Wednesday, May 18, 2016

ሦስቱ የዓለም ፈተናዎች፤   Read in PDF                                      
ፈተና ከሰው ልጅ ሕይወት ጋር የተያያዘ ነው። ፈተናን አልፎ ውጤታማ ደረጃ ላይ መድረስ፣ በፈተና ወድቆ ከወደቁበት ምክንያት ተምሮ እንደገና ፈተናውን ማለፍ ፈተናውን ሳያልፉ እንደወደቁ መቅረት የሰው ልጅ በሕይወቱ ውስጥ የሚገጥሙት የማያቋርጥ ሰንሰለታዊ አዙሪት ነው።  አስታውሱ! ከመጀመሪያው የጌታ ፍርድ በኋላ ፈተናዎቹ በበቂ ምጣኔ ሲሆኑ መሠረታዊ የሰው ልጅ የሕይዎት ፍላጎቶች መሆናቸውን በመዘንጋት የቀረበ አይደለም። ሆኖም አመጣጣቸውና ከመጠን በላይ በሆነ ፍላጎት የሰውን ልጅ ሲያጠምድና ሲያሰክሩ የሚያሳድሩት ተጽዕና የሚያስከትሊት አደጋ ምን ይመስላል የሚለውን ለማጠየቅ የቀረበ ነው።
መጽሐፍ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተጠንቀቁ እያለ ሲመክር እኛም ወደ ፈተና አታግባን እያልን ስንጸልይ ፈተና እና የሰው ልጅ በማገናኘት እንደሚፈልጉት ብዙ አጋጣሚዎች እንዳለ ወይም የሰው ልጅ በሚሄድበት የሕይወት መንገድ አጋጣሚ ሁለ ፈተና እንደሚያገኘው እንደሚከተለውና አብሮትም እንደሚሄድ አውቆ ከፈተና ለመዳን ዘወትር እንዲጸልይ የታዘዘበትን ስንመለከት ብቸኛ መፍትሔው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቆ ማለፍ እንደሚገባ ያስተምረናል ማለት ነው።
በመሆኑም በፍጥረታት የመጀመሪያው ዘመን /ኦሪት ዘፍጥረት/ ጀምሮ እስከ አለንበት የዓመተ ምሕረት ዘመን/ሐዲስ ኪዳን/ ድረስ የሰው ልጅ ከፈተና ገጠመኝ ውጪ ሆኖ የኖረበት ዘመን የለም። ብዙዎች በፈተና አልፈዋል፤ ብዙዎች ከፈተና ወድቀው ከወደቁበት የፈተና ሁኔታ ተምረው እንደገና ፈተናውን ወስደው አልፈዋል፤ ብዙዎችም በፈተና ተረተውና ተሸንፈው ወድቀው ቀርተዋል።
በዘመነ ኦሪት የመጀመሪዎቹ የሰው ልጆች እግዚአብሔር ከዚህ አትብላ ብሎ ወይም ወደ ፈተና እንዳትገቡ ብል የከለከላቸውን ፈተና ማለፍና ማሳለፍ አቅቷቸው የተከለከሊትን ምግብ በሊ፤ በመብላታቸውም ምክንያት በፍርድ አደባባይ ቀረቡ፤ በተድላ በደስታ፣ ያለድካም ያለኅማም፣ ያለሀፍረት ያለሰቀቀን፣ ያለፀብ ያለሙግት ከሚኖሩበት የገነት ሕይወት ተሰደው እንደወጡና ለፈተና የዳረጋቸውን ምግብ በውጣ ውረድ በድካም በጣርና በጋር እንዲበሊ ተፈረደባቸው። እዚህ ላይ የምናስተውለው ነገር ምግብ እራሱ ፈተና ሆኖ የማይሻር ይግባኝ የማይጠየቅበት በምድር ላይ የዘላለም የማይቀረውን የሞት ፍርድ ቅጣትን በሰው ዘር ሁለ እንዳመጣብን መረዳት ይገባናል።
የእግዚአብሔርን መንበረ ዙፋን ከበው ሌት ተቀን ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ! እያለ እንዲያመሰግኑ ከተመረጡት ቅዱሳን መላእክት መካከል ሳጥናኤል የመላእክት አለቃ ሆኖ እንዲያገለግል የተሰጠው ቅድስና አልበቃው ብሎ፤ በፈጣሪው የመፍጠር የማይመረመር ሥልጣን ውስጥ ቅናት አገረሸበትና  እኔ ፈጣሪ ነኝ! ብሎ በፈጣሪው ላይ አመጸ።  መንግሥት በመንግስቱ፤ ጎልማሳ በሚስቱ ፤እግዚአብሔር በመለኮቱ  ቀናኢ ነውእኔ ቀናተኛ  አምላክ  ነኝ ፤ ከእኔ  ከፈጣሪህ በስተቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ተብሎ እንደ ተጻፈ በሊቃውንትም እንደተሰበከ፤ ፈጣሪ በሳጥናኤል ላይ የማያዳግም ፍርድን ወሰደ። ከማኅበረ መላእክት አንድነት ለይቶ ጣለው። ለሕይወት ሳይሆን የጥፋት መንገድ አለቃ ሆኖ ቀረ። ሳጥናኤል ከተመረጠበት ከፍተኛ የማዕረግ ልዕልና ተልዕኮ ተለይቶ የተሰናበተበት ምክንያት ከተሰጠው ሥልጣን በላይ ሌላ የማይገባው ከመጠን ያለፈ የሥልጣን ባለቤት ነኝ በማለቱ ነው።
እዚህ ላይ የምንረዳው ከመላእክት መካከል እንኳን የፈጣሪን የመፍጠር ሥልጣን ለመቀማት የሥልጣን ጥመኝነት ተግባር ሲያንጸባርቁ ያመጣባቸው ፈተና ለከፋ ዘላለማዊ የጥፋት አደጋ የሚዳርግ መሆኑን ነው።
የዓለም መድኅኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋለ ሥጋዌው በዚህ ዓለም ሲመላለስ ቅዱስ ቃሊን ለዓለም እንዲያስተምሩ ሂዱና ዓለምን አስተምሩ ተብለው ከታዘዙ የአገልግሎት መመሪያ ከተሰጣቸው አሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት መካከል፤ ይሁዳ በመሆን ለድሆች መርጃ የሚሆን ገንዘብ የሚሰበሰብበትን የሳጥን ቁልፍ እንዲይዝ የተመረጠ የታመነ ነበር። ገንዘብ የሚሰጠውን ጊዚያዊ ጥቅም ቀስ በቀስ ከተለማመደ በኋላ ለከፍተኛ ፈተና ተዳርጎ፤ ለሐዋርያዊ ተልዕኮ የመረጠውን ጌታውን ለሰላሳ ብር አሳልፎ ለአላዊያን ነገሥታት ለካሀዲያን የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ጉንጩን ስሞ ሸጠው። 

ይሁዳ በገንዘብ ጊዚያዊ ጥቅም ተገፋፍቶ ጌታውን አሳልፎ እንደሸጠው ባወቀና በነቃ ጊዜ ተቅበዝብዞና ከመጠን በላይ ተጨንቆ ራሱን በራሱ በዛፍ ላይ ሰቅሎ ይቅርታ የሌለው የሞት ሞትን ሞተ። በዚህ አንቀጽ ለሦስተኛ ጊዜ የምንረዳው ገንዘብ ለጊዜያዊ ጥቅም፣ ጊዚያዊ ችግርን ወይም ፍላጎትን ለማቃለልና ለሟሟላት ሲባል ከማያልፍ ዘላለማዊ የቅድስና ሕይወት መንገድ አስክዶ ፍጹም ሰው /በጭራሽ ሀጥያት ያልነካውን/ በገንዘብ አሳልፎ መሸጥና እስከማስገደል ድረስ የፈጸመው ቅጥፈት በመጨረሻ ውጤቱ ተመልሶ በገንዘብ ምክንያት በፈተና ወድቆ  እራሱን በመግደል የአስከፊ ፍርድ ባለቤት እንደሆነ እንማራለን ማለት ነው። አሳልፎ የሰጠኝ እርሱ የባሰ ሀጢያት አለበት። ብሎ ጌታ እንደተናገረ ። ዮሐንስ 19፤11
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆረንጦስ አርባ ቀንና ሌሊት በጾምና በጸሎት ተወስኖ ቆይቶ ባጠናቀቀበት ወቅት በሥጋ ሲራብ ፈታኙ ዲያቢሎስ፤ ጌታ ሰው ሥጋ መልበሱን እንጂ አምላክ መሆኑን ዘንግቶ ፈተናዎችን አወጠንጠኖ ሊፈትነው ቀረበ፤ ዲያቢሎስ ጌታን እንዲህ አለው «በውኑ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እስቲ ድንጋዩን እንጀራ እንዲሆን እዘዝ አለው?» ይህ ፈተና በምግብ የመጣ ፈተና ነው። ጌታ እንዲህ ሲል መለሰለት ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብ፡ ተጽፏል። ሲል በምግብ የመጣውን ፈተና ውድቅ አደረገው።
ቀጥሎም ዲያብሎስ፤ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ አንድ ከፍተኛ ቦታ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታትን ግዛት ሁለ በአንድ ቅጽበት አሳየውና  እንዲህ አለው «አንተ ለእኔ ብትሰግድልኝ ለእኔ የተሰጠኝን ሀብትና ንብረት እሰጥሀለሁ አንተም ለፈለከው ትሰጠዋለህ» በማለት ሁለተኛውን የገንዘብ  ፈተና አቀረበለት፤ ጌታ ግን እንዲህ አለው ለአምላክህ ለእግዚአብሔር  ብቻ  ስገድ እሱንም አገልግል። ተብሎ ተጽፏል አለውና ሁለተኛውን የገንዘብ ፈተና ውድቅ አደረገበት። 
ከዚያም ዲያቢሎስ ኢየሱስን ወደ ኢየሩሳላም ወስዶት ከቤተ መቅደስ ጫፍ ላይ አውጥቶ «አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እስቲ ከዚህ ከቤተ መቅደስ ጫፍ ላይ ወደታች ዘለህ ውረድ» በማለት በሥልጣን ፈተነው፤ ጌታ ግን አምላክህን እግዚአብሔርን አትፈታተነው። ተብሎ ተጽፏል በማለት ሦስተኛውን  የሥልጣን ፈተና ለሦስተኛ ጊዜ ውደቅ አደረገው። ለቃስ 4፤1-13
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፆሙን በአጠናቀቀበት ማግስት የቀረቡለትን ሦስቱን የዓለም ፍተናዎች አስቀድሞ የተነገረ መሆኑን ማስረጃ እየጠቀሰ በአምላክነቱ በድል አድራጊነት ተወጣ። ፈተናዎቹን በትህትና ተቀብሎ በድል አድራጊነት ያስተናገዳቸው ዓለም ከነዚህ ፈተናዎች የማያመልጥ መሆኑን ሲያስተምረንና በፈተና ወቅት በጥንካሬና በትግሥት መጠበቅ፤ ለሚያልፍ ነገር የማያልፍ ክብርን እንዳያሳጣን ሲመክረን ሲያስተምረን ነው። ለዚህም ነው ወደ ፈትና እንዳትገቡ ተጠንቀቁ ያለው። እነዚህ ሦስቱ የዓለም  ፈተናዎች በተለያየ ምክንያት በተለያየ መንገድ በዓለም ላይ ተዘርተው  በየክፍልፋይ ስዓቱና በየዕለቱ የሰውን ልጅ ሲፈትኑ የሚኖሩ ናቸው። 
ከላይ እንደተጠቀሰው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለሰላስ ብር አሳልፎ ለመሸጥ የአስቆሮቱ ይሁዳ ምክንያት ይሁን እንጅ ፣ የወንጀል ክስ የተመሠረተበት የኦሪትን ሕግ በመተላለፍ በሰንበት ሙታን በማስነሳቱ፣ እውራንን በማብራቱ፣ ለምጻምን በማንጻቱ  ሸባዎችን በመፈወሱ በጠቅላላው በገቢረ ተአምራቱ የአመነውና የታመነው ሕዝብ ሁለ ጌታን በመከተሊ ምክንያት በወቅቱ የነበሩት የኢየሩሳሌም የነገደ አይሁድ አላዊያን ነገሥታት ከሀዲያን ሊቃነ ካህናት፤ ከሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ከበሬታና የንግሥና ሥልጣን
እንዳይጓደልባቸው፣ የሚገባላቸውን የአዝዕርትና የእንስሳት ግብር ምግብ እንዳይቋረጥባቸው፣ እንዲሁም የታክስ ቀረጥ ገንዘብ እንዳይቀርባቸው፤ በሦስቱ የዓለም ፈተናዎች እሳቤ እኛ ቄሳራዊያን ነገሥታቱ እያለን እሱ እንዴት የአይሁድ ንጉሥ ነኝ ይላል?
«...አንተ ነህ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ የምትል..»  በሚል ቅናትና በማሽሟጠጥ ክፉ መንፈስ ምድራዊ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን የመከራ ቀንበር ሁሊ በማሸከም ቀድሞ ወንጀለኞች ይቀጡበት በነበረው መስቀል ቸንክረው ቀማኞችን፣ በረት ከፋቾችና ቋንጃ ቆራጮችን በግራና በቀኙ ደምረው ሰቅለው ገደሊት። ዮሐንስ 19፤1-27 በኋላ ያ የወንጀል ዕዳ የተከፈለበት የመከራ መስቀል የክርስቶስ ዘላለማዊ የሕይወት ደም ስለፈሰሰበት አማናዊ ሥጋው ስለተቆረሰበት ለአመነውና ለተማጸነው ለእኛ ኃይል፣ መደኅኒትና ቤዛ ሆነን በማለት እናምናለን። አሜን፤
እዚህ ላይ ከርዕሱ ጋር በተያያዘ የምንረዳው ዐቢይ ጉዳይ ምግብ፣ ሥልጣንና ገንዘብ አንዱበአንዱ ላይ ጥገኛ ወይም የሚጓተቱና የሚሳሳሙ በመሆናቸው፤ በዚያን ዘመን በከፍተኛ የሕዝብ አስተዳደር በንግሥና ወንበር ተቀምጠው የነበሩ የአይሁድ ነገሥታትና ሊቃነ ካህናት ከተቀመጡበት የማስተዳደር ከፍተኛ ሕዝባዊ ኃላፊነት አደራ ይልቅ፤ በሦስቱ የዓለም ፈተና አሽከላ ውስጥ ተጠምደው ወንጀል የላለበትን  ሀጢያትን  የማይሠራውን  ፍጹም  የሰው ልጅ  ፍጹም አምላክ ወልደ ማርያምን፤ የሀሰት ክስ አቀነባብረው  መልካም  በሠራ ክፉ ፣ ምህረት  ባደረገ  ጭካኔ፣  ፈውስ በሰጠ መራራ ሀሞት እየጋቱ  አንገላቱት ስቀለው! ስቀለው!  በሚል ጫጫታና  አድማ  በጎልጎታ አደባባይ  እራስ ቅል በሚባለው ቦታ በመስቀል ላይ ሰቅለው ገደሊት።ዮሐንስ 19፤17 ሆኖም አምላክ በአምላክነቱ የምሕረት አምላክ ነውና  አባት ሆይ የሚያደርጉትን  አያውቁምና  ይቅር  በላቸው ከማለት ውጪ እላፊ ትራፊ አልተናገም ይልቁንም ተፈጸመ! በማለት በጽሞና በአርምሞ ሕይወቱን አሳልፎ ስእለኛ ሰጠ እንጂ።
ከላይ የምናየው የተጠቀሱትን  ሦስቱ የዓለም  ፈተናዎች ዓለም ሲፈጠር ዘመን ሲቆጠር ጀምሮ ሰው ሕግን በመተላለፉ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ተጥለው ሰውን በማጥመድ ከባድ መሰናክሎችን የሚፈጥሩ ዕዳዎች ናቸው። ሁሊም የሰው ልጅ የጥፋት መሰናክሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በእነዚህ በሦስት የዓለም ፍተናዎች ተዋስያንነት የተመረዘና የተበከለ በሽታ ያለበት መሆኑን እንረዳለን።
ዛሬ ቤተ ክርስቲያን የገጠማት ፈተና፤ ሊቃነ ካህናቱ ቀሚስ እያስረዘሙ መስቀል እየቀሰሩ የከበሬታ ወንበርን እየናፈቁ ነገር እያሳመሩ ውስጣዊ ሳይሆን አፋዊ አማኝ መስለው በመታየት ፤ በማኅበራት እየተደራጁ አንዱን የአባት የእናት ልጅ አድርገው እያሞገሱ ከጻድቃን ማኅበር የሚጨምሩ ሌላውን ደግሞ የእንጀራ ልጅ አድርገው ያለ የሌለውን የበደል ስያሜ እየሰጡ በፈረጠመ ክንዳቸው የሚደቁሱ በመርዛማ ምላሳቸው የሚነድፉ፣ በቤተ ክርስቲያን ስም በገለልተኝነት እየተደራጁ መንጋውን እየከፋፈሊ የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ዶሮ ብልት የሚገነጣጥሊ፣  ቤተ ክርስቲያን ታልባ የማትነጥፍ ጥገት፣ ምርታማ የሆነች ድንግል መሬት መሆንዋን ጥናት ያደረጉ ጮሌዎች ሁለ ጻድቅ መስለው በመቅረብ ሀብትና ንብረቷን በግል ባለቤትነት ለመቀማት በግልም ሆነ በቡድን እየተደራጁ የሚሞግቱ፣ በሃይማኖት ሽፋን ተጠግተው ነገር ግን በገንዘብ፣ በምግብና  በሥልጣን  በሦስቱ የዓለም ፈተናዎች  ብልጫ ያለው ኃይልና ጉልበት ለማግኘት የሚያደርጉት ሽሚያ ሁሊ የመጨረሻ ኢላማው በሕገወጥ መንገድ በቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ የበላይ ሆኖ ለመኖር የተፈጠረ ግብግብ እንጅ መንፈሳዊነት የተላበሰ አይደለም።
የፈተናዎቹ ምርኮኛ የሆኑት በሚፈጥሩት ትግል መካከል የቤተ ክርስቲያን አካል አንጡራ ሀብትና ንብረት የሆነው አማኙ ሕዝብ ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጧል። እራሳቸውን በከንቱ ከጻድቃን ተርታ ያሰልፉ ሁለ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መለያየት ተወግዶ አንድነት ሰላምና ፍቅር እንዳይፈጠር ነቀርሳ ሆነዋል። እነዚህ ሁለ በሦስቱ የዓለም ፈተናዎች እንደ ብራና የፍየል ሌጦ የተወጠሩ በመሆናቸው ነው። ሞት ሲዘገይ የቀረ እንደሚመስለው ሞኝ ካልሆነ በስተቀር የበደል ጽዋው ሲሞላ ሁለም እንደሥራው የሚከፈልበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም
በመንግሥት አስተዳደርም ቢሆን በዓለም ላይ የሰው ልጆች መብታቸው ተረግጦ ሕይወታቸው በየቀኑ እንደ ቅጠል የሚረግፈው የጠባብ አስተሳሰብ ጎሳዊ የፓለቲካ ሴራ ነግሦ በትውልደ መካከል የማያቋርጥ የሰነልቦና እና አካላዊ ጦርነት የከፈቱ በሥልጣን ላይ ያሊ ሰዎች ሥልጣናቸው የሚቆይበትን፣ ገንዘብ እየጎረፈ ኪሳቸው ያለድካም የሚሞላበትን፣ እየተመገቡ የድሎት የፈንጠዝያ ኑሮ የሚኖሩበትን የምግብ ዓይነት በማስጠበቅ በተቃራኒው ላላው በተወለደበት ሀገሩ አስከፊ በሆነ በሽታና ረሀብ እየተቆራመደ እነሱ
በብቸኝነት በተሟላ ሁኔታ በበላይነት ተቆጣጥረው ለመቆየት የሚደረግ እራስ ወዳድነት የቁማር ጨዋታ ሁለ የሦስቱ ዓለም ፈተናዎች ምርኮኛ  አረመኔያዊነት የመሆን ገጽታ ነው።
በተጨማሪም በሕዝብ ስም ትግል እናደርጋለን ሕዝብን ነጻ እናወጣለን በማለት እራሳቸውን የሚያደራጁትም ቢሆን ከሥልጣን በፊት ለሕዝብ የሚገቡትን ቃል ኪዳን፤ ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ይዘነጉትና ቃል የገቡለትን ሕዝብ እንደ እንስሳ ይቆጥሩታል፣
የፈለጉትን ያክል ሊጭኑት፣ በፈለጉት ገበያ ወስደው በተገኘው ዋጋ ሊሸጡት፣ ባለተመቻቸው ጊዜ ሊያንገላቱትና ሲያፈናቅሉት አፍነው ይዘው በመዶሻ ይቀጠቅጡታል፤ በመጨረሻም ጭካኔው ሲመረው ኅማሙ ሲበዛ ቁስለን መሸከም ሲያቅተው ሕዝቡ በሚያሰማው ብርቱ የድረሱልኝ ጩኸት ምክንያት ይገድለታል። 
ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ከላይ በተዋረድ እንዳየነው ከመጠን ባለፈ  በሦስቱ የዓለም ፈተናዎች ተተብትብው በመያዛቸውና አዙሮ የሚመለከት አንገት የሚያስተውል ኅሊና  አጥተው ግዙፍ ስግብግብነት እስከ ዕለተ ፈጻሜ ቀናቸው ድረስ በፈተናዎቹ መጋረጃ የተሸፈኑ በመሆኑ ነው። በእርግጥም በሦስቱ ፈተናዎች አጥብቆ የታሠረ ሁለ አውዳደቁና አሟሟቱ እጅግ የከፋና የከበደ ይሆናል። ከላይ እንዳየነው ጊዜው ሲደርስ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በይሁዳና ሳጥናኤል ያላመለጡት የበደል ፍርድ መቀበል የወዴታ ግዴታ ይሆንባቸዋል ።
ዛሬ በአክራሪ ሙስሊሞች በእስልምና ፈጣሪ ስም ንጹሐን ሰዎች እንጀራ ፍለጋ ከሀገር ሀገር ሲንከራተቱ፣ በሰማይ፣በየብስና በባህር  መጓጓዛዎች ውስጥ በጉዞ ላይ እንዳሉ፣ የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን ለመግፋት በሥራ ገበታ በተጠመደበት ወቅት፣ አምልኮታቸውን ለመፈጸም በተሰበሰቡበት የሰላምና የፍቅር አደባባይ ላይ የሚደርሰው እንደ ፍየል አንገትን ቆልሞሞ በስለት ማረድ፣ ቦንብ በማፈንዳት ክቡር የሰው ልጅ ደም እንደ ጅረት ወንዝ እንዲፈስ የማድረግ አጥፍቶ ማጥፋት አስከፊ ተግባራትና ሰዎች ተወልደው ባደጉበት ሀገር ቀያቸውን፣ ባህላቸውን ጥለው ስደትን ብቸኛ አማራጭ አድርገው በጀምላ እንዲፈልሱ ከአቅም በላይ
የሚደርስባቸው ማስገደድ፣ ማስፈራራትና ማሸበር ሁሉ በሃይማኖት መሰል ሽፋን እኛ ያልነው ካልሆነ፣ እኛ የአመነውን ካለአመናችሁ፣ አስገድደን ካልገዛናችሁ በሚል ከሦስቱ የዓለም ከፈተናዎች ጋር ጥልቀት ያለው ቁርኝት በፈጠረው ምርኮኝነት ጥቁር ጭብል ባጠለቁ ጽንፈኞችና ደጋፊዎቻቸው ላይ የተፈጠረው አስከፊ የሆነ የአዕምሮ በሽታ የተበከለ አስተሳሰብ ነው።
ከላይ እስከታች አንድ በአንድ ያየናቸውን ሦስቱ የዓለም  ፈተናዎች አመጣጥ እንደ ክርስቲያናዊ የሃይማኖት ትንታኔን በማጠቃለል፤ ፈተናዎቹ  ሰው  በራሱ  ሕግ ተላላፊነት  በሕይወቱ ጉዞ ውስጥ ተቆራኝተው እንዲኖሩ  በእራሱ  ላይ ያመጣቸው  የቅጣት ፍርዶች ናቸው።  ይሁን እንጅ  ሰው በራሱ  አቅምና  ቸልታ  በግንባሩ ወዝ የሚያገኘው የተመጠነ ማለትም አጥቶ ፈጣሪውን እንዳያማርር ፤ ይበልጥ አግኝቶ ፈጣሪውን  እንዳይበድል  ከሰሳ ወቀሳ የሌለበት ንጹህ ሰላማዊ  ሕይወቱን  ሊገፋ የሚያስችል ምግብና ገንዘብ  እራሱን  ለመጠበቅ፣ ለመከላከልና  አስከብሮ  ለመኖር የተመጠነ ሥልጣን ለሰው ልጅ መሠረታዊ አስፈላጊ ነገሮች  መሆናቸውን   መዘንጋት  የለበትም ።  በእርግጥም  በምንም  ዓይነት  ሊዘነጉ  አይችለም ።  ነገር ግን በሥልጣን በገንዘብ በኃይል ተመክቶ፣ በሃይማኖት፣ ታርካዊ መሠረትነት በላለው መጨረሻቸው በማያምር የፓለቲካ ስሪቶች፣ በሰለጠነው ዓለም አይጥና ድመት፤ ውሻና ድመት ተላምደው ተቃቅፈው በአሳዳሪያቸው ቤት በሚኖሩበት ዘመን በልዩ ልዩ ጠባብ ጎሳና የዘር መድልዎች ተደራጅቶ የላላውን ሰባዊ የመኖር መብት፣ መሠረታዊ ፍላጎት የማሟላት ነጻነት፣ በማኅበራዊ ኑሮ ተባብሮና ተዛዝኖ
በአንድነት የመኖርን እሴት አፈርሶና ነፍጎ፤ በማሸበር በማስፈራራት እራስን ብቻ በሦስቱ የዓለም  ፍተናዎች ከአቅም በላይ ማደለብ፤ በዚህም የተነሳ በሚፈጠረው ትዕቢትና ጥጋብ የሌሎችን ብሶት አለመረዳት፣ ጩኽታቸውን አለመስማት፣ ማንገላታት፣ መከፋፈል፣ ያለፍርድ ማሰር፣ በጭካኔ መግደል እና ሌሎችም…… ወደፈተና እንዳትገቡ ተጠንቀቁ ! የሚለውን ትእዛዝ መጋፋት ወደፈተና አታግባን ብሎ ከመጸልይ መዘናጋት የሚመጣ ከሚዛን ያለፈ ግፍና ጭካኔ በሦስቱ የዓለም ፈተናዎች መርዝ ተነድፎ ዘለዓለም ለማይኖሩበትን የግፍ ሕንፃ መገንባት፣ በልተው የማይጨርሱትን ሁሉ ከመጠን በላይ በመሰብሰብና በማግበስበስ ምክንያት የሚመጣ በደል ይግባኝ የማይገኝለትን ፍርድ እንዳያስከትል አስቀደሞ ማሰቡ ተገቢ ነው።
 እግዚአብሔር ከፈተና ይጠብቀን፣ ሀገራችን በአንድነት፣ ሕዝባችን በስምምነት፣ ሃይማኖታችን በተዋሕዶ ያጽናልን። አሜን፤
                 መጋቤ ጥበብ  መንገሻ መልኬ                 
  2008 ዓ.ም፤ ዘመነ ዮሐንስ ወንጌላዊ፣ ከታላቋ ብርታንያ፤ ለንደን


7 comments:

 1. Enante rasachihu arategna ye alem fetenawoch nachihu. Besefer wore yetetemedachu, akitacha yetefabachihu.

  ReplyDelete
 2. እውነቱ ይነገር ይሰማMay 19, 2016 at 5:37 PM

  መጋቢ ጥበብ መንገሻ!

  መልካም መልእክት ነው፤ ይበል!በርታ!ማለት እወዳለሁ፤ ነገር ግን ኢዲቲንግ ይጎለዋል /በተለይ ሉ የምትባለዋን ፊደል ኮምፒተርህ ጨርሶ አያውቃትም/!

  ጠቅላላ ሃሳብህ በሚያጠነጥንበት ያገር ጉዳይ ላይ ግን ሁላችንም የማይወለድ ምጥ ላይ ነን። ስለዚህ ምጡ በተገቢ መልኩ እንዲወለድ የሚያደርግ ኃይል ለማግኘት ሁላችንም በግልጽና በቅንነት እንደ አምላካችን ቃል መነጋገር ይኖርብናል።

  ስለዚህ በመተዋወቁ፣ በመመካከሩና ለመልካም የጋራ ሥራ ግብዝነት በሌለው ንጹህ ፍቅር በጋራ ለመነሳት ፈቃደኛ ከሆንክ በ eunethiwot@gmail.com ኢሜል ብንገናኝ ደስታውን አልችለውም! ይህን እንደቃሉ የመመካከርን ሃሳብ የምትቀበሉ ሌሎች ወገኖች ካላችሁም በዚሁ ኢሜል ሃሳባችሁን መላክ ትችላላችሁ። ልባችሁ ለፍቅር ሥራ ከልብ ካልተነሳሳ ግን ዝም እንድትሉ በእግዚአብሔር ፍቅር እለምናችኋለሁ???

  ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክ!

  እውነቱ ይነገር ነኝ

  ReplyDelete
 3. TEHADISO....Arategnaw Ye Alem Fetena...

  ReplyDelete
 4. melkam melkt new yebarekeh ybarek

  ReplyDelete
 5. HARATEKA nachihu.

  ReplyDelete