Wednesday, November 15, 2017

ገድል ወደ ሞት ሲወስድ ወንጌል ግን ወደ ሕይወት ይመራል


Read in PDF
በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የምትመራ 400,000 በላይ አገልጋዮች ያሏት 35,000 አጥቢያዎች ተከፍላ ቁጥሩ 40,000,000 የሚደርስ ተከታይ ያላትና በሁሉም ያገሪቱ ክልሎች የተዘረጋችዋ ቤተ ክርስቲያናችን 4ኛው ክፍለ ዘመን በትውልድ ሶርያዊ በሆነው በወቅቱ የእስክንድርያ ጳጳስ ከነበረው ከአትናቴዎስ እጅ የአገልግሎት ስልጣንና ሃላፊነት ተቀብሎ በመጣው በፍሬምናጦስ (የመጀመሪያው የሀገራችን ጳጳስ) በኋላም በወንጌል አገልግሎት አባ ሰላማ (የሰላም አባት) ከሳቴ ብርሃን (ብርሃን ገላጭ) እየተባለ በተጠራው ሊቀ ጳጳስ አማካኝነት ክርሰትናን ተቀብላ ብሄራዊ ሃይማኖት አድርጋ የኖረች ቤተክርስቲያን ናት። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በባህል በቅርስ የግሏ በሆነ  የስነ-ጽሁፍ የፊደል እንዲሁም በሌሎች ዓለማት የማይገኙ  የአምልኮ ስርዓትና መሳሪያዎች ባለቤት የሆነች ታላቅና ጠንካራ መዋቅር ያላት  ቤተ ክርስቲያን ናት
1.     ጀማሪዋ (ከሣቴ ብርሃን) በወቅቱ ዓለም አቀፍ ተቀባይነትና ዕውቅና ከነበረው ከአባ አትናቴዎስ መማሩና መሾሙ
2.    የተቀበለቻቸው የሃይማኖት ውሳኔዎች መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሆናቸው (ጸሎተ ሃይማኖት)
3.    በመፅሃፍ ብቻ ተቀምጠው ያሉት ትክክለኛ የሆኑት የነገረ መለኮት ትምህርቶቿ (ትምህርተ ሥላሴ ያልተበረዘው  የስጋዌ ትምህርቷ)
4.    ዛሬ የተመሠረቱበትን ዓላማ ቢለቁም ከልደቱ እስከ ዕርገቱ የሚያሳዩ ስዕላት በቤተክርስቲያን መገኘታቸውና የተጀመሩበት ዓላማ ታሪክ
5.    የቤተክርስቲያን ምሥጢራት እየተባሉ የሚጠሩት (ጥምቀትና ቁርባን) መልካቸው መገኘቱ (ዛሬ ዓላማቸውና ትርጉማቸው ቢዛባም) ወዘተ የቤተክርስቲያኒቱን ጥንተ አመሠራረት ወንጌላዊት የነበረች ለመሆኑ ምሥክር ናቸው።

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ያበረከተችው አስተዋጽኦ
1.  ቋንቋን ከነፊደሉ በማዘጋጀትና ለባለ ቋንቋዎች ፊደልን መስራት
2.  መንፈሳዊና ስጋዊውን ኣስተዳደር በመቅረፅ ህዝብ የሚተዳደርበት ህግ መስጠቷ
3.  ሃገሪቱ እንደሌሎቹ የአፍሪካ አህጉራት በእስልምና እንዳትወሰድ መከላከል
4.  ወራሪዎችን ለመከላከል ህዝብን ማስተባበር
5. ማህበራዊ ኑሮን መመስረት (ፅዋ እድር ማህበር ወዘተ)
6.  የሃገሪቱ የታሪክና የቅርስ ባለቤትና ግምጃ ቤት መሆን
7.  እግዚአብሔር በምድራችን ስሙ እንዲጠራና በሕዝቡ ዉስጥ ያሠረፀችው ፈሪሀ እግዚአብሔር
8.  በሃገሪቱ የስነ ጽሁፍ እድገት አንዲመጣ ማድረግ ጥቂቶቹ ናቸው።

የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን የገጠሟት ችግሮች
1.     ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያኒቱ ጳጳስ አባ ሰላማ ሞት በኋላ በቋንቋ በባህልና በስርዓት እንግዳ የሆኑ 1600 ዓመታት ያህል በቤተክርስቲያኒቱ ጳጳስ ከቡራኬ በስተቀር ለወንጌል  አገልግሎት ትኩረት አለመስጠት
2.    በተለያዩ ምክንያቶችና ዓመታት ወደ ኢትዮጵያ የፈለሱት ነገዶች ይዘውት የመጡት የእምነትና የስርአት ተፅኖዎች ምሳሌ (የአይሁዳውያን አረባውያን)
3.    የተስዓቱ ቅዱሳን (የ፱ኙ ቅዱሳን) መምጣትና ምንኩስናን የጽድቅ መንገድ አድርገው ማስተማራቸው
4.    የዮዲት ጉዲት ወረራና ዓመት ግዛቷ የፈጠረው የመጻህፍት መቃጠልና የመምህራን እልቂት እንዲሁም የይሁዲነት ባህል መስፋፋት
5.    ነገሥታት ለቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ልዩ ልዩ ስጦታ በመስጠት በቤተክርስቲያን ሥፍራን መያዝ ሲሶ መንግስት መስጠቷ
6.    የግራኝ መሐመድ ወረራ ያስከተለው የሊቃውንት ጭፍጭፋ የአብያተ ክርስቲያናት ውድመትና የፈጠረው ክፍተት
7.    የስሕተት መጻህፍት በገፍ እየተጻፋ ያለ እርምት የወደሙትን ለመተካት ሲባል ወደ ቤተክርስቲያኒቱ እንዲገቡ መደረጉ
8.    ለጥቂት ግዜም ቢሆን ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀው የካቶሊክ እምነት ያስገባው እንግዳ ትምህርትና ባህል
9.    ወደ ሃገራችን የገቡ ሚሲዮናዊያን ወደ ሃገራችን ሲገቡ ወንጌል ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ልማድ ባህልና ወግ አንዲሁም ስርዐት ይዘው በመግባታቸው ለሃገራችን ህዝብ ስለ ሃይማኖት የፈጠረበት ግርታ
10.  በየዘመናቱ የተነሡና አሁንም ያሉት የስሕተት አስተማሪዎችና ድርጅቶቻቸው የሚነዙት የክህደት ትምህርት በሃገሪቱ ክርስትና ላይ ያስከተለው ፍርሃት
11.    በቤተክርስቲያኒቱ ተጠልለው የሚገኙና የተሰወረ ዓላማቸውን ለማስፈጸም የሚታገሉ ቡድኖች የፈጠሩት የስም ማጥፋት ዘመቻ የፈጠረው ጥርጥር
12.  አብዛኛው የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመን ለመጽሐፍ ቅዱስ እንግዳና ባዕድ መሆን በቤተክርስቲያኒቱ ከጥንት ጀምሮ ዓላማዋን አንዳታከናውን እንቅፋቶች ሆነውባታል።

አስቀድማ ዓለም ክርስቶስን እና የክርስቶስ የሆኑትን ሁሉ እየተቃወመ በወህኒ ሲያስር ሲያሳድድና ሲገድል እንደዛሬው  ክፉ ትውልድ ዘር ጎሳና ነገድ ቋንቋ ባህል ሳያግዳት በፈቃዷ በትውልዱ ሶርያዊ የነበረውን ሰው ወደ እስክንድርያ በመላክ ክርስቶስንና ለድህነት የሆነውን ንጹህ ወንጌል ተቀብላ ስትሰብክ የነበረችውን ቤተክርስቲያን ከላይ በጥቂቱ በተዘረዘሩትና በሌሎችም ምክንያቶች ዛሬ ለምትገኝበት ውድቀትና ውርደት ተዳርጋለች፡፡
ልዩ ልዩ ነገዶች ወደ ሃገራችን ሲፈልሱ ይዘውት የመጡት ባህልና ወግ በተለያየ ዘመናት የዮዲት ወረራና ዓመት ግዛቷ ያስከተለውን የሊቃውንት እልቂት የመጻህፍትና የቅርሳ ቅርስና ውድመት 9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በየዘመናቱ የተነሱ የሃገራችን ነገስታት ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው ቤተክርስቲያኒቱን በስጦታና በሲሶ መንግስት (መሬት) ችሮታ እጃቸውን በመንፈሳውዊው ጉዳይ ማስገባታቸው፣ 1434-1468 የዘርዓ ያዕቆብ እንቅስቃሴ መነሳት 1524-1543 የግራኝ አህመድ ወረራ የፈጠረው የመምህራንና የቀሳውስት ጭፍጨፋ 1626-1632 ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በሃገራችን ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀው የካቶሊክ እምነት አስከትሎት የነበረው የመጻሕፍት መቆነጻጸልና መከላለስ /1626 - 1632/ በልዩ ልዩ ዓመታት ወደ ሀገራችን የገቡት ሚሲዩናዊያን ከወንጌል ጋር ይዘውት የመጡትና ያስገቡት ባዕድ ባህልና ወግ አንዲሁም 17 ዓመታት ሀገራችን ሰፍኖ የነበረው የሶሺያሊዝም ፍልስፍና /1666- 1983/ ወዘተ. በጥንታዊቷና በባለ ታሪኳ ቤተክርስቲያናችን የወንጌል አገልግሎት ላይ በቀላሉ ሊነቀሉ የማይችሉ ችግሮችን ተክለውባት አልፈዋል።
በተለይ የዮዲትና የግራኝ አህመድ ወራራ ያሰክተሉት የመጻሕፍትና የሊቃውንት እልቂት በርካታ ልበ ወልድና የተረት መጻሕፍት ባልተማሩና መናፍስታዊ ተልዕኮ በነበራችው ሰዎች እየተደረሱ ወደ ቤተክርስቲያን ያለከልካይ እንዲገቡና በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ላይ ራሳችውን ሾመው የመንግሥተ ሰማያት በር ዘጊና ከፍች ነን በማለት እስከዛሬ ድረስ የወንጌልን ቦታ እንደተኩ ይገኛሉ። እነዚህንና የመሳሰሉትን በቅዱሳን ስምና አንዳንዴም የእግዚአብሔርን ስም በተደራቢነት በመጥቀስ ራሳቸውን ሰውረው የሚገኙትን ድርስቶች ከተሰቀሉበት የከፍታ ስፍራ ወርደው ቦታውን ለከበረው የጌታችን ወንጌል እንዲለቁ ቤተክርስቲያናችም በጉዳዩ ነቅታ ወደቀደመው የወንጌል አገልግሎት ክብር እንድትመለስ የሚል ጥያቄን የያዘ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየጎላና እየደመቀ መጥቷል።
ይህም ጉዳይ ሰፊ ቁጥር ባለው ወጣትና በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዩች መካከል አለመግባባት ፈጥሯል። በአጭር ጊዜ በሁሉም የቤተክርስቲያናችን አጥቢያዎች የተቀጣጠለውና በልዩ ልዩ ምክያቶች የገቡትን የመናፍቃን መጻሕፍትና ትምህርቶች የይታረሙ ጥያቄ የችግሩን መፈጠር የሚፈልጉ ጥቂት ሰዎች እንደሚሉት አግዳና አዲስ እንዲሁም ጴንጤዎች ወይም ፕሮቴስታንቶች እያልን የምንጠራችው ድርጅቶች የፈጠሩት ጥያቄ ሳይሆን ሚሲዮናውያን ወደ ሀገራችን ከመግባታቸው በፊትና በአውሮፓ የፕሮቴስታንት ጀማሪ ነው የሚባለው ማርቲን ሉተር ሳይነሣ 15ኛው ክፍለ ዘመን በነበሩትና እግዚአብሔር በቤተክርስቲያናችን የገባባትን ስሕተት እንድታርም በየጊዜው አስነስቷቸው በነበሩት መነኩሴ በአባ እስጢፋኖስና በተከታዮቻቸው የተጀመረ ነው።
ዛሬ የተፈጠረውን ችግር በረጋና ብስለት ባለው ክርስቲያናዊ መልኩ እንዲፈታ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል። ምክኛቱም የአሁኑ ጥያቄ ሰፊ ቁጥር ባለው የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመን ኅሊና ውስጥ ሥር የሰደደና የሁለቱንም ወገኖች ብስለት የሚያስፈልገውና ጥንቃቄ የሚሻው ጉዳይ ነው። ትናንት በወጣቶች ላይ ያነጣጠረው ጣታቸው ዛሬ ደግሞ አንቱ የተባሉትን መተኪያም የሌላቸውን መምህራንና ሊቃውንት ጴንጤ ተሐድሶ ሆነዋል ወይም ይደግፋሉ በማለት ህዝብ በማሳደም ከጉባኤና ከመቅደስ እያሳገዷቸው ነው፡፡ ስንት መምህራንና ሊቃውንት ከወንጌል አገልግሎት ታግደው በቤታቸው ውለዋል?
ወጣቶቹ ይዘዋችው የተነሱት ጥያቄዎች በመጽሃፍ ቅዱስ ሳይመረመሩ ዝም ብሎ ጸረ-ማርያም ጸረ-ቤተክርስቲያን እያሉ ከማውገዝ ጥያቄያቸው ይምጣ መምህራን ይዩት በማለት የተናገሩ ሁሉ በተለጣፊ ስሞ እየቀቡ ይጣላሉ።
እነዚህ ቤተክርስቲያናችንን ለከፋ ችግር ለመዳረግ ታጥቀው የተነሱ በመሆናቸው ብጽዐን ጳጳሳትን ሳይቀር ተሃድሶ ናቸው በማለት አባቶችን ከምእመናን ጋር ለማጋጨት ብሎም መረጋጋትስ እንዳይኖር ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው። በእነዚህም ስም አጥፊዎች ቅጽረ-ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ የታገዱ ሰዎች ቁጥር የቤተክርስቲያናችንን የወደፊት እጣ እጅግ ወደ ሆነ ደረጃ ያደርሰዋል። በየአካባኢያችን አያሌ የወጣት ማህበራት በስም አጥፊዎች ሴራ ተበትነዋል። ወጣቶቹ ቤተክርስቲያናችንን በማለት የደረሰባቸውን ሁሉ በመታገስ ለመማር ቢሞክሩም ችግር ለመፍጠር ታጥቀው በተነሱት ጥቂት ሰዎች ተደብድበውና ተፈነካክተው ከቅጽረ ቤተክርስቲያን እንዲባረሩ ተደርጓል።  
«አንድ ስህተት ተፈጥሯል ጥያቄያችን በትክክል ለብጻአን አባቶቻችን አልደረሰም ቢደርስ እንኳ በግርግር ፈጣሪዎች ምክንያት አልተረዱልንም ብለን እንገምታለን። የወጣቶቹ ጥያቄ ጳጳሳትን ሽሮ ላላ ጳጳስ ይሾም ቀሳውስትና ዲያቆናትን ወይም መነኮሳት አያስፈልጉም አልነበረም። ቤተክርስቲያናችንም ሙሉ ወንጌል መካነ ኢየሱስ ትሁን የተዋበው ድንቅ ባህላችን በእንግዳውና በውጭ አለማት ባህል ይለወጥ የሚል ሃሳብ የያዘ አይደለም።»
ክፉዎች ግን ለተሰወረ ዓላማቸው እንዲያመቻችው አድርገው በሃሰት በጋዜጣቸው በመጽሄታቸው በአገኙት የክርስቶስ ወንጌል አውደምህረት ላይ በህዝቡም ሆኑ የተከበሩት የቤተክርስቲያኒቱ ውሳኔ ሰጪ አካላት ብጽአን ሊቃነ ጳጳሳት የወጣቱን እውነተኛ ጥያቄ አቅጣጫ በማዞር እግዚኦ በሉ ተሃድሶ የሚባል ጭራቅ ልዪ ፍጡር መጣ በማለት ወደ ህዝቡ ሲደርሱ ጸረ  ማሪያሞች ወደ ቀሳውስት ሲደርሱ ቀሳውስት የማይወዱ ወደ ጳጳሳት ሲጠጉ ቤተክርስቲያናችን በፓስተር ትመራ ወደ መጠጥና ጭፈራ ቤቶች ባለቤቶች ሲደርሱ መጠጥ የሚቃወሙ .. በማለት ለአላማቸው መልካሙን ጥያቄ ያጣምሙታል።  
ትልቁ የሕዝቡን ጆሮ ሰጥቷቸው ያለው የፈጠራ ድርሰታቸው ሃይማኖት ይታደስ ይላሉ በማለት ሕዝቡን በማወናበድ ሳይ ናቸው ሃይማኖት እንዴት ይታደሳል፧፨ ሰው ሰራሽ ካልሆነ በስተቀር፨ የክርስትና ሃይማኖት ደግሞ በጌታችን ሞት የተመሠረተች በሐዋርያት አባቶቻችን የተሰበከች በደጋግ አባቶቻችን የተመሠረተች በእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነች ናት።
ታድያ እግዚአብሔርን ማን ሊያርመው ይችላል፧ የዚህ ትውልድ ሆነ በቤተክርስቲያኒቱ ያሉ ደጋግ የወንጌል መምህራን ዋና ጥያቄ በየዘመናቱ ወደ ቤተክርስቲያናችን የገቡና የክርስቶስን ወንጌል ቦታ የያዙ ሁሉ ቦታውን ለከረው ወንጌል ይልቀቁ የሚል ነው። አንድ ምሳሌ እንውሰድ  መዳን የሚገኝው ክርስቶስን በማመን ነው ብለው ሐዋርያቱ የሰበኳትን ሃይማኖት አንዳንድ ሰዎች ገብተው መገረዝን ካልጨመራችሁ አትድኑም በማለት በተወደደችው ሃይማኖት ላይ የጨመሩትን በመቃወም መገረዝ እንዲሻር ደብዳቤ ጽፈው ይህን የክርስቶስን ሕግ የሚቃወሙ ግን ከፈለጉ ራሳቸው ይቆረጡ እንጂ ግዝረት ከደኅንነት ጋር አይያያዝም አይጠቅምም በማለት ተቃውመዋል ገላ. ፭፥ ፪፡ ፲፩ የሐዋ. ፲፭፥ ፳፪፡፳፱፡፡ አሁን ሐዋርያት ሃይማኖት አዳሾች ናቸውን? ሊባሉስ ይችላሉን? በፍጹም ይልቁንም ሃይማኖታቸውን ከብክለት ጠበቁ እንጂ። የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ጥያቄ ይህ ነው። ሃይማኖት እንዴት ይታደሳል? በሃይማኖታችን ላይ የተደረተ ሁሉ ግን መታደስ አይደለም መፍረስ ሲያንሰው ነው።
አንዳንዶችን ያታለሉበትና የዓላማቸው ማስፈጸሚያ የሆናቸው ዘዴም ቤተክርስቲያናችን ፈጽሞ ስሕተት የሌለባት የነጻች እንከን አልባ እንዲያውም መላእክት እንኳ የሚያምልኩባት ናት በማለት የታሪካችንን እና የዕድሜያችንን ርዝማኔ እንደመጋረጃ በመጠቀም የሚያናፍሱት ወሬ ነው።
ነገሩ ያልገባቸው አልያም ለቤተክርስቲያን ውድቀት ሆን ብለው የተነሱ ካልሆነም የዋህነታቸው እንደመጽሐፍ ቅዱስ ያልሆነ ሰዎች እንደሚሉት የትውልዱ ጥያቄ ዓላማ ቤተክርስቲያንን የሚያፈርስ ሃይማኖት የሚያፍልስ ሃገር የሚቆርስ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን የሚጠላ ክርስቶስን ፍጡር ሰጋጅ አድርጎ የሚያስተምር እንዲሁም ለወንጌል ክብር ስለ ክርስቶስ ስም መከራ የተቀበሉትንና እየተቀበሉ ያሉትን የእምነት አርበኞች የሚቃወም አይደለም አይሆንምም።

ይቀጥላል

28 comments:

 1. sejemere enanete Wenejelen enij Wengelen meche tawekalacho ena new mekebatere yejemerachowete ....enanete ye Dabilose Leijoche selewenacho min gizem Wenejelene tawero endewene enij Wengelen Mesebek atechelom ...Wengelen le mesebek kasebacho mejemera Nisa megebate ena ye Egizahber Leij mewen yasefelegale

  ReplyDelete
 2. menswfikan zor belu woregna

  ReplyDelete
 3. ወሬ ጠላሁ!!! ቀዳዳ ብቻ!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. Yemttifutn book (metihaf) lalanebe ewunet lewongel yemtseru ymeslal daru gn letifat new.lezihm masaya yemihunew. ethiopia crstnan yetekebelechw 31E.C new enj,enante endemtlut 4th c. ayidelem.

  ReplyDelete
 5. ከመቀላወጥና የጋጥ የቃቱን ከመለፍለፍ ራስን ለንስሃ ማዘጋጀት

  ReplyDelete
 6. Please You 'Aba selamas' be orthodox."ገድል ወደ ሞት ሲወስድ ወንጌል ግን ወደ ሕይወት ይመራል" is by no means Orthodox preaching rather that of protestants.Don't you know that ገድል is greatly supported by Bible??? when any one look your preaching, no one can deny that you are completely protestants."Birds of the same feather fly together"

  ReplyDelete
  Replies
  1. Tebarek. Gira sigebachew Orthodox lmemsel mokeru enji yaw Protestant nachew!!!!

   Delete
 7. በጣም የሚገርመኝና ሊገባችሁ ያልቻለው ገድል ማለት ስለወንጌል፣ስለክርስቶስ መስዋእት የሆኑ ተግባራቸው የተጻፈበት መጽሃፍ ነው በወሬ ጌታ ጌታ ሳይሆን በተግባር ኖረውበት ስለሆነ ብዙ ባትዳፈሩ ጥሩ ይመስለኛል ።መድሃኒአለም ኤየሱስ ክር ስቶስ አይነብሃናችሁን ያብራላችሁ

  ReplyDelete
 8. "በሃይማኖታችን ላይ የተደረተ ሁሉ ግን መታደስ አይደለም መፍረስ ሲያንሰው ነው።" GOD BLESS YOU!

  ReplyDelete
  Replies
  1. መጀመሪያ አንተ ታደስ!!!!!!!!!!

   Delete
  2. እኔ ማነኝ ታዲያ????????????????? የእኔ እና የሌሎች የእግዚአብሄር ምርጦች ስብስብስ አይደል እንዴ ቤተ ክርስቲያን የሚባለዉ???? ነው ወይስ በቡልኬት የተገነባው ህንጻ ነው ቤተ ክርስቲያን????????? ታዲያ ሰዉ አይሳሳትም እያልከኝ ነው???????? ከተሳሳተስ ከስህተቱ መመለስ / መታደስ የለበትም ትላለህን?????????? መመለስ/ መታደስ የለበትም መቼም አትለኝም!!!!!! ስለዚህ ለራሴ እለት እለት እየታደስኩኝ እስክሞት ወይም ጌታ እስኪመጣ እጠብቃለሁ:: ይህ ማለት ከቤተ ክርስቲያን አንዱ አካል ታደሰ ተመለሰ ማለት ነዉ:: ጌታ ማስተዋሉን ያድልህ

   Delete
  3. ብትታደስማ ኖሮ ሐዋርያው ያለውን ታስተውል ነበር ሃይማኖትን ይቀበሉታል እንጂ አያድሱትም
   የይሁዳ መልእክት 1
   3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

   አለ እንጅ አሁን እናንተ እንደምዘላብዱት አልተናገረም:: ድንግል ልቦና ትስህ!!!

   Delete
 9. ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል ይላሉ አበው። ክርስትና ወደ ሀገራችን በ4ኛው መ/ክ/ዘ እንደገባ ተናገርክ አይደል? ለመሆኑ ክርስትናን ቀድመው ሣይቀበሉ ደርሶ ሊቀ ጽጽስና መሾም አለ እንዴ? በተሃድሶው መንደር ከሆነ ሊሆን ይችላል። እንደ ቅድስት ተዋህዶ ቤ/ያን ታሪክ ግን በሐዋ.ሥ 8:26-39 የተጠቀሠዉ ኢትዮጽያዊው ጃንደረባ በ34 ዓም ክርስትናን ወደ ኢትዮጽያ እንዳስገባና በ4ኛው መክዘ ክርስትናው ብሔራዊ ሃይማኖት እንደ ሆነ ተቀምጧል። ስለማታውቀው ገድልም ለመዘባረቅ ሞክረሄል፤ ስለ ገድል ለመረዳት ወንጌልን ተረዳ መጀመርያ ወዳጀ፤ አነበብከው እንጅ መቼ ተረዳኸው። ባዶ በርሚል መጮሁ ልማድ ነው። አወ ገድል ለተሃድሶ ገደል ሲሆን ለተዋሕዶች ግን ያወጣል ከገደል። በቤ/ያን ያሉ ችግሮች አስተዳደራዊና አንተና መሠሎችህ የምትጽፋት ጹሁፍ ነው፤ ይሁን እንጅ አምላክ ይመስገን አሁን አሁን ሁሉም እየተረዳችሁ ነው።

  ReplyDelete
 10. Thank you Aba Selama for putting out important information, religious teaching articles, and historical facts.
  It is amazing how Satan's disciples get roused up and start spewing insults at anything that comes out on Aba Selama. They never read what is written. If they read it, maybe their horns might grow shorter and they might look like humans. As it is, their ugliness both in spirit and body is shown in their vile words they vomit out of their mouths on to these pages. What parents brought up these types of wild bunch. Satan himself believes there is a God, he just does not want to acknowledge and worship Him. Eight out of the 9 of you that commented on this article belong with your master. Would you read? I know it is difficult, but would you try to understand then speak or write even if you are deceitful you would look half way believable. As your master does, He tells a little truth then a lot of lies. That is how he made you disciples, is it not? Grow up, a 10 year old kid can think and put down ideas than you morones!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ante yefelekewn asteyayet yemiset sitefa erash lerash asteyayet mesteth yemigermnew . yichin tiyake gin melsilign yehawaryat siran sinmeleket hawaryat abatochachin kgeta erget behuala yaderegutin tegadlo neew miterkilin tadya behawariat egir yeyetekut tsadikan semaitat yaderegutin tegadilo bitsaf lemin yihon yangebegbachihu?

   Delete
 11. እውነትም ባዶ በርሜል ..... ደንቁራችሁ ሰውን ለማደንቆር ትደክማላችሁ ግን መቼም አይሳካላችሁም፡፡

  ReplyDelete
 12. በብዛት ገድሎች ኑፋቄ የተዎላባቸው ናቸው የእግዛብሄር ስም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ስለተጠራና መንፈሳዊ መስለው ስለታየ እውነት አደለም መመዘኛ ሊኖር ይገባል ለምሳሌ ፅድቅ በእምነት የሚገኘው እያለን ገድላት ላይ ግን የገድሉ ባለቤት በሆነው ስም በመደገስ ሆዳም ሁላ፣ቦታ በመርገጥ በመሳለም ይለናል ገድሉ ላይ ያሉት ያለክፍያ የተሰጠንን የእግዛብሄርን ፅድቅ ሊያስረሳ ይመስላል ለዚህም ይመስለኛ ሰው ማረፍ ያቃተው እዚ ሲባል ይሄዳ እዛም አለ ይሄዳል ዝክር ዘክር አይ እሱ ብቻ አይበቃም እየሩሳሌም መሄድ አለብህ ግሸን ከሄድክ ሰባት ትውልድ አረ ስንቱ ይቅበዘበዛል ደሞስ እሱ የሰጠን ፅድቅ አይበልጥም እኛ ከምንሰራው ጌታ ልብ ይስጠን ገድል ወደ ገደል ነው ሚወስደው ከቤታችን ተጠራርጎ ይውጣልን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያቆብ ስሞት ወስዳችሁ ከአባቶቼ መቃብር ቅበሩኝ ያለው አረ ለመሆኑ ምን ፈልጎ ነው ንግስተ ሳባ ምን ፈልጋ ነበር እየሩሳሌም ድረስ የሄደችው; ይህን ያደረገ እስከ 7 ትውልድ እምራለሁ የሚል ቃል መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ የለም ልት፤ል ነው; በዮርዳኖስ ውሃ ተጠመቅ ሲባል እዚህ ደረስ ለምን ለፋሁ ለዚ ለዚህማ የሀገሬ ወንዞች ይሻላሉ ያለው ያ ለምጻም ንጉስ ማን ነበር በመጽሃፍ ቅዱስ የተጠቀሰው አንተም የዛው ቢጤ ነው ዕኛ ጥቅሙን ያወቅነው ወደተቀደሰው ቦታ እንዞራለን

   Delete
 13. gedelema gedel new

  ReplyDelete
 14. ከክርስቶስ የመስቀል ላይ ገድል በላይ ምን ተፈልጎ ነው ሰይጣንን አመንኩሶ ከእግዚአብሔር ጋር የማስታረቅ የውሸት ገድል ፍለጋ?
  ይልቅስ ጸሐፊው ገድል ወይስ ገደል የሚለውን ያንን ከእንቅልፌ ያነቃኝን ጉሩም መጽሐፍ እንደገና እንዳነበው አሳሰበኝ፤ በርቱ እናንተ የቤ/ክርስቲያኒቷ ታማኝ ልጆች!!!!

  እውነቱ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያባትህ ልጅ ውሽቱ!!!!

   Delete
 15. ባንተ ድምዳሜ የሐዋርያት ገድልን የሚተርክልን የሐዋርያት ሥራ የወንጌል ክፍል ስለሆነ ወንጌልም ወደ ገደል የሚወስደን ነዉ ማለት ነዉ:: ወይ አለማወቅ ! ይቅር ይበልህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሲጀመር የተክልዬ ገደል ከሀዋርያት ገድል ጋር በምን ሲገኛኝ ነው ምታነፃፅረው ማስተዋል ያብዛልህ ሀዋርያት አንድና አንድ ኢየሱስን አሳይተውን አክብረው አምልከው ሰብከው መከራ ተቀብለው ያለፉ ናቸው ወታደሩ ተክልዬ እራሱን ሰብኮ የሰራውን ታምር በስሙ የሚሰጠውን ጽድቅ የተገባለት ቃልኪዳን በጣም አስነዋሪና ዘግናኝ በሆነ ከመስቀሉ ስራ ጋር አስቀምጦ እራሱን የሚያስመልክ ገደል ነው እና በምን እስኪ ተገናኙ ለምንስ እነፔትሮስ ይህን አላስደረጉም? ማስተዋል ያድለን ከገደል ላወጣን ጌታ ክብሩ ይስፋ

   Delete
 16. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሐሪያት ሥራ ለምን ድነው የሐዋሪያት ሥራ የተበላው? እርሱንስ ታምናለህ? ከወንጌሉ ውስጥ ቅዱስ ጳውሎስ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ ያለውስ ላንተ ምን ድነው? የቀደሙ አባቶቻችሁን ተመልኩ በእምነትም ምሰሉአቸው የተባለውስ ምን ማለት እንደሆነ ተረድተህ ታውቃለህ? ክርስትና ማውራት ሳይሆን መኖር እንደሆነ አሰበህ ታውቃለህ? መኖር ከሆነ ደግሞ ምን ማለት እንደሆነ አስበህ ታውቃለህ? ማመን እና መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ እማ ድያብሎስም ያምናል ያውቃልም፡፡ የእርሱ ተከታዮችም ቢያንስ ለመቃወም እና ለማጣመም ሲሉ ያውቃሉ፡፡ የማይችሉት ግን በዚያው ሊክ መኖር እና ስለጌታ ፍቅር ሲሉ መንፈሳዊ ተጋድሎ ማድረግን ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ቅዱሳን ለማውራት አንደበታቸው ዲዳ ነው፡፡ ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ " በቅድሳን ላይ ……. አንደበት ዲዳ ይሁን" የሚለው ደርሶባቸዋል፡፡ አንተም የዚሁ አካል ስለሆንክ ደርሶብሀል፡፡ ለዚህ ነው ስለ ቅዱሳን ማወቅና ማገናዘብ መናገርም ያልቻልከው፡፡ እግዚአብሔር ይግለጥልህ!

  ReplyDelete
 17. ተሐድሶ ሁሉ በየ አዳራሽ ብትቦራጨቅ አይሻልም! ተዋሕዶዎች እንደ ሚስማር ናቸው፡፡ ከላይ ሲመቱ በእንዳንተ አይነት ሲሰደቡ ላይነቀሉ ይጠብቃሉ፡፡ በየአዳራሹ እያደረክ ያለኸው ተግባር already recorded, no one denies the fact, never! እመኑኝ ይኽቺ ቤተክርስቲያን አትገኝም፡፡ በእውነተኛው የክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተች ናትና፡፡ ለሐራ ጥቃ/ተሐድሶ/መናፍቃን/ፕሮቴስታን ተላልፋ አትሰጥም፡፡
  አሁን በምን ያህል ፍጥነት ዝናራችሁን ወርውራችሁ እየጨረሳችሁ እንደሆነ እንኳን እየገባችሁ አይመስለኝም፡፡ የቱንም ያኽል ተደራጅተህ እንኳን ብትንቀሳቀስ በክርስቶስ ደም የተመሠረተችዋን ተዋሕዶን መንካት አትችልም፡፡ በድንግል ማርያም ምልጃ ትጠበቃለቻ! በመላክት እቅፍ ውስጥ ናት! ከሺ ዓመታት በላይ ገድላቸውን ስታነብ ለነበረች ሐዋርያዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለገድል ለማስተማር ያነሳሀው ነጥብ አይመጥናትም!!! ዞርበል!!! ደርሶ አስተማሪ!!! አዳሜ ሐራ ጥቃ/ተሐድሶ ስትወሰልቺ ተገኝተሽ ተባረርሽ የሱን ቁጭት በየአዳራሹና በየብሎጉ ስትቀድ ትኖራለህ!
  አንድ ቁም ነገር የሚጠቅማችሁ ከሆነ ልንገራችሁ፡፡ እናቴ 15 ልጆች አሏት፡፡ አሁን የ90 ዓመቷ ነው፡፡ ጤነኛ ናት፡፡ 15ቱም ልጆቿ ጤነኞች ናቸው፡፡ 15ታችንም የተወለድነው ሆስፒታል እንዳይመስልህ፡፡ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ማርያም ማርያም እየተባለ፡፡ ድሳነ ሩፋኤል እየተነበበ፡፡ የቅዱሳኑ ገድል እየተሰለሰ፡፡ ብዙ ዕጽፍ ነበር ግን ምንያረጋል… እባካችሁ ንሰሐ ንሰሐ ንሰሐ!

  ReplyDelete
 18. Betekrstiyan Tetadese yemenel Ewenet lekrstose mengeste Yemenekena kehone Agelgelotachen megemeriya Belebachen metades Enelewet..keza ye orthodox Betekrstyan cheger enkwan binorbat Hulwen wedemichelew Geta Entselye....Mene yadergal Ethiopia weste krstena seme bech.Ezeme Ezam bado chwet Ye0×0=0 hayemanot keyern Enge Bekrstose Alarefenem .kerstena yelet elet nuro new , kerstena tehetena new, kerstena begonet, chernet, yewahenet, feker , yelelawe dekame yenenew belo metseleye new.Erese bersachen benenekakes eresebersachen endanetefafa Egziyabeher yedereselen. Amen!!

  ReplyDelete
 19. The issue here is not about whether these human beings considered saints are creating confusion between the centerpiece Jesus Christ and these saints which by any form comparison do not have a single item that one can say about their devotion to Christianity is surpassing way too many levels remaining on a parallel level with almost an dimension similar to the creator. who gave the standard in regards to the dimension is we human beings;when taking these in to context, what is obvious is that the parishioners are( were)deviated from the trinity,which is that christians ion Ethiopia are worshiping saints on equal dimension with the trinity, because they find the saints who would stand on their behalf do not forget we have KIRSTOS SEMIRA who relentlessly work to achieve sooner or later that the reconciliation between JESUS and lucifer becomes , final; it is said that she has the power to let 3000 souls leave hell and as result of her mediation which GOD is doing it everyday-such an embarrassing,insult and mockery which really makes the people rely on human beings, so it is not a cliff but also suicidal.
  the aposstels are completely different we are reading the bible because they are the ones who for sure were there during the time of Jesus, the case of Paul is different Jesus spoke to him and used him as instrument to reveal the Gospel through the entire world. and also these disciples did not request their followers to see them on equal level to Jesus. Had the people of Ethiopia been fully aware of the trinity would people depend on witch, witch doctors, voodoo and on those who casts spell.
  But whether the current generation of Ethiopia able to read and write is willing to go back to where our ancestors were about 600 years a go or would need to be renewed is up to the holly spirit, but the holly spirit will be their when our hearts are wide open to receive Jesus. The current generation seem unwittingly favoring zeal out of the center piece of CHrISTIANITY.

  ReplyDelete
 20. “ ክርስትና ካሉ……….. መኖር ነው !!! ”
  አንዳንዶች ሀዋርያትን ትተው ከማያምኑ ፈሪሳውያን ክርስትናን ሊማሩ ይሞክራሉ፡፡ ለምን? ሲባሉ “ፈሪሳውያን ከሀዋርያት በፊት የነበሩ ናቸው” ይላሉ፡፡ እውነት ነው ፈሪሳውያን ብዙ ቆይተዋል፣ የሙሴም መንበር ላይ ተሰይመው ይሆናል(እንደ ሙሴ መሆን ባይችሉም)……. ነገር ግን ሀዋርያት ያላቸው ብርሃን፣እውነት፣ህይወት፣መንገድ፣ፍቅር፣ሰላም፣ጥበብ፣ማስተዋል፣እምነት፣ፀጋ፣ሀይል…………. ክርስቶስ እየሱስ የላቸውምና እንደምን ክርስትናን ከነሱ ልማር - መሰረትና ራስ የሆነው ከነርሱ ጋር ሳይኖር?! በርግጥ ጌታችን ከሙታን ተነስቱአል ፡፡ ስለሆነም ክርስትና ትናንት የተኖረ፣ ዛሬ እየተኖረ ያለ፣ ነገም የሚኖር ህይወት ነው፡፡ ለነዛ ግን ትናንት የተኖረ ብቻ …..ዛሬ ላይ ግን የሞተ ቅርስ ነው!! ፡፡ምክንያቱም ለነሱ ክርስቶስ ዛሬም በመቃብር ነው……… ከሞት አልተነሳም…..… በልባቸው ገለውታል ! ፡፡ አናምነውም እንዳይሉ ህዝብ ያምፅባቸዋል፣እናምናለን እንዳይሉ የሀዋርያት ትምህርት ይሆንባቸዋል :: ስለዚህ ስሙን ለይምሰል እየጠሩ የሞት ትምህርታቸውን ይዘራሉ፡፡ እግዚአብሄር ከህዝባችን ላይ ይንቀላቸው!!! የእግዚአብሄር ልጅ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ብቻውን ያድናል!!! ፡፡

  ክብር ለእግዚአብሄር ለአምላካችን ይሁን!!!
  የክርስቶስ ፀጋ እና ሰላም ይብዛልን፡፡ አሜን ! ! !

  ReplyDelete