Thursday, June 23, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ወንጌልን ማቆም ያልቻለው ለምንድነው?ምንጭ፦ ደጀ ብርሃን
ከዙፋን (ተስተካክሎ የቀረበ)

ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሰረተ 25 አመት ሞላው። ድርጅቱ ከተመሰረተ ጀምሮ የፕሮቴስታንት፣ የካቶሊክና ሌሎች የክርስትና ክፍሎች የወንጌል ስብከት በፊት ከነበራቸው ውስንነት በበለጠ ሲሰፉ እንጂ ሲጠፉ አልታየም።

በተለይም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች የሆኑና ቤተክርስቲያኒቱ ከወንጌል ጋር አንዳንዴም ከወንጌል በላይ ስፍራ የምትሰጣቸው ትውፊቶች፣ ድርሳናት፣ ገድላት ከዚያም ባለፈ ልዩ ልዩ አስማትና ተረቶች የእግዚአብሔርን የክብር ስፍራ ወስደውና ጋርደው መገኘታቸውን ያስተዋሉና ከውስጥ የተነሱ የተሃድሶ እንቅስቃሴዎች ከነበሩበት ሁኔታ እየሰፉና እያደጉ መጥተዋል። ግንዛቤያቸውን በሁሉም ዘንድ በማዳረስ ረገድ ሰፊ ተቀባይነት በማግኘታቸው ከነበሩበት የተወሰነ ሁኔታ ወጥተው ዛሬ ከማኅበሩ 25 ዓመታት ቁጥጥር ውጪ ናቸው። ማኅበሩ የተሐድሶ እንቅስቃሴን ለመጨፍለቅ ያልቆፈረው ጉድጓድ፣ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። ከንግድ ድርጅቶቹ የሚያገኘውን ግዙፍ ገንዘብ፣ የሰው ኃይልና ማቴሪያልም ጭምር ለዚህ ስራ ያውላል። በተሐድሶ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ፣ ዐውደ ርእይ፣ ስብሰባ፣ ወርክሾኘ፣ በንግሥ በዓላት፣ በዐውደ ምሕረት፣ በፅሑፍ፣ በምስል ወዘተ ልዩ ልዩ መንገዶች ህዝቡን ያስተምራል፣ ያስጠነቅቃል ቪዲዮ ይበትናል፣ ካሴት ይለቃል፣ በራሪ ወረቀቶችን ያሰራጫል። በዩኒቨርሲቲዎች፣ በኮሌጆች፣ በሕጻናት፣ በወጣቶች፣ በጎልማሶች፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ባሉ ሰንበት / ቤት ተማሪዎች ላይ ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ሰርቷል። ተጽእኖውና መልእክቱ ያልገባበት ቤት የለም። ተሐድሶ፣ ሃራጥቃ፣ መናፍቃን፣ የአውሬው ተከታዮች፣ ፀረ ማርያሞች፣ ጠላቶች፣ ነካሾች፣ ቡችሎችወዘተ ብዙ ስም አውጥቶ ለማስጠላት ሞክሯል። በስለላ፣ በክትትል፣ በጥርጠራና በድጋፍ አብሮት ያልቆመውን ሁሉ ስም እየለጠፈ በማባረርና በማስፈራራት ብዙ ቢጓዝም ትምህርተ ተሐድሶ ግን ሊቀንስ አልቻለም። ከዚህ ሁሉ ልፋት በኋላ በውጤቱም 25 አመት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማታወቅ መልኩ 15 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከኦርቶዶክስ አካውንት ወደ ፕሮቴስታንት እምነት ጎርፏል።
ብዙ ሚሊዮን ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን፣ መምህራን፣ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ መነኮሳት፣ ጳጳሳት ሳይቀሩ ባሉበት ቤታቸው ሆነው የተሐድሶ እንቅስቃሴን ደጋፊና አራማጅ ሆነዋል። የተሐድሶ እንቅስቃሴ መጀመር ወደሌላ የእምነት ድርጅት የሚኮበልለውን ምዕመን ቁጥር መቀነስ ችሏል። ችግሩ ያለው ከኦርቶዶክስ መሠረታዊ አስተምህሮ ሳይሆን በጊዜ ብዛት በገቡ የስህተት ትምህርቶችና የፈጣሪን ሥፍራ የተረከቡ የክህደቶች አምልኰዎች የተነሳ መሆኑን ተሐድሶዎች ማሳወቅ በመቻላቸውና ይህንን ለማስወገድ ደግሞ እዚያው ሆኖ በማስተማርና በመለወጥ እንጂ በመኮብለል አለመሆኑን ብዙ በመሥራታቸው የተነሳ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ የሱን የኑፋቄ ጽዋ ለመጨለጥ ያልፈለጉት እዚያው ከሚቆዩ ይልቅ ኮብልለው የትም ገደል ቢገቡለት ይመርጣል። በጀትና ኃይል መድቦ ተሐድሶዎችን ከመከታተል ይልቅ ከበረት አስወጥቶ፣ በረቱ ውስጥ የቆዩለትን በጎች የራሱ የግል ንብረት አድርጎ ለመቆጣጠር ያመቸዋል። ያስቸገረውና ብዙ ድካሙን መና ያስቀረው ነገር የተሐድሶ ኃይል በእውቀት፣ በጥበብና በተዋሕዶ ቀደምት እውነት ሁሉን ማዳረስ መቻሉ ነው።

የማኅበረ ቅዱሳን ትልቁ ችግር ራሱን የእውነትና የእምነት ጫፍ አድርጎ መመልከቱ አንዱ ጉዳይ ሲሆን ሌላው ደግሞ በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተምህሮ ጥግ ላይ ከማኅበረ ቅዱሳን ውጪ ያለው ለማስተማር መሞከር ማለት አፍን ማሞጥሞጥ እንደሆነ አድርጎ ማሰቡ ነው። እውነታው ግን በተሐድሶ ምሁራንና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያለው የእውቀት ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ የመሆኑ ጉዳይ ነው። ተሐድሶ አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ይቀመጥ ሲል ማኅበሩ ደግሞ በአሮጌው አቁማዳ አዲሱን የወይን ጠጅ ማስቀመጥ ይቻላል በሚለው የእምነት አስተሳሰብ ልዩነት የተነሳ በተደራጀ አቅምና ሥልጣን በሚያደርገው ሩጫ ተሐድሶን ማስቆም አልቻለም። ተሐድሶ የግለሰቦች አሳብ ሳይሆን የእግዚአብሔር አሰራር መገለጫ በመሆኑ ማንም ድርጅት በትግል ሊያቆመው አይችልም።

ወልበስዎ ለሐዲስ ብእሲ ዘሐደሶ እግዚአብሔር በጽድቅ፣ ወበርትዕ፣ ወበንጽሕኤፌ 4:24
ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱየሚለን እግዚአብሔር በቃሉ አማካይነት ነው። በተረታ--ተረትና በእንቶ ፈንቶ ጩኸት በመባከን ፈንታ የወንጌልን እውነት መጨበጥ፣ ባዶ ተስፋ ከሚያስጨብጡ ዝናብ አልቦ ደመናዎች ዝናብ ከመጠበቅ ይልቅ ባለቤቱ ራሱ የሕይወት ውሃ ምንጭ እኔ ነኝ ካለው እውነት ቃሉ በመጠጣት መርካት መቻል ማለት መታደስ፣ መለወጥ፣ አዲስ ሰው መሆን ማለት ነው። እግዚአብሔር ሁሉም ሰው እንዲታደስለት ይፈልጋል። የተሰራነው አንድ ጊዜ ተሞልቶ ፈፅሞ ከማይደክም የባትሪ ኃይል አይደለም።

ወዘንተ ውስጥነሰ ይትሔደስ ኩሎ አሚረ

“...
የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል” 2 ቆሮ 4:16 እንዳለው መታደስ በመንፈሳዊነት ኃይል እግዚአብሔር እንደሚወደው ሆኖ መሰራት ማለት ነው።

በዚህም የተነሳ ማኅበረ ቅዱሳን የሚታገለው የእግዚአብሔርን ሃሳብ ለማስቆም ነው። ነገር ግን እስካሁንም አልቻለም፣ ወደፊትም አይችልም። ምክንያቱም ተሐድሶ፣


1.
የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው።
በመጨረሻው ዘመን የክርስቶስ ወንጌል በምድር ሁሉ ሊሰበክ ግድ ነው። ሉቃ 12:49 “በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁእንደሚለው ጌታ የጣለው እሳት ይነዳል እንጂ አይጠፋም። ሐዋ 5-38
 ይህ አሳብ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፣ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ እንዳትገኙእንዳለው ከእግዚአብሔር ስለሆነ ሊጠፉ አልቻሉም፣ አይጠፉምም።

2.
የአብርሖት (enlightenment) ዘመን በመሆኑ፣
ይህ ዘመን ትምህርት የተስፋፋበት ብዙዎች ከመሃይምነት ነጻ የወጡበት መረጃ የበዛበት ነው። የሰዎች መንፈሳዊ ረሃብ በማይረዱት ግእዝ የማያውቁትን ነገር ተቀብለው ወደቤት ከመሄድ ባለፈ መጽሐፍ ቅዱስና መንፈሳዊ ፅሑፎችን በማንበብ ማብራሪያና መልስ የሚፈልግበት ዘመን ነው። ትውልዱ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ልምምድን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይፈትሻል። ለእምነቱ በቂ ማብራሪያ ይሻል። ያነጻጽራል። መጽሐፍ ቅዱስን በሞባይሉ አስጭኖ የትም ቦታ ያነባል። እንደ መጨረሻ ባለሥልጣን ቃልም ያየዋል። ከዚህ ቃል ጋር የሚጋጭ ወይም ለማስታረቅ የሚሞክርን ማንኛውንም ውሸት ለመቀበል አይፈልግም። ይህንን ዘመነ አብርሖት ከእውነት ጋር በመስማማት እንጂ በመሸፋፈን ወይም ትቀሰፋለህ፣ በሰይፍ ትቆረጣለህ በሚል ማስፈራራት ማስቆም አይቻልም።

3.
ዛሬም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መዳንና ፈውስ ስላለ፣
እግዚአብሔር በአንድ ቃልና በጸሎት በአንዴ መፈወስ ያቃተው ይመስል ለሥጋዊ ፈውስ ሸንኮራ፣ ጻድቃኔ፣ግሼን፣ሚጣቅ፣ ሺፈጅ፣ ኩክየለሽ፣ ግንድአንሳ፣ ከድንጋይ አጣብቅ፣ መሿለኪያ፣ መንከባለያ፣ ገልብጥ፣ ሰንጥቅ ወዘተ አዳዲስ የፈውስ መደብር እየፈጠሩ የአንዱ ወረት ሲያልቅ ሌላ እየፈለሰፉ ገንዘብ ጉልበት ጊዜ ጨርሶ መፍትሄ በማሳጣት ተራራ ለተራራ መንከራተት ስለሰለቸው ሰው ከዚህ እንግልት ማረፍ ፈልጓል። 5 ትውልድ ወደ10 ትውልድ፣ ወደ 30 የማይጨበጥ ቃል ኪዳን ለመጨበጥ ሲያበላልጥ በክርስቶስ ላይ ብቻ አንዴ ታምኖ በመኖር ዕረፍትን ፈልጓል።

4. ትውልዱ ከሱስ መፈታትን ስለሚፈልግ
የጫት፣ የሲጋራ፣ የሺሻ፣ የሃሺሽና የመጠጥ ሱስ በየመንደሩ ብዙ ወጣቶችን ተብትቧል። ሴተኛ አዳሪነት፣ ስርቆትና ዝሙት አንገቱ ላይ ያሰረው ክር ወይም መስቀል ነፃ ሊያወጡት አልቻሉም። የጠለንጅ ወይም የጊዜዋ ቅጠል ማጫጫስ መፍትሄ አልሆኑትም።

44
ታቦት ባነገሠ ማግሥት ከነበረበት ሕይወት ሊፈታ ባለመቻሉ ከተስፋ መቁረጥ የሚያድነውን ይፈልጋል። ይኼውም ያልተቀላቀለበት የእውነት ወንጌል መስማት መቻሉ ነው።

2
ቆሮንቶስ 42 ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም፣ የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን

5. ለሥራ ስለሚያነሳሳ፣
እምነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያስተካከለ ሁሉ ለበጎ ሥራ የተነሳሳ ሰው ነው። ከወንጌል ሥራን እንጂ ስንፍናን አይማርም። ዐባይን ብቻዋን እንድትጠቀም ግብጽ በሕዝባችን ላይ የጫነችው የስንክሳር የበዐላት ሸክሟን ከራሱ ላይ አራግፎ በመሥራት ራሱንና ወገኖቹን የሚጠቅም ትውልድ እንጂ ስለአባ እገሌ እያለ የሚለምን ዜጋ ሊኖር አይችልም። ትንሽ ሠርቶ ያገኛትን ደግሞ በፍትሃት ድግስ እያራገፈ፣ ብዙውን ጊዜ ደግሞ ዛሬ መልአከ እገሌ፣ ነገ አባ እገሌ፣ በዓታ፣ ጸአታ፣ ፍልሰታ፣ ልደታ፣ ግንቦታ፣ እያለ አበሻ ሥራ ቢሰራ የተለየ ቀሳፊ የተመደበበት ይመስል ዐዛሬ ቅጠል አልበጥስምእያለ ይኖርበት ከነበረው ዘመን ተፈትቶ በዘመነ ተሐድሶ ነፃ እየወጣ የዕለት እንጀራውን ለማግኘት ሌሊትና ቀን እየሰራ ነው። በዐል ሳያከብር ፈረንጅ ያመረተውን ስንዴና ዘይት በእርዳታ የሚለምን በዐል አክባሪ እንደአበሻ ግብዝ የት ይገኛል?

ስለዚህ የዘመነ ተሐድሶ የክርስቶስን ወንጌል የሚቋቋም ማንም አይኖርም። የክርስቶስን ወንጌል የሚያቆም ከሰማይ በታች ምንም ዓይነት ኃይል ወይም ማኅበር የለም። ይሁን እንጂ ወርክሾፕ፣ ስልጠና አቅም ግንባታ፣ ሕንጻ ግንባታ፣ ኤግዚብሽን ግንባታ፣ ዐውደ ርእይ ወዘተ መደረጉ አይቀርም፣ ይኽ መደረጉ የእግዚአብሔርን የተሐድሶ ሐሳብ አያቆመውም። ማኅበረ ቅዱሳን የብር ኢዮቤልዩውን እንዲህ ካሳለፈ ዕድሜው ከሰጠው የወርቁን ደግሞ አመራሩ ራሱ ከኑፋቄ ወጥቶ ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ በማምለክ ያከብረው ዘንድ የእግዚአብሔር የተሐድሶ እቅድ መሆኑን አንጠራጠርም።

16 comments:

 1. ክብር ለአብ ለወልድ ለመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ
  እግዚአብሄር ይመስገን ለዚህ ጊዜ ያበቃን። በእውነት ላለፍት ቤተሰቦቼ አዘንኩ ይህን የቤተክርስቲያ ለውጥ ሳያዩ ማለፍቸው። ቤተክርስቲያኖ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የተሰበከላትን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በልጆቾ ሲሰበክ ማየት ምንኛ መታደል ነው ክብር ሁሉ ለእግዚአብሄር ይሁን።
  እኔ ካጋጠመኝ ላካፍላቹ ከአንድ እስራኤላዊ ይሁዲ ጋር ሳወራ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ክርስትና ይሁዲው እንዲህ አለኝ እሱ እኮ ለአይሁድ እምነት ተሃድሶ ነው ያመጣው አለኝ ሃይማኖታችን ደግሞ አይታደስም አለኝ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንኮን ይሁዲዎች ተሃድሶ ያመጣ ነው የሚሉት።
  ወንጌል እኮ በአለም ሁሉ ተሰብኮል በሚገርም ሁኔታም የአለም ህዝብም ቀላል የማይባል ህዝብ ለዚህ ወንጌል ተንበርክኮል አምላክ ከሰማይ መቶ አማኑኤል (እግዚአብሄር ከኛ ጋር) ሆኖ ስለኛ ደግሞ ሞተ በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ አምኖል በእግዚአብሄር ፀጋ እንጂ በስራችን እንደማንፀድቅ አውቆል አምኖል ፀድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው ተብሎል ለዚህም ክብር ለታረደው ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን በእውነት አምልኮ ዝማሬ ምስጋና ሀይገባዋል ከ 12 መዝሙሮች 8 ሳይሆን 12 ለሱ ቢዘመር ይገባዋል
  ግን ዘመኑ2000 ዓመት አስቆጠረና ይህን እውነት ክርስቶስን የሚሸፍኑ ነገሮች ብቅ ማለት ጀመሩ እምነት ሳይሆን ሃይማኖተኛነት በአለማችን ነገሰ። ክርስቶስን እዳናይ ብዙ እቅፍቶች ብቅ አሉ። ክርስቶስ ፊት ለፊት ተሰቅሎ ከኃላ ያለውን የመስቀል እንጨት እንድናይ የሚያደርጉ ትምህርቶች ብቅ አሉ የእነ እከሌ ገድል በብዛት ተስፍፉ በጌታችን እናት በእመቤታች ቅድስት ማርያም ስም ብዙ ተነገደ በእውነት ይህ ደግሞ ትልቅ ወንጀል ነው አረ ብዙ የአሁኑን ትውልድ የግንዛቤ ደረጃ ያላገናዘበ ተረት ተረት ተጻፈ ተቸበቸበ። ማህበረ ቅዱሳንም ድርጅቱ በለጋ እድሜው ይህን ተረተረት እየቸበቸበ ሌላ ተረት ተረት እየፈጠረ መገስገሱን ቀጠለ ለቤተክርስቲያን ቆሚ ጠበቃ ነኝ እያለ ህዝቡን ሲያደናግር ቆየ አሁንም እያደናበረ ነው ግን ዋና አላማው የሸዋውን የንጉሳዊ አገዛዝ ለማስመለስ እንደሆነ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ነገር ነው። ይህ ማህበር በእውነት ወንጌል ሲሰበክ የት ነበር? እውነት አርነት ያወጣል ክርስቶስ ሲሰበክ ማይወደው የዚህ አለም ገዢ ብቻ ነው ። በእውነት ማህበሩዋን የሚገዛውም እሱ ነው። በእውነት እሱ በክርስቶስ የመስቀል ሞት ተሸንፉል። አሸናፊውን ክርስቶስን ይዘን አንሸነፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው!
  አሜን

  ReplyDelete
 2. አይ አለማስተዋላችሁ አምላካችን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስም ሲሰብክ በነበረበት ዘመን እንካን እራሱን ባለቤቱን ያልተቀበሉት ብዙ ነበሩ።ከስንዴ መሀል እንክርዳድ አለና አስተውሉ።
  መቼም አይምሮ ያለው ጸሀፊ ይህን አልጻፈም

  ReplyDelete
 3. መዝሙረ ዳዊት 31:18 "በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።"

  ReplyDelete
 4. ኦ እግዝእትየ ማርያም ርጉመ ይኩን ወይረግመኪ ወቡሩክ ይኩን ወይባርከኪ ነገራተ ክልኤ ኢይርሳዕ ልብኪ!!!!

  ReplyDelete
 5. አይ አባ ሰላሳዎች ! ምኞታችሁ ብዙ ነው።

  ReplyDelete
 6. I am Orthodox from today on I will accept only the "Bible" no room for (taret); we Love you,
  thank you for giving us good information all the times keep us informed.

  ReplyDelete
 7. ወንጌል ሁሌም አሸናፊ ነው።

  ReplyDelete
 8. ድሮስ ለአእያ የት ነው ማር ጥሞት የሚያውቀው?የሉተርን ዘይትና ዱቄት የቀመሰ የማእበረ ቅዱሳን እስተምሮ እንዴት ሊጥመው ይችላል?እኛስ የኢትዮጱያ ኣርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንላለን ማእበረ ቅዱሳን ሆይ ዝም ብለእ ስራህን ስራ።

  ReplyDelete
 9. እስኪ አሁን በምክንያትና በመጽሃፍ ቅዱስ ቃል ይህንን ጽሁፍ ሞግቱ፡፡ አትሳደቡ አትናደዱ 'ስንዱ' የሆነዉን አስተምህሮአችሁን ከዎንጌሉ ቃል ጋር አስማምታችሁ ተከራከሩ፡፡ በበኩሌ ተረታችሁ ከሰለቸኝ ድፍን 8 ዓመቴ ቤቴ ቁጭ ብያለሁ፡፡ አባ ሰላማዎች ደግሞ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባችሁ የሰማኛል፡፡

  ReplyDelete
 10. ማኅበረ ቅዱሳን ወንጌልን ማቆም ያልቻለው ለምንድነው? አንተ ስላልመራኸው

  ReplyDelete
 11. Keep it up. That is what a gospel means. May God bless you!!!!

  ReplyDelete
 12. በንትርክና በጭጭቅ ላይ ጊዜ ስለሚያጠፋ የሰውን ደካማ ጎን ፣የፈጠራ ወሬ ፣አሉባልታ ፣ መጥፎ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ከኔበላይ ላሳር የሚል ትምክህት ስላለበት
  እግዚያብሄር መማራችንን ለበረከት እንጂ ለእርግማን አያድርግብን አሜን!!!!!

  ReplyDelete
 13. በጣም ደስ የሚል ነገር ነው ወንድማችን የፃፍክልን ተባረክ ማህበረ ቅዱሳን በጣም የሚያሳዝን ሚስኪኑ ነህምያ ብየዋለሁ ነህምያ ያባቶቹን ቅጥር በመንፈስ ቅዱስ ተነሳሽነት ሲሰራ ማህበረቅዱሳን ደሞ በመናፍስት ምክር የሳቱትን የአባቶቻችን ቅጥር ለመሥራት ደፋ ወና ሲል ይታያል እግር ከሳኦልነት አውጥቶ ወደ ጳውሎስነት እንዲቀይራቸው ልንፀልይላቸው ይገባል ።

  ReplyDelete
 14. እናንተ መናፍቆች ማኅበረ ቅዱሳን የሐሰት ትምሕርታችሁን ቢያጋልጥባችሁ በድንጋጤ ስሙን ማጥፋት ጀመራችሁ አይደል፡፡

  ReplyDelete