Monday, June 27, 2016

ሰማዕትነት በክርስቶስ ስም እንጂ በማርያም ስም ወይም በእምነት ተቋም ስም የለምከዘሩባቤል
በክርስትና ትምህርት መሠረት ሰማዕትነት በክርስቶስ አምነው የዳኑ ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ ሲመሰክሩ በክርስቶስ ስም የሚቀበሉት መከራ ነው፡፡ ጌታም በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤” (ማቴ. 10፡32) ባለው መሠረት የሚፈጸም የሕይወት መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ ምስክርነት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የመጀመሪያውን ሰማዕትነት የተቀበለው ቅዱስ እስጢፋኖስ ነው፡፡ ከእርሱም በኋላ ብዙዎች በዚሁ የምስክርነት መንገድ ስለ ክርስቶስ ስም ልዩ ልዩ መከራዎችን በመቀበል ሰማዕትነትን እንደ ተቀበሉ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል፡፡ ይሁን እንጂ ሰማዕትነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ትርጉሙ እየ ሰፋና እየ ተለዋወጠ በመሄዱ ስለ ክርስቶስ ስም ብቻ ሳይሆን በሌላም ምክንያት ሁሉ እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት የደረሰ ዋጋ የሚከፍሉ ሰዎችም ሰማዕታት እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ለምሳሌ በፖለቲካው መድረክ ስለ አገር ነጻነት በተለያየ ጊዜ መሥዋዕትነትን የከፈሉ ሰዎች ሰማዕታት እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ይህ ግን በዚያው በፖለቲካው መድረክ እንጂ በክርስትና ውስጥ ስፍራ ያለው አይደለም፡፡ ምክንያቱም በክርስትና ውስጥ ያሉ ሰማዕታት ሰማዕትነትን የሚቀበሉበት ብቸኛው ምክንያት በክርስቶስ ስም ስላመኑና ስለ ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ቅዳሴውም “በአሚነ ዚኣሁ ሰማዕታት ከዓዉ ደሞሙ በእንቲኣሁ” ትርጉም፡- “ሰማዕታት እርሱን በማመን ደማቸውን ስለ እርሱ አፈሰሱ”  ይላል፡፡

በክርስትና ዐውድ ሰማዕትነት ይህ ሆኖ ሳለ ከዚህ ውጪ ሰማዕትነት እንዳለ የሚሰብኩና በልዩ ልዩ መከራ ውስጥ የሚያልፉ ሰዎችን “ሰማዕታት” እያሉ የሚሰይሙ ሞልተዋል፡፡ ቁም ነገሩ ሰዎቹን ሰማዕት ለማለት ሰዎቹ መከራውን የተቀበሉት ስለ ክርስቶስ ሲመሰክሩ ነው? እና መከራው የደረሰባቸው በክርስቶስ ስም ነው? የሚሉት ወሳኝ ነጥቦች ከግምት መግባት አለባቸው፡፡ ይህን ለማለት ያነሣሣኝ ሰሞኑን በሐራ ብሎግ ላይ ያበብኩት ጽሑፍ ነው፡፡ የጽሑፉ ርእስ “ስለ ድንግል ማርያም ፍቅር የተመተረውን የእናት ወሰን የለሽ ፈቃዱን እጅ አየሁት፤ የሰማዕትነት ቋጠሮ ነው፤ ንሥኡ ፍሬ ሃይማኖት!” የሚል ነው፡፡ ጽሑፉ በብዙ ሕጸጾች የተሞላ ቢሆንም እኔ ግን በአንዱ ጉዳይ ላይ ብቻ ነው የማተረኩረው፡፡ በጽሑፉ ውስጥ ጉዳቱ የደረሰባቸው አንዲቱ ምእመን “በቀዶ ሕክምና የማይመለሰውን የግራ እጃቸውን ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው እና ስለ ድንግል ማርያም ስም ሳይመለስላቸው ዐጡት፤” ይላል፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰማዕትነት ከሚያስተምረው ውጪ የሆነ “ሰማዕትነት” ነው፡፡
      ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማያት ባለው አባቱ ፊት የሚመሰክርለት ሰማዕት በክርስቶስ አምኖ ስለ ክርስቶስ በመመስከር ስለ ክርስቶስ ስም ሕይወቱን ጭምር በእርሱ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር የቆጠረ ሰው ነው፡፡ ይህን እውነት መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ስፍራ ይመሰክራል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ሰማዕትነት ከክርስቶስና ስለእርሱ ከመመስከር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ስለ ሃይማኖት ተቋምም ሆነ ስለቅዱሳን ወይም ስለማርያም ምስክር በመሆን የሚቀዳጁት ስም አይደለም፡፡ ስለ ሃይማኖት ተቋም ወይም ስለ ድንግል ማርያም ሰማዕት የሆኑ ቢኖሩ እንኳ ሰማዕትነታቸው ምድራዊ እንጂ ሰማያዊ ሊሆን ከቶ አይችልም፡፡  ስለአግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ሰማዕት የሆኑትን ብቻ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ዕውቅና የሚሰጠው፡፡ ለማስረጃ የሚከተሉትን ማስረጃዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት፦
·        እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ(1ጴጥሮስ 5፥1)
·         እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ። (ራእየ ዮሐንስ 1፥9)
·        አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።” (ራእየ ዮሐንስ 6፥9)
·        “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤” (ራእየ ዮሐንስ 12፥17)
·        “ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።” (ራእየ ዮሐንስ 19፥10)
በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ምስክርነት ስለእግዚአብሔር ቃል እና ስለኢየሱስ ተብሎ ተገልጿል፡፡ ከዚህ ውጪ በእግዚአብሔር ዘንድ ምስክርነት ወይም ሰማዕትነት የለም፡፡ በሐራ ላይ የቀረበው ሐሳብ ግን ከዚህ የክርስትና ትምህርት ውጪ በሆነ መንገድ የቀረበ ነው፡፡ በሙስሊም አክራሪዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ምእመናን “ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው እና ስለ ድንግል ማርያም ስም” ሰማዕትነትን ተቀበሉ ብሎ ነው ያቀረበው፡፡ ለምን ይሆን እንዲህ ያለው? አክራሪዎቹ እንኳን በምእመናኑ ላይ ይህን ያደረጉት በክርስትና ስም መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ክርስትና ደግሞ በክርስቶስ ነው የተገኘው፡፡ ዞሮ ዞሮ ነገሩ የሚያያዘው ከክርስቶስ ጋር ነው፡፡ ታዲያ ጉዳይ እንዲህ ሆኖ ሳለ ነገሩን ወደ ሃይማኖት ተቋሙና ወደ ማርያም መሳቡ ለምን አስፈለገ? የጽሑፉ መሠረታዊ ስሕተት ይህ ነው፡፡

ሐራ ለማደናገር “ስለ ተዋሕዶ” አለ እንጂ ይህን ትምህርት የቀዳው ከተዋሕዶ ምንጭ እንዳልሆነ በብዙ ማስረጃ ማስረዳት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የጻድቃንንና የሰማዕታትን ታሪክ የያዘው ስንክሳር የተሰኘው መጽሐፍ እንኳን ቅዱሳን ሰማዕትነትን የተቀበሉት ጻድቃንም የተጋደሉት ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን እንደሆነ “ወተአመነ በስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት. . . ወነሥአ አክሊለ ስምዕ በመንግሥተ ሰማያት ወአእረፈ በሰላም” ትርጉም “ክብር ምስጋና ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ፤ በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ፤ በሰላምም አረፈ” ነው የሚለው፡፡ አክሊል የሚሰጠው መንግሥተ ሰማያትም የሚወረሰው ወደፊት ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በአሁን ጊዜ ግስ ቢጠቀምም “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ፣ በሰላምም አረፈ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጀ” የሚለው ግን ሰማዕትነት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በማመንና በመታመን እንጂ በማርያም ስም ወይም በሃይማኖት ተቋም ስም በማመንና በመታመን እንደማይገኝ ያስረዳል፡፡

በማርያም ስም ሰማዕትነት እንደሚደረግ የሚያምኑ ሰዎች ምናልባት በቅዳሴ ማርያም ላይ አንዳንዶች “በአሚነ ዚአሃ ለማርያም ንገኒ” (እርሷን በማመን ለማርያም እንገዛለን) የሚለውን የስሕተት ትምህርት ሊጠቅሱ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ነገር ግን ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነና በብዙዎች ሊቃውንት ዘንድ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ እንደሌሎቹ ቅዳሴዎች “በአሚነ ዚአሁ ለክርስቶስ ንገኒ” (እርሱን በማመን ለክርስቶስ እንገዛለን) በሚለው እያረሙ እንደሚጠቀሙበት ይታወቃል፡፡ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት ተከታዮች ግን እንዲህ “በአሚነ ዚአሃ”ን ስለያዙ በማርያም ስም ሰማዕትነት አለ ብለው እንደሚያምኑ በሐራ ጽሑፍ ላይ እማኝ ሆኖ የቀረበው ዶ/ር አክሊሉ ደበላ በቂ ማስረጃ ነው፡፡
  
ቅዱሳን ሰማዕታት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ሆኑ እንጂ እነርሱ ሰማዕትነትን ከተቀበሉ በኋላ ስለ እነርሱ ምስክር ልንሆንና በስማቸው ሰማዕትነትን ልንቀበል አልተጠራንም፡፡ የሰማዕትነት ታሪካቸውን ግን በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ እንጠቅሰዋለን እንማርበታለን፡፡ ምንም ቢሆን ግን በእነርሱ ስም ሰማዕትነትን መቀበል ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አይደለም፡፡

በድንግል ማርያም ስምም የሚቀበሉት ሰማዕትነት የለም፡፡ ውዳሴ ማርያም እንኳን “አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም ወከዓዉ ደመሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዐገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት፡፡” ትርጉም፦ “ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፣ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፣ ስለመንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሡ” ሲል ሰማዕትነት በስመ እግዚአብሔር እንጂ በስመ ማርያም እንደሌለ ያስረዳል፡፡

አረጋዊ ሰምኦን ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና እናቱ በእርሱ ምክንያት ስለሚያገኛት መከራ ሲናገር “እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።” (ሉቃስ 2፡34-35) ባለው መሰረት ሕፃኑን ኢየሱስን ከሄሮድስ ሰይፍ ለማትረፍ በመሰደድ፣ በመጨረሻም በልጇ መከራና ሞት ሐዘን እንዳገኛት ግልጽ ነው፡፡ ይህም እንማርበት ዘንድ በቅዱስ ቃሉ ተጽፎልናለና ልንማርበት እንችላለን እንጂ ማርያምን አንሰብክበትም፡፡ ስለዚህ “የድንግል ማርያምን ልዩ ፍቅር መስበክ” የሚለው የሐራ ትምህርት ስሕተት በመሆኑ የቤተክርስቲያን አባቶች እንዲህ ያለውን ኑፋቄያዊና ፍጡራንን ወደመመለክ የሚወስደውን የክሕደት ትምህርት ሊቃወሙና ትክክለኛውን የክርስትና ትምህርት ሊያጸኑ ይገባል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሠረት ለእኛ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር በተግባርም የታየው የክርስቶስ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ የምንሰብከውና ሕይወታችንን ሳይቀር ልንሠዋለት የሚገባው ይኸው የክርስቶስ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል ያለው ከዚህ የተነሣ ነው፡፡ ማርያምም በዚህ ፍቅር የተያዘች እንጂ ከዚህ ፍቅር ውጪ አይደለችም፤ ዋጋ የከፈለችውና በሐዘንም የተሠቃየችው ለዚህ ፍቅር ነው፡፡ እኛም የእርሷን አርኣያ ተከትለን ስለ ክርስቶስ ፍቅር እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት ልንታመን ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ መንፈሳዊ አስመስለን በአስደናቂው የክርስቶስ ፍቅር ላይ “የድንግል ማርያምን ልዩ ፍቅር መስበክ” ማለት መንፈሳዊ ምንዝርና ነውና ሊታረም ይገባዋል፡፡ አባቶች እንዲህ ያለውን ኑፋቄና ክሕደት ማረም ይገባችኋልና ደምፃችሁን ብታሰሙ መልካም ነው፡፡
    

 


21 comments:

 1. ምቼም ልቡናው የታወረ ሰው ካልሆነ በቀር የመጽሓፍ ቅዱስን ቃል አጣሞ ለመተርጎም ካልተሞከረ እኝህ አናት ምንም ስሀተት
  የለባቸውም ለምን ክርስቶስ እራሱ ሲነግረን ‹‹ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔን የሚቀበል ይላከኝን ይቀበላል›› ይላል ቃሉ
  ማቴ 10፡40 ታዲያ እኝህ እናት ድንግል ማርያም የክርሰቶስን እናት ተቀበሉ ደግሞም ሳያፍሩና ሳይፈሩ በተቀበሉዋት እናት እሰከሞት ድረስ ለመታመን በእናትነቷ እና ባማላጅነቷ ጸንተው ቢቆዩ ምኑነው ስህተtቱ ? ደግሞስ ሀዋርያው ጳውሎስ ሲነግረን እኔ ክርሰቶስን እንደምመስል እናንተም አኔን መስሉ ሲል ለምን ይመስለሀል እናታችንም ክርስቶስን አዝላ የተሰደደች ብጽህይት እናትን አይተው ስለ ክርሰቶስ የደረሰባትን መከራ እያሰቡ ቢንገላቱ ምኑ ነው ስህተቱ ? እናንተ ግን ይህን ሁሉ እንዳታስተውሉ አዚም ያደረገባችሁ ማነው ???? የሉተራውያን ጉርሻ ፣ የዲያቢሎስ አገዛዝ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልመ ልብ ይስጣችሁ እናታችን ግን ብዙውን አስተምረዋል እናንተም ተማሩ ሰማህትነትን በገንዘብ አይገዛም በምርጫ ሳይሆን በመመረጥ ነው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ‹ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔን የሚቀበል ይላከኝን ይቀበላል› ይላል ቃሉ
   ማቴ 10፡40
   ለመሆኑ ይህ ምን ማለት ነው???? እሰኪ በሙሉ ምእራፉን አንብብ…….የሚናገረው ወንጌል ይዘወልን የሚመጡትን መልእከተኞቸን መቀበል የተላኩ መሆናቸውን ማመን እንደ እግዚያብሄር መልእከተኞች የህወትን ቃል የሚያደረሱ የጌታ ባሪያዎች አድርጎ መቀበለን የሚመለከት ነው፡፡ሰለሆነም አይኖቻችን የሚያረፉት መልክት ላኪውን ጌታንና ይዘውት ለመጡት መልክት መሆን ይገባዋል፡፡ለዚህም ዋና አስረጅ፡
   ገላትያ 1፡7-9፡ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። ይላል፡፡እነዲሁም
   1ኛ ቆረንጦስ 1፡12 ይህንም እላለሁ። እያንዳንዳችሁ። እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?
   23...እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥
   ሰለዚህ ስብከት የሚያነጻጽርው ክርስቶስ ላይነው፡፡በመቀጠልም
   ታዲያ እኝህ እናት ድንግል ማርያም የክርሰቶስን እናት ተቀበሉ ደግሞም ሳያፍሩና ሳይፈሩ በተቀበሉዋት እናት እሰከሞት ድረስ ለመታመን በእናትነቷ እና ባማላጅነቷ ጸንተው ቢቆዩ ምኑነው ስህተቱ ? ብለሃል
   አዎ ስህተቱ ምን መሰለክ መጽሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ ጳውሎስ አማለጅነትን አለሰበከም ይልቁንስ ከአጵሎሰ ከኔም አይናችሁን አንሱ የተሰቀለውን ክርስቶስን ተመልከቱ ነው ያለው፡፡ድንግል ማርያም የጌታ እናት እግዚያብሄር ጸጋውን ያበዛላት ጻዲቅ ነች፡፡ግን እስዋን ያከበርን እየመሰለን ለምን አማላጅ አናደርጋታለን?አስኪ ማሰረጃ ከመጻፍ ቅዱስ ስጡን

   Delete
 2. እኔ ምን እንደገረመኝ ታወቃለህ ውድ መናፍቅ!
  እስከ አሁን ስለእመቤታችን ሲነገር ስለጌታችን ፣ስለጌታችን ሲነገር ስለእመቤታችን
  የሚነገርበት ምስጢሩ አለገባህም ማለት ነው? ዳሩ እንዴት ይገባሃል አንተ የእግዚአብሄርን
  ፍቅሩን ቸርነቱን ደግነቱን ምህረቱን ወዘተ ሳይሆን የምትመረምረው ባልቴት ይመስል ቃላት ስትሰነጥቅ ስትሳለቅ ነው የምትውለው
  ለመሆኑ መንፈሳዊ ምንዝርናስ ምን እንደሆነ ገብቶሃል፡መንፈሳዊ ምንዝርና እያመንዘራችሁ ያለችሁት እኮ እናንተ ናችሁ፤ መንፈሳዊ ምንዝርና ተሀድሶ ነው፣
  በእናቴ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖቴ ቤቷ ውስጥ መዕዷን እየተቋደሳችሁ ውስጥ ውስጡን ሚሥጥራቷንና ሥርዓተ በተክርስቲያንን ለመሸርሸር ከመሰሎችህ መናፍቃን ጋር የተጋባህ/ያመነዘርክ አንተ እያለህ እንዴት ነው የዓለም ዓማላጅ የጌታዬ እናት ስሟ በመጠራቱ ይህ ያለተገራ አንደበትህን የከፈትከው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ስደብ የሰይጣን ነው፡፡ይልቁንስ ቀጥተኛውን ያለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ማስረጃ ስጠን፡፡ጠጋ ጠጋ ያለ የራስህን ግን አልፈልግም ፡፡ከቃሉ በተለይ ደግም ከሃዋረያት ትምህርት፡፡ስላማላጅነት ማለቴ ነው፡፡ለነገሩ የለለውን ከየት ታመጣዋላህ፡፡በስደቡም በምኑም እያደነጋገርህ ወደሞት እንዳትገባ ጳዎሎስም ሃዋርያትም ወደመሰከሩት አነዲም ወዳመለከቱት እራሱ ጌታችንም ወዳዘጋጀው የደህንነት መንገድ ይህም እሱን ክረስቶስን በማመን በመንፈስ ቅዱስ በመጠመቅ መንፈስ ቅዱስንም በመቀበል በክርስቶስ የተዘጋጀውን የሕይወት መንገድ መከተል ነው፡፡
   አሁንም ወንድሜ መንገዱ ክርሰቶስ ነወና ና ወደመነገዱ፡፡ቃሉም እንዲህ ይላል-
   የዮሐንስ ወንጌል 14 (3-6) ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ። ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው። ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
   ሌላ መንገድ የለም ካለ በቃ የለም ነው፡፡እነዴት ያለ አዚም ነው ግን የያዛችሁ፡፡ ባማላጅ… ባሰታረቂ …ወዘተ...በሬ ወለድ በሆነ ነገር ግን ሰይጣን ከመዳን መንገድ ሊያወጣህ ባዘጋጀው የስሀተት ትምህርት አትጠለፍ፡፡
   አሁንም በፍቅሩ ክርሰቶስ ወደመንገዱ ና ይልሃል፡

   Delete
 3. ALBO FIRE...

  You are not living a mystical life. What is mystery for you?

  ReplyDelete
 4. Orothodox eko yesatew ezih lay naw. Bertu Glorify Jesus. I am orthodox too.

  ReplyDelete
 5. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 6. ምቼም ልቡናው የታወረ ሰው ካልሆነ በቀር የመጽሓፍ ቅዱስን ቃል አጣሞ ለመተርጎም ካልተሞከረ እኝህ አናት ምንም ስሀተት
  የለባቸውም ለምን ክርስቶስ እራሱ ሲነግረን ‹‹ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔን የሚቀበል ይላከኝን ይቀበላል›› ይላል ቃሉ
  ማቴ 10፡40 ታዲያ እኝህ እናት ድንግል ማርያም የክርሰቶስን እናት ተቀበሉ ደግሞም ሳያፍሩና ሳይፈሩ በተቀበሉዋት እናት እሰከሞት ድረስ ለመታመን በእናትነቷ እና ባማላጅነቷ ጸንተው ቢቆዩ ምኑነው ስህተtቱ ? ደግሞስ ሀዋርያው ጳውሎስ ሲነግረን እኔ ክርሰቶስን እንደምመስል እናንተም አኔን መስሉ ሲል ለምን ይመስለሀል እናታችንም ክርስቶስን አዝላ የተሰደደች ብጽህይት እናትን አይተው ስለ ክርሰቶስ የደረሰባትን መከራ እያሰቡ ቢንገላቱ ምኑ ነው ስህተቱ ? እናንተ ግን ይህን ሁሉ እንዳታስተውሉ አዚም ያደረገባችሁ ማነው ???? የሉተራውያን ጉርሻ ፣ የዲያቢሎስ አገዛዝ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልመ ልብ ይስጣችሁ እናታችን ግን ብዙውን አስተምረዋል እናንተም ተማሩ ሰማህትነትን በገንዘብ አይገዛም በምርጫ ሳይሆን በመመረጥ ነው ፡፡

  ReplyDelete
 7. እግዚአብሔር ስለ አከበራቸው ቅዱሳን ለመናገር አንደበትህ ዲዳ፣ ለመፃፍ እጅህ ሽባ ነው፡፡ ሁለቱም እንዲፈቱልህ ለምን፡፡

  ReplyDelete
 8. why our orthodox church members compare Lord God Jesus Chris with his mother virgin Mary. What everyone is talking or writing it doesn't makes seance. Please just read a holy bible about how to worship God. Virgin Mary chosen and blessed by God. Do not give God glory to somebody. Let all of us worship Almighty God than is good enough for christian people. Do not argue something not written in the bible. Jesus is only died on the cross and washed our natural sins from us. stop compare Jesus Chris with his mother or others holy angels and holy people.

  ReplyDelete
 9. Hi brother you are wrong. Because receive and worships is very big difference. According Meth ch 10:40 means all holy people received in the name of God interpreted as not worships those whom chosen by God.Just listen them what they are teaching about Jesus Chris died for our sins on the cross and gave us freedom through his blood. Please don not twisted word of God for your stupid purpose. God said in holy bible, do not worship anything be side me!!!

  ReplyDelete
 10. Keep going aba Selma now is a teaching time

  ReplyDelete
 11. አንድ ወቅት፣ጌታችን እንዲህ ብሎ ነበር:-ኦሪት ዘኁልቁ 12:8 "እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፤በምሳሌ አይደለም የእግዚአብሔርን መልክ ያያል፣በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለምን አልፈራችሁም?አለ እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።፣"አሁን ምን እንደሚላችሁ ቢገባችሁ ይግባችሁ

  ReplyDelete
 12. ምናልባትም እናንተ ተሀድሶ ከሃዲያን ጀለብያ ለብሳችሁ የማረዱን ሥራ የሠራችሁት ራሳችሁ ትሆናላችሁ፡፡ለእናንተ እምነት ማለት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ማጥፋት እንጅ በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ማመን አይደለምና፡፡ ቢሆን ኖሮ ቢያንስ በኢየሱስ አምላክነት የሚያምነውን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ለቀቅ አድርጋችሁ ከአፍንጫችሁ ሥር ላሉት ሙስሊም ወገኖቻን ክርስቶስን በሰበካችሁ ነብር፡፡
  ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እና አማላጅ እንዳለሆነ ያምናል፡፡ እናንተ ፕሮቴስታንቶችም/ተሀድሶዎችም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ግን አማላጅ እንደሆነ ታምናላችሁ፡፡ ሙስሊሞች ግን ኢየሱስ ጌታ ሳይሆን ነቢይ እንደሆነ ነው የሚያምኑት፡፡ ስለዚህ ለማን ነበር ወንጌል የሚያስፈልገው?
  ሌላው የሰይጣን መልእክተኛ እንደሆናችሁ የሚያረጋግጠው አንድም ቀን ራሳችሁን ሳትገልጡ በድብቅ ክህደታችሁን መዝራታችሁ ነው፡፡ ሕሊና ቢኖራችሁና እውነት ኢየሱስን የምትሰብኩ ቢሆን ኖሮ በአደባባይ ታደርጉት ነብር፡፡ በድብቅ ወንጌልም መስበክ ሆኖም አያውቅ፡፡
  እኛ ግን በዓለም አደባባይ ኢየሱስ ጌታ ድንግል አማላጅ ብለን ሰማእትነትን እንቀበላለን፡፡ ምስክሮቻችንም የቅርቦቹ የሊቢያዎቹና የጂማዎቹ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እስኪ የትኛው ተሀድሶ ነው ስለኢየሱስ ሰማእት ሆኖ ያሳየን? ወሮበላ! ለስጋው ኢየሱስን አሳልፎ የሸጠ ሆዳም! ለጊዜው ለሆዳችሁ ስትሉ ይህን ብታደርጉ አይገርመንም፡፡ የፖለቲካ አጋጣሚውን ተጠቅማችሁ ብትፍጨረጨሩም በሕይወት እያለን አሳልፈን አንሰጣችሁም፡፡
  በክርስቶስ ደም የተምሰረተችና ስንት ሰማእታት ሕይወት የከፈሉባት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ሲያምራችሁ ይቅር፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Melkam bilehal !

   Delete
  2. Nice comment "God Bless You"

   Delete
 13. ካተስተዋለ መልካም ት/ት ነው።በርቱ።

  ReplyDelete
 14. እናንት አባ ሠላማወች እንደምን ከርማችኃል በታላቁ አባታችን ስም ራሳችሁን ሰይማችሁ ይህችን
  ንህጽሒት ቅድስት የሆነች ቤተክርስቲያናችንን ለማናወጽ ከግብር አባታችሁ ከዲያብሎስ የተሰጣችሁን
  የጥፋት ተልዕኮ ለማስፈፀም ሌትተቀን ትለፋላችሁ፡፡
  ሆኖም ግን የድንግል ማርያም ልጅ መድሐኒዓለም ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን እንዲህ በቀላሉ ለእናንተና
  ለግብር አባታችሁ ለዲያብሎስ አሳልፎ አይሰጣትምና በከንቱ አትድከሙ፡፡

  ReplyDelete
 15. Yehen Yetsafkew WANAW Ye Christos TEKAWAMI NEH. DYABILOS Yemichawetebeh. Christosen yemayagola Christina Ke Dyabilos Naw.

  ReplyDelete
 16. What I didn’t understand is, if you don’t believe in orthodoxy that is fine, I know so many protestant who don’t believe in this that is there misguided choose but your argument is nonsense stay where you are and live alone us.

  ReplyDelete