Thursday, May 5, 2016

አባ ሳዊሮስ ከማኅበረ ቅዱሳን ጠላትነት ወደወዳጅነት እንዴት ተሸጋገሩ?ከዚህ ቀደም የፓትርያርክ ጳውሎስን ዜና ዕረፍት ተከትሎ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ ተግባራዊ ለማድረግና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር ከአባ እስጢፋ ጋር በመመሳጠር ያረቀቀውን የለውጥ መዋቅር ለመቀልበስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪዎችና ሌሎችም ሃላፊዎች በተሰበሰቡበት አባ ሳዊሮስ እንዲህ ብለው ነበር “ይህን በማየቴ በጣም ደስታ ተሰምቶኛል፤ የሚቆረቆሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አሉ ማለት ነው፡፡ የማህበሩ ሁኔታ እንደዚህ ለሁሉም ሰው ግልጽ መሆኑ የሚያስደስት ነው፡፡ እኔ በርግጥ ብቻዬን ያለሁ ነበር የመሰለኝ፡፡ እናንተን ማግኘታችን በጣም ያኮራናል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን የካህናት ጉዳይ ብቻ እንዳታደርጉት አደራ፡፡ በጣም በሰፊው ልትሄዱበት ይገባችኋል፡፡ ግብ ሳትመቱ ወደ ኋላ እንዳትመለሱ፤ ግብ ሳትመቱ ከተመለሳችሁ እናንተ ናችሁ የምትመቱት፡፡


“ቀደም ሲል በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ ብዙ አባቶች ስለ ማህበረ ቅዱሳን አልገባንም ነበር፡፡ ሲኖዶሱንና አቡነ ጳውሎስን ሲያዋጉ እና ሲያደባድቡ የነበሩ እነርሱ ናቸው፡፡ ነገ የምንወስንበትን ጉዳይ ዛሬ ማታ ገብተው ለአባቶች መመሪያ ይሰጣሉ፡፡ በዚያ ምክንያት በእነርሱ ተቃጥለው እኮ ነው አቡነ ጳውሎስ የሞቱት፡፡ አሁን ሲያታልሉን ነጠላ አደግድገው ሲሳለሙ የቤተክርስቲያን ልጆች ይመስላሉ፤ እምነት የላቸውም መናፍቃን ናቸው ነው እኔ የምለው፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሰው፣ የቤተ ክርስቲያን ልጅ የሆነ ሰው አባ እገሌ ወልዶአል፤ አባ እገሌ ገሎአል፤ አባ እገሌ ሰርቆአል ብሎ ለመናፍቃን፣ ለአለም ጽፎ አይሰጥም፡፡ እናንተ አሁን ያልተናገራችሁት የለም፡፡ ሁሉን ተናግራችኋል ሙሉ ቀን ብትናገሩ በጣም ደስ ይላል፡፡ እናንተ ባትደርሱ ኖሮ እነርሱ በአቋራጭ ቤተክርስቲያኗን ሊረከቡ ነበር፡፡ አላማቸው ምንድን ነው? ቤተክህነቱንም ቤተመንግሥቱንም ተረክቦ እኛን ስርቻ ውስጥ ወርውሮ ቁራሽ እንጀራ ሊጥሉልን፣ እንደ ውሻ በሰንሰለት አስረው ሊያኖሩን ነው፡፡ ብዙዎቻችን ብፁዓን አባቶች ግን ይሄ አልገባንም፡፡ ስልጣኑን ሁሉ ከእኛ ተረክበው ለሌሎች ሰጥተዋል እኮ፡፡ ሰዎቹ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረቂቅ ሕግ ተብሎ ለእኛ ለሲኖዶሱ የቀረበልን 5 ገጽ ነበር፡፡ ሌላውን ግን አላየነውም፤ ቤተክርስቲያኒቱን ተረክበው ሊቃውንቱ አያስፈልጉም የሚል ነው አላማቸው፡፡ ከዚያ በፊት በአባቶች አንመራም በሚል ወስነዋል፡፡ በየሀገሩ ቅስቀሳ አድርገዋል፤ እኛ ግን አልገባንም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቅስቀሳ እያደረጉብኝ ነው፡፡ ለምን ተናገርክብን ብለው በየመንገዱ እየጠበቁኝ ነው ያሉት፤ ለመግደል ማለት ነው!! ብዙ አባቶችም ደግሞ በእነርሱ እጅ ሞተዋል አልቀዋል፤ በመርዝም በተለያየ መንገድ የገደሉአቸው አሉ፡፡ (ብፁዕ አቡነ መርሐን የመርዝ መርፌ ወግተው የገደሏቸው የማቅ አባላት መሆናቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል)፡፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን የእነዚህ ካህናት ጥያቄ በቅርቡ መፍትሔ ማግኘት አለበት፡፡ ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ስም የሰበሰበውን ሀብት እያሸሸና ወደአክስዮን እያስገባ ነው፤ ሻይ ቤታቸውን ጭምር አክሲዮን እያስገቡና በሌላ ሰው ስም እያደረጉ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተ ወደኋላ እንዳትመለሱ ነው አደራ የምላችሁ፡፡”

ከሁለት ዓመት በፊት ይህን አስደናቂ ንግግር ያደረጉት አባ ሳዊሮስ በአንድ ጊዜ ተገልብጠው የማቅ ደጋፊ ይሆናሉ ብሎ የጠበቀ ማንም አልነበረም፡፡ ከማቅ በተጻራሪ ቆመው ሲዋጉት የነበሩት አባ ሳዊሮስን የማቅ ምርኮኛ ያደረጋቸው ማቅ ከያዘባቸው የሥነምግባር ችግር ጋር በተያያዘ በሐራ ላይ ከጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከትና ሌሎች አብያተ ክርስቲያን በዘረፉት ገንዘብ ‹‹ሺበሺ›› በሚለው አስከፊ የሙስና ስያሜ የሚታወቁትና በነፍስ ግድያ ወንጀሎች የሚጠረጠሩት አቡነ ሳዊሮስ የሚያስተባብሯቸው የግብር አምሳሎቻቸው፣ ወዘተ ብሎ” ዘገባ ከሰራባቸው በኋላ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች እየተናገሩ ነው /በሐራ ዘተዋሕዶ ላይ በOctober 16/2013 `የመንግሥትን የአክራሪነት ፍረጃ ተከትሎ የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ ለውጥ የሚቃወሙ ጥቅመኞች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚሰነዝሩት ውንጀላ ተጠናክሯል፤ ማኅበሩ ክሥ ለመመሥረት እየተዘጋጀ ነው በሚል ያወጣውን ዘገባ ይመልከቱ/፡፡ አቡነ ሳዊሮስም ከዚህ በኋላ አሰላለፋቸውን በማስተካከል ማቅን ከመዋጋት ለማቅ ወደ መቆርቆር፣ ማቅ ተሐድሶ የሚላቸውን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከመቀበልና እንዲያገለግሉ ክህነትና ስፍራ ከመስጠት ቦታ የሰጧቸውን ጭምር ተሐድሶ እያሉ ወደማባረር ከተሸጋገሩ ሰነባብተዋል፡፡

ይኸው ከሰሞኑ ደግሞ ሀገረ ስብከታቸው ምዕራብ ሸዋ የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች እንዳሻቸው የሚፈንጩበት መስክ ሆኗል፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቦታ ያጣው ማቅ ትኩረቱን ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉት ሀገረ ስብከቶች ላይ በማድረግ ስለ ተሐድሶ የግንዛቤ ማስጨበጫ የሚለውን ዲስኩሩን በስፋት ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በዓለምገናና በሰበታ ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ደብዳቤ በመጻፍ ሁሉም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው ጉባኤ ተዘግቶ ዓለምገና ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲሰበሰቡና ዳንኤል ክብረትና ያረጋል አበጋዝ በሚሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ዲስኩር ላይ እንዲገኙ አድርገዋል፡፡ ዳንኤል ክብረት ፓትርያርኩን በተሳደበበት ማግስት ዲስኩር እንዲያሰማ መጋበዛቸው “አበጀህ የኔ ልጅ” የማለት ያህል ነው፡፡

ከወር በፊትም በእነርሱ በኩል ከግብጽ አገልጋዮችን አስጋብዘው ይኸው የእነርሱ ዲያቆናትና ጳጳሳት ባለ ዲግሪ ናቸው የእኛ ግን ወደኋላ ቀሩ ናቸው በማለት በሰበታ አማኑኤል አውደ ምህረት ላይ አባ ሳዊሮስ ራሳቸውን ጭምር ሲያሰድቡ እንደ ነበር በስፍራው የነበሩ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ ይህ የግብጽያኑ የሰበታ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ በቤተክህነቱ ዕውቅና ያገኘ ይሆን? ግብጽውያኑ በሰበታ ነጻ ሕክምና እንሰጣለን በማለት ወደዚያ የሄዱ ሲሆን በመጨረሻ ግን ለእነያረጋል የተሐድሶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ማጣፈጫ ሆነዋል፡፡ አባ ሳዊሮስም ለዚህ ውለታቸው ግብጽ ለ10 ቀናት ቆይተው ተመልሰዋል፡፡ ከወር በፊትም በአባ ሳዊሮስ አማካይነት ባለሀብቶችና የማቅ አባላት ብቻ በተገኙበት ያረጋል አበጋዝ ዲስኩር ደስኩሯል፡፡ በዚያው ወቅት በአማኑኤል ቤተክርስቲያን አንድም ካህን እንዳይቀር ተደርጎና ሙሉ ቀን መፈረሚያ ተቀሞጦ ካህኑ ሁሉ ሳይወድ በግድ የያረጋልን ዲስኩር ሲሰማ እንዲውል ተደርጓል፡፡ በዲስኩሩ መጨረሻም አባ ሳዊሮስ “ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር እንሰራለን” ብለዋል፡፡

የማኅበረ ቅዱሳንን አሠራር ከመቃወም ወደ መደገፍ፣ ይልቁንም ቅዱስ ፓትርያርኩ ማኅበሩን መሥመር ለማስያዝ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት አባ ሳዊሮስ ከማኅበሩ ጋር እንሠራለን ብለው ማለታቸው ከምን የተነሳ ነው? እንዲህ ያሉት ከዚህ በፊት እርሳቸው ይቃወሙት የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን መሻሻል አሳይቶና ወደትክክለኛው መስመር ገብቶ ሳይሆን ማኅበሩ እንደ አባ ሳዊሮስ ያሉትን አባቶች በሚማርክበት ስልቱ ስለማረካቸው እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ማኅበሩ በስለላ መረቡ አማካኝነት ይዤባቸዋለሁ የሚለውን ነውር ይፋ አደርጋለሁ በሚል ከእርሳቸው ጋር እንደ ተደራደረ በስፋት ሲነገር ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በጽኑ ይቃወሙት የነበረውን ማኅበር ወደመደገፍና በሀገረ ስብከታቸው ከዚህ ቀደም አጥቶ የነበረውን ስፍራ እንዲያገኝና እርሱ ተሐድሶ በማለት የፈረጃቸውን ሁሉ እንዲመነጥሩለት ስለተስማሙ አባ ሳዊሮስ ተሐድሶ ተብለው በማቅ የተፈረጁትን አንዳንዶቹን ከሥራ አባረዋል፡፡ በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ እንዳይሰብኩም አድርገዋል፡፡ ከሀገረ ስብከታቸው እስከ አገር አቀፉ የሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ ድረስ ማቅን በመዋጋት ከእርሳቸው ጋር ብዙ መሥዋዕትነት የከፈሉትን ሥራ አስኪያጃቸውንም እስከማባረር በመድረስ የማቅን ትእዛዝ ፈጽመዋል፡፡

ይህ የአባ ሳዊሮስ የአቋም መዋዠቅ የመጣው ማቅ ይዤባቸዋለሁ ከሚለው መረጃ የተነሣ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ በዚህ ረገድ አባ ሳዊሮስን ነጻ ማውጣት ያስፈልጋል፡፡ ነጻ እንዲወጡ ደግሞ ያን ማቅ ይዤዋለሁ የሚለውን መረጃ ይፋ ማድረግ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ አባ ሳዊሮስ ከዚህ በፊት ከተናገሩት በተቃራኒ እየሄዱበት ያለውን ፀረ ወንጌል አካሄድ ማረም አለባቸው፡፡ ማቅ የአደባባይ ምስጢር ያደረገው ነውራቸው የተሸፈነላቸው መስሏቸው ከማቅ ጎን መቆማቸው እርሳቸውን ትልቅ ትዝብት ላይ የጣላቸው፣ በቀጣይም እምነት የማይጣልባቸው ሰው እንዲሆኑ እያደረገ ነውና አቋማቸውን ሊያስተካክሉ ይገባል፡፡       

19 comments:

 1. የተከበሩ አባ ሳዊሮስ
  ቢሰሙኝ?

  ማቅን የመደገፍና ለዓላማውም ሁለንተናቸውን የመስጠት የግል መብታቸውን መንግሥት ሳይቀር ማክበር የትክክለኛው ዲሞክራሲ ባህሪ ነው፤ ሕገ ወጥ የሚያደርጋቸው የክርስቶስን ወንጌል ለሕዝቡ ለማስተማር የያዙትን የአባትነት ኃላፊነታቸውን ዘንግተው የቡድን ምድራዊ ዓላማ ፈጻሚና አስፈጻሚ መሆናቸው ነው።

  ስለዚህ ሳይመሽ ሚናቸውን አስተካክለው ወይ የማቅ ተጋዳላይ ወይም ላጠለቁት 'ቆብና' 'ለሚያሳልሙበት መስቀል' ታማኝነታቸውን ቢያስተካክሉ ቢያንስ የራሳቸውን ኅሊና በጥቂቱ ያሳርፋሉና የምትቀርቧቸው ሰዎች አማክሯቸው!!!

  ካስፈለገ እራሳቸው በ eunethiwot@gmail.com ቢያገኙኝ መንፈስ ቅዱስ ያቀበለኝን ላቀብላቸው ያስችለኛል!

  መልካም የሕይወት ጉዞና ፍጻሜ ይሁንልዎት!

  አሜን።

  እውነቱ ይነገር ነኝ
  እንድኖር ከተፈቀደልኝ ምድር!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማን ነህና አንተ መንፈስ ቅዱስ ያቀበለኝን ላቀብላቸው ያስችለኛል!የምትለው? እዚያው የለመድክበት አዳራሽ ቢጤዎችህን ሰብስበህ አጓራ።

   Delete
  2. መንፈስ ቅዱስ አቀበለሽ የኔ መንፈስ አንቺ ጋር ያለው መንፈስ አይደለም ሌላ ሊያንጽ ለአንቺም አልሆነም ስለዚህ ደፍተሸው በአዳሲ መንፈስ ብትሞ ይሻላል፡፡መንፈስ ቅዱስ አቀበለሽ የኔ መንፈስ አንቺ ጋር ያለው መንፈስ አይደለም ሌላ ሊያንጽ ለአንቺም አልሆነም ስለዚህ ደፍተሸው በአዳሲ መንፈስ ብትሞ ይሻላል፡፡

   Delete
 2. Praise to God! Abba Sawiros is doing his pastoral duty! Satan become angry.

  ReplyDelete
 3. አንድ እውነት በትክክል ገባኝ
  አባ ሰላማ ብሎግ የበግ ለምድ የለበሳችሁ ተኩላዎች ናችሁ ለምዱ ምንድነው ቢባል ስማችሁ ና ነራችሁን የኦርቶዶከስ አስተምህሮ አስመስላችሁ ግን የመናፍቃን ትምህርት የምታስፋፉ ኑፋቄ የምትዘሩ የቤተክርስቲያን ጠላቶች በአንድ ሰው ንስሀ መግበት በሰማየት ታላቅ ደስታ የሚደረግ መሆኑን እያወቃችሁ ዳሩግን ስንቱን ክህደት ውሸት ሁከት አመጽ አስተማራችሁ በሰማይ ደስታ እንዳይሆን የምትደክሙ የጠላታችን አሽከሮች በእውኑ የእግዚአብሔርን መንፈስ ለምን ታሳዝናላችሁ ተኩላነታችሁም ይህነው፡፡
  ማህበረቅዱሳን ዓላማው ቤተክርስቲያን ማገልገል ትህትና መሰረቱ ነው ብጹዕ አባታችንም አቡነ ሳሮስ ከማህበሩ ጎን መቆማቸው እውነትን ቢያገኗት ነው አባ ሰላማ ብሎጎች ግን ሁልጊዜ ማህበሩን መውቀስ ማጥላላት ተግበራችሁ ሆኗል በዚህም ማህበሩ ለእናንተ ለመናፍቃን እራስ ምታት የጎን ውጋት እንደሆነባችሁ በትክከል ተረዳሁ እውነት አርነት ያወጣችኋል እባካችሁ እውነትን ስሙ እውነትን ተናገሩ ለእውነት ኑሩ ከእንናተ ጋር ካለው ብዙ የውሸት ሰራዊት ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ያለው እውነት አንድ እግዚአብሔር ይበልጣልና ማህበራችንን ማህበረ ቅዱሳንን የምንወደው የወደደን አምላካችን ዳግም እስኪመጣ ድረስ አገልግሎቱን ያዝልቅልን ያሻግርልን አሜን፡፡
  ኢዮብ ቀናው
  ሚያዚያ 27/2008 ዓ.ም

  ReplyDelete
 4. Teshegageru alteshegageru.mk egziabher yeferedebat elet enkwan abune sayros manm ayaskomwom.

  ReplyDelete
 5. እንዲህ ያለ ነገር መጻፍ ከአንድ ክርስትያን አይገባም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሲጀመር ክርስቲያኖች ናቸው እንዴ?

   Delete
 6. TEHADISO KESERE orthodox gena grna tisefalech. dabilose zinarun cherese serawitun gen del madrege alchalem.
  lenantem lebona yistaxchehuna wod tewahido retit haimanot yimelsachehu

  ReplyDelete
 7. Eski tengebgebu demo ye Luther kitregnoch.

  ReplyDelete
 8. እናንተ የሰይጣን ቁራጮች እስከመቼው እንዲህ ውሸት እያወራችሁ ትኖራላችሁ፡፡ እናንተ የጴንጤ ባንዳዎች የሆናችሁ የእግዚአብሔርን ልጆች ለዲያቢሎች አሳልፎ መስጠት ግብራችሁ የሆነ ዘመኑ ቀርቧልና ንስሐ ግቡ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመኑን ያርዝምልን፡፡አሜን፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን 8620 ኢአማንያንን በመተከል ዞን አስጠመቀ፡፡

  ReplyDelete
 9. እናንተ የሰይጣን ቁራጮች እስከመቼው እንዲህ ውሸት እያወራችሁ ትኖራላችሁ፡፡ እናንተ የጴንጤ ባንዳዎች የሆናችሁ የእግዚአብሔርን ልጆች ለዲያቢሎች አሳልፎ መስጠት ግብራችሁ የሆነ ዘመኑ ቀርቧልና ንስሐ ግቡ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመኑን ያርዝምልን፡፡አሜን፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን 8620 ኢአማንያንን በመተከል ዞን አስጠመቀ፡፡

  ReplyDelete
 10. We are tired of Personal attack! We are tired of Personal attack!We are tired of Personal attack! Please STOP.

  ReplyDelete
 11. Barking dogs never bites!

  ReplyDelete
 12. አባ ሰላማ ብሎግ የበግ ለምድ የለበሳችሁ ተኩላዎች ናችሁ ለምዱ ምንድነው ቢባል ስማችሁ ና ነራችሁን የኦርቶዶከስ አስተምህሮ አስመስላችሁ ግን የመናፍቃን ትምህርት የምታስፋፉ ኑፋቄ የምትዘሩ የቤተክርስቲያን ጠላቶች በአንድ ሰው ንስሀ መግበት በሰማየት ታላቅ ደስታ የሚደረግ መሆኑን እያወቃችሁ ዳሩግን ስንቱን ክህደት ውሸት ሁከት አመጽ አስተማራችሁ በሰማይ ደስታ እንዳይሆን የምትደክሙ የጠላታችን አሽከሮች በእውኑ የእግዚአብሔርን መንፈስ ለምን ታሳዝናላችሁ ተኩላነታችሁም ይህነው፡፡
  ማህበረቅዱሳን ዓላማው ቤተክርስቲያን ማገልገል ትህትና መሰረቱ ነው ብጹዕ አባታችንም አቡነ ሳሮስ ከማህበሩ ጎን መቆማቸው እውነትን ቢያገኗት ነው አባ ሰላማ ብሎጎች ግን ሁልጊዜ ማህበሩን መውቀስ ማጥላላት ተግበራችሁ ሆኗል በዚህም ማህበሩ ለእናንተ ለመናፍቃን እራስ ምታት የጎን ውጋት እንደሆነባችሁ በትክከል ተረዳሁ እውነት አርነት ያወጣችኋል እባካችሁ እውነትን ስሙ እውነትን ተናገሩ ለእውነት ኑሩ ከእንናተ ጋር ካለው ብዙ የውሸት ሰራዊት ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ያለው እውነት አንድ እግዚአብሔር ይበልጣልና ማህበራችንን ማህበረ ቅዱሳንን የምንወደው የወደደን አምላካችን ዳግም እስኪመጣ ድረስ አገልግሎቱን ያዝልቅልን ያሻግርልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 13. ‹ናቂ ስድብ› የሚባለው ዘዬ ማኅበረሰቡን የናቀ፣ ያዋረደና ለዕውቀትና ለኅሊና ቦታ የሌለው ዘዬ ነው፡፡ ‹እገሊት ባኞ ቤት ውስጥ ራቁቷን ሆና የሆነ ነገር እየሠራች ናት፡፡ ሙሉውን ለማየት ላይክና ሼር አርጉኝ› በሚለው አባባሉ ይታወቃል፡፡ መንግሥት በየመሥሪያ ቤቱ ኪራይ ሰብሳቢ እዋጋለሁ ሲል እዚህ ፌስቡክ ላይ ደግሞ ‹ላይክና ሼር ሰብሳቢዎች› ተፈጥረዋል፡፡ ናቂ ስድብ እነዚህ ላይክና ሼር ሰብሳቢዎች የሚግባቡበት የስድብ ዓይነት ነው ፡፡ ናቂ ስድብ አሠሥ ገሠሡን እያቀረቡ ማኅበረሰቡን ለማበሳጨትና ፌስቡክ ከሚባለው ክልል ጨዋዎችን ለማፈናቀል፣ ብሎም ፌስቡክ የተባለው ክልል በ‹ፌስዳቢዎች› ለመሙላት የሚጥሩ የጎሳው አባላት የሚጠቀሙበት ቋንቋ ነው፡፡ በእነዚህ ‹ናቂ ስድብ› ዘዬ ተጠቃሚዎች ምክንያት ብዙ ዐዋቂ ፌስቡከኞች ከክልሉ ወጥተው ወደሌላ ክልል ለመሄድ ተገድደዋል፡፡ ‹እስኪ እነዚህን ቆንጆዎች ተመልከቷቸው? ዐሥር ሺ ላይክና ሼር ይገባቸዋል› የሚለው የዚህ ዘዬ ታዋቂ ተረቱ ነው፡፡


  ‹ጨርጋጅ ስድብ› የሚባለው ዘዬ ደግሞ ታላላቅ የምንላቸውን፣ የምናከብራቸውን፣ በሁለት እጅ የማናነሳቸውን ሰዎች ገጽታ ለማጥቆርና ብሎም ‹የገጽታ ግድያ› ለማድረግ በማሰብ በስድብ የሚጨረግድ ዘዬ ነው፡፡ በሰውዬው ወይም በሴትዮዋ ላይ ምን ያስከትላል፣ ልጆቹስ ምን ይላሉ፣ አድናቂዎቹ ወይም ወዳጆቹ ምን ይሰማቸዋል፣ ይህንን የሚያነቡ አዳጊ ልጆች ምን ያስባሉ፣ ውጠቱስ ምን ይሆናል? የሚለውን ማሰብ አይፈልጉም፡፡ እንዴው ዝም ብሎ መጨርገድ ብቻ ነው፡፡ የሚባለው ነገር እውነት ወይም ሐሰት ለመሆኑ ማሰብ አይፈልጉም፤ ማረጋገጥ የሚፈልጉት መጨርገዳቸውን ብቻ ነው፡፡
  ‹ባለጌ ስድብ› የሚባለው ዘዬ ደግሞ አፋቸውን ያልተጉመጠመጡና ምላሳቸውን ያልገረዙ ‹ፌስዳቢዎች› የፈጠሩት ዘዬ ሲሆን በየመንደሩ የጠፉትን የባለጌ ስድቦች በሙሉ ሰብስበው በዚህ ዘዬ ውስጥ ጨምረዋቸዋል፡፡ ያልታጠበ ኅሊና፣ ያልታጠነም ልቡና ይዘው፣ ገና ራሳቸውን ከማስተካከላቸው በፊት ፌስቡክ ድንገት በስልካቸውና በኮምፒውተራቸው በኩል የመጣባቸው የጎሳው አባላት የሚናገሩት ዘዬ ነው ‹ባለጌ ስድብ› ማለት፡፡ አበው ‹ከባለጌ ጡጫ፣ ከዳገት ሩጫ› ያድንህ ይላሉ፡፡ ለምን ከባለጌ ጡጫ? ቢሉ ባለጌ የት ላይ መማታት እንዳለበት አስቦ አይማታም፡፡ እጁን መሠንዘሩን ብቻ ነው የሚያየው፡፡ ስለዚህም ድንገት ብሽሽትህን መትቶ ጸጥ ያደርግሃል ሲሉ ነው፡፡ ይሄ ምርቃት ለሽማግሌዎች ሸንጎ ቀርቦ ‹ከባለጌ ፌስቡከኛ አቋራጭ ከሚወድ መንገደኛ ያውጣህ› ተብሎ መዘመን አለበት፡፡
  ‹ተንኳሽ ስድብ› የሚባለው የ‹ፌስዳቢዎች› ዘዬ ደግሞ ጎሳዎችን፣ ነገዶችን፣ እምነቶችን፣ ፓርቲዎችን፣ ግለሰቦችን፣ ድርጅቶችንና ሌሎችንም እየተነኮሰ ማብሸቅ፣ ማናደድ፣ ማጋጋልና ለጠብ እንዲፈላለጉ ማድረግ ነው ዓላማው፡፡ በዚህ ዘዬ የሚጠቀሙ ‹ፌስዳቢዎች› የትንኮሳ ስድባቸውን ሲረጩ ለአንደኛው ወገን እንደሚቆረቆሩ መስለው ነው፡፡ አንዳንዴም የአንድን ማኅበረሰብ ወይም ተቋም ውክልና የያዙና የዚያ ማኅበረሰብን ወይም ተቋምን ሐሳብ እንደሚያንጸባርቁ መስለው ስለሚቀርቡ፣ ያንን የሚመለከቱ ሌሎች ማኅበረሰቦችና ተቋማት ጉዳዩን የግለሰብ አድርገው እንዳይወስዱት ያደርጋቸዋል፡፡
  ‹ፈጥሮ አደር› የስድብ ዘዬ ድንገት አንድን ነገር ፈጥሮ በማራገብ የታወቀ ነው፡፡ እገሌ ሞተ፣ እገሌ ታሠረ፣ እገሌ ከሰረ፣ እገሌ ጠፋ፣ እገሌና እገሊት ተፋቱ፣ እገሌና እገሊት ተጋቡ፣ እሌና እገሌ ተደባደቡ እያለ አንዳንዴም በተቀናበረ ፎቶ እያስደገፈ ይበትናል፡፡ ‹እስኪጣራ ማን ይጉላላል‹ እንዳለቺው ዕንቁራሪቷ ወሬው እስኪጣራ ብዙ ሰው ይጉላላል፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች ለ‹አፕሪል ዘፉል› ቀን በዓመት አንድ ‹ጊዜ ብቻ የሚደረገውን እነዚህ ግን ዓመቱን ሙሉ ‹አፕሪል ዘፉል› ያደርጉታል፡፡ ቀንጨር በባዘበት እርሻ እህል እንደሚጠፋው ሁሉ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች እየተበራከቱ መምጣት ፌስቡክ ከተባለው ክልል ብዙ ባለ አእምሮዎችን እያስወጣ ነው፡፡
  ‹ፌስዳቢ› በተባለው ጎሳ ባህል ውስጥ አንድ ወጥ ስም የሚባል ነገር አይታወቅም፡፡ ዐሥር፣ ዐሥራ አምስት ዓይነት ስም ሊኖርህ ይችላል፡፡ ትግሬን መሳደብ ሲያምርህ የአማራ ስም፣ አማራን መሳደብ ስትፈልግ የኦሮሞ ስም፣ ኦሮሞን መሳደብ ስትፈልግ የአማራ ስም መያዝ ትችላለህ፡፡ ያ ካልሆነ ደግሞ የቁስ ስምም ቢሆን ይዘህ መሳደብ ነው፡፡ በጎሳው ሥርዓት መሠረት በመታወቂያህ ላይ ፎቶህን ለመለጠፍ አትገደድም፡፡ ብትፈልግ ባዶ ትተወዋለህ፣ ብትፈልግ የሌላ ሰው ፎቶ ትጠቀማለህ፣ ብትፈልግ ደግሞ ስድብ ታደርገዋለህ፡፡ ዋናው ምሽግ ይዘህ ለመሳደብ መቻልህ ነው፡፡

  ReplyDelete
 14. kemenem belay yemehaber degafi kemehon lemotelen le KIRSTOS mehon yibejal.

  ReplyDelete
 15. ማቅ አባቶችን ይሠድባል፣ያዋርዳል፣በሃሰት ይከሣል፣ይወነጅላል…ወዘተ በማለት የጹሁፋችሁ 99.9% ይመሠክራል።ነገር ግን በማኅበሩ ብሎግ ከወንጌል ውጭ ምንም ስለምትሉት ውንጀላ አይቸም ሠምቸም አላቅም፤ መረጃችሁ ሁሉ ከዲያቢሎስ ነው እንዴ? ይልቁንም የአባ ድሜጥሮስን፣ የአባ ማቴዎስን፣የአባ ሉቃስን፣ የአባ ቀለሜንጦስን፣ የአባ ሳዊሮስን፣አባ እንድርያስን፣ አባ ሕዝቅኤልን፣ በአጠቃላይ ከፓትራሪኩ በስተቀር ሊቃነ ጻጻሳትን በሙሉ ሰባኪያንና መምህራንን፣ ዘማርያንን፣ ማኅበረ ቅዱሳንን፣ ማኅበረ ካህናቱን፣ አሰተዳዳሪዎችን፣ ሰ/ት/ቤት ተማሪዎችን...በመሣደብ መንግሥተ ሠማያት ትገባላችሁ የተባላችሁ ትመስላላችሁ። የስድብ ዩንቨርሲቲ አላችሁ እንዴ?

  ReplyDelete