Wednesday, June 1, 2016

የሰሞኑ የሲኖዶስ ውሎና የማህበረ ቅዱሳን ቡርሳ ጳጳሳትየእርቅ የሰላምና የመረጋገት ምንጭና ባለቤት ናት ተብላ የምትታወቅ ቤተክርስቲያን በአመጻ እና በተንኮል ከተሞሉ ከመንፈሳዊነት ይልቅ ዘረኝነትና ቡድንተኝነት በሚያጠቃቸው አንዳንድ ጳጳሳት አማካኝነት የሲኖዶሱ ስብሰባ በታሪክዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለመስማማት ሊበተን ችሏል። አለማውያንና ሥጋውያን ነገስታት ሲጣሉ ታስታርቃለች ተብላ ትጠበቅ የነበረችው ቤተክርስቲያን በአለማዊ መንግሥት ሥር ሆና ሽምግልና ለመቀመጥ ተገድዳለች።
የተጣሉ ሊያስታርቁ የሚጠሩ ጳጳሳት የሠላምና የዕርቅ መንፈስ ርቆዋቸው በዱርዬ ምላስ ሲዘላለፉ ከርመው በጸብ ለመለያየት ተገድደዋል። ኋላም ህጋቸውን የሚያስጠናቸው ባለሥልጣን መሀላቻው ቁጭ ብሎ የሚተዳደሩበትን ህግ ዝርዝር ሀሳብ እያስረዳ የስብሰባን አካሄድ አስተምሯቸዋል። አንድ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃል አምናለሁ አስተምራለሁ ትልቁ የቤተክርስቲያን መሪና ወሳኝ አካል እኔ የሚል አካል ከተራ ሰው በምን ልለያችሁ ተባለ ሲባል መስማት በጣም ያሳዝናልም ያሳፍራልም። ከተራ ሰው በምን ልለያችሁ መባሉ ቢያሳዝንም እውነትነቱን ግን የሳተ አይደለም።

ምንም ጊዜ ቢሆን የራሳቸው አጀንዳ የሌላቸውና የማኅበረ ቅዱሳንን አጀንዳ እንደ ጭን በቅሎ ተጭነው የሚጓዙት የጀርባ ቁስል ያለባቸውና ብሔር ተኮር ጳጳሳት አየር አንደአጠረው ጎማ በቀን ሶስት ጊዜ ከማኅበሩ የሚሞሉትን አጀንዳና የሙግት አቅጣጫ በመከተል ሲኖዶሱን ላለፉት አራት ቀናት ሲያምሱና ሲበጠብጡ ሰንብተዋል። የህጋቸውን ሀሁ ተምረው አደብ እስኪይዙ ድረስም እንደ ሜዳ አደግ ሥድ ፓትርያርኩን ሲዘልፉ ከርመዋል። ማኅበረ ቅዱሳንንም የጫናቸውን ጭነት በአግባቡ እንዳራገፉለት በመረዳት በብሎጉ አበጃችሁ በርቱልኝ ሲል ሰንብቷል።
እነዚህ እንደ አንድ የወታደር ክፍለ ጦር ራሳቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን በቡርሳነት የለዩ ጳጳሳት እንደራሴ ካልተሾመ በሚለው አጀንዳ ላይ ያገነገኑበት ዋነኛው ምክንያት ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳን በህግና በሥርዓት ይተዳደር ልኩንም ይወቅ በማለታቸውና ማኅበሩም በእምቢተኛነት በመጽናቱ ሊወሰድበት ከሚገባው እርምጃ ለመታደግና የፓትርያርኩን ሥልጣን ለመቀነስ ነው። እንደራሴ ላልታመመ ላልተጎዳ ችግር ላላጋጠመው ፓትርያርክ አይሾምም። እንራሴ ማለት ተጠባባቂ ፓትርያርክ እንደ ማለት ነው። ታድያ በዚህ ጊዜ ፕትርያርኩ ምን ሆኑ ተብሎ ነው ተጠባባቂ ፓትርያርክ የሚያስፈልገው?
ቡርሳዎቹ ጳጳሳት ያልገባቸው ነገር ማኅበሩ ሀሳቡን እስካልተቀበሉና ያሉትን የማይፈጽም ከሆነ ለእነርሱም የማይመለስ መሆኑን ነው። በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ የነበረው የሲኖዶስ ንትርክ ምንጩ ፓትርያርኩ ለማኅበሩ ባለማጎድደዳቸው መሆኑን የሚያጡት አይደለም። አቡነ ማትያስ ሥልጣን እንደያዙ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ምንም አይነት ችግር ስላልነበረ የሲኖዶሱ ስብሰባ ያለምንም ችግር ይጠቃለል እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። አሁን ማቅ ሥርዓት ትያዝ በማለታቸው ግን ማኅበሩ ሥልጣን የሚቀንስ አጀንዳ በቡርሳ ጳጳሳቱ አማካኝነት ይዞ ብቅ አለ። ሁልጊዜም ቢሆን በዓለማ እና ለእውነት የማይቆም ሰው የተጫነበትን ነገር ተቀብሎ ከመሄድ ያለፈ ሌላ አማራጭ ሊኖረው አይችልም።
አሳዛኙ ዜና ራስዋን የሰላም ጠበቃ አድርጋ የምታስብ ቤተክርስቲያን ሰላምን ፈልጋ ወደ ዓለም መሄድዋ ነው። አሳዛኙ ዜና ሕዝቡን ወደ ችግዚአብሔር ከፍታ ያደርሳሉ የተባሉ ጳጳሳት የእውነት የአካሄድና የእግዚአብሐየር ቃል አቅጣጫ ጠፍቶዋቸው ሲወናቸሩ ማየት ነው። ቡርሳዎቹ ጳጳሳት ከትልቅዋ ቤተክርስቲያን ዓጀንዳ ወርደው ራሳቸውን ለአንድ ማኅበር ዓላማ ማስገዛታቸው ነው።
ማህበረ ቅዱሳን ስብሰባውን ወደ ፈለገው አቅጣጫ ለመጠምዘዝ ብዙ ቢታታርም አልሆነለትም። ምንም እንኳ መንግስት ይገኝ እና ይዳኘን በሚለው ሀሳብ እኛም እንደእነርሱ ባንስማማም ነገሩን ያልተስማማንበት ምክንያት ግን ለየቅል ነው። እኛ ስብሰባው የማኅበረ ቅዱሳንም የመንግስትም ጣልቃ ገብነት ሳያስፈልገው ቅር   ጹን ጠብቆ ይሂድ የሚል የሚል ሲሆን ማቕ ደግሞ መንግስት አያስፈልግም እኛ ግን እንደፈለግን እንቧችርበት የሚል ሀሳብ ነው።
ዳንኤል ክብረት መንግስት ስብሰባው ላይ ከተገኘ እኛ መንፈስ ቅዱስ ወስነናል የሚለው ቀርቶ እኛ እና መንግስት ወስነናል ሊባል እኮ ነው ሲል ጽፏል። ዳኒ አንተን ያናደደክ እኛ እና መንፈስ ቅዱስ ወስነናል አለመባሉ ሳይሆኑ እኛ እና ማኅበረ ቅዱሳን ወስነናል አለመባሉ ነው። የእናንተ አካሄድ አድማና ሸፍጥ ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ገፎቶ ራስን በቦታው ላይ የማስቀመጥ አካሄድ መሆኑ ግልጥ ነው።
ቤተክርስቲያን ምዕመናንዋን በከፍተኛ ሁኔታ እያጣች ባለችበት ሁኔታ ወደ ተሾሙበት ሀገረ ስብከት ሄደው ለመስራትና ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት እቅድና ዓለማ የሌላቸው ጳጳሳት ማቅ ተነካ ብለው እምቡር እምቡር ከማለት ባለፈ ምንም ሥራ ላለመስራት  አይናቸውን በጨርቅ አስረው ራሳቸውን እያሞኙ ተቀምጠዋል።
እንዲያ ያሉ ለግርግር የተመቹ ቡርሳ ጳጳሳትን ይዛ የቤተክርስቲያን መጨረሻዋ ምን ይሆን?

36 comments:

 1. Egziabher Libuna yistachuh Bego Maseb ena Mesrat yemaywedew yegibir abatachuh hulem yewushet mabel yimolabachuhal. aye alemeshashal???

  ReplyDelete
 2. መቸም እናንተ የማታመጡት የለ ደግሞ ቡርሳ ምን ማለት ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. የከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃለት በቀድሞ ዘመን የወታደር ክፍል መጠሪያ ነው ይለዋል።

   Delete
  2. ከሳቴ ብርሃን የሚባል መዝገበ ቃላት አለ እንዴ?

   Delete
  3. እንግዲያማ!!!!!! ድንቅ መዝገበ ቃላት ነው።

   Delete
 3. hahahahahahaha ewnetem buresa

  ReplyDelete
 4. enante ye diablos ye gibir lijoch, be sidib siltenaw professor hunachuhal ikko!

  ReplyDelete
 5. እነዚህን የወንጌል ጠላት የሆኑ ጳጳሳትና ማህበር እግዚአብሄር ከሰመይ ካልፈረደ በቀር ይህ ምስኪነወ ህዝብ ሳይድን መጥፋቱ ነው።እኔ ነየኛ ሀገር ጳጳሳት ጥቅም አይታየኝም።እንድ ማእከላዊ የሆነ ቦታ ለይ ተቀምጠው ሀገር የሚያምሱና የሚያሳምሱ ናቸው።የተጠሩበትን አላማ የሳቱበት ምክንያት በትክክል ተጠርተው ሳይሆን በዘር ተጠራርተው ስለተሰበሰቡ ቤተ ክርስቲያንዋን የቅርጫ ስጋ አደርጓት።በመንፈስ የተጠሩ ቢሆኑ ኖሮ አላማቸው ሁሌ ሰላም እና ፍ ቅር ይሆን ነበር።ስራ ይስሩ ምንድነወ አነድ ቦታ መዘፍዘፍ።እዚህ አዲስ አባ እንኳን በየደብሩ የሰርክ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ያስተምሩ ይባርኩ ያፀናኑ።አለበለዚያ ገዳም ገብተው ይቀመጡ።እርባና ቢሶች ሆኑ እኮ።በነሱ ምክንያት ለምን ቤተ ክርስቲያን ትታመሳለች።እስላምና ጴንዘጤ ቢበዛ ምን ይደንቃል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ማን ሆነህ ነው እንደዚህ የሚስደነፋህ??? አናውቃችሁም እንዴ በያዳራሹ እንዴት እንደምትዘረሩ!!! እናንተም ለዚህ በቃቸሁ አባቶቻችንን ለመተቸት "ውሃ ሸቅብ አይፈስም እሺ ጠንቀቅ እያልሽ ጀለሴ አረጋጊው!!!"

   Delete
 6. Hahaha burnt.የምትሉት ሁሉ ጠፋችሁ እኮ። የዲያብሎስ አፋችሁ ሁሉ ተሳሰረ።

  ReplyDelete
 7. ብርሳ ቡርሳ ቡርሳ what a nice name

  ReplyDelete
 8. ለቡርሳዎቹ ጳጳሳት
  ህሊና የሚባለውን ነገር ለነውራችሁ ሸቅላችሁት
  ዓላማ የሚባለውን ነገር መናጆነት አድርጋችሁት
  የምትሰሩት ሥራ ሁሉ በታሪክ ፊት ተጠያቂ ከመሆን አያድናችሁም።

  ReplyDelete
 9. ቡርሳዎቹ እኮ ዛሬ የጀመሩት አይደለም ንግሥና እና ጵጵስና ከእኛ አይወጣም ( ዘኢይትወጽ) ነው የሚባለው እያሉ አገሪቷን ለሺህ አመታት ሲያምሱ የኖሩ ናቸው። እንደዚያ ባይሆን ወንጌል በተዋዶ መላ አፍሪካን ባዳረሰ ነበር። የአገሬ ህዝብ በፋራ ጎኑ እንደተኛ ከወንጌሉም እንደራቀ ይኸውና ዘመኑ ከፋ፤ ንስሐ እና ፋራ አለመሆን(ሁሉን መጠየቅ ፣ ማንበብ፣መመራመር፣ ዝግ አለመሆን፣ ከስሜት መፅዳት፤ መንፈስቅዱስን ያስገኛል።it is not really spiritual for these bishops to adamantly deter the spread of the word of GOD and still make the church the house of evil thoughts; well; I am sorry for them to behave so naive and act away from the holly spirit.

  ReplyDelete
 10. ያሳዝናሉ።

  ReplyDelete
 11. ይህን መልእክት ለዻንኤል ክስረት ይድረስ ወንድሜ ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ ተንጋለህ የምትተፋው መልሶ አንተን እንደሚያቅሽሽህ እፈራለሁ፡ እግዚአብሔር የቀባቸውን ስትናገር እንዴት አልፈራህም፡ ፖትርያርኩን እምነት የለሽ አድርገህ ያንተን ድቁና እንዴት እንመን። ብቁ ነህ ትመራለህ ተብሎ የተሾመውን ሚኒስትር ከሀዲ ብለህ ኩሀዲ በሚመራበት አገር እንዴት ትኖራለህ። ፍሬን ከተበጠሰብህ ቆይቷል ነዳጅ ባትሰጠዉ መልካም ነበር ቢያንስ ጉዳቱን ይቀንሳል አላዋቂዎች እገሌ ይህን አደረገ ይላሉ ሊቃውንት በምን ምክንያት አደረገ ይላሉ መንፈሳውያን ግን ይፀልያሉ። አንተ ከሶስቱ ምድብ የትኛው ላይ ነህ ያለህ? ቤተክርስቲያን የናንተን ምክር ብትሰማ ትደሰት ነበር። ዛሬ የዋለው ሲኖዶስ እኛና ማህበረ ቅዱሳን ወስነናል ከማለት ውጭ እኛና መንፍስ ቅዱስ ወስነናል ማለት አይችልም። እባካችሁ የቤተክርስቲያኗን አንድነት አትበጥብጡ፡ አትከፋፍሉ። አቶ ዳንኤል ከየሜዳውም ከሚስትም ለወልድካቸው ልጆችህ እርግማን ባታቆይ ጥሩ ነበር ።።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዴት ትኖራለህ ? ለምን ለምንስቲሩ በቀጥታ ይህን ደብዳቤ አትልክላቸዉም ? ሃሳቡን በምክንያት እያስረዳ የሚፅፍ ሰዉ አሳጥታችሁን እንዳንተ እና እንደዚህ ብሎግ ሚስት ልጅ እያለ አሉባልታኛ ዜጋ እንድንሆን ነዉ አላማችሁ::

   Delete
 12. ከእግዚአብሔር አብ: ከእግዚአብሔር ወልድ: ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሆነ ሰላም ይብዛላችሁ::

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ የምትጽፉትን ጽሑፎች እያነበብኩ ነው:: ችግራችሁ ቢገባኝም እንደ እኔ እምነት ከማቅ ጋር የቃላት ጦርነት ውስጥ ከመግባት በጸሎት ለጌታ ማሳሰቡ የሚበጅ ይመስለኛል:: እንደሰማሁት ከማቅ በስተጀርባ ሆኖ የሚሠራ አጋንንታዊ ኃይል ያለ ይመስለኛል:: ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያውቅ ሰውን አይገድልም: አያሳድድም:: እነዚህ ሰዎች የተነሱት በናንተ ላይ ሳይሆን በጌታና በወንጌሉ ላይ ነው:: ጌታ ደግሞ በአላማው ላይ የሚቆመውን የሚታገስ አምላክ ዓይደለም:: በሳውል ላይ የደረሰውን እንስታውሳለን::

  ዘመናችሁና አገልግሎታችሁ ይባረክ:

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዝፍጥ ጅል

   Delete
  2. አጋንንትማ የት እንዳለ አንተ እራሱ ዘቅዝቆ የሚጫወትብህ መንፈስ በቅዥትህ ሁል ጊዜ እየነገረህ ስለሆነ አያሳስበኝም:ባንዳ የባንዳ ልጅ መናፍቅ የሉተር አዳራሽ ሄደህ አፈንድድ የሰይጣን አገልጋይ ድህረገጽ

   Delete
 13. ቡርሳ የሚለው ቃል ደስፈቅ አስኝቶኛል

  ReplyDelete
 14. [ቦርሳ] የሚለዉ ስም ይሻላል።
  ቦርሳ ማለት የወረቀት ወይም የእቃ መያዣ ማለት ነዉ
  እነሱም የማቅ እዠንዳ የታጨቀባቸዉ በራሳቸዉ ሀሳብ የማይሄዱ የማቅን ሃሳብ ተሽካሚ ቦርሳዎት ናቸዉ ።
  ያሳዝናል በጣም ያሳዝናል
  እኛም በእባቶቻችን ተስፋ ቆረጥን
  እግዜብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያናችን ይጠብቅልን።

  ReplyDelete
 15. የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። (የዮሐንስ ራእይ17:3)Ytebalew labte new yihich bete irstyan besintu af tisedeb!!!!!

  ReplyDelete
 16. ቅ/ሲኖዶስ የእንደራሴ ምደባ ደንብ አርቃቂ ኮሚቴ ሠየመ፤ ልዩ ጸሐፊው እና የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሓላፊው በአጭር ጊዜ እንዲነሡ አሳሰበ

  ReplyDelete


 17. ‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› ማለት ሊቀር ነውን?

  ቅዱስ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን እንደራሴ ሹመት በተመለከተ ለመወያት የያዘው አጀንዳ የመንግሥት ተወካይ ባለበት እንዲታይ መወሰኑን ዛሬ ጠዋት ሰማን፡፡ ከብጹዐን ጳጳሳት በቀር ካህናትና ቆሞሳት እንኳን የማይገቡበት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አማኝ ይሁን ኢአማኒ፣ ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን የማይታወቅ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝበት መጋበዙ የደረስንበትን የውርደት ደረጃ የሚያሳየን ነው፡፡
  በአንድ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ወሳኝ አካል መሆኑን ስናስበው፤ በሌላ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚደረገው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው፤ ውሳኔውም በሐዋርያት ሥራ እንደተገለጠው ‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› የሚባልበት ነው(የሐዋ. 15፣29) የሚለውን ስናየው ‹የመንግሥት ተወካይ ይኑርልን› የሚለውን ውሳኔ ኢሃይማኖታዊ ነው ያሰኘዋል፡፡ ለአንድ የሲኖዶስ ጉባኤ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት አልበቃው ብሎ ነው የመንግሥትን ተወካይ የሚጋብዘው? ‹ሱባኤ ይዘን፣ ጸሎት አድርገን፤ አንድ ገዳም ወርደን፣ ከእግዚአብሔር ጋር መክረን› አይደለም ይሉን አባቶቻችን፡፡ ‹የመንግሥትን ተወካይ ጋብዘን› ነው ያሉን፡፡ እንዲያውም ቀኖናው የሊቀ ጳጳሳቱ(ፓትርያርኩ) ጉዳይ ሲታይ ‹በመቀመጫቸው መካከል አንድ ወንበር አስቀምጠው፣ ቅዱስ ወንጌሉን በዚያ ላይ አኑረው፣ ሊቀ ጳጳሳቱ በፊታቸው ተቀምጦ፣ አንድነት ተነሥተው በሩን ዘግተው ይጸልዩ፤ የተሰበሰቡበትንም ጉዳይ በሥውር(በኅቡእ) ይመርምሩ› ነው የሚለው(ፍ.ነ. ዐ.168)፡፡ እንዴት ተደርጎ ነው የመንግሥት ተወካይ ባለበት የሚታየው? አግዚአብሔር ያየናል የሚለው ጠፍቶ ታዛቢ ቢያስፈልግ እንኳን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ለታዛቢነት አይበቁም? ቅዱስ ጳውሎስ ‹በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?› (1ኛቆሮ. 6፣5) ያለው ለዚህ ጊዜ አይሆነንም?

  በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝ መጋበዙ በአንድ በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና የሚነካ በሌላ በኩልም ሕገ መንግሥቱን የሚጥስ፤ በመጨረሻም ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚያፈርስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያለ ማንም ጣልቃ ገብነትና ታዛቢነት የራስዋን ጉዳዮች በራስዋ ሕግጋት፣ ቀኖናና ሥርዓት መሠረት የመወሰን መብት አላት፡፡ አባቶቻችን ከንጉሥ ሐርቤ ዘመን ጀምረው ከግብጽ ሲኖዶስ ጋር ሲሟገቱ የኖሩት ይህን ሉዐላዊነት ለቤተ ክርስቲያናቸው ለማስገኘት ነው፡፡ ጳጳሳትን ለማግኘት የግብጽ ሡልጣኖች መለማመጥ፣ የግብጽንም ፓትርያርኮች መለመን ሰልችቷቸው፡፡ ከግብጽ ቀድማ ክርስትናና የተቀበለች ሀገር፣ የራስዋን ጉዳይ ለመወሰን አለመቻሏ አስደናቂ ስለሆነባቸው፡፡ ከቤተ ክርስቲያንዋ ታላቅነትና ከሀገሪቱ ክብር ጋር ስላልተመጣጠነላቸው፡፡
  ዛሬ ያ ሁሉ ተረስቶ መንግሥትን በገዛ ፈቃዳቸው ‹አንተ በመካከላችን ካልተገኘህ አንሰበሰብም› የሚሉ አባቶች መጡ፡፡ ቀደምት አበው ‹አንተ ከኛ ጋር ሁን› የሚሉት ፈጣሪያቸው ነበር፡፡ ዘመን ተቀየረ፡፡ በቀደመው ጊዜ ‹መንግሥት ለምን በጉዳያችን ውስጥ ይገባል?› ነበር ክርክሩ፡፡ ‹አሁን መንግሥት ከሌለ ይህንን አጀንዳ አናይም› የሚባልበት ዘመን ላይ ደረስን፡፡ የፓትርያርክ እንደራሴ ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ እንደራሴውም የሚፈጽመው ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ነው፡፡ የሥልጣን ክልሉም በቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን ክልል ነው፡፡ ታድያ ለምንድን ነው መንግሥት ያስፈለገው? ይህንን ጥያቄ ፓትርያርኩ ጠይቀውት ይሆናል፡፡ እንደመከራከሪያ ቢያቀርቡት አይገርምም፤ ቢያሳዝንም፡፡ የምልዐተ ጉባኤው መቀበል ግን ሕመም ነው፡፡
  መንግሥትስ ቢሆን ምን ብሎ ነው ተወካይ የሚልከው? ምናልባት ‹ጠሩኝ፣ ሄድኩ› ካላለ በቀር፡፡ ሕገ መንግሥታችን መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ በግልጽ እየደነገገ እንዴት አድርጎ ነው በቀኖናዊ ስብሰባ ላይ የሚገኘው? ውሳኔውንስ ከየትኞቹ የቀኖና መጻሕፍት ጋር ሊያገናዝብ ነው? በጉባኤው የሚኖረውስ ሚና ምን ሊሆን ነው? ምን ዓይነት ወኪልስ ነው የሚወክለው? በየትኛው ሥልጣንና ሕግ ነው የሚገኘው? የዚህ ዓይነቱ አሠራርስ መጨረሻው ምን ይሆናል? በጉባኤው ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ የማን ውሳኔ ነው? ‹የእኛና መንፈስ ቅዱስ› ወይስ ‹የእኛና የመንግሥት›? መንግሥትም ጉዳዩን ሊያስብበት ይገባል፤ ‹ሲጠሩት አቤት› ሳይሆን ‹ሲጠሩት ለምን?› መሆን አለበት፡፡
  የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ኤጲስ ቆጶስ በዚህ ዓለም መኳንንት ርዳታ አንዳይቆም ያዝዛል፡፡ በእምነቱና በእግዚአብሔር ቃል ብቻ እንዲጸና፡፡ (ፍትሐ ነገሥት፣ 176፤ረስጠብ 21) በዲድስቅልያም ላይ ‹ከቤተ ክርስቲያን ሹሞች በቀር ሕዝባዊ አይፍረድ› ይላል (ዐንቀጽ 71)፡፡ ታድያ በምን ሕግ ነው የመንግሥት ተወካይ ባለበት የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤውን የሚያደርገው?
  ዛሬ እንደዋዛ የሚከፈተው በር ነገ እንዝጋህ ቢሉት አስቸጋሪ ነው፡፡ አንድ አባት የመንግሥት ተወካይ ይገኝልኝ ባለ ቁጥር የሚፈቀድ ከሆነ፤ ነገ ደግሞ ወንድሜ ባለበት፤ እናቴ ባለችበት፤ ሐኪሜ ባለበት፣ ፖሊስ በተገኘበት ይሄ አጀንዳ ይታይ የሚል ነገር መስማታችን አይቀሬ ነው፡፡ ጋባዡም፤ ተጋባዡም ቆመው ሊያስቡበት ይገባል፡፡ መቼም እንደዘንድሮ የእንጦንስና ጳውሊ ራእይ በተግባር የታየበት ዘመን የለም፡፡

  ReplyDelete
 18. ምድረ ኮተት ብቻ .....ድሮስ ከፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ምን ይጠበቃል
  ድልብ ጅሎች!!!

  ReplyDelete
 19. yegna Abatoche Zeregnete ...Politica ....Mosegnete ke Beate Kirestan yeweta yelalo ..... ፖሊቲካ_ከቤተ_ክርስቲያን_ይውጣ፤እውነት_ይገለጥ"
  “በጎጥ እና በቋንቋ የምንመራው እስከ መቼ ድረስ ነው?”
  “ቤተ ክርስቲያን መናገጃ አይደለችም! ሌቦች ይውጡ! ጉበኞች ይውጡ! ሠርተው ይብሉ! በቤተ ክርስቲያን አውደልዳይ አይብዛ፤ ቦታ ይሰጠው፤”
  “ቢሮው የማን ነው? በጉቦ የገባ ማን ነው? ወንጌሉ የሚሰበከው ለማን ነው? ሕዝቡ ተሰብኮ፣ ተሰብኮ ዐውቆታል፤ ከቢሮ ውስጥ ነው ችግሩ፤ ጥያቄው ሲጎርፍ አለመመለስ ነው ችግሩ፤ በዚኽ ዓለም ያልታመነ በእግዚአብሔር መንግሥትስ ቦታ አለው እንዴ? ትምህርቱ የጆሮ ቀለብ ኾኗል፤ ውስጥ ገብተው ሲያዩት ያስለቅሳል፡፡”
  “ምርጫ በሞያ ይኹን፤ በጎጥ አይደለም፤ ሲጠየቅ መልስ የሚሰጥ የሕዝብ አባት ይኹን፤ ድኻ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ የሚል አባት ከሌለ ትርጉሙ ምንድን ነው? መሰብሰባችንም ምንም በቈዔት የለውም፤”
  “አእምሯችን ሳይገራ፣ ለሕጉ ተገዥ ሳንኾን ከየትም ከየትም መጥተን እግዚአብሔርን የምናስቀይም ነው የምንኾነው፤ ያልተቀጣ ልጅ ኹልጊዜ እንደሰረቀ ይኖራል፤ ልቡናው በእግዚአብሔር ቃል እና ምስጢር ያልተቀጣ ሰው ኹልጊዜ እንደበጠበጠ ይኖራል፤ ፖሊቲካ ከቤተ ክርስቲያን ይውጣ፤ እውነት ይገለጥ ቅዱስ አባታችን፤ ስለእውነት እንቁም፤ በአራቱ ማዕዝን ጥያቄ ተቀስሯል፤ ስለ ሃይማኖት ጥያቄ እየተነሣ ነው፤ ጥያቄውን የሚመልሰው ማን ነው? ብዙ ችግሮች ቀርበዋል፤ የሚፈታቸው ማን ነው? አእምሮ ያስባል፤ ጆሮ ይሰማል፤ ድኻ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ፤ የሚል አባት ከሌለ ትርጉሙ ምንድን ነው? ዙሪያውን ሰይፍ ተመዞ እየተብለጨለጨ የደነዘዘውን አእምሮ እናስወግደው፤ ቃሉን እንጠይቀው፡፡”
  “ዓመታዊ በዓል ነው፤ ለጉባኤው የማመለክተው፡- ሕጉ ይከበር፤ ስም ብቻ አንያዝ፤ ሕጉን ወደ ኋላ አሽቀንጥረን ትተን እንዴት መምራት እንችላለን? ተንኰል ይቅር፤ በውሸት አንመን፤ በዝባዥ ይጋለጥ፤ ጨርሻለኹ፡፡”
  ብፁዕ አቡነ እንድርያስ -የቅዱስ ሲኖዶስ የምልዓተ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ የተናገሩት ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.


  Aba Mahtias degimo segawe asaben bicha selemearamido ..lemin bilewe poleticawe yewene negere kalegeba ...bilewe lay tache belom ahletesakalachewem Enderase yasefelegale tebalo.....mahferaweche

  ReplyDelete
 20. Ayachihu Wedimoche Balefew Abatochin Mesadeb Ayigebam Metsihaf Kidus Ayazewim Bisasatum Enqua Beadebabay Endih Metsaf Ayigebam Wezete wezete Sitilu Neber .....Gin yene Bicha,Yeafi sew, Lenante yetemech Bicha Yemimesegen....wezete mehonu ezasachihu Awetachihut....lemanignawim Egiziabhier Betekerstianin Yitebik. Enantem Asmesayinetachihu Yibika....eteley Degimo Kidusan Ayamalidum Eyale Yemitsif Blog Silebetekiristian Tekorkuari hono sikeraker Yigermal...

  ReplyDelete
 21. አየ ቡርሳዎች እስከመቸ ?ህዝብን እያሰለፍ ሲያዋጉት ኖሩ፣ወንድሙን በንጉሱ ለመተካት ህዝብን እየገዘቱ ሲያገዳድሉት፣ ሲያስተራርዱት፣ ልጆች ያለአባት ሚስት ካ ለትዳር እያለቀሰች በችግር እንድትኖር የሆነበት የአንድ ጊዜ ሳይሆን የዘልአለም ታሪክ የሆነበት በእነርሱ ፤በሁሉም የታሪካችን ዐውድ ሁሉ የተከናወነ ነው። ህዝቡ ወንጌል እንዳያውቅ አድርገው፣ ህዝቡ ወንጌልን ከአወቀ እነሱንም ሆነ ነገስታትን በወንጌሉ ቃል መሠረት እንዲመሩ ይህ ካልሆነ ግን እእግዚአብሔርን የሚከተሉትን ነገስታት እና ካህናት እንፈልጋለን ብሎ ያምፃል ከሚል ክፋት በመነጨ ለሟርት ጥንቆላ እና መተት አጋልጠውት ፤ከንቱ አድርገውት ቀሩ፤ ለእነዚህ እንኳን በአቶ ካሳ ፊት በሰዱቃውያን እና በአረማውያን ፊት ቢዳኙ ምን ይደንቃል (በጥባ ጮቹን) ማለቴ እንደሆነ ይታወቅልኝ።

  ReplyDelete
 22. እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ እኮ ሥጋ የለበሰ ልብ (ደንዳና ያልሆነ) ንፁህ ልብ ባላቸው ክርስቲያኖች ውስጥ የሚገኝ እንጅ ካህን ስለሆኑ ብቻ የደነደነ ልባቸውን ይዘው በረ ዥም ፀሎት ታጅበው ቢሰበሰቡውጤቱ ያው መሰዳደብ ነው። አንቀልድ።ወዲህ ወደ አትላንታ ጆርጂያ አንድ የምንወዳቸው የተማሩ ካህን ከፖለቲክው በላይ ወደ ጦር ምዘዙ አይነት እየሄዱ ይመስላል ፤በጣም ብዙሀኑን ያሳሰበ ነገር ነዉ ራስን መግደል ይሏል ፤ ያን ወደ አስመራ አቅንተው የነበሩትን ማለቴ አይደለም፣ ወንጌላዊዉን ነው። እሁን ያስጨነቀን ታላቁን፣ ሊቁን ብዙሃኑን በወጌል ያጠመዱትን ይጠብቅልን ነው ወደ ፖእቲካዉ ወሰድ ሲያደርጋቸው እየሰጋን፤ በያዙት የውንጌል ስራ ቢበረቱ ማን እንደእነሱ የታደለ። በዚህ በኩል እንኳ ቢደርሳቸው በማሰብ ነው እንጅ ማነጋገር ቢቻል ደህና ነበር ግን ከባድ ነዉ ።ዛሬ ላይ ህዝቡ የተጠማው ወንጌል ነው። ካህንቱም ስራቸዉ ጥም ማርካት ሊሆን የግድ ነው።

  ReplyDelete
 23. እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ እኮ ሥጋ የለበሰ ልብ (ደንዳና ያልሆነ) ንፁህ ልብ ባላቸው ክርስቲያኖች ውስጥ የሚገኝ እንጅ ካህን ስለሆኑ ብቻ የደነደነ ልባቸውን ይዘው በረ ዥም ፀሎት ታጅበው ቢሰበሰቡውጤቱ ያው መሰዳደብ ነው። አንቀልድ።ወዲህ ወደ አትላንታ ጆርጂያ አንድ የምንወዳቸው የተማሩ ካህን ከፖለቲክው በላይ ወደ ጦር ምዘዙ አይነት እየሄዱ ይመስላል ፤በጣም ብዙሀኑን ያሳሰበ ነገር ነዉ ራስን መግደል ይሏል ፤ ያን ወደ አስመራ አቅንተው የነበሩትን ማለቴ አይደለም፣ ወንጌላዊዉን ነው። እሁን ያስጨነቀን ታላቁን፣ ሊቁን ብዙሃኑን በወጌል ያጠመዱትን ይጠብቅልን ነው ወደ ፖእቲካዉ ወሰድ ሲያደርጋቸው እየሰጋን፤ በያዙት የውንጌል ስራ ቢበረቱ ማን እንደእነሱ የታደለ። በዚህ በኩል እንኳ ቢደርሳቸው በማሰብ ነው እንጅ ማነጋገር ቢቻል ደህና ነበር ግን ከባድ ነዉ ።ዛሬ ላይ ህዝቡ የተጠማው ወንጌል ነው። ካህንቱም ስራቸዉ ጥም ማርካት ሊሆን የግድ ነው።

  ReplyDelete
 24. phaphasatu lemenafikan bursa letewahido lijoch gin anbesa.Inante beabatachihu matiyas iyetemerachichu bexbixu phaphasatu gin iyaxeru yinoralu .yih iskefitsamewu yiqetilal.

  ReplyDelete
 25. እናንተ መሳደብ ስትጀምሩ ጥሩ ነገር እንዳለ እገነዘባለሁ ተመስገን

  ReplyDelete
 26. It is known from what you are writing as you are menafik

  ReplyDelete
 27. You have write what you want but,try to write what the truth is.

  ReplyDelete