Tuesday, May 31, 2016

ሰበር ዜና - የሲኖዶሱ ስብሰባ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በተገኙበት ቀጠለ



የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን የሆነው ሐራ ሰሞኑን ባናፈሰው ወሬ የማቅ ተላላኪዎች ቅዱስ ፓትርያርኩን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር መሥራትዎ ግድ ነው፤ ሕዝብ ይግባ፤ መንግሥት ይግባ ማለት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ሕገ መንግሥቱን አለማወቅ ነው፤ ማንም በማንም መግባት አይችልም፤ እኛም አንፈልግም፤ ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ መካከል ኾና ኹሉንም በአንድነት የምትጠብቅ ችግር ፈቺና አስታራቂ ተቋም ናት፤ እነእገሌ ይግቡ፤ እነእገሌ ይምጡ የሚለው አስተሳሰብ የመከፋፈል አጀንዳ ያላቸው ሰዎች ከውጭ የሚረጩት ነው፤” ማለቷ የሚታወስ ነው፡፡ እንዲህ ሲሉ የነበሩት የእንደራሴ አጀንዳ አቀንቃኞች በፓትርያርኩ አቋመ ጽኑነት ሐሳባቸውን ለውጠው መንግሥት ጣልቃ ይግባ ማለታቸውን ተከትሎ ለዛሬ ከሰዓት በኋላ ተላልፎ የነበረው እንደራሴን የተመለከተው አጀንዳ የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በተገኙበት ተካሄደ፡፡

ሚኒስትሩ በሚገኙበት የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት መሠረት ያደረገው ውይይት ኪሳራ ላይ የሚጥላቸው መሆኑን የተረዱት የማቅ ሰዎች በሐራ በኩል አሠራጭተውት የነበረው ወሬ አቅጣጫውን በመቀየሩ “ለምን መንግሥት ጣልቃ ይግባ አላችሁ? መንግሥት ጣልቃ ከገባ አቅጣጫው ይቀየራል” በማለት፣ አጀንዳ መሸከማቸውን እንጂ ጥቅምና ጉዳቱን በሚገባ ላላጤኑት ተላላኪዎቹ መልእክት ስላስተላለፈ ወዲያው አባ ሳዊሮስና አባ ሉቃስ ወደፓትርያርኩ ሄደው “እኛው በስምምነት እንጨርሰዋለን የመንግሥት ሹም አይምጣ” ብለው ለማግባባት ሞክረው የነበረ ቢሆንም፣ ፕትርያርኩ ግን “እንድ ጊዜ ጥራ ብላችሁኛል በ9 ሰዓት ሚንስትሩ ይመጣሉ” ባሉት መሠረት ስብሰባው በ9 ሰዓት ተጀምሮ እስከ 12 ሰዓት መቀጠሉ ታውቋል፡፡

በስብሰባው ላይ ከተናገሩት ብፁዓን አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ “እንደራሴነት የጠየቁት ለቤተ ክርስቲያን አስበው ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳን ልኳቸውና ገንዘብ ሰጥቷቸው ነው” በማለት የተናገሩ ሲሆን፣ እርሳቸው እንዲህ ማለታቸውን ተከትሎ የአጀንዳው አቀንቃኝ ሆነው የሰነበቱት “ምን ያለበት ምን አይችልም” እንደሚባለው ለጵጵስናቸው በማይመጠን መልኩ ተንጫጭተዋል፡፡ በተለይም አባ ሳሙኤል አባ ሳዊሮስና አባ ዮሴፍ ማንነታቸውን በሚያጋልጥ ሁኔታ ያልተገባ ትርፍ ቃል በሚናገሩበት ጊዜ ክቡር ሚኒስትሩ “ከተራ ሰው እንዴት ልለያችሁ?” በማለት በጳጳሳቱ ሁኔታ ሀፍረት የተሰማቸው መሆናቸውን ገልጸው፣ አመፅ የሚያነሡ ከሆነ መንግሥት ጣልቃ እንደሚገባ በማሳሰብ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ውይይቱ እንዲቀጥል ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡
በውይይቱም እንደራሴ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም በሚለው ላይ ለጥቅምት አጥንቶ የሚያቀርብ ኮሚቴ የተሰየመ ሲሆን፣ ፓትርያርኩ ያላመኑበትና ይሁንታ ያልሰጡት እንደማይመረጥ ሚንስትሩ የቤተክርስቲያኒቱን ሕግ በማጣቀስ በስብሰባው ላይ አመልክተዋል፡፡ ሕጉን የሚያወጡትም ሊቃውንቱ ጭምር እንጂ እነርሱ ብቻ እንደማይሆኑ ገልጸው ተስማምተዋል፡፡ በሚንስትሩ ጨዋነት የተሞላው አነጋገር የአድመኞቹ ቁጥር አንሶ ታይቷል፡፡
ከሴረኞቹ አንዱ አባ ዲዮስቆሮስ “የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይ ህገ ቤተክርስቲያን ላይ አለ፡፡ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት ጽ/ቤቱ ግን የለም ስለዚህ ይነሱልን” ሲሉ ከአንድ ሊቀ ጳጳስ የማይጠበቅና ለሲኖዶስ የማይመጥን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ሚንስትሩም በልዩ ጽ/ቤትም ሆነ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሚሾሙት ፓትርያርኩ ያመኑበትን ነው፡፡ ምን አልባት የሚያስነቅፍ ነገር የሚሰሩ ሰዎች ከተቀመጡበትም በራሳቸው በፓትርያርኩ ይነሳሉ እንጂ እንደዚህ ባለ ሁኔታ የሚለወጥ ነገር የለም ሲሉ ህገ ቤተክርስቲያንን አክብረው እንዲሰሩ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ሊላው ቢቀር ሥራ አስኪያጅ በምልአተ ጉባኤው ቢመረጥም እንኳን የፓትርያርኩ ይሁንታ ከሌለበት እንደማይጸና ሕጋችሁ ይደነግግ የለም ወይ? በማለት እስካሁን እየሄዱበት ያለው መንገድና በአድማና በአመፅ የፓትርያርኩን ሥልጣን ለመሸርሸር የሚደረገው ጥረት ሕገወጥ ተግባር መሆኑን በተዘዋዋሪ ነግረዋቸዋል፡፡


25 comments:

 1. yeseyitan telalakiwochu tinish megibiya ber sitagegnu ema.....

  ReplyDelete
 2. thank you very much.

  ReplyDelete
 3. AMSTEBGNAWU YE MAHIBERE KIDUSAN AWUDE RAYI 750000 SEW GOBEGNEWU. KEZIM KETIKET SHIYACH MAHIBERE KE 15 MILLION BIRR AGEGNE.

  ReplyDelete
 4. The wisest King ever said that there is time for everything. MK's time is now. The beginning of the end in in progress. You dug a hole big enough to get you and followers get buried in it.
  Proverbs 26:22-28 says it all!!
  22 The words of a whisperer are like dainty morsels,
  And they go down into the innermost parts of the body.

  23 Like an earthen vessel overlaid with silver dross
  Are burning lips and a wicked heart.

  24 He who hates disguises it with his lips,
  But he lays up deceit in his heart.

  25 When he speaks graciously, do not believe him,
  For there are seven abominations in his heart.

  26 Though his hatred covers itself with guile,
  His wickedness will be revealed before the assembly.

  27 He who digs a pit will fall into it,
  And he who rolls a stone, it will come back on him.

  28 A lying tongue hates those it crushes,
  And a flattering mouth works ruin.

  ReplyDelete
  Replies
  1. God bless you man You got them exactly!!!

   Delete
 5. Betecrstiyanin yawarde mahberna degafiwochachewon egziabher amlak lezih
  Meskin hizb sil yastagselen.

  ReplyDelete
 6. Aye senodos aya bekerbachehu every 6 month chekchek

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዳንተ አይነት ደነዝ ሲኖዶስን ሊሰድብ ማፈሪያ!!!!

   Delete
 7. Aye senodos aya bekerbachehu every 6 month chekchek

  ReplyDelete
 8. Becarful abatachen next time mk need kill you like aba Paulus.

  ReplyDelete
 9. የተከበሩ አቶ ካሳ ተክለብርሃን በመጀመሪያ ያገር ሽማግሌዎች በጉዳዩእንገባ ዝምታን እስከመቼ ብለን ነበር እግዚአብሔር ግን በርሶ ላይ አድሮ ገላገለን እርሶም ቀሚስ ለብሰው ቆብ አድርገው መንፈሳዊ የሚመስሉትን አባት መሳዮቹ የማህበሩ አባላትን በስብሰባው ተገኝተው ለመረዳት አበቃዎ። ከሁሉም በላይ የሆነው አልፋና ኦሜጋ እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥዎ የዘሩት ሁሉ ይብቀል፡ መርቀንዎታል። እባክዎ የተከበሩ አቶ ካሳ፡ ይህንን ሀገር በቀል የሀገር፡ የወገን፡ የእድገት ጠላት፡ የሆነ እራሱን ቅዱስ ብሎ የሰየመ የሁከት ማህበር ይገላግሉን። ይኸ ሁሉ ጫጫታ የማህበሩ ብር የሚያመጣው ነው። እረ ስለ እግዚአብሔር እንኳን ይህን የሁከት ማህበር ቀርቶ አፍሪካን በሙሉ መደምሰስ እችላለሁ ያለውን ነፍሰ ገዳዩን ደርግን እንኳ አሽመድምዳችሁ ጥላችዃል። የተከበሩ አቶ መለስ ዜናዊ በስብሰባ ላይ ሲናገሩ ሰለፌ ማለት የማህበረ ቅዱሳን ግልባጭ ሲሉ ተናግረዋል። ይህ መልእክት ሊረሳ አይገባውም። አሁንም በድጋሚ እግዚአብሔር ይጠብቅዎት እያልን እንፀልያለን።

  ReplyDelete
 10. inate wushetamoch yaltetsfe yemitanebu yedabilos telalakiwoch Ministrum bihon Abatoch yalutin newu yatsedekut tebabochina gotegnoch yiwetalu papasum kesinodosu wesane wichi meramed indemayichilu awukewal yechelemawu hayilachewu keshefe kirstos betun liyatseda tenestuwal silezih yedabilos gibraberoch min tihonu Mk awuderiyun akahede fetari yimesgen

  ReplyDelete
 11. put the following cote inconsideration and make your day. I am pride of Mahibere Kidusan "በፓትርያርኩ እንደራሴ አስፈላጊነት ከስምምነት ተደረሰ፤ “ወቅቱን የጠበቀ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ቅ/ሲኖዶሱ ተስማምቶ ካልወጣ ለሕዝብም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ብለዋል

  ReplyDelete

 12. በፓትርያርኩ እንደራሴ አስፈላጊነት ከስምምነት ተደረሰ፤ “ወቅቱን የጠበቀ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ቅ/ሲኖዶሱ ተስማምቶ ካልወጣ ለሕዝብም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ብለዋል

  ayedelem menefesaweyane Abatochachen Alemaweyane Merewchachen enkane Enderase be meshome yaminalo ....Menfese yeteleyachewe Aba Mahtias Beate Kiresetane endefelego lemaderege selemefelego Eredate Ahyasefelegegnem ..yelaloooo ye megeremo Ye Aganete Keteregna Nachewe ....Egizahber Lebona yesetachewe ke segaweyane ken Kass Tekele Birhane yemayeshalo Abate selalen betam new Yazenewe

  ReplyDelete
 13. ማህበረ ቅዱሳ አቅዋም የለውም እኔ ይገርመኛል ውሸታም ከሐዲና ተሳዳቢ ነው አባቶችንም ሳይረዱት ያዳምጡታል ለምን እንደማይነቁበት ይገርመኛል የተማረ ወሮበላ መሆኑን ጠንቀቅ ነው እንደሽንፍላ አይጠራም ብዙ የጓዳ ጉድ አለው

  ReplyDelete
 14. ማህበረ ቅዱሳ አቅዋም የለውም እኔ ይገርመኛል ውሸታም ከሐዲና ተሳዳቢ ነው አባቶችንም ሳይረዱት ያዳምጡታል ለምን እንደማይነቁበት ይገርመኛል የተማረ ወሮበላ መሆኑን ጠንቀቅ ነው እንደሽንፍላ አይጠራም ብዙ የጓዳ ጉድ አለው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተነቅቶበታል እኮ ግን በጥቅምና በነውራቸው ስለያዛቸው ነው

   Delete
 15. እባካችሁ በእምነታችን አትምጡ! መንግስት ከቤተ እምነት እጅን ይሰብስብ! ምኒስትሩ የቤተ ክርስቴያናችን የመጨረሻ ስልጣን የሲኖዶሱ መሆኑን አለማወቃቸው እና ፓትርያርኩ እንደራሴ እንዳይመረጥ ከፈለጉ በቃ አይመረጥም ማለታቸው የእምነቱ ተከታይ ላይሆኑ ይችላል! የሲኖዶስ ውሳኔ ይከበር።

  ReplyDelete
 16. በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንዲህ ያለ ሁከትና ብጥብጥ በመነሳቱ በጣም ያሳዝናል ሌላዉን ስርዓት የምታስይዝ ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ እልበኞች ወረዋት እንዲህ ክብሩእ ሲዋረድ ማየት ህሊናን ያደማል
  በእዉነት እንደቤተ ክርስቲያናችን ስራት የፓትርያርኩ ቃል መከበር እለበት
  ፓትርያርኩ የጳጳሳቱ ሁሉ እባት ናቸዉ።
  ጳጳሳቱ እባታቸዉን እባታችን ብለዉ ካላከበሩ እነሱን ማን እባት ብሎ ይጠራል።

  እግዜብሔር እስተዋይ ልቦና ይስጣቸዉ።

  ReplyDelete
 17. ጉድ ነው!መንፈሳዊ ተቋሟ አንገት ስታንጋጥጥ ታምራትን አንገት ስትደፋ ጥበባትን(ከመሮጥ ማንጋጠጥ፤ከታዳጊ ጌታ ሰግደድ ያለ ቦታ)፩ኛ ቆሮ.፩.፳፪ ተጠባባቂ እንጂ አስታራቂ ሆናም አታውቅም ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት ካልሆነ በስተቀር፤ እንዲያውም በግራኝና በዘርዐ ያዕቆብ ጊዜ ከዚያም በኋላ ከነገሥታት እየተለጠፈች የሊቃውንትን አንገት ስታሰይፍ እውነተኛ አማኞችን ስታስገርፍ
  በአመጽና በግፍ ተሞልታ የምትውተፈተፍ ተቋም ናት። የተባለው እውነት ቢሆን ኖሮ ከጳጳሳት
  ጀምሮ እስከታችኞቹ አገልጋዮች ድረስ በቀላሉ አጠገባቸው የሚገኘውን ቅዳሴ ሕቱ ርእሰክሙ
  (ራሳችሁን መርምሩ ያላችሁበትን ደረጃ አስከብሩ)የሚለውን አንድ ኀይለ ቃል ተገንዝበው ራሳቸውን በተቈጣጥሩ መንፋሳዊ ተቋሟንም ባስከበሩ ነበር እንዳለመታደል ሆኖ አልተፈጸመም አሁንም ጊዜው አለ ጸሐይ አልጠለቀም ቅዳሴውን ያውም አጭር አረፈተ ነገር ሕቱ ርእሰክሙ
  የሚለውን እስከ አሥራ ሁለት ጊዜ መላልሰው እንዲያነቡት አደራ እንላለን ይህም ለራሳቸው
  ህልውና ሲባል ነው።

  ReplyDelete
 18. ማቅ ውሸታም አድመኛ በታታኝ ተሳዳቢ ነው አባቶች በሱ ከተመራችሁ ህዝቡን በጣም ነው የሚያዝንባችሁ ነብሰ ገዳይ ተደባዳቢን ነውረኛ ስለሆነ አባቶች እባካችሁ በቀሚሰችሁ ስር አትደብቁት ታማኝ ሁኑ ወደፊት አክባሪያችሁን ደግፉ ምን ይታወቃል ወደፊት መታሰቢያ አቁሙልኝ ወይም ወይም ቤተክርስቲያን አቁሙልኝ ከፈፍ ሲልም ምን እንደሚጠይቅ አናውቅም ጠንቀቅ ነው እንደ ሽንፍላ አይጠራም ብዙ የጓዳ ጉድ አለው ጠንቋያም ነው መተተኛና መርዘኛ ነው እናንተ ጉቦ እንስጥ የሚል አባላት ያሉት ነውረኛ ማህበር ነው እኮ አቤት!!! አቤት!!! አቤት!!! ማለት ነው ወደ እግዚያብሄር ፤ እኛንም ይቅር ይበለን እግዜብሔር እስተዋይ ልቦና ይስጣቸዉ።
  ወንጌሉን እንዳንማር እንቅፋት ሆኑ መጽሀፈ ባልቴት ካልተማርንም አልተማርንም ማለት ነው በእነሱ ወንጌሉን እንማር እባካችሁ እንዳንበት ለንስሀ እንብቃበት
  እግዚያብሄር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 19. አባታችን አባማቲያስ ጽናቱን ይስጦት !!!!!!

  ReplyDelete
 20. አቶ ካሳተከብርሃን እውነትም ተክለብርሃን፤ ይህን ህዝበ ክርስቲያኑን ሰንጎ የያዘውን የዘመናት በሽታ ማስተካከልና ስርአት ማስያዝ እንዲቻል የችግሩ የዘመናት ምንጭ የሆነው ጉዳይ ላይ ጥናት ይደረግ እና ለመጨረሻ የሚሆን መፍትሔ ለዚህ ህዝብ ቢቸረው። መንግስት ሲሰሩ እና ሲያወርዱ የኖሩ ካህናት ናቸዉ፤ የዋዛ አይደሉም ጭራሽ አሁን ማቅ ተጨምሮ ደግም ልዪ ተአምር ይፈጠራል ብሎ ማሰብ ሞኝነት አይመስለኝም። አቶ ካሳ አሁን እንደታደጉን እንዱሁ ደግም ክርስቲያኑ ህዝብ ከወንጌሉ ብርሀን ጋር ሳይተዋወቅ ምፅአት አይቀሬ ነው እና ይታደጉት።መቸም የነዚህ ካህናትና የስውሩ ዘዋሪያቸው ነገር ሲሰላ ጉዳዩ አንዱ እንዳለው መንግስት እና ፓትሪያርክነት ለእኛ ብቻ ከሚሉት ክፍሎች ውጭ አይሆንም፤ በዚህ ምክንያት ስንት ምእተ አመት ህዝብ እየተናጠ ይኖራል። አአይቻልም። በቃ።

  ReplyDelete
 21. knij09jmn98uij

  ReplyDelete
 22. በበኩሌ አዲስ ነገር አይታየኝም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከፍተኛ ዉዝግብ ያስነሱ ጉዳዮችን ባብዛኛዉ ራሷ ቤተ ክርስቲያኗ ሳትሆን የምትፈታዉ ፖለቲከኞች በወሰኑላት ነበር የምትሄደዉ፡፡ ለአብነት ያክል የ ኤዎስጣጢዎስ እንቅስቃሴ በሰንበት ዕለት ዙሪያ በተነሳበት ጊዜ አጼ ዳዊት ነበር ሁለቱም ቀናት እንዲከበሩ የወሰነላት፡፡ በኋላም ከ ስላሴ ዉጪ ለሌላ መስገድ አይገባም …… ብለዉ እስጢፋኖሳዉያን በተነሱ ጊዜ አሁንም አጼ ዘርዓ ያቆብ ነበር የቅጣት ዉሳኔዉን ያስተላለፈዉ፡፡ በ ተዋህዶ፣ በጸጋና በቅባት መካከል ለዘመናት የተደረገዉን ክርክር ቦሩ ሜዳ ላይ ከጎጃም የመጣዉን መሪጌታ ምላሱን ቆርጠዉ ተዋህዶን አዉጀዉ የተነሱት አጼ ዮሃንስ ናቸዉ፡፡ ይን ስል በበቂ ምንጭ ተመርኩዠ ነዉ፡፡ ያም ሆኖ ግን ፖለቲከኛ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንዲገባ አልደግፍም፡፡

  ReplyDelete