Saturday, June 25, 2016

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን ፕሮግራሟ መጀመሩ ተበሠረ

Read in PDF

ቤተ ክርስቲያኒቱ የ24 የቴሌቪዥን አገለግሎት መጀመሯ ተበሠረ፡፡ ሰኔ 16/2008 ቅዱስ ፓትርያርኩ ባሰሙት ንግግር የቴሌቪዥን ሥርጭቱ የተበሠረ ሲሆን፣ የንግግራቸው መጀመሪያ ያደረጉት ቃለ ወንጌል ‹‹አማን አማን እብለክሙ ዘይሰምዕ ቃልየ ወየአምን በዘፈነወኒ ይረክብ ሕይወተ ዘለዓለም፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛል፤ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይሄድም›› (ዮሐ. 524) የሚል ነው፡፡ መልእክቱ ለሰው የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት፣ ከሞት ወደ ሕይወት ለመሸጋገርና ወደፍርድ ከመሄድ ለመዳን ቃሉን መስማት ወሳኝ መሆኑን የሚያስገነዘብ የጌታችን ቃል ነው፡፡ በዚህ ቃል ንግግራቸውን የጀመሩት ፓትርያርኩ ምእመናንንና ምእመናትን በሚዲያ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ይህን ያደረገ እግዚአብሔርን “ክብርና ምስጋና፣ አምልኮትና ስግደት ለእርሱ ይሁን” በማለት እግዚአብሔርን ወድሰዋል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉ በላይ ነው፤” ያሉት ቅዱስነታቸው የቃሉን ታላቅነትና ሕያውነት ተግባሩንም በጥልቀት ያብራሩ ሲሆን ቃሉ በሰው ሕይወት ውስጥ የሚያከናውነውን ዋና ግብር እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፡፡ ፍጡራንም በእርሱ ሕይወትነት ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ፣ ዛሬም ሆነ ወደፊት ሰዎች ከፍርድ ነጻ ሆነው የዘለዓለምን ሕይወት የሚያገኙ ይህንን ቃል በመመገብ ነው፤ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የሆነ ሕይወት ሊኖር አይችልምና፡፡ ይህ እውነት የታወቀውና ሊታወቅ የሚችለው በእግዚአብሔር መገለጥ ብቻ ነው፤” ከዚህም ንግግራቸው የተከፈተው የቴሌቪዥን ጣቢያ በዋናነት ይህ የእግዚአብሔር ቃል ሊተላለፍበት የሚገባ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል አገልግሎቷን ከዚህ ቀደም ጊዜው በፈቀደው ቴክኖሎጂ ስትጠቀም የአሁን የመጀመሪያዋ እንዳልሆነ መረጃዎች ይጠቁሟሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ከ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የወንጌል ትምህርትን በኢትዮጵያ ሬዲዮ ጣቢያ ስትሰጥ የነበረ ሲሆን፣ በየዕለቱ ዘወትር ጠዋት ለ15 ደቂቃ ያህል ጸሎትና ትምህርተ ወንጌል ይተላለፍ ነበር፡፡ እንደገናም በ1955 ዓ.ም የብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ ሲከፈት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ስር በተቋቋመው ሐዋርያዊ ድርጅት አማካይነት በየዕለቱ ለ30 ደቂቃ ያህል ትምህርተ ወንጌል ስትታስተላልፍ አገልግሎቷ እስከ ደርግ መነሣት ድረስ ዘልቆ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን በየአውደ ምሕረቱና በፕሬስ ውጤቶች ካልሆነ በቀር ትምህርተ ወንጌልን ለማስተላለፍ የተጠቀመችበት አጋጣሚ አልነበረም፡፡

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ታኦሎጎስና ቃለ ዓዋዲ ከፍተቱን ለመሙላት የየራሳቸውን ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም፣ በማኅበረ ቅዱሳን በኩል እንደ ተቀሰቀሰ በሚታመነው ታኦሎጎስንና ቃለ ዓዋዲን ለማዘጋት በተደረገው እንቅስቃሴ የራሱም መርሐ ግብር ጭምር እንዲዘጋ ተደርጎ ሕዝቡ አማራጭ በማጣቱ የሌሎችን ፕሮግራሞች ለመስማትና ለማየት የተገደደበት ሁኔታ ለወራት ዘልቋል፡፡ ነገር ግን አሁን የቴሌቪዥኑ ፕሮግራም መጀመሩ ጥሩ አጋጣሚ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ ሆኖም እንደሚገባ ካልተሰራበትና የሕዝቡን የልብ ትርታ ባለማድመጥና ዘመኑና ባለመዋጀት ከትምህርተ ወንጌል ውጪ ሌሎች ያረጁና ያፈጁ ነገሮችን ማስተላለፍ ከሆነ የቴሌቪዥኑ መከፈት ፋይዳ አይኖረውምና ለትምህርተ ወንጌል ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ በኢቢኤስ ይተላለፉ ከነበሩት ሶስቱ ፕሮግራሞች ሕዝቡ በንቃት ይከታተል የነበረውና በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣው የትኛው እንደነበረም መለስ ብሎ መቃኘት ያስፈልጋል፡፡ ይልቁንም በብሥራተ ወንጌል ይተላለፉ የነበሩ ስብከቶችና ትምህርቶች ይዘት ምን እንደ ነበረ መለስ ብሎ ማየትና ከዚያ የተሻለና ዘመኑን የዋጀ የእግዚአብሔር ቃል በልዩ ልዩ መልክ ሊቀርብበት ይገባል፡፡
     
በዚህ ረገድ ቤተክርስቲያኒቱ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት እጅግ ወደኋላ እንደቀረች ምስክሩ እስካሁን ድረስ አንድ እንኳ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሳይኖራት መቆየቷ ነው፡፡ እስካሁን አንድ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በላይ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ሊኖሯት ይገባ ነበር፡፡ የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንኳ በዚህ አቅጣጫ ምን ያህል እንደተራመደች መመልከት ይቻላል፡፡ በአሁኑ ወቅት እንኳን ወደ 8 ያህል የቴሌቪዥን ቻናሎች አሏት፡፡ ስለዚህ የእኛም ቤተክርስቲያን ብትዘገይም አንድ ብላ የጀመረችውን የቴሌቪዥን አገልግሎት በጥራትና በስፋት ዘመኑንም በዋጀ መልኩ በመጠቀም እያሰፋች እንደምትሄድ የብዙዎች ተስፋ ነው፡፡


9 comments:

 1. ለሁሉም የቴሌቢጅን መንፈሳዊ ፐሮግራም ዋናው እና ጀማሪው ታኦ ሎጎ ነው።ሁሉንም ሲበልጡ ሰይጠን በዘመድኩንና በ ማህበረ ሰይጣን አድሮ ለግዜው አጨናገፈው።በተለይ የማህበሪቱ ኘሮግራም እንቅል የሚያመጣ ነው የነበረ።

  ReplyDelete
 2. ልዩ ወንጌል በመስበክ በምድራችን/በሕዝባችን ላይ የሆነብንና እየሆነ ያለብን መርገም(ገላ1፡6-10)እንዳይቀጥል የመንግሥቱ ወንጌል ብቻ(ሮሜ 1፡1-5)እንዲሰበክ ለመንፈሳዊ አባቶቻችን ማስታዋልንና ብርታትን ይስጣቸው!

  እውነቱ ይነገር

  ReplyDelete
 3. ጥሩ ጽሁፍ ነው።

  ReplyDelete
 4. Kehulum wegen seat teseto wengelen yisbeku. Teruwn merach hezeb bihon teret terachochen yaswegedlen neber. Yegeta wengel yisebekal engdih seytan cherqehen tal. Ellelelel...

  ReplyDelete
 5. ስለ ሰማእትነት ብዙ ትንተና ሰጠህ ቁርስህን ለደሃ ተዉ ቢሉህ ግን አቧራ ታስነሳለህ

  ReplyDelete
 6. ወንጌል አይደለም እየተሰበከ ያለው ዶክመንተሪ ምናምን እንጂ።ቤተክርስቲያነ አላማዋን ስታለች ህዝቡም ህረኛ እንደሌለው በግ እየተቐበዘበዘ ነው።አላማዋ ወንጌል መሆን ነበረበት።

  ReplyDelete