Thursday, June 2, 2016

አባ ሳዊሮስ ለማቅ እጅ የሰጡበት ምስጢር ሲገለጥማኅበረ ቅዱሳን የአንዳንድ አባቶችን ገበና ይዞ በእርሱ እያስፈራራ የእርሱ ደጋፊዎች እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የተገለጸ ጉዳይ ሲሆን ከንግግር ባለፈ በተግባርም የታየ ነው፡፡ እነዚህ አባቶች የማቅን አጀንዳ እያስፈጸሙ የሚቀጥሉ ከሆነ በማቅ ዘንድ ከእነርሱ በላይ ብፁዕ እና ቅዱስ የለም፡፡ ከማቅ በተጻራሪ ከቆሙ ግን ስማቸውን በማጥፋት በእርሱ ዙሪያ ባሉ ሰዎች በኩል ተቀባይነትን እንዲያጡ የሚያደርግበት ሁኔታ አለ፡፡ 
እነዚህ ሰዎች ገበናቸው እንዳይገለጥ ከማቅ ጋር በመደራደር ከተስማሙ ማለትም ማቅን ደግፈው እንጂ ተቃውመው በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንዳይናገሩ፣ ማቅ ተሐድሶ ናቸው ያላቸውን ሰዎች አንድ በአንድ እየመነጠሩ ከሀገረ ስብከታቸው ከስራ ገበታቸው እንዲያስወጡ፣ ለማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ደግሞ ተገቢውን ቦታ በማስያዝና ሥራቸውን እንዲሰሩ ትብብር እንዲያደርጉና በመሳሰሉት ጉዳዮች ስምምነት ላይ ከደረሱ ማቅ ስለእነርሱ ምንም ክፉ ነገር ላያወራ፣ እነርሱም እርሱን ላይቃወሙ እንዲያውም ሊተባበሩና ሊደግፉ ይስማማሉ፡፡ በዚህም መንገድ የማቅ ጠንካራ ተቃዋሚዎች የነበሩ አባቶች ሳይቀሩ ድርድር ውስጥ ገብተው ማቅን በተቃወሙበትና ብዙ ጉዱን ባወጡበት አንደበታቸው ማቅን ወደማወደስና አስፈላጊው ትብብር ለማኅበሩ እንዲደረግ ወደመስበክ የዞሩበት አጋጣሚ አለ፡፡
በዚህ ረገድ ከሚጠቀሱት ጳጳሳት መካከል አባ ሳዊሮስ አንዱ ናቸው፡፡ እኚህ ጳጳስ ከዚህ ቀደም ማቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኩል ቤተክርስቲያኗን ለመቆጣጠር ይዞ የነበረውን ዕቅድ በማክሸፍ ረገድ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት ጋር በመሆን የታገሉ ነበሩ፡፡ ለካህናቱ ባደረጉት ንግግርም መታገል ያለባቸው ከፊታቸው ላለው የህጉ ጉዳይ ብቻ መሆን እንደሌለበትና ከዚያ ባሻገር ለቀጣይ ህልውናቸው ሲሉ ማቅን መታገል እንዳለባቸው ታሪካዊ በተባለ ንግግራቸው ማስገንዘባቸው ይታወሳል፡፡ 

ይልቁንም በአቡነ መርሐ ክርስቶስ ሞት የማቅ እጅ እንዳለበት በመናገር ማኅበሩ የጠላቸውን አባቶች እስከሞት ድረስ እንደሚዋጋ ያሰገነዘቡ መሆናቸውን ዘገብን የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማቅ ዘወትር ተሐድሶ እያለ የሚከሳቸውን ሰባክያን በሀገረ ስብከታቸው እንዲሰብኩ በማድረግና ሥልጣነ ክህነትን በመስጠት ጭምር የማቅን ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ በሀገረ ስብከታቸው ሲታገሉ ነበር፡፡ በሰበካ መንፈሳዊ አጠቃላይ ጉባኤ ላይም ማቅ በሀገረ ስብከታቸው እያደረሰ ያለውን ጥፋት በማጋለጥ በማኅበሩ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደር ችለው ነበር፡፡  
እንዲህ ባለው የፊት ለፊት ንግግር ሊረታቸው ያልቻለው ማቅ አባ ሳዊሮስን ሊረታ የሚችልበትን የተለመደውን መንገድ ወደመፈለግ ገባና ለጊዜው በእጁ ላይ የነበረውን የእርሳቸውን ገበና በሀራ ብሎግ ላይ ለቅምሻ ያህል ለቀቀ፡፡ “ከጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከትና ሌሎች አብያተ ክርስቲያን በዘረፉት ገንዘብ ‹‹ሺበሺ›› በሚለው አስከፊ የሙስና ስያሜ የሚታወቁትና በነፍስ ግድያ ወንጀሎች የሚጠረጠሩት አቡነ ሳዊሮስ የሚያስተባብሯቸው የግብር አምሳሎቻቸው” ወዘተ ብሎ ጻፈባቸው፡፡ ለቅምሻ ያህል ይህን የጻፈው አባ ሳዊሮስን ወደ ድርድር እንዲመጡ የገበናቸውን “ሃይላይት” ለማሳየትና ለማቅ እንዲገብሩ ለማድረግ ነበር፡፡ በዚህም ሐራ ተሳክቶላታል ማለት ይቻላል እንደ ታሰበው አባ ሳዊሮስን ከፀረ ማቅነት ወደ አፍቃሬ ማቅነት በአንድ ጊዜ ማዛወር ችሏልና (በሐራ ዘተዋሕዶ ላይ በOctober 16/2013 `የመንግሥትን የአክራሪነት ፍረጃ ተከትሎ የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ ለውጥ የሚቃወሙ ጥቅመኞች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚሰነዝሩት ውንጀላ ተጠናክሯል፤ ማኅበሩ ክሥ ለመመሥረት እየተዘጋጀ ነው በሚል ያወጣውን ዘገባ ይመልከቱ)፡፡ አባ ሳዊሮስም አሰላለፋቸውን በማስተካከል ስለማቅ መቆርቆር የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ደግሞ ተሐድሶ እያሉ ማባረር የያዙት ከዚያ ወዲህ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አባ ሳዊሮስ በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳበርጋ አዳዳ ባለወልድ የተወለዱ የሸዋ አማራ ሲሆኑ ቋንቋውን ስለሚችሉ ግን ኦሮሞ ነኝ ብለው የተሾሙ ናቸው፡፡ የቀድሞ ስማቸው አካለ ወልድ ሞገስ ነው፡፡ በምስካየ ኅዙናን ገዳም ሲያገለግሉ በምንኩስና እያሉ ልጅ የወለዱ ሲሆን እዚያው ወንድማቸው ዲያቆን ግርማ ሞገስ የተባለ የሚያሳድገው ከእሳቸው የተወለደ ልጅ አላቸው ስሙም ግርማ አካለወልድ ይባላል፡፡
አሁን የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን እዚያው ምስካየ ሕዙናን ት/ቤት እየተማረ ነው ያለው አባ ሳዊሮስ 6 ሺ ብር ይከፍሉለታል፤ ምግብ ከገዳሙ ድርጎ ያገኛል፡፡ ይህን ምስጢር በፊት የወሊሶ አሁን የሆረጉድሩ ወለጋ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አዕላፍ ተስፋዬ ዋቅጅራ ያውቃሉ ይባላል፡፡ ብዙ ጊዜ ከአባ ሳዊሮስ ጋር ሲጣሉ የሚናገሩት ይህንኑ ነው ይላሉ ምንጮች፡፡
በሠበታ ጌቴ ሰማኒ የሴቶች ገዳም የምትኖር አገር ቤት በሚኖረው አበበ ሞገስ በሚባለው ወንድማቸው ስም የምትጠራ “የትናዬት” የምትባል ልጅም አላቸው፡፡ የዚህች ልጅ እናት አሁን አቃቂ የምትኖር ሲሆን ግሮሠሪ አላት፡፡ አባ ሣዊሮስ ቦረና በነበሩ ጊዜ የቤት አስቤዛ በገፍ እንደሚያመጡላት የዓይን እማኞች ይመሠክራሉ፡፡ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ለመታረቅ መንስኤ የሆነችው ይህች ሴት ናት፡፡ ምክንያቱም የማቅ አባላት ከፍተኛ ብር በመመደብ እናትየውን ያሳመኑ ሲሆኑ እስዋም ልጅህን አጋልጣለሁ በማለትዋ አባ ሳዊሮስ ከማቅ ጋር እንደ ታረቁ የታመኑ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ይህ እንግዲህ ሰው ገሎአል ከሚል ሌላው መረጃ ነው የሀራ ዘገባ ይህን ዘግቦአል፡፡ ይህችን አባ ሳዊሮስ የወለዱላትን ሴት ያደራደሩትና ጉዳዩንም ከጫፍ ያደረሱ
1.     ለወሊሶ ከተማ የሚኖር የመንግሥት ሠራተኛ መምህር የሆነ ጌታሁን አማረ
2.    ወጣት ሣሙኤል ደረሰ የተባለ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ የማቅ ማዕከል ሰብሳቢ በዋነኛነት ይጠቀሳሉ
አሁን አባ ሳዊሮስ በቅምጥነት የምታገለግል በሰበታ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ምክትል ሊቀመንበር የሆነች ሜዘር የምትባል ባልዋ የሞተባት ሴት ስትሆን አባ ሣዊሮስ ቤትዋን ሀገረ ስብከታቸው እንዳደረጉት ይነገራል፡፡
ይህን ምስጢር ያውቃሉ የሚባሉትን ሰባክያነ ወንጌል ተሃድሶ የሚል ታፔላ ተለጥፎባቸው ተባረዋል፡፡ ለምሳሌ፡- የሰበታ አማኑኤል ቤ/ክ ሰባኬወንጌልን፣ የሰበታ ወረዳ ቤተክህነት ስብከተወንጌል፣ የተጂ መድኃኔአለም ሰባኬ ወንጌል ይጠቀሳሉ፡፡
አባ ሣዊሮስን በሞኝነት እየዘወረ ያለው የመንገድ ትራንስፖርት ዳይሬክተሩ ቀንደኛ ማቅ የሆነውን ካሣሁን ኃ/ማርያም ሲሆን ቅዳሜና እሁድ ውሎው ወሊሶ እንደነበረ ሣዊሮስ ገንዘብ በመመደብ እስከ እኩለ ሌሊት አቶ በላይ ሆቴል በማምሸት ከአንድ ጳጳስና የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊ የማይጠበቅ ተግባር ፈፅመው ያመሹ እንደነበር ምንጮች ይናገራሉ፡፡
አባ ሣዊሮስን በቅርብ የሚያውቁ ደብረ ፅሞና ገዳም እያሉ ከገዳሙ እስከ እንጪኒ ከተማ አረቄ በመጠጣትና በመዝፈን የወጣትነት ጊዜያቸውን እንዳሳለፉ ይገልፃሉ፡፡
አባ ሣዊሮስ የተሾሙበት ሀገረ ስብከት ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው የታላቁ አባት የወንጌል ገበሬ የሆኑት አቡነ ዲዮስቆሮስ የኖሩበት ሀገረ ስብከት ሲሆን ሰውን በወንጌል አገልግሎት አሳርፈዋል፣ በኋላም ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ደክመው አልምተውታል፡፡ አባ ሣዊሮስ የተጠመዱት ግን ማቅ በሰጣቸው ስም ዝርዝር መሰረት አገልጋዮቹ ላይ ተሃድሶ የሚል ታፔላ እየለጠፉ በማገድና ሴት ወይዘሮዎችን በመቀያየር ነው፡፡
ከወሊሶ እስከ ሠበታ ባሉት የደብር አለቆች እና የቢሮ ሠራተኞች አበይት በአላትን፣ የጾም ፍቺዎችን እየጠበቁ ከ1ዐ-4ዐ ሺ ካላመጡ ያግዳሉ፣ ይቀይራሉ በተሃድሶነት ይፈርጃሉ፡፡ ለምሳሌ አለምገና ሚካኤል አባ ወ/ጊዮርጊስ አስተዳዳሪ የሆኑበት ደብር ሙዳየ ምፅዋት ሲቆጠር በየወሩ 15ሺ ብር ስለሚሰጡ ስንቱ አለቃ ሲዘዋወር እኚህ አለቃ ግን ይታለፋሉ፡፡
ከሀገረ ስብከታቸው ውጪም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ የአባ ሣዊሮስን የቤተ ክህነቱን መኖሪያ ቤት ሽምገል ያሉት ጳጳሳት ሁለተኛው የሲኖዶስ ጽ/ቤት ይሉታል፡፡ አድማ፣ ረብሻ፣ ተንኮል የሚጠነስሰው በዚሁ ቤት ነው፡፡ ሲኖዶስ በመጣ ቁጥር አስቀድመው በዚህ ቤት መሰብሰብን የሚያዘወትሩ
1. አባ ማቴዎስ
2.አባ ዲዮስቆሮስ
3. አባ ሉቃስ
4. አባ ቀሌምንጦስ
5. አባ ሔኖክ
6. ከውጭ ደግሞ አባ ፋኑኤል ናቸው
የሲኖዶስ ስብሰባ ተጀምሮ እስከሚያልቅ አባ ሣዊሮስ ቤት የመዋጮ ተራ በመግባት ሲበሉ ሲጠጡ ከውስኪ ጋር ነገር ሲያወራርዱ ያመሻሉ፡፡ ይህም ተራ የሚገቡት ሙክት ፍየል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ምግብ በተለይ የፈረንጁን አሣምሮ የሚሠራላቸው የመልከጸየዴቅ ገዳም አስተባባሪ የሆነ ለይኩን የተባለ ሰው ነው፡፡ ልብ በሉ በመንበረ ፓትርያርኩ በጀት ማዕደ አበው የተባለ ለብፁዓን አባቶች የተመደበውን አይነኩትም፡፡
ብዙዎች አባቶች አባ ሳዊሮስን በጣም “ጅል” ናቸው ይላሉ፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት ስብሰባ ሌሎች አባቶች ቤት እንዲደረግ ፈቃደኛ ስለማይሆኑ የእርሳቸውን ቤት ለአድማ ይጠቀሙበታል፡፡ “በሞኝ ክንድ የዘንዶ ጉድጓድ ይለኩበታል” ይባላል፡፡ ሊበሉ ሊጠጡ ተለወጡ ሊዘፍኑም ተነሱ እንደ ተባለው ከዚህ በኋላ ነው የቀድሞውንም የአሁኑንም ፓትርያርክ መከራ የሚያሳዩት፡፡ በአባ ሣዊሮስ ቤት ውስጥ እልፍነሽ የምትባል ሴት ትኖራለች፡፡ ምናቸው እንደሆነች ባይታወቅም የዚችን ሴት እህቶች በተለያየ ቦታ እንደቀጠሩ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌ 1) በሰበታ ገብርኤል ገንዘብ ያዥ፣ የዚያው 2) የዚያው የወረዳው ቤተ ክህነት ሂሳብ ሹም አዳነች ትባላለች፣ 3) ሌላ ወለቴ ሥላሴ እቃ ክፍል ነች፡፡ ስለዚህ እርሳው ያለአንዳች ምክንያት ከአንድ ቤተሰብ እነዚህን መቅጠራቸው ለምን ይሆን ሲሉ ብዙዎች ይጠይቃሉ፡፡

14 comments:

 1. ተራ አሉባልታና በሃይማኖት/በእምነት ሚዛን ሲለካ ባዶ ጽሑፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተራ አሉባልታና በሃይማኖት/በእምነት ሚዛን ሲለካ ባዶ ጽሑፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
   Reply

   Delete
 2. If you translate this into English, Your Lutherian Bosses would have rewarded you dozens of Money.

  ReplyDelete
 3. አንተ ሠይጣናዊ ቡድን ይህን በሃሠት የአባቶችን ክሥ አታቆምም? የራስህን ግብር ለማኅበረ ቅዱሣን ለመስጠት ትሞክራለህ አይደል? ድከም ያለህ በራስህ መጥፎ ምግባር እየተጠላለፍክ ትወድቃለህ አይደል? የማኅበሩ ሥራ በሕዝብ ፊት እያበራ ሲታይ የሠይጣናዊው ቡድን(አባ ሠላማ ነኝ ባዪ) ደግሞ ሥራው ከባህርይ አባቱ ከዲያቢሎስ በቡክርና የተቀበለውን የአባቶችን ሥም ጥላሸት የመቀባትና የቤ/ያኗን አስተምህሮ የመቀየር አጀንዳ ይዞ እንደሚንቀሳቀሰ የታመነበትና የተረጋገጠ ነው። የሚጽፈውም በምግባር ለሚመስሉት ለተከታዮቹ ብቻ እንጅ ሌላ የሚሠማ ክፍል የለውም። ተከታዮቹም ቢሆኑ እየተረዱት መጥተዋል።

  ReplyDelete
 4. BTAM TASAZENALCHU

  ReplyDelete
 5. Please do not publish such kind of rubbish and false story. Please do not spoil individuals image in stead you better look at your evil activities, sine and other offensive deeds exercised by you through out your life. We don't expect a milk from scorpion, Hara teka Tehadiso, Menafik. Manete kelfarious. I wish a blessed working time for both Abune Sawiros and Abue Diwoscoros.

  ReplyDelete
 6. Gude sayesema meskerem ayteba.

  ReplyDelete
 7. Replies
  1. ድሮስ ሰይጣን እየጋለባችው አደል

   Delete
 8. በመጄምሪያ ብፁዕነታቸው ማናቸው ብሎ መጠየቅ በተሻለ ነበር፡ ብፁዕነታቸው በትክክል የበቁና የፀዱ አባት ላመኑበት ነገር ወደፊት ወደኋላ የማይሉ ቆራጥና ሀቀኛ አባት ናቸው።
  እናንተ ተሀድሶያውያን እና ማህበረ ቅዱሳን የምትባሉ ፀረ ቤተክርስቲያን እንደሆናችሁ ገና ህዝብ ያላወቃችሁ አታላዮች ናችሁ። የኛ የተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሁለታችሁም አታስፈልጉም የስም ላፒሶች። ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የአቁአም ሰው ናቸው፡ ከማንም ጋር ችግር የላቸውም። ብፁዕነታቸው እና ቅዱስነታቸው አይጣሉም። አባቶቻችን መሀል እየገባችሁ የምታበጣብጡ ማቅ እና አባ ሰላማዎች እባካችሁ ሰላም ስጡን። አቡነ ሳዊሮስ እምነትን ከምግባር ጋር የያዙ ሀቀኛ አባት ናቸው። ግን አባቶች እባካችሁ ለቤተክርስቲያን ከቆማችሁ እነኝህን የሀገር የወገን የቤተክርስቲያኗ የመንግሥት ጠላቶች አባራችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትን አደራ ብትፈፅሙ ይኸ ሁሉ ግር ግር ቤተክርስቲያን ውስጥ ባልነበረ ነበር። አሁንም ሩቅ አይደለም እባካችሁ ትምህርትና ዲግሪ አይደለም የሚያስፈልገው በእግዚአብሔር መታመን ብቻ ነው። እናንተም እኮ ለቤተክርስቲያን ፐሮፌሰር ናችሁ። ስንት ሺህ ዘመን ያደረች ቤተክርስቲያን ከመንግሥት ተፅዕኖ ተላቃ እራስዋን ስትችል፡ ዛሬ በሀያ አመት ወይፈን በሌቦችና በቀማኞችና የቤተክርስቲያን ተልእኮ የሌላቸው ቡድኖች እና ማህበር አሳልፋችሁ እየሰጣችሁ ነገ ታሪክ ይፋረዳችሁዋል። ይኸ ሁሉ ስድብና የመደፈር መሠረቱ እነዚህ ናቸው ። የተዋህዶ መሠርት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም እኛ ነን ለማለት ምንም አልቀራቸውም።ማህበራም እኛም ሁላችንም በቤተክርስቲያን አና በአባቶቻችን እንመራ። ቤተክርስቲያንም አባቶቻችንም ሞግዚት አያስፈልጋቸውም።።።።

  ReplyDelete
  Replies
  1. በእውነት ልብ የሚያሳርፍ ትልቅ መልዕክት ነው እግዙአብሔር አምላካችን ማስተዋሉን ያድለን

   Delete
 9. yihin lemenager eskahun yet neberachihu ke MK gar siletesimamu new

  ReplyDelete
 10. መቸም ቢሆን እንደናንተ ካለ የቤተክርስቲያን ጠላት ከዚህ የዉሸት አሉባልታ በቀር ምንም አይጠበቅም፡፡ እንኳን በስጋ ያሉትን አባቶች ቀርቶ ቅዱሳን ሰማእታትን ስትዘልፉ ስለእመቤታችን ስትዋሹ አታፍሩም፡፡ አባታችሁም ዲያብሎስ እንዲሁ ነበርና፡፡ ሀሰተኛ የሀሰት አባት እነዳደረገ እናንተም የአባታችሁን ስራ እየሰራችሁ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር ይገስጻችሁ፡፡

  ReplyDelete