Monday, May 30, 2016

አርባ ሦስተኛው የስደተኛው ሲኖዶስ ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት።በስያትል ክብረ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ከረቡዕ 25/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው ቅዱስ ሲኖዶስ ከሁሉም ስብሰባዎች በሰላም እና በአንድነት የተከናወነ እንደነበር የደረሰን ሪፖርት ያመለክታል። ቅዱስ ሲኖዶስ በዋናነት በሚከተሉት አጀንዳዎች ተዋያይቷል። በኢየሩሳሌም ስለተቋቋመው የሁለቱ ሲኖዶሶች የእርቅ ኮሚቴ ተዋያይቶ የሰላሙ በር ክፍት መሆኑን አጽድቆ የሚደራደሩ ሰዎችን ለመምረጥ ወስኗል። በሲኖዶሱ ስር ያሉ ካህናት የሚያካሂዱት የስድስት ወር ጉባኤ ደካማ ጎኑ ተገምግሟል እርሱም ተመሳሳይ መምህራንና ተደጋጋሚ ትምህርት መሰጠቱ ሲሆን ጠንካራ ጎኑ ደግሞ ካህናት መገናኘታቸውና በሃይማኖት ጉዳይ ላይ መወያየታቸው አንዳንድ ርምጃዎችን በጋራ ለመውሰድ የሚያስችል መሆኑ ነው። በዚህ የካህናት ጉባኤ ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ይዛ የቆየችውና መታረም ወይም መቀጠል ያለባቸው ልማዶችና የስሕተት ትምህርቶች የሚገመገሙበት ታላቅ የትምህርት ጊዜ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ይህ ጉባኤ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ወስኗል።

   የሊቃውንት ጉባኤው ባቀረበው ሪፖርት መነሻነት ዘመኑን የዋጀ ወጥ የሆነ የትምህርተ ሃይማኖት የሥርዓት  መጻሕፍት እንዲዘጋጅ ተወስኗል። አንድ ሊቀ ጳጳስ መጻሕፍት በተጻፉ ቁጥር ጴንጤ እና ተሃድሶ እየተባልን መግቢያና መውጫ አተናልና አርፈን እንቀመጥ ሲሉ ተማጽነዋል። ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ግን በጣም ተገርመው መጻሕፍት ይጻፉ አዲስ ነገርም ካለ እንወቀው የተሠወረ ካለም ይገለጥ በማለት የተለመደ ማበረታታቸውን አሳይተዋል። አቡነ መልከ ጼዴቅ በቤተ ክርስቲያን መወሰድ ያለባቸውን መንፈሳዊ እርምጃዎች ሁሉ ያለ ፍርሐት እውነትነቱን ሳይለቅ መወሰድ እንዳለበት ገልጠዋል። 

  ሳምንታዊ የስልክ ኮንፈረንስን በተመለከተ በተነሣው አጀንዳ ላይ በየሚድያው ለሚሰጡ የስሕተት ትምህርቶች  ተገቢ መልስ እንዲሰጥባቸው የተወሰነ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ የታምረ ማርያም ጉዳይ ተነስቶ ነበር። ታምረ ማርያም የተባለው መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያንን እየረበሸ ትውልድን እየከፋፈለ መሆኑ ይታወቃል መጋቤ ሐዲስ መምህር ልዑለ ቃል አትላንታ ቅዱስ ገብርኤል ባስተማረው ትምህርት ላይ ታምረ ማርያም ችግር ያለበት መጽሐፍ መሆኑን ገልጦ መናገሩ ይታወሳል። በዚህ የሲኖዶስ ጉባኤ ላይም በ1987 ዓ.ም የታተመው ታምረ ማርያም እመቤታችን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡኑ ጳውሎስ ተገልጣ መታየቷን የሚተርከው ታሪክ ከእውነት የራቀና መታረም ያለበት መሆኑ ታምኖበታል። አንድ ሊቀ ጳጳስ ግን ነገሩን አታጩሁት እኛ ውስጥ ለውስጥ እናርማዋለን በማለት ከሕዝብ የሚመጣውን ቁጣ በስውር ለማለፍ ተማጽነዋል። 

ከጥንት ከአባ እስጢፋኖስ ጀምሮ ታምረ ማርያም ተቃዉሞ የገጠመው መጽሐፍ መሆኑና በዚህም ብዙ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ተሰደውና ተገልለው የኖሩበት አደገኛ ክህደት ያለው መጽሐፍ ነው። አሁን የሠአጼ ቴዎድሮስን ክብር ዝቅ እያደረገ እነ አጼ ሚኒልክን እየነካካ አባ ጳውሎስን የሚያጸድቅ ታሪክ ስለ ተጨመረበት ታምረ ማርያም ጥያቄ ውስጥ መግባቱ የሚያስገርም ነው። ድንግል ማርያም የመሐመድን ብልት ይዛ መጣች፣ ሰዶምና ገሞራን ያጠፋች ድንግል ማርያም ናት፣ ጳውሎስን ሐዋርያ ያደረገችው ድንግል ማርያም ናት፤ ዮሐንስ አፈወርቅን አፈወርቅ ብላ የሰየመችው የሴት አፈ ማህፀን (ብልት) በመሳሙ ነው እያለ የሚዘባርቀው ታምረ ማርያም እስከ ዛሬ ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስን ስፍራ ወርሶ መኖሩ ይታወቃል።
   እስከሚመጣው የጥቅምት ሲኖዶስ ድረስ በሲኖዶሱ ሥር ያሉ ወደ 80 የሚጠጉ አብያተ ክርስቲያናት አመሠራረታቸውና ታሪካቸው ተጽፎ እንዲቀርብ ተወስኗል። በመቀጠልም የኢጲስ ቆጶሳትን ሹመት በተመለከተ ስምንት ቆሞሳት ተመርጠው የተዘጋጁ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ሰኔ 19/2016 በኦክላንድ መካነ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በዓለ ሲመት እንዲሆን ተወስኗል። የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በዶክተር አምባቸውና አቶ ዘውገ በተባሉ ሰዎች በሚመሩ ሁለት የተለያዩ ቡድኖች ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ግን እነዚህን ሁለት ቡድኖች ሐሳባቸውን ከደብዳቤያቸው ይዘት መርምሮ የማይመለከታቸው መሆኑን በመገንዘብ በሹመቱ ቀጥሎበታል።
ካህናቱ የተሻሚዎችን ስም ለማወቅ ያቀረቡት ጥያቄ ሳይመለስ እስካሁን ድረስ በምስጢራዊነቱ ተጠብቋል። እንዲሁም ከ200 በላይ የሚሆኑ የዳላስ ሚካኤል ምእመናን በቀሲስ አንዷለም ዳግማዊ ላይ  ባቀረቡት አቤቱታ ሲኖዶሱ በቤተ ክርስቲያኑ ሁከት ሊነሣ ይችላል የሚል ሥጋት ያደረበት ሲሆን ሦስት ሽማግሌዎችን ሄደው እንዲያስተካክሉ ወስኗል። አቤቱታው ቄስ አንዷለም በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ላይ የፈጸመውን ግፍ በመቃወም የቀረበ እንደነበር ታውቋል። ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ከዳላስ ሚካኤል እንዲነሱ ደብዳቤ ከደብሩ መጻፉ የሚታወስ ሲሆን ቋሚ ሲኖዶሱ በዚያው በደብራቸው እንዲቀጥሉ የወሰነውን ውሳኔ ቅ/ሲኖዶስ አጽድቆታል።
  ባገር ቤት ስላለው ወገን በተወያየበት አጀንዳው ረሐቡን በተመለከተ ሕዝበ ክርስቲያኑ ወገናዊ እርዳታ እንዲያደርግ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ከወልቃይት ጠገዴ ተነሥቶ የኦሮምያንና የጋምቤላን ሕጻናት ጉዳይ ተመልክቷል። በዚህም መንግሥት ዜጎችን መጠበቅ ባለመቻሉና ሕዝቦችን በመከፋፈሉ እንዲሁም የሕዝቦችን መሬት በመንጠቁ ውግዘት ተላልፎበታል። የሊቢያ ሰማዕታት በየአመቱ እንዲታሰቡ እንዲሁም በተለያዩ ሀገራት በክርስትና ሃይማኖት ላይ የሚደርሰውን የአሽባሪዎች ጥቃት አጥብቆ አውግዟል።         

5 comments:

 1. ምነው ስሉ ቁጥራቸው በየግዜው መመንመን ብዙም አትዘግብም?

  ReplyDelete
 2. ማን ይሆን እንዲህ ያለ ውልግድግድ ያለ እጅ እግር የሌለው ጽሁፍ የሚጽፈው? ማቅ ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው ስለውጭ ሲኖዶስ ኮንሰርንድ መሆን የጀመረው? መቸም አንዱአለም በየፌስቡኩ ከተለጠፈው የሲኖዶሱ ስብሰባ ተሳታፊዎች ፎቶግራፍ ውስጥ ሲታጣ ገርሞን ነበር፤ መታየት ስለሚወድ ማለት ነው። እንደጣኦት ሲመለክ የነበረውን አንዱአለምን ነው። “ቄስ አንዷለም ያደረሰው ግፍ” እየተባለ የሚጻፍበት?ይገርማል መጋቢ ሃይማኖትን እንዲህ መቀለጃ ታደርጉት?ይህ ከውነት የራቀ ነው። የውሸታቸሁ ብዛት በስብሰባው ያልነበሩበትን ፓትሪያርክ የመቸ ፎቶግራፍ እንደሆነ የማይታወቅ አምጥታችሁ ለጥፋችኋል። ጸሃፊዎች ዶ/ር አንዱአለምን ቢያጽፉ ይሻላቸው ነበር። ከናዝሬት እስከ ዳላስ በጽሁፍ ስራ ነው የተካነው የተመረቀው እንዲህ ያለ ጭቃ ልጠፋ ጽሁፍ አይጽፍም ነበር። እሱ የጀመረውንና ስንት የደከመበትን የእርቅ ማፍረስ ስራ ነጠቃችሁት፤ከማቅ አታበሩት ምን ቸገርው እሱ፤ ማቅን ይዞ ገና ብዙ ይሰራል። ውርድ ከራሴ ሲባል አልሰማችሁም?

  ReplyDelete
 3. እግዚያብሄር አይነልቦናችሁን ይክፈትላችሁ ነገሩ ስምነተኛው እሺ ላይ ነው ያለነው ሊያስደንቀን አይገባም የተሃድሶ ጥርቅምቅም ሁሉ ቅዱስ አባታችን በሌሉበት ፎቶአቸውን ትለጥፋላችሁ ውሸታሞች።እናንተ ብሎ ለሃይማኖት መሪወች መጀመሪያ እናንተ ሃይማኖታችሁን ለይታችሁ እወቁ እመቤቴ ተአምር ታሳይ የዛሬን ሳቁ በገንዘብ ደልባችኋልና በውኑ አንዳችሁም ለቤተክርስቲያን ተቆርቁራችሁ ነው ወይስ በደሙ ለተገነባችው ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ወይስ የህዝበ መእመናኑ ጉዳይ የናንተ ጉዳይ ያለቀለት ነው እንደፈሪሳዊ ልብሳችሁን አሳምራችሁ አምልኩን እያላችሁ ነው እሩቅ አይደለም ጊዜው ዝምታ ወርቅ ነው ከእርሱ ቁጣ ይሰውራችሁ

  ReplyDelete
 4. እግዚዮ ማህረነ ክርስቶስ መጥፌያችሁ እየደረሰ ነው እናንተ አንድነትን የማትሰብኩ ሰአታትና ታምረ ማርያም ታምረ እየሱስ የምትቃወሙ በቅዱስ እቡነ መርቆርዮስ ስም ስውን ግራ ለማጋባት ታጥቃችሁ የተነሳችሁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ማልያ ለብሳችሁ ለእራሳችሁ ጥቅም የተሰለፋችሁ የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ፍርዱን ያሳያችሁ። ተረት ተረት አለቀ ያለፈው ይብቃችሁ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 5. His grace Abuna MelkeSdike all his life working extremely hard for EOTC, still active in his action at age of 91.

  ReplyDelete