Sunday, May 29, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ፓትርያርኩን በደብዳቤ ይቅርታ ጠየቀለብዙ ዓመታት አንገቱን አደንድኖ የኖረውና በተደጋጋሚ የይቅርታ ጠይቅ ደብዳቤ ቢጎርፍለትም የይቅርታ ልብም ሆነ አፍ ኖሮት የማያውቀው ማኅበረ ቅዱሳን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል በሚችል መልኩ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ኢግዚብሽኑ ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማለትም ግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ እርሱ “ከልብ” ያለውን ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሌሎች የበደላቸውን አካላትም ውይይት ካደረገ በኋላ ይቅርታ እንደሚጠይቅ ገልጿል፡፡  

በጉዳዩ ላይ “ይቅርታ ስለመጠየቅ” የሚል ርእስ የተሰጠው ደብዳቤው እንደሚለው “ባለፉት ጊዜያት ቤተ ክርስቲያናችንን በልጅነት መንፈስ ለማገልገል በምንላላክበት መጠነኛ የአገልግሎት ሂደት በተፈጠሩ ክፍተቶች ምክንያት ሐሳቦቻችንን ያስረዳን መስሎን በጻፍናቸው ደብዳቤዎች እና በአንዳንድ ሥራዎቻችን ቅዱስነትዎ ቅር እንደ ተሰኙብን ተረድተናል፡፡ ስለዚህም እኛ ልጆችዎ ሆነ ብለን ቅዱስነትዎን ለማሳዘን ያላደረግነው መሆኑን ተረድተውልን ይቅርታ እንዲያደርጉልን ከልብ እንጠይቃለን፡፡” ይላል፡፡


የይቅርታ ደብዳቤው ከመጻፉ በፊት መሪዎቹ ግንቦት 10/2008 ዓ.ም ፓትርያርኩ ዘንድ ቀርበው ከፓትርያርኩ መመሪያ እንደ ተቀበሉና በተቀበሉት መመሪያ መሠረት ይህ ደብዳቤ እንደ ተጻፈ ከደብዳቤው መረዳት የተቻለ ሲሆን፣ በቅዱስነታቸው መመሪያ መሠረት “የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ወይይቶች ከተደረጉ በኋላ አግባቡን ጠብቀን ይቅርታ ለሚጠየቅባቸው ጉዳዮች ሁሉ ይቅርታ” እንጠይቃለን ይላል፡፡ የማቅ አመራሮች ከፓትርያርኩ ጋር እንዲነጋገሩ ያደረጉት የፈደራል ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ሲሆኑ፣ በንግግሩ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ መሆኑን እንደገለጹና ይቅርታም እንዲጠይቅ ማድረጋቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ይቅርታውን ለመጠየቅ ግን ግፊቱ ከውጪ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ የማኅበሩ አንዳንድ አመራሮችና አባላት “ጥፋት ተፈጽሟልና ይቅርታ ልንጠይቅ ይገባል” ሲሉ ሐሳብ ማቅረባቸውና በዚህ የተነሣም ክፍፍል ተፈጥሮ የነበረ መሆኑን ምንጮች ያስታውሳሉ፡፡  

የማኅበሩ ይቅርታ እጅግ የዘገየ ቢሆንም “ተደራድሬ ነው ይቅርታ የጠየቅሁት” የሚለው እንዲመዘገብለት በመፈለግ ዓይነት የቀረበ ስለሚመስል ልባዊነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ነገሮችን እኔ ባቀረብኩት የመደራደሪያ ሐሳብ መሠረት ነው ያስፈጸምኩት የሚል አንድምታ ያለው ነው፡፡ ለምን ቢባል ከመጀመሪያው ጀምሮ እንነጋገርና ጥፋተኛ ሆኔ ከተገኘሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ ነበር ያለው፡፡ ሆኖም ግን ይቅርታ መጠየቁ ጥፋተኛነቱን ማመኑን ያሳያልና ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ፓትርያርኩ እንደማኅበሩ ግትር ሳይሆኑ በአባትነታቸው ማኅበሩን ማነጋገራቸው የሚያስመሰግናቸው ነው፡፡ ትሕትና መሸነፍ ለሚመስለው ለማቅም ይህ ትልቅ ትምህርት የሚሆነው ነው፡፡ ጥፋቱን ማመኑና ይቅርታ መጠየቁ ላይቀር እስካሁን ማንገራገሩ ራሱን ትዝብት ላይ ጣለ እንጂ ማንንም አልጎዳም፡፡  

አሁን ትልቁ ጥያቄ የማቅ ይቅርታ እርሱ እንዳለው “ከልብ” ነወይ የሚለው ነው፡፡ ሰው ይቅርታ የሚጠይቀው ላለፈው ብቻ ሳይሆን በቀጣይም በተቻለው መጠን ላለመበደል በመወሰንም ነው፡፡ “ለዘኀለፈ ስርየት ወለዘይመጽእ ዕቅበት” አይደል የሚባለው? ማቅ ግን በአንድ በኩል ይቅርታ ለመጠየቅ ከቅዱስነትዎ ጋር ልነጋገር እያለ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እንዲህ ያደረጉኝ እርሳቸው ናቸውና የእርሳቸውን ስልጣን ለመሸርሸር እንደራሴ ማሾም አለብኝ ብሎ በደጋፊ ጳጳሳቱ በኩል በቅዱስነታቸው ላይ እንደራሴ ለማሾም በማቀድ ከፍተኛ በጀት መድቦ ደጋፊ ጳጳሳቱ አጀንዳ አድርገው እንዲያቀርቡለት ሲያደርግ ነበር የቆየው፡፡ አጀንዳውን ለሲኖዶሱ ስበሰባ ያቀረቡት ጳጳሳትም በአብዛኛው የማቅ ደጋፊ በመሆን የሚታወቁ ናቸው፡፡ በዕቅዱ መሠረትም ሲኖዶሱን ሲያስበጠብጥ መሰንበቱ የሚታወስ ነው፡፡

ይህን የምንለው ከሜዳ ተነሥተን አይደለም፡፡ አጀንዳው የማቅ ለመሆኑ በቂ ጠቋሚዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የማቅ ደጋፊ የሆኑት አባ ቀውስ ጦስ በሰሞኑ ስብሰባ ላይ “አጀንዳው ተግባራዊ ካልሆነ እስከ መወጋገዝ ልንሄድ እንችላለን” ብለው ማስፈራራታቸው ይጠቀሳል፡፡ እውን ይህ አጀንዳ ተቀባይነት ማጣቱ ወደመወጋገዝ ይመራል ወይ? ጳጳሱ በትንሽ በትልቁ ለውግዘት ምን ያህል ችኩልና ወፈገዝት እንደሆኑ የሚያሳይ ሲሆን እንደእነዚህ ባሉት አንዳንድ ጳጳሳት ቤተክርስቲያኒቱ የምትመራ መሆኗ ግን በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ ጳጳሱ ይህን ጉዳይ እንወጋገዝበታለን ማለታቸው ግን ዝም ብሎ የተባለ አይደለም፡፡ ማቅ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የመክፈል አደጋ መጋረጡን ቅዱስነታቸው ከዚህ ቀደም ያነሱትን ሐሳብ ይበልጥ የሚያጎላ ነው ይላሉ ታዛቢዎች፡፡

ጉዳዩን በአንዳንድ ጥያቄዎች ስንፈትሽ አጀንዳው የማቅ ለመሆኑ በቂ ምልክቶችን እናገኛለን፡፡ ከሁሉ በፊት አሁን ባሉበት ሁኔታ ፓትርያርኩ እንደራሴ ያስፈልጋቸዋል የተባለው ለምንድነው? እርሳቸው እንደራሴ ያስፈልገኛል አሉ? ጠቅላይ ቤተ ክህነቱስ ሥራቸውን መሥራት አለመቻላቸውንና እንደራሴ ማስፈለጉን አምኖበታል ወይ? ካመነበትስ ማስረጃዎቹ ምንድናቸው? አጀንዳውን ያቀረቡት ጳጳሳትስ ከምን ተነሥተው ነው እንደራሴ ያስፈልጋቸዋል ያሉት? በፓትርያርኩ በኩል እነርሱ ላይ ወይም ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰ ችግር አለ ወይ? እነርሱ ምን ሆኑ? ፓትርያርኩስ ምን አደረጓቸው? ቢባል ሊቀርብ የሚችል አንድም በቂና ውሃ የሚያነሳ ምክንያት የለም፡፡ ፓትርያርኩ አንድ ያደረጉት ነገር በዘመነ ፕትርክናቸው ቤተ ክርስቲያን (በማቅ አደገኛ አካሄድ) ለሁለት ስትከፈል ማየት አልችልም፡፡ እንዲሁም ቤተክርስቲያንን ከቅኝ ገዢ (ማቅ) ነጻ ማውጣት አለብን ማለታቸውና ያ እንዳይሆን መንቀሳቀሳቸው ነው፡፡ ስለዚህ አጀንዳው የማቅ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡  ሁሉ የሚያውቀው ግን ፓትርያርኩ በቢሮአቸውም ሆነ ከዚያ ውጪ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ ሥራቸውን በብቃት እየተወጡ መሆኑን ነው፡፡ ማቅ ይቅርታ እንዲጠይቅ ጥብቅ መመሪያ መስጠታቸውና ቢዘገይም እንኳ የማታ ማታ ይቅርታ መጠየቁ የአመራራቸውን ጥብቅነትና ቆራጥነት የሚያሳይ አንድ ትልቅ ተግባር ነው፡፡

ማቅ አለልማዱ ለአፉም ቢሆን ይቅርታ ቢጠይቅም ይቅርታውን የጠየቀው ካስቀመጠው የእንወያይ ጥያቄ አንጻር ይቅርታ መጠየቅ ካለበት ጊዜ እጅግ ዘግይቶና ታግዶ የቆየው አውደ ርእይ ለሁለተኛ ጊዜ ሊከፈት አንድ ቀን ሲቀረው ነው፡፡ ይህም ምናልባት አውደ ርእዩ ዳግም እንዳይታገድበት ከነበረው ሥጋት የሚመነጭ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ 

29 comments:

 1. አጥንትህ ይሰበር ምኑ ነው ሰበር ዜና ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስድብ የሚመንጨው ከሰይጣንና ከሰይጣን ልጅ ነው:: የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ካልክ አትሳደብ::
   አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ:: ቆላ 3:8

   Delete
  2. ወደው አይስቁ አለ ምን አጥንቱ ብቻ አይምሮውም የተሰበር ስለሆን እኮ ነው ትሃድሶ የሆነው አጥንትስ ይጠገናል

   Delete
 2. ኢግዚብሽኑ እንዳይታገድበት በመፍራትም ቢሆን ማኅበርዋ ይቅርታ መጠየቅዋ ትንሽ ትንሽ አስተዋይነት ወደ ማኅበርዋ መንደር እየገባ መሆኑን ያመለክተናል። ጥሩ ነው።

  ReplyDelete
 3. ማቅ ምነው ይቺን ነገር ሳትነግሪን ቀረሽ ይቅርታው ኢግዚብሽኑ እንዳይታገድ ከመፍራት እንጂ ከልብ አይደለም ማለት ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምን አለበት ለአላማ እኮ አይደለም መልካሙን ነገር ይቅርታ መጠየቅ ሰው ይገደል

   Delete
 4. ይሄ ትዕቢተኛና አጉራ ዘለል ማህበር በመጨረሻም ቢሆን ጥፋን አምኖ ይቅርታ መጠየቁ ጥሩ ነዉ፡፡ አሁንም ቢሆን ልካቸዉን አዉቀዉና ርቀታቸዉን ጠብቀዉ
  ቢጓዙ መልካም ነዉ፡፡ ከእኛ ወዲያ ሃይማተኛ ላሳር በሚል ግትር አቋም ሰዎችን
  ጥላሸት ከመቀባትና ከማሳደድ መታቀብ አለበት፡፡

  በመጀመሪያ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን ማቅ ሳይፈጠር ነበረች ወደፊትም ትኖራለች፡፡ አጉል ትዕቢትና ግብዝነት ለማህበሩም አይበጀዉም፡፡ ስሙን የሚገልጥ ስራ መስራት ከፈለገ
  በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ መሰረት ብጹአን አባቶችን አክብሮና ታዛዥ ሆኖ ሊንቀሳቀስ
  ይገባዋል፡፡

  ReplyDelete
 5. ቂ…ቂ…ቂ..ቂ አይ ሠላማ ይሄ ኤግዚቢሽን እንደ እቶን እሳት አቃጥሎ…. አቃጥሎ.. አቃጥሎ ሊጥልሽ ነው፡፡ ምን ብለሽ እንደምትጽፊ ግራ ገባሽ…. አባትን ይቅርታ መጠየቅ ለሃይማኖት ሰው እንጂ ድሮስ ለመናፍቅ መች ትልቅነት ይመስለዋል፡፡

  ReplyDelete
 6. ይቅርታ መጠየቅ የብልሆችና የአስተዋዮች ክርስቲያኖች ምርጫ ነው፥
  ደግሞም መጻህፉ ተበድላችሁም ይቅር በሉ ይላል ፣ እግዚአብሔር የይቅርታ አምላክ ነውና፣ ለናንተም የነሱን የይቅርታ ልቦና ይስጣችው፣
  አምላክ የማህበሩን ቅን አገልግሎት ይባርክ!

  ReplyDelete
 7. ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ራስ የሆኑትን ፓትሪያርክ ይቅርታ ቢጠይቅ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረና ጮቤ አስረገጣችሁ!? ማኅበሩ እናንተ ለምትነዙት አሉባልታና ክስ ጊዜ ስለሌለው እየሰራ ያለውን ሥራ ሄዳችሁ ኤግዚቢሽን ማዕከል ጎብኙ! በታሪኩም በተግባር እንጂ ድጋፍ በማሰባሰብ ፈተናዎችን አልፎ እዚህ አልደረሰም! እንናንተ እንደምትሉት አባቶችን በርካሽ ቃላት ማብጠልጠል ሳይሆን አባቴቿ የተከበሩባት ቤተ ክርስቲያንን ለማየት እየተጋ ነው፣ በዚህም ላለፉት 24 ዓመታት አሉባልተኞች የሚጋርጡበትን እንቅፋቶች ሁሉ አልፎ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን አንገት የሚያስደፋ ልጆቿን ግን የሚያኮራ ተግባራትን ተፈጽሟል፤ ገና ብዙም ይሰራል! ለዚህ ሁሉ ደግሞ ትልቁ መሳሪያው የቅዱሳን አባቶች ፀሎት እንጁ ሌላ ምንም አይደለም!!!
  አምላከ ቅዱሳን ማኅበራችንን ይባርክልን!!!

  ReplyDelete
 8. ከተርጓምያን ሊቃውንት የአተረጓጎም ስልት ሳይቀስሙ መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም መሞከር “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ “ እንደሚባለው ይሆናል፡፡የተሳሳተ ትርጉም የሚመጣው ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ያለ መሪ ወደ ሩቅ ቦታ የሚሄዱ ማየት የተሳናቸው ሰዎች እሾህ ላይና ድንጋይ ላይ መውደቃቸው አይቀሬ ነው፡፡መጽሐፍቅዱስንም ያለተርጓሚ ያለ መምህር ያነበቡት ሁሉ እንድፍላጎታቸው እንደየስሜታቸው እንደየአመለካከታቸው እንደመሰላቸው ከተረጎሙት መሰረታዊ የትርጓሜው ትምህርት ሣይኖራቸው ከመሬት ተነስተው ከገለጽት በንባብ ዳጥ ተንሸራተው ወደ ስህተት ጉድጓድ መግባታቸው አይቀርም፡፡

  የእያንዳንዱ ሰው ግንዛቤ የተለያየ ነውና፡ እንደ መልኩ ፤እንደ ቁመቱ፤እንደቅርጹ፤እንደ ድምጽ፤ሐሳቡና አሰተያየቱም ይለያያል፡፡ መጽሐፍቅዱስን እያንዳንዱ ሰው እንደ አመለካከቱ ከገለጸው በኤፌ4፤4 የ ቅዱስ ጳውሎስ አንዲት ሃይማኖት የሚለው አነጋገር ይዛባል፡፡ያለትርጓሜም የመጽሐፍ ቅዱስን ሐሳብ ለመጨበጥ መከጀል ጤፍን ሳይፈጭ ፤ሳይቦካ፡ሳይጋገር ለምግብነት እንደማቅረብ ይቆጠራል፡፡የመጽሐፍ ቅዱስን መልክዓ ምድር ሳያጠኑ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የሚሄዱበትን ሳያውቁ ታክሲ መሳፈር ማለት ነው፡፡መጽሐፍ ቅዱስን በተሻለ መልኩ ለመረዳት ሰባት ነገሮች አስፈላጊ ናቸው፡፡የመጽሐፍ ቅዱስ መልክዓ ምድር ፤የመጽሐፍ ቅዱስ ሕዝቦችታሪክ፤፤የመጽሐፍ ቅዱስ ሕዝቦችባህል፤፤በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እንሰሳትጥናት፤በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ዕጽዋትጥናት፤በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ማዕድናትጥናት፤እና መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈባቸው የመጀመሪዎቹ ቋንቋዎች ጥናት ናቸው፡፡

  የመጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢር እንደ ድንች ና እንደ ካሮት ተቆፍሮ የሚወጣ እንጂ እንደ በቆሎ ፍሬ ለመንገደኛው ሁሉ የሚታይ አይደለም፡፡ስለዚህ በጥልቀት የ ሚቆፍር ጠንካራ የአዕምሮ ጡንቻ ያለው ቆፋሪ ያሰፈልጋል፡፡የተወሰኑት ፡የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ብዙ ምስጢርን አምቀው የያዙ ስለሆኑ በቀጥታ አይፈቱም ውስጠ -ትርጉም አላቸው ማለት ነው፡፡ በተለይም በምሳሌዊ አነጋገር የተገለጽት ፡የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትና ራእይ ነክ ወይም ትንቢት ነክ የሆኑ ፡የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባት የተሸከሙት ምሥጢር በቀላሉ አይገኝም፡፡ እንደ ወራጅ ወንዝ ውኃ(እንደ አባይ ውኃ ሁሉም )የሚቀዳው አይደለም፡፡ታዳ በሰው ፍቃድ ያልመጣውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከትርጓሜ አዋቂዎች ጠጋ ብለን ልንረዳ አይገባንምን?እንኳን እኛ የቅጅ ቅጅ የደረሰን ጌታም በመካከላቸው ተገኝቶ ያሰተማራቸው ሐዋርያትም ሲከብዳቸው ተርጉምልን በማለት ጥያቄ ያቀርቡ ነበር፡፡ ጌታም ይተረጉምላቸው ነበር፡፡ማቴ13›;36-43፤1 5;15-20
  መጽሐፈ ኢሳይያስን ሲያነብ የነበረው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባው ም ፊልጶስ “የምታነበውን ታስታውለዋለህን ?ብሎ በጠየቀው ጊዜ የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል የሚል መልስ ነው የሰጠው፡፡የሚተረጉምልኝ ሳይኖር እንዴት ላውቀው እችላለሁ ማለቱ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እንዲተረጉምለት ፊልጶስን ጠየቀው ፊልጶስም ተረጎመለት፡፡ሐዋ.ሥራ8፡26-40 ወገኖቼ ከአባቶቻችን እግር ሥር ቁጭ ብለን እንማር “መማር የበሽታዎች ሁሉ መደኃኒት ነውና፤የችግሮችም መፍትሔ ነው̋ እንዳሉ አቡነ ሽኖዳ፡፡ በዚህ በ21ኛ ው ክ/ዘ መን ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች የአጭር ጊዜ እቅዳቸው መብላት መጠጣት የረጅም ጊዜ እቅዳቸው ደግሞ መሞት ነው፡

  ፡ዛሬ በአለማችን የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ነን የሚሉ ሰዎች በዝተዋል፡፡ ከመብዛታቸውም የተነሳ ትውልዱ ትክክለኛው የቱ ነው? በሚል ግራ እየተጋባ ነው፡፡ ይኸውም ሃይማኖታቸውን ከእውነተኞቹ የመጽሐፍቅዱስ መምህራን ባለመማራቸው ነው ግራ የተጋቡት ታዳያ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ለማጥፋት ነው በጎቿን ሰብስባ ጉባኤ ዘርግታ በየቦታው የምታስተምረው ፡፡ ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን ማስተማር የሚገባቸው እነማን ናቸው?መጽሐፍ ቅዱስን የተሸከሙት ሁሉ ናቸው? ጥቅስ የጠቀሱት ሁሉ ናቸው?እነማን ያስተምሩ?መልሱን ለአንባቢያ ትቸዋለሁ ለነገሩ አሁንማ ጸሎተ ሃይማኖት ን እንኳን በሥርዓት ሳይማሩም መጋቢ ሐዲስ እየተባሉ አይደለም ምን ይደንቀናል ፡፡ምንም ያልተማረን ሰው መጋቢ ሐዲስ ማለት በቤተ ክርስቲያን ላይ እሳት ማንደድና ክብሪት መለኮስ እኮ ነው፡፡.......temirete yasefelegachewale lememare lebonachewen kefetooooo

  ReplyDelete
 9. አያችሁ የልጅነት ወጉ ይህ ነው፡፡ አሁን ምድረ ተሃድሶ ሁላ ተንጫጪ ማህበሩ ከክርስትና ሚጠበቅ ትልቅ ስራ ሰርቷል ….ያውም ይቅርታ…. ምክንያቱም እንኳን የበደልነውን የበደሉንን ይቅር እንድንል ጌታችን አስተምሮናልና፡፡ እንግዲህ እላችኋለሁ እናንተም የደላችኋት ቤ/ንን ይቅርታ ጠይቃችሁ ተመለሱ፡፡ በተለይ ማህበረ ቅዱሳን አውደ ርዕዩን እንደሚያሳይ ቀን ከተቆረጠ ጀምሮ የምታወጧቸው መጣጥፎች ሁሉ የምቀኝነትና ባልበላውም ጭሬ ላጥፋው አይነት ግርግር አስመሰለባቸሁሳ፡፡

  ReplyDelete
 10. የይቅርታና የሰላም ተቃዋሚዎች!!!

  ReplyDelete
 11. በምንም ይሁን በምን ከማቅ እፍ ይቅርታ የሚለዉ ቃል መዉጣቱ በራሱ ትልቅ ነገር ነዉ

  ReplyDelete
 12. ማህበረ ቅዱሳን ማለት የዳቢሎስ ተላላኪ ነው። እስቲ ከነሱ ዶክተር ሁኖ አክሞ ያዳነ፡ ኢንጅነር ሁኖ አገር የገነባ፡ ፈላስፋ ሁኖ ለሀገሩ የጠቀመ፡ ኢኮኖሚስት ሁኖ ሀገርንና ወገኑን የጠቀመ። አንድም የለም። ከማዳን መግደል፡ ከመገንባት ማፍረስ፡ ከመቆጠብ ማዉደም፡ የሚወዱ ሀገር በቀል የሀገር ጠላቶች ናቸው ። እነሱን በመደገፍ በገንዘብና በሆዳችሁ ተገዝታችሁ ቤተ ክርስቲያናት አሳልፋችሁ የምትሰጡ፡ እርግማን ከቤታችሁ አይውጣ። እግዚአብሄር በኪነጥበቡ ይፋረዳችሁ ኢትዮጵያ ትፋረዳችሁ።አምላከ እስራኤል ይፍረድ። የ አርባ ሚሊዮን ክርስቲያን አምላክ ፍርድ ይስጥ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውቀት ካለበት ገብታችሁ የማታውቁ ጨዋ መሐይም ሁላ የምሁራኑ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና መቆም አንገበገባችሁ አይደል አይዟችሁ ኋላ ዋጋችሁን ታገኛላችሁ፡፡ ከመንፈሳዊ ዕውቀት አይሏችሁ የትኛው ማስመስከሪያ ገብታችሁ ተማራችሁና? ከዘመናዊው ዕውቀት አይሏችሁ አቅም የለ ችሎታ የለ ዩኒርስቲም ለመግባት? ብቻ ወሬ ወሬ ወሬ...የቤተ ክርስቲያን አምላክ ፣ የሊቃውንቱ የነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምላክ...እንዲህ መሰላችሁ እንዴ...ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመናዊ ትምህርት ፍልስፍና የተማረ ሊቅ ነበር ...እናም መሐይምነት ሳይቀብራችሁ አላዋቂ መሆናችሁን አውቃችሁ ብትማሩ...

   Delete
 13. le kifu alamaw mk hulun yaderegal edtebalew yekiretawe yemiasegegnelet tekim selal enji amenobet ayemeselegnem demo yekerta be were becha selalehon wedefit mk ne enayewalen

  ReplyDelete
 14. ማህበረ ቅዱሳን የት ላይ የቅዱሳንን ስስራየሰሩት፡ የት ነው ሀኪም ሆነው ሰው ያዳኑ፡ የት ነው ሀገር የገነቡ፡ የት ነዉ ለቤተክርስቲያን የቆሙ። እስቲ ንገሩን፡ አባቶች ይች አለም ሀላፊ ናት የታሪክ ተጠቃሚ እንጂ ተጠያቂ ባትሆኑ ይሻላል የኢትዮጵያ አምላክ ይፋረዳቸዋል። በቤተክርስቲያኗ እርግማን በዛ ሰቆቃ በዛ ለዚህ ሁሉ ምክንያት ማቅና የማቅ ተላላኪ ጳጳሳት ናቸው ።አምላከ እስራኤል ይፍረድ።

  ReplyDelete
 15. Ke kerestiyan yemitebek new Yekereta

  ReplyDelete
 16. Wow Mk endih kerestenan betegebar sdayachehun

  ReplyDelete
 17. ማኅበረ ቅዱሳን ሆይ እንወድሃለን!! ማኅበረ ቅዱሳን ሆይ እናመሰግናለን!!!

  *የፖለቲካ አራማጅ ነው ስትባል... የዓለም ጫጫታ ሳይለያየን ሁላችንም ለቤተ ክርስቲያን እንነሣ ብለህ ጠራኻን!

  *አባቶችን ይሳደባል ስትባል ... እንዲህ የሊቃውንቱን ሕይወትና ክብር በግልፅ መስክረህ አሳየኸን!

  *ቤተ ክርስቲያንን ለመውረስ ይፈልጋል ስትባል...ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ በላይ መሆኗንና ሁሉም ለርሷ ታዛዥ መሆኑን ገለፅክልን!

  *ሊዘጋ ነው ስትባል ... ከ100,000 ሰው በላይ ጠርተህ ስለ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ትመሰክራለህ!

  *ማኅበረ ቅዱሳን ሆይ ይበልጥ ቤተ ክርስቲያንን እንድናውቃትና እንድንቀርባት፣ በኦርቶዶክሳዊነታችን እንድንኮራም ስላደረከን እናመሰግንሃለ!!!

  እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚተጉና የሚቆሙ እውነተኛ ማኅበራትን ያብዛልን!

  (ፌስቡክ ላይ አገኘሁትና ደስስ አለኝ እናንተም እንደኔ አንብቡት .እንግዲህ ምን ትሆኑ ምን ታወሩ ለወሬ ግዜ የለው ማህበረ ቅዱሳን እናንተ ምን ሃሳብ አለባቹህ። አታስቀድሱ አትቀድሱ ማህሌት የለ ሰአታት የለ የገዳማት ጉዳይ አይጨንቃቹህ ስለ አብነት ት/ት ቤት ጉዳያቹህ አይደል ።የተሰፋ ቆብ እ ተረተራቹህ ስፉ ።ዝንብ ቢሰበሰብ ወጭት አይከፍትም አሉ ዝንብ ይመስል ቆሻሻ የሆነ ስድብ ይናፍቃቹሃል።

  ReplyDelete
 18. ተሐድሶ መናፍቃንና በቤተ ክ/ን ውስጥ ተመስገው በገንዘብዋ አላግባብ የበለጸጉ አካላት ማህበረ ቅዱሳን ያጋልጠናል በሚል ለመቅደም& በተቀደደ መጋረጃ ግብራችሁን ለመሸፈን ብዙ ደከማችሁ ነገር ግን ብጹዕ ወቅዱስንና አገልግሎቱን የሚያውቁለትን ማህበር ለማራራቅ ብዙ ተጋችሁ፡፡ አልተሳካላችሁም! እንደለመዳችሁት የሚቀራችሁ ነገር ፓትርያርኩ መደለያ ገንዘብ ከማህበሩ ተቀብለው ነው የሚል ነው፡፡ የተንሸዋረረ የእምነት ዕይታችሁንና ግብራችሁን ሲረዱት ማህበሩ ከእሳቸው ጋር እንዲሰራ የበለጠ ያቀርቡታል፡፡

  ReplyDelete
 19. mahebru tilk sira ly nw enante yeseyetan kurachoch ...betkrestiyan mechem ende indian atehonm eshi gebahe amasagnuuuuuuuuuuuuuuuuu!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 20. ወዳጆቹ እንደሆኑ ተው ተመለስ አይሉትም ይቅርታም ጠይቅ ሲሉ አልሰማንም ጎበዝ ጎበዝ እኒህ ስጳጳስ ስራ አያሰሩም ሊያፈርሱን ነው ተሀድሶ ናቸው በርታ እንዳትበገርላቸው ጎሽ የኔ ጎረምሳ አንተ ባትኖር ኖሮ ቤተክርስቲያን ትፈርስ ነበር 2ሺ ዘመናት ሁሉ በ20 አመት በታሳቢነት ስንጠብቃት ነበር በርታ አድርግ የተጻፈ መረጃ ተገኘባቸው ታድሶ መሆናቸው ሲሉ ቆተው የህያ ባል ከጅብ አያስጥል ተሳዳቢ ፍንዳታ ሁላ አሁን ደግሞ ጎሽ እንኩአን ይቅርታ ጠየክ ይሉሀል ጠላቶችህ ተናደዱ ማንም ለማንም ጠላት አይደለም ዳቢሎስ ነው ለሰው ልጅ ጠላቱ አሉ ወሬ ተዉ በቤተክርስቲያን አትቀልዱ ተሸፋፍኖ መኖር አይቻልም ትገልጦባችኋልና ሴራው ቤተክርስቲንን በበላነት ለመምራት አስባችሁ ነበር ግን ቦታችሁን ደረጃችሁን አላወቃችሁም አሁንም ልብያለው ልብያድርግ ወደ መስመሩ ካልግባችሁ ዋጋ ትከፍላላችሁ በአጉራ ዘለልነት ቤተ ክርስቲያን አትታመስም ባለቤት አላት ጠባቂዋ አያንቀላፋም
  እግዚብሄር ሆይ ቤተክርስቲያንና ህዝቧን ጠብቅ!!!!! አሜን!!!!!

  ReplyDelete
 21. ዘይገርም ያኔ የት ነበር አሁን ሚጠይቀው ይሄ ኮ ግልፅ ነው ሌላ ያሰበው ተንኮል አለ ማለት ነው እኔ ሚገርመኝ የማቅ ማህበር አድማቂና አድናቂዎች ናቸው

  ReplyDelete
 22. hulunim bayinachin silayen litwaashen atimokir mk sirawun eyesera new ante gin awura

  ReplyDelete
 23. Burnt. Pente burnt like devil.

  ReplyDelete
 24. በጣም የሚገርም ነው!! እኔ አንድ ተራ ምዕመን ነኝ፡፡ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ብዙም ዕውቀቱ የለኝም ነበር ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ ስከታተል በአንዳንድ አካላት ምናልባትም በተሃድሶዎች ሊሆን ይችላል የሚጻፉት ጽሁፎች ማህበረ ቅዱሳንን እንደ አንድ ትልቅ ልዕለ ሃያል ሃገር አድርገው ሲርበደበዱ አያለሁና በጣም እገረማለሁ፡፡ ምን ይሆን የሚያስፈራቸው ብየ ሳስብ ትንሽ እውነት ይዘው ስለሚፈራገጡ ማህበረ ቅዱሳን በሃያል ክንዱ ስለሚደቁሳቸው የሚፈጠርባቸው ስሜት እየመሰለኝ ነው፡፡ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በስበከተ ወንጌሉ… ወዘተ የበላነቱን አምነው የተቀበሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲያወም የስለላ አቅሙን ስትገልጹ ከ ሲአይኤ፣ ሞሳድ፣ ኬጂቢ…ወዘተ ሁሉ የላቀ አድርጋችሁ ነው፡፡ በጣም እየተገረምኩ ነው ለካ ማህበረ ቅዱሳን እንዲህ ትልቅ አቅም አለው? በሃገራችን እንዲህ አይነትጀግና ድርጅት መፈጠሩን አሁን ነው የተረዳሁት፡፡ የዚህ አኩሪ ተጋዳይ ድርጅት አባል መሆንን በፍጹም ልቤ ናፈኩት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በለው! በለው! በለው!!
   እንዴት ነው ባክህ ያጋነንሀው !ማቅ አንተ በልብህ እንደቀረጽሀው በህሊናህም እንደሳልሀው ሳይሆን ከገለባ የቀለለ ፍሬ የማያፈራ ለምንም የማይጠቅም ሙሰኞችና የንዋይ ፍቅር ያለባቸው ትቂቶች የሚበለጽጉበት ብዙዎችን የሚዘረፍ ብዙዎችንም ላመጽና ለብጥብጥ ለጥላቻ የሚያሰማራ ከፋፋይ መንፈስ ያለበት የወንጌል ጠላት የዲያቢሎስ ወኪል የክርሰቶስ ተቃዋሚ ማህበር ነው፡፡ይህ ማለት ግን በየዋህነት በስሩ ያሉ ተራ አባላት ማህበሩ እራሱን አግዝፎ የቅዱሳን ማህበር እንደሚለው ቅዱስ መሰሎዋቸው በየዋህነት ጉለበትና ገነዘባቸውን የሚዘረፉ ለአኩይ አላማው የሚጠቀምባችው ገለሰቦች የሉም ማለት አይደለም፡፡እኔም ካመታት በፊት እወነት መሰሎኝ የዚህ የሙት ማህበር አንዱ አባላ ነብረሁና፡፡
   ማህበሩ በክርሰቶስ የሆነልንን ወንጌል እንዳይሰበክ ይልቁንስ ወደ ሲወል የሚያወርድን ተረትና ኑፋቄን የሚዘራ የጽድቅ ጠላት ነው፡፡
   የሚያሳዝነው ብዙዎች ለዚህ የዲያቢሎስ ማሀበር ሰለባ መሆናቸው ነው፡፡የኛ …እኛ… በሚል የትቢት መንፍስ ራሳቸውን አግዝፈወ ባዶ መሆናቸውን ሳያውቁ ያወቁ እየመሰላቸው ስንቶቸን ባለማወቅ ወግተው ገደሉ፡፡እግዚያብሄር የፍቀር አምላክ ነውና አሁንም በምሀረቱ ከርሰቶስ ወደሞተለት ሃዋረያትም ወደሰበኩት የደህንነት ወንጌል ፊታቸውን ዘወር እንዲያደርጉ ይርዳቸው፡፡   Delete