Wednesday, May 25, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ኦርቶዶክሳዊነትን ዝቅ ያደረገ ማኅበርማኅበረ ቅዱሳን “ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል ርእስ ያዘጋጀው 5ኛ ዐውደ ርእይ ትልቅ ርእስ የተሰጠው ቢሆንም፣ ማኅበሩ ኦርቶዶክሳዊነትን እርሱ ጠንቅቆ ሌላውም እንዲጠነቅቅ የሚያደርግ ብቃት አለው ወይ የሚለው ግን አጠራጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ኦርቶዶክስ የሚለውን ስመ ሃይማኖት እርሱ ተጠራበት እንጂ ራሱ ጠንቅቆ እንዳላወቀውና ለሌላውም የማሳወቅ ብቃት እንደሌለው ከዐውደ ርእዩ ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠና ኦርቶዶክስን ኦርቶዶክስ ካሰኘበት መሠረታዊ ነገር እየራቀ ከመጣ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይበልጥ የዘቀጠውና ከስሙ በቀር አስተምህሮው በሌላ አስተምህሮ ተተክቶ የሚገኘው ግን ማኅበረ ቅዱሳን በተነሣበትና ቀጥሎ ባበት በዚህ ዘመን ነው ቢባል ትክክል እንጂ ስሕተት አይሆንም፡፡ ለምሳሌ በዛሬው ዕለት የሚቀርበው አንዱ መርሐ ግብር “ንባብ፣ ቅዳሴ እና ሰዓታት” በሚል ርእስ የንባብ ይዘት የቅዳሴ ምንነት ይዘትና አገልግሎትና ሥርዓቱ ንባቡንና ቅዳሴ አቀራረቡን በመድረክ በአብነት ተማሪዎች ማቅረብ እንደሆነ የወጣው መርሐ ግብር ያስረዳል፡፡ እውን ይህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን “አስተምህሮ” ተብሎ የሚቀርብ ጉዳይ ነወይ? ማኅበረ ቅዱሳን ኦርቶዶክሳዊነትን ዝቅ ያደረገ ማኅበር ነው ለማለት የደፈርኩትም ከዚህ በመነሣት ነው፡፡
  ኦርቶዶክስ ርቱዕ ሃይማኖት (የቀናች ሃይማኖት) ማለት ሲሆን በኒቅያ ጉባኤ ውሳኔ ላይ ተመሥርቶ የወጣ ስመ ሃይማኖት ነው፡፡ ይኸውም “ወልድ ፍጡር” ያለውን የአርዮስን ክሕደት መርምሮና እሱን ረትቶ ወልድ ፍጡር ሳይሆን ፈጣሪ መሆኑን በማስረዳት ለወሰነው ውሳኔ የተሰጠው ስም ነው፡፡ ተዋሕዶም በኤፌሶን ጉባኤ የንስጥሮስን ኑፋቄ በእግዚአብሔር ቃል መርምረውና ስሕተትነቱን በማወጅ አንዱ ጌታችን ኢየሱ ክርስቶስ መቀላቀልና መለያየት በሌለበት ተዋሕዶ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነበት ምስጢር መሆኑን ለመግለጥ የተጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ ስለዚህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ብሎ ማመንና በክርስቶስ ፍጹም አምላክነትና ፍጹም ሰውነት በአዳኝነቱም ማመን ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ሲል ግን ከዚህ መሠረተ እምነት በእጅጉ የራቁና እንደ አስተምህሮ የማይቆጠሩ ጉዳዮችን “አስተምህሮ” በማለት ሰይሞ ኦርቶዶክሳዊነትን ዝቅ ያደረገ ማኅበር ሆኖ ይገኛል፡፡
በሁለቱ ዓለም ዐቀፍ ጉባኤዎች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስያሜ ሊሰጥ የቻለው በክርስቶስ ማንነት ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ ስለዚህ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለው ስያሜ ከክርስቶስ ተለይቶ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ያለ ክርስቶስ ከሆነ ግን ስሙ ትርጉም አልባ ይሆናል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ውስጥ የክርስቶስ አምላክነትና ጌትነት፣ ክርስቶስ ብቻ አዳኝ መሆኑ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን የተቋቋመው ስላንቀላፉ ቅዱሳን እና ስለትውፊት እንጂ ስለ ክርስቶስ አይደለምና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለውን ስም ሳይገባው የሚጠራበት ስም ሆኗል፡፡ ስለዚህ ዛሬ በኦርቶዶክስ ስም ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ የማይመጥን ጉዳይ ላይ ብዙ ነገር እያባከነ ይገኛል፡፡   
እስቲ አንዳንድ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ላቅርብ፣ “ንባብ፣ ቅዳሴ እና ሰዓታት” በሚል ርእስ የንባብ ይዘት የቅዳሴ ምንነት ይዘት፣ አገልግሎትና ሥርዓቱ ንባቡና ቅዳሴ አቀራረቡ በመጀመሪያ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ነወይ? ሁለተኛ አሁን ያለው አንገብጋቢ ጉዳይ ይህ ነወይ? በተለይም ሕዝቡ በስፋት እየፈለሰ ያለው ማኅበሩ ርእሰ ጉዳይ አድርጎ የያዘውን “ንባብ ቅዳሴና ሰዓታት” ስላላወቀ ነወይ? ይህን ማሳወቅ ከተቻለ የሕዝብን ፍልሰት ማቆም ይቻላል ወይ? እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉት ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ይዞት የተነሣውን ይህ ርእሰ ጉዳይና ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ግን የሚገናኙ አይመስለኝም፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ርእስ የመረጠው የተሐድሶን እንቅስቀሴ ለመግታት በሚል ነው፡፡ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ግን ለቤተ ክርስቲያኑ ግድ የሚለው ጌታ ቤተ ክርስያኑን ከስሕተት አሠራር ለመጠበቅና ከወደቀችበት ለማንሣት የጀመረው እንቅስቃሴ በመሆኑ ማንም የሚገታው አይደለም፡፡ እንቅስቃሴውን ለመግታት መሞከር ከጌታ ጋር መጣላት ነው፡፡ ከጌታ ጋር የሚጣሉ ደግሞ ተጎጂዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሰዎች ከምንም በላይ ከክንደ ብርቱው ጌታ ጋር ሲጣሉ እንዳይገኙ መጠንቀቅ አለባቸው፡፡
ማቅ ይዟቸው የተነሣው ርእሶች በጣም የተለመዱና ሰዉ ኤግዚቢሽን ማእከል መሄድ ሳያስፈልገው ዘወትር ቤተክርስቲያን ተገኝቶም ሆነ ቤተክርስቲያን መሄድ ሳያስፈልገው በድምፅ ማጉሊያ ያለበት ድረስ የሚመጣለት እርሱ የሚከውነውና ሲከወን የሚታደመው ክዋኔ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ማኅበረ ቅዱሳን ይህን በማቅረቡ ኦርቶዶክስን እንዲጠነቅቁ አድርጌያለሁ ቢል ራሱን ነው ያታለለው፡፡ ጊዜውንም አባክኗል፡፡ የሌሎችንም ጊዜና ገንዘብ እንዳባከነ ነው የሚሰማኝ፡፡
በቅርቡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ችግር በማስመልከት የሕዝቡን ፍልሰት ለመግታት መደረግ ያለበት ምን እንደሆነ የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች የሰጡት የመፍትሔ ሐሳብ ሊጤን የሚገባው ይመስለኛል፡፡ በቅርቡ በፓትርያኩ በዓለ ሲመት ላይ በተሠራጨው መጽሔት ላይ የቀረበውንና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የተናገሩትን በዚሁ ብሎግ ላይ ማርች 9, 2016 ወጥቶ የነበረውን መልእክት ማጤን ያስፈልጋል፡፡ እጠቅሳለሁ “ምናልባት በሰሜኑ ሀገራችን ትንሽ ልንቆይ እንችል ይሆናል፡፡ አሁን ከዚህ በፊት ምንም በማናይባቸው አካባቢ ትልልቅ አዳራሾች እየታዩ ነው፡፡ ይህም በምሥራቁ በደቡብ በምእራቡ በእጅጉ እየሮጡ ሳይሆን እየተበረሩ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ ይሄንንም ትንሽ ለማቆየት የአህጉረ ስብከትና የወረዳ ሊቃነ ካህናትን አድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎችን የሰበካ ጉባኤ ኣባላትን በማሰባሰብ ስለ ችግሩ አሳሳቢነት መመካከር ያስፈልጋል፡፡ ሕዝባችን ጠንካራ ነበር፤ ሥራ ሲሉት ይሠራል ስጥ ሲሉት ይሰጣል፡፡ ትልቁ ችግር ግን ጠላት ሲመጣ የሚመልስበት ትጥቅ ሳይዝ አገኙት፤ በምን ይከላከላል ከዚህ በፊት ማህሌት ይቆምለታል ቅዳሴ ይቀደስለታል እሰየው በቃ ክርስቲያን ነው፡፡ ግን ስለ እምነቱና ስለ ማንነቱ አልተማረም፡፡ በዚህ መሠረት የተዘጋጀና አውላላ ሜዳ ላይ የተገኘ ምርጥ ሆነላቸው፡፡ ማርከው ከበረታቸው አስገቡት፤ ሆኖም መፍትሄው መንቃት ብቻ ነው፡፡ … ከመላው ዓለም አስቀድማ በአምልኮተ እግዚአብሔር ያፀናችው ጥንታዊትዋ፤ ታሪካዊትዋና ብሔራዊትዋ ብሎም ዓለም አቀፋዊትዋ ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ጊዜ ትጥቋ ላልቶ ባእዳን ሊያስታጥቋት ሲዳዳቸው ይስተዋላል፡፡ … በአሁኑ ጊዜ የተሾምነው በቁጥር የበዛን ስንሆን ትጥቃችን በመላላቱ በቁጥር ያነሱት ያለፉት አባቶቻችን ህልውናውን ጠብቀው መብትዋን ሳያስደፍሩ ያስረከቡንን ቤተ ክርስቲያን እኛ ብናስደፍራት ባለውም በሚመጣውም ትውልድ ዘንድ የታሪክ ተወቃሾች እንዳንሆን የላላውን ትጥቃችንን አጥብቀን ልንነሣ ይገባናል፡፡”
በትክክል ሕዝቡን መያዝ የምንችለው አሁን ማቅ በኤግዚቢሽን መልክ የንባብን የቅዳሴንና የሰዓታትን ክዋኔ ስላቀረበ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ይልቅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ይህን ስያሜ ያገኘችበትን ክርስቶስን በቅዱሳንና በትውፊት ከመሸፈን ይልቅ ሁሉ እንዲያውቀው የክርስቶስ አዳኝነት ብቻ የሚነገርበት ወንጌል በግልጥነት መስበክ አለበት፡፡ ሕዝቡ ያላወቀው ክርስቶስን እንጂ ቅዳሴን ሰዓታትን ንባብን አይመስለኝም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም በሥጋ ስላላዩት ሁሉ እንዴት ያለ ትልቅ መጋደል እንዳለኝ ልታውቁ እወዳለሁና። ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ። የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና። (ቆላ. 2፥1-3)፡፡
ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ አካሄዱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር ከማባባስ በቀር መፍትሔ ይዞ አልቀረበም፡፡ ዐውደ ርእዩም ለማኅበሩ የገቢ ምንጭ ከመሆን ያለፈ ትርፍ ለቤተክርስቲያኒቱ አያስገኝላትም፡፡ ቤተክርስቲያን ሕዝቡን ከፍልሰት መግታት የምትችለው የተመሠረተችበትን ዋና ዐላማ ክርስቶስን በመስበክ ክርስቶስ እርሷም ዘንድ መኖሩን በተግባር በማሳየት ነው፡፡ ክርስቶስን ፈልጎ ወደሌላ እየፈለሰ ያለውን ወገን “መናፍቅ ተሐድሶ” እያሉ ማውገዙን ትቶ የሚፈልገውን ክርስቶስን መስጠት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡      

31 comments:

 1. አንድ ጥያቈ ብቻ ልጠይቃችሁ ቅዳሴ ማለት ሙሉበ ሙሉ ሰለጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እንዴት ሳታውቁ ቀራችሁ?አሃ_____
  መልሱ ወደ አዳራሽ እንጂ ወደ ቤተ ክርስትያን ስለማትሄዱ________በቃ ኤግዝቢሽን ሂዱና ተማሩ መቼም አዳራሽ ይመቻችሗል____

  ReplyDelete
 2. ዐውደ ርእዩም ለማኅበሩ የገቢ ምንጭ ከመሆን ያለፈ ትርፍ ለቤተክርስቲያኒቱ አያስገኝላትም፡፡ ቤተክርስቲያን ሕዝቡን ከፍልሰት መግታት የምትችለው የተመሠረተችበትን ዋና ዐላማ ክርስቶስን በመስበክ ክርስቶስ እርሷም ዘንድ መኖሩን በተግባር በማሳየት ነው፡፡ ክርስቶስን ፈልጎ ወደሌላ እየፈለሰ ያለውን ወገን “መናፍቅ ተሐድሶ” እያሉ ማውገዙን ትቶ የሚፈልገውን ክርስቶስን መስጠት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡

  ReplyDelete
 3. “ምናልባት በሰሜኑ ሀገራችን ትንሽ ልንቆይ እንችል ይሆናል፡፡ አሁን ከዚህ በፊት ምንም በማናይባቸው አካባቢ ትልልቅ አዳራሾች እየታዩ ነው፡፡ ይህም በምሥራቁ በደቡብ በምእራቡ በእጅጉ እየሮጡ ሳይሆን እየተበረሩ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ ይሄንንም ትንሽ ለማቆየት የአህጉረ ስብከትና የወረዳ ሊቃነ ካህናትን አድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎችን የሰበካ ጉባኤ ኣባላትን በማሰባሰብ ስለ ችግሩ አሳሳቢነት መመካከር ያስፈልጋል፡፡ ሕዝባችን ጠንካራ ነበር፤ ሥራ ሲሉት ይሠራል ስጥ ሲሉት ይሰጣል፡፡ ትልቁ ችግር ግን ጠላት ሲመጣ የሚመልስበት ትጥቅ ሳይዝ አገኙት፤ በምን ይከላከላል ከዚህ በፊት ማህሌት ይቆምለታል ቅዳሴ ይቀደስለታል እሰየው በቃ ክርስቲያን ነው፡፡ ግን ስለ እምነቱና ስለ ማንነቱ አልተማረም፡፡ በዚህ መሠረት የተዘጋጀና አውላላ ሜዳ ላይ የተገኘ ምርጥ ሆነላቸው፡፡ ማርከው ከበረታቸው አስገቡት፤ ሆኖም መፍትሄው መንቃት ብቻ ነው፡፡ … ከመላው ዓለም አስቀድማ በአምልኮተ እግዚአብሔር ያፀናችው ጥንታዊትዋ፤ ታሪካዊትዋና ብሔራዊትዋ ብሎም ዓለም አቀፋዊትዋ ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ጊዜ ትጥቋ ላልቶ ባእዳን ሊያስታጥቋት ሲዳዳቸው ይስተዋላል፡፡ … በአሁኑ ጊዜ የተሾምነው በቁጥር የበዛን ስንሆን ትጥቃችን በመላላቱ በቁጥር ያነሱት ያለፉት አባቶቻችን ህልውናውን ጠብቀው መብትዋን ሳያስደፍሩ ያስረከቡንን ቤተ ክርስቲያን እኛ ብናስደፍራት ባለውም በሚመጣውም ትውልድ ዘንድ የታሪክ ተወቃሾች እንዳንሆን የላላውን ትጥቃችንን አጥብቀን ልንነሣ ይገባናል፡፡”

  ReplyDelete
 4. ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ርእስ ነጠላዜማ የሆነውን የመረጠው የተሐድሶን እንቅስቀሴ ለመግታት በሚል ነው ግን ባዶ ጩኸት ምን አለበት ወንጌሉን ቢከፈት ስርአትዋን እንኩአን ኦርቶዶክሱ ሙስሊሙም ያውቃል ወንጌሉ የከፈት ይነገር የምስራቹ
  ፡፡

  ReplyDelete
 5. ቅዳሴው፣ንባቡና ሰዓታቱ ስለማታውቀው ነው እንጅ ወንጌል ነው ያውም የፀሎት፣የምስጋና....ነው፡፡ግን ምን ያደርጋል ለማወቅ ሣይሆን ለመወንጀል የተፈጠረ አእሞሮ ነውና።

  ReplyDelete
 6. የዘመኑ ሰባክያን በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት
  ዝነኛነትን ለመመሥረት በተራው አእምሮ ጭንቀት ለመዝራት በመድረክ ሆነው የስድብ ናዳ ያወርዳሉ
  ይህም ብልሀት ከማጣት ዕውቀት ካለማግኘት
  የተነሳ ነው የምን ቄስ ቅዳሴ ቢጎልበት ሽለላ ሞላበት
  ስድባቸውም መናፍቅ ተሐድሶ ነው የራስዋን አበሳ በሰው አብሳ እምተረፈ ልብ ይነብብ አፍ
  ራሳቸው መናፍቃን በመሆናቸው ባደባባይ ያስቀባጥራቸዋል አይጣል ነው

  ReplyDelete
 7. የዘመኑ ሰባክያን በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት
  ዝነኛነትን ለመመሥረት በተራው አእምሮ ጭንቀት ለመዝራት በመድረክ ሆነው የስድብ ናዳ ያወርዳሉ
  ይህም ብልሀት ከማጣት ዕውቀት ካለማግኘት
  የተነሳ ነው የምን ቄስ ቅዳሴ ቢጎልበት ሽለላ ሞላበት
  ስድባቸውም መናፍቅ ተሐድሶ ነው የራስዋን አበሳ በሰው አብሳ እምተረፈ ልብ ይነብብ አፍ
  ራሳቸው መናፍቃን በመሆናቸው ባደባባይ ያስቀባጥራቸዋል አይጣል ነው

  ReplyDelete
 8. “ንባብ፣ ቅዳሴ እና ሰዓታት” ዉስጥ ምን እንዳለ ስላላወቅህ ማፈር ሲገባህ አለማወቅህን በድፍረት ስላቀረብክ ላንተ እኔ አፈርኩ!

  ReplyDelete
 9. በመጀመሪያ ደረጃ ማህበሩ የወንጌል ጠላት መሆኑን በተግባር ያስመሰከረ ነዉ፡፡
  ወንጌል ሰባኪዎችን የሚያሳድድና እንደነ ዘመድኩን በቀለ አይነት መንደርተኞችን
  ከሚያቅፍ ማህበር የተሻለ ነገር መጠበቅ ሞኝነት ነዉ፡፡

  ማቅ እዉነተኛዉ የክርስቶስ ወንጌል ሲሰበክ ይነስረዋል፡፡ ስለገዳማት፣ ሰማዕታት
  ወዘተ ግን 24 ሰዓት ቢወራ አይጎረብጠዉም፡፡ ታዲያ ይህ ጸረ ወንጌል ማህበር
  ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ከሌለዉ በስተቀር ምኑ ነዉ ቤተ ክርስቲያንን እንዲወክል
  የሚያደርገዉ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማነው የላከህ?እነ ፓስተር?ሲያምርህ ይቅር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ለኑፋቄ ቦታ የላትም እንዲሁ እንደ ተቃጠላችሁ ትኖራላችሁ ምድረ ግሪሳ ሁላ።

   Delete
  2. እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ!! ድከም ብሎህ እንጂ እውርና ደንቆሮ ለሆነ የማቅ ጀሌ በሜጋፎን ብታጮህበት አይሰማህም እንኳን በጽሁፍ። ኢየሱስ ክርስቶስን የማያምን ማህበር እንዴት አድርጎ ነው ክርስቲያን የሆነው? ክርስቶስ የሌለው ሳጥናኤል አለው። የቅዱሳን ማህበር? ቅዱስ እግዚአብሔር ብቻ ነው!! ስጋ ከለበሰ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ሌላ የለም። ሳጥናኤል እራሱ በትምክህት ታብዮ አምላክ ነኝ፤ ቅዱስ ነኝ ብሎ ነው እግዚአብሔር አሽቀንጥሮ የወረወረው በምድር ማቅን ወልዶ ይኸው መከራቸውን ያያሉ። ትምክህታቸው፤ ውሸታቸው፤ የአፍ፤ የአይን ፤ የእጅ ሌቦች፤ የነጠላ አስመሳይ ክርስቲያኖች፤ ከአፋቸው አንዲት መልካም ነገር አትወጣ፤ ከምን ጉድጓድ እንደአንብጣ እንደፈሉ የማይታወቅ፤ የንጹሃን ሰማእታት አባቶች የእርግማን ውጤት ሲሆኑ ከዲያብሎስ ለመሆናቸው በስራቸው ያስመሰከሩት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲጠራ የሚንቀዠቀዡ የሚያጓሩ የሚጮሁ የሚሳደቡ የሚደባደቡ የሚገሉ፤ ይኸ በቀጥታ ከአብታቸው ከድያብሎስ የወረሱት ስለሆነ እንደመዥገር ተጣብቀው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ደም እየመጠጡ ስለሆነ የመዥገር መድሃኒት ፈልጎ ከቤተክርስቲያን ማስወገድ ያስፈልጋል እስከዛሬ ያደረሱት ጥፋት የዘረፉት ገንዘብ ንብረት ይበቃቸዋል። እስከምጽአት ቀን እርሱን ይብሉ።

   Delete
  3. To AnonymousMay 26, 2016 at 12:47 PM
   ማቅ ጸረ ወንጌል አይደለም ካልክ ሂድና ያዘጋጀዉን አዉደ ርዕይ ተመልከት፡፡ የማፍያ ቡድኑ የሰበሰበዉ ዘባተሎ ትዕይንት ሰዉን ወደንስሐ የሚጠራ ነገር የለዉም፡፡ስለታሪክ፣ ቀለም፣ ባንዲራ እንጅ ስለወንጌል ግድ የማይለዉ በቅዱሳን ስም የሚነግድ ነጋዴ ማህበር ነዉ፡፡

   Delete
 10. የናንተን ወሬ የምንሰማበት ጀሮ የለንም፡፡ ተሐድሶ መናፍቅ አንፈልጋችሁም፡፡

  ReplyDelete
 11. ሃሃሃሃሃ አቤት ድፍረት! አንተ ነሃ ኦርቶዶክስን ከፍ ያደረከው¡ ሃሃሃ ደፋር የጴንጤ ተላላኪ።

  ReplyDelete
 12. tehadiso atilefilif yemisemah yelem

  ReplyDelete
 13. ዳዊት አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ ብሎ እንደፀለየው እግዚአብሔር ንፁህን ልብ ካልሰጠን ሰው በራሱ ንፁህ ልብ ሊኖረው አይችልም በዚህ ግብዝ አለም ላይ እግዚአብሔር ንፁህ ልብ የሰጠው ሰው እውነተኛውን መንገድ የሚከተል ሰው ተቀባይነት አያገኝም ምክንያቱም ይሄ ዓለም እግዚአብሔርንም እውነትንም ስለማይወድ ክፉ ሰዎች ጥሩ እየተባሉ ተከብረው ጥሩ ሰዎች የእውነትን መንገድ የሚከተሉ መጥፎ ተብለው ይኖራሉ በአመዣኙ ጥሩ የሚባል ሥም ያገኙ ሰዎች ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰዎችን ስለሚፈሩ ሰው ፊት ጥሩ ለመምሰል ይሞክራሉ እውነታው ግን ተንኮለኞችና ግብዞች ከህሊናቸው የተጣሉ ናቸው ውስጣቸው የሌለውን ጥሩነት ለማሳየት ይጥራሉ ንፁህ እግዚአብሔር ብቻ ነው ።

  ReplyDelete
 14. Replies
  1. You call him foolish, it is because he underscored how the world we live is deceitful, mischievous and impudently brutal, this is a reality which had been addressed by our Lord Jesus Christ; what he attempted to reiterate here was a simple obvious truth, and any one outside of the christian religion could agree totally about it, because his/her soul will never let him/her deny that, goodness gracious, why are you filled with evil thoughts;listen.............., whether you and people of your sort like it or not, the name Jesus Christ will prevail all over Ethiopia, and you will see when the Ethiopian TEWAHIDO denomination revert to where it was before the mid thirteen century immaculate as it was, and by that retrieving the overshadowed Name Jesus Christ so as worshipers rumble, grumble and speak out instead of the current situation, which in fact quite a few courageous Ethiopians are adamantly working hard on it and also what you have to swallow as a mere occurrence is that
   The time to converge over the father, the son and the holly spirit is approaching, it is visible we have so courageous theologians, singers, priests, bishops who are determine to raise this name Jesus Christ above anything, and we shall see when those of you who wanted to stick with the names of human beings and consider them as your saviors, intermediaries and who have given you salivation.

   Delete
 15. ወንጌል አልተሰበከም የምትሉት እንደናንተ ጻድቃ፤ ሰማዕታት ቅዱሳን መላዕክት አያስፈልጉም ክብር ምስጋና ይግባውና ክርስቶስን አማላጅ ያልተባለ ነው ኸረ ልብ ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 16. ውሻ በበላበት ይጮሃልና ከማን ወገን እንደሆናችሁ ይታወቃል፤ ግን አምላክ ልቦና ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 17. min yahikil bekirstos sim kihdet yeyazachihu mehonu ahun bedenb geletachihut!!!!!!!!!!!!!!!ahhhhhhaaaaaa
  kidasie. mahilet anan seatat be Orthodox tewahodo betekirstiyan yale kirstos yelemna. enante yemitilut hasetegnawu'kirstos' gin endenegerachihun tehadisona menafik saybalu "kirstos.... kirstos... geta geta" lemilut newua!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 18. እንዴ ቆይ ቆይ ቆይ ለመሆኑ አባ ስላማዎች ሲጀመር ራሳችሁን ኦርቶዶክስ አድርጋችሁ እንድትቀርቡ ማን ፈቀደላችሁ
  ሲቀጥል ይህን ርእስ የኦርቶዶክሳዊ ተቆርቋሪ አድራጋችሁ እንዲህ ኦርቶዶክስን ዝቅ የሚያደረግ ጽሁፍ የምትጽፉት ሰክራችሁ ወይም ቅማችሁ መሆን አለበት
  ስለዚህ ስለ ማህበረ ቅዱሳን የምትጽፉትን በሙሉ ገልብጠን እንደምናነበው አሁንም አልተረዳችሁም እንዴ
  ማህበረ ቅዱሳኖች ስለእናንተ በጎ እየጻፉ ያሉት አባ ሰላማዎች ይቀጥሉ አይደል ምክንያቱም እኛ ገልብጠን ነዋ የምናነበው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ገልብጠን ኪኪኪ ስለኣጫት አወራህ መቼም የሚቅም ነው ምናልባት ገልብጦ ሚያነበው

   Delete
 19. ለተሃድሶ መናፍቃን መድረካችን ዝግ ነው!!!

  ReplyDelete
 20. አይ ማቅ ኢየሱስ ይሰበካል ካሉ ለምን ኢየሱስ የሚለውን ስም ጠሉት ሰው በሚገባው ቆንቆ ቢሰበክ ክፋቱ ምን ይሆን? በዛኑ መጠን ገደል ለገደል እያዞሩ ብር መሰብሰብን ቤተክርስትያን እንዲ ሆነ ብር ይቀራላ ተነቅቶበታል ይሄ መቅቅቅ ያለ ብድን

  ReplyDelete
 21. በጣም ይገርማል አምልኮት ለአንድ አምላክ ብቻ መሆን ስገባው ለእመቤታችንና ለቅዱሳኑ ሁሉ የአምልኮት እየቀረበ ባለበት ዘመን ላይ ነን ያለነው። ውዳሴ አምልኮት ስግድት አንዱ አምላካችን ለኢየሱስ መሆን ስገባው በቅድስት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያናችን ግን ለእመቤታችንና ለክቡር መስቀሉ እያቀረብን ነን። ሁሉም እንደ አምላክ ተቆጥረው ይመለካሉ ይወደሳሉ። መቼ ይሆን እውነተኛውን ወንጌል የሚለውን በህይወታችን የምንገልጸው። ሁለ ዝማረውን ከእግዚአብሔር ይልቅ ለእመቤታችንና ለቅዱሳኑ ብቻ ነው በእግዚአብሔር ቤት የምዘመረው። በቅዱሳኑ እኮ አድሮ ስራ የሚሰራው አንዱ ሁሉን የፈጠረ አምላክ ብቻ ነው። ኤረ ወደ ህያው ቅዱስ ቃሉ ተበመልሰል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ያለደባል እናምልከው። እዉነቱን እንቀበለው። ለሎች ቅዱሳን እደየደረጃቸው ክብር ልንሰጥ ይገባል እጅ ከአምላክ ጋር እኩል አንዳንደም እያስበለጥር እያቀረብነው ያለው ውዳሴ የከርስትያናዊና አገልግሎት አይደለም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ምርጥ ዱዝ ነህ!!!!

   Delete
 22. ማህበረ ሰላማ ኦርቶዶክሳዊነትን ከፍ ያደረገ ማህበርiiiiiiiii

  ReplyDelete
 23. tehadiso tewarede!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 24. Sorry for your view regarding Kidase

  ReplyDelete