Wednesday, June 15, 2016

ጅማ ውስጥ የተፈጸመውን የአክራሪዎች ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን Read in PDF
አክራሪዎች በሃይማኖት ሽፋን እያደረሱት ያለው ጥፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ መጥቷል፡፡ በሌሎች አገሮች በሩቁ እንሰማው የነበረው የሰው ልጆችን ውድ ሕይወት የመቅጠፉ አባዜ ወደአገራችን ዘልቆ ከገባም ውሎ አድሯል፡፡ ዜጎቿ ተከባብረውና ተቀባብለው የሚኖሩባት አገር ኢትዮጵያ ሃይማኖተኛ ነን በሚሉ ሙስሊም አክራሪዎች የክርስቲያኖች ደም በከንቱ የሚፈስስባት አገር ከሆነች ሰነባብታለች፡፡ እንዲሁም አክራሪ አልሆናችሁም ተብለው ሙስሊሞች የሆኑትም ጭምር የጥቃቱ ሰለባ እየሆኑ ነው፡፡ ይህ ድርጊት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያሳዝንና ሊወገዝ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡
በትናንትናው ዕለት በጅማ ሀገረ ስብከት በየም ልዩ ወረዳ በቁንቢ ቀበሌ አክራሪ ሙስሊሞች ባደረሱት ጥቃት 2 ኦርቶዶክሳውያንና 5 ሙስሊም ወንድሞቻቸው ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ለርካሽ ዓላማ ሲባል በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸመው እንደዚህ ዓይነቱ ጥቃት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና ሁሉም ሰው አጥብቆ ሊቃወመው የሚገባ አሳፋሪ የጭካኔ ተግባር ነው፡፡ ከዚህ ቀደምም በዚያው ሀገረ ስብከት ውስጥ ተመሳሳይ ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት መድረሱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህም ችግሩ አሁን ሙሉ በሙሉ እንዳልተወገደ የሚያሳይ ነው፡፡  
እንዲህ ካለው አክራሪ እንቅስቃሴ በስተጀርባ እስልምናን ሽፋን በማድረግ ፖለቲካቸውን በዘረኛ አስተሳሰብ ለውሰው ለማስረጽ የሚተጉት አፍቃሬ እስላማዊና ጸረ ክርስቲያን አቋም ያላቸው እነ ጃዋር መሐመድ የሠሩት ሥራ ውጤት መሆኑን ማንም አይስተውም፡፡ ስለዚህ ሁሉም አክራሪነትን ሊቃወምና ሊያወግዝ ይገባል፡፡ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን፡፡    

9 comments:

 1. አይ አባ ሰላማ ማኅበረ ቅዲሳን አለበት ብትል አይሻልም ግጥሙ ቤት አልመታም እኮ

  ReplyDelete
 2. እይ ምን እነሱ ብቻ የተሃድሶ ስራም ነው ብቻ እግዚያብሄር የመጨርሻውን ቅጣት ሲያመጣ ምን እንመልስ ይሆን? እናንተ መናፍቃን ኦርቶዶክስ ትታደስ እያላችሁ ህዝቡን ከምታወናብዱት ወደ ቀደምችው ጃኡማኖት ተመለሱና በአንድነት እንዋጋ እናንተ ምክንያት ከምትሰጡት ጠላታችን እናንተ ናችሁ የቤተክርስቲያን ጠላቶች።ተሃድሶ ማለቴ ነው እና መጀመሪያ እራሳችሁን አስተካክሉ አዛኝ ቅቤ አንጓች አትሁኑ ህዝቡ አውቋል ማን እንደሆነ ጠላቱ የናት ጡት ነካሽ።

  ReplyDelete
 3. እውነት እንነጋገር ከተባለ ማህበረ ቅዱሳን የሚባል ቀንደኛ ሰይጣን እጁ እንዳለበት ለሰከንድ አንጠራጠርም። እንኳንስ ምንም የማያውቁትን የዋሕ ሕዝብ ቀርቶ በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ ቅጠል ቀለባቸው በፀሎት የደከሙ የነሱን ጫማ ብንስም እንፀድቃለን ልብሳቸዉ ብንዳስስ እንፈወሳለን ብለን እምናምንባቸውን አባቶቻችንን እንኳ ሉሁለት ጒራ ከፍሎ የሚያበጣብጥ አላማውን ለማሳካት ሌት ተቀን እንቅልፍ የሌለው ማህበሩ አይደለም፡ ዋልድባ ገዳሙ ተቆፈረ ብሎ ሕዝብ ለማስነሳትና ሁከት ለመፍጠር ሲሮጥ የነበረው ማህበረ ቅዱሳን አልነበረም፡ የጥምቀት ተመላሽ ብሎ ያዘጋጀው አዲስ አምልኮ ምንጣፍ አንጣፊ ባንዲራ አይሉት ቡቱቶ ሰቃይ ለብጥብጥ ያዘጋጀው አይደሉም ቤተክርስቲያን ጩቤ ይዘው አልወጉም ለሠርግ አጅበው የመጡ የቤተክርስቲያን ልጆች አላስደበደቡም፡ የጅማው ትያትር ያለምንም ጥርጥር የማህበሩ የመንግሥት ግልበጣ ሙከራዎች ሀገር ሰላም አይደለም ለማሰኘት የሚያደጉት ውጥን ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግሥት ያለሕ እያለ ነው። አሁንም የመንግሥት ያለህ የድረሱልን ጥሪያችንን ስሙን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጥላቻ የተመረዝክ ሰዉ ነህ፡፡ አነዲያዉም እንዳነተ ያሉ ስርኣት አልበኞች ሣይሆኑ አይቀረም

   Delete
 4. መንግሥት ሱማሌ ላይ የተደረገውን በሚዲያ ሲገልፅ ማቅ ደግሞ ይችን እረብሻ አመቻችተው ድሆችን ሰለባ አደረጒ። አይ ማቅ ይችን ስራዎቻችሁን መንግሥት የደረሰበት ቀን። የመንግሥትን ሚዲያ ለማስተባበል አገር ለመረበሽ ለእሳት ቴሌቪዥን ጣቢያችሁን ተአማኒ ለማድረግ የተመቻቸ ሤራ ነዉ።

  ReplyDelete
 5. እንደው ብዙ አትቀባጥሩ እናንተ ልባችሁ የደንደን ተኩላዎች መናፍቃን አውቀናል የናንተ ክህደታችሁ ሳይበቃ ሰውን የምታፋጁ እግዚያብሄር ይቅር ይበላችሁ ይሕው ያለፈው አልበቃ ብሎ አሁንም በዚህምስኪን ላይ ድጋሚ ድራማ ትሰራላችሁ ያሉን ፓፓሳቶች ስርዓት ሳታስይዙ ሌላ ጳጳሳት ለምን አስፈለጋችሁ እና እናንተ ምን እያደረጋችሁ ነው ህዝቡን እየከፋፈላችሁ አይደለም የኛ አዛኝ ቅቤ አንጓቾች አትጃጃሉ ህዝባችን አሁን ነቅቷል አጭር ንርው ቀኑ ለራሳችሁ ወደንስሃች ሁ ተመለሱ።

  ReplyDelete

 6. በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን ።
  እግዚአብሄር የእያንዳንዱን ሰው ልብ ያብራ ። ከሃይማኖተኝነት አስተሳሰብ ያውጣን! በእውነት እነዚህ ሰዋች ሃይማኖተኞች ነን እያሉ የሃይማኖታቸውን አጀንዳ ያስገጽማሉ ግን ታላቁን እግዚአብሄር እረስተውታል። ከእግዚአብሄር ይልቅ ለድርጅታቸው አጀንዳ ወይም አላማ ይታዘዛሉ በእውነት እነዚህን እግዚአብሄር አያውቃቸውም እነርሱም አያውቁትም የእሱን ሳይሆን የዚህን አለም ገዢ አላማ ነው የሚያስፈጽሙት።
  የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትም የመዳን ነገር: የመዳን እውቀት: የመዳን ቃል: የመዳን ጥበብ እና የመዳን ወንጌል የሆነውን ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከረሳች ስንት ክፍለ ዘመን አስቆጠረች? ጌታችን የከፈለውን የመዳናችን ዋጋ ተዘንግቶ አረ የመዳን መንገድ እነ ተክልዬ ናቸው እየተባለ መሰበክ መዘመር ከተጀመረ እኮ ብዙ ክፍለ ዘመን አለፈ። አረ ለመሆኑ ማን በከፈለው ዋጋ ነው ማን የሚወደሰው? አቁም የሚል እኮ ነው የጠፍው። ይህን ጉድ ኢትዬጵያዊው ጀንደረባ ቢሰማ ምን ይል ይሆን? እሱ እኮ ወንገልን ሲመሰከርለት ከሰረገላው ወርዶ እኮ ነው የተጠመቀው ወገኖቼ ከሃይማነተኝነት ወይም ከድርጅት አስተሳሰብ እንውረድ ለጀንደረባው የተመሰከረለትን የመዳን መንገድ የሄነውን አየሱስ ክርስቶስን ይዘን እንጽና መዳን በማንም የለም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው እርሱ ሁሉንም ፈጽሞል ክብር ምሰጋና ለታረደው በግ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን!!!

  ReplyDelete