Tuesday, May 24, 2016

የማቅ ኤግዚቢሽን በግንቦቱ ሲኖዶስ መክፈቻ ዕለት መከፈቱ ለምን ይሆን?

በዘንድሮው ዐቢይ ጾም ውስጥ ሊደረግ ታስቦ የከሸፈውና የነፈሰበት የማቅ ኤግዚቢሽን በነገው ዕለት ሊከፈት መሆኑን ማቅ ፈራ ተባ እያለ በመግለጽ ላይ ነው፡፡ ኤግዚቢሽኑ ባልጠፋ ቀን በዚህ ዕለት መዘጋጀቱ በኤግዚቢሽን ማእከል የነበረው ክፍት ጊዜ ይህ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎና ከሲኖዶሱ ስብሰባ ጋር እንዲያያዝ ተፈልጎ እንደ ተዘጋጀ የሚናገሩ አሉ፡፡ ማኅበሩ ኤግዚቢሽኑ ተፈቀደልኝ ካለ በኋላ ሊያሳይ የቀጠረው በሲኖዶስ ስብሰባ የመጀመሪያ ቀን ላይ መሆኑ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ጥላውን ለማጥላት አስቦ ያደረገው መሆኑን ብዙዎች ይገነዘባሉ፡፡
ይህን ኤግዚቢሽን ከዚህ በፊት እንደ ተደረገው እንደ አብነት መምህራኑ የግዮኑ ጉባኤ የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን የፈቃድ ደብዳቤ ፓትርያርኩ ባላቸው ሥልጣን ድንገት ያግዱታል ብሎ እስከ አሁን እየተኛና እየባነነ እንዳዘጋጀው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡

በማኅበሩ አካባቢ ያሉ ምንጮቻችን እንደሚናገሩት ባለፈው በታገደው ኤግዚቢሽን ስም ቀደም ብለው ከሸጡት ቲኬት የተሰበሰበ በርካታ ብር መጥፋቱን ይናገራሉ፡፡ ለዚህም ኤግዚቢሽኑ ታገደ ሲባል ከአመራሮቹና ከዝግጅት ክፍሉ ከፊል ኮሚቴዎቹ በጣም ተደስተው እንደነበር ይነገራል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ባባከኑት ብር ከተጠያቂነት ለመዳን ብለው ነው ይላሉ፡፡
ከዚህ በፊት በዓመት ሁለት ጊዜ በሚደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ዋዜማ ላይ ከመንገድ ላይ እየጎተተ ጭምር በሰንበት ተማሪ ስም ዩኒፎርም አስለብሶ አጀንዳ ይያዝልኝ ማለቱ የተለመደ ነበር፡፡ ከ2 ዓመታት ወዲህ ግን ይህ ዓይነቱ ድርጊት ቀርቷል፡፡
በዚህ ኤግዚቢሽን አባ ሳዊሮስ፣ አባ ኤልያስ፣ አባ ሉቃስ፣ አባ ማቴዎስ አባ ቀውስ ጦስ፣ አባ እንድርያስ እንደሚገኙ ይገመታል፡፡ እነርሱንም በኤግዚቢሽኑ “ተሐድሶ መጣብህ” የሚል መልእክት በማስተላለፍና እነርሱን በመጫን ጩኸቴን አሰሙልኝ ለማለት እንደሆነ ከፍተኛ ግምት አለ፡፡ በዚህም እንደ አቡነ ጳውሎስ ጊዜ ፓትርያርኩን እንዲያውኩለትና ማቅ የሚፈልገው አጀንዳ እንዲያዝለት ለማድረግና አሁንም ለቤተክርስቲያን ያለሁላት እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁልኝ ለማለት ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሆኖም ፓትርያርኩና ለማቅ ሳይሆን ለቤተክርስቲያን የቆሙ ጳጳሳት  የማቅን እኩይ ዓላማ ቸል እንደማይሉትና በጽናት እንደሚታገሉት ይጠበቃል፡፡  
ማቅ ከራሱ ውጪ ሌላ አጀንዳ የለውም፡፡ ዛሬ ቤተክርስቲያኒቱ በብዙ ነገር ግራ ተጋብታ፣ በመልካም አስተዳደር እጦትና በሙስና እየተንገላታች፣ በአስከፊ ሁኔታ የምእመናን ፍልሰት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ እርሱ ግን አሁንም የሚያስበውና የሚያልመው አትራፊ የሚመስለውን “የተሐድሶ መጣብህ” ርእስ መርጦ ገንዘብ  መሰብሰብ ነው፡፡
ሀገራዊ ድርሻን በተመለከተ እንኳን ስንቱ ወገን በጎርፍ ቤቱንና ንብረቱን እያጣ ስንቱ ሕይወቱን ጭምር እየተቀጠፈ፣ ድርቁ ባየለባቸው ቦታዎች ሕጻናት እየረገፉ፣ ከራሳቸው በላይ የቤት ጣሪያ የሌላቸው የክረምት ዝናብ የሚወርድባቸው የበጋ ጸሐይ ያከሰላቸው ስንት ወገኖች በሞሉባት አገራችን ማቅ አሁንም “ተሐድሶ መጣብህ” እያለ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚያደርገው ጥረት ሲታይ በሃይማኖት ሽፋን ገንዘብ መሰብሰብን ሥራዬ ብሎ መያዙን ያስረዳል፡፡


24 comments:

 1. ውይ የተሰረዘው ኤግዚቢሽን ሊከፈት ነው? እንደዛ ተዘጋ ብላችሁ የጨፈራችሁበት? የዲያብሎስ ደስታ መከና! ሃሃሃ አይ አባ ዲያብሎሶች። ግራ ገባችሁ እኮ።

  ReplyDelete
 2. አበጀን ገና ይሰበሰባል .....እነ ሆድ አምላኩ....

  ReplyDelete
 3. ምንም ቁምነገር የሌለው ገለባ.....

  ReplyDelete
 4. the propaganda blog,MK does not touch a penny for their on intreset.

  ReplyDelete
 5. enem yegeremegn esu new

  ReplyDelete
 6. እውነቱ ይነገር ይሰማMay 25, 2016 at 2:38 AM


  ይድረስ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ!
  አንድ መሰረታዊ ጥያቄ አለኝ ?
  የሚችል ወገን ካለ ይመልስልኝ?

  በእውነት ይች አገር/ቤተ ክርስቲያን በቃሉና በመንፈሱ የበሰሉ ሽማግሌ መሪዎች ጨርሶ የሏትም ማለት ነው?

  ኦ! እግዚአብሔር ሆይ!!!እባክህ ይህን እረኛ ያጣ ሕዝብ በመስቀሉ የልጅህ የማዳን ሥራ ስትል ብቻ በመለኮታዊ አሠራርህ ድረስለት???

  ወገኖች ሆይ! እባካችሁ ሰሞኑን በጾም በጸሎት ከእንባ ጋር በአምላካችን እግር ሥር እንድንሆን በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ???

  እግዚአብሔር ሆይ!
  የሲኖዶሱን ስብሰባ
  ለአገር/ለቤተ ክርስቲያን
  ጥቅምና ብርታት የሚሆን ውሳኔ
  በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንዲወስን
  ጣልቃ ግባ???
  ክፉው መንፈስ ይፈር
  ኢየሱስ ክርስቶስ ይክበር
  የሳተም ይመለስ
  ሕዝባችን በሙሉ ይባረክ
  አ ሜ ን !

  በመለኮት ፍቅር

  እውነቱ ይነገር ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ውሸቱ ሙልጭ ያልክ ወንበዴ ነህ!!!!ታስታውቃለህ!!!!!!!!!!

   Delete
 7. ሰይጣናዊ አስተሳሰብህ አስተካክለህ የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ መሆኑን መስክር፡፡ የአግዚአብሔር ሥራ ከአንተ ተንኮል እና ግምት እጅግ የረቀቀ መሆኑን አስተውል፡፡ አግዚአብሔር ለሚያምኑት የልባቸውን መሻት እንደሚፈጽም ተረዳ፡፡ ሰይጣን ግን አይደለም የሰውን ልጅ ሥራ የአግዚአብሔርንም ሥራ በተንኮል አጣሞ በማስተማር የሰውን ልጅ ከእግዚአብሔር መንግሥት ውጪ ቢያደርግም ከሰው አዕምሮ አስተሳብ በላይ በሆነ ሁኔታ እንዴት ወደ አግዚአብሔር መንግሥት እንደመለሰው አስብ፡፡ አሁንም የአግዚአብሔር ሥራ ከአንተ ተንኮለኛ አዕምሮ በላይ መሆኑን ተመልከት፡፡
  አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ በለህ ለምን! ይሰጥህማል፡፡

  ReplyDelete
 8. rasih tehadiso silehonk mehonu yastawuqbihal

  ReplyDelete
 9. እንግዲህ ምን ታመጣ ኤግዚቢሽኑም ተጀመረ ምዕመኑም ስለ ቤተክርስትያኑ፣ ስለሚጠበቅበት ድርሻና ስለናንተ መሰሪነት በደንብ ሊያውቅ ነው

  ReplyDelete
 10. እውነትም መጣብሽ ሐራ ጥቃ/ተሐድሶ/ ሁሉ! ማኅበረ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ኃይል ልዕልናውን ያሳበት አውደ ርዕይ ብዬዋለሁ! ማኅበሩን ከመንግሥት ጋር በማጣላት ለማትረፍ ነው አይደል የረሀቡን ጉዳይ ያነሳሽው፡፡ ተነቃብሽ፤ መንግሥትም ባነነብሽ ሐራ ጥቃ/ተሐድሶ/ ሁሉ! እንግዲህ ከሊቃውንቱ ጋር ገጽ ለገጽ ናና ተሟገት፡፡ ቤተ ከርስቲያኒቷ ምን ዓይነት መሠረት ላይ የቆመች እንደሆነች እንድታይ እንደምዕመንነቴ አባ ሰላማ ብሎገሮች/ሐራ ጥቃ/ተሐድሶ/ በሙሉ ጥሪ አድርጊያለሁ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ስም ኖኖኖ በራሴ ስም ትኬቱን እኔው እራሴ ስፖንሰር አድርጊያችኋለሁ፡፡ ብትቀሩ ወየሁ እቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ...

  ReplyDelete
 11. kikikiki.......

  ReplyDelete
 12. Aba Hasetoch eferuuuuuuu engdih, We will go to the Exhibition and know your lies in detail. What ever MK is doing, you always complain. You thought that the exhibition will be held, but God and our Mother are always with us. Libona Yistachu nuna gudachihun Eyu.

  ReplyDelete
 13. Hi haratikas/Tehadiso/ You can also prepare exibition and show Jacket of Luther.
  Waw nice exhibition.....temesgen....

  ReplyDelete
 14. የተለሠነ መቃብር፤ ውሃ የሌለብህ ምንጭ እንደሆንክ ሁሉም ይረዳሃል:: የርኩሰት ልጅ ማለት እንደ አንተ ያለው ነው:: ስለራስህ እምነት ብታወራ ያምርብህ ነበር በማታምነው እምነት ስም ከምትቀባጥር::

  ReplyDelete
 15. teru new hezbu tegneto neber ... ahun ke hasetegna ketadeso tetenkeku sibalu... tadson defend lemareg metsaf kedusen endiyaneb yaregewal.... metsaf kedus siyanebu ewenet yegeletselachewal.... eweneten siyawk tereten yetewal....... Metsaf kedus endatanebu belo bimekrachew Mk cherash endiyanebu mekeskes new........ ena melkam new awde ray

  ReplyDelete
 16. The very sensitive or pivotal issue is whether or not we Ethiopians for the most part understand how we are redeemed, get salivation, and achieve the propitiation, and by that, is it really fully perceived that what are mentioned above as given to us through his( Jesus) grace are also the salivation of the father and holly spirit? so when we confront this reality, the thing is that Ethiopians across the Nation need to be indoctrinated with the gospel so as to fully perceive GOD( the trinity), and evade confusion which for the most part has engulfed the community for centuries that sorting out the distinction between the redeemer and followers of GOD........human beings is still controversy. There is no life devoid of the name Jesus, the name itself is liberator, redeemer, a name so precious above all names be it in the heavens or earth. and also we know that Jesus has said to us any one who testifies for this name will in return receive my testimony before the angles of GOD, our mouth will never refrain from calling this name called Jesus as part of the trinity......Jesus is LORD........Christ is the almighty......., as the father is still working, Jesus is also working, he is the omnipotent, the omnipresent, so why do I require another help from human being? did Christ said that he is tired and needs help? no, his divinity is every where, his fullness has covered the universes beyond our comprehension,no one other than the trinity has such an authority of fullness and his Love is true and honest, so why are people deceived with teachings that force them depend on human beings who are not even away from emotions? we shall remain preaching Jesus Christ who has been crucified.

  ReplyDelete
 17. The very sensitive or pivotal issue is whether or not we Ethiopians for the most part understand how we are redeemed, get salivation, and achieve the propitiation, and by that, is it really fully perceived that what are mentioned above as given to us through his( Jesus) grace are also the salivation of the father and holly spirit? so when we confront this reality, the thing is that Ethiopians across the Nation need to be indoctrinated with the gospel so as to fully perceive GOD( the trinity), and evade confusion which for the most part has engulfed the community for centuries that sorting out the distinction between the redeemer and followers of GOD........human beings is still controversy. There is no life devoid of the name Jesus, the name itself is liberator, redeemer, a name so precious above all names be it in the heavens or earth. and also we know that Jesus has said to us any one who testifies for this name will in return receive my testimony before the angles of GOD, our mouth will never refrain from calling this name called Jesus as part of the trinity......Jesus is LORD........Christ is the almighty......., as the father is still working, Jesus is also working, he is the omnipotent, the omnipresent, so why do I require another help from human being? did Christ said that he is tired and needs help? no, his divinity is every where, his fullness has covered the universes beyond our comprehension,no one other than the trinity has such an authority of fullness and his Love is true and honest, so why are people deceived with teachings that force them depend on human beings who are not even away from emotions? we shall remain preaching Jesus Christ who has been crucified.

  ReplyDelete
 18. " ልብህ ንፁህ ከሆነ አሸናፊ ነህ " ከሚለው ጀምሮ ብዙ ይባላል ግን ማሸነፋም ይቅር እና ..ልበ ንፅሁዎች በሰላም ይኖራሉ ወይ ? እስቲ እውነቱን እንመልከት ..ብዙ ግዜ አንድ ግዜ ብቻ አይደለም ለዚያውም በተደጋጋሚ የሚጎዱት ልባቸው ንፁህ የሆኑት ናቸው ህይወታቸው የስቃይ እና የመከራ የሚሆንባቸው ...የደስታ ፀሀይ የማትወጣላቸው ..ለደግ እና ለቅን ሰዎች ነው ግን ለምን ? ምንም እንኩዋ ልበ ንፁህና ቅን መሆን ደስ የሚል ባህሪ ቢሆንም..መልሶ ለራስ የሚተርፍ መልካም ሀሴት እንደሆነ ቢታወቅም ሊከበሩበት በሚገባቸው .ነገራቸው ለምን ይጠቁበታል ...ለምን ይጎዱበታል ? በሌሎች ጥፋት ለምን እነሱ ተጎጅ ይሆናሉ ? ንፁህ ልብ ስንል የንፅህና ወሰኑ እስከምን ድረስ ነው ...የሚለው መታወቅ አለበት...ይህ ከታወቀ ለመጠንቀቅም ይበጃቸዋልና ምክንያቱም " የመልካም ሰዎች እድል በክፋት ሞት መጠቃት ነው " ይባላልና እናስ መልካም እና ልበ ንፁህ ሰዎች ..ለምን በክፋት ሞት እንዲጠቁ በር እንከፍታለን ? ማለቴ ንፁህ ሰዎች ለእኛ ንፁህ ስለሆኑ ለምንድን ነው የምንጎዳቸው...እሺ በሌሎች ሲጎዱ ስናይ ..ለምን ዝም እንላለን ..ልንከላከልላቸው ..ልንጠብቃቸው አይገባም ወይ ..ከተጎዱ ...ከወደቁ በሁዋላ " እከሌ እኮ ጥሩ ሰው ነበር " ብለን ከንፋር ከመምጠጥ ባለፋ ..ቀድመን እኛ ልንደርስባቸው አይገባም ወይ ?እኛ እያየን እንዳላየ ካለፍን ..ከጎጂዎቹ ያልተናነሰ ተግባር አልፋፀምንም ወይ? ከዚህም በላይ ..በምድር ላይ እድሚያቸው አጭር ነው " ደግ አይበረክትም "እንላለን ... ፈጣሪ ስለወደደው ነው ብለን ስበብ እንፋጥራለን ... በአንድ ወቅት በጣም የምወደውና የማከብረው ልበ ቅን የሆነው ጉዋደኛየ ..በልብ ህመም እየተሰቃየ ሳየው .." ስንት ልብ የሚያቃጥሉ ስዎች እያሉ ..ለአንተ የህን ሰጠህ እያልኩ አስብ ነበር .. እስቲ በዙሪያችሁ...በጎረቤታችሁ ..በዘመዶቻችሁ በቤተሰባችሁ አስተውሉ ...ጥሩ ሰዎች..ልበ ንፁህ ሰዎች .. ..እየተመረጡ ሄደዋል ..አለዚያም በስቃይ እና በመከራ ውስጥ ናቸው ክፋዎች ..ልብን የሚያቃጥሉ ግን በሰላም ይኖራሉ ...( የፋጣሪ ተአምር እና ስራ እንዲህ ነው ተብሎ ባይመረመርም) እኔ ግን እጠይቃለሁ ..ንፁሆች ..ያለጥፋታቸው ለምን ይቀጣሉ ? ደግና ቅን ሰዎች በሌሎች ሰዎች ምክንያት የስቃይ እና የመከራ ህይወት እንዲኖሩ ይገደዳሉ ..ለምን ? ለምን ?

  ReplyDelete
 19. የሁለት ጊዜ አንበሶች….
  የ363 ቀን የቤተክርስቲያን ችግሮች……ሊቃነ ጳጳሳት!!
  (ይህ ጽሁፍ ሁሉንም ጳጳሳት አያካትትም)
  ሁላችንም እንደምናውቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሱን በቅዱሳን ስም “ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል የሰየመው ሃይማኖታዊ የፖለቲካ ድርጅት ላለፉት ከሁለት አሥርት አመታት በላይ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን እና በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን አገልጋዮች፤ አማንያንና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ሐቅ ነው፡፡ መነሻ ሀሳቤ ማህበረ ቅዱሳን ያውም ገና ጨቅላው ማህበር አሁን የሚሰራውንም ሆነ ወደፊት ሊሰራ ያሰበውን ተግባር ቤተክርስቲያናችን ማህበረ ቅዱሳን ከነ ስም አጠራሩ ባይኖርም አሳምራ እንደምትሰራው ነው፡፡ ‹‹በእውነት ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም››.. እንደሚባለው፡ አሁን አሁን በዚህ ጊዜ እስትራቴጂክ መቋቋምና መደራጀትን መሰረት ያደረገው ማህበር ያቀደውና ያሰበው ተግባር በይፋ ቁልጭ ብሎ በግልጥ መታየቱ ሃይማኖተኛው ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያዊም ስለ ቤተክርስቲያናችን እንዲያወራ ያደርገዋል፡፡
  ገና አንድ ፍሬው ማህበር የ25 ዓመቱ ወጣት ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንደዚህ ሲያምሳት፤ ቅዱስ ፓትርያርኩን በመቃወም ሰጣ ገባ ውስጥ ከገባበት ቀን ጀምሮ ብሎም ላለመበገር በማሰብ ድብቅ ተግባሩን በጳጳሳት ላይ አድርጎ በመስራት ያቦካው ቡኮ ይኸው ዛሬ ለዘመናት ተከብሮና ተወዶ በኖረው የሲኖዲዎስ ስብሰባ ላይ በጉልህ በመታየት ግጭት ፈጥሯል፡፡ በተቀጠሩ ጸሀፊያን በመጻፍ የሚያደናግረው ማህበረ ቅዱሳን ሰሞኑን በሚያወጣው ጽሁፍ በጣም ብገረምም፤ ለካስ የሚሰራውን ድብቅ ተግባር እየተረከልን ኖሯል እንድል አድርጎኛል፡፡ እኛም ብንጽፍ የሱኑ ያህል እጥፍ ድርብ ነገር ለዚህ የዋህ ህዝባችን ባሳወቅነው ነበር፡ ግን ማንም የማንንም ታሪክ በመጻፍ ለውጥ መናፈቅ ስለማይኖርበት ስለተመረጡ ጉዳዮች መጻፍን መረጥኩ፡፡
  ማህበረ ቅዱሳን በአሁኑ ሰዓት በቅዱስ ሲኖዲዎሱ ላይ ስሚያደርገው እኩይ ተግባር ለመጻፍ መነሳቴ ያለምክንያት አይደልም፡፡ ማህበሩ እንዳቀደውና ጳጳሳትን አስቀድሞ መስመር ባስያዘበትና ማህበር ተኮር አደረጃጀትና ማህበር ተኮር ስር ነቀል ለውጥ ለማካሄድ ባቀደው መሰረት ይኸው አሁን አሁን የሚበሉትን ምግብ እንኳን ለመጉረስ ደጋፊ የሚያሻቸውና የወጣትነት ዘመናቸውን ነውረኝነት ለማህበሩ አሳልፈው የሰጡት….. እድሜ ጠገቦቹ ሊቃነ ጳጳሳት ንትርክና ብጥብጥ አምሯቸው ይመስል ለእውነት ላለመገዛት ችግር በመፍጠር በየዘር ተጓዳኝተው ላለሙለት አላማቸው አልያም ለሚናፍቁት ስልጣን ለመቆናጠጥ በሆነውም ባልሆነውም ችግር በመፍጠር ቤተክርስቲያንን እየከፋፈሏት ይገኛሉ፡፡
  ውድ አንባቢዎቼ ምናልባት እውነታው የሚገባቹ እኔ በምጽፍበት ቦታና መረዳት መጠን ላይ ስትሆኑ ይሆናል ቢሆንም በተቻለኝ መጠን ላስነብባችሁ ስለወደድኩት እውነታ ላስረዳችሁ እሞክራለሁ፡፡ እርግጥ ነው በዚህ ሰዓት ለማህበሩ ሁሉም ነገር የሞት ሽረት በሆነበት ሰዓት ምንም አይነት የጉልበትም ሆነ የተቃውሞ ጽሁፍ የማይዋጥለት ማህበረ ቅዱሳን ይህንን ሲሰማ እንደ እድሜ ጉዋደኛው ወሬውን ሊያቀላጥፍ እንደሚችል አስባለው፡፡ ሆኖም ይህንን ጽሁፍ በእውነት ለእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ባለኝ ጊዜ ሁሉ ለማድረስ እሞክራሁ፡፡

  ReplyDelete
 20. ለዚህች ሀገር ድርሻችን ምንድን ነው? ሁሉን ያወቅን ነን ስንል፡ የእውነት መገኛ መሠረት ነን ስንል፡ ታሪካዊና ዘመን ጠገብ ሆነናል ስንል፡ አፋችን ሙሉ ነው፡፡ ግን ለዚህች ሀገር ዕለት ዕለት ችግርና ጭንቅ፤ ዘረንኝትና ጎጠኝነት፤ መከፋፈልና ጥቅመኝነት፤ ግፍና በደል ዲያቢሎሳዊ ስራ እያበረከትን ነው፡፡ ለነገሩ ስንት ልዕልና የነበራቸው አባቶቻችን እና እናቶቻችን የሰሩትን እምነትና የገነቡትን ቤተክርስቲያናዊ ሀብት ዛሬ እራሳቸውን እንኳን መርዳት የማይችሉ የኋሊት ተጓዞቹ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲህ አናንቀው ቢጫወቱበት አይደንቅም፡፡ ያልደከሙበት ገንዘብና ያለሰበኩት ሃይማኖት እነርሱ ከሞቱ ምንስ ቢሆን ደንታ አይሰጣቸውም፡፡ ይህ ነው ወይ የእነርሱ ውለታ? (ምንም እንኳን ከሰው ውለታን ባይጠብቁም)። ከዚህ ፀሐይ የሞቀው እውነታ በመመርኮዝ ማኅበሩ የሚመራው በእነዚህ መሳጢዎች በመሆኑ ይህ ድርጅት ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ ነው ማለት ከኩርንችት በለስን እንደ መጠበቅ፣ ከዓይን ጆሮን እንደ ማመን ይቆጥራል። ለቤተ ክርስቲያን ሕይወት/ ለክርስትና መቆርቆር፣ የቅዱሳን አባቶቻችን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን አሰረ ፍኖት መከተል ማለት ከእንደዚህ ዓይነቱ በደል ነፃ ሆኖና እንዲህ ዓይነቱን ዕዳ አወራርዶ ነው።
  የአሁኑ ጳጳሳት ተበላ ተዘረፈ ቢሏቸው አያስጨንቃቸውም፡፡ የሀገረ ስብከቱን ምንነትና ደረጃ ተንቅቆ የማያውቅ ጳጳስ ሁላ ለመላዋ ቤተክርስቲያን ጨነቀኝ ጠበበኝ ቢል እውነቱ ባዶ ነው፡፡ ከሀገረ ስብከቱ በማዳበሪያ እየዘረፈ፡ አዲስ አበባ መጥቶ ቤተክርስቲያንን አዘረፋችኋት፤ ፓትርያርኩ እረዳት ይኑረው፤ የኛ ወዳጆች ይምሩን የሚል ጳጳስ በበዛበት ዘመን እውነተኛ ሲኖዲዮስ ይኖራል ማለት ዘበት ይሆናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ አምላካዊ ሥርዓት እየተጣሰ መሪው ተመሪ ተመሪው ደግሞ መሪ እየሆነ ሥርዓት አልባነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰፈነ ይገኛል፡፡ የዚህ ውጤትም ውሎ አድሮ እውነተኛው የሃይማኖት ትምህርት በሌላ የስሕተት ትምህርት እንዲለወጥ፣ አምላካዊው ሥርዓትም ፈርሶ በስፍራው የሰው ሥርዓት ምናልባትም ሥርዓት አልበኛነት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡

  ReplyDelete
 21. የፓትርያርኩ ይቆየኝና ምክንያቱም በሁሉም መንገድ እየተዘለፉና እተሰደቡ ስላሉ….ፋታ ያግኙ ብዬ ነው፡፡ የነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት ነገር ውስጤን እየከነከነኝ ነው፡፡ እንደ እውነተኛ ሸንጎ ፈራጅ ስብሰባ የገቡት፤ እንደታታሪ አንጥረኛ ከኛ በላይ ዘበት ያሉት፤ ቤተክርስቲያንን ለግለሰብ በማይረባ የይሁዳ 30 ብር የሸጧት፤ ዛሬ ሲኖዲዎስ ገብተው እውነተኛ መስለው ህዝብ የሚያደናግሩት፡ ቤተክርስቲንን የሚበድሉት እውነት ለምንድ ነው?፡፡ በመላው ሀገሪቱ ቤተክርስቲንን እንዲያስተዳድር የተሾመው ጳጳስ ነው ወይስ ፓትርያርክ? ያውም ገደብ በሌለው ስልጣን፡፡ የእምነታችን ችግርና መከራስ በብዛትና በጥራት እንዲሁም በአይነት ያለውስ የት ነው?፡፡ አዲስ አበባ ወይስ ጳጳሳት ባሉበት ሀገረ ስብከታቸው?፡፡
  የእውነት ይገርማችኋል የማህበረ ቅዱሳን የ25 ዓመት የድል ፍሬዎች የሆኑት በርካታ ብሎጎች የሚጽፉትን ስንመለከት የአሁኑ ሰዓት ጳጳሳት አንዳች ሀይል በየቤታቸው ቁም ስቅላቸውን እንደሚያሳያቸው ተረዳሁ፡፡ ወይ አባቶቼ በቁማችሁ ተሸጣችሁ ነው ያልኩት፡፡ ከዚህ በላይ ባርነት ከዚህ በላይ የበታችነት ከቶውኑም ከጳጳሳት አይጠበቅምና፡፡ ለካስ ሰይጣን እናተም ጋር አለ ለታይታ መኖር ተጠናውቷችኋል፡፡ 360 ቀን ድፍን ኢትዮጵያን በየሀገረ ስብከታቸው ሲመዘብሩና ግፍ ሲሰሩ ቆይተው ዛሬ በዓመት ሁለቴ ስብሰባ እውነተኛ መስለው ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ሆነው የሚበጠብጡት የኒህ ጳጳሳት ነገር ምንድን ነው?፡፡

  ReplyDelete
 22. አምላኬ ፈጣሪዬ ስለ ጳጳሳት ገመና እንዳልናገር ይርዳኝና አሰቃቂ ወንጀልና በደል፤ የካህናት የማያቋርጥ እንባ ፤ የምዕመናን ግፍ፤ የዘረኝነት ሰፊ ሜዳ፤ የፍትህ ጉድለት፤ የሙስናና የምቀኝነት መድረክ፤ የጥቅምና የሀሰተኝነት ዜማ የሚዜመው የት ነው? አዲስ አበባ ወይስ ፓትርያርኩ ጋር? ‹‹ማን ላይ ሆነሽ ማንን ታሚያለሽ….›› እንደተባለው በየሊቃነ ጳጳሳቱ ሀገረ ስብከት አይደል እንዴ? በድፍን ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አይደል እንዴ? የቤተክርስቲያናችን ችግር ፈጣሪው ማን ነው? እውነት ልብን የሚነካ ነገር ነው ተረጋግቶ ለተመለከተው ሰው፡፡ 360 ቀን ደሀን ሲበድሉት፤ ወገን አልባውን ሲያባሩት ፤ በዘረኝነት ሜዳቸው ጎጥ ሲያደራጁ፤ ሀግ ባይ በሌለው የአባታችን ቤት ገንዘብ ጮቤ እየረገጡ፤ ሙስናና ኢፍትሀዊነት ቤተክርቲያናችንን ሲወራት ደስተኛ ሚሆኑት፤ ሰላምና ፍቅር እውነትና አብሮነት ትክክለኛ ቤቷን ለቃ በዓለም ስትሰደድ ቁጭ ብለው የሚያዩት፤ በየሀገረ ስብከታቸው ያሉት ጳጳሳት አይደሉም? ልክ ባጣ ስህተት ህዝብ የሚበድሉ፤ ዛሬ ታዲያ ምነው በማን ጠጅና ጠላ ሰክረው ነው ቅዱስ ሲኖዲዎሱ የተረገጠው? ሲኖዲዎስም መድፈር እኮ ህገ ወጥነት ነው፡፡ ግን ማን ይቀጣቸዋል መኖሪያ ቤታቸው ነው፡፡ አይፈረድባቸውም የተሞሉትን ነው ሚዘረግፉት ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን ነው የሚተፉት ይህ ነው የማህበረ ቅዱሳን የ25 ዓመት ትሩፋት፤ አባቶችን በጉቦ መግዛት፤ በጠፊ እንጀራ ማንነትን ማሸጥ እውነትም ማህበረ ቅዱሳን ተሳክቶለታል፡፡
  ለምሳሌ እንውሰድ ቀለል አድርገን አንድ መቶ ሺህ ብር እንደምንም ለፍታችሁ ደክማችሁ አግባብታችሁ ከተወሰነ ጉዋደኞቻችሁ ጋር ሆናችሁ ለአንድ ጳጳስ ቡራኬ ለመቀበል ነው በላችሁ ብትሰጡት እረ እንደው አይገባም ብለው በአንድ አቡነ ዘበሰማያት ብትለያዩ፡፡ ለዚህ ጳጳስ እናንተ መልዓክ ናችሁ፡፡ ታዲያ ይህ ጳጳስ ምንስ ቢያደርግና ለማድረግ ቢሞክር ምስክር ይዛችሁ ስለምትከሱት በሰጣችሁት 100 ሺህ ብር ስለምታስፈራሩት ለምታዙትና ከምትነግሩት ነገር ውጭ ለማድረግ አይደፍርም ምክንያቱም እንድም ጳጳስነው መዋረድን አይፈልግም፡ የታዘዘውን እንቢ ቢል ስሙ ስለሚጠፋና ወንጀለኛ ስለሆነ ሀይማኖቷ ገደል ብትገባም ለብሩ አላማ መጋደሉ ግድ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ጳጳስ ለዚህ ሲኖዲዎስ ጥቅሙ ምንድነው?፡፡ የዚህን ያህል የተሰራ እቅድ ነው ማህበሩ የሰራው፡፡ በእንደዚህ ዓይነት በአፍኣዊ ነጭ ልብስ የየዋሃን ምእመናንን ዓይን የሚያማልሉ፤  ውሳጣዊ ሕይወታቸው/ተልኳቸው/ ዓላማቸው ግን ፍፁም ሥጋዊ/ ምድራዊ፣ ከፋፋይ፤ የመድኅን ክርስቶስ ስም የጉባኤያቸው መክፈቻና መዘጊያ እንጂ ውስጡ ባዶ፤ እንኳን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ወደ ሰማያዊቷ እንደራሴ ወደ ሆነች ምድራዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት ምእመናንን በአንድነት ሊያስገባ ይቅርና አንድነትን የሚንድ፣ በታኝ፣ ፈታኝ፣ ከሳሽ፣ ፈራጅ በመሆን ከቤተ ክርስቲያን ጉያ ልጆቿን እያስወጣ ለነጣቂው አውሬው የሚያስበላ፣ ለኑፋቄ ትምህርት በእጅጉ የሚያጋልጥ ኢክርስቲያናዊ ዓላማው ገሃድ ከሆነ እነሆ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ የዘለቀ የአፈራሽ ቡድን/ ስብስብ “ማኅበር” ነው።

  ReplyDelete
 23. የሁለት ጊዜ አንበሶች….
  እነዚህ ጳጳሳት አንድ ሰው ተርቦ እያለቀሰ ሆዱ ባዶውን እያደረ ያውም ያለጥፋቱ ተቀጥቶ፤ እነርሱ ግን ይህን እያወቁ ዝምታን የታጠቁት፤ በአማራጭ ምግብና መጠጥ ጠግበው በበሽታ የሚያድሩት ሲታመሙም ያሳመማቸውን መልሰው አክመኝ የሚሉት፤ እንጀራና የሰው ህይወት ግራ የተጋባባቸው፤ እነዚህ የትኞቹ ናቸው የየሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው፡፡ ዛሬ በሲኖዲዎስ ስብሰባ ብጥብጥ ያማራቸው፡፡ እውነት ነው ይህን ሁሉ ለመሸፈን እንዲህ መሆን ላያስጠላ ይችላል ነገር ግን ቀሚስ ገልጦ ለሚመለከት አምላክ የእውነት እፍረት ነው፡፡ በሁሉም ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን ብቻ አምላክህ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።” በማለት ነው የሙሴ ተከታይ የነበሩት የመለሱት (ኢያ. 1÷16-17)፡፡ ታዲያ የተሳሳተው ማነው?
  በቀድሞው ፓትርያርክ ዘመን ትንሽም ቦታ ስለነበራቸው ይህ ብጥብጥ አላሰቡበትም፡ አሁን ግን አላስፈላጊነታቸው እንደታመነበት ስላወቁ ፓትርያርኩንና ጳጳሳቱን ከፈሉ በጎራም አስቀምጠው እንዲባሉ ፈለጉ ልክ በአሜሪካውና በዚህ መካከል እንዳረጉት አስትራቴጂ……..የማኅበረ ቅዱሳን ስውር አመራር ስደተኛውን ሲኖዶስ ለፖለቲካ መሸሸጊያነት እንጂ ለሌላ እንደማይፈልገው ይታወቃል። በውጪ ያሉ አባቶች በአገር ውስጥ ካሉት አባቶች ጋር ታርቀው ቤተክርስቲያን አንድ እንድትሆንም ማኅበሩ አይፈልግም። የእነርሱ መታረቅና አንድ መሆን ለማኅበሩ ህልውና አስጊ ነውና። ምክንያቱም በውጪ ያለችው ቤተክርስቲያን ብዙዎቹ አገልጋዮች ማኅበሩ ከአገር ውስጥ «መናፍቅ» «ተሀድሶ» ወዘተ እያለ አለስማቸው ስም እየሰጠ በህገወጥ መንገድና በሌለው ስልጣን በጉልበት ያሳደዳቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ስለሆኑ፣ ሁለቱ ወገኖች ከታረቁ ኪሳራው ለማኅበሩ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ሁለቱ ወገኖች እንዳይታረቁ ጠንክሮ ይሰራል። በአገር ውስጥ የውጪውን፣ በውጪ ደግሞ የአገር ቤቱን ሲኖዶስ ሲነቅፍ የኖረውም ለዚሁ ነው። ይህ አካሄዱ ሁለቱም እንደተጣሉ ሳይታረቁ እንዲኖሩና ከሁለቱም ጋር ተስማምቶ ለመኖር የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ተብሎ እንደተጻፈው። 
  ታዲያ ጳጳሳቱ እንዲህ የሚሆነው የቤተክርስቲያንን ችግር ለመነጋገር ጊዜ አጥቶ ነው? አይደለም በተናጥል ቢሆን ኖሮ ሁለም ፈሪሳዊ፡ ኢአማኝ ብኩን ነው፡፡ ግን ዛሬ ተግባራቸው አንድ የሆኑቱ ለቤተክርስቲን ያዘኑ በመምሰል ጩኸቱ ምንድን ነው?፡፡ በየዓመቱ የሁለት ጊዜ አንበሶች ጀግኖች ነን ባዮች 363 ቀን ግን በግፍ፤ በበደልና በኢፍትሀዊነት፤ በአይገቤ ሃይማኖታዊ ጥቅም የኖሩት፤ እነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት የነሱ ችግርና ግፍ እንዳይነገር ይሆን በከበረው ስብሰባ እንደደህጻን የሆኑት?፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ችግርስ ፓትርያርኩ ጋርና አዲስ አበባ ብቻ ነው ያለው፡፡ መላው ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ያለው ችግር ይህ ብቻ ነው?፡፡ አንበሶቹ ሊቃነ ጳጳሳት ለምን እንዲህ ሆኑ ብዬ ሳስብ አንድም ድብቅ ገመናቸውን ለመሸፈን እና ጣልቃ አይገባበትም ስለሚሉት ሀገረ ስብከታቸው ምንም አይነት ጉዳይ እንዳይነሳ እነርሱ ለቤተክርስቲን ተቆርቋሪ እንደራሴዎች እና እራሳቸውን ባለመፍትሔ አድርገው ለማሳየት ከመፈለግ የመነጨ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ባለው ልክ ነውና ለሌላው የሚተርፈው። ባዶ በርሜል/ገረወይና ትንሽ ቢነኩት ጩኸቱ መከራ ነው፤ ቢሞላ ግን ድምጽ አልባ ነው።  ቢማር/ቢያውቅ ኖሮ የዐዋቂዎች/ የምሁራን/ የሊቃውንት ጥቅማቸው ይገባውና ይቆረቆርላቸው ነበር።  ወርቅን ለሚያውቀው ነው ወርቅነቱ፤ ለማያውቀው ግን ተራ ብረት ነውና።
  እንደአጠቃላይ በጣም የሚያሳዝነው የቤተክርስቲያን የበርካታ ወራት ችግር የሆነ አካል የሁለት ቀን መፍትሔ ፈጣሪ፡ አማራጭ አምጪ ፤ ቁም ነገር ሰሪ ለመሆን መሞከር የሚያስተችና የሚያሳፍር ብሎም በላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የነውረኝነት ተግባር እንዲማር የሚያደርግ ጉዳይ ነው፡፡ ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት በየተመደቡበት ሀገረ ስብከት ያበረከቱት አስተዋጽኦና መልካም ተግባር ምንድን ነው? የስራ አፈጻጸማቸው እንዴት ነው? የገንዘብ አስተዳደራቸው ውጤቱ ምን ያህል ነው? ምዕመናንን ለማርካት ያረጉት ምንድ ነው? ቤተክርስቲያንን ያስደሰታት ማን ነው? ሰው ጎዳን ብለው እምነታችንን በአደባባይ የሚሸጡ፤ ስሟን ለአዝማሪ በመስጠት እነርሱ የሚዝናኑ፤ ከንቱ ተግባራትን ተንተርሰው እኛ እውነተኛ ነን የሚሉ ስራ ከመስራት ይልቅ ድፍን አመቱን አልጋ አሙቀው እየመጡ ዛሬ የቤተክርስቲያን ጉዳይ በሲኖዲዎስ ለማየት ትክክለኛና ቀጥተኛ የመሰሉት እነዚህ ጳጳሳት፡፡ ወገኖቼ ይህ አይነት ተግባር መሰለኝ ምንፍቅና ብሎም ከእናት ቤተክርስቲያን እያስጎረሰ ለማህበረ ቅዱሳን የሚያስውጥ ገመና፡፡ ከዚህ ቀደም ጋዜጣው ማኅበረ ቅዱሳንን ተቃውሞ በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ እንደ ተገለጸው፣ ከቤተ ክርስቲያን ጎርሶ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን መዋጥ ተጀምሮ ይሆን ወይ? (ዜና ቤተክርስቲያን 1996፣ 7)፡፡” (ገጽ 35) እንደተባለው አመቱን ሙሉ ደንታ ሳይሰጣቸው እያወቁ እየሰሙ በዝምታ በራቸውን የሚዘጉት ስፍር ቁጥር ያለፈውን ገመናቸውን ሲያስቡ ስራውን የረሱት፤ ዛሬ ምን ለመሆን ነው ለቤተክርስቲያን መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ በነገር ሚባሉት፡፡ ቀን አይውጣልሽ የተባለች ይመስል ዛሬ ቤተክርስቲያን በዚህ ትውልድ ማፈሪያ ትሁን፡፡ እንግዲህስ የሚታመን ማነው? ተቆርቋሪ እውነታን ተከትሎ ለትውልድ ነዋሪ፡፡

  ReplyDelete