Monday, June 13, 2016

በጎች በበጎች ላይ እንዳይሰማሩ፣ ጠባቂዎችም ተጠባቂዎችም አንድ ዓይነት እንዳይሆኑየቤተ ክርስቲያን ልሳን የሆነው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ “በጎች በበጎች ላይ እንዳይሰማሩ” በሚል ርእስ በጻፈው ርእሰ አንቀጽ ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርተ ወንጌል ላይ ትኩረት ሳትሰጥ ባሏት ባህላዊና ትውፊታዊ ነገሮች ብቻ ትውልዱን ይዛ መዝለቅ እንደማትችልና ለህልውናዋ አስጊ መሆኑን በመግለጽ ለትምህርተ ወንጌል ትኩረት እንዲሰጥ በማሳሰብ የሚጀምረው ርእሰ አንቀጹ እንደሚለው “ባለንበት ዘመን በትምህርተ ወንጌል እንጂ እንደ ቀድሞው በአዋጅ ብቻ የሚከበር ሃይማኖት የለም፤ በጸሎተ ቅዳሴው በሰዓታቱ በማኅሌቱ በተአምሩና በገድላ ገድሉ ብቻ የሚያምነውም ትውልድ እያረጀ እያፈጀ ሄዷል፡፡ የተዘረዘረው ሁሉ ተደማምሮ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ጸሎታ ምስጋና ነው፡፡ ጸሎቱና ምስጋናው ውስጡ ስብከት አዘል ቢሆንም አገልግሎቱ የሚፈጸመው በግእዝ ቋንቋ ስለሆነ ሕዝበ ክርስቲያኑ ትርጉሙንና ምሥጢሩን አይረዱትም እንኳን ሕዝበ ክርስቲያኑ ካህናጹም ቢሆኑ ጥሬ ቃሉን ከማንበብና ከማዜም ያለፈ ትርጉሙንና ምሥጢሩን ከሚረዱት ይልቅ የማይረዱት ያመዝናሉ፡፡ ቅኔው በግእዝም በአማርኛም ቢዥጎደጎድም ከማስገረምና ከማስደነቅ ብሎም ከፍልስፍና አልፎ አንድ አማኝ ሊያስገኝ አይችልም፡፡”
 
ከዚህ በተጨማሪ ርእሰ አንቀጹ ብዙ ሀገረ ስብከቶች ክፍት ሆነው የአባት ያለህ እያሉ መሆናቸውን ጠቅሶ “በዚያው ላይ ‘ከአባ ቁፍር እሸት ተበልቶላት’ እንዲሉ በውጭ ያሉ የአባቶች መከፋፈል” ሌላው ችግር መሆኑን ጠቅሷል፡፡ እንደዚህ ባሉ ችግሮች ውስጥና ተልእኮዋን በሚገባ ለመፈጸም የሚያስችሏትን አባቶች በጵጵስና ለመሾም በዝግጅት ላይ ያለችው ቤተክርስቲያን ጳጳሳቱን በብርቱ ጥንቃቄ መምረጥ ያለባት መሆኑንና ከዚህ ቀደም በአንዳንድ ጳጳሳት በታዩ የተለያዩ ጉድለቶች ቤተክርስቲያን ዳግም ችግር ውስጥ እንዳትገባ መደረግ ያለበት በመሆኑ ላይ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡ “ታዲያ በዚህ ጊዜ በአባቶች እግር አባቶችን መተካት ግዴታ ቢሆንም በጎች በበጎች ላይ እንዳይሰማሩ ማለት ጠባቂዎችም ተጠባቂዎችም አንድ ዓይነት እንዳይሆኑ ከአለፈው ተሞክሮ በመውሰድ “እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል አሰማራችኋለሁ” በተባለው መሰረት በትምህርት ብቃታቸው ከተኩላዎች ጋር ግብ ግብ በመግጠም በጎችን ከነጣቂ ተኩላዎች ማዳን የሚችሉትን፣ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ” በተባለው መሰረት ዕውቀት ቢኖራቸውም የጋን ውስጥ መብራት ሳይሆኑ የሕዝብ መብራት የሆኑትንና “ቸር እረኛ ነፍሱን ለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣል” የተባለውን ቃል ተግባራዊ በማድረግ ነፍሳቸውን ለበጎቻቸው አሳልፈው የሚሰጡትን ለይቶ ማየትና መምረጥ ያስፈልጋል” ሲል በቅርቡ ሊደረግ በታቀደው የጳጳሳት ምርጫ ላይ ብርቱ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡

በተለይም በጎች በበጎች ላይ እንዳይሰማሩና ጠባቂዎችም ተጠባቂዎችም አንድ ዓይነት እንዳይሆኑ ካለፈው ተሞክሮ ልምድ መወሰድ ያለበት መሆኑ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ገልጿል፡፡ “ካለፈው ተሞክሮ በመውሰድ” ሲልም በአቡነ ጳውሎስ ዘመን ከተሾሙት አንዳንዶቹ በዕውቀትም፣ በቅድስናዊ ሕይወትም በሌላውም ሁሉ ችግር የነበረባቸውና በራሳቸው መንገድ እንጂ በትክክለኛው መንገድ ወደ ጵጵስና እንዳልመጡ የሚጠቁም እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ አንዱና ዋናው ጉዳይም “የቀድሞው ሕገ ቤተክርስቲያን ስለጳጳሳት ምርጫ ባወጣው መስፈርት መሰረት ከዚህ ቀደም የተሾሙት አንዳንዶቹ ስለማንነታቸው በካህናትም በምእመናንም ምስክርነት ሳያገኙ በሲኖዶስ ውሳኔ ብቻ መመረጣቸው አንድ ክፍተት መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ ጵጵስና እጅግ ወርዶ የተገኘበት አጋጣሚ የተፈጠረውም በዚህ ምክንያት በመሆኑ ያ በአሁኑ ምርጫ እንደይደገም ከዚያ ተሞክሮ በመውሰድ ብቃቱ ያላቸውን አባቶች መምረጥ የሚገባ መሆኑ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡ ርእሰ አንቀጹ መልእክቱን ሲደመድም “ከሁሉም በላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲመርጥ ሁሉም ሊጸልይ ይገባል ሲል” አሳስቧል፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለራሳቸው ጥቅም የቆሙ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች የተማረ፣ በእውቀቱና በቅድስናው የተመሰከረለትንና ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ የሚጠቅመውን አባት ትተው ለእነርሱ የሚስማሙ ያሏቸውን አባቶች ለመምረጥ አሰፍስፈው ያሉበት፣ ልዩ ልዩ ሴራና ተንኮል የሚጠነስሱበትና ከዚህ ቀደም እንደ ተለመደው በሁሉም አቅጣጫ እነርሱ ካሉት ውጪ ምንም እንዳይሆን ጠንክረው እየሠሩ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በዚህ ውስጥ የራሳቸውን ቢዝነስ ሊሰሩበት የሚከጅሉም አይጠፉም፡፡ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ለቤተክርስቲያኑ ግድ የሚለው አምላክ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙ አባቶችን እርሱ እንዲሰጥ አጥብቆ መጸለይ ቅደሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ “የዳንኤል ክብረት የተዛቡ እይታዎች” በሚል ርእስ ዳንኤል ክብረት በፓትርያርኩ ላይ ያቀረበውን ተገቢነት የሌለው ስም ማጥፋት በመተቸት ጽሑፍ ስነበበ ሲሆን፣ ጽሑፉ በስሜታዊነት የተነዳና የመረጃ እጥረት ያለበት መሆኑን በመጥቀስ እንዲህ ያለው ጽሑፍ ግለሰብን ሳይሆን ቤተክርስቲያንን የሚነካ በመሆኑ በሲኖዶስ በኩል ይህን በሚመለከት ሊታሰብበት ይገባል ብሏል፡፡          

5 comments:

  1. ምድረ ቱሪናፋ ብቻ!!! ሚዛን የሚደፋ ቃል የሌላችሁ!!!!

    ReplyDelete
  2. ለምን እንግዲያ አሁን በድብቅ ስለምትሾሟቸው የትሃድሶ መናፍቃን ጵእጵሳት ለምን በግልጽ አትናገሩም አታወሩም።ውሸታሞች

    ReplyDelete
  3. ጠንካራ ወንጌል ሰባኪያን ወያኔን እየወቀሱ እየወነጀሉ ስለሆነ ጌታቸዉ እየተነካባቸው ያሉት ተንበርካኪ ባንዳዎች በማኩረፍ እየታመሱ ነው።

    ReplyDelete