Friday, May 6, 2016

መፍትሔ ላጣው ደብር መፍትሔ የሚሰጥ ማነው?የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን መፍትሔ አጥቶ ሰላም ከራቀው ይኸው ከነችግሩ አንድ ዓመት አስቆጠረ፡፡ አሁን ያለው የደብሩ ችግር በካህናት ኑሮ ላይ አፍጦ እየታየ ነው፡፡ የበዓል ቦነስ ቀርቶ ደመወዛቸው ተረጋግቶ ሊከፈላቸው አልቻለም፡፡ የባለፈው ወር ደሞዝ ሌሎቹ አድባራትና ገዳማት ከተቀበሉ ከ15 ቀን በኋላ ነበር የተከፈላቸው፡፡ ለገንዘቡ መጥፋት ተጠያቂው ደግሞ የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው አባላት ሲሆኑ በተራዘመ የሕንጻ አሠራር ስልት ገቢውን ለግላቸው እየከበሩበት ካህናቱ ግን እየተራቡ ያለው የደብሩን ገቢ ሙልጭ አድርገው በመውሰዳቸው ነው፡፡ ተከታዮቻቸውንም ለሕንጻው እንጂ ለደብሩ ሙዳየ ምጽዋት አታስገቡ በማሰኘት ለበለጠ ዝርፊያ ሁኔታውን አመቻችተውላቸዋል፡፡
የዚህ ደብር ባለቤት ማነው? ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነት? ወይስ ሀገረ ስብከት? ወይስ የአካባቢው የጎበዝ አለቆች? ማን እያስተዳደረው እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ካህናቱም ጠዋት ኪዳን አድርሰው ቀን በየሰፈሩ ቀብር አስፈጽመው ቀድሰው ለበዓል የሚውሉበትን ገንዘብ በልምምጥ መልክ ምንም የማይመለከታው የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴዎችን ገንዘብ ስጡኝ ብለው መጠየቅ ውስጥ መግባታቸው ለእነርሱ ትልቅ ውርደት ነው፡፡ ካህናቱ በማገልገላቸው የሚገባውን ገንዘብ ህንጻ አሠሪዎቹ በተራዘመና በሰለቸ የሕንጻ አሰራር ስልት በእጅጉ እየተቀራመቱት ነው፡፡
·        ባለሲኖትራኩ አቶ ታረቀኝ፣
·        ባለ 5 ፎቁ አቶ ጉዳ ወይም በለጠ፣
·        ባለብዙ ቤት አከራዩ አቶ ብርሃኑ ድረሴ
·        በየጊዜው 55 ሺ ብር እየከፈሉ ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዙት አቶ ካሣ
·        ፎርማን የነበረውና 8 ሺህ እየተከፈለው ዛሬ የሕንጻ መሣሪያ ሱቅ ባለቤት የሆነው ባይሳ
·        የሕንጻውን ፎቶ በአሜሪካ ስቴቶች በመቶ ዶላር እየሸጡ ያሉት አቶ ዳንኤል ተገኑ ወዘተ እየተጫወቱበት ነገ የማይኖሩበትን ቤት እየገነቡበት ይገኛሉ፡፡
·        የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እስጢፋኖስ ሀይሉ ደግሞ ፒያሳና አትክልት ተራ ላሉት የኤሌክትሪክ ሱቆቹ ያለ ጨረታ ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ በበለጠ ወይም በጉዳ አማካይነት የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አቅርቦበታል፡፡

አሁን አንድ ሚስጢር እየተገለጠና ብቅ እያለ ነው፡፡ ይኸውም ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች በቀጥታ ከውጭ አገር በደብሩ ስም ያለ ቀረጥ እንዲገባ የሚያስችል ደብዳቤ እንደ ተጻፈ የታወቀ ሲሆን፣ በሕንጻው ስም ለራሱ ሱቅ እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ ሙስና ነውና መንግሥትን በቀጥታ ይመለከተዋል፡፡ በቤተ ክርስያን ስም ለግል ጥቅም ያለ ቀረጥ ዕቃ ማስገባት በመንግስት ገቢ ላይ የሚፈጸም ሙስና ነውና ቦታው ወደ ውንብድና እንደ ተቀየረ ይጠቁማል፡፡
ይሄ ሁሉ ሲሆን የሌላ ደብር አገልጋዮች የበዓል ደመወዝ ከነቦነሱ ሲያገኙ፣ የዚህ ደብር ካህናት ግን በገዛ ገንዘባቸው ተቸግረው በዓልን ባዶ ቤት አሳልፈዋል፡፡ የደብሩ አስተዳደር ከበዓሉ በፊት ለሀገረ ስብከቱ አመልክቶ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በቀጥታ ለሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው ክፈሉ ቢልም ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው ግን በዓመት አንዴ የሚከበረውን የስቅለትን በዓል ወደጎን በመተው የተለመደውን የዐመፅ ቅስቀሳ አካሂዶ ነበር፡፡ አመጹን ለማቀጣጠል በየበሩ ወረቀት ለጥፈው ነበር፡፡ ለሕንጻው የሚገባው ገንዘብ ሊበላ ነው በማለት ባለፈው ሰኞ ሕዝቡን ጠርተው ነበር፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ ደርሶበት እስጢፋኖስን፣ ዮናስን፣ ሻለቃ ጣሰውንና ሌሎችንም ግብረ አበሮቻቸውን ወደ ጣቢያ በመውሰድ እንዲፈርሙ አድርጎ ለቆአቸዋል፡፡
ደብሩን በጤናማ መንገድ ማስተዳደር ከተፈለገ ካህናቱ ለቅዱስነታቸውና ለሀገረ ስብከቱ ባመለከቱት መሠረት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ሰኔ 2 ቀን እንደተባለው መመረቅ አለበት፡፡ ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው ግን ይህን አይፈልግም፡፡ ምክንያቱም በሕንጻው ሽፋን እየበዘበዙ ያለው የገቢያቸው ምንጭ ይደርቃልና፡፡ በቅርቡ እንኳን አደራ ማርያም የተባሉ በጎ አድራጊ የቤተ ክርስያኑን ሁሉንም በር አሠርተው ቢያመጡም አይገጠምም ይቆይ ብለዋቸው ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በሩ ከተገጠመ የቤተክርስቲያኑ ምረቃ ሊፋጠን ስለሆነ በር የለውምና ይራዘም ለማሰኘት ነው፡፡ በጎ አድራጊዋ ግን የራሳቸውን ባለሙያዎች በማስምጣት በሩን አስገጥመዋል፡፡ ስለዚህ ሰኔ ሁለት ከተመረቀ ያን ጊዜ ችግሩ መፍትሔ ያገኛል፡፡
ሌላው መፍትሔ ተብሎ የሚወሰደው ማህበረ ካህናቱ አንድ እሑድን አገልግሎት ማቆም አለባቸው የሚል ነው፡፡ ይኸውም እየተራብን እየተቸገርን የበዓል ደመወዝ እየተከለከልን የልጆቻችንን የት/ቤትና የቤት ኪራይ እያሰቃየን ሌላው የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ የሆነ ምእመን ደግሞ ገንዘቡን ለግል ጥቅሙ እየተከፋፈለ እኛ ለምን እናገለግላለን? ብለው ሕዝብ ችግሩን እንዲያውቀው የበለጠ ቢያደርጉ መፍትሔ ይመጣል ብለው ያስባሉ፡፡
ደብሩ ከሀገረ ስብከቱ ከመንግሥትም እይታ ውጪ ከሆነ ቆይታል፡፡ የሚገርመው ደግሞ ወጣት ዮናስ መኮንን የተባለው ግለሰብ ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት ፈረጅያ እናሰፋ ከዚያ አለቃውን እናነሳለን ይኸውም ከጥምቀት አያልፍም ብሎ ከሕንጻ አሠሪውና ከአቶ እስጢፋኖስ ሀይሉ ገንዘብ በመቀበል በጣም ይቀርባቸዋል በተባሉት በአቡነ ሳዊሮስ በኩል ተደራድሮ ሰጥቷል እየተባለ ነው፡፡ አባ ሳዊሮስ የፈረጂያውን ገንዘብ ወይም ፈረጂያውን ለሌሎች ያደርሱ ለግላቸው ይውሰዱት ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ ይሁንና ገንዘቡም ተበልቶ አለቃው በተወሰነላቸው መሠረት እስካሁን እያስተዳደሩ ይገኛሉ፡፡ እንግዲህ ካህናቱ በገዛ ሀብታቸው ላይ የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው አባላት ቁማር እየተጫወቱባቸው ይገኛሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ነባር ካህናት ትልቁን መፍትሔ ማምጣት ሲችሉ ቀን ቀን ከአለቃው ጋር ሠርተው ማታ ማታ ደግሞ ከሕገ ወጦቹ ጋር ጽንፍ በመያዝ የላይ ፈሪ የታች ፈሪ እያሉ ችግሩን እያባባሱ ይገኛሉ፡፡ ነገሩን እንዲህ ያልተረዱት ምእመናንም ለቤተክርስቲያናቸው የቀኑና ገንዘቡን ያተረፉ መስሏቸው በሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው ቅስቀሳ እንደ ጠፍ ከብት ተነድተው እንደ መስክ ውሃ ተጠልፈው ለደብሩ መስጠት የሚገባቸውን አስተዋፅኦ ለሕንጻው ሰጥተው በአልጠግብ ባዮች እያስበሉት ይገኛሉ፡፡
የአጥቢያው ባለሀብቶች እንደዱሮው ለአካበቢው ፖሊስና ለወረዳ ሰባት ፍትሕ ቢሮ በየጊዜው በሚሰጡት ጉቦ ወንጀለኞች ሳይጠየቁ በሰላም እንዲኖሩ አድርጓል፡፡ ጉዳዩ ወደ ጉለሌ ፖሊስ መመሪያ ከሄደ በኋላ ግን ሲረብሹ እንደ በፊቱ ሳይሆን ለሕግ በማቅረብ አስከ ማሰር የደረሰው እርምጃ ጸጥታን በተመለከተ አንጻራዊ ሰላም አስገኝቷል፡፡ እንዲህ ያደረገው የፖሊስ መምሪያውም ሊመሰገንና በዚህ ተግባሩ ሊገፋበት ይገባል፡፡
ሀገረ ስብከቱ በሕግ ክፍሉ በኩል ያለውን አሻጥርም መመርመር አለበት፡፡ ከዚህ ቀደም ደብሩን አስመልክቶ የተወሰኑ ውሳኔዎች ተግባራዊ ቢሆኑ ለደብሩ ችግር መፍትሔው ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ  ቤት የሸጠውን እስጢፋኖስን በቀጥታ የክስ ቻርጅ  እንዲደርሰው ቢያደርግ በካህናቱ ጥያቄ መሠረት ደግሞ ሰኔ 2 ሕንጻ ቤተክርስያኑ እንዲመረቅ ቢደረግ ትልቅ መፍትሔ ይኖረዋል፡፡ ከዚህ በኋላም የሕንጻው ኮሚቴ ስለሚበተን ኦዲት ተደርጎም ተገቢው እርምጃም ቢወሰድ መፍትሔ ይሆናል፡፡ ነባሮቹ ካህናት ደግሞ ከሕገ ወጦቹ ጋር ከመሞዳሞድ ለቦታው ቢያስቡ የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ካልሆነ ግን ደብሩ “ምንትስ ያለበት ደብር ዐሳ ያለበት ባሕር ሳይበጠበጥ አያድር” የሚለው ተረት የሚፈጸምበት ቦታ ሆኖ ይቀራል፡፡   

5 comments:

 1. For God sake please Abba Sawiros in peace.

  ReplyDelete
 2. aba selamawoch betam enamesegenalen

  ReplyDelete
 3. ሰው የማይታነጽበት ስራዎች ናቸው እየተሰሩ ያሉት። ማቅ እንኳን በትግራ ተወላጆች የተሞላ አመራር ስላሌው ብቻ ማንም ልነካው አልቻለም። ለማስመሰል ግን ከእነ አባ ማትያስ ጋር አልተስማማም እንደገና የኢህአድግም መንግዝት አውቆ የኦርቶዶክስ ተከታዮችን ለማደናገር አንደ አሸባር ሌላ ግዜ ጸረ ሰለም በማለት ስያደናግር ብዙ ዘመን አስቆጠርን።ይህ ሁለ ህዝባችንን በእምነቱ እንድታወክ በማድረግ ላይ ነው። ስለዚህም ነው ማንም ደፍሮ የማህበረ ቅዱሳንን ቢሮ ልዘጋው ያልቻለው። የመንግስት ሰላዮች በማቅ ውስጥ ስለምገኙ በሐይማኖት ሽፍን ማደናገርያ ድብቅ ማደናገርያ ብቻ መንገድ ስለሆነ ነው። ወገኔ ንቅ ለዘለአለም አትሞኝ ። ማቅ ያልታወቀበት የኢህአድግ ድብቅ በሐይማኖት ሽፋን እየገዘገዘንና ሰላምን እያሳጣን ነው። እስት እግዚአብሔር ያሳችሁ የማቅ አመራር አባላት በአደባባይ በተለያዩ ምድያዎች እንደ ፈለገ በአባ ገነንነት ስጨፍር ቤተ ከህነትም ሆነ መንግስት ማስቆም መዝጋት ይችሉ ነበር። ነገር ግን የእነርሱ ጠመንጃ በመሆኑ እንደ ፈቀደ ይነግዳል ያተራምሳል ይፎክራል። ይበቃል እንንቃ ..................

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ketafi washo beminim yalkew ke ewunetaw gar aygenagnim.

   Delete
 4. you write it out of the truth. it is the work and the nature of davil and his followers. and you are number one in this journy. you alway write, go and talk agains the will of the God i.e Truth. lets God rise your heart to reach at the right way- orthodox Tewahido not tehadiso

  ReplyDelete