Friday, May 27, 2016

እንደራሴ ይሾም የሚለው አጀንዳ በፓትርያርኩ በሌሎችም ጳጳሳት ተቀባይነት አጣሲኖዶስ ከያዛቸውና አጀንዳው እንዲያዝ ባደረገው ክፍል በኩል ዋና አጀንዳ ተደርጎ የተወሰደው “ለፓትርያርኩ እንደራሴ ይሾም” የሚለው አጀንዳ ለጳጳሳቱ መከፋፈል ምክንያት ሆኖ መዋሉንና ከስምምነት ላይ አለመደረሱን መረዳት ተችሏል፡፡ ወደ ሥልጣን ከመጡ 3 ዓመታትን ያስቆጠሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመልካም ጤንነትና በጥሩ አመራር ላይ እንዳሉና የቤተ ክርስቲያን “ነቀርሳ” የሆነውን ማቅን አደብ ለማስገዛት በጀመሩት ጥረት ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ እንደራሴ ይሾም የሚል አጀንዳ እንዲቀረጽ የመደረጉ ምስጢር ሌላ ሳይሆን ማቅ ለምን ተነካ በሚል እንደሆነ ከጉዳዩ አካሄድ መረዳት ይቻላል፡፡ ከሲኖዶሱ ስብሰባ በፊት የማቅ ሰዎች በዚህ ላይ ሲሰሩና ለደጋፊ ጳጳሳት ከፍተኛ በጀት መድበው ሲንቀሳቀሱና አጀንዳውን በአጀንዳነት ለማስያዝ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበርና ያንንም ማሳካት እንደቻሉ ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ አጀንዳው ምክንያታዊ ባለመሆኑ ማቅ እንደ አእዱግ እየቀረቀበ አጀንዳውን የጫናቸው ጳጳሳት ድል አልቀናቸውም፡፡
በማቅ በኩል የማቅን ይህን አጀንዳ ይዘው የተነሡትና እንደራሴ ይመረጥ ያሉት ጳጳሳት አባ ቀውስ ጦስ፣ አባ ማቴዎስ፣ አባ ዮሴፍ፣ አባ አብርሃም፣ አባ ዲዮስቆሮስ፣ አባ ኤልሳዕ፣ አባ እንድርያስ፣ አባ ቀሌምንጦስና በቅርቡ ማቅን የተቀላቀሉት አባ ሳዊሮስ ናቸው፡፡ ይህን በምክንያት ላይ ያልተመሠረተ የማቅን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የቀረበውን አጀንዳ የተቃወሙትና እንደራሴ አያስፈልጋቸውም በራሳቸው ቤተክርስቲያንን እየመሩ ነው ያሉት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ ብፁዕ አቡነ ሙሴ፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ናቸው ተብሏል፡፡ 

አጀንዳውን የተቃወሙትን ጳጳሳት በመቃወም ንዴታቸውን “ምነው በጎጥ አደረጋችሁት” ሲሉ የገለጹት አባ ዮሴፍም በዓይናቸው የተጋደመውን የዘረኛነት ግንድ መመልከት ተስኗቸው የሌላውን ጉድፍ አየሁ ሲሉ ተስተውሏል፡፡ ይልቁንም ሌሎቹን ጳጳሳት በወገን እንዲሰለፉ የገፋፋ የመሰለው እነርሱም እንደራሴ ይሾም የሚለውን አጀንዳ ለቤተ ክርስቲያን በማሰብ ሳይሆን ደጋፊ የሆናቸውን ማቅን ይዘውና በዘረኛነት ተቧድነው መቅረባቸው መሆኑ አልታወቃቸውም፡፡ ለዚህ የአባ ዮሴፍ ውንጀላ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በሰጡት ምላሽ “ለካስ የአንድ መንደር ሰዎች ሆናችሁ ቤት ዘግታችሁ ስታድሙ የነበረው ይህን ነበር?” በማለት አጀንዳውንና የአባ ዮሴፍን ተቃውሞ ተቃውመዋል፡፡
በተሰነዘሩት ሐሳቦች ውስጥ ማስተዋል የተሞላበትን ሐሳብ ያቀረቡት ብፁዕ አቡነ ያሬድ ሲሆኑ፣ ስለ እንደራሴነት ከማውራታችን በፊት የእንደራሴው መብት፣ ግዴታ፣ ዕውቀት፣ የትምህርት ደረጃና የመሳሰለውን አስቀድማችሁ አዘጋጅታችኋል ወይ? በማለት አጀንዳውን ላቀረቡትና የተጫኑትንና በጭፍን  “እንደራሴ ይሾም” ላሉት ጳጳሳት ያልጠበቁትንና ለመመለስ የሚቸገሩበትን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ እንዲህ ያሉትም አጀንዳው የመጣበት አቅጣጫ ስለገባቸው ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ይህ አጀንዳ የጳጳሳቱ የራሳቸው ሳይሆን በፓትርያርኩ ላይ ዘመቻ የከፈተው የማቅ ነውና፡፡ ፓትርያርኩ ለማቅ ስላልተመቹት እርሳቸውን ከሥልጣን ካላወረደ ዕረፍት እንደሌለው የሚያሳይ አጀንዳ ነው፡፡
በጣም አስገራሚው ነገር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ላይ እንደራሴ ለመሾም ሲል ማቅ ማንሣት የማይፈልገውን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን እንደራሴነት ጠቅሶ ያለልማዱ እርሳቸውን ለማሞገስ ተገዷል፡፡ የማቅ አባቶች ቅዱስነታቸውን ያስገደሉ መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ስለሆነ ልጆቹም እርሳቸውን በተሐድሶነት ፈርጀው አንድም ጊዜ ስለእርሳቸው መልካም ሥራ ሳያወሩ ኖረው ዛሬ የፓትርያርክ ማትያስን በሳልና ቆራጥ አመራር ለመሸርሸርና በማኅበሩ ላይ የተጋረጠበትን የመፍረስ አደጋ ለመቀነስ በሚል ለያዘው “እንደራሴ ይሾም” አጀንዳ ማዳበሪያ አድርጎ ተጠቀመባቸው፡፡ ሆኖም ይህ ለቅዱስነታቸው ያለውን የኖረ ጥላቻ የሚሸፍን አይሆንም፡፡
በጣም የሚገርመው እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በሌሎቹ ፓትርያርኮች ጊዜ ሌሎች እንደራሴዎችም ነበሩ ብላ የማህበረ ቅዱሳን አፍ ሐራ ለማጭበርበር መሞከሯ ነው፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት እንደራሴ ነበሩ፣ አቡነ ዜና ማርቆስ ደግሞ ለአቡነ መርቆሬዎስ እንደራሴ ነበሩ ማለቷ ዓይናችሁን ጨፍኑና ላቂላችሁ ጨዋታ መሆኑ ነው፡፡ ለእነዚህ ፓትርያርኮች እንደራሴ የተሾመላቸው የውጭውን ቋንቋ ስለማያውቁ ከእኅት አብያተ ክርስቲያናትና ከሌሎችም ጋር ሲገናኙ የውጪውን ቋንቋ ከሚያውቁት ጋር እንዲያግባቧቸው ለማድረግ ነበር፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ግን በቂ ዕውቀትና ችሎታ፣ መግባቢያ ቋንቋውም ያላቸው ፓትርያርክ ስለሆኑ እንደራሴ አያስፈልጋቸውም፡፡ ሲመረጡም ይህን መስፈርት አሟልተው መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም፡፡
እንደ ራሴ ይመረጥ ባዮቹን ጳጳሳት ከተቃወሙት መካከል ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ ፓትርያርኩ የተመረጡት በእኛ ብቻ ሳይሆን በሕዝብም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ ለሕዝብም ለመንግሥትም እናሳውቅ ሲሉ ተደምጠዋል ተብሏል፡፡ አባ ሳሙኤልና አባ አብርሃምም “መንግሥት ምን ሃይማኖት አለው? ሕዝብስ ወሬ ያውራ እንጂ ምን አገባው” ብለዋል፡፡ መንግሥትን፣ በተለይም ገንዘቡን እየሰጠ እነርሱን እያንደላቀቀ የሚያኖራቸውን ሕዝብ እንዴት እንደሚመለከቱትና ለሕዝቡ ያላቸው ንቀት ምን ያህል እንደሆነ ያሳያል፡፡
አቡነ ኢሳይያስ ግን በመቀጠል ከሁላችን ጳጳሳት ንጹሕ ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁላችን ገዳም እንግባና ሌሎች አባቶች እንደ አዲስ ተሹመው ሌላ ፓትርያርክ ይምረጡ፡፡ ስለዚህ እያራመዳችሁ ያላችሁት መፈንቅለ ፓትርያርክ ነው፡፡ ይህም የሌላ እጅ እንዳለበት ያሳያል ብለዋል፡፡              
የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም ግን እስከ ጥቅምት ያስቡበት ለዚህም ዕድል እንሰጥዎት በማለት ትልቅ ድፍረት የተሞላበትና ራሳቸውን በሥልጣን ሰጪ ስፍራ በማስቀመጥ ሲናገሩ፣ ፓትርያርኩ አንተ ነህ ለእኔ ዕድል የምትሰጠኝ በማለት የጉድ ሙዳዩን ገሥጸዋል፡፡ በመጨረሻም ዛሬም ነገም እንደ ራሴ አልሾምም በሚል ቆራጥ ውሳኔያቸውን አሳውቀዋል፡፡   
ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ አጀንዳዎችን ከመቅረጽና በዚያ ላይ ተወያይቶ ለቤተክርስቲያን ጥቅም ለእግዚአብሔር ክብር የሚውሉ ውሳኔዎች ከመወሰን ይልቅ በአንዳንድ ጳጳሳት በኩል የማቅን ሐሳብ ለማስፈጸም በአጀንዳነት በማቅረብ ሞገሱን እያጣና ተሰሚነቱን እየቀነሰ በመሄድ ላይ እንደሚገኝ ከጊዜ ወደጊዜ እየታየ ነው፡፡ ለዚህም በተገቢው መንገድ ዕውቀታቸው፣ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ብቃታቸው ታይቶ ሳይሆን እጅ መንሻ ሰጥተውና በተለያየ የዓመፅ መንገድ ወደ ጵጵስና የመጡ የስም ጳጳሳት ተጠያቂ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሲኖዶሱን እያወኩና እጅግ በዘቀጠው ሕይወታቸው ለቤተ ክርስቲያኗ ማፈሪያ እየሆኑ የሚገኙት እነዚሁ የስም ጳጳሳት ናቸው፡፡
ስለዚህ ቅዱስ ፓትርያርኩ አሁን በሚሾሙት ጳጳሳት ላይ በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ የተፈጸሙትንና እስካሁን ለሲኖዶሱ በሽታ የሆኑትን ጳጳሳት ዓይነት በመሾም ሌላ ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ እየወጡ ባሉ አንዳንድ መረጃዎች አንዳንድ ጠንካራ አባቶች ለጵጵስና መታጨታቸው  ለቤተክርስቲያን ተስፋ ነው፡፡ ከጳጳሳቱ በስተጀርባ ሆኖ በእርሳቸው ላይ እንደራሴ ይሾም የሚል አጀንዳ ያንቀሳቀሰውን ማኅበር ጉዳይ ብዙዎች እየጠበቁ ነውና ጅምሩን ከዳር ማድረስ አለባቸው፡፡ ከዚህ የተሻለ ዕድልና ጊዜም የለምና፡፡ አሊያ ጥቅምትና ግንቦት በመጣ ቁጥር እንዲህ ባለ እርባና ቢስ አጀንዳ የሲኖዶሱ ስብሰባ መታወኩን ይቀጥላል፡፡    

13 comments:

 1. ይህች ብሎግ ለናንተ ለተሐድሶ መናፍቃኑ የተመቸ ሃሳብ ያነሳ አባት ያገኛችሁ ሲመስላችሁ ብጹዕ አቡነ እገሌ ትላላችሁ ነገር ግን የናንተን አካሄድ ተረድቶ ቀድሞ ለቤተ ክርስቲያን ወግኖ ቁርጥ ያለ ሃሳብ ያቀረቡትን ብጹዓን አበውን አባ እገሌ ትላላችሁ፡፡ ሃይማኖት የለሽ ምግባረ ብልሹ ስለሆናችሁ ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስን በተደጋጋሚ (ቀውስ ጦስ) እያላችሁ ትጽፋላችሁ፡፡ እሳቸውስ ታላቅ የወንጌል መምህር የጸሎት አባት ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ ይድረስላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 2. You bloger’s, you were /are/ will write false statements. Let the Holy Synod members to debate and decide upon the issue which will benefit us (the church members). You are not the members of the tewhido church, go soon the protestant halls. If you have spritual heart to drop everything away that is not belongs/represents to the church. Our church fathers and the God immedialy accept you. But I doubt you don’t have such spritual heart. Finally, you are always telling us MK is after all issues, which is not true. Leave MK to do its tasks which has been taking the assignments from the Holy Synod two decades ago. It is time for MK to serve the church, the country and the world at wide. Byeeeeeeee!

  ReplyDelete
 3. ሂሂሂሂ
  ወሬኛ ጴንጤ

  ReplyDelete
 4. ተሃድሶ ማን ነው? በእውነት ቤተክርስቲያንን ያደሰው ማን ነው? ዘረያዕቆብ አይደለምን ለምን ይህ እውነት ይደበቃል። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ በማመን የዘላለም ህይወት እንደምናገኝ በፀጋው መዳናችንን እንዳናምን በፀጋው እንደዳንን ይህን እውነት ሰምተን አምነን እንዳንታተም ክፍ ዛሬም ዘረያዕቆብ ባደሳት ቤተክርስቲያን ላይ ሲሰራ እናያለን። በእውነት ለትውልዱ መዳን ይሁን ይህን እጅግ ዋጋ ተከፍሎበት ያገኘነውን መዳን እድናምን እግዝአብሄር በጌታ በኢየሱስ ስም ይርዳን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የፓስተር ጌታቸው ምልምል!!!

   Delete
 5. መናፍቅ ማን ነው? ትርጉሙስ ምንድን ነው? ተሐድሶ ውይም ቤተክርስቲያንን ያደሳት ማን ነው? ንጉስ ዘረያአዕቆብ እና መሰሎቹ ለራሳቸው በሚያመች ሀኔታ አዲስ ሀሳባቸውን ከስጋ እና ከደም ያመነጩትን አስገብተው ትውልዱን ሲያስቱ አሁንም የእነሱ ጠበቆች ለዚህ ውሸት ጠበቃ ሆነው ሲቆሙ እናያለን። የተምታታ አቑም ይዞ ሲጎዝ እናያለን ለምሳሌ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታማልዳለች እንጂ እንደ ካቶሊክ ሃይማኖት ሰማያዊ አይደለችም ከእግዚአብሄር በታች ነች ይባላል ግን በሀገራችን አንዲት ሴት ስትወልድ በሃይማኖት አበውም በምዕመኑም ዘንድ እኮን ማርያም ማረችሽ ይባላል እንዴ ይህ ሚያሳየው እኮ ማርያም የመማር ስልጣን እዳላት እኮ ነው። ይህ ሚያሳየው አስተምሮው እራሱ የተምታታ መሆኑን ነው። በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እየተባለ ብዙ ግፍ ተሰርቶል ይህም ንጉስ ዘረያቆብ የጻፈው ታዕምር ምስክር ነው! እግዚአብሄር ከዚህ የድንግዝግዝ እምነት በጌታ በኢየሱስ ስም ያውጣን። በእውነት እግዚአብሄር ይፈርዳል! በእውነት ይህ የውሸት አሰራር ኪዳኑ ለዘላለም በጌታችን በኢየሱስ ስም ይፈረስ። ዛሬ ይቺ ሃይማኖት በመንፈስ እና በዕውነት ሳይሆን ሰው ባወጣላት ከስጋ እና ከደም የሆነ መርህ እና ትምህርት ምትተዳደር ሆናለች ለክርስቶስ ሳይሆን ለቅድሳን ገድሎች ሰፊውን ቦታ ሰታለች! ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰበክ ወንጀል ነው ብላ ትከሳለች ታወግዛለች ግን ግን ይህም ወርቅ ስም ዋጋ ያስከፈላልና ስለዚህ ስም ዋጋ የከፈላቹ ወንድሞች ፀጋው ይብዛላቹ በክርስቶስ የሆነ እንደ ጳውሎስ እስር ሳይሆን ሞትም በደስታ ይጠብቃልና መንፈስ ቅዱስ ያበርታቹ እውነትም አርነት ያወጣል ትውልዱን በተረተረት አትሸንግሉት እውነት የሚያወጣው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ማመን ነው ። ስለዚህ እውነተኛ ክርስቲያን ከስጋና ከደም ሳይሆን ውጊያው በእናንተ ላይ ሆኖ ከሚሰራው ከክፉ ጋር ነው ይህም ምክሩ እና ስራው በታረደው በግ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የፈረሰ ይሁን ። ይህ እውነት በዚህ ሃይማኖት ከእደገና እንዲገለጠ ለትውልዱም ማምለጥ እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ስም ይርዳን።

  ReplyDelete
 6. Sijemer ehadeso menafik yemtelu sewoch erasachu menafik tehadsowoch nachu.be kirstos yemiyamen sew menafik ayibalim .midere tesadabi betecrstiyan asedabiwoch .mesakiya mesalkiya aderegachwaht betecrstiyanwan.mk yeneged derejit kebetecrstiyanachin tekesha lay weredu.hezbu yerefebet.sidbachun yizachu wede giber
  Abatachu diyabilos hidu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተሃድሶ መናፍቃን እርር ድብን በሉ!!!!!!!

   Delete
 7. Layenager Telate Zime bilale Telate Zime bilale Dabilose Zime Bila 2x

  Mahber Kidosan sera betegebare eyasetemaren new Abatochachen atekefafelo enanete Ye Dabilose Leijoche dese selacho be Zere tekefafelonalecho ahewe eye alesaka selacho degemo ....be abatochachene metacho .........

  ReplyDelete
 8. የሁለት ጊዜ አንበሶች….
  የ363 ቀን የቤተክርስቲያን ችግሮች……ሊቃነ ጳጳሳት!!
  (ይህ ጽሁፍ ሁሉንም ጳጳሳት አያካትትም)
  ሁላችንም እንደምናውቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሱን በቅዱሳን ስም “ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል የሰየመው ሃይማኖታዊ የፖለቲካ ድርጅት ላለፉት ከሁለት አሥርት አመታት በላይ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን እና በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን አገልጋዮች፤ አማንያንና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ሐቅ ነው፡፡ መነሻ ሀሳቤ ማህበረ ቅዱሳን ያውም ገና ጨቅላው ማህበር አሁን የሚሰራውንም ሆነ ወደፊት ሊሰራ ያሰበውን ተግባር ቤተክርስቲያናችን ማህበረ ቅዱሳን ከነ ስም አጠራሩ ባይኖርም አሳምራ እንደምትሰራው ነው፡፡ ‹‹በእውነት ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም››.. እንደሚባለው፡ አሁን አሁን በዚህ ጊዜ እስትራቴጂክ መቋቋምና መደራጀትን መሰረት ያደረገው ማህበር ያቀደውና ያሰበው ተግባር በይፋ ቁልጭ ብሎ በግልጥ መታየቱ ሃይማኖተኛው ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያዊም ስለ ቤተክርስቲያናችን እንዲያወራ ያደርገዋል፡፡
  ገና አንድ ፍሬው ማህበር የ25 ዓመቱ ወጣት ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንደዚህ ሲያምሳት፤ ቅዱስ ፓትርያርኩን በመቃወም ሰጣ ገባ ውስጥ ከገባበት ቀን ጀምሮ ብሎም ላለመበገር በማሰብ ድብቅ ተግባሩን በጳጳሳት ላይ አድርጎ በመስራት ያቦካው ቡኮ ይኸው ዛሬ ለዘመናት ተከብሮና ተወዶ በኖረው የሲኖዲዎስ ስብሰባ ላይ በጉልህ በመታየት ግጭት ፈጥሯል፡፡ በተቀጠሩ ጸሀፊያን በመጻፍ የሚያደናግረው ማህበረ ቅዱሳን ሰሞኑን በሚያወጣው ጽሁፍ በጣም ብገረምም፤ ለካስ የሚሰራውን ድብቅ ተግባር እየተረከልን ኖሯል እንድል አድርጎኛል፡፡ እኛም ብንጽፍ የሱኑ ያህል እጥፍ ድርብ ነገር ለዚህ የዋህ ህዝባችን ባሳወቅነው ነበር፡ ግን ማንም የማንንም ታሪክ በመጻፍ ለውጥ መናፈቅ ስለማይኖርበት ስለተመረጡ ጉዳዮች መጻፍን መረጥኩ፡፡
  ማህበረ ቅዱሳን በአሁኑ ሰዓት በቅዱስ ሲኖዲዎሱ ላይ ስሚያደርገው እኩይ ተግባር ለመጻፍ መነሳቴ ያለምክንያት አይደልም፡፡ ማህበሩ እንዳቀደውና ጳጳሳትን አስቀድሞ መስመር ባስያዘበትና ማህበር ተኮር አደረጃጀትና ማህበር ተኮር ስር ነቀል ለውጥ ለማካሄድ ባቀደው መሰረት ይኸው አሁን አሁን የሚበሉትን ምግብ እንኳን ለመጉረስ ደጋፊ የሚያሻቸውና የወጣትነት ዘመናቸውን ነውረኝነት ለማህበሩ አሳልፈው የሰጡት….. እድሜ ጠገቦቹ ሊቃነ ጳጳሳት ንትርክና ብጥብጥ አምሯቸው ይመስል ለእውነት ላለመገዛት ችግር በመፍጠር በየዘር ተጓዳኝተው ላለሙለት አላማቸው አልያም ለሚናፍቁት ስልጣን ለመቆናጠጥ በሆነውም ባልሆነውም ችግር በመፍጠር ቤተክርስቲያንን እየከፋፈሏት ይገኛሉ፡፡

  ReplyDelete
 9. ውድ አንባቢዎቼ ምናልባት እውነታው የሚገባቹ እኔ በምጽፍበት ቦታና መረዳት መጠን ላይ ስትሆኑ ይሆናል ቢሆንም በተቻለኝ መጠን ላስነብባችሁ ስለወደድኩት እውነታ ላስረዳችሁ እሞክራለሁ፡፡ እርግጥ ነው በዚህ ሰዓት ለማህበሩ ሁሉም ነገር የሞት ሽረት በሆነበት ሰዓት ምንም አይነት የጉልበትም ሆነ የተቃውሞ ጽሁፍ የማይዋጥለት ማህበረ ቅዱሳን ይህንን ሲሰማ እንደ እድሜ ጉዋደኛው ወሬውን ሊያቀላጥፍ እንደሚችል አስባለው፡፡ ሆኖም ይህንን ጽሁፍ በእውነት ለእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ባለኝ ጊዜ ሁሉ ለማድረስ እሞክራሁ፡፡
  ለዚህች ሀገር ድርሻችን ምንድን ነው? ሁሉን ያወቅን ነን ስንል፡ የእውነት መገኛ መሠረት ነን ስንል፡ ታሪካዊና ዘመን ጠገብ ሆነናል ስንል፡ አፋችን ሙሉ ነው፡፡ ግን ለዚህች ሀገር ዕለት ዕለት ችግርና ጭንቅ፤ ዘረንኝትና ጎጠኝነት፤ መከፋፈልና ጥቅመኝነት፤ ግፍና በደል ዲያቢሎሳዊ ስራ እያበረከትን ነው፡፡ ለነገሩ ስንት ልዕልና የነበራቸው አባቶቻችን እና እናቶቻችን የሰሩትን እምነትና የገነቡትን ቤተክርስቲያናዊ ሀብት ዛሬ እራሳቸውን እንኳን መርዳት የማይችሉ የኋሊት ተጓዞቹ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲህ አናንቀው ቢጫወቱበት አይደንቅም፡፡ ያልደከሙበት ገንዘብና ያለሰበኩት ሃይማኖት እነርሱ ከሞቱ ምንስ ቢሆን ደንታ አይሰጣቸውም፡፡ ይህ ነው ወይ የእነርሱ ውለታ? (ምንም እንኳን ከሰው ውለታን ባይጠብቁም)። ከዚህ ፀሐይ የሞቀው እውነታ በመመርኮዝ ማኅበሩ የሚመራው በእነዚህ መሳጢዎች በመሆኑ ይህ ድርጅት ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ ነው ማለት ከኩርንችት በለስን እንደ መጠበቅ፣ ከዓይን ጆሮን እንደ ማመን ይቆጥራል። ለቤተ ክርስቲያን ሕይወት/ ለክርስትና መቆርቆር፣ የቅዱሳን አባቶቻችን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን አሰረ ፍኖት መከተል ማለት ከእንደዚህ ዓይነቱ በደል ነፃ ሆኖና እንዲህ ዓይነቱን ዕዳ አወራርዶ ነው።

  ReplyDelete
 10. የአሁኑ ጳጳሳት ተበላ ተዘረፈ ቢሏቸው አያስጨንቃቸውም፡፡ የሀገረ ስብከቱን ምንነትና ደረጃ ተንቅቆ የማያውቅ ጳጳስ ሁላ ለመላዋ ቤተክርስቲያን ጨነቀኝ ጠበበኝ ቢል እውነቱ ባዶ ነው፡፡ ከሀገረ ስብከቱ በማዳበሪያ እየዘረፈ፡ አዲስ አበባ መጥቶ ቤተክርስቲያንን አዘረፋችኋት፤ ፓትርያርኩ እረዳት ይኑረው፤ የኛ ወዳጆች ይምሩን የሚል ጳጳስ በበዛበት ዘመን እውነተኛ ሲኖዲዮስ ይኖራል ማለት ዘበት ይሆናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ አምላካዊ ሥርዓት እየተጣሰ መሪው ተመሪ ተመሪው ደግሞ መሪ እየሆነ ሥርዓት አልባነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰፈነ ይገኛል፡፡ የዚህ ውጤትም ውሎ አድሮ እውነተኛው የሃይማኖት ትምህርት በሌላ የስሕተት ትምህርት እንዲለወጥ፣ አምላካዊው ሥርዓትም ፈርሶ በስፍራው የሰው ሥርዓት ምናልባትም ሥርዓት አልበኛነት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡
  የፓትርያርኩ ይቆየኝና ምክንያቱም በሁሉም መንገድ እየተዘለፉና እተሰደቡ ስላሉ….ፋታ ያግኙ ብዬ ነው፡፡ የነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት ነገር ውስጤን እየከነከነኝ ነው፡፡ እንደ እውነተኛ ሸንጎ ፈራጅ ስብሰባ የገቡት፤ እንደታታሪ አንጥረኛ ከኛ በላይ ዘበት ያሉት፤ ቤተክርስቲያንን ለግለሰብ በማይረባ የይሁዳ 30 ብር የሸጧት፤ ዛሬ ሲኖዲዎስ ገብተው እውነተኛ መስለው ህዝብ የሚያደናግሩት፡ ቤተክርስቲንን የሚበድሉት እውነት ለምንድ ነው?፡፡ በመላው ሀገሪቱ ቤተክርስቲንን እንዲያስተዳድር የተሾመው ጳጳስ ነው ወይስ ፓትርያርክ? ያውም ገደብ በሌለው ስልጣን፡፡ የእምነታችን ችግርና መከራስ በብዛትና በጥራት እንዲሁም በአይነት ያለውስ የት ነው?፡፡ አዲስ አበባ ወይስ ጳጳሳት ባሉበት ሀገረ ስብከታቸው?፡፡

  ReplyDelete
 11. enante zibrkochi yaletederge atawiru bihonim methalat besew zendi yale new. have understand me unless......
  ReplyDelete