Tuesday, June 7, 2016

እልህና ግዴለሽነት በኢ ት ዮ ጵ ያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን !

 Read in PDF
መሪጌታ እውነቱ ከቤተክህነት

የእልህና  የግዴለሽነት  አባዜ  ሀገርን  ያሸጣል።  ወገንን  ያስክዳል።  እግዚአብሔርን  ያስረሳል።  እልህና  ግዴለሽነት  በንዴትና  በሥሜት  ስለሚታጀብ  እንደ  ጋሪ  ፈረስ  ወደፊት  እንጂ  ግራና   ቀኝን  አይመለከትም።  በተለይም  እልህ  በሥሜት  ፈረስ  ስለሚጋልብ  መነሻው  እንጂ  መድረሻው  አይታወቅም።  ሥሜት  ልጓም  የሌለው  ፈረስ ነውና።  

    
ሁለተኛውን   ሳምንት   በአገባደደው   የቅዱስ   ሲኖዶስ    ጉባኤ   ጆሮን   ጭው    የሚያደርግ   ብዙ  ነገር   እየሰማን   ነው።   ከሚሰማው   እጅግ   ዘግናኝ    ክስተት   ይልቅ   አንገትን   የሚያስደፋ   እንዲህ  ዓይነቱ   ነገር   ከማይጠበቅባት   ከቅድስት   ቤተ   ክርስቲያን   መሰማቱ   የሰው   ኃይል   ሳይሆን  የእግዚአብሔር   ዱላ    ነው   ለማለትም   እንድንደፍር   አድርጎናል።   እግዚአብሔር   የቁጣውን   ዱላ  ሲያነሳ   ነገር   ሁሉ   ይጨልማል።   ማስተዋልም   ይጠፋል።   አዋቂዎች   አላዋቂዎች   ይሆናሉ።  ሽማግሌዎችም   ወደ   ሕጻናት   አእምሮ   ይመለሳሉ።   ያከበሩኝ  አከብራለሁ  የናቁኝም ቃሉ አይሆንልኝም` ያለው   እግዚአብሔር   ከዝምታ   በኋላ   ጆሮን   ጭው    የሚያደርግን  ነገር  ያመጣል።  እግዚአብሔር  ሲናቅ  በተከበሩት  ላይ  የተናቁትን  ያስቀምጣል።
 ሕዝቡን  ሲቀጣ  ክፉውን   በሕዝብ   ላይ   ይሾማል።   ልጆቹን   መገጸጽ   በአቃተው   በኤሊ   አባትነት   ያዘነው  እግዚአብሔር   ,  ለቤት ሽማግ ዳይ ክንድህ የአባህንም  ክንድ ርበት ይመጣል።   በእስራኤ በረከት ሁሉ ደሪያዬ ላትህን ታያቤትህም ለዘላለ ሽማግ አይገኝም.  (1.ሳሙ. 2:31-32) እንዳለ  ቅዱስ  መጽሐፍ  ያስረዳል    
  
የሲኖዶሱን  ጉባኤ  ሲያውክ  የሰነበተውና  አንዳንድ  ውሳኔዎችንም  የሥሜት  ውጤት  ያደረገው  ይኽው  እልህና  ግዴለሽነት  እንደሆነ  ተስተውሏል።  እልህና  ግዴለሽነት  በቤተ  ክርስቲያንዋ  ውስጥ  እግሩን  ከተከለ  ዓመታትን  አስቆጥሯል።  ዛሬ  የምንታመስበት  ምክንያት  ቀደም  ሲል  በእልህና  በግዴለሽነት  ላይ  በተመሠረቱ  ውሳኔዎች  ነው።  ለምሳሌ  ያህል  የቅርብ  ጊዜ  ትዝታችን  የሆነውን  ወደ   ኋላ  ተመልሰን  ብናነሳ፦  

1.   የቤ   ክርስቲያ   ለሁለ   መከፈል   ቤተ   ክርስቲያንን   ለሁለት   የከፈለው  እንደሚባለው   የቀኖና   ጥሰት   ጉዳይ   ሳይሆን   የእልህና   የግዴለሽነት   ጉዳይ   ነው።  
ሁሉም በየወገኑ በራሱ ሀሳብ እየተሳበ ለአንዲት ቤተክርስቲያን ልዕልና ሳይሆን የግል ስሜቶች ስላየሉ በበቤተክርስታንዋ ታሪክ ለመጀመራ ጊዜ ሁለት ሲኖዶስ ተቋቋመ።   አባቶች   መከፈሉ   የሚያስከትለውን   ችግር   ሳይገነዘቡ   በሥሜት   ነጎዱ።  በእልህ  የእርቁንም  ዕድል  አጨለሙ።  የቤተ  ክርስቲያንን  ችግር  ለመፍታት  የደከሙ  የብዙዎች   ሽማግሌዎችንና   ሊቃውንትን   ድካም   ፍሬ   አልባ   አደረጉ።   በሃይማኖት  መሰል   ፖለቲካ፤   በጎጥ፤   ለተለያየው   ሕዝብ   ምንም   ሳያስቡ   አሁንም   ልዩነቱን  አሰፉ። ሁሉም ነገር እልህ ስለሆነ ከእልህና ከግዴለሽነት ሥራ ለመውጣት አልተቻለም።
  
2.   የብፁ    ወቅዱ    አቡ    ጳውሎ    መመረ   የኢኃድግ   በትረ    መንግሥት  መጨበጥን   ተከትሎ   ወደ   ፕትርክና   የመጡት   ብፁዕ   ወቅዱስ   አቡነ   ጳውሎስን  
በወቅቱ   ካለው   የፖለቲካና   የዘር   ወላፈን   ጋር  በተያያዘ የስልጣን ዘመናቸው ከባድ ነበረ።  በእውቀታቸውና   በችሎታቸው   ብቃት    ምንም   የማያንሳቸው   አቡነ   ጳውሎስ   ዕድላቸው  ሆነና    ዘመናቸው   የመከራና   የሁከት   ዘመን   ሆኖ   አለፈ።  በዚህ ጥላቻ ምክንያት እርሳቸውም እልህ ስለገቡ በግዴለሽነት ዛሬ የምናያቸውን   የፍንዳታና   ወሮበላ  ጳጳሳትን   ያለ   ገደብ   አምርተውልን   አለፉ።  
ጵጵስናው   የነበረውን   ክብር   ያጣው፤  ደላላዎችና   የስም   ካህናት   ቤተ   ክርስቲያንዋን   የተረከቧት   በእርሳቸው   ዘመን   ነበር።  በገንዘብ   ጡንቻውን   አፈርጥሞ   ፓትርያርክን   ያህል   የሚያዋርድ፤   ጳጳሳትን   ለግል  አጀንዳው   የሚጠቀም   ማኅበረ  ቅዱሳንም   የተፈጠረውና   እግሩን   በቤተ    ክርስቲያን  ውስጥ   የተከለው   በቅዱስነታቸው   ዘመን   ነበር።   አቡነ   ጳውሎስ   ብዙ   የሠሩት   በጎ  ሥራዎች   እንዳሉ   ሆኖ   የመልካም   አስተዳደር   እጦት፤   የማዕረገ   ክህነት   ክብሩን  ማጣት፤   የደላሎችና   የሕገ   ወጥ    ሰዎች   በቤተ    ክርስቲያንዋ   መዋቅር   ውስጥ  መሰግሰግ  ምክንያት  ዘመናቸው  ተጠቃሽ  ነው።      
  
3.   የብፁ   ወቅዱ   አቡ   ማትያ   ዘመን  ቅዱስነታቸው  ፍፁም  መናኝ፤  ጸሎተኛ  አባት  መሆናቸው  ይታወቃል።  ከብሕትውናቸው  በተጨማሪ  ብዙ  ዘመን  በውጭ  ሀገር  የኖሩ፤  በዘመኑ  ተንኮልና፤  አሁን  በቤተ   ክህነት  አከባቢ  ባለው   ክፋትና  መሠሪይነት  ያልተካኑ    የዋኅ    አባት    ናቸው።    ዕድላቸው    ሆኖ    በምንም    ዓይነትና    መልክ  ከማይመስሏቸውና    ከማይግባቡአቸው    ሊቃነ     ጳጳሳት    መካከል    ገቡ።    ቀጥተኛና  እውነተኛ   አካሔድ   እንጂ   ዓለም   ፈሊጥ   የሚለው   የተንኮል   ችሎታ   የላቸውም።  ስለሆነም   በቋንቋም   ሊግባቡ   አይችሉም።   በዚህ   ሁኔታ   ባሕሪያቸው   ሳይዋሐድ  ክፍተቱ    እንዳለ    ቀጥተኛው    ፓትርያርክ    ሙስናንና    ሕገ    ወጥነትን    የመቃወም  አቋማቸውን   ግልጽ   አደረጉ።   ለአመኑበት   አቋም   ታማኝ   ስለሆኑ   በየመድረኮችና  በአገኙበት   አጋጣሚ   ሁሉ   ተጠቀሙ።   ,ሙስናና   ሕገ   ወጥነት.   ግን   ያለው   በሕዝቡ  መካከል  ሳይሆን  ከዋና  የቤተ  ክርስቲያን  መዋቅሮችና  ከማኅበሩ  ወደ   ታች   የሚፈስ  ጅረት   መሆኑ   የሚታወቅ   ነው።   በዚህ   ምክንያት   ሙስናንና   ሕገ   ወጥነትን   ተንተርሶ  ቤተ   ክርስቲያንን   የሚያምሰው   ማኅበረ   ቅዱሳን   አኮረፈ።   በሕገ   ወጥነት   ለአካበተው  ንብረትም   ሥጋት   ውስጥ   ገባ።   ፓትርያርኩ   በያዙት   አቋም   በሕገ   ቤተ   ክርስቲያን  ለመተዳደርም   አሻፈረኝ   አለ።   ፓትርያርኩም   ,ቤተ   ክርስቲያን   ከተያዘችበት   ቅኝ  ግዛት/ማኅበር   ነጻ   መውጣት   አለባት.   የሚለው   አቋማቸውን   ይፋ   አደረጉ።   ማኅበሩ  አንዳንድ   የዋኅ   አባቶችን   ለማወናበድ   ፓትርያርኩ   ማኅበሩን   ሊያፈርሱ   ነው   ብለው  ቢተነብይም   ቅዱስ   ፓትርያርኩ   ግን   በሕገ   ቤተ   ክርስቲያን   ሥር   ይተዳደሩ   ነው  ያሉት   እንጂ   ይፍረሱ   አላሉም   ነበር።   ይኽንኑ   ለማስፈጸም   ቅዱስ   ፓትርያርኩ  ባላቸው   ሥልጣን   ሲንቀሳቀሱ   ማኅበሩ   በጎን   ይቅርታ   እጠይቃለሁ   ብሎ   ጉዳዩን  ካረገበ   በኋላ   ፓትርያርኩ   በምንም   ስለማይደለሉ   ከሥልጣናቸው   ማውረድ   አማራጭ  የሌለው   መንገድ   መሆኑን   ወስኖ   ተነሳ።   ይኽንን   አጀንዳውንም   ለጳጳሳቱ   ከብዙ   እጅ  መንሻ   ጋራ   አሸከመ።   ቀድሞኑ   ከፓርያርኩ   ጋር   ያልተግባቡ   አዲስ   ተክል   ጳጳሳት  የማኅበሩን   አጀንዳ   ለማሳካት   ,እንደ   ራሴ.   መሾም   አለብን   ብለው   አጀንዳ   ቀረጹ።  ይኽም   ለሁለት   ዓላማ   ነበረ።   1)   ቢሳካላቸው   የፓርያርኩን   ሥልጣን   ለመሸርሸርና  ለመገደብ  ሲሆን   2)  ፓትርያርኩን  በዚህ  ለማጨናነቅና  ለፓትርያርኩ  የማይታዘዘውና  ሕገ  ቤተ  ክርስቲያንን  የሚጋፋው  ማኅበሩ  ስሙ   እንዳይነሳና  በአጀንዳነት  እንዳይያዝ  ለማድረግ   እንደሆነ   ታውቋል።   በመሆኑም   የመጀመሪያው   ባይሳካላቸውም   ሁለተኛው  ሀሳባቸው   ተሳክቶላቸዋል።   ማኅበሩ   ይኽንን   የማደባደብ   አጀንዳ   ለጳጳሳቱ   ከሰጠ  በኋላ   በሲኖዶስ   መክፈቻ   ዕለት   ዐውደ   ርዕዩን   ከፍቶ   በቤተ    ክርስቲያን   ስም   ንግዱን  ያጧጥፍ   ነበር።   በሥርዓትና   በሕግ    ቢሆን    ሁሉም   ባልከፋ   ነበር።   ነገር   ግን   እልህና  ግዴለሽነት  ሆነና   ቤተ  ክርስቲያን  ተጎዳች    
  
4.  
ጠቅላ/        አስኪያጅ  የቅዱ  ሲኖዶ    ፀሐ   ምርጫ  ከላይ   ለማተት   እንደተሞከረው እልህና ግዴለሽነት የተጠናወታቸው  የሲኖዶስ  አባላት  ለሁለቱ  ቦታዎች  ከሚጠቆሙት  መካከል  አቡነ  ዲዮስቆሮስንና  አቡነ  ሳዊሮስን   ዕጩ   ተጠቋሚ   አድርገው   አቀረቡ።   ቅዱስ   ፓትርያርኩ   የሁለቱንም  ዕውቀትና   ሥነ   ምግባር   አልባ   ሕይወታቸውን   ስለሚያውቁ   ይልቁንም   እነዚህ   ሁለቱ  በየጊዜው   ጉባኤውን   የሚያውኩ   መሆናቸው   ግልጽ   ስለሆነ   ተቃወሙአቸው።   ይሁን  እንጂ   አባላቱም   ተቃውሞውን   አልተቀበሉም።   ምክንያቱም   የእልህና   የግዴለሽነት  ጉዳይ    ስለሆነ።    እነዚህ    ሁለቱ    አባቶች    ጵጵስና    ሲሾሙ    የሲኖዶስ    አባላት  ተቃውሞአቸው   እንደነበረ   ይታወቃል።   በተለይም   ከሽማግሌዎቹ   አቡነ   ቀውስጦስና  አቡነ   ቄርሎስ   ,እነዚህን   ጳጳሳት   ከምናደርጋቸው   በሲኖዶሱ   ገንዘብ   ብንድራቸው.  ብለው   በመናገራቸው   የሚጠቀሱ   ናቸው።   አሁን   እንዴት   ዝም   አሉ?    ከእነዚህ  የተሻሉ   ምራቅ   የዋጡ፤   የተማሩ   አባቶች   የሉም   ማለት   ነው?   ወይንስ   ቤተ  ክርስቲያንዋ   አንደኛዋን   እንድትጠፋ   ተወሰነባት?   ዓለም   አቀፍ   የሆነችው   ቤተ  ክርስቲያን    ወደ    አንድ    ጎጥ    ሥር    ተካተተች?    የሲኖዶሱ    አባላት    በተለይም  ሽማግሌዎቹ   ይኽ   ሁሉ   ጠፍቶአቸው   ሳይሆን   ከፓትርያርኩ   ጋር   እልህ   ስለ   ተጋ  ነው።  በእልሁ  ምክንያትም  ለነገዋ  ቤተ  ክርስቲያን  በግዴለሽነት  ሳያስቡ  ቀሩ።    
  
,እልህ   መርፌ   ያስውጣል.   የሚባለው   ይኽው   ነው።   በእርግጥ   በቤተ    ክርስቲያንዋ  ውስጥ   የሰፈነውን   እልህና   ግዴለሽነትን   ለመግለጽ   ነው   እንጂ   የእግዚአብሔር   እጅ   ምን   ላይ  እንደ   ሆነች   አናውቅም።   ቅዱሱ   ጉባኤ   በአድማና   በግል   ጥቅም   ስለታወከ   እግዚአብሔር  ስላልከበረበት   አሳልፎ   መስጠቱ   ሊሆን    ይችላል።   አዋቂ   እርሱ   ብቻ   ነው።   ወይም   የተናቁትን  አስቀምጦ   ሊሰራባቸውም   ፈልጎም   ሊሆን    ይችላል።   የእኛም   ጸሎታችን   እውቀትና   መልካም  ሕይወት   የሌላቸውን   ሰዎች   እግዚአብሔር   እንዲጠቀምባቸውና   ከቅዱስ   ፓትርያርኩም   ጋር   ሆነ  ከሲኖዶሱ   አባላት   ሁሉ   ጋር   ተስማምተው   ቤተ   ክርስቲያንዋን   እንዲመሩ   ነው።   እልህና  ግዴለሽነት  ጊዜያዊ  ሥሜት  ስለሆነ  ለማንም  አይጠቅምም።  ከሁሉም  በላይ  በከበረው  በክርስቶስ  ደም  የቆመችውን  ቤተ  ክርስቲያን  እንድናስብላት  ቸሩ  መድኃኔ  ዓለም  ይርዳን  አሜን።  
    
  
  
 

23 comments:

 1. የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ እንደሚባለው ሁሉ በተለይ በዚህ ድረ ገጽ አንድም ቁም ነገር ሲነበብ ተምልክቼ አላውቅም። ለነገሩ እናንተም ለቆማችሁበት እኩይ ዓላማ ስለሆነ የምትታገሉት ምንም አዲስ ነገር የለውም። ምንም አላችሁ ምንም እንዲሁ ባዶ እየሆናችሁ ትቀራላችሁ። ማኅበሩም በቅድስት ድንግል ማርያም ተራዳኢነት የየጊዜውን ፈተና ይወጣውል። ለእንናተ እውነትን በሃሰት ጠቅላላችሁ ለምታቀርቡት ግን ጊዜው መሽቶአልና ወደ ኅሊናችሁ ተመለሱ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የመሸብህ አንተ ነህ የጨለማ ልጅ!! እውነት ምን እንደሆነ ስለማታውቅና ስለተጋረደብህ ማህበርህ ያስነገበህን አፈ ታሪክ እንደሜዳ አህያ ታናፋለህ። እውነት ክርስቶስ ነው ካመንበከት ክርስቲያን ትባለለህ እሱን ትመስላለህ፤ የማህበርህን ሰይጣን ካመንክ ደግሞ ወደ ጥልቅ ጭለማህ ትወርዳታለህ እንጂ የእውነት ብርሃን በአንተ አካባቢ ሊታወቅም ሊደርስም አይችልም። ስለህሊና የሚናገር በብርሃን የሚመላለስ የክርስቶስ ተከታይ የሆነ ህሊና ያለው ሰው ነው። አንተ የማህበረ ሰይጣን አባል ስትሆን ህሊና ከየት አመጣህ? ኢየሱስ ክርስቶስ ይገስጽህ!!

   Delete
  2. የመሸብህ አንተ ነህ የጨለማ ልጅ!! እውነት ምን እንደሆነ ስለማታውቅና ስለተጋረደብህ ማህበርህ ያስነገበህን አፈ ታሪክ እንደሜዳ አህያ ታናፋለህ። እውነት ክርስቶስ ነው ካመንበከት ክርስቲያን ትባለለህ እሱን ትመስላለህ፤ የማህበርህን ሰይጣን ካመንክ ደግሞ ወደ ጥልቅ ጭለማህ ትወርዳታለህ እንጂ የእውነት ብርሃን በአንተ አካባቢ ሊታወቅም ሊደርስም አይችልም። ስለህሊና የሚናገር በብርሃን የሚመላለስ የክርስቶስ ተከታይ የሆነ ህሊና ያለው ሰው ነው። አንተ የማህበረ ሰይጣን አባል ስትሆን ህሊና ከየት አመጣህ? ኢየሱስ ክርስቶስ ይገስጽህ!!

   Delete

  3. ክርስቲያን የሚመስለው ክርስቶስ ነው ለዚህ ነው በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልነው አባታችን ክርስቶስ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሏልና ይቅር ይበልህ ወንድሜ አንተ አሁን እውነት በክርስቶስ ነህ አንተ በብርሃን ውስጥ ነህ በግብር ዳቢሎስን እየመሰሉ የክርስቶስ ነኝ አይሰራም እምነት ያለምግባር ከንቱ ነው ይላል ወንጌሉ ሁልጊዜም ቤተክርስቲያን ስለእናነተ ትጸልያለች ሲጀመር ክርስቶስ ሰፈውስ እንኳን ፍቃድ የጠይቃል ልትድን ትወዳለህን ብሎ እናንተ ግን በማያገባችሁ ገብታችሁ እንደዓለሙ ስትራቴጂክ ዕቅድ ነድፋችሁ እና ካለ እምነታችሁ መጥታችሁ በግድ መቀየር አለብን ካለበላዛ እንዳንተ ስድብ ይህ ደግሞ የዓለም አካሄድ ነውና በጨለማ ያለህ ያልክ ወንድም ወደራስህ ተመለስ እውነቱን መርምር፡፡ ወንድሜ ልቦና ይስጥህ፡፡

   Delete
  4. @ AnonymousJune 8, 2016 at 5:19 PM
   አንተ ከመገሰጽ ሳትወጣ ሰው ልትገስጽ ያምርሃል ኧረ እፈር ተራ መናፍቅ
   እግዚያብሄር ይቅር ይበልህ!!

   Delete
 2. Replies
  1. betam yasazinal . e/r libona ysitachew .min madreg enichilalen ?

   Delete
 3. It is rather a rubbish munchirchir! menafikan irir belu teqatelu keabatachihu diyabilosina aganint gara.Ineho papasat beand hasab komu.Ahunim tsinatun yistilin lebetekirstiyan yemibejewun yadrigulin

  ReplyDelete
 4. wedaje ye Abeselom zemen eko new zim bilo mayet new

  ReplyDelete
 5. tikikil nachihu ,min enadrgachew gin ?

  ReplyDelete
 6. በጣም ይገርማል ከ42 ሊቃነ ጳጳሳት አንድ ሊቀ ጳጳስ(ፓትርያርክ) ማስበለጣችሁ፣ ለቤተክርስቲያን ሣይሆን ለግለሰብ የምታዳሉ ፤ ስለዚህ እናንተ መናፋቃን ናችሁ ማት ነው

  ReplyDelete
 7. አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ ደካማ ባላችኋቸው ሰዎች ላይ አድሮ እንደሚሰራ ማመን አቃታችሁ? እንዲህም ወንጌል አዋቂ! ዝርክክር ጴንጤ ሁሉ! ተነቃብሽ፡፡ የዲያብሎስ ዝናሩ እያለቀ እንደሆነ ጽሑፋችሁ ማሳያ ነው፡፡ ዙሪያ ጥምጥም አትዙሩ! ጊዜው ቢረፍድም፤ተመለሱ! በክርስትና ካፈርኩ አይመልሰኝ... አይሠራምምምምምምምምምምመ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ድሮውኑ መች ደረስክና! ክርስትና እኮ ለክርስቶስ ተከታዮች የተሰጠ ሃይማኖት ነው። አንተ እንዴት አድርገህ ነው ስለማታውቀው እምነት የምታፍረው። አውቀኸው ካፈርክማ እሱም እዛ ስትደርስ ያፍርብሃል አድርሻህም ተለውጦ ወደ ዘመዶችህ ወደ አጋንንት መንደር ጥርስ ማፋጨትና ጥልቅ ጭለማ ትወርዳለህ ማለት ነው። ድንገት ቢዘልቅህና ከአይንህ ቅርፊት ቢወድቅልህ አንብብና ተረዳ!! እግዚአብሔር ከጭለማ ያውጣህ!!

   Delete
 8. it is greats true spiritual website. we proud of brothers for you guys doing wonderful task. today, we are not hearing and seeing truth or regarding loves each others from our orthodox church leaders.Everyday hate, accusing one another, fault finders, and makes enemy. When do we humble one another instead of selfishness and hypocrites.If we don't have any broken heart for word of Lord God and commandment, there is a problems in our faith. When do we stand together as children of God ?

  ReplyDelete
 9. አይይይ… አዛኝ ቅቤ አንጓች! ከ ወር በፊት መንሳዊ አባት አይሰደብም ብላችሁ ስትሟገቱ ነበር፡፡ ወዲያው ረሳችሁትና አባቶችን እንዴት ባሉ ቃላት መስደብ ጀመራችሁ፡፡ አሁን ስለ እናንተ ማንነት ሌላ ሰው እንዲመሰክርልን አያስፈልገንም፡፡ የራሳችሁ አቋም፣ ጽሑፋችሁና አንደበታችሁ ይመሰክርባችኋል፡፡ ለመሆኑ የተወገዘ ማህበር ስለ አወገዘችው ቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ መሆን ይችላል አዛኝ ቅቤ አንጓች! እባካችሁ ከቻላችሁ ንስሐ ግቡና ተመለሱ፣ ካልቻላችሁ የራሳችሁን እምነት አራምዱ እንጂ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አትግቡ፡፡ እኛ ግን ልቦና እንዲሰጣችሁ ዘወትር እንጸልያለን፡፡

  ReplyDelete
 10. እዉነት በዘመናችን ጠፎቶ ያለው በእኛ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዘንድ ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው ህይወቱ በወንጌል ላይ ካልታነጸና ካልተገነባ ውስጡ ሁል ግዜ ባዶ ነው። ብዙዎች በልብስ ብቻ ተሸፍነው ነው የምኖሩት። በእግዚአብሔር ፊት ባዶ ስሆን በሰው ዘንድ ግን ክብር ነው። ሰው ልብሱንና ፊቱ ብቻ ነው የምመለከተው። እግዚአብሄር ግን ጥልቁን የውስጥ ህዋሳታችንን ይመለከታል። የሰው ልጅ ህይወቱ በወንጌል ካልታነፀ ዘወትር የሰይጣን ሥራ ብቻ ነው የሚሰራው። ጥላቻ ፤ መለያየት ፤አድማ ፤ ተንኮል፤ ክፋት፤ ምቀኝነት፤ ያለ መፋቀር፤ አለመከባበር፤ ነዋይ ናፋቅነት፤ ስልጣን ወዳድነት፤ምስጢራትን አለመቋጠር፤ ትምክት፤ ትግስት አልባነት የመሳሰሉት ማደረግ ይቀናቸዋል። ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ጋር የማይሰማማና ደስ የማያሰኝ ስራዎችን መሰራት ይወዳሉ። ስለዚህም ነው ከእምነት ይልቅ ወግን በቻ ማጥበል የምሹት።

  ReplyDelete
 11. መሪ ጌታ በዚህ መጣጥፍ ያስነበቡት ብዙ እውነትነት አለው። እስተዛሬ ለምን ቆዩ ለሚለው ጥያቄ ብዙ መልስ እንዳለዎት ይገመታል። የጥንቶቹን ደጋግና እውነትን ተመርኩዘው የክርስቶስን ወንጌል የሰበኩትን ያስተማሩትን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ህይወታቸውን እስከመስጠት የቆሙትን አባቶች እንደው ለማነጻጸሪያ እንኳ አለማቅረብዎ ብዙዎቻችንን አስገርሞናል። የሚያስደንቀው ደግሞ ምን ያህል እርስዎ እንዳጤኑት ባናውቅም የዳያስፖራው ሲኖዶስ ደግሞ በመሃል አገር የተደረገውን ስህተት በአሁኑ ወቅት በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለመድገም በመሯሯጥ ላይ ይገኛል። ከዘገቡት አንዳንድ ነጥቦች ብንጠቅስ፤

  “በዚህ ጥላቻ ምክንያት እርሳቸውም (አቡነ ጳውሎስ)እልህ ስለገቡ በግዴለሽነት ዛሬ የምናያቸውን የፍንዳታና ወሮበላ ጳጳሳትን ያለ ገደብ አምርተውልን አለፉ።
  ጵጵስናው የነበረውን ክብር ያጣው፤ ደላላዎችና የስም ካህናት ቤተክርስቲያንዋን የተረከቧት በእርሳቸው ዘመን ነበር። በገንዘብ ጡንቻውን አፈርጥሞ ፓትርያርክን ያህል የሚያዋርድ፤ ጳጳሳትን ለግል አጀንዳው የሚጠቀም ማኅበረ ቅዱሳንም የተፈጠረውና እግሩን በቤተክርስቲያንዋ ውስጥ የተከለው በቅዱስነታቸው ዘመን ነበር። አቡነ ጳውሎስ ብዙ የሠሩት በጎ ሥራዎችእንዳሉ ሆኖ የመልካም አስተዳደር እጦት፤ የማዕረገ ክህነት ክብሩን ማጣት፤የደላሎችና የሕገ ወጥ ሰዎች በቤተ ክርስቲያንዋ መዋቅር ውስጥ መሰግሰግ ምክንያትዘመናቸው ተጠቃሽ ነው።”

  እርስዎ ያሉት ሁሉ እንደተጠበቀ ሆኖ በዳያስፖራው ደግሞ የማህበረ ቅዱሳን ሳያንስ፤ የወያኔው ጎራ ቀሚስ ለብሰው ካህንና ጳጳስ ነን የሚሉት ናቸው ፓትርያርኩን እያዋረዱ ያሉት፤ አልፈው ተርፈውም ደጋፊዎቻቸውን ጵጵስና ሊያሾሙ በሩጫ ላይ ይገኛሉ። መሪ ጌታ! ታዲያ ይኸ ከእርስዎ ጽሁፍ ጋር ተመመሳሳይነት የለውም ብለው? ወይስ??

  “በተለይም ከሽማግሌዎቹ አቡነ ቀውስጦስና አቡነ ቄርሎስ እነዚህን ጳጳሳት ከምናደርጋቸው በሲኖዶሱ ገንዘብ ብንድራቸው. ብለው በመናገራቸው የሚጠቀሱ ናቸው።? ከእነዚህ የተሻሉ ምራቅ የዋጡ፤ የተማሩ አባቶች የሉም ማለት ነው? ወይንስ ቤተ ክርስቲያንዋ አንደኛዋን እንድትጠፋ ተወሰነባት? ዓለም አቀፍ የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ወደ አንድ ጎጥ ሥር ተካተተችን?”

  አይገርምዎትም! ጎጥ ደህና! ወደ አንድ ቀዬ ቢሉ “ፋርጣ” ቢሉ አይሻልም ነርዋል!! ያ ሁሉ ንጹህ ደም አላጋባብ ሲፈስ ዝም ያለች ቤተክርስቲያን ዛሬ ያለችበት ሁኔታ ለምን ያስደንቃል ያሳዝናልስ? እግዚአብሔር በምህረቱ ይግብኘን።

  ታዲያ እኮ ርእስዎን “እልህና ግድየለሽነት” አሉት እንጂ በገላትያ 5:19-21 (19 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ 20 መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ 21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።) ከነዚህ ከተዘረዘሩት መምረጥ ይችሉ ነበር!

  አባቶቻችን የተሰጣቸው ግዴታና ሃላፊነት በገላትያ 5:22-23 እንደተጠቀሰው በመንፈስ እንዲመሩ ሆኖ ሳለ (22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። 23 እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። 24 የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። 25 በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። 26 እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።) እነርሱ ጠፍተው እኛን ደግሞ ጨምረው በማጥፋታቸው ዋጋቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጠብቃቸዋል። ግማሾቹም በዚሁ በምድር እየከፈሉ እያየን ነው።

  ReplyDelete
 12. ምነው ተበሳጨህ አዎ አሁንም እደግመዋለሁ ምንም የረባ ነገር አይነበብበትም። ይህ ማንም የሚያውቀው ነው። ለጥቅም በጨልማ ውስጥ የምትኖር አንተ ነህ። ማን እንደሆንክ አጻጻፍህ ይለያልና አሁንም ጊዜው መሽቶአል ወደ ኅሊናህ ተመለስ። ስለማኅበሩ መልካም መናገር አባል መሆን አያስፈልገውም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታይ መሆን እንጂ። ስለሆነም እደግመዋለሁ " የሌብ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ" ከዚህ የተሻለ ምሳሌ አይኖርም።

  ReplyDelete
 13. የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ እንደሚባለው ሁሉ በተለይ በዚህ ድረ ገጽ አንድም ቁም ነገር ሲነበብ ተምልክቼ አላውቅም። ለነገሩ እናንተም ለቆማችሁበት እኩይ ዓላማ ስለሆነ የምትታገሉት ምንም አዲስ ነገር የለውም። ምንም አላችሁ ምንም እንዲሁ ባዶ እየሆናችሁ ትቀራላችሁ። ማኅበሩም በቅድስት ድንግል ማርያም ተራዳኢነት የየጊዜውን ፈተና ይወጣውል። ለእንናተ እውነትን በሃሰት ጠቅላላችሁ ለምታቀርቡት ግን ጊዜው መሽቶአልና ወደ ኅሊናችሁ ተመለሱ።

  ReplyDelete
 14. አባ ሰላማዎች ዘገባዎቻችሁ እጅግ በመረጃ ላይ የተመሠረቱ እና እውነት ናቸው፡፡ የአንዳንድ ‹ጳሳቶች እብደት እኔንም ያሳስበኛል፡፡ በተለይም ለማቅ ጥሩ ፈረስ በመሆን ቤተክርስቲያናችንን ወደ ገደል እየመሯት ነው፡፡ እነርሱ ገደል ይግቡ እንጂ ቤተክርስቲያናችን ፀንታ ትኖራለች፡፡ ማህበሩ የዝንጀሮ ስብስብ ሆኖ ከራይ በመሰብሰብ አስቸገረን፡፡ እግዚኦ ፈጣሪ ሆይ አስበን!!!

  ReplyDelete
 15. ለአንተ ዓይነቱ ጥቅመኛና ፀረ ቤተክርስቲያን አሉባልታው ያለ ምንም ምክንያት ስም ማጥፋቱ ነው መረጃ የምትለው። አሁን ያንተ መሰሉ ካልሆነ ማንም የሚሰማችሁ እንደሌለ አንተም በሚገባ ታውቀዋለህና ይህ ለአንተ የሚነገር አይደለም። እውነት እየትገለጠች ስለሆነ የሚሆነውን ወደ ፈት ይታያል። ርኩስ መንፈስ ለጊዜው ይገናል በእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ተረዳኢነት ተኖ ይጠፋል። አሁንም ጊዜው መሽቶል ወደ ህሊናህ ተመለስ። ማኅበሩ በበጎ ሥራው እየታየ ነው አንተ ግን እንዲሁ ወሬ እንዳወራህ ከዚህ ዓለም ታልፋለህ ሌላ እድል የለህም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የማህበረ ቅዱሳን ቡችላ በራስህ ህሊና ለማሰብ ሞክር ያኔ ከእንቅልፍህ ትነቃ ይሆናል፡፡

   Delete