Thursday, May 26, 2016

እየተካሄደ ባለው የሲኖዶስ ስብሰባ የፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል

Read in PDF 
ቅዱስነታቸው ከአንድ መሪ የሚጠበቅና ብስለት ያለው ንግግር ያሰሙበት የግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በቀረጻቸው አጀንዳዎች መወያየቱን ቀጥሏል፡፡ ቅዱስነታቸው እንደ ከዚህ በፊቱ በተገኙባቸው መድረኮች ደጋግመው ሲገልጹት እንደነበረው አሁንም ወደ ውስጣችን መመልከት አለብን እያሉ ነው፡፡ ገደብ ለሌለው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንነሣ በማለት የቤተ ክርስቲያኒቱ የአሁንና የወደፊት እርምጃ የተስተካከለ እንዲሆን የቃለ እግዚአብሔር ትጥቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ንግግራቸው ፓትርያርኩ የውስጥ ተጽዕኖው እንደ ተጠበቀ ሆኖ የውጪው ጫና ማለትም ሴኪዩራሊዝም ግሎባላይዜሽን አክራሪነት እጅግ የወረደ ሥነምግባር በምድር ላይ ያለችውን ቤተክርስቲያን እየተጫናት፣ ተፅእኖ እያመጣባት ይገኛል ብለዋል፡፡
የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት እውነት ነው ዛሬ ባህር ላይ እንደወደቀ ኩበት ቤተክርስቲያን ወዲያ ወዲህ እያለች፣ ሞገስዋ ቀንሶ፣ ልእልናዋ ቀጭጮ፣ “የአባትህ ቤት ሲወረር አብረህ ውረር” በሚል ልማድ የሚመራ የሚመስለው የቤተክርስቲያን ኃላፊና ሠራተኛ ምዝበራውን፣ ዝርፊያውን የቤት፣ የመኪና ግዢውን አጧጡፎታል፡፡ አንድ ደብዳቤ ለማብረር ያለ ገንዘብ የማይሠሩ የቤተክርስቲያን ሠራተኞች፣ ጳጳሳት (ጥቂቶች ካልሆኑ በቀር) የደብር አለቆች ሁኔታ ሲታይ በቤተክርቲያን ላይ ያንዣበበው አደጋ በመጨረሻው ፍልሰተ ምእመናንን እያባባሰው ይገኛል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደከዚህ በፊቱ ችግሮቹን ሁሉ በሌሎች ላይ በማሳበብ ጊዜውን ከሚያጠፋ “ውስጥን ማየት” ለበሽታው ፍቱን መድኃኒት ነው።

ቅዱስነታቸው በመክፈቻ ንግግራቸው ውስጥ እጅግ በጣም ወሳኝና አስፈላጊ አንገብጋቢም ነገር ተናግረዋል፡፡ ይኸውም “ህዝብ እየጠየቀ ነው” የሚል ነው፡፡ እውነቱን እንነጋገር ካልን ቤተ ክርስቲያኒቱ ጥያቄን ታፍናለች፣ የሚጠይቀውን ትቆጣለች፣ አሊያም ታባርራለች፡፡ ይህን ጥያቄን የመፍራትን ባሕል የደረበባት ማቅ ስለሆነ ህልውናዋ ላይ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ ነው፡፡ አንድ ተማሪ ያልገባወን ከጠየቀ፣ አንዳንድ ከሃይማኖቱ ያፈነገጡ አስተምህሮዎችን አስረዱኝ ካለ፣ ይህ ተሐድሶ ነው፣ ጴንጤ ነው ይሉታል፡፡ ስለዚህ፡- እውነቱን ለማወቅ ለመረዳት፣ ለመገንዘብ፣ ለመሻሻል ለመለወጥ፣ ራእይ ያለውን ትውልድ፣ ምእመናንን፣ ቀሳውስትንና ጳጳሳትን ለማፍራት መሠረታዊው ነገር ጥያቄን አለመፍራት ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም የሕዝብ ጥያቄ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል፡፡
ቅዱስነታቸው ሕዝብ እንዲህ ብሎ እየጠየቀ ነው፤ የሚለግሰው ገንዘብ ለሃይማኖቱ አላማ እንዲሆን ብቻ እየፈለገ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዛሬ በገዛ ገንዘቧ ሰላሟ ደፍርሶ፣ በአገልጋዩም በተገልጋዩም ዘንድ ጥርጣሬ አለመግባባት ተከስቶ፣ አውደ ምህረቶቹ የብጥብጥ የትርምስ ሂደት የሚታይባቸው፣ ወጣቱ እየተነሣ ቢሮ በላሜራ እያሸገ የሚገኝበት ይህ ሁሉ ሁኔታ መነሻው የሚለግሰው ገንዘብ ለሚፈለገው መንፈሣዊ አገልግሎት ባለመዋሉ ነው፡፡ ስለዚህ ለጥያቄው ሲኖዶሱ መልስ መስጠት አለበት፡፡
ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ዝቅተኛ አገልግሎት የሚባለው ስብከተ ወነጌል ነው፡፡ ነገር ግን ለዚህ ወሳኝ አገልግሎት የረባ በጀት አልተበጀተም፡፡ አጥቢያዎች ለዓመት ክብረ በአል ለበሬ መግዣና ለድግስ ዳጎስ ያለ በጀት ሲመድቡ ስብከተ ወንጌልን ግን ዞር ብሎ የሚያየው የለም፡፡ ነገር ግን ሕዝብ የሚለግሰው ገንዘብ ከካህናት ደሞዝ ባሻገር በአብዛኛው ለወንጌል አገልግሎት ለካህናት ሥልጠና ቢውል የቤተ ክርቲያኒቱ ሕይወትና ጉዞ ተስፋ ይኖረው ነበር፡፡ ስለዚህ ቅዱስነታቸው ሕዝቡ ገንዘቤ ምን ላይ ዋለ? ብሎ እየጠየቅን ነው ብለዋል፡፡
ዛሬ እኮ እኛስ ማን አለን? የሚሉ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች ሥራና ገቢ ሳይኖራቸው መኪና እየገዙ፣ ሰንበት ት/ቤታቸውን እንደ ገቢ ምንጭ እያዩ የሚገኙ አመራሮች ጥቂት አይደሉም፡፡ እንደ አልማዝ ያለው መአድን ያላቸው እንደ ኮንጐ ያሉ የአፍሪካ ሀገሮች በሃብታቸው ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ሲገባቸው እነርሱ ግን ሲጣሉበት እንደኖሩ ሁሉ በዚህች ቤተክርስቲያን ከሕዝብ በልዩ ልዩ መንገድ የሚሰበሰበው ገንዘብም በጳጳሳት፣ በአለቆች፣ በደብር ልዩ ልዩ ሀላፊዎችና በመሳሰሉት ሁሉ መካከል ተመሳሳይ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ ሕዝቡ ግን ቤተክርስቲያን ውስጥ መልካም አስተዳደር ሰፍኖ፣ አድልዎ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ፣ መለያየት በአጠቃላይ ከሃይማኖት መርሕ ጋር የማይጣጣም ኋላቀር አሠራር፣ አስተሳሰብ ተወግዶ የተስተካከለ ሥርዓት ማየት እፈልጋለሁ እያለ ነው፡፡
ለዛሬይቱ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ችግር መባባስ “ከሃይማኖት መርሕ ጋር የማይጣጣሙ” ተግባራት ከእለት ወደ እለት እየተከሰቱ መምጣታቸው ነው፡፡ በዘር ላይ የተመሠረተ ቅጥር እድገት ዝውውር፣ እየታየ ባለበት ጊዜ ይህን ሲሰማ ጥያቄ ያቀርባል፡፡ ከምንም በላይ ኋላቀር አስተሳሰብ ይወገድልኝ እያለ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ጥያቄ ሲጠራቀምና መልስ ሲያጣ አማራጩ በተሰጠው ሀገራዊ ነፃነት የእምነት እኩልነት መሠረት ወደ ሌላ ቤተ እምነት መፍለሱን ይያያዘዋል፡፡ “ስለ ሃይማኖት ክብር ሕልውና ከልብ የሚቆረቆሩ መልካም ሥነ ምግባርና የተስተካከለ ሰብእና ያላቸው እንዲሁም በኑሮአቸው ሁሉ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንደአርአያ የሚጠቀሱ ውሉደ ክህነትና ሠራተኞች እንዲመሩት እየጠየቀ ነው፡፡”
ዛሬ እንዲህ ዓይነቱ ቀና እምነትና በጎ ምግባር ያለውና ህይወቱን በትክክል የሚመራው በአብዛኛው በሚገርም ሁኔታ ስም ተሰጥቶት ይባረራል፡፡ በትግል ላይ የሚገኝም አለ፡፡ ዛሬ እኮ እንዲህ ዓይነቱን አገልጋይ እንመልከት ተብሎ ነው የታወጀው፡፡ በከፋ የሥነ ምግባር ችግር ውስጥ ያለው ደግሞ ተከብሮ ይኖራል፡፡ ይልቁንም አገልጋዩ ማቅን አይንካ እንጂ በየትኛውም የሥነ ምግባር ችግር ውስጥ ቢገኝ ማንም ሊነካው አይችልም፡፡ ብቻ ጠንካራ፣ አቅም ያለው ሆኖ ለሕዝቡ ልቡን የሚያሳርፍ ወንጌል አያስተምር እንጂ ክርስቶስን ተግቶ አይስበክ እንጂ በሌላው ችግር የለም እየተባለ ነው፡፡ በተለይ በማቅ ወገን ከሆነ ምን ችግር አለው? እንዲህ ያለው ሰው “የምግባር እንጂ የሃይማኖት ችግር የለበትም” ተብሎ ከመወቀስና ከመከሰስ ይድናል፡፡ ይህ አነጋገር ወደፊት የቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አካል ሆኖ እንነዳይቆጠር ያሠጋል፡፡  
ሲኖዶሱ ይህን የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ ንግግራቸው በበቂ ሁኔታ ሊወያይበት ይገባል፡፡ ሕዝቡ እምነቱም ሕይወቱም የሚመራኝ ካህን ሰባኪ፣ መነኩሴ ጳጳስ እፈልጋለሁ እያለ ነው፡፡ ቅዱስነታቸውም ለሕዝቡ ይህን ጥያቄ እንመልስለት ነው ያሉት፡፡ ይህም  ልብን የሚያሳርፍ የእምነት የስብከት አርአያና ምሳሌ የሆነ አገልጋይ እንደሌለ ነው የቅዱስነታቸው ንግግር ያብራራው፡፡ ሕዝቡ ቤተክርስቲያን በሁሉም መስክ ጠንካራ አቅምን ገንብታ እንደዚሁም ለሕዝብ ክርስቲያኑ መንፈሳዊና ማህበራዊ ችግር ደራሽና አለሁላችሁ ባይ ሆና ማየት እንደሚፈልግ ከሚያነሳው ጥያቄ ማወቅ ይቻላል፡፡ የክርስቶስ አካሉ የሆነች ቤተክርስቲያን የአዳም ዘርን ፍላጐት ፈፃሚ፣ የሕዝቡን ማህበራዊ ችግሮች ፈቺ በውስጠዋ በሚፈሰው ፀጋ እግዚአብሔር ተከታዮቿን በሀብት ሰባ በረድኤት አቅርባ እግዚአብሔር በልጁ በኩል የሠራውን የማዳን ሥራ ምጥ እስኪይዛት ድረስ ለሕዝቡ የምትሰብክ መሆን አለበት፡፡
ጌታ ደቀ መዛሙርቱን ወደ አለም የላካቸው አባቱ እሱን በላከው አኳኋን ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔር ልጁን የሰውን ልጅ ሁለንተናውን እንዲሸከምና በሞቱ በትንሣኤው እንዲያድነው ነው፡፡ ስለዚህ የሠባራው ዓለም ቁስል በክርስቶስ ኢየሱስ እንደ ተጠገነ ሁሉ፤ ዛሬም አካሉ የሆነች ቤተክርቲያን የእርሱን የማዳን ዜና በማወጅ ይህን ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ ሕዝቡ እያየና እየሰማ እየተሳቀቀም ያለው በሚታየው የሥነምግባር ዝቅጠት የሞራል መላሸቅ፣ ከክርስቶስ የራቀ ትምህርትና ሕይወት ተከታዮች መያዛቸው፣ እረፍት አልባ ኑሮ ስለሆነ ለኔው መፍትሄ እኔ እንጂ ቤተክርስቲያን ምን አገባት ከሚል ወደወጣ አመለካከት አዘንብሏል፡፡በከተማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት የመጣውን የሀገራችን ብሔራዊ ሱስ ለመሆን የተቃረበውን፣ ጫት ሺሻ አሽሽ፣ የሴተኛ አዳሪዎች ሕይወት፣ ግብረ ሰዶማዊነት ሁሉ ማህበራዊ ቀውሶች ናቸው፡፡
በእነዚህ ሁሉ በምድር ላይ ላለችው ሰማይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ህዝቡን በሃይማኖትም በማህበራዊ ሕይወትም ለሚደርስበት ችግር ፈጥና እንድትደርስ የሚፈልግ ጥያቄ ሕዝቡ እያነሣ እንደሆነ ነው ቅዱስነታቸው ያሳሰቡት፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስም ተግባር ስለ ገንዘብ ብክነት ብቻ ሳይሆን ስለ ባከነች ግራ ስለ ገባት ነፍስ ነገ ምን እሆናለሁ ከሚል የማህበረሰብ ጥያቄ ከብርቱ ፀሎት ጋር መልስ ይ መቅረብ አለት፡፡ ምክንያቱም ቅዱነታቸው ያቀረቡአቸው የሕዝቡ ጥያቄዎች የሁሉ ጥያቄዎች ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከውጭ በምታገኘው እርዳታ በልማት ኮሚሽን ከምትፈፅመው ልማት ሌላ ሀይልዋ፣ ጉልበትዋ፣ አቅምዋ ሀብትዋ ይህን ሁሉ አገልጋይ የምትመግበው ከሕዝቡ ከሚሰጥ መዋጮራትና መባ የሰበካ ጉባኤ የአባልነት ክፍያ ነው፡፡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት የገነቧቸው ሕንጻዎች ሁሉ በሕዝቡ ገንዘብ የተገነቡ ናቸው፡፡ ስለዚህ ህዝቡን የሚያሳርፍ የወንጌል ትምህርት በመስጠቱ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባ፡፡ የቅዱሰነታቸው የእንወያይበት ሐሳብ እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ቢያንስ ሕዝ እየጠየ መሆኑን ማወቅና ይህንንም ከፓትርያርክ አንደበት መስማት ለውጥ ትልቅ ተስፋ ነው፡፡
በዚህ ለሲኖዶሱ ወሳኝ አቅጣጫ ጠቋሚ በሆነ የፓትርያርኩ ንግግር ደስ የተሰኘ እንዳለ ሁሉ ይህን ወሳኝ ንግግር ወደ ጎን በመተው በተራና የራሳቸውን የልብ ምኞት ለመፈጸም የያዙትን ዕቅድ የሚያሳይ ወሬ ያወሩ አሉ፡፡ ማቅ የልቡን የሚተነፍስባት ሐራ ብሎግ ለዚህ ትጠቀሳለች፡፡ ሐራ ሲኖዶሱ በአጀንዳው ውስጥ ለፓትርያርኩ እንደራሴ ለመሾም ማሰቡን ጠቁማለች፡፡ ይህም የሌለና ማቅና በማቅ ድጋፍ ያጡትን ፕትርክና መልሰው በእንደራሴነት በኩል በእጃቸው ለማስገባት ከሚቋምጡ አንዳንድ ጳጳሳት ጋር የተደረገ ምክር እንጂ የቤተክህነቱ ጥያቄ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡
ፕትርክናዉ ሳይሳካላቸው የቀሩት እንደራሴ ለመሆን መመኘታቸው ግን ያስቃል፡፡ መቼም ምኞት አይከለከልም፡፡ ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት አቅም ላቸው መሆኑን በተግባር አሳይተዋል፡፡ ሁሉ የፈራውን ማቅን ሳይፈሩ በቆራጥነት ያነቃነቁና ቤተክርስቲያኒቱን ከማቅ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ጠንካራ መሆናቸውን ያስመሰከሩ አባት ናቸው፡፡ ታዲያ እንደራሴ ያስፈልጋቸዋል ለምን ተባለ? ያው ለማቅ ስላልተመቹትና የጎን ውጋት ስለሆኑበት ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱስነታቸው አሁኑ ባሉበት ሁኔታ አልደከሙ አልታመሙም፡፡ እንደራሴ የምትለዋ ሐሳብ ፓትርያርኩን ለመበቀል ማቅ የጠነሰሰው ሴራ ነው እንጂ ሌላ ምን ይባላል? በእርግጥኝነት ይህን ሐሳብ የሚያቀርብ ጳጳስ ካለ በማቅ የተሞላ ለመሆኑ በቂ መረጃ ሊሆን ይችላል፡፡
ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎሎስ ለረም ጊዜ የፓትርያርክ ቡነ ባስልዮስ እንደራሴ የሆኑት በወቅቱ ፓትርያኩ አይናቸው እስከ መታወር ስለደረሰ ነበር፡፡ አሁን ግን ምን  ተገኝቶ ነው እንደራሴ ያስፈለገው? ይህ ፓትርያርኩ በማቅ ላይ የጀመሩትን ሥርዓት የማስያዝ ሥራ ለማደናቀፍ ታስቦ የተጠነሰሰ ማስፈራሪያ ነው፡፡ ቅዱስነታቸው ሕዝቡ እንዲህ እየጠየቀን ነው እያሉ ማቅ የሚያሳስበው ግን ለእርሱ ያልተመቹትን ሰዎች በወታደራዊ (ሐራዊ) አነጋገር “እገሌ ሊወገድ ነው ፓትርያርኩ እንደራሴ ያስፈልጋቸዋል፣ የሦስተኛ አመት በአለ ሲመት ግብዣ ይገመገማል የሚል የወረደ የመንደር ወሬን የሲኖዶስ አጀንዳ አስመስሎ ማናፈሱ ምን እያሰበ እንዳለ የሚያሳይ ከመሆን አያልፍም፡፡ ምናልባትም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስፍራ ስላጣ በዚህ የተሰማውን ጥልቅ ቅሬታ ለመግለጽና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፓትርያርኩን ለመሸንጥ ነው፡፡ ስለዚህ እንደራሴ ሲል ምኞቱ ሐሳቤን የሚያስፈፅምልኝና የልቤን የሚያደርስልኝን እንደራሴ ምረጡልኝ ብሎ ለመቀስቀስ የፈለገ ይመስላል፡፡
በሲኖዶሱ ስብሰባ ከሚነሱ አጀንዳዎ መካከል የኮፒራይት ነገር አንዱ ነው፡፡ ማቅ የወሬ መንዣ ሐራ ግን ይህን አጀንዳ አልፋዋለች፡፡ ለምን ቢባል ይህ በቀጥታ ማቅን ስለሚመለከት፣ ገፋ ሲልም ወደነአባ ሳሙኤል ሊደርስ ስለሚችል በዝምታ ማለፉን መርጣለች፡፡ ማቅን በሚመለከት ቢያንስ ከአባ ጊየርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ያለገዳሙ ፈቃድ ያሳተመው መጽሐፈ ምስጢር በጠቅላይ ቤተ ህነት ህግ ክፍል እንከሰስ ደብዳቤ መጻ ታውቆአል፡፡ ይህ ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል፡፡ ሐራ ግን  ሦስተኛ አመት በአለ ሲመት ግብዣ ይገመገማል” በሚለው ተክታዋለች፡፡
        ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በተመለከተ በተለይ እንደ አባ ዲዮስቆሮስ አይነቶቹ ጳጳሳት ስማቸው ከሚጠራበትና ደመወዝ ከሚበሉበት በቀር እንደሚገባ የማያገለግሉበትን 3 ሀገረ ስብከት ደርበው የያዙ በወር ከሦስቱም ከእጥቅማቸው እስከ 5ዐ ሺ ብር የሚያገ ስለሆኑ ምርጫው ይቆይ አሁን አይመረጥ እያሉ ከጥቅምት ወደ ግንቦት ከግንቦት ወደጥቅምት ማንከባለልን ሥራዬ ብለው አስቀድመው ከመሰሎቻቸው ጋር አድማ እንደያዙበት በቤተክህነት አደባባይ ሲወራ የከረመ ነው፡፡
በአጠቃላይ ቅዱነታቸው ያቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ፍሬ ሐሳብ ችግር ውስጥ ነን፣ የምዕመናን ማህበራዊ ችግሮችን እንቅረፍ፣ እምነትም ሕይወትም ይኑረን፣ ሀገራዊ ድራሻችንን እንወጣ፣ ሕዝቡ የሚሰጠን ገንዘብ ለተልኮዋ ብቻ እንገለገልበት፣ ወዘተ ማለታቸው በጠቅላላው በሰው ሕይወት ላይና በአንገብጋቢው የቤተክርስቲያን ችግር  ላይ ብቻ ያተኮረ ንግግር ማድረጋቸው ይበል የሚያሰኝና ከአንድ መንፈሳዊ አባትና የቤተክርስቲያን መሪ የሚጠበቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ውድ ልጁን የላከው ለሰው ነውና 
መቅምም ያለበት ው ነው፡፡ ሰውን መለወጥ ማፅናናት፣ በወንጌል ማሳረፍ፣ ኑሮውን በበረከት እንዲመራ መምከር፣ ለምድራችን ለውጥ እንዲያመጣ ማገዝ ማህበራዊ ሕይወቱ ከጉስቁልና እንዲላቀቅ መርዳት የቤተ ክርስቲያን ድርሻ ነው፡፡ መልማት ካለባቸው ነገሮች ቀዳሚው የሰው አእምሮ ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ለተከታዮችዋ ተስፋ መሆን አለባት፡፡ ለዚህም ቅዱስነታቸውን ማገዝ ከሲኖዶስ አባላት ይጠበቃል፡፡ አሁንም ቢሆን ክርስቶስ የሞተለት ሰው ይቅደም፡፡ እናድነው ከባዘነበት እንመልሰው፣ ከሞተለት አምላክ ጋር በስብከታችን እናስታርቀው፡፡

14 comments:

 1. thank you aba selama for ur information.

  ReplyDelete
 2. ማቅ የእውነት ጠላት መሆኑን እናውቃለን። ክፋቱ ስር የሰደደ እና ከአባቱ ከዲያቢሎስ የተማረው ነው።

  ReplyDelete
 3. ማቅ አስተሳሰቡ መሞቱ የተረጋገጠ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም የብዙ ቅዱሳን ደም ለመጠጣት ግን ህዝቡ እየቀሰቀሰ መሆኑ ግን ሊታወቅ ይገባል።

  ReplyDelete
 4. betam des ylal Tebareku


  ReplyDelete
 5. who ever who is writing this msg, we know why you do so. Let God forgive you

  ReplyDelete
 6. ewnetga yebatekrestyane lrjochema enemane endehone egzebsene maekele hadeke eye mecame mesmihe tedefnoale bewere 27.000 berer yemikflke yeluter telalki mehonaceue tebanobacuhle Batekrestyane erasua krsetose newe maneme aysenfateme medre arateka hulu errrrrrrrrrrr belu ye Ethiopia amelake gena bezu yserale aleme be Ethiopia ortdox kuteter sere endemtwedeke aykera newe neseha gebtacheu keri zemnacheune luterene sayhone Krestosene endetaglgelu lbona yestaceueh betame tasaznalcheu baleke zemene ye lutere telalki bemhonachu Ceresku

  ReplyDelete
 7. ምክንያቱም በዚህ አጋጣም አንዳንድ የማቅ ደጋፊ የነዋይ ሰዎች የሆኑትን ጳጳሳትን በእለቱ እንድገኙለት አጋጣምውን ለመጠቀም የታቀደ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያናችን እውነተኛ አባት ወይንም ጳጳስ የአጣችበትና ባዶ እየቀረች ያለች ቤተ ክርስትያን ናት።በካህናቱ እና በህዝቡ መካከል ዛሬ ፍቅር አንድነት ህብረት ሰላም ትግስት ትክክለኛ የአምልኮት ስራት የጠፋበት ወቅት ላይ ነው ያለነው።ሁሉም በየእራሱ ጎዳና ዘመቻውን እያደረገ ነው። ማቅም የኢህዳግን ድብቅ አላም በስውር እያካሄደ ነው። ለዚህም ነው እነደ ፈለገ እየፈጨ እርሱን የማይቀቡሉ ካህናት ሰባክያን እያሰደደ ያለው። እውነት ከሆነ ማቅ ሽብር ፈጣር ነው እየተባለ በመንግስት ይወነጀላል ነገር ግን አንድም ግዜ የማቅ ቢሮ ህገ ወጥ የሆኑት የንግድ ድርጅቶቹ ተዘግተው አያውቁም።ምክንቱም እነ ዳንኤል ክብረት የመንግስት ሰላዮች ሰለሆኑ ብቻ ነው።የኦቶዶክስ ህዝብ ሰላም እዳይኖረው ኢሕዳግ በማቅ በኩል በድብቅ እየከፋፈለ እነ በሃይማኖት መካከል አልገባም በማለት በአዳባባይ ይለፈልፋላ።

  ReplyDelete
 8. እግዚአብሔር ያሳችሁ በአዲስ አበባ ያለው ስኖዶሳችን የመነጋገርያ ነጥቡ ሳይቀር በየማቅ ድህረ ገጾች ስወጡ እናያለን። ለመሆኑ የጳጳሳቱ ጉባይ በአንዳንድ የማቅ አባላት ጳጳሳት በኩል ምስጥሩ ወደ ውጭ እየወጣ እየተገለጸ ባለበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። የየትኛው ሀገረ ስኖዶስ ስብሰባ ሳይፈጸም ለአደባባይ የሚቀርው? የዶርቶደክስ ሆኑ የካቶሊክ ቤተ ከርስትያናት ስኖዶስ ጉባይ ለማንም ጋዘጠኛ ሆነ ድህረ ገጽ አይወጣም። የእኛ ስኖዶስ ግን የማቅ አምላክዎችና ደጋፍዎች ሰለሆኑ እንደ ፈለጉ ይጫወቱባታል። እጅግ ያሳፊራል። ብሆንማ የስኖዶሱ ጉባኤ ከተጠናቀቀ በሗላ የጋራ መግለጫ ስሰጥ በየድህረ ገጹ ይወጣ ነበር። አለመታደል ስለሆነ በማቅ አባቶች እራቃናች እየተጓዝ ነን።

  ReplyDelete
 9. ለስነጥበብ ባለሞያዎቻችን የማስተላልፈዉ የአግዚአብሄር መልዕክት ቢኖረኝ በቤተክርስቲያን ስራዓት ዉስጥ ሊቃዉንቶች የሚያስተምሩት ትልቅ አባባል አለ ከመጠምጠም መማር ይቅደም።
  ስለዚህ ቤተክርስቲያን በመንፈስቅዱስ አንጂ በተንኮል ተቧዳኞች አልተመሰረተችም አልተመራችም ወደፊትም አትመራም።

  ReplyDelete
 10. ይሄ መሰሪ ማህበር

  ReplyDelete