Friday, May 20, 2016

የደቡብ ውሎ ሀገረ ስብከት በማኅበረ ቅዱሳን መዳፍ ውስጥ ወደቀማኅበረ ቅዱሳን በሚል ስያሜ የሚታወቀው ድርጅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በልዩ ልዩ ስልትና በከፍተኛ የገንዘብ አቅም እየታገለ ለዓመታት ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
    ቤተ ክርስቲያኒቱ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ድረስ ያላትን አደረጃጀት በሙሉ ለመቆጣጠር በሚያመች ሁኔታ ተመሳሳይ አደረጃጀትና መዋቅር በመዘርጋት ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትሠራውን ሁሉ ተክቶና በሁሉም ጉዳይ ጣልቃ እየገባ የማይገባውን ሁሉ ያለ ከልካይ በማከናወን የሚንቀሳቀሰው ማኅበር ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በዚህ ወቅት ስውር አሠራሩና ዓላማው የአደባባይ ምስጢር እየሆነ ሲመጣ ሥርዐት እንዲይዝና ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊጠቅም በሚቻልና ተጠያቂነት ባለበት ሥርዐትንና ሕግን በተከተለ መንገድ እንዲሠራ የማስተካከያ ርምጃ እየተወሰደ መሆኑም ይታወቃል፡፡
    ማቅን ሥርዓት የማስያዝ ርምጃ እንዲወስድብት የጠቅላይ ቤተ ክህነት 18ቱ መምሪያዎች በአንድ ድምጽ የተስማሙ ሲሆን የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችም ጭምር ማቅን ሥርዐት የማስያዝ እርምጃ የሚመለከተው ክፍል በአፋጣኝ እንዲወስድ በተደራጀ መንገድ አቋም ይዘው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
    ከጠቅላይ ቤተ ክህነት 18ቱ መምሪያዎች የተጀመረው ማኅበሩን በሕግና በሥርዐት እንዲሄድ የሚጠይቅ እንቅስቃሴ በቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት ማግኘቱንና የሚደግፉት የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት እየጨመሩ መምጣታቸውን ተመልክቶ የደነገጠው ማቅ እንቅስቃሴውን ለማስቀልበስና ለቤተ ክርስቲያን ሌላ ስጋት የሆነ አካል አለ በማለት ‹‹የግንዛቤ ማስጨበጫ›› በሚል ከአዲስ አበባ ውጪ በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ፀረ-ተሐድሶ በሚል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መረጋጋት እንዳይኖር፣ ምእመናን አገልጋይ ካህናቱንና መምህራኑን እንዲጠራጠሩና እንዲታወኩ በከፍተኛ በጀት ባለፉት ጥቂት ወራት በሙሉ ኃይሉ እየሠራ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
    ለቤተ ክርስቲያን የሚቆረቆሩ አባቶች የማቅን ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር ውድቅ ያደረጉ ሊሆን እንደነአቡነ ገብርኤል ያሉ አባቶች ደግሞ ፈቅደው የማኅበሩን ዲስኩር ካዩ በኋላ እውነትን ካለማወቅ የመነጨ የቤተ ክርስቲያን መሠረት ጉልላት የሆነው ኢየሱስን እንዳይሰብክ የሚከላከል በስውር የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ የሚሠራበት እንደሆነና “መጽሐፍ አንብቡ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የሚሠራ ካለ እንጂ ኢየሱስን የሚስብክ ተሐድሶና አፍራሽ ነው ማለት አላዋቂነት ነው” ብለው በተግሳጽ የማኅበሩን ዓላማ ከንቱና ለቤተ ክርስቲያን የማይጠቅም እንደሆነ አሳስበዋል፡፡
በአንዳንድ አህጉረ ስብከቶች በተለይም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት እየታየ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ከዚህ የተለየ ሲሆን ማቅ ሙሉ ለሙሉ ሀገረ ስብከቱን ተቆጣጥሮ የሚፈልገውን ለማድረግ እየሠራ ይገኛል፡፡

    የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ አትናቴዎስ ፓትርያርክ የመሆን ፍላጎታቸው ባለመሳካቱ የቅዱስ ፓትርያርኩን መመሪያ በመጣስና በመቃረን ለማቅ በራቸውን ከፍተው ሙሉ ለሙሉ የፈለገውን እንዲያደርግ አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ እንደሚታወቀው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም በጵጵስና የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ሆነው በሚያገለግሉበት ጊዜ ከሓላፊነታቸው እንዲነሱና ከኢየሩሳሌም ወደ አሜሪካ እንዲሰደዱ በተደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ዋና ተዋናይ የነበሩት የአሁኑ አቡነ አትናቴዎስ የቀድሞው አባ ዮሐንስ እንደሆኑ የማይዘነጋ ነው፡፡
በአቡነ አትናቴዎስና በማቅ መካከል ግንኙነቱ የተሳለጠ እንዲሆን ትልቁን ሚና እየተጫወተ ያለው በብልሹ ሥነ ምግባሩ የብዙ ሰንበት ተማሪ ሴቶችን ሕይወት ያበላሸውና በደሴ ብዙ ወላጆች የሚያለቅሱበት እንዲሁም በጥቅማጥቅም ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማኅበሩ የሸጠው የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊ ብርሃነ ሕይወት የተባለው ሰው ነው፡፡
    ይህ ሰው በብዙ አቅጣጫ እጅግ ጸያፍ በሆነ የሕይወት ዝቅጠት ውስጥ ያለ ሲሆን ስለዚህ ግለሰብ የተበላሸ ሕይወት ከተበደሉ ወጣት ሴቶችና ከቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ያጠፋቸውንና ቤተ ክርስቲያንን ያስደበበትን ታሪክ ሰፊ መረጃ ስላደረስን በሌላ ጊዜ በዝርዝር የምንመለስበት ሲሆን አሁን ከተነሣንበት ርዕሰ ጉዳይ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ነገሮች እናነሣለን፡፡
    ይህ ሰው የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ሲሆን ማቅ የተገለጠውን ጉዱን እንዳያነሣበትና ሕዝብን እንዳያሳምጽበት ያለ ምንም ድርድር በተሰጠው ሓላፊነት ተጠቅሞ ሀገረ ስብከቱ የማቅ መፈንጫ እንዲሆን ቤተ ክርስቲያኒቱንና አገልጋዮቿን የሚያውክ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡
    ለዚህ እንዲያመቸው ከፀሐፊነቱ በተጨማሪ ከሕግ ውጪ በደሴ ዩኒቨርስቲ አካባቢ የተተከለው ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በመሆን በማቅና በሀገረ ስብከቱ መካከል ቁልፍ ሚና በመጫወት ማቅ በአሁኑ ጊዜ እየሠራቸው ያሉትን አፍራሽ ሥራዎቹን ያለ ከልካይ እንዲሠራ የአንበሳውን ድርሻ በመያዙ ከማኅበሩ ልዩ ልዩ ጥቅሞችንም በማግኘት ላይ ይገኛል፡፡
    ማቅ በአገር ውስጥና በውጪ ዓለም በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እንዳይነግድ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙትን የቦሩ የትርጓሜ ት/ቤትን የተድባበ ማርያም ቤተ ክርስቲያንንና የጋስጫ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን በገንዘብ እንዲረዳ በሚል ሰበብ የንግድ በር ከፍተውለታል፡፡ ማቅ በእነዚህ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትና ት/ቤት ፕሮጀክት ነድፎ ከፍተኛ ገንዘብ እየሰበሰበ ሲሆን ከሚያገኘው ድጋፍ ለቤተ ክርስቲያን ፈሰስ የሚያደርገው ከአንድ በመቶኛ የማይበልጥ መሆኑን የውስጥ አዋቂዎች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
    በተለይ በጋስጫ ፕሮጀክት የሚገኘው ገንዘብ የትየሌሌ መሆኑን የገለጹት የማቅ ውስጥ አዋቂ ሰዎች ሀገረ ስብከቱም ሆነ ጋስጫ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይህን ያህል ለማቅ ራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው እንደሚያስቆጫቸው ተናግረዋል፡፡
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ማቅ ሥርዐት እንዲይዝ በጠቅላይ ቤተ ክህነትና በፓትርያርኩ መውሰድ ለጀመረው ርምጃ ሁሉም አህጉረ ስብከቶች ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ፓትርያርኩ ያስተላለፏቸውን መመሪያዎች የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ወደ ጎን በመጣል ለማቅ ሙሉ ለሙሉ በሩን ከፍቶ በመስጠት በሀገረ ስብከቱ እንደፈለጉ እንዲሠሩና በፓትርያርኩና በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ላይ ሕዝብን እንዲያሳምጽ እያገዙት ይገኛሉ፡፡
    በሀገረ ሰብከቱ ፀረ ተሐድሶ ብሎ ያቋቋመው ሙሉ ለሙሉ የማቅ አባላትና ምርኮኞቹን ያካተተው ኮሚቴ በየደብሩ የፈለገውን እንዲሠራ በተሰጠው ስልጣን ካህናቱና የሚመለከታቸውን አገልጋዮች አስገዳጅ በሆነ ደብዳቤ በመሰብሰብ የማቅን ዲስኩር እንዲቀበሉ በማስገደድ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በደሴ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሚያዝያ 12/2008 ዓ.ም በተጠራው ሰብሰባ ብዙ ክርክርና ጥያቄ ተነሥቶ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሚያዝያ 28/2008 ዓ/ም በደሴ መድኀኔዓለም በወረዳው ለሚገኙ አገልጋዮች ሁሉ አስገዳጅ ጥሪና ቁጥጥር የተደረገበት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በሁለቱም ስብሰባዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናትና መምህራንን በፕሮጀክተር ፎቷቸውን ጭምር በማሳየት ማኅበሩ ሲወነጅላቸው ታይቷል፡፡
    በተለይ ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል›› ብሎ መስበክ፣ ማስተማርና ማመን ፈጽሞ ኦርቶዶክሳዊ እንዳልሆነ ለማሳመን ያደረገው ጥረት ብዙ አገልጋዮችን ግራ ያጋባ ሆኗል፡፡
    በሀገረ ስብከቱ ውስጥ አንዳንድ ለማቅ ያልተንበረከኩትን አገልጋዮች በዚህ አጋጣሚ ለመቀበል ቀጣይ ሥራዎችን ለመሥራት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፀረ ተሐድሶ የተባለውና በብርሃነ ሕይወት የሚመራው ሙሉ ለሙሉ የማቅ አባላት ያሉበት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ትልቅ ስልጣን የተሰጠው ኮሚቴ ለጥፋት እየተፋጠነ ሲሆን ጠቅላይ ቤተ ክህነቱና ቅዱስ ፓትርያርኩም በሀገረ ስብከቱ የሚሠራውን ፀረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴና ማቅን በማይደግፉ አገልጋዮች ላይ በግፍ ሊወሰድ እየተሠራ ያለውን ተንኮል ለማስቆም አስፈላጊው ርምጃ መውሰድ አለባቸው፡፡
    ማቅ በመጀመሪያ ራሱ ሥርዐት በመያዝና በሕግ በመመራት ለቤተ ክርስቲያን ያለውን አክብሮት ሳይገልጽ የቤተ ክርስቲያኒቱ አለኝታ መስሎ በመታየት ሥርዓት እንዲይዝ የተጀመረውን ሥራ ለማክሸፍ የሚያደርገውን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ አንዳንድ አህጉረ ስብከቶች ማቅን በመደገፍ እያደረጉ ያሉትን ቤተ ክርስቲያንንና አገልጋዮቿን የማወክ ሥራ ከመተባበር እንዲቆጠቡ የሚመለከተው አካል ጥብቅ መመሪያ መስጠት እንዳለበት ሳንጠቁም አናልፍም፡፡
    በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ደቡብ ውሎ ሀገረ ስብከት የሚመራው በደቡብ ወሎ ዞን የማቅ ንዑስ ማዕከል ሥር ሲሆን፣ ይህም የሆነው የአቡነ አትናቴዎስ እርጅናና የጤና እክል በተጨማሪ የፓትርያርኩን መመሪያ ለመቀበል ያለመፈለጋቸው፣ የብርሃነ ሕይወት እጅግ አፀያፊ የሆነ የሥነ ምግባር ብልሽትና ማኅበሩ እየተጠቀመባቸው ላሉ ሰዎች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በጥቅም የታወሩና ቤተ ክርስቲያኒቱን የሸጡ ጥቅመኞች ከማቅ ጎን በመቆማቸው ነው፡፡
    ለቤተ ክርስቲያን፣ የምትቆረቆሩ በሀገረ ስብከቱ ሥር የምትገኙ ካህናትና ሰባክያን ለሕሊናችሁ ለሃይማኖታችሁና ለእግዚአብሔር ብሎም ለእናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ብላችሁ እስከ አሁን እንደፀናችሁ ከዚህም በኋላ የሚደርስባችሁን መከራና ፈተና በመቋቋም ትግላችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ሞትን ድል ባደረገና የትንሣኤና የእውነት ጌታ በሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ ልናበረታታችሁ እንወዳለን፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናትናም ዛሬም እስከ ለዘላለም ድረስ ያው ነው!

18 comments:

 1. Yelam beret.......cos i could not finish this trash article....Garbage as usual. But you are not still writing as per your payment by the Lutherans......

  ReplyDelete
 2. ስለ መረጃችሁ ጌታ ይባርካችሁ! ጉዳዩ በደሴ ብቻ አልቆመም ሰሞኑን ደግሞ በኮምቦልቻ መዳኒአለም ቤተክርስቲያን በሙንታርቦ ማስትታወቂያዉን አስነግሮ ስብሰባዉን ጀምሯል:: ፓዉሎስን ከአሳዳጅነት ወደ ተሳዳጅነት የመለሰ ጌታ በኢየሱስ ስም እነሱንም ይመልሳቸዉ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. The protestantism (lutheran) mission is going down as the people get aware. Ethiopian orthodox church
   is free of illuminate. freeeeeeeeeeeeeeee

   Delete
 3. ከምታወሩት የሐሰት ፕሮፖጋንዳ የተነሣ አምላክ ይመስገን ማኅበሩ እየበረታ መጣ፤አወቅነው ተረዳነው። ራሱን ሳይሠብክ ለዓመታት የቤተክርስቲያን አገልግሎት ብቻ እየሠራ ቆዬ፤ ይህ አገልግሎት ያላስደሠተው ጠላት በማኅበሩ ላይ አምርሮና አዘውትሮ የተለመደ የሃሰትና የዓመጽ ጩኸቱን ማሠማት ጀመረ። እኛም ማኅበረ ቅዱሣን መኖሩን የማናውቅ የሥም ክርስቲያኖች የማኅበሩን ማንነት ከሥራውና በቤ/ያን ካለውና ከተሠጠው ፈቃድ አንጻር ፈተሺነው፣መረመርነው፣አገላበጥነው። የሚጮኸውን ክፍልም ለማወቅና ለመረዳት ብዙ ደከምን ወጣን ወረድን። የሚጮኸው ክፍል በቤ/ያን ቦታ የሌለው፣የቤ/ያኗን አስተምህሮ ለመቀየር ለፕሮቴስታንት በባንዳነት የሚሠራ፣ ራሱን ደብቆ በቤ/ያን ውስጥ የሚሽሎከለክ እኩይ ፍላጻ መሆኑን ተረዳን። ማኅበሩንና ቤተክርስቲያንን የማወቅ መልካም እድል በእናንተ በኩል ስለተፈጠረልን ለአምላካችን ምስጋናን ለእናንተም ለንስሃ እንድትበቁ በመፀለይ ይኸውና በገፍ ወደ ማኅበሩ መጉረፍ ጀምረናል። ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ማኅበሩ የራሱ የሆነ አጀንዳ የለውም፤ አጀንዳዎቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ሕዝቡ ገብተዋል። ትርፍና ኪሳራ ማለት ይኸው ነው እንግዲህ። ሌላው አንድ ትርፍ የሚያስገኝ ነገር ከጹሁፋችሁ ትዝ አለኝ። "ኢየሱስ ያድናል ብሎ መስበክ ማስተማር ኦርቶዶክሳዊ አይደለም በማለት ማኅበሩ አስተማረ"ብላችኋል። አንባቢያን ሆይ በትምህርተ መለኮት ዙርያ ማኅበሩ የሚጽፋቸውን ጹሁፎች፣መጽሔቶችን ፣መጽሐፍቶችን...በማንበብ እውነታውን ትረዱ ዘንድ በእግዜአብሔር ስም አደራ እላለሁ። ሐሰትም መጠን ሊኖረው ይገባል። በሐሰት ከሠውም ሆነ ከእግዜአብሔር ትርፋችሁ ምን ይሆን?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሔር ይባርክህ ወዳጄ! እነሱ ከጻፉት ኮተት ያንተ ጥቂቷ እውነት ያለባት ጽሁፍ ሚዛን ትደፋለች!!!

   Delete
 4. As per the Bible this world is the devils kingdom, his disciples slither, cloak, deceive and destroy by any means possible until King Jesus appears. All true Christians should know this and fervently pray for the church and the lost. The evil ones sniff every blog, website, social media and they are the first to show crude intelligence of insults and spew their caustic and vile language. We should not expect more than what they portray from the likes of the Hadgi Kiros.

  ReplyDelete
 5. kkkkkkkkkk ere atasikegn yewah nh ebakih desse balihon tishewudegn neber lemin gizehin tabakinalh ortodox tewahido mechem atitefa mahibere kidusanim talaq sira eyeseralin nw yewah nh yiliq ye ageligilot menifesu yigibah sayih yewh nh wendim be simet sayihon be ewunet ena be menfes begeta eyessus kal tsina eyesus yadinal yemil alitefam yekelekelem yelem be hiwot yeminor nw yetefaw

  ReplyDelete
 6. ከመንደርተኛ የቡና ወሬ ምንም አይተናነስም ይህ መረጃ ሊሆን አይችልም እግዚአብሔር ልቦና ይስጥህ ።

  ReplyDelete
 7. you protestant messenger,let God allow Mk TO CONTROL AND THE WHOLE ORGANIZATION OF OUR CHURCH FOR GOOD,NOT FOR BAD AS YOU WROTE THE THRUSH ARTICLE.

  ReplyDelete
 8. ፊስዳቢዎች እንዴት ከረማችሁ

  ReplyDelete
 9. ማኀበረ ቅዱሳን ገና ያብባል፡፡ ..... እናንተም ታወራላችሁ እኛም እናያለን ይኸው ነው፡፡ የማኀበሩን እድሜ ያርዝምልን፡፡

  ReplyDelete
 10. ጸሃፊውስ አንዴ አብዷል!!! ጨርቅ መጣል ብቻ ኮ ነው የቀረው እውነት ሚባል ኮ ጽፈው አያውቁም!! እንደው ይህን እውነት መረጃ ብላቸሁ የመትደግፉት ታሳዝኑኛላቸሁ!!!
  እገዚአብሄር ልቦና ይስጣቸሁ!!!!

  ReplyDelete
 11. ye leboche gize eyabeka new ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በሓላፊነታቸው እንደማይቀጥሉ በፓትርያርኩ ተነገራቸው፤ የአያሌ አባቶች እንባና እርግማን አለባቸው

  ReplyDelete
 12. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 13. Great job MK. Aba selam is becoming mad nowadays. please continue t

  ReplyDelete
 14. We know MK. You never told as about MK, because you are TEHADSO (The Activist of Reformation). I am from Dessie and I know about Bishop Atnatus and Birhan hiowt,they are the sons of the true Orthodox church.

  ReplyDelete