቀድሞ በእግዚአብሔር መሠረትነት እውነተኛ የተባሉት ትምህርቶች ዛሬ እንደ ኑፋቄ እየታዩና ብዙዎችን እያስወገዙ ናቸው፡፡ በሊቃውንቱ ዘንድ በኑፋቄነት ተፈርጀው የነበሩት የስሕተት ትምህርቶች ደግሞ ዛሬ ላይ እንደ ትክክለኛ ትምህርት እንዲታዩ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ወደየት እያመራች እንደሆነ መገመት ቀላል ነው፡፡

በተለይም በውጭው ዓለም ባለች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ዘንድ እየታየ ያለው አካሄድ ምእመናን የመሪዎችን ስፍራ በመንጠቅ ለሃይማኖት ትምህርት ተጠሪዎችና መሪዎች እየሆኑ ሲሆን፣ መሪዎች ደግሞ በምእመናን የሚመሩ ተመሪዎች እየሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ መሪዎች የሃይማኖትን ትምህርት በማስተማርና ስለዚያ ተጠያቂ በመሆን መሪውን ካልጨበጡና ባለማወቅና ለሃይማኖት በመቅናት ስም ያለ ጸጋቸው ቤተ ክርስቲያንን እንምራ በሚሉ ሰዎች እጅ ከገባ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ቀውስ ውስጥ መውደቋ አይቀሬ ነው፡፡ በቅርቡ በካናዳ የተከሠተውና በየመረጃ መረቡ የተለቀቀው ቃለ ጉባኤና ደብዳቤ ፍሬ ሐሳብ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ እነ አቶ እና ወ/ሮ አለቦታቸው ገብተው ራሳቸው ከሳሽ፣ አጣሪና ዳኛ በሆኑበት ሃይማኖታዊ ጉዳይ ነገር እንዴት እንደተበላሸ መረዳት ይቻላል፡፡
በቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሐድሶ ተነሥቷል በሚል ራሳቸውን አደራጅተው በተሐድሶነት ጠርጥረናቸዋል ያሏቸውን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለማስወገዝና ከቤተ ክርስቲያን ለማስወጣት ታጥቀው የተነሡ ምእመናን በዲ/ን ወንድወሰን ሙላት በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ፣ በወ/ሮ ካተሪና በቀለ፣ በወ/ሮ ታደለች አየለ እና በአቶ ጌትነት አበጀ ላይ የያዙትን “ተሐድሶ ሆነዋል” የሚል አቋም ሕጋዊ ለማድረግ በሕዝብ ስም ራሳቸውን በመሰየም የጀመሩት አውጫጪኝ፣ ደረስንበት ያሉት ግኝት የሃይማኖት ትምህርት በእነርሱ ዘንድ ምን ዓይነት እንደሆነ መታዘብ የተቻለበትን ትልቅ አጋጠሚ ፈጥሯል፡፡ ሃይማኖትን ያህል ነገር ሃይማኖታዊ ዕውቀት የሌላቸው ምእመናን ሲይዙት ምን ያህል ወርዶና ተበላሽቶ እንደሚገኝ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሆኗል፡፡
እዚህ ላይ ችግሩ የሚጀምረው የሃይማኖትን ጉዳይ እነዚህ ምእመናን እንዲያጣሩ ከመደረጉ ነው፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ፣ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ እና ቄሰ ገበዝ ሕይወት በቀለ የኮሚቴው አባላት ቢሆኑም፣ ሌሎች ስምንት ምእመናንም የሃይማኖትን ጉዳይ እንዲያዩ መደረጉ አግባብነት አልነበረውም፡፡ ቁጥራቸው ስለበዛ ብቻ ሳይሆን የሃይማትን ምንነት በሚገባ የማያውቁ መሆናቸውን በቃለ ጉባኤያቸው ላይ ያሰፈሩት ሐሳብ ይመሰክራል፡፡ በቃለ ጉባኤያቸው ላይ እንዳመለከቱት እነርሱ ሃይማኖትን ወደማጣራት ሥራ የገቡት፣ የተሐድሶ ጉዳይ ምእመናኑን ስላሳሰባቸውና ነገሩ እንዲጣራላቸው ለሰበካ ጉባኤውም ሆነ ለቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር አቅርበው መፍትሔ ሊሰጥ ባለመቻሉ “በእግዚአብሔር ፈቃድ” እነርሱው እንደገቡበት ነው የተጠቆመው፡፡ በቅድሚያ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብሎ መቀበል ይቻላል ወይ? የሃይማኖትን ጉዳይ የሚያስተምሩና ችግርም ካለ የሚመረምሩ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ናቸው እንጂ ምእመናን አይደሉም፡፡ ለቤተ ክርስቲያን መምህራንን የሰጠ እግዚአብሔር (ኤፌ. 4÷11) ምእመናን የሃይማኖትን ጉዳይ እንዲያጣሩ ፈቃድ የሰጠበት መንገድ የለም፡፡ ስለዚህ የራስን ፍላጎት የእግዚአብሔር ፈቃድ አድርጎ ማቅረብ በእግዚአብሔር ስም ከመዋሸት ውጪ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የራሳቸው የሆነ ሚናና ድርሻ አላቸው፡፡ ድርሻቸው ግን በምንም መልኩ ሃይማኖታዊ ጉዳይን ማጣራት ሊሆን ከቶ አይችልም፡፡ የሃይማኖትን ጉዳይ ለመምህራኑ ቢተዉ የተሻለ ነበር፡፡ ነገር ግን ያለ አንዳች ዕውቀት ሃይማኖትን ለማጣራት እነርሱው ስለገቡበት ብዙ ስሕተቶችን ፈጽመዋል፡፡ እውነተኛውን ትምህርት ስሕተት ብለዋል፡፡ የተሳሳቱትን ትምህርቶች ደግሞ እውነተኛ አድርገዋል፡፡ ለቤተ ክርስያን ከዚህ በላይ ውድቀት የለም፡፡
ምእመናን መራሹ አጣሪ ኮሚቴ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን የዕውቀታቸውን መጠን በእነርሱ አነጋገር “ሥላሴዎች” እንደገለጹላቸው ነው የመሰከሩት፡፡ ይህ ግን ራሳቸውን ታማኝ ለማድረግ የተጠቀሙበት አገላለጽ ከመሆን አያልፍም፡፡ መርምረናል ያሉትን ሃይማኖታዊ ጉዳይ ምንነት ስንፈትሽም አለን የሚሉትን ዕውቀት እንኳን እግዚአብሔር ሊገልጽላቸው ከእውነተኞቹ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያልተማሩትና ሐሰተኞች ወደ ቤተ ክርስቲያን አሹልከው ያስገቡት የስሕተት ትምህርት መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ እግዚአብሔር እኮ ቃሉን አይቃረንም፡፡ እርሱ ፈቃዱንና ሐሳቡን፣ እውነተኛውንም ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገልጿል፡፡ ከእግዚአብሔር የተማረ ሰው ያንን እንጂ ከዚያ የሚቃረነውን የስሕተት ትምህርት ሁሉ ከእግዚብሔር ተምሬዋለሁ ቢል በእግዚአብሔር ለይ እየዋሸ ነው፡፡
እነዚህ ምእመናን አጣርተናል በማለት ያቀረቡት ግኝት ዶግማና ቀኖና ተጥሷል የሚል ነው፡፡ አንዳንዶቹ ተከሳሾች ዶግማን፣ አንዳንዶቹ ቀኖናን አንዳንዶቹ ደግሞ ሁለቱን ጥሰዋል ነው የሚለው ቃለ ጉባኤው፡፡ ነገር ግን ወደታች ዝቅ ብለን አገኘነው የሚሉትን ግኝት ስንፈትሽ አንድም የዶግማም ሆነ የቀኖና ነገር መመልከት አልተቻለም፡፡ እንደሚታወቀው ዶግማ የማይለወጠው መጽሐፍ ቅዱሳዊው እና በእግዚአብሔር ባሕርይና ግብር ላይ የተመሠረተው አስተምህሮ ነው፡፡ በዋናነትም ትምህርተ ሥላሴና ትምህርተ ሥጋዌ ናቸው፡፡ ሌሎቹም ይህን የመሰሉ የእምነት አቋሞች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ይህን የተመለከተ አንድም ነጥብ ግን በቃለ ጉባኤው ውስጥ አላነበብንም፡፡ ስለዚህ ምእመናኑ ስሙን እንጂ ምንነቱን በውል የማያውቁትን ዶግማን ጠቅሰው ዶግማ ተጥሷል ሲሉ፣ በባዶ ሃይማኖታዊ ቅናት የሚያሳፍርና አንገት የሚያስደፋ ስሕተት ነው የፈጸሙት፡፡
በዲያቆን ወንድወሰን ሙላት ላይ ዶግማን በተመለከተ አገኘነው ያሉት ኑፋቄ ከተዋሕዶ እምነታችን ጋር የሚጻረሩ መጻሕፍትን ማንበብና ማሠራጨት የሚል ነው፡፡ አንባብያን እስኪ ፍረዱ እውን ይህ ዶግማ ነው? ሰው መጽሐፍ አነበብክ ተብሎ ዶግማን ጥሰሃል እንዴት ይባላል? መጽሐፍ ማንበብ ዶግማን መጣስ የሆነው በየትኛው የቤተ ክርስቲያን ሕግ ነው? እነዚህ ምእመናን ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንደማይኖራቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ዲያቆን ሌላው ጥሷል የተባለው ቀኖና ሲሆን እርሱም በቅዱሳን አባቶቻችን እና በቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት ላይ ያለው የተሳሳተ አመለካከትና የሚሰነዝራቸው ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ቃላት ጉድለት ነው ይላል፡፡ ምን ማለት ይሆን? የተሳሳተ ነው የተባለው አመለካከት ምንድነው? የተሳሳተ መሆኑ በምንድነው የተመዘነው? አመለካከት እምነት ካልሆነ  እንዴት ስሕተት ሊሆን ይችላል? አመለካከት ቀኖና ነው ያለው ማነው? ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ቃላት የተባሉትስ የትኞቹ ናቸው? ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ቃላት የቀኖና ጥሰትን ያመጣሉ የተባለው በምን መሠረት ነው? ምእመናኑ ኦርቶዶክሳዊ ያሏቸው ቃላት ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ይበልጣሉ ወይ? በእነዚህ ጥያቄዎች እንኳን ቢፈተሹ የቀረበው የምእመናኑ ግኝት የዶግማም ሆነ የቀኖና ጥሰት ሊባል ቀርቶ የመንደር ወሬ ከመሆን የማያልፍ ነው፡፡ ምእመናን የሃይማኖትን ጉዳይ እንይ ሲሉ የሚያጋጥመው ችግር እንግዲህ ይህ ነው፡፡ 
በሌሎቹም ላይ የቀረበው ማብራሪያ በደፈናው ቀኖና ቤተክርስያን ተጥሷል የሚል ነው፡፡ ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ በነገረ መለኮት አስተምህሮ ላይ “በቀኖና ቤተ ክርስቲያአን አስተምህሮ ላይ ግን መዛባትና ስሕተት” ፈጽመዋል ይላል፡፡ ሦስቱ የሰንበት ት/ቤት መዘምራንም በተመሳሳይ በቀኖና ላይ ስሕተት ፈጽመዋል ነው የሚለው፡፡ ይሁን እንጂ የትኛውን ቀኖና እንዳፈረሱ በግልጽ አላስቀመጠም፡፡ ሆኖም በመጨረሻው ላይ “ግኝታችን” ብለው ባቀረቧቸው ሦስት ነጥቦች ውስጥ ቀኖና ፈረሰ ብለው የጠቀሱት ስለማርያም እንዲሁም ስለ አዋልድ መጻሕፍትና በዚያ ላይ ተመሥርተው ስለሚተላለፉት ትምህርቶች ነውና ፈረሰ ያሉት ቀኖና በመጽሐፍ ቅዱስም በቤተ ክርስቲያን ትምህርትም ስሕተት የሆኑትንና እነርሱ ግን ትክክለኛ ለማድረግ የሚፈልጉትን የስሕተት ትምህርት መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም፡፡
የመጀመሪያው ተጣሰ የሚሉት ዶግማ “በፍርድ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እውነተኛውን ፍርድ የሚፈርደውን አምላክ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስን አሁንም አማላጅ ነው ብለው የሚያምኑ ስለሆነ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማታችን ጋር በምንም መልኩ አይመስሉንም፡፡” በሚል የቀረበ ነው፡፡ ይህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተቀነቀነ የመጣና እውነተኛውን መጽሐፍ ቅዱሳዊም ኦርቶዶክሳዊም ትምህርት የለወጠ፣ የክርስቶስን የሊቀ ካህናትነት ስፍራ ለፍጡራን ለመስጠት ሲባል ለስሕተት ትምህርት የተሠዋ እውነት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን አስታራቂ ወይም መካከለኛ ወይም አማላጅ መሆኑን በግልጽ ይናገራል፡፡  
ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር በሥጋ በሚመላለስበት ጊዜ ምልጃ ማቅረቡን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል (ዮሐ. ምዕራፍ 17 በሙሉ፤ ሉቃ. 22፥31-32)፡፡
መጽሐፈ ቅዳሴ ላይም “አንቃዕደወ ሰማየ ኀበ አቡሁ፥ ወአስተምሐረ ወላዲሁ፥ ወአማሕጸነ አርዳኢሁ ከመ ይዕቀቦሙ እም ኵሉ እኩይ”
ትርጉም “ወደ ሰማይ ወደ አባቱ ቀና ብሎ አየ፤ ወላጅ አባቱንም ማለደ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ከክፉው ሁሉ ይጠብቃቸው ዘንድ አደራ አስጠበቀ” የሚል ተጽፏል፡፡ (ቅዳሴ ማርያም)፡፡
በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለም ወደ አባቱ ምልጃን እንዳቀረበ የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ይመሰክራሉ (ኢሳ. 53፥12፤ ሉቃ. 23፥34፤ ዕብ. 5፥7)፡፡
ሃይማኖተ አበው ላይም ይህንኑ የተመለከተ ሐሳብ ሰፍሯል “ወሰአሎ ለአብ ያኅልፍ እምኔነ መዓተ ዘረከበነ እም ቅድም ከመ ዘለሊሁ ይኌልቍ ስእለተ ሎቱ እስመ ውእቱ ነሥአ አምሳሊነ ከመ ይስአሎ ለአብ በእንቲኣነ ከመ ምዕረ ዳግመ ይዝክረነ ወኢይኅድገነ እምኔሁ።”
ትርጉም “እርሱ ለራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው። እንደ ገና ደግሞ እንዲያስበን ከእርሱም እንዳይለየን ስለ እኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባሕርያችንን ነሥቷልና” (ሃይማኖተ አበው ገጽ 324)፡፡
ምናልባት ከዚህ በላይ በቀረቡት ማስረጃዎች ሁሉም ሊስማማ ይችላል፡፡ ልዩነቱ ያለው ግን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣና ወደሰማይ ካረገ በኋላ ኢየሱስ በቀደመው ምልጃው አሁንም አስታራቂያችን እርሱ መሆኑን የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው ለማስተባበል የሚፍጨረጨሩት፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣና ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ መውደቅ መነሣት ሳይኖርት በቀደመ ልመናውና አንድ ጊዜ ባቀረበው መሥዋዕት አማካይነት እንደሚማልድ የሚከተሉት የመጽፍ ቅዱስ ክፍሎች ያስረዳሉ፡፡ ሐዋርያቱ የክርስቶስን ምልጃና ጠበቃነት የገለጹት በኃላፊ አንቀጽ ሳይሆን በትንቢት አንቀጽ ነው (ሮሜ 8፥34፤ ዕብ. 7፥25፤ 1ዮሐ. 2፥1)፡፡ እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክሮች ባገናዘበ መልኩ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትም ኢየሱስ ወደሰማይ ካረገ በኋላ ምልጃው እንደሚቀጥል መስክረዋል፡፡  
“ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አዓርግ ኀበ አቡየ ወእስእሎ በእንቲአክሙ”
ትርጉም “ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ አባቴ ዐርጋለሁ ስለ እናንተም አለምነዋለሁ አላቸው፡፡” (ድጓ ገጽ 291)፡፡
“ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አዐርግ ሰማየ ኀበ አቡየ ኀበ እስእል ምሕረተ በእንተ እሊአየ”
ትርጉም “ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የኔ ስለሆኑት ምሕረትን ወደምለምንበት ወደ አባቴ ወደ ሰማይ ዓርጋለሁ አላቸው።” (ድጓ ገጽ 113)።
“ኦ ወልድ ክላሕ ከመ ዘሐመ ወበል ላማ ሰበቅታኒ ኤልማስ፡፡ ወእንዘ ሀሎ ውስተ አፉሆሙ በል አባ ወአቡየ መሐር ወተሣሃል እለ በልዑ ሥጋየ ወሰትዩ ደምየ”
ትርጉም “ወልድ ሆይ እንደ ታመመ ሰው አሰምተህ ተናገር። ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ በል። በአፋቸውም ውስጥ ሳለ አባ አባቴም ሆይ፥ ሥጋዬን የበሉትን ደሜን የጠጡትን ማራቸው፤ ይቅር በላቸው በል።” (ቅዳሴ አትናቴዎስ ገጽ 119)።
ከላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም ከቤተክርስቲያን መጻሕፍት የቀረቡት ምስክርነቶች ኢየሱስ አሁንም መካከለኛችንና አስታራቂያችን መሆኑን ይመሰክራሉ፡፡ ታዲያ የቱ ነው ትክክል? የቱስ ነው ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት? እዚህ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ ብቻ ሳይሆን ፈራጅ ሆኖ መሾሙ እውነት ነው፡፡ እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ መካከለኛና አስታራቂ ሲሆን በዳግም ምጽአቱ ግን ለፍርድ ይመጣል፡፡
ሁለተኛው ተጣሰ የሚሉት ትምህርት የማርያምን ምልጃ ክደዋል፣ የቅዱሳንን የአማላጅነት ጸጋና የመላእክትን ተራዳኢነት ስለማያምኑ እኛን አይመስሉም በሚል የቀረበ ነው፡፡ የድንግል ማርያምም ሆነ የቅዱሳን አማላጅነት በኦርቶዶክስ ትምህርት መሠረት ምን ይመስላል? የሚለውን ለመመለስ የእነዚህ ምእመናን ዕውቀት በቂ እንዳልሆነ ካቀረቡት ሐሳብ መረዳት ይቻላል፡፡ ቤተክርስቲያኗ የቅዱሳንን ምልጃ በተመለከተ በተለይ በሊቃውንቱ ዘንድ ሲነገር የቆየው በማርያምም ሆነ በአንቀላፉ ቅዱሳን አሁን ልመና ወይም ምልጃ የለባቸውም በቀደመ ልመናቸው ስለሚያስምሩ ነው የሚል ሐተታ ነው የቀረበው ውዳሴ (ማርያም አንድምታ የሰአሊ ለነን ሐተታ ተመልከት)፡፡ ምእመና ግን ይህን ስለማያውቁት ካንቀላፉ ቅዱሳን ጋር በጸሎት በመነጋገር አማልዱን የሚል ከንቱና ሰሚ የሌለው ጩኸት ያሰማሉ፡፡
ያንቀላፉ ቅዱሳን በምልጃቸው የሚያገለግሉ ቢሆን ኖሮ በሕይወት በነበሩ ቅዱሳን ምትክ ሌሎች ባልተሾሙ ነበር፡፡ ለእስራኤል ልጆች መካከለኛ ሆኖ የቆመውና ሲማልድላቸው የነበረው ሙሴ ካንቀላፋ በኋላም መካከለኛነቱ ቢቀጥል ኖሮ ሌላ መካከለኛ ኢያሱ መሾም አያስፈልገውም ነበር፡፡ ነገር ግን እንዲያ ሊሆን ስለማይችል ሙሴ ሲያንቀላፋ ኢያሱ ተተካ፡፡ ሕዝቡም ኢያሱ ሲሾም ሙሴ ቢያቀላፋም በአጸደ ነፍስ መካከለኛችን እርሱ ነውና ሌላ መካከለኛ አያስፈልገንም አላም እንዲያውም “ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ እንሄዳለን። በሁሉም ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን ብቻ አምላክህ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።” በማለት ነው የመለሱት (ኢያ. 1÷16-17)፡፡ ታዲያ የተሳሳተው ማነው?
ከዚሁ ነጥብ ጋር ተያይዞ የተነሣው በማርያም ፊት የመላእክት አለቆች ከነሠራዊታቸው በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ እንደሚቆሙ የያሬድ የተባለውን ድርሰት ጠቅሰው ያቀረቡት ሐሳብ ከመምህራኑ መማር የሚገባቸው ምእመናን ያለ፡ቦታቸው ገብተው ለሃይማኖት ትምህርት ተጠያቂ ነን ሲሉ ምን ያህል ነገር እንደሚያበላሹ ከዚህ ሐሳብ እንረዳለን፡፡ መላእክት በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ የሚቆሙት በእግዚአብሔር ፊት ብቻ ነው፡፡ በማርያም ፊት እንዲህ ይቆማሉ የሚል ትምህርት ቤተክርስቲያን የላትም፡፡ ይህን ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አስደግፎ ማቅረብ አይቻልም፡፡ እንዲህ ዓይነት ትምህርት ይዘው የተገኙ መጻሕፍት በቤተክርስቲያን ውስጥ ቢገኙም እንኳን የሐሰት መጻሕፍት ናቸውና ተቀባይነት የላቸውም፡፡
በሦስተኛ ደረጃ ተጥሷል የሚሉት ስለአዋልድ መጻሕፍት ያላቸው አቋም ነው፡፡ እነርሱ “ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስ የሆኑ አዋልድ መጻሕፍትን ድርሳናትን ገድላትን ስለማይቀበሉ አንቀበላቸውም” ብለዋል፡፡ አክለውም በተሐድሶነት የፈረጇቸው አገልጋዮች ተረታ ተረት የሚሏቸው “ለእኛ ግን የጽድቅን መንገድ የሚያሳዩን መጻሕፍት” ናቸው ይላሉ፡፡ እዚህም ላይ ምእመናኑ ያለዕውቀት በሆነ ባዶ ቅናታቸው ነው ያሳዩት፡፡ አዋልድ መጻሕፍት በተለይም ገድላትና ድርሳናት ከቅዱሳን የሕይወት ተመክሮ የምናገኝባቸው መጻሕፍት መሆናቸውን ነው ሊቃወንቱ የሚያስተምሩት እንጂ የጽድቅን መንገድ የሚያሳዩ አይደሉም፡፡ የጽድቅን መንገድ የሚያሳየው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ የጽድቅ መንገድም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐ. 14፥6)፡፡ ገድላትና ድርሳናት ግን ይህን የጽድቅ መንገድ ሳይሆን የገድሉን ባለቤት ታላቅነትና በእርሱ ስም በሚፈጸሙ ድርጊቶች የሚገኘውን ጽድቅ ነው የሚሰብኩት፡፡ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጸው የእግዚአብሔር ጽድቅ ጋር ይቃረናል እንጂ አይስማማም፡፡ ስለዚህ የትምህርታቸው ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን ሌላ ነው፡፡ የትምህርታቸው ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ከሆነም እንኳን ልንቀበላቸው የምንችለው በመጽሐፍ ቅዱስ መዝነንና ትክክለኛ መሆናቸውን አረጋግጠን እንጂ በደፈናው አይደለም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ የቤተክርስቲያን ሕግ ይህን በደፈናው ተቀበሉ አይሉንም፡፡ እንዲያውም ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጪ የሆነውን ትምህርት የያዙትን አዋልድ መጻሕፍት ቤተክርስቲያን እንደማትቀበላቸው በፍትሐ ነገሥትናበሌሎችም መጻሕፍት ላይ ገልጣለች፡፡ በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 2 ላይ ቤተክርስቲያን የተቀበለቻውን መጻፍት ዝርዝር ማትም ብሉያትንና ሐዲሳትን ከዘረዘረ በኋላ የሰማንያ አሐዱ አካል ከሆኑት አንዳንዶቹን ጠቅሶ ሲያበቃ “እንድትጸኑባቸው ያዘዝናችሁ መጻፍት እነዚህ ናቸው፤፤ ከሐድያን ካስቀመቷቸው የሐሰት መጻሕፍት የወሰደና ንጽሕት የሆነች የእግዚአብሔር መጽሐፍ እንደሆነች አድርጎ ሕዝብን ለማሳሳት ወደ ቅዱስ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ያገባ ሰው ቢኖር ይለይ፡፡” ይላል፡፡ ሐሳ ግልጽ ነው ከመጽፍ ቅዱስ ውጪ የሆኑና ከእርሱ ትምህርት ጋር የሚቃረኑት መጻሕፍት ከሐድያን ያስቀመጧቸው የሐሰት መጻሕፍት ስለሆኑ እነርሱን ወደ ቤተክርስቲን ያገባ ሰው ከቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲለይ (እንዲወገዝ) ይደነግጋል፡፡ አሁን እየሆነ ያው ግን ይህ የቤተ ክርስቲያን ሕግ ይጠበቅ ያሉት እንዲወገዙ፣ የሐሰት መጻሕፍቱ እውነተኛ ናቸው ያሉት ደግሞ አውጋዥ የሆኑበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ ለዚህ አንድ ማሳያ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ሁሉም ሰው የሚያውቀው የበላኤ ሰብእ ታሪክ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ በላኤ ሰብእ ሰው በላ ከመሆኑም በላይ ሥላሴን የካደና በማርያም አማላጅነት ዳነ የተባለ ሰው ነው፡፡ ይህን የሚተርክልን ተአምረ ማርያም ነው፡፡ ይህንና ይህን የመሳሰሉ ታሪኮችን የያዘውንና በዚህ ገጽታው የሐሰት መጽሐፍ ተብሎ ሊፈረጅ የሚገባውን ተአምረ ማርያምን መቃወም ሊያስመሰግን እንጂ ሊያስወገዝ ባልተገባም ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ሕገ ቤተክርስቲያን ጠንቀቀው የማያውቁትና ያለቦታቸው የሃይማኖትን ጉዳይ ለመመልከት ራሳቸውን የሰየሙት ምእመናን እንዲህ ላለው የክሕደት መጽሐፍ ሽንጣውን ገትረው ቢሟገቱና የጽድቅን መንገድ የሚያሳየን ነው ቢሉ አይፈረድባቸውም፡፡ ለዚህ የዳረጋቻው አለማወቃቸውና አለማወቃቸውንም አለማወቃቸው ነው፡፡
በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ትገኛለች፡፡ ችግሮቹን እያባባሰ ያለው ደግሞ የሃይማኖትን ጉዳይ መምህራኑ ሳይሆኑ ምእመናኑ እንመልከት ማለታቸው ነው፡፡ የዚህም ውጤት እውነተኛው ትምህርት የሐሰት ትምህርት የሐሰቱ ትምህርት ደግሞ እውነተኛ ትምህርት መስሎ እንዲቀርብ እያደረገ ነው፡፡ ይህም ቤተ ክርስቲያንን ወደባሰ ጨለማ ይወስዳታል፡፡ መጨረሻዋም ጥፋት ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ መምህራን የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለው በምእመናን የተነጠቁትን የሃይማኖትን ትምህርት የመመልከት ጉዳይ መልሰው ከእጃቸው ሊያስገቡና ምእመናን በተገቢው መንገድና በሚመለከታቸው ጉዳይ ብቻ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስተማርና መስመር ማስያዝ አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ቤተ ክርስቲያን መከፋፈል ውስጥ ትገባለች ብዙ ሊጠቅሟት የሚችሉ ሰዎችን ታጣለች፡፡


9 comments:

 1. http://www.abaselama.org/2016/05/blog-post_10.html?m=1

  ኢየሱስ ክርስቶስ'ማማለድ'የሚለው ቃል ብዙወች እሚያስደነግጣቸው ቃሉ የኢየሱስን መለኳታዊነት/አምላክነት እሚነሳ ስለሚመስላቸው ነው። ስለ ሚስጢረ ስጋዌ (Incarnation) እና ሚስጥረ ስላሴ (Trinity) ጠለቅ ያለ እውቀት የሌለው ሰው (አብዛኛው ምእመን) በ ማቅ ውዥንብር መታወኩ አይቀሬ ነው።

  ሌላው ችግር የአማርኛ ቋንቋ ነው። በእንግሊዝኛው የክርስቶስን አስታራቂነት Mediation የጻድቃን አማላጅነት intercession እሚሉት ይገልጹታል። እኛ ጋር አስታራቂ እሚለው አማላጅ ከሚለው የክርስቶስን ስራ የበለጠ ይገልጻል ባይ ነኝ።

  ጥል/ጭቅጭቅ ስለምንወድ እንጅ ለነገሩ የጻድቃን እና የኢየሱስን ስራ አንድ ቃል እንኳን ብንጠቀም ያለው የሰማይና የምድር ያህል ልዪነት ለሁላችንም ግልጽ መሆን ነበረበት።

  የኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂነት በማንም በምንም ሊተካ እማይችል በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን መለያየት እግዚአብሔር ወልድ እኛን ሁኖ
  1. ሰው ራሱን በእግዚአብሔር ፊት defend ማድረግ ስላልቻለ incarnated God Jesus Christ ጠበቃ ሁኖ፤
  2. ሰው በቂ መስዋእት ማግኘት ስላልቻለ incarnated God Jesus Christ መስዋእት ሁኖ፤

  3. ሰው የልዪነቱ የጥሉ party ስለሆነ መስዋእቱ ለማቅረብ እጁ ንጹህ ስላልሆነ
  incarnated God Jesus Christ ሊቀ ካህን ሁኖ፤
  በመስቀል ላይ የተረገውን ስራ ከቅዱሳን ምልጃ ጋር ምንም ህብረት የለውም።

  ሌላው በዝህ ጹህፍ ላይ ስለ ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ አያማልዱም እሚለው የ Protestant አስተምህሮ ነው። ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ በህወትም እያሉ በአጸደ ነፍስ ይጸልዪልን/ያማልዱን ዘንድ እንጠይቃቸዋለን ። ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ጻድቃን ሲያርፉ ከኛ ጋር ህብረታቸው አለቀ ብለን አናምንም። በሁለት ከተማ እምንኖር፤ ስሪቸውን የፈጸሙ እና ገና በስራ ላይ ያሉ ፤ ግን በክርስቶስ የተቆራኘን አንድ ቤተሰብ ነን።

  ይህን አስተምህሮ ሁለም Oriental Orthodox Churches እሚቀበሉት ነው። አባ ሰላማወች በዝህ ላይ ያላችሁ እምነት ፕሮቴስታንታዊ እንጅ የኦርቶዶክስ አይደለም። አንዳንድ አዋልድ መጻህፍት መጥቀሱ የመጻህፍቱን ችግር እንጅ የቤተ ክርስቲያንን አቋም አያንጸባርቅም። በዝህ ላይ ክርክር ቢኖር እንኳን የአስተምህሮቱ ጎራ መለየት ግድ ይላል። ኦርቶዶክሳዊ መስመር ይዞ መከራከር ጅልነት ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ግሩም እይትል

   Delete
 2. ye Ethiopia Orthodox betekiristiyan min yahil yetemare sew alatina new? minim eko yelatim endew bikefitu teliba nech. Tadiya yetemare sew binorat new bizu mestekakel yalebachew kenonawech lemisale sele bariya agezaz fiteha negest yemibalew yemiyatitew? endew kewere besteker sewechu tikitoch nachew degimo kesawust ena diyakonat kemiemenan ayshalum selezih enikuan liyastemiru lememar zigiju kehonu tiru new yihen sil gin tikit kesawustina diyakonat enidalun salizenega new.

  ReplyDelete
 3. "ኦርቶዶክሳዊ መስመር ይዞ መከራከር ጅልነት ነው" ያልከው፣ ስለ ክርስቶስ አማላጅነት በኦርቶዶክስ ሊቃውንት መካከል መሳ ለመሳ ልዩነት መኖሩን አታውቅም? የምታውቅ ከሆነ እውነትን አትደብቅ፡፡ ካላወቅህ ስለማታውቀው አታውራ፡፡

  ReplyDelete
 4. ወዳጀ

  እሱን ያልኩት ስለቅዱሳን አማላጅነት ነው። ሁሉም oriental አብያተ ክርስቲያን ያምናሉ። እማታምን ከሆንክ ፕሮቴስታንት። ሌላ ትአምር የለውም።

  ስለ ክርስቶስ ስራ በደንብ ገልጨልሀለሁ። የቃላት ጭዋታ ውስጥ አልገባም። ለእኔ የፈለከውን እረፍት የሰጠህን ቃል ተጠቀም እንቅልፍ ይዞህ ከሄደ። ዋናው የክርስቶስ ማንነት ላይ አንድ መሆናችን ነው

  ReplyDelete
 5. የሆነ የምትከተለዉ እዉነት ሊኖርህ ይችላል :: ያንን መከተል ሰዎችን እንዲከተሉ ማድረግም መብትህ ይመስለኛል:: ያንተ ስህተት ቤትህ ያልሆነዉን ቤቴ ነዉ ብለህ ድርቅ ማለትህ ነዉ:: ፕሮቴስታንት ሆኖ ማርያም አታማልድም ማለት እና ኦርቶዶክስ ነኝ እያልክ ማርያም አታማልድም ማለት ልዩነቱ የገባህ አልመሰለኝም:: ለዚህም ነዉ ሁሌ ብሎጋችሁን ለማንበብ አጀምርና ያልሆንከዉን ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስ ነኝ ስትል የተጭበረበርኩ ስለሚመስለኝ መጨረስ የሚያቅተኝ፡፡ እስቲ ከእዉነት ጋር ታረቅ እና ድርጅቴ (እምነቴ ) እንደዚህ ነዉ በል ከዚያም የሚከተልህ ይከተልሃል የማይከተልህ ቢያንስ ይረዳሃል:: ምናልባት አንተን የሚያንቀሳቅስህ እዉነት ሳይሆን ለአፍራሽ ተልእኮነት የሚያገለግል ብር ከሆነ ግን ማንም አይመልስህ :: ማቅ ማቅ እያልክ ስታቀነቅን መክረምህ ነዉ::የሆነ የምትከተለዉ እዉነት ሊኖርህ ይችላል :: ያንን መከተል ሰዎችን እንዲከተሉ ማድረግም መብትህ ይመስለኛል:: ያንተ ስህተት ቤትህ ያልሆነዉን ቤቴ ነዉ ብለህ ድርቅ ማለትህ ነዉ:: ፕሮቴስታንት ሆኖ ማርያም አታማልድም ማለት እና ኦርቶዶክስ ነኝ እያልክ ማርያም አታማልድም ማለት ልዩነቱ የገባህ አልመሰለኝም:: ለዚህም ነዉ ሁሌ ብሎጋችሁን ለማንበብ አጀምርና ያልሆንከዉን ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስ ነኝ ስትል የተጭበረበርኩ ስለሚመስለኝ መጨረስ የሚያቅተኝ፡፡ እስቲ ከእዉነት ጋር ታረቅ እና ድርጅቴ (እምነቴ ) እንደዚህ ነዉ በል ከዚያም የሚከተልህ ይከተልሃል የማይከተልህ ቢያንስ ይረዳሃል:: ምናልባት አንተን የሚያንቀሳቅስህ እዉነት ሳይሆን ለአፍራሽ ተልእኮነት የሚያገለግል ብር ከሆነ ግን ማንም አይመልስህ :: ማቅ ማቅ እያልክ ስታቀነቅን መክረምህ ነዉ::

  ReplyDelete
 6. አቤት ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ይሏችኋል የዚህ ዓይነት መዘባረቅ ነው። አውጣን!!!!

  ReplyDelete
 7. when it comes to oriental orthodox churches there are a lot which we share in common, of course, but the thing is still the issue whereby we utterly differ by having innumerable saints of which most of the stories could seem completely falsified and besides which compel believers deviate from the center or the focal point Jesus Christ.
  When it comes to the nature of Christ, it is assumed that full human and full divine, as the "incarnate logos" suited to him, we believe as the hypostasis union is the sole characteristic which made him leave his throne and kingdom becoming like one of us and give us salivation, redemption and we have been saved and we have been provided such a unique reconciliation that has already made us the children of the father(GODHEAD); so in general, in order for us to make such a wonderful reconciliation with the father, his solely begotten son was the one who dare to make it happen, he underwent a huge pain, suffer leading to death,and rise on the third day. These all occurred simply because he is GOD and that salivation which he gave us is also a salivation from the father and the holly spirit( trinity). now, the question is who is that individual coming in between to intercede between GOD and his children? believing in that, do not you think is not a mockery to the pain and death of Christ? is it not narrowing the gap between man and God? is it not falsifying the word of GOD so that people could put man and GOD on the same orbit, caliber and the likes? is it not pushing people towards worshiping human beings? is it not misleading people that each one have his choice of saints or too many of them so that who would worry about giving every fraction of second towards praying, thanksgiving, imploring and worshiping GOD? do not you think that a lot people in the Ethiopian Orthodox congregation do not have a clue in identifying the distinction between divinity and humanity? is it not what people totally embrace as a culture? these all happened because of preachers who do not care about the dogma of our Tewahido teachings, but they care more about what would give them popularity? The Ethiopian Tewahido church teaching are so amazing and it is focused on the Trinity,having more to do with the divinity.
  Jesus said that "I will not leave you like orphans;I will come to you, I will ask the father, and he will give you another helper, that he may be with you forever"John 14:15-18, and John16:6-11, says that "it is to your advantage that I go away;and I send him to you and the holly spirit encourages you, tells you which I don not tell you, prepare you so that you believe in me, receive me in my second coming, renew you and detach you from the 600 or so laws you have been trapped, stay connected to GOD in every fractions of your time,also the holly sprite will make you feel remorse and make your regular repentance so that you remain renewed and embrace GOD."Now, my dear brother, when you seem caring about saints you call having the power of interceding,do not you think people are just distancing themselves big time from the holly spirit? by the way when we say this time it is the time of the holly spirit, by that we mean that the father and the son are also with us, because as the holly spirit is the breathe and life to himself, he likewise is the breathe and life for the father and the son. so what is really crucial to the christian people of Ethiopia is to be abide by the miaphysite( tewahido) principles and devote ourselves to it, and also firmly resist those preachers who are swaying away believers from Jesus Christ and compel them live embracing Humans.by the way this is no less than making Christ more of a person than believing He descended from the heavens to save us by his grace-for we were all wicked. NB: I have a great respect for people who scarified their lives for the spreading the gospel and worked relentlessly for Christianity; I don't have any problem for their stories to remain in the churches.

  ReplyDelete
 8. First Aba Selama thank you for posting this article. I am impressed with the content of this educational article from both biblical as well as liturgical and traditional Orthodox teachings. This is what is lacking in this day and age. There is more than enough blame to go around to all concerned. The religious Zealots (fanatics like Mahibere Kidusan and those in it for their greedy and selfish interest, the clergy those that know the Word but are fear stricken and/or are impotent because they have no back bone to stand up and get counted, the dysfunctional Synod that had abandoned its responsibility of leadership, the woyane government that had stuck its ugly head in religious matters.) With all these thrown at the Ethiopian Orthodox faith it is with The Almighty God's providence that it has not yet been dismantled and its members disbanded. We the majority of Ethiopians have rebelled against God as the Israelite did back in the Old Testament times. If you go back and read what God did back then, He had wiped them out from their homeland several times because they did what we are doing now, mainly worshiping idols. We have not met their fate only because of Jesus whom most of us deny and persecute the ones that even mention His name. The Bible as the author of this article was trying to explain is the only inerrant book, Jesus is the only way to salvation. The choice is given, take it or leave it. Those of us that have nothing to do with the bible, it is our God given choice let us do what we have have been doing until we are hit by a bullet train called time and it is no more. Those of us that have something to do with the bible and believe Jesus is the only way, let us not bother our brothers and sisters on the other side. Is there not a verse somewhere in the bible where it says "If someone does not receive or listen to you shake off the dust before you leave.....". There is a day of judgement, a day of reckoning for all!! No one could hide!! GOD HAVE MERCY ON US!!

  ReplyDelete