Sunday, May 15, 2016

“አትታደስም” በሚል ርእስ የተዘጋጀ ፀረ ወንጌል “መዝሙር” እንዳይመረቅ ታገደ


 Read in PDF
በማኅበረ ቅዱሳንና በተከታዮቹ ቤተክርስቲያንን ከእውነተኛው የወንጌል ትምህርት በማንሸራተት ወደ ተረት ለመውሰድ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ፣ “አትታደስም” የሚል ስያሜ የተሰጠውና ወንጌልን ለመቃወም የተዘጋጀውና ግንቦት 4/2008 ዓ.ም ሊመረቅ የነበረው መዝሙር የምረቃ ሥነሥርዓት ታገደ፡፡ ታታ ዘየካ ለተባለ ግለሰብ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደርጎ የተሠራው ይህ መዝሙር ግለሰቡን ሽፋን አድርጎ ወንጌልን የመቃወም የተለየ ዓላማ የያዘ ሲሆን የምረቃ ሥነሥርዓቱ ሕገወጥና ከቤተክርስቲያን ፈቃድ ያልተሰጠው በመሆኑ በ11ኛው ሰዓት ላይ ታግዷል፡፡

 ምረቃው እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የወጣቶች ማእከል አዳራሽ ውስጥ ሊደረግ ታስቦ የነበረ ሲሆን  ምርቃቱ ገና ከመጀመሪያው ግልጽነት የጎደለው ነበርና አዘጋጆቹ የአዳራሽ ኪራይ የከፈሉት ራሳቸውን ደብቀው የማይታወቅ ሰው በመላክ ነበር፡፡ የቀበሌው ሥራ አስፈጻሚ ምንም የሚያውቀው እንደሌለ ሲገልጽ የተዋዋለው ሲጠራ የቀረቡት እነታታ ሳይሆኑ ስለጉዳዩ ምንም የማያውቀው ግለሰብ ነበር፡፡ እርሱም ተጠይቆ “ልከውኝ ክፈልና ና ብለውኝ ነው” በማለቱ ፈቃድ ከቤተ ክርስቲያን እንዲያመጡ ተጠይቀዋል፡፡ ያን ማድረግ ባለመቻላቸው ምረቃውን ማካሄድ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ታዛቢዎች ሕጋዊ ቢሆኑና ድብቅ ዓላማ ባይኖራቸው ኖሮ ራሳቸው ቀርበው መዋዋል ይችሉ ነበር ይላሉ፡፡

በዕለቱም ያረጋል አበጋዝን የተካው ዘሪሁን ሙላቱ በምረቃ ሽፋንነት የቀረበውን ስለ ተሐድሶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ለማቅረብ ተመድቦ የነበረ ቢሆንም በፕሮግራሙ መሰረዝ ምክንያት ምንም ማድረግ ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ይህን ህገወጥ ጉባኤ የጠሩት ቀድሞ በየዓውደ ምሕረቱ ከስድብ በቀር ወንጌል የማይሰብኩ፣ በአሁኑ ጊዜ በሕገ-ወጥነታቸው ምክንያት አውደ ምሕረት ላይ እንዳይሰብኩ በመደረጉ መድረክ ያጡ፣ ባይሳካላቸውም ለመታወቅ የሚጓጉና በአራት ኪሎ ቡድናቸው አባላት “ወዲህ በሉ” የተሰኘ ስም የወጣላቸውና የማቅን ይሁንታ ለማግኘት የፈለጉ ስብስቦች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ግጥምና ዜማውን የሠሩት አቶ ደረጀ ወይንዬ (ወርቃለማሁ) እና የማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሰባኪ ብሩክ ሲሆኑ በመዘመር ከተሳተፉት መካከል በዳግም ጋብቻ የተጣመሩ ሲ/ር ሕይወትና ዲ/ን ይትባረክ ይገኙበታል፡፡ ሲ/ር ሕይወት ወልዳ በይፋ ከተፋታች በኋላ ዲ/ን ይትባረክን ያገባችው ሲሆን፣ እርሱም እንደ ዳንኤል ክብረት ከትዳር ውጪ ከወለደ በኋላ ዲያቆን እየተባለ ይጠራል፡፡ ነገም መቀሰሱ አይቀርም፡፡ “አትታደስም” በሚል ስያሜ የተዘጋጀውን መዝሙር ርእስና የአዘጋጆቹን ይህን የመሰለ ሁኔታ ስንመለከት “አትታደስም” ለማለት የበቁት በዚሁ ሕይወት መቀጠል ስለሚፈልጉ ነው የሚሉ ታዛቢዎች አሉ፡፡
የዚህ መዝሙር ምረቃ አዘጋጆች እንደሚታወቀው “ፍኖተ ዘተዋህዶ” የተባለውን ማህበር እናቋቁማለን ብለው የተሰባሰቡና ከዚህ ቀደም ከሥላሴ ካቴድራል፣ ከሥላሴ ኮሌጅና ከአራት ኪሎ ሜታ የጡረተኞች አዳራሽ በተደጋጋሚ ዝግጅታቸው ሕገወጥ በመሆኑ የታገደባቸው ሲሆኑ፣ አሁን ግን መልካቸውን ለውጠው በመዝሙር ምረቃ ሰበብ ለመገናኘት የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ እነርሱም ደረጃ ወይንዬ፣ ፀዳለ ዳና፣ ብሩ ማርቆስ፣ ሲስተር ሕይወት፣ አዜብ ከበደ፣ ምንዳዬ ብርሃኑና አንድነት አሸናፊ ሲሆኑ የነዚህ መሪ ሆና እየነዳቻቸው ያለችው የልደታዋ ፌበን መሆኗን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በመዝሙር ምረቃ ሽፋን ያሰቡት ድብቅ አጀንዳ ሳይሳካ በመታገዱ ኪሣራ ገጥሞአቸዋል፡፡
ሰውን መርዳትና ማገዝ የሚገባው በፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ ውስጥ ተከልሎ፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለእነርሱም ሕይወት ጠቃሚ የሆነውን ተሃድሶን ጠልቶ ሳይሆን ራሱን የቻለ ንፁህና ሰውን የሚያንጽ ሥራ ሠርቶ፣ እውነት የሆነውን ወንጌልን መስክሮ ነው፡፡ እነርሱ ግን በህልማቸውም በእውናቸውም የሚያባንናቸውንና ከአቅማቸው በላይ የሆነውን መለኮታዊ ምሪት ያለበትን የእግዚአብሔርን አጀንዳ የምድራችንን ተስፋ፣ የቤተክርቲያናችን ፈውስ የሆነውን ተሃድሶን ተከልለው ይህን አሳፋሪ ሥራ መስራት አልነበረባቸውም የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ሳውል ተለውጦ ቤተክርስቲያንን ከማሳደድ ለቤተክርስቲያን መታነጽ ወደ መሰደድ እንደመጣ ሁሉ፣ እነዚህም የወንጌል ተቃዋሚና አሳዳጅ ሆነው የተሰለፉት ሰዎች አንድ ቀን የወንጌሉን እውነት ምን እንደሆነ አስተውለው ያሳደዱትን ወንጌል ይዘው ስለወንጌል እነርሱም ሊሰደዱ ይችላሉ፡፡ ማን ያውቃል? እነዚህ ሁሉ ቆም ብለው ካሰቡ ዛሬ የሚቃወሙትን ንፁህ ወንጌልና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዝማሬ ለቤተ ክርስቲያን ሊያበረክቱ ይችላሉ፡፡ ለሁሉም እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጣቸው፡፡

14 comments:


 1. ሰምቶ ለሚጠቀም
  ብልህና አስተዋይ ሰው!!!

  ብርሃንም በጨለማ ይበራል፤
  ጨለማም አላሸነፈውም። /ዮሐ 1፡5/

  የሚለው ህያው የታማኙ አምላካችን ቃል በራሱ ጠላቶቹን የመምታትና የማስደንገጥ አቅም አለውና እናንተ የጌታ ታማኝ ባሪያዎች ለዚች በክፉ ልጆቿ ለምትጨነቅ ታሪካዊት እናት ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያናችን በጸጋው ቃል መታደስ/ወደ ቀደመ የወንጌል መሰረቷ/ እንድትችል የመንፈስን አንድነትን በጠበቀ መልኩ በጋራ ጨክነን እንነሳ???

  በእውነት ለወንጌል እንኑር?
  በወንጌል ለመኖር ግን አንሥራ???

  ለሁላችንም ማስተዋል ይብዛልን!
  የገባው ብቻ አሜን ይበል!

  በወንዝ ልጅ ሳይሆን
  በአዳነኝ ጌታ በኩል
  ወንድማችሁ

  እውነቱ ይነገር ነኝ


  ReplyDelete
 2. አይ ተሃድሶ፦
  ተሃድሶው ቀርቶ እንዲህ የመንደር ወሬ ለቃቃሚ፣ አምራችና አከፋፋይ ሆናችሁ? ሃሃሃሃሃሃ ወሬ ፍጠሩ።

  ReplyDelete
 3. አባ ሠይጣኖች ሃሠትና የሃሠት አባቶች ጀግናው ማቅና ዲ.ዳንኤል እንዲሁም ጀግኖች የተዋሕዶ ዘማርያን የአይን ውስጥ ምጥሚጣ ሆኑባችሁ እንዴ? አይይ... ምን ይሻላችኋል? እዛው ከምትዋሹበት አዳራሻችሁ ይሻላችኋል፤ይህቺ እውነተኛዋ ቤ/ያን ግን ለእውነተኞቹና ሃሰትና ስድብ ሲፈራረቅባቸው ከወንጌል ውጭ ምንም ለማያውቁት ለማቅ፣ ለዲ.ዳንኤልና ለጀግኖቹ ዘማርያን ነች።አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ከመለሣችሁልኝ? በእግዜአብሄር ላይ ማመጽን በተመለከተ አዳም ከሄዋን፣ሄዋን ከሠይጣን፣ ሠይጣን ደግሞ አመጽን፣ሐሰትንና የሐሰት ሥራዎችን ከእናንተ ተማረ፤ ለመሆኑ እናንተ ከማን ተማራችሁ? ከ22ቱ ሥነፍጥረታት መካከል አይደላችሁምና አፈጣጠራችሁ ከምን ክፍል እንደሆነ ብትነግሩኝ? ምን ጊዜም ሐሰት ሐሰት ሐሰተ....።

  ReplyDelete
 4. አዳሜ ተሃድሶ ሁሉም ነቅቶብሻል!!! መግቢያሽን ፈልጊ ወይ ንስሃ ግቢ!!!

  ReplyDelete
 5. woregna, tedesekuralachu. You nare ant-gosple and anti- christ

  ReplyDelete
 6. እውነቱ ይነገር ይሰማMay 16, 2016 at 7:34 AM

  ማቆች!!!

  ካለ ተረት ተረት እና ጉልቤ በቀር ሌላ የምትሉት ቁምነገር የላችሁም ማለት ነው? ጉድ ነው!!!

  እውነቱ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ እውነት እቴ!!! መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ አሉ!!! አንተ ና መሰሎችህ ውሽቶ ነው መባል ያለባችሁ!!! ያባታችሁ ልጆች!!

   Delete
  2. "ተሀድሶ ማለት ነፍሳትን ለፕሮቴስታንት የሚገብር ገባር ወንዝ ማለት ነው፡፡" ሊቀጉባኤ ጌታሁን

   Delete
 7. ለነገረኛና ለ፭ሳንቲም መልስ የልኝም

  ReplyDelete
 8. ለመሆኑ ሃይማኖት አላችሁ? እኛ ተሃድሶዎች ንፁህ ወንጌል ነው የምንሠብከው ትላላችሁ። አይይ...እኔን ይስበከኝ፤ ሃሰቱን፣ ስድቡን...፣በመናገራችሁ እውነትም ንፁህ ወንጌል መስበካችሁን በተግባር አስመሠከራችሁ።

  ReplyDelete
 9. ወሬ ብቻ .... ግን ማ/ቅ እስካለ መንቀሳቀስ አይቻልም፡፡

  ReplyDelete
 10. ተሀድሶ የሚቃወም ጨርሶ የበሰበሰ ነው<!!!!

  ReplyDelete
 11. bado chikilat ayyy tehadiso bichawin kere tedemisiso

  ReplyDelete