Sunday, May 22, 2016

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሕግ መምሪያ ሃላፊ በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን የቤት ሽያጭ ላይ የተወሰነውን ውሳኔ ለመቀልበስ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ የተሰየመው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ ከዚህ ቀደም በማስረጃ ተደግፎ በቀረበው የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ንብረት የሆነ ቤት ሕገወጥ ሽያጭ ላይ ተወስኖ የነበረው ውሳኔ እንዲቀለበስ በመደረጉ የአስተዳደር ጉባኤው አባላት ለሁለት መከፈላቸው ተሰማ፡፡ አዲሱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ የተወሰኑት አባላት ለጉዳዩ አዳዲስ ቢሆኑም ከነባሮቹ ጥቂቶቹ ከዚህ ቀደም የተወሰነው ውሳኔ እንዲቀለበስ ለማድረግ ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡ በተለይም የተወሰነውን ውሳኔ ወደፊት እንዲሄድና ተገቢውን የውሳኔ አፈጻጸም እንዲኖረው ማድረግ የሚገባው የሕግ መምሪያ ኃላፊው መ/ር ባሕሩ ተፈራ እና ታጋይ የተሳሳተና፣ የተጣመመ ሐሳብ በማንሳታቸውና በበሉበት እንዲጮኹ ያደረገ ሙግት ማድረጋቸውን ምንጮች ይናገራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የተወሰነው ውሣኔ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይሄድ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ባሕሩ ተፈራ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ባሕሩ ተፈራ (በቅጽል ስሙ ወ/ወ/ሩ - ወጣቱ ወልደ ሩፋኤል ይሉታል አለባበሱንና ሕይወቱን ከግምት በማስገባት) ከመጀመሪያው አንስቶ ውሳኔውን ላለመቀበል የራሱን እርምጃ ሲወስድ እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም የአስተዳደር ጉባኤው የውሳኔ ቃለ ጉባኤ ላይ ሳይፈርም ቆይቷል፡፡ ያቀረበው ምክንያት ክፍለ ሀገር ሄጇለሁ የሚል እንደነበር ምንጮች ጠቅሰው፣ በሙሉ ድምፅ የተወሰነውና በህገወጥ መንገድ የተሸጠውን ቤት የተዋዋለውና የሸጠው የደብሩ ምክትል ህንፃ አሠሪ ኮሚቴ እስጢፋኖስ ሀይሉ ይከሰስ ሲባል፣ ፋይሉ ላይ መተኛትንና እንዳይንቀሳቀስ ማድረግን ነው የመረጠው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ  ባሕሩ ተፈራ በተደጋጋሚ ከእነ ዮናስ መኮንን፣ የትናየት ሀይሉ፣ እስጢፋኖስ እስኪሰለቸው ድረስ ጽዮን ሆቴል፣ ሶራንባ ሆቴል፣ ኤፍሬም ውስኪ ቤት በተደጋጋሚ ሲጋብዙትና ለጉቦ የሚሆን ብርም ሲሰጡት እንደቆዩ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ለዚህም እነእስጢፋኖስ ነሸጥ ሲያደርጋቸው “አይዞን ነገሩን ባሕሩ ይዞልናል” ሲሉ መደመጣቸውን እንደ ማስረጃ ያቀርባሉ፡፡

ሌላው ተማጋች አሁንም አላርፍም ያለው ቄስ ታጋይ ነው፡፡ ቄስ ታጋይ በቀድሞው ሥራ አስኪያጅ አስተዳደር ጉባኤ ላይ መከሰስ አለባቸው ብሎ የተስማማና በቃለ ጉባኤውም ላይ የፈረመ ቢሆንም እርሱም ያን ቃል አጥፎ ምንም ጥፋት አልተፈጸመም ሲል መሟገትን የመረጠው ከግብዣውና ከጉቦው ተቋዳሽ ስለሆነ እንጂ የመጀመሪያው ውሳኔ ውሸት ስለሆነ አይደለም፡፡

ባለፈው ሳምንት በተሰየመው የአስተዳደር ጉባኤ ላይ ባህሩ ተፈራ ቤቱ የተሸጠው በደብሩ ስምምነት ነው በማለት በሕግ ላይ አምጿል፡፡ ታዛቢዎች ግን ባህሩ እንዳለው ቤቱ የተሸጠው በደብሩ ስምምነት ከሆነ የስምምነቱን ሰነድ ለምን አያቀርብም? እንዲሁም በቃለ አዋዲው መሠረት እንዲህ ዓይነት የቤት ስጦታ የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ ባለበት ፈቅዶ ጨረታ ወጥቶ ነው መከናወን ያለበት ይላል፡፡ ነገር ግን በዚህ መንገድ መከናወኑን ግን ማስረዳት አልቻለም፡፡ በተጨማሪም ቤቱ ያለ ጨረታ በግለሰብ ውል ተዋዋይነትና ሻጭነት የተከናወነና የገዢውን ማንነት እንኳን ለመግለጽ ፈቃደኛ ያልሆኑብት ሁኔታ እያለና ይህ ሁሉ ሲሆን ድርጊቱ ወንጀል አይደለም ብሎ ባሕሩ መከራከሩ የባሕሩ ዐይኖች በጉቦ መታወራቸውን እንደሚያሳይ ሂደቱ ያስረዳል ይላሉ፡፡ አስቀድሞም በቀድሞው ሥራ አስኪያጅ የአስተዳደር ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ላይ አልፈርምም ያለው በጉቦ የታወሩ ዓይኖቹ ሐቅን መመለክት ስላልቻሉ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ ነበር ክሱ ወደ ሕግ እንዳይመራና ውሳኔ እንዳገኝ አፍኖ የያዘው፡፡

የእግዚአብሔር ቃል “ፍርድን አታጣምም ፊት አይተህም አታድላ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።” ዘዳ. 16፥19 እንዲሁም “በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!” ኢሳ. 5፡23 ይላል፡፡

ሁልጊዜ በሁለት ቢላዋ የሚበላው፣ ከሴትና ከውስኪ ሌላ አላማ የሌለው ወንድሞችን በማጋጨት የሚታወቀውና የማቅ ሰዎች የሆኑ ጓደኞቹን ሲያገኝ፣ እገሌ ተሃድሶ ነው ጴንጤ ነው በማለት የሚከስ፣ በወንጌል አገልግሎት የተጠመዱትን ሲያገኝ ደግሞ እገሌ የማቅ ደጋፊ ነው እያለ እርስ በእርስ የሚያጣላ፤ ከገንዘብ ውጪ ምንም ራዕይ የሌለው ይህንንም ለማግኘት ከመግደል ወደ ኋላ የማይል፣ የሀገሩን ሰው ብቻ የሚጠቅም ዘረኛና በጥቅም የታወረ ነው ይሉታል የሚያውቁት፡፡ ለምሳሌ በቀድሞው ሥራ አስኪያጅ የሥራ ጊዜ ሰባክያንን ለመቅጠር በተዘጋጀው ፈተና ላይ ባሕሩ ለአገሩ ተወላጆች ብቻ እየለየ መልስ ይሰጥ እንደነበር ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ በፈተናው ውጤትም ከ1ኛ እስከ 7ኛ የወጡ ሳይቀጠሩ 17ኛ የወጣው ንጉሡ ዓለሙ በባህሩ እርዳታ ለቄ ሚካኤል ተቀጥሯል፡፡ ይህም በአገር ልጅነት የሖነ ነው፡፡

በደብረ ሲናው እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን የቤት ሽያጭ ወንጀልን ለማፈን ሲል በጉቦ የተነከረው ባህሩ ተፈራ በጉቦ ታውሮ ውሳኔውን ለማሻር ጥረት ቢያደርግ አይገርምም ይላሉ ታዛቢዎች፡፡ የአስተዳደሩ ጉባኤ በተለይ ነባሮቹ አባላት ግለሰቡ ቃለ ጉባኤው ላይ ያልፈረመውና ወደ ሕግ ያልወሰደው በጉቦ መሆኑ አውቀዋል፡፡ ከሁሉም የሚገርመው ግን የደብሩ ካህናት በዕለታዊ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ችግር ላይ እያሉ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ የቤት ሽያጩ ውሳኔ የት ደረሰ? ብሎ መጠየቅና ተፈጻሚነቱን መከታተል ሲገባው በድጋሚ ለማየት ለምን ፈለገ? የሚለው አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል፡፡ የሀገረ ስብከቱ የሕግ መምሪያ ሃላፊ በሀገረ ስብከቱ ፍትህ እንዲሰፍን ከመሥራት ይልቅ የወንጀለኞችን ሰነድ መደበቁና ለእነርሱ ከለላ መስጠቱ በራሱ ወንጀል ነው፡፡ ፍትሕ ጠፍቷል ተብሎ ሹም ሽር ቢካሄድም እንዲህ ዓይነት አይን ያወጣ ክሕደት ያውም ሕግን ይተረጉማል ተብሎ በሚጠበቅ ግለሰብ ፍትሕ ሲቀለበስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስተዳደር ጉባኤ ለምን ዝም አለ?

የደብሩ ማይክ አዟሪ ንብረት ክፍል የነበረውና አሁን ደግሞ ገንዘብ ያዥ ሆነው ብርሃን መኮንን በ600 ብር ደሞዝ ባለአንድ ፎቅ ሕንጻ እዚያው ቤተክርስቲያን አጠብ ሲገነባ የእነ እስጢፋኖስ ቤተኛ ስለሆነ ብቻ ከተጠያቂነት ተከልሏል፡፡ እነባሕሩ ይህን ነበር ወደ ብርሃን ማውጣት የነበረባቸው፡፡ እነርሱ ግን ለእነርሱ ሽፋን ነው እየሠጡ ያሉት፡፡ በሰንበት ት/ቤቱ አመራሮች የባከነውን ገንዘብ በተመለከተም በሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ተሰጥቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አመራሩ በዮናስ መኮንን በኩል ለባህሩ በሰጠው ጉቦ ነገሩ ታፍኖለት ተይዟል፡፡

ባህሩ የሕግ ትምህርቱን ዩኒቲ ኮሌጅ የተማረ ሲሆን እርሱን ጨምሮ 10 ልጆችን ቤተ ክህነቱ አስተምሯል፡፡ ከዚህ የተነሳ መወገን የነበረበት ፍትሐዊ ሆኖ አስተምራ በስራ ላይ ላሰማራቸው ቤተክርስቲያን ነበር፡፡ እርሱ ግን የቤተክርስቲያንን ገንዘብና ንብረት ለዘረፉት ጥብቅና መቆሙ ሃላፊነቱንና የቤተክርስቲያንን ውለታ መርሳቱን ያሳያልና ትልቅ ጥፋት ሆኖ የሚቆጠር ነው፡፡    

ይህ በእንዲህ እንዳለ አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ቀደም ብሎ ኮሚቴው ለካህናቱ ደመወዝ እንዲከፍሉ ደብዳቤ ጽፎ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፈው ማክሰኞ የሕንጻ አሰሪው ኮሚቴ ንቡረ እድ ኤልያስን ካነጋገረ በኋላ አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ቀደም ብሎ የጻፈውን ይህን ደብዳቤ በቃል ትእዛዝ ሽሮ ቆጠራ አካሂዱ ብሎ ማዘዙ ሌላ የተጫነው አካል እንዳለ ያሳያል፡፡ የደብሩ ካህናት አሁን የሚያስፈልጋቸው ተፈጻሚ የማይሆን የሀገረ ስብከቱ ደብዳቤ ሳይሆን ወርኃዊ ደመወዛቸው ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ለቤተክርስቲያን ብልሹ አሠራር መንሰኤ ከሆኑት መካከል የሕንጻ አሰሪዎች ዘረፋ፣ የሰንበት ት/ቤት አመፅ የጥቂት ካህናት ከወንበዴዎች ጋር መወገን በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የአጥቢያው ምእመናን ግልዴለሽነት ለመሆኑ፣ ውሳኔ ተሰጥቶት ውሳኔው መፈጸም ያልቻለው የደብረ ሲና እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በግልጽ የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ የሥራ አስኪያጁ ደብዳቤ በቃል ትእዛዝ እንዲሻር መደረጉ ግን ከንቡረ እድ ኤልያስ ጋር ነው የሚያያዘው፡፡ በዚህ ውስጥ ንቡረ እድ እንደዚህ ባሉ ጉዳዮች ዳጎስ ያለ ጉቦ መቀበልና በቀድሞው ሥራ አስኪያጅ የተሠሩ መልካም ሥራዎችን የማበላሸትና ወደኋላ የመመለስ ሥራ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ ለዚህም በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ላይ የተወሰነውን ውሳኔ ወደኋላ የመቀልበስና ለጥቂት ዘራፊዎችና ሕገወጦች ጥቅም ሲባል የካህናቱን ዕለታዊ የኑሮ ችግር የማባባስ አካሄድ መጀመሩ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ የቤት ሽያጭ ጉዳይ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በእነባሕሩ የተሣሣተ መረጃ መሳሳት የለበትም፡፡ ሌላው ቀርቶ ቤቱ ያለጨረታ መሸጡ ብቻ እንኳን ከታየ ወንጀል ነው፡፡ እርሳቸው ምንም ይሁን ምንም በመረጃ ተደግፎ የተወሰነውን የቀድሞውን የአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ ወደማስፈጸምና አላስፈጽም ያለውን የሕግ ክፍሉን መጠየቅ እንጂ የቀድሞውን ትክክለኛና በማስረጃና በማጣራት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለመሻር ሁኔታዎችን የሚያመቻች ስብሰባ መጥራት ወይም በዚህ አጀንዳ ላይ ለመነጋገር መድረክ መክፈት አልነበረባቸውም፡፡ አሁንም አማራጩ ውሳኔውን መስፈጸም ብቻ ነው፡፡


28 comments:

 1. ai orthodox yegubo ena ye Amenzira bet yasazinal

  ReplyDelete
 2. በጣም ያሳዝናል። ጽደቅን የሚወድ ትውልድ ከየት ይመጣ ይሆን ሁሉ በዘር በቀበሌ በኃጢአትና በገንዘብ ፍቅር ተቧድኖ የእግዚአብሔርን ዓይን ይወጋል። እናት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ያስብሽ። በውስጥሽ የሚርመሰመሰውን የኃጢአት ሠራዊት ይንቀልልሽ። የክስርስቶስን ፊት በደስታ የምዪበትን ቀን ቅርብ ያርግልሽ።

  ReplyDelete
 3. አይ ባህሩ አፍር አባትህን ብላ አዋረድኸን ። መቸ ይሆን እርሷ ክርስህ የምትሞላዉ
  ሴት ና ወድህን ትወዳለህ

  ReplyDelete
 4. 'Aba Selamas' most of the time you feed us false information. I can say atleast 95% is wrong.I think this is due to you are (forged/artificial/fake)orthodox. So,it is better to ask our selves to the responsible body and know the reality.

  ReplyDelete
 5. ሊቄ ሚካኤል ፲፯ኛ ወጥቶ አሁን የተቀጠረው ንጉሡ ባህሩ ፭ሺ ብር ለዳዊት መሠጠት አለበት ብሎ ተቀብሎታል ንጉሱ አለሙ ቱሉ ዲምቱ ድረሥ ሒዶ ለባህሩ ሰጥቶታል ያውም ቱሉ ዲምቱ ለማጣራት ሒዶ ሥራ ላይ እያለ ሰጥቶታል

  ReplyDelete
 6. ስለዚህ መሠሪ ሰው ጉቦኛ ዘረኛ በወንድሞች መካከል ጠብ እየዘራ በጥርሡ እየገደለ ላለ ሰው አባ ሰላማዎች እስከዛሬ አለመጻፉችሁ ይገርመኝ ነበር

  ReplyDelete
 7. እንዴ እንዴ እንዴ በስንቱ ሴት ላይ የተጫወተ እኮ ነው እኔ አባ ሰላማን እንዳይ ሰው ነገረኝ እኔን ራሴ አገባሻለው ብሎኝ በልቶኛል[ ሰላም ነኝ ከአራት ኪሎ ከአንዱ የሴቶች ቡቲክ ]ሥለእሡ ብዙ መረጃ አለኝ እባካችሁ ሌሎች እንዲነቀቁ ልሥጣችሁ ግን በምን በኩል

  ReplyDelete
 8. የባህሩ ሌላ ሥሙ የሚከራይ ሚዜ ይባላል

  ReplyDelete
 9. የዮናሥ ፍቅረ ሚሥት በሥተመጨረሻ ሕይወቷ ተቃና እንጂ ባሕሩ ምን እንደሰራ የሚያውቅ ያውቃታል

  ReplyDelete
 10. ባህሩ እኮ ከአንቦ ውጪ ሌላ ሰው ኢትዮጵያዊ አይመስለውም መምህር ሆኖ በሀላፊነት ላይ ያውም በህግ ተቀምጦ እንዲህ ሲያስብ ይገርመኛል[ከጓደኞቹ አንዱ]

  ReplyDelete
 11. እጅግ ትክክለኛ ስያሜ ወወሩ[ ወጣት ወልደ ሩፋኤል ]ከረባትና ሱፍ ይወዳል ባህሩም እንደዚያው ፣ወልደ ሩፋኤል ዘረኛ ነው ባህሩም እንደዚያው ፤ ወልደሩፋኤል አላገባም ባህሩም እንደዚያው ፤ ወልደሩፋኤል መንገድ ላይ ያያትን ሴት ዝም ብሎ ይከተላታል ባህሩም እንደዚያው፤ወልደሩፋኤል ከማቅ ጋር ሢያሠኘው ከእነርሡ ተቃዋሚ ጋር ይበላል ይጠጣል ባህሩም እንደዚያው፤ይህን ስያሜ ያወጣ ሰው ይገርማል።ወይ ወወሩ

  ReplyDelete
 12. No wonder the real Orthodox Christian flock is fleeing the danger of being the receiver of God's wrath. At this stage of its history the Ethiopian Orthodox Church is very ripe for God's wrath. The corruption top to bottom, the injustices done to those that ask why the church became a political arena, the persecution, maiming and killing of devout Bible teaching Christians by a rogue out of control so called Christian organization named “Mahibere Kidusan (MK), etc. etc. It is just too much to fathom that a religious organization could mire in such a rut it could not pull itself out from. It seems like Satan has won the battle in this giant religious organization that is too big to fail. In God’s time, it is our prayer that He sends his angel to clean house for the sake of the persecuted. Until then let us all get on our knees and pray for those that are persecuted and the persecutors that worship the idol named ‘almighty dollar’ instead of the living Almighty God. They, by their greed and pride led millions of unsuspecting and innocent worshipers astray. Let God have mercy on their soul.

  ReplyDelete
 13. የናንተዉ ጉድ ግብረሶዶሙ 'ደን' አሸናፊ መኮንን

  ReplyDelete
 14. የባህሩ ጉቦ ጠቅላይ ቤክ ሥብከተ ወንጌል መምሪያ ጸሀፊ እያለ የሚጀምር ነው የሀገሩን የአንቦ [ጉደር]ካልሆነ አይፅፍም ነበር እሥኪ አሥራት አያንሣ፣ተስፋዬ ቂንጤሣ ይጠየቁ አሥናቀ ስጋ ቅብ ይመስክር

  ReplyDelete
 15. በመሠረቱ ለባህሩ ወደዚህ ለሀገረ ሥብከት እንዲገባ ትልቅ እርዳታ ያደረገለት ደስታ ጌታሁን መሆኑን ስንቶች እናውቃለን ምን ያደርጋል ታዲያ በደስታ ከሚያሤሩ አንዱ በጥርሱ ገዳይ ባህሩ ነው

  ReplyDelete
 16. የአባ ሰላማ ሚዛናዊነትን አሁን ተረዳሁ

  ReplyDelete
 17. ዳዊት ታደሰ ባህሩን ውሥኪ እያጠጣ መልሶ ይህ መሬት ቸብቻቢ ይለዋል እዚያው ኤፍሬም ውሥኪ ቤት አይ ወወሩ

  ReplyDelete
 18. ባህሩ ተፈራ ጉቦ የማይፈራ

  ReplyDelete
 19. ባህሩ ድንቁርናውን በከረባት በሱፍ ውስጥ ይደብቃል

  ReplyDelete
 20. በሁለት ቢላ ያላችሁት ትክክል ቢሆንም የእሡ ግን በፊት ለፊቱ ይሠራል [ይወጋል]የጥላሁን አበበ መልሥ እለት ፕሮግራም ሲመራ ቆይቶ በጋሻው ሢመጣ ስሙን ላለመጥራት ያደረገው ነገር በጣም እሥከዛሬ ያንገበግበኛል በጋሻው ግን ሰርግ ጠራው ባህሩም ሂዶ በላ

  ReplyDelete
 21. አቤት የቢሮ ጠረጴዛ ውሥጥ የከተታቸው ያልተፈፀሙ ፋይሎች እሥከዛሬ ይደራርባቸዋል

  ReplyDelete
 22. ወወሩ የ፩ ወር የዱባይ መዝናናት የሰላም የገንዘብ ወጪ እባክህ አሁንም እንደሌሎች አትተዋት አግባት

  ReplyDelete
 23. ለውጥ እየታየበት ካለው ክፍል አንዱ ስብከተ ወንጌሉ አንዱ ነው እንደ ባህሩ አይነቱ ግን በዳዊት ሥም እየነገደበት ነው ንጉሱ አለሙ ፭ሺ አምጣ እያለው በዳዊት ሥም ወሥዷል ዳዊትን ተጠንቀቁ

  ReplyDelete
 24. የዚህን የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤ፨ክ ጉዳይ ለምን በውሰት ለሌላ ደብር አይሰጡት

  ReplyDelete
 25. በአዲስ አበባ ሀገረ ሥብከት ታሪክ በስጦታ የተገኘ ቤት የተሸጠበት ደብር ምን አይነት ሌቦች ቢሆኑ ነው ባህሩ ደላላ ቢሆንሥ ይህን አረጋግጡ በቅድሚያ

  ReplyDelete
 26. የሥብከተ ወንጌል መምሪያ ጸሀፊ እያለ መጋቤ ብሉይ አይመረ ባቀረበው በሳል አመታዊ ሪፖርት የተናደደው ባህሩ የመምሪያውን ሰባክያንን አሳምጾ አዕመረን ማሥነሳቱ ይገርመኛል ይህን ሲያደርግ ግን እየሳቀ ነው

  ReplyDelete
 27. እውነት አባ ሰላማ ብሎግ ባይኖር ይህቺ ቤተክርሥቲያን ምን ይውጣት ነበር የመረጃችሁ ጥራት ሁሌም ይገርመኛል ተግታችሁ ለእውነት ብላችሁ እንደምትሠሩ ያሥታውቃል በርቱ በተለይ ስለ አዲግራት ያረጁ ፅላቶች የሚቀየሩበት መንገድ የዘገባችሁት ደስ ይለኛል ሁልጊዜ

  ReplyDelete
 28. እውነት አባ ሰላማ ብሎግ ባይኖር ይህቺ ቤተክርሥቲያን ምን ይውጣት ነበር የመረጃችሁ ጥራት ሁሌም ይገርመኛል ተግታችሁ ለእውነት ብላችሁ እንደምትሠሩ ያሥታውቃል በርቱ በተለይ ስለ አዲግራት ያረጁ ፅላቶች የሚቀየሩበት መንገድ የዘገባችሁት ደስ ይለኛል ሁልጊዜ

  ReplyDelete