Saturday, June 4, 2016

ዲሲ ገብርኤል መቼ ይሆን ገብርኄር የሚያድላትፉት የአቢይ ጾም ሳምንታት ስያሜአቸውና ትምህርታዊ ነጥባቸው በውስጤ እንቅልፍ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሲያብኝ ቆይተው ር።
እነዚህም
ምኩራብ ታላቁ ካቴድራልና መን ፓትርያርክ የነረው፣ስንት ታላላቅ አባቶች ወንጌል የሰበኩበት፣ ዛሬ እንዴት የጥቂት ሰዎች መነገጃ እና ምእመናን ሪያ ሆነ?
መጻጉ ኢትዮጵያን እና ቤተ ከርስቲያንን ከሚንጣት የዘረኝነትና ጎጠኝነት ደዌ የዲሲ ገብርኤልስ መቼ ይሆን የሚድነው?
ደብረዘይት ፋቸው ወሰን ያጣው የዲሲ ገብርኤል ቦርድ በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር ዘዴ ፓትርያርክ፣ሊቃነጳጳሳት፣ መነኮሳት፣ቀሳውስት፣ዲያቆናት፣ለምን ባይ ምዕመናን በግፍ ሲያባ የመድኃ ክርስቶስን ዳግም ጽአትን ማለትም ማንም በማንም ጀርባ የማይደበቅበትንና ብቻውን የሚቆምበትን የፍርድ ቀን እውነት ካመኑ መዘንጋታቸው ለምን ይሆን?
እነዚህን ሃሳቦች ሳሰላስል፣ ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ ሳሳኝ ደግሞ፤- “መኑ ውእቱ ገብር ኄርታምኝ አገልጋይ ማነው? የሚለው ቃል ነው። ይህ ቃል እንዲሁም የመዝሙሩ ትምህርት አንድ የክርስትና አማኝ ከሊቀ ጳጳስ እስክ ምዕመን በተሰጠው መክሊት እግዚአብሔርን ማገልግልና ሰውን ወደ ህይወት መን ወደ መድኃዓልም ክርስቶስ ማቅረብ ነው። ለዛሬ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካህናትን በተመለከተ ትኩረት ሰጥተን እንመልክት።
አንድ ካህን ሁሉም በፊት ቅና መረዳት ያለት፣ ሲነጋም ሲመሽም በልቡ ሊያስብ የሚገባው ከአምላኩ እና ከእውነተኛው እረኛ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠውን የበጎቹን ነው። ይህን የመጀመሪያ አደራ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
1 ጴጥ 5 2-4  
ታማኝነታቸው ከማንም በፊት ለእግዚአብሔር እና ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ አንዳንዴ ለብር፣ ለግል ጥቅም፣ ለቦርድ፣ ወይንም ለዘመድና ለዘር ሊሆን አይገባም፣ አይችልምም። ታዲያ ዛሬ // ገብርኤል ያሉት ካህናት መምህር ፍሬሰው፣ መሪጌታ ተስፋዬ፣ መሪጌታ ዲበኩሉ፣ ቀሲስ ይስሃቅ ራሳቸውን ዚህ ቃልና ትእዛዝ ጋር እንዴት ያያሉ?  ይታያሉ? የስም ቅደም ተከተሉ አቅማምጥ ምክያት ው። ከሀገር ቤት መጣበት ጥቂት አመታት ጊዜ ጀምሮ ቁልፍ የሚላቸውን ሰዎች ሲያጠናና ሲዛመድ፣ ከእግዚአብሔር ሰላምታ ይልቅ ኃይል ቃል የሚቀድማቸውን ሰዎች ሲመምል ቆይቶ ዛሬ የቤተ ክርስቲያኑ አራጊ እና ፈጣሪ እንዲሁም አስተዳዳሪ መምህር ፍሬሰው፣ / ነጋ አቶ ያረጋል እንደሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። መሪጌታ ተስፋዬ እንደ ድምጽ ማጉሊያ ማይክሮፎን የተሰጣቸውን ትእዛዝ ከማስተላልፍ ባሻገር ምንም ስልጣን እንደሌላቸው በቅርብ ያሉ ሲናገሩ ከዚህም አልፎ ከራሳቸው አንደበትየእንጀራ ጉዳይ ሆኖብኝ ነው እንጂእያሉ ብዙ ዛሬ እየተሰሩ ያሉ ነገሮች እንደማያስደስታችው ሲናገሩ የሰሙ ብዙ ናችው።
ሎቱ ስብሐት፣ አንድ ካህን በእግዚአብሔር ቤት ቆሞ እውነትን ትቶ ብር ሲያነሳና በነ ነፍስ ምን ይባላል? እጅግ የሚያሳዝነው በሌላ ንዳ የመጣውን ፍሬሰውን አስድስታለሁ ድሮ በአባ ወልድትንሳኤ ስብ የቀነሰብን እና ባዶ የሆነብን ቤተ ከርስቲያናችን አሁን እሱ ከመጣ በኋላ ዕምናኑ በዝተዋል ሲናገሩ መሬት ተክፍታ አልመዋጧ የእግዚአብሔርን ቸርነት ልጻል። ትላንት በነ አባ ወልደ ትንሳኤ ጽኑ ስብት፣ በእነ አቶ መሃሪ፣ አቶ ዘውዱ፣ ስንት ጠንካራ የቦርድ አባላትና ምእመናን ድካም እንዲሁም ደፋ ቀና ቤተ ክርስቲያኒቱን ባቆሙ ካህናት በተዘጋ እዳ ዛሬ እንዲ ሲባል አምላክስ ምን ይላል? ሰው እውነትን ተናግሮስ አንቱን ይስጥ አልነ?  ሐስት እስከመናገር መድረስ ለምን? ዛሬ ቤተ ከርስቲያኑ ሲሄዱ ግርማውን፣ ጸጋውን አላጣም ወይ? ስንቱ ምዕምን እያዝነ እያለቀሰ ሄዶ ቀረ? ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ ሲሄዱ እውነት ወንበሩ ነው የሚበዛው ወይንስ ሰው? ስድቡ ነው የሚበዛው ወይንስ ቃል እግዚአብሔሩ?
ስድብን ካነሳን ወደ መምህር ፍሬሰው እንመስ። ይህ መምህር ጥቂት ወራት ቀድሞት ከኢትዮጵያ በመጣው በቄስ ይስሃቅ ጠቋሚነት ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ጸባዩ ሲቀየር ሰውን ልፍ፣ ሲያሳድ፣ ሲያንቋሽሽ ከኔ በላይ ሰባኪ፣ ቄስ፣አዋቂ የሚል ሲሆን፡ ስለርሱ በሀ ቤት ለጠየ ሁሉበቦሌ ሚካኤል የሰራው ጉድ ብዙ ነው” “ እኛ ስናውቀው ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ የመንግሥት አግልጋይ ነውየሚሉና በአንድ ሰባኪ የቤተ ክህነት ደሞዝ ሊመጡ የማይችሉ ፎቆቹንና ንግዶቹን የሚጠቅሱ ብዙ ናችው። በቅድስት ሥላሴ ፈሳዊ ኮሌጅ ሲማር አንድም አውቀዋ የሚል የቲዎሎጂ ምሩቅ ሳይኖር ሪኮርዱ ሲታይ ግን የተልኮ ዲግሪ እንዳ ያሳያል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? እንደ አንዳንድ ባለ ስልጣናት ዲግሪ ይሆን? በቅርብ ጊዜ በኮሌጁ እንደዚህ አይነት ሥራዎችን ሲሠራ የኖረው የማህበረ ቅዱሳን አባል ተይዞ እንደተባረረ በዚሁ ብሎግ ተዘግቦ ነበር። እርሱም አሜሪካ ሆኖእንዴት ውን ሰው አባረሩትእያል ሲያወራ የሰሙ ብዙ ናቸው። እንዲህ የተመሰገነበት ሥራ ምን የሆን? ከሁሉ ከሁሉ በላይ ደግሞ መምህር ፍሬሰው ለወንጌል ሰባኪያን ያለው አሳዳጅነት አሁን ባለበት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንም ይታያል። ዘለዓ እነ አባ ወልደ ትንሳኤን  ተሃድሶ ሲል ብጹዕ አቡነ ኤልያስንተሃድሶ የሆኑትን አባ ወልደ ትንሳኤን ሮፓ ለምን ይጋብዛሉሲል፣ / አባ ገብሥላሴንና  እንዲሁም በአሜሪካ በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ ያሉ ሊቃውንትና ሰባኪያንን ላነሳለት ሁሉ ሲያንቋሽሽ፣ ትምህርታቸው ስህተት የተሞላ እንደሆነ ሲናገር የሚሰሙ ብዙ ናቸው። እንዚህ የተጠቀሱ ስባከያን፣ እነ አቡነ ሚካኤል፣ እነ መምህር ጸጋዬ፣ እነ መምህር በኃይሉ አልፎም ታላቁና ያለፍርሃት ወንጌል ሲሰብኩ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ሲያቅኑ የኖሩትን ብጹዕ አቡነ መልጼዴቅ ባስተማሩበት፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ በሰጡበት አውድ ምሕረት ላይ ቆሞ በላይ ሊቅ የልምእያል የሰንበቱን ትምህርት ትቶ ራሱ ሲያ ያዩና የሰሙ ምእመናን አዝነው ሄደዋል። የእግዚአብሔር ታማኝ አግልጋይ መሆን እንዲህ ይሆንን? ምን ይሁንጋኖች አለቁና ንቸቶች ጋን ሆኑነውና ነገሩ! ባዶ ቤት ተገኘ።

የሚያሳዝነው በተደጋጋሚ ሳምንታት ወንጌሉን ትቶ የትእቢት ቃላት፣ ለራሱ ገመና መሸፈኛ ትምህርት ሲስጥ ቆይቷል። ለምሳሌ ባለፈው በዚሁ አባ ሰላማ ላይ እንደተዘገ ትዳሩን አፍርሶ ሳለ ቤተ ክርስቲያን የፍቺውን ምክንያት ሳታጣራ አግልግሎት መስጠትና መቀደስ ይችላል ወይ የሚል ጽሑፍ እስኪወጣ፣ እርሱና ግብረ አበሮቹ አንድ ቀንአልፈታም እኮ እንደውም በዚህ ወር ቨርጂኒያ ስቴት ከባለቤቱ ጋር ቤት ገዝተው ሊገቡ ነውሲሉ፣ አንድ ቅን ደግሞቆቡን እና ቀሚሱ ስላላረገ ነው እንጂ መንኩሷልሲሉ ቆይተው እድሜ ለአባ ሰላማ ብሎግ እውነቱ ሲጋ እንዲሁ በሰንበት ወንጌሉን ትቶበአንድ ቤት አይነት ወጥ ከሚሰራ ቤተ ክርስቲያን ፍቺ ትፈቅዳልችሲል በየጊዜው ንስሃ አባት እርሱን ያዙት እየተባሉ የሚወተወቱት ምእመናን ምን ያስቡ ይሆን? ታማኝ አገልጋይ ይህን ነውን ለበጎቹ የሚመክረው? ቃለ እግዚአብሔሩስ እንዲህ ይላልን? በእንደዚህ አይንት ሁኔታዎች ላይ ሁልጊዜ የሚያሳዝነኝ ብሯን አፍስሳ፣ ፕሮ አድርጋ መወጣጫ ሆና የቀረችውን የቀድሞ ባለቤ የት ነሽ፣ ያንቺስ አንደበት ምን ይላል ሳትባል ቤተ ክርስቲያን ዝም ነው። ከቶ ዚህን ጳጳሳት፣ መነኮሳትና ቀሳውስትን እናት ወልዳ አላሳደገቻቸውምን? ማስረጃ ካለ እኔው እራሴ እርምጃ እወስዳለሁ ሲሉ የቆዩት ታላቁ ሊቀ ጳጳስ ወዴት አሉ? በአዎሮፓ አካባቢ የሚታሙበት ሃሜት እውነት ነው መቀበል ይከብደናል። አባቶቻችንበክርስቶስ ክርስቲያንየሚል አንድ ዝምድና እንጂ ከላይ የተጠቀሰው ችግር ሊኖርባቸው አይገባም። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሰርተው በመልካም የሚነሱ አባት ናቸው እንጂ በመጥፎ ሰው ምክር ታሪካቸውን አበላሽተው አያልፉም።
የዛሬ ስድስት ወር በቅዱስ ሲኖዶስ ስብስባ ላይ ከተሳተፉ በኋላ እስከዛሬ ሲደረግ እንደነበረው የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ እና መግለጫ አናብም ብለው ለጠየቃቸው ሁሉ ተገኝተው የነበሩበትን ስብሰባ እንዳልነበሩ አንድ ቀንወረቀቱ አልደረሰንምአንድ ቀንጊዜው አላመቸንምሲሉ ተው ጭራሽአትጨቅጭቁን ኢንተርኔት ላይ አለላችሁ አንብቡትእያሉ ለጠያቂ ምዕመናን በሚያሳዝን ሁኔታ መልሰዋል። ይህን ሲያረሳሱ የማይረሳ ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በተጠናቀቀ በሳምንቱ እነ መምህር ፍሬሰው ምን አሳውጀዋል? ታቦት ቆሞ ጸሎት ቆሞምዕመናን ተጠንቀቁ ጥሩ ሰባኪ መስለው፣ ጥሩ አገልጋይ መስልው፣ የዋህ ምዕመን መስለው ተሃድሶዎች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሉሲያስብሉ የደበቁት የሲኖዶስ ውሳኔና ውይይት ምን ይል ነበር? በእውነቱ በኃይለኝነትና በጎጠኝነት ካባ ምን ይሆን ዛሬ ቅዱስ ገብርኤል የገባ? ደስ የሚያሰኘው ነገር ግን ይህች ሥራ ከቅዱስ ሲኖዶስ ደርሳ ስለተጠየቁበት ሳይወዱ በግድ የባለፈው ሳምንቱን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲነብብ አድርገዋል።
ነገሩን አተኩሮና ረጋ ብሎ ለተመለከተ ጳጳሳትንና ካህናትን  በተለይም እነ መምህር ልዑለ ቃልን፣ እነ / አባ ገብረ ሥላሴን፣ እነ አባ ወልደ ትንሳኤን እንዲሁም ሌሎች ጳጳሳትንና ካህናትን ፊት ለፊት ሰላም እያሉ ከጀርባ ሌላ ክፉ ወሬ መዝራት አላማ ሁኖ የተያዘውን ተግባራዊ ሊያደርጉ ተመልመልው የተላኩ ካህናት እና ቦርድ ውስጥ ያሉ፣ ለስላሳ ቃል እየተናገሩ ነገር ግን መርዝ እየወጉ ዝምድናን አድርገው የገቡ ሰዎች አላማ ቅዱስ ሲኖዶሱን ለማዳከምና በመጨረሻም ለመበትን እንደሆነ ታውቆባቸዋል።

ታዲያ  እንደ እነ ይሁዳ ዛሬ ከጎን አብረው ሁነው ነገ አሳልፎ ሰጪ እንደ እነ ኢያጎ አማካሪ መስሎ በአላማ አጥፊ ከሆኑ ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ ግድ አይልምን? ቅዱስ ፓትርያርኩ ስንት ዓመት እንዳልኖሩበት ቤተ ክርስቲያን፣ ስንት ሊቃነ ጳጳሳት፣ ስንት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዳላገለገሉበት ዛሬ እነ መምህር ፍሬሰው ከቅዳሴ በኋላ ሃይማኖተ አበው እና ተዐምረ ማርያም ስላስነበቡእስከዛሬ የተሟላ አገልግሎት አልሰጠን ከዛሬ ጀምሮ ግን ይኸው ጀመርንተብሎ ባዶ እየሆነና ግርማ ሞገሱን እያጣ በመጣ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚታወጅ?
ለዛሬ በዚህ እንቋጭናየአሜሪካ ኑሮ ለኔ አይሆንም ሐብታም የነበርኩት ኢትዮጵያ ጸሐፊ ሆኜ ሥሰራ ነበርየሚሉት ቄስ ይስሓቅን እና ወዳጆቻቸው ተከፍለው ወጥተው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መሥርተው አብረው እንዲሄዱ ሲጠይቋቸውእነዚህ ሞኞች ተጠናክረው ቆመው የማይቋርጥ ደሞዎዝ እንደሚከፍሉኝ ሳላውቅ፣ ቤተሰብ እያ ምን ብዬ ይህን ቋሚ ገቢ ትቼ እሄዳለሁኝያሉት ለአቋም ሳይሆን ለገንዘብ የቀሩት፣ የጅማ ዥም ታሪክ ያላቸውን መሪጌታ ዲበኩሉን በሌላ ጊዜ እንመለስባቸዋልን። የምሕረት አምላክ ለእነዚህ ካህናት የንስሓ ልብ ይስጣቸው፣ ለቤቱም ቸር አግልጋይ፣ እውነተኛ እረኛ ያድል።

-    ሰይፈ ገብርኤል

4 comments:

 1. አይ ሰይፈ ገብርኤል! እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ፤ አባ ሰላማም ትኩረታችሁ ማህበረ ሰይጣን ወእኩይ ላይ ብቻ ስለሆነ የዚህን አይነቱን ጽሁፍ ቸል ያላችሁት ይመስላል። አንዳንዴ እንኳ እንዲህ ያሉ የቤተክርስቲያን ነቀርሳዎች ታሪክ እንዲጻፍ ብታደርጉ ሕዝቡ ከልጆቹ ጉሮሮ ነጥሎ የሰራውን፤ የገዛውን፤ ያደራጀውን ቤተክርስትያን ከነጣቂ ማዳን በተቻለ ነበር። ያ ባለመደረጉ ይኸው ዛሬ የወያኔ ቡችሎችና ወኪሎች እነፍሬሰውና ግብረአበሮቻቸው ስማቸውን ቄስ ይጥራውና ያልደከሙበትን ቤተክርስቲያን ባለንብረቱን ሕዝብ እያባረሩ በሕዝብ ገንዘብ እመሃል አገር ፎቅ ይገነባሉ ንግድ ይከፍታሉ። ግማሹም ጳጳሳቱ ሳይቀር ሁለትና ሶስት ሚሊዮን የሚያወጣ ቪላ እየሰሩና እየገዙ ያከራያሉ። እንደ ሰይፈ ገብርኤል የሚያወቀውን የሚያሳውቅ በመጥፋቱ እኮ ነው እስከ ዛሬ እንኳን ክህነት በቤተክርስትያን አካባቢ ደርሶ የማያውቅ የወያኔ ተቀጣሪ ፖለቲከኛ፤ የሁለት ወይም የሶስት መንግስት ሰላይ፤ ነፍሰ ገዳይ፤ የሰው ዝቃጭ የሰው አተላ ሁላ በዳያስፖራ አብያተክርስቲያናት ተሰግስጎ አመጽ በማካሄድ ህዝቡ ቃለ እግዚአብሄር እንዳይማር ሰላም በመንሳት የሚያውከው። ይኸ ሁሉ ወሸከሬ ባለብሎግ ያንዱን ጽሁፍ ኮፒ እያደረገ ከመለጠፍ እንዲህ አይነቱን የህዝብ ጉዳይ እያጠና የማይለጥፈው ለምን ይሆን? እነሱም የወያኔ ደሞዝተኞች ይሆኑ? አልወይንኩም የምትል ሁሉና አማኝ ነኝ የምትል አካባቢህን መርምር፤ ለልጆችህ ልታሰተላልፍ ያቆምከውን ቤተክርስቲያን በነቂስ አጥራ፤ በጾም በጸሎት ትጋ፤ እግዚአብሄር ከሁላችን ጋር ይሁን ይርዳን!!

  ReplyDelete
 2. አይይይይ ዲሲ ገብርኤል ስንቱ ይሰደድብሽ። የተበላሸ ስጋ ሽቱ ቢቀቡት በጨርቅ ቢሸፍኑት የበለጠ እየገማ ይሄዳል እንጂ አይድንም። አዲሱን ሰባኪ ባላውቀውም በዙሪያው ያሉ ሰዎች ግን ጠንቅቄ አውቃቸዋለሁኝ። እኔም ቤተሰቤም ዛሬ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ነው የምንሄደው። ምክኒያቱም ልጄ ሰው ሲገድል አይቼ ዝም ብል እኩል ሃጢአተኛ ነኝ። ማንም ምእመን እራሱን አያታል ያለ ይቅርታ ህይወት ክፋት እየሰሩ፣ የሚሰሩን ሰዎች ምን እንርዳ የሚሉ ካህናት የእናንተ አጥፊ እንጂ መካሪ አስተማሪ ሊሆኑ አይችሉም። እኔ መሪጌታ ተስፉዬ በሥራ ቀን ልሳለም መጥቼ ያሉትን ሰምቼ ነው አያሳየኝ ብዬ ለስንት አመታት ከገብርኤል የቀረሁት። ዛሬ ቦርድ ውስጥ ያሉትም በውጭ ያሉትም አይደለም በቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ተስፋ የሚያስቆርጡ ናቸው። ከኢትዮጵያ ወጥተው ስቲል መንደር ውስጥ ያሉ እጅግ በጣም የሚዋሹ ጳጳስ ልደብድብ ብለው የሚነሱ ናቸው። ያሳደጓቸው አገልጋዮች አባረው እንርሱን የሚምስላቸው ጥቁር ቢያመጡ አይደንቅም። ይልቁንስ ለእነ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና አቡነ ኤልያስ ጸልዩ ከእነዚህም ሰዎች ምክር ጠብቋቸው። እንደ እነ አቡነ ዜናማርቆስ መንፈስ ቅዱስ ሲመራቸው መጨረሻቸው ያምራል።

  ReplyDelete
 3. Aba Selama is one blog that is trying to objectively put out valuable information that keeps Mahibere Kidusan on their toes, and all of the woyane agents such as memhir Fresew, Aba Melaku and the likes on notice by threatening them that they will pull out the skeleton out of their closets, i.e., tell all about their hidden secrets. There should be 10 Seife Gebriel’s that write on every blog there is to stop these highway robbers from their Idolatry, adultery, deceit, theft……!!
  What really happened to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church? What happened to us all? Our lay forefathers used to talk to God every morning and night and everything they asked for happened for them. They pray for rain, rain happened, they pray for peace, peace happened, etc., etc., etc.…….
  What happened to this generation? How can a 3000-year history disappear in one generation? How can the clergy, the religious, non-religious all worship the same idol “the almighty dollar”? How did we become big in trying to pluck a twig from our neighbors eyes, before we pull the LOG out of our own? Is this what was expected from us by our forefathers as Orthodox Christians? It is so sad and depressing we have gotten to this stage!!
  We should/must cry out to the merciful God for forgiveness!

  ReplyDelete
 4. መችም አሁን ብዙ ቢወራ ዋጋ የለውም። ይህ ቤተክርስቲያን በጠላት ከተያዘ እና እውነተኛነቱን ከሳተ ቆየ። በተለይ እነ ዶ/ር ተብየ ለሁለተኛ ግዜ አጭበርብረው ከገቡ ግዜ ጀምሮ የጥፉቱ ስራ ተያይዘውታል። የዋሆች እየተሰደዱ ክፋዎች እየነገሱ አሁንም ቀጥሏል። በእርግጥ የነሱ ደጋፊ የሚመመስል ሁላ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ እንተዋውቃለን። ቤተክርስቲያኑ ግን ወደ ነበረበት አይመለስም ይብስበታል እንጂ።

  ReplyDelete