Thursday, May 12, 2016

“ቅድስና” እንደ “ማኅበረ ቅዱሳን” እና እንደ መሪው “ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ይሁንልን!



አንድን ጉዳይ ደጋግሞ በፉለት ቁጥር ዕውቅና እንዲያገኝ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ግል ነው።  ስለ ዳንኤል በመፍ ጊዜ ማባከን ለምን አስፈለገ? ቢባልም በርግጥ ሳያውቁት “ዲያቆን” በሚል ተቀጥላ ስሙ የሚታለሉ የዋሃን ቁጥር  ብዙ ነውና እውነቱን መግለጡ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም። ለመሆኑ ዳንኤል ክብረት ማን ነው? የሚመራውስ ማኅበር (ማቅ) ዓላማው ምንድን ንው?    

በመሠረቱ ዳንኤል ክብረት አንድ ተራ ግለሰብ ሲሆን እታይ እታይ፤ እታወቅ እታወቅ በሚል በተጠናወተው አባዜው  የተነሣ ባልዋለበት ሊቅ መስሎ በየሄደበት የሚጮኸውና በምን ልታወቅ  ሁፎቹ መንገድ ዳር በበቀሉት ዕዋት በሚመሰሉት የዋሃን ምእመናንን ማደናገሪያ ከንቱ ድካሙ ያለ አቅሙ በዘመናዊውም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት  ስንት የደከሙ ሊቃውንትን የሚዘልፍ ከኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ዲፕሎማ ተነሥቶ በ advanced standing admission ከአማርኛ የመጀመሪያ ዲግሪ የማትዘል ዕውቀቱ በአንድ በኩል የሥነ መለኮት ተመራማሪ፤ በሌላው መለኩ ደግሞ የታሪክ ተመራማሪ በመምሰል የሚፈጨረጨር በውዳሴ ከንቱ ካባ ተጀቡኖ የሚኖር እሳት የላሰ ባዶ ናስ ነው።  በመሆኑም  በእግዚአብሔር ጋ የከበሩ  አባቶች ሊቃውንትንም ሆነ በዘመናዊ ትምህርትና ሥነ ምርምር  የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የደረሱ ምሁራንን ሲዘልፍ ይሉኝታ፣ ልጓምና ለከት ያጣው የዕውቀቱ ልክ ግድ ስለሚለው ነው። ምክንያቱም ሰው ባለው ልክ ነውና ለሌላው የሚተርፈው። ባዶ በርሜል/ገረወይና ትንሽ ቢነኩት ጩኸቱ መከራ ነው፤ ቢሞላ ግን ድም አልባ ነው።  ቢማር/ቢያውቅ ኖሮ የዐዋቂዎች/ የምሁራን/ የሊቃውንት ጥቅማቸው ይገባውና ይቆረቆርላቸው ነበር።  ወርቅን ለሚያውቀው ነው ወርቅነቱ፤ ለማያውቀው ግን ተራ ብረት ነውና።

ዳንኤል ከዚህች ከተጠቀሰችው ትምህርቱ በስተቀር ሌላ የሚያወላዳ ዕውቀት የለውም ከጥራዝ ነጠቅ መንፈሳዊ ከሚመስሉ የተኮረጁ ቃላቶቹ በስተቀር። በባህር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት አባል (የሰንበት ት/ቤቱ የትያትርና ሥነ ጽሁፍ ክፍል ቋሚ አባል) ሆኖ እየተወነና መነባንብ ለሰ/ት/ቤቱ ጉባኤ እያቀረበ እንደ ማንኛውም የሰ/ት/ቤት አባል በቤተ ክርስቲያን ከመቆየቱ በስተቀር የአብነት ትምህርት ከማንም መሪጌታ/አስተማሪ ጋር፤ አይደለም ዓመታትና ወራት፣ አንዲት ሳምንት ብሎም አንዲት ነጠላ ቀን ቁጭ ብሎ ፊደል የቆጠረበት ጊዜ የለም። ዛሬ “ዲያቆን” የምትለውን ማዕረግ ከስሙ በፊት ለጥፎ ሲታይ ላላወቀው በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ያለፈና ግዕዝ/ቅኔ የቆጠረ፣ መጽሐፍ የተማረ ይመስላል። ደግነቱ  በመድረክ ላይ ጩኸቱ ተውሶም ቢሆን የግዕዝ ቃላትም ሆነ ምስጢር ያለው ቅኔ ወርወር አድርጎም አያውቅም፤ ከቃላት አጠቃቀሙ የተነሣ ጨዋነቱ እንዳይገለጥበት።
 ያም ሆኖ በጨዋ ስብከቱ ማንነቱ አልተነቃበትም ማለት አይደለም። ይህችንም “ዲያቆን” የምትል ተቀጥላ ያገኘው ኮተቤ በሚማርበት ወቅት ክረምት ክረምት ኮሌጁ ሲዘጋ በወቅቱ የነበሩት የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጎርጎርዮስ ከነበራቸው ቅን አመለካከት የተነሣ ዳንኤልና መሰሎቹ በሰ/ት/ቤት የነበራቸውን ተሳትፎና አፈ ቀላጤነታቸውን በማየት ለወደፊቱ የወንጌል አገልግሎት ይጠቅሙ ይሆናል በሚልና ይህንንም አገልግሎት ለማከናወን አቶ ተብለው ሕዝብ ፊት ከሚቆሙ ዲ/ን ቢባሉ አገልግሎታቸው ተቀባይነት ይኖረዋል በሚል እሳቤ በዝዋይ የካህናት ማሰልጠኛ በሁለት በሁለት ወር የክረምት ኮርስ ስልጠና ለተልእኮ ይህችን ማዕረግ ስለሰጧቸው ዛሬ በውዳሴ ከንቱ መጠለፊያ ሆኖበታል/ሆኖባቸዋል። “ዲያቆን” ነኝ ይበል እንጂ ግባና ቀድስ ቢባል ግብረ ዲቁናውን አልሞከራትምና “ተንሥኡ”ን የሚያዜምባት ቅንጣት ታክል ችሎታና አቅም የለውም። በንባብ ካልሆነም በስተቀር አይደለም መልክአ ኢየሱስና መልክአ ማርያምን የዕለት ውዳሴ ማርያምን በቃሉ ቢዘልቅ ከምላሴ ፀጉር። 

የድፍረቱ ድፍረት ይህችን ማዕረግ ሲቀበል በተማሪነቱ (የሠራት ስህተት) ከዛሬዋ ሚስቱ ሌላ ቀድሞ የወለዳትን ልጁ ትዝ አላለችውም። ምን አልባት ለእርሱና ለማህበሩ አመራር አባላት እንዲህ ዓይነቱ ከመንገድ የወጣ ጥፋት ዛሬ ዛሬም ቢሆን እንደ እርም የሚቆጠር ጥፋት አይደለም ይሆናል። ወልዶ ክዶ ዲቁና ሹመት በ”ማህበረ ቅዱሳን” ሕገ ደንብ ክልክል የለው ይሆናልና። ለቤተ ክርስቲያን ሕይወት/ ለክርስትና መቆርቆር፣ የቅዱሳን አባቶቻችን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን አሰረ ፍኖት መከተል ማለት ከእንደዚህ ዓይነቱ በደል ነፃ ሆኖና እንዲህ ዓይነቱን ዕዳ አወራርዶ ነው። 
በሌላኛው የሕይወት ገታው ዳንኤል ተማሪ እያለ ዓለሚቱ ከምትባል የባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት አባል የነበረች አሁንም በሕይወት ያለች ሴት ልጅ ወልዶ የካደና፤ ደርግ ሊወድቅ አካባቢ ስለተወለደች  የልጁም ዕድሜ 25/26 ዓመት የሚደርስ ሲሆን፤ ከአብራኩ ለተከፈለች ልጁ ያልራራ ለእርሱ ባእዳን የሆኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን፣ አባቶች ቆሞሳትን/ ካህናትን፤ ወንድሞች ዲያቆናትን፣ በክርስቶስ ክርስቲያን የሆኑ ምእመናት/ንን ስም ጥላሸት ሲቀባ ውሎ ቢያድር፣ ክብራቸውን ቢያዋርድ ምን ይደንቃል? ከዚህም አልፎ ይህ ሁሉ ጉድ ጫንቃው ላይ እንዳለ ዲቁና ተቀበልሁ ብሎ ስሙን ሲለውጥና ራሱን ሲክብ በድንግልና የምትገኝን ክህነት ምን ያክል እንዳቃለላት ሲታይ ማን አለብኝነትና የድፍረት ድፍረት ነው።  ይህም አልበቃው ብሎ በክህደት ላይ ክህደት እንዲሉ ድርጅታቸው ለለመዱት ገንዘብ ማሰባሰቢያ አውደ ርዕይ 1994 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ ለማሳየት በተጓዙ ጊዜ አባቴን ካላሳየሽኝ ብላ ልጁ እናቷን በማስጨነቋ አውደ ርዕዩን በሚያሳዩበት ቦታ ከጓደኞቹ ፊት ድንገት ደርሳ እናትየዋ ልጅቷን ከአባቷ ስታገናኛት/ስታያይዛት በተከናነበው ውርደቱ  በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ዓይነት ዓለሚቱን (የልጅ እናቱን) ይቅርታ በመጠየቅ እስከ ዛሬ በድያችኋለሁ፤ እኔም ቆጭቶኛልና ከዚህ በኋላ ግን አብረን እንሆናለን፤ ልጃችንም አንድ ላይ ሆነን እናሳድጋታለን ብሎ ሸንግሏቸው ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ አፍንጫችሁን ላሱ ብሎ አዲስ አበባ ከተዋወቃት የአንድ ማየት የተሳናቸው የሕግ ባለሙያ ልጅ ጋራ በጀመረው አፍላ ፍቅር ከሰው ዕይታ ለመደበቅ (ከእግዚአብሔር ዓይን መሰወር ይቻል ይመስል) እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ ተክሊል ጋብቻ የፈጸመ ፍፁም አስመሳይና የታይታ ክርስቲያን በመሆኑ ለቤተ ክርስቲያንና ልጆቿ ህይወትና ደኅንነት ምን ገዶት የመንጋው መበተን፣ የምእመናን መፈለስ ያስጨንቀው?

        እንግዲህ ማኅበሩ በእንደዚህ ዓይነት በአፍኣዊ ነጭ ልብስ የየዋሃን ምእመናንን ዓይን የሚያማልሉ፤  ውሳጣዊ ሕይወታቸው/ ተልኳቸው/ ዓላማቸው ግን ፍፁም ሥጋዊ/ ምድራዊ፣ ከፋፋይ፤  የመድኅን ክርስቶስ ስም የጉባኤያቸው መክፈቻና መዘጊያ እንጂ ውስጡ ባዶ፤ እንኳን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ወደ ሰማያዊቷ እንደራሴ ወደ ሆነች ምድራዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት ምእመናንን በአንድነት ሊያስገባ ይቅርና አንድነትን የሚንድ፣ በታኝ፣ ፈታኝ፣ ከሳሽ፣ ፈራጅ በመሆን ከቤተ ክርስቲያን ጉያ ልጆቿን እያስወጣ ለነጣቂው አውሬው የሚያስበላ፣ ለኑፋቄ ትምህርት በእጅጉ የሚያጋልጥ ኢክርስቲያናዊ ዓላማው ገሃድ ከሆነ እነሆ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ የዘለቀ የአፈራሽ ቡድን/ ስብስ “ማኅበር” ነው። ይሁን እንጂ ይህ ድርጅት እንደ ስሙ እውን ለቤተ ክርስቲያን የሚሠራ ቢሆንማ ለቤተ ክርስቲያን መሪ በመሆን ከአበው ቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ሰማያዊ ሹመት/ኃላፊነት ስለ ቤተክርስቲያን አስተዳደርና አመራር የተሰየሙ አባቶች የሚያወርዱትን መመሪያ/ትዕዛዝ አልቀበልም ማለት ምን ማለት ነው? በቅንነት ለሚጓዙ ወገኖች “መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል” ትልቅ ብሂል ነውና። ከልጅነት እስከ እውቀት ስንት ለፍተው፤ የሌሊት ቁር፣ የቀን ሐሩር ሳይበግራቸው፤ ደበሎ ለብሰው፣ ዳዋ ጥሰው፣ ጤዛ ልሰው፣ በእንተ ስማ ለማርያም ብለው ለቁራሽ ከውሻ ተፋልመው፣ ሆዳቸው ባዶ እንዳይሆን አፋቸውን ለክከው፤ የኔታ እያሉ መምህራኑን አክብረው/ጉልበት ስመው፣ ለመምህራቸውም ‘እንደ ዋርካ ያስፈዎ/ እንደ ችበሃ ያለምልምዎ’ ብለው ዕድሜ ለምነው፣ አመስግነው፣  ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀው፤ ከደመወዝ ደመወዝ ሳይቆረጥላቸው የነጻ አገልግሎት በምታክል/በምትመስል  ሕይወት ከእጅ ወደ አፍ በሆነች ኑሮ ተኮራምተው ለልፋታቸው እንኳን ማካካሻ የሚሆን የረባ ሥጋዊ ጥቅም ሳያምራቸው በኋለኛው ዘመን በእምነት ከአምላካቸው/ከፈጣሪያቸው በሚአገኙት አክሊል ተስፋ መንግሥተ ሰማይ የአሁኑን ኑሯቸውን ለውጠው ቤተክርስቲያንን እዚህ ያደረሱ አባቶች በእነዚህ የተረገሙ ጋጥ ወጥ የማኅበሩ (ማቅ) አመራር  እንዴት ይዘለፉ/ይዋርዱ? ይህ ነው ወይ የእነርሱ ውለታ? (ምንም እንኳን ከሰው ውለታን ባይጠብቁም)። ከዚህ ፀሐይ የሞቀው እውነታ በመመርኮዝ ማኅበሩ የሚመራው በእነዚህ መሳጢዎች በመሆኑ ይህ ድርጅት ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ ነው ማለት ከኩርንችት በለስን እንደ መጠበቅ፣ ከዓይን ጆሮን እንደ ማመን ይቆጥራል።

በአጠቃላይ ይህ ድርጅትና አመራሩ ከሃያ አመት በላይ ቤተ ክርስቲያንን ሲንድ፡ ልጆቿን ሲያሳድድ፡ መተኪያ የሌላቸውን ብርቅና ድንቅ አባቶች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በዘመናዊ/ ዓለማዊ እውቀቱ ምንም መንፈሳዊነት በሌለብት ዓላማውና እኩይ ተልእኮው በድፍረት ሲገዳደርና ሲያዋርድ፤ የውጭ ሲኖዶስ የአገር ውስጥ እያለ መለያየት እጅግ እንዲሰፋና የራሱን እድሜ ለማራዘም ብሎም ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ምእመናኑ ድርጅቱን እንዲያስበልጥ በአስመሳይ ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ስብከቱ አሥራት በኵራቱን እንኳን ከቤተ ክርስቲያን እየነጠቀ በራሱ ካዝና በማስገባት  ካፒታሉን ሲያካብትና ሲነግድ፤ የድርጅቱን ስውር ደባ የተረዱና ጥያቄ የሚያነሱ ማንኛውንም አካላት ስም በማጥፋት ዘመቻው ጥላሸት እየቀባ ከሥራ ገበታቸው ሲያስባርርና የእለት ጉርስ በማሳጣት በጉሮሯቸው ጋሬጣ ሲሰነቅርባቸው፤ በምእመናን ዘንድ መቻቻል እንዲጠፋና ለድብድብ እስኪዳረጉ ድረስ ክርስቶስ ለሞተላት ክቡር የሰው ልጅ ሕይወት መጥፋት በዋነኛ አስተባባሪነት ምክንያት ሆኖ የኖረና አሁንም ቢሆን  ታጥቆ የተነሣው ታሪክ የማይሽረውን በየትኛውም ዘመን ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ለቤተ ክርስቲያኗ ውድቀተና ውርደት አሌ የማይባል አስተዋጻኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት እንጂ ቤተ ክርስቲያንን የሚደግፍ ማኅበር ላለመሆኑ ያሰለጠው አባቱ ዲያብሎስ ሕያው ምስክሩ ነው።
ከዚህ በኋላ ግን ተራው የአባቶች ነው። ከሃያ አመት በላይ እንደ ኤሊ ዘመን አባቶችም ይሻለው ይሆን በሚለው አዚም ውስጥ  ነበሩ።  እንደነ አፍኒንና ፊንሐስ የድርጅቱ ጨዋ አመራሮችና የድርጅቱን እኩይ ተልእኮ ያልተረዱ አባላቱ ቤተ ክርስቲያኗን አዛዥ ናዛዥ ሆነውባት ኖረዋል። አሁን ግን ይበቃል፤ አሁን የእግዚአብሔር ጊዜ፤ አሁን እውነት ወደ ሰገነት ጭላንጭሏ እየፈነጠቀ ያለበት ጊዜ፤ የድንግዝግዙ ጊዜ አልፎ ቤተ ክርስቲያን አጥርታ የምታይበት የብርሃን ጸዳል ጊዜ፤  ይህ መሳጢ "ማኅበር" ኢክርስቲያናዊ ሩጫው፣ አፈራሽነቱና ከፋፋይነቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚገታበት፤ ከቤተ ክርስቲያን ትከሻም ሊወርድ የሚገባብት ጊዜ ነው።
ኃያሉ አምላክ  ትህትና ሀብት የሚሆንበትን፤ የቤተ ክርስቲያን መሪ አባቶች የሚከበሩበትን፤ ልጆች እንምራ ሳይሆን አባቶች ምሩን እኛ እንከተል የምንልበትን የደጋግ ቅዱሳን አባቶቸን ራስን ዝቅ የማድረግን ዘመን፣ በረከት ይመልስልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር!   አሜን!!! 
እ ታ  ነኝ።

46 comments:

 1. you are really the messenger of devil- the father of lie. aba selam, please do not wast your time by insulting one of the most the 21st centurY precious spiritual youth association under EOTC. LAING is sin
  NB: MK'S exibition program was allowed to be seen in the near futur. What do you do? Cry Cry cry,other wise no solution

  ReplyDelete
 2. ቀጣፊዎች መቼም አይሳካላችሁም፡፡

  ReplyDelete
 3. የላም በረት ....

  ReplyDelete
 4. ይህ እውነት ከሆነ፤ የዝህን እርኩስ ሰው ማንነቱን ለምን በገሀድ አይወጣም።
  1. የተባለችውን ሰው አፈላልጓ፤ እንድትከሰው ለምን አይደረግም ? የጠበቃ እና አስፈላጊ ወጭዋ ለምን አይሰጣትም። እኔ ራሴ ቃል እገባለሁ

  2. ይህ እንደ ማቅ ስም ለማጥፋት ሳይሆን ይህ እርኩስ ሰው በአባቶቻችን በቤክ እሚነዛውን መርዙን ለማቆም ነው።

  3. ጽሀፊው ጀግና ቢሆን ይህን ያድርግ። ለዝህ ስራ እኔ እንዳልኩት ገንዘብ እሰጣለሁ። contact me on this comment.

  ReplyDelete
 5. I Could not finish this article.. GARBAGE IN , GARBAGE OUT. Now Everybody makes sure that you are following "YECHELEMAWUN YESUS...SATAN".
  I am really sorry for you since you use the work Aba Selama

  ReplyDelete
 6. ውሸት ከጻፍኩ ከምላሴ ፀጉር ይነቀል ትላለህ፣ አንተ ራስህ ከቤተክርስቲያን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተነቅለህ ተባረህ የለ እንዴ? ምን ምላሴ ምኔ ትላለህ፡፡ እንግዲህ መግቢ የለሽ አዳሜ ሐራ ይቃ/ተሐድሶ ሁሉ፡፡ በየአዳራሹ ስታጓሪ ትኖሪያለሽ እንጂ ተዋሕዶ እንደሆን አትገኝም፡፡ ግም ለግም አብረህ አዝግም አለ ያ ወዳጄ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለዘለዓለም ኑር…. ወደፊት ደስታዬ ወደር የለውም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን የመንገድ ተሳዳቢን፤ ጆሮ ደፍኖ፣ እንዳላዩ ሆነው ነው ማለፍ፡፡ ወንጌል ትላህ ደግሞ ወንጌል በደረሰበት አንተና ወዳጆችህ ዞራችሁ አታውቁም፡፡ ዲያብሎስ አፉን ሲከፍት ምን እንደሚያወጣ ታውቃለ ልክ እንዳንተ ስድብ ነው፡፡ እውቀት የሚባል ነገር በዞረበት አልዞረም የሚያውቀው እውነቶቹኑን የተዋሕዶ የወንጌል ሰዎች መሳደብ ነው፡፡ ለውሸቱ ከምላሴ ላይ ፀጉር ይነቀል ይላል፤ እራሱ ከነምናምኑ ተነቅሎ! ይገርማል እኮ!!! ልቦና ይስጥህ… ቢቻልህ ንሰሐ ግባ! የቤተ ክርስቲያኒቷን እውነተኛ ልጆች ለቀቅ አድርግ አትመጥናቸውም ለዛ ነው እነሁ መልስ ከሚሰጡህ እኔ የሞከርኩት… አንተና እነሱ የሰማይና የምድር ዕርቀት አላችሁ፡፡ እባክህ ይግባህ ወንጌል እያልክ የስድብ ቴክኒክ አታስተምር፤ ላም ባልዋለበት ኩበት እንድንለቅም አታድርገን በጭራሽ አትረባም… ወንጌል ውስጥ እኮ እውነት ነው ያለው፡፡ ስድብ የለም የሌለውን ነገር እየቀጣጠሉ አይወራም፡፡ ሐራ ይቃ/ተሐድሶ መሠረታዊ ችግራችሁ የቆማችሁበትን እውነት መመልከት አለመቻላችሁ ነው፡፡ እርስ በርስ የሐሳብ መመሳሰል የለባችሁም፤ ለስድብ እንኳን መብቃት ይጠይቃል፡፡ እጣጥ እንጣጥ ምንድን ነው?

  ReplyDelete
 7. እ ታ ፥ ኮተታም ተራ ወሬኛ መንደሬ መንደር ለመንደር እየዞርሽ(ክ)የወሬ ቱልቱላሽን(ህን) ልቀቂ(ቅ)ጾታ ለመለየት ስለተቸገርኩ ነው።

  ReplyDelete
 8. ሐራ ይቃ/ተሐድሶ ማለት የሚያመነዥክ እንስሳ ማለት ነው፡፡ አንድ ማኅበር ምን አድርግ ነው የምትሉት? እስቲ ዘገባችሁን ተመልከቱት ሁሌ ስድብ! ሁሌ ውሸት! ይደብራል እኮ!

  ReplyDelete
 9. የመሓበር ቀዱሳን አውደ ራእይ ሊካሂደድ ነው ቅስማችሁ ተሰበረ ፡፡እንገዳ ወርቅ ነጻወጣ ፡፡ በየ እለቱ ውሸታችሁ ተጋለጠ አይ ሓራ ጥቃዎች፡፡

  ReplyDelete
 10. እንትዴት ታወራላችሁ አንድ ሺ ሁናችሁ ብትጽፋም የዲያቆን ዳንኤል ሩቡን አትጽፋም መሃይምች ናችሁ
  ምድረ መናፍቅ

  ReplyDelete
 11. የሰውን እንዲህ ስትተረትር የአንተ አነጋገር ለጽድቅ ይሆን? ለሆድ ተገዝቶ ቤተ ክርስቲያንን ማተራመስ ስለአልተመቸ የሆነ ያልሆነውን ትቅላምዳለህ። ይህ የአላዋቂ ወሬ ነው። አወራህም አላወራህም የምታመጣው አንድም ነገር የለም። አንተው እንደቀለልክ ትኖራለህ።

  ReplyDelete
 12. Mahbere Qdusanen Cheru yeEthiopia Amlak, Liul Egziabher beselam, be'andnnet yitebbeqellen. Yatenkerellen!

  "Aba Selamam" lemmifeberrekew sem matfat hullu yiqerta yemeteyyeq hellina yinurew.

  ReplyDelete
 13. በቅናት እርር ድብን አላችሁ። አይ እታ።
  ለማንኛውም
  “ቅድስና” እንደ “ማኅበረ ቅዱሳን” እና እንደ መሪው “ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ይሁንልን! ላልሺው፣ ያው ሃሜተኛ ነሽና በሴት ፆታ ልጥራሽ ብዬ ነው አሜን እንላለን።
  ክፋትና ውሸት እንዳንቺና አንደ መሪያችሁ አባሰላማ አይሁንብን። አይደረግብን። ከምንፍቅና ያርቀን።

  ReplyDelete
 14. ተስፋ ቆርጣችሁ በጣም ተዝረከረካችሁ ክህደት ውስጥ ናችሁና የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረትም አይታያችሁም ምንም ብትደክሙ ነፍሳችሁ አታርፍምና ወደተዋህዶ በረት ተመለሱ። ለተዋህዶ ልጆችም ሆነ ለዳነኤል እንዲህ አይነት አርቲ ቡርቲ ጉዳይም አይደለም...ወየው ለእናንተ ለማይረባ አእምሮ ተላልፋችሁ ለተሰጣችሁ ከንቱዎች።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kkkkkkkk....ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ የሰጣችሁስ እንደናንተ አይነቱን በእመቤታችንና በቅዱሳን ስም ለምትነግዱት። እግዚአብሔር ያያል ይፈርዳል። ልቦና ይስጣችሁ። ዳሩ ትንቢቱ ሊፈጸም ግድ ነውና ሰይጣን እንድታስተውሉ አያደርግም። ደፍኖባችሁ እስከ ሞት ድረስ ያገለገላችሁ እያስመሰለ ወደ ጥልቁ ይዧችሁ ይወርዳል ብቻውን መውረድ አይፈልግምና። እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ፍቅር ከሌላችሁ እግዚአብሔር የላችሁም። እናስተውል ።

   Delete
 15. zare yetenekabet pente ale malet new

  ReplyDelete
 16. Ezihi lay ketsafkew yiliq, yanten kentunet betam adirgen teredan.

  ReplyDelete
 17. ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የምታወራው በውቤ የደነቆረ ውቤ ውቤ እንዳለ ሞተ እንደሚባለው ነው፡፡ ክነቱ ጩኸት፡፡

  ReplyDelete
 18. ቃላት አጣሁ አናንተን ለመናገር!!!! በእውነት ህያው እግዚአብሔር ምስክር ነው ሰይጣን እንኳ እንደ እናንተ የሚዋሸ አይመስለኝም .....የውሸት ጥበብ እያስተማራችሁት ነው .....አንዴ ዳንኤል ዲግሪ የለውም ትላላችሁ አንዴ ደግሞ " ከ advanced standing admission ከአማርኛ የመጀመሪያ ዲግሪ የማትዘል ዕውቀቱ " ትላላችሁ ከራሳችሁ እንኳ መግባባት ያቃታችሁ እንዴት ሰው ለማነጽ ታስባላችሁ????

  ReplyDelete
 19. ጅብ በማያቀው ሀገር .....

  ReplyDelete
 20. ሰይጣን አሳዘነኝ ምን ይስራ እናንተ ስራውን ነጥቃችሁት!!!! ሰይጣን ፍርድ ቤት እንዳያቆማችሁ ተጠንቀቁ!!! ለነገሩ በገሃድ አይመጣ እናንተ የክብር ዙፋኑ እያላችሁለት!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. የሰይታንንማ ማህበረ እርኩሳን አጦጡፈውታል ከሳሽ ተሳዳቢ ሌባ ማን እንደሆነ ከገባህ ሰይታን እንደሚሸነፍ እያወቀ ይሮሮጣል እስኪ ስንት ሰው ኪዳኑን እንዳፈረሰ ዳኒ ይጠይቀው ሰይጣን ወዳጅ አደል ካልዋሸው ኪኪኪኪ ኪ ወይ ተክልዬ ያጠመቀውን

   Delete
 21. ማስቀደስ ወይም መቀደስ ታውቃላችሁ.... እባካችሁ? ውዳሴ ማሪያም ነዉ ያላችሁት.... ቂቂቂ

  ReplyDelete
 22. በናትህ ውዳሴ ማርያም: መልክአ ማርያም : በእንተ ስማ ለማርያም አልክ መሰለኝ !!! ታውቃታለህ ግን እሷን አንዴ እናታችን አይደለችም ስትሉ ደሞ አሁን ምንድን ነው????
  "አዛኝ ቅቤ አንጓች"

  ReplyDelete
 23. አሁን አንተ የእግዚአብሔር ሰው ነህ?????? ይቅር ይበልህ

  ReplyDelete
 24. እናነተ ዉሸታሞች

  ReplyDelete
 25. Ene yemigermgne ye degafiwochu.ena min yitebes deg adergew enkwan tesadebe yemilu sidb hatiyat aydelm bilo astemrwachewal mesel.dani ena mk ye wengel telatoch betcrstiyan yemiyasedebu yemiyasdefru.egziabher beka yebel.

  ReplyDelete
 26. የተሃድሶው አቀንቃኝና የዚህችን ቤ/ያን አፍራሽ ተልዕኮ አንግበህ የምትጮኸው ተላላኪ ምን አልክ? ለመሆኑ ስለ ክህነት፣ስለ አባቶች ክብር፣ ቅዳሴ፣ አብነት ት/ት፣ መልክአ መልክ፣ውዳሴ ማርያም፣አጠቃላይ ገድላትና ተዓምራት...ወዘተ እያንቋሸሽክ የምትጽፍ መደዴ አሁን ምን አገባህና ስለነዚህ አነሳክ? የማታምንበትንና የማይመለከትህን...? የቤ/ያንን ልጆች ለመስደብ ሲባል...? አይ ጂሎ ለማያውቁሽ። እኛ የቤ/ያን ልጆች ግን መደዴውን፣ የአዳራሽ ወንበዴውንና የአንድ ሳምንት የእብራውያን ሠልጣኙን ጠንቅቀን ስለምናውቃችሁ አትልፍ አይሳካላችሁም። ዳንኤልና ማቅ ፈጽሞ በአንተ አንደበት ሊጠቀሱ አይችሉም።

  ReplyDelete
 27. ቀዳዳዎች ወሬ ብቻ

  ReplyDelete
 28. Diakon Daniel Akerkariyachihun sebruachihual malet new endih yetencherecherachihut. Ay enanite meche yihon ke Mahibere Kidusan wuchi yehone neger yemititsfut. tasazinalachihu lefirfari bilachihu hilinachihun sitshetu.

  ReplyDelete
 29. Sitasazinu.
  Zibazinke.
  Artiburti.
  Zebatelowoch.

  ReplyDelete
 30. "Abba Selama"?! Better call yourselves "Abba Saytan"! Shame on you

  ReplyDelete
 31. በመሰረቱ ዳንኤልን ለመቃወም ይሔ ሁሉ ሐተታ የሚያስፈልግ አይመስለኝም። ዲቁናዉም ሆነ ቅስና ሰለምትለዉ ነገር እንዴትም ይሾም አይሾም ጉዳያችን አይደለም ፣ የትኛዉም ነቢይና ሐዋርያ በድንግልና ደቆነ በድንግልና ቀሰሰ የሚል አላየንም። ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል መስፈርቱ እሱ አይደለም ። ፣ ልጅ ወለደ እንኳን ወለደ ስንቱ መነኩሴና ዻዻስ ይወልድ የለ እንዴ
  እሱን መቃወም ከፈለክ ሰዉየዉ አድር ባይ ካድሬ ነገር ነዉ በለን እኛም እንዳንተ ብዙ ታዝበነዋል ይሁንና ቅስና ዲቁና ምናምንህን እዛዉ ።

  አባ ገ ማርያም


  ReplyDelete
 32. Minwagaw TemesgenMay 15, 2016 at 5:17 AM

  What do you mean by blackening one's name, be that a father or brother? What are you doing yourself? Do you think that something is a curse when said by others and a blessing when it is by you, the Abba Selama? Is it?

  ReplyDelete
 33. Yegilesebochin sime bematifat yetesakalin mesilochihu ke hone tesasitachihual yih hulu temesasilachihu orthodox tewahido christianin lemeberez yaderegachihut sera sele keshefe new yih hulu kibzibzinet selehonem gileseboch minim yihunim minim be million yemikoterut wetatoch maninetachihu seleteleye kentu atidikemu manim aysemachihum

  ReplyDelete
 34. yigermal ke betechristian be tehadisonetachew tebarew ahunim yegilesebochin seme bematifat mesemaratachew ayidenkim bezih tsihuf yantew degafiwech yinchachu kalhone besiteker lisemah yemichil yelem !MK bileh betekarno sititsif atafirm millionochin asketilo betechristianin yemiyagelegil enku ye orthodox tewahido lijoch nachew wedefitim ende enante yemesaselutin tehadissoch enkirdadun ketirew endemiley hulu ke hizbe christianu gar be mehon yemeleyetu sera tetenakiro yiketilal

  ReplyDelete
 35. wow Dniel bro... I love&respect you again and again.You protesters your article indicates that;how much dieniel kibiret is the Guard of our lovely orthodox church and a headache for protestants.please,go head to right more about himv& other critical brothers (Abayneh,Yaregal,Birhanu ,so on.)

  ReplyDelete
 36. አባሰላማዎች በጣም እናመስግናችዋለን። በሩቱ ለእውነት ቁሙ።የማቅ መሪዎች ጉዳቸው ተነግሮ አያልቅም ኦረቶዶክስን እየገደሉ አማኞቿ ከቤተ ከርስቲያኗ እያረቁ ናቸው። መቅደሱ የእነ ዳንኤል መሰሎች እየረከሰ እየተዋደ ያለበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። የቅድስና ትርጉም የማይገባቸው የሌቦች ዋሻ ሆኖ ነው ያለው።እስት እግዚአብሔር ያሳያችሁ እነ ዶክተር መስፍን እነ ብርሃኑ ጎበና ሎሎች በብዛት ያለ ስርዓቱ በነዋይ በሰከሩ ጳጳሳት ስንቶቹ ናቸው ቀስ ተብለው ተሹመው ግራ ህዝቡን የምያጋቡት።ከመጋረጃው ጀርባ የምሰራው ስራ ከአምላክ በስተቀር የተመለከተው የለም። ተረታ ተረት ከማውራት በስተቀር ስው የሚድንበት በት አልሆነም። እነ ዳንኤል ከመንግስታችን ጫን ያለ ገንዘብ በስላላችው እየጎረሱ በተመቻቸ ህይወት ይደላቀቃሉ። ሌላው ምስኪን ህዝባችን ገንዘቡን ይገብራል። ለሠጋ ወይንም ለነፍስ የማይሆነ ስጦታ። እውነትማ ብሆን ኖሮ ጳጳሳቱን ካህናቱ ተወጋግዞ ከመጋረጃው ተስተጀርባ በክርስቶስ ስጋውና ደሙ እያሉ ባለነገዱ ነበር። የይቅርታ ልብ ሳይኖር ከውግዘት እርግማን ሳይወጡ ክቡር ደሙንና ቅዱስ ስጋውን መቀበልም ማቀበልም ቀድሞ በተጻፉት ህጎች ስልጣን አልነበራቸው። ማን አለብኝ ተብሎ አይደል ሁለም ቀስ ሁሉም መነኮሳት ሁሉም ጳጳሳት ሳይገባቸው ተሸክመው በዲያቢሎስ ነዋይ እያበዱ ያሉት።ለዚህም ነው ዛሬ ዛሬ የቤተ ከርስትያናችን ምዕመን እየተነጠቀ ያለው።የኢትዮጵያ መንግስት በአደባባይ ሽብር ፈጣሪ እያለ ማህበረ ቅዱሳንን የማይደግፍ መስሎ ይናገራ በስውር ግን በከፍተኛ ገንዘብ ለማቅ አባለት ይከፍላል። ምክንያቱም የውጭውን ስኖዶስ ለማዳከምና የተዋህዶ ህባችንን ለመካፋፈል። ለመሆኑ እነተኛ ሽብርተኛ ነው ከተባለ ለምን ቢሮዎቹና የንግድ ድርጅቱ ለስኖዶሱ እንድያሰረክብ አያደርግም። ውሸት ስራዎች የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት እንዳይኖረው በጥላቻ አይን እንድተያይ መንግስት በማቅ በኩል እጅግ የላቀ ስራ እየሰራ ነው። ንቃ ንቃ ንቃ እውነቱ ይህ ነው>>>>>>>>>>

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንደው ጅል ቢጤ ነህ ልበል???? ከመቸ ጀምሮ ነው ሁለት ሲኖዶስ ለአንዲት አገር ሚኖራት ....መናፍቅ ሆነህ ግን መናፍቅ እንደሆንክ እንኳ አታውቅም?? ሲገርም የተሃድሶ ፍሬ ነህ!!!

   Delete
 37. “አባ ሰላማዎች” የሰይጣንን ተግባር ሙሉ ለሙሉ ኮንትራት ወስዳችሁ ስለምትሰሩ ክፍያችሁን ዲያብሎስ በርክክቡ ወቅት ጥሩ የሳት ወንበር ይሰጣችኋል ከዝንብ ማር አንጠብቅም ዱሮስ ዲያብሎስ የግብር ልጆች ምን ይገኛል

  ReplyDelete
 38. ስለመረጃው እናመሰግናለን በርቱ እኛም በአይናችን ቅድስናቸውን እያየን ነው ኪኪኪኪኪ እኔ ሚገርመኝ ግን ከእነሱ አባል ውጪ የሆነ ሲያብጠለጥሉ የራሳቸው እንዲነካ አለመፈለጋቸው ለቤተክርስትያን ከቆሙ ዳኒ ስራት አፍርሶ ሲገኝ ለምን አይገስፁትም ለምን አይወቅሱትም ይሄ እራሱ ለማህበራቸው እንጂ ለቤተክርስትያን አይደለም ማለት ይቻላል

  ReplyDelete
 39. የዳንኤል ዉሾች ጮሁ

  ReplyDelete
 40. የዳንኤል ዉሾች ጮሁ

  ReplyDelete
 41. ዘገብርኤልMay 23, 2016 at 6:30 AM

  ማቆች:- አባሰላማ ያወጣው ጽሁፍ ሃሰት ከሆነ፤ ሃሰትነቱን በማስረጃ መግለፅ እንጂ ስድብን ምን አመጣው? ጽሑፉ ክፉ ከመሰላችሁና እናንተ ቅዱስ ወንጌልን የምትከተሉ ከሆናችሁ ክፉን ለምን በክፉ ትመልሳላችሁ? የክርስቶስን አራዓያነት ተመልከቱ:-
  "ዮሐ.18:23 ኢየሱስም መልሶ። ክፉ ተናግሬ እንደ ሆንሁ ስለ ክፉ መስክር፤ መልካም ተናግሬ እንደ ሆንሁ ግን ሰለ ምን ትመታኛለህ? አለው።"
  ስለዚህ ሃሰት ተናግረው እንደሆነ ስለ ሃሰት መስክሩ እውነት ተናግረው እንደሆነ ግን ስለምን ትራገማላችሁ ትሳደባላችሁም?

  ReplyDelete