Saturday, June 18, 2016

ሰበር ዜና - በስደተኛው ሲኖዶስ የሚሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት ስም ዝርዝር ታወቀበስደተኛው ሲኖዶስ የሚሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት ስም ዝርዝር ታወቀ። አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህና ዶ/ር አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ ከሚሾሙት መካከል ናቸው።
እነዶክተር አምባቸውና መሰሎቻቸው በከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ወድቀዋል። የአባ ወልደ ትንሣኤ እና የአባ ገ/ ሥላሴ መሾም እውነተኛ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች ያስደሰተ ሲሆን በቤተ ክርስቲያን ሊነግዱ ያሰቡ ቡድኖች ሁሉ ግን በተስፋ መቁረጥ እያለቃቀሱ ነው። ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ተቃዋሚዎችን አሁን ስለነቃሁባችሁ ዘወር በሉ በማለት በአቋማቸው ጸንተዋል፡፡ እነ ዶክተር ነጋ የራሳቸውን ጀሌ መነኮሳትን ጳጳስ በማድረግ ሲኖዶሱን ለመቆጣጠር ያቀዱትት እቅድ ነበር፣ ጳጳሳት ይሾሙ የሚለውን ሐሳብ ያመጡትም እነርሱ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር ግን ከነእርሱ ስለቀደመና ያላሰቧቸው ሰዎች ስለተሾሙ ራሳቸው ያመጡትን ሐሳብ ራሳቸው ተቃውመውታል። እነ አቶ ዘውገ ደግሞ የሲያትሉን አባ ገብረ ሥላሴን ተቃውመው ደብዳቤ ጽፈዋል። ተቃውሞዎች ሁሉ ዋጋ ባለማግኘታቸው ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ  ሁሉም ከየአቅጣጫው በኦክላንድ መካነ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በመሰባሰብ ፕሮግራሙን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
በዚህ መሠረት፦
1. አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ ከሎስ አንጀለስ ድንግል ማርያም
2. አባ ገ/ሥላሴ ጥበቡ፣ ከአትላንታ ቅዱስ ገብርኤል፣
3. አባ ጽጌ ደገፋው፣ ከሎስ አንጀለስ ቅድስት ማርያም፣
4. አባ ሳሙኤል ወንድ ይፍራው ከዴንቨር ቅድስት ማርያም፣ (ደቡብ አፍሪካ የነበሩ ናቸው)
5. አባ አቢዩ ከኡጋንዳ
6. አባ ሀብተ ኢየሱስ ከኖርዌይ
7. አባ ሳሙኤል ከካናዳ ኤድመንተን መድኃኔ አለም
8. አባ ገ/ ሥላሴ  ከሲያትል ቅ/ገብርኤል ይሾማሉ። የኡጋንዳውና የኖርዌዩ ይገኙ አይገኙ አልተረጋገጠም።
ያሁኑ ሹመት የውጩን ሲኖዶስ ጠንካራ ያደርገዋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። በተለይም ወንጌል በሲኖዶስ ውስጥ ክብር ሊያገኝ ይችላል ተብሎ ይታመናል። ከተራ ቁጥር አንድ እስከ ስድስት ያሉት አባቶች የቤተ ክርስቲያን ታማኞችና የሚገባቸው ናቸው የተባለ ሲሆን ተራ ቁጥር ሰባትና ተራ ቁጥር ስምንት ግን ምን ዓይነት መንፈሳዊ ሕይወት እንዳላቸው ብዙም አልታወቀም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም በእውነት እንዲቀባቸው እየጸለይን ጠቅላላ ዝርዝሩን እንደ ደረሰን እናቀርባለን።  

14 comments:

 1. Oh my God, these monks are the protestants. That means the exiled Synod is becoming full of protestants. Aba Melketsedek is known protestant.

  ReplyDelete
 2. God bless you all

  ReplyDelete
 3. God bless you all the supporters of sidetegnaw sinodos .congratulations these two fathers are the back bone of the sidetegnaw sinodos. Thank God.

  ReplyDelete
 4. God bless you all!!!!!
  Congratulations these of you who are the supporters of sidetegnaw sinodos.Aba Woldesen say Ayalneh and Dr Aba Gebreslasse.you two are the back bone of the sidetegnaw sinodos. God bless you.

  ReplyDelete
 5. Congratulations! !!!

  ReplyDelete
 6. Aba weldtensaye Ayalneh and Aba Dr Gebre Selassie Tibeb are the backbone of the Sidetegnaw sinodos. Congratulations!! You deserve it.!!!!!

  ReplyDelete
 7. አይ አባ ዲያብሎሶች በሁለት ቢላዎ የምትበሉ ከየትኛው ወገን ናችሁ? አንዴ ሀገር ውስጥ/ውጭ ያለውን ሲኖዶስ በመደገፍና በማጥላላት ትባዝቃላችሁ። አቋም የላችሁም። እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ለምዕመናንና ለአባቶች እንዲሁም ለቤተ ክ/ን አንድነት አትሰሩም። ወዮላችሁ ወዮታ አለባችሁ!

  ReplyDelete
 8. the hooll gonder

  ReplyDelete
 9. ሹመት ያዳብር አዳዲስ ጳጳሳት፤ ይህም ይህ ነው ከዚህም ጋር ዘመኑ ዘመነ መንሱት መሆኑ እንዳይዘነጋ ልብ ይሏል።ከዚህ በኋላ ትግሉ ፈጣሪውን አምኖ በቅንነት ከሚያዘግመው ምእመን ጋር ሳይሆን ከሰማይ በታች ከምድር በላይ የጨለማውን ዓለም ለመቈራኘት ጥረት ከሚያደርጉ አስመሳዮች ጋር ነው። አስመሳይ አጋንቶች፤ ሳይሆኑ ሀይማኖተኛ ነን እያሉ ተቈርቋሪዮች ነን በማለት ራሳቸው መናፍቃን ከሀድያን የቤተክርስቲያን ተቃዋሚዮች ሲሆኑ የራሷን አበሳ በሰው አብሳ የራሳቸውን መጥፎ ስድብና የስንፍና ቀንበር በሌሎች ላይ ይጭናሉ በመሆኑም ዑቅዎሙ ለከለባት ምንን ምን ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል እንደተባለው ከልብ የፈጣሪን ስም በመጥራት ካልጸለዩበት እንዲህና ይህን የመሰለ ቁራኛ ሊወገድ አይችልም። ወዝንቱ ዘመድ ኢይወጽእ ዘእንበለ በጾም ወበጸሎት

  ReplyDelete
 10. ሹመት ያዳብር አዳዲስ ጳጳሳት፤ ይህም ይህ ነው ከዚህም ጋር ዘመኑ ዘመነ መንሱት መሆኑ እንዳይዘነጋ ልብ ይሏል።ከዚህ በኋላ ትግሉ ፈጣሪውን አምኖ በቅንነት ከሚያዘግመው ምእመን ጋር ሳይሆን ከሰማይ በታች ከምድር በላይ የጨለማውን ዓለም ለመቈራኘት ጥረት ከሚያደርጉ አስመሳዮች ጋር ነው። አስመሳይ አጋንቶች፤ ሳይሆኑ ሀይማኖተኛ ነን እያሉ ተቈርቋሪዮች ነን በማለት ራሳቸው መናፍቃን ከሀድያን የቤተክርስቲያን ተቃዋሚዮች ሲሆኑ የራሷን አበሳ በሰው አብሳ የራሳቸውን መጥፎ ስድብና የስንፍና ቀንበር በሌሎች ላይ ይጭናሉ በመሆኑም ዑቅዎሙ ለከለባት ምንን ምን ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል እንደተባለው ከልብ የፈጣሪን ስም በመጥራት ካልጸለዩበት እንዲህና ይህን የመሰለ ቁራኛ ሊወገድ አይችልም። ወዝንቱ ዘመድ ኢይወጽእ ዘእንበለ በጾም ወበጸሎት

  ReplyDelete
 11. Egzbher abzto yebarkot

  ReplyDelete
 12. God bless you!!!

  ReplyDelete