Wednesday, June 8, 2016

በርካታ ሀገረ ስብከቶች ያለጳጳስ እየተመሩ ተጨማሪ ጳጳሳትን ለመሾም ሲኖዶሱ እስካሁን የዘገየው ለምንድነው?ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ሆነው ከተሾሙ ሦስት ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡ እስካሁን ግን አንድም ጳጳስ አልሾሙም፡፡ አንድ ፓትርያርክ በዘመነ ሲመቱ ሊያደርጋቸው ከሚገቡ ተግባራት መካከል አንዱ ጳጳሳት መሾም ነው፡፡ ይህም ለመሾም ያህል ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ስለሚገኝ ነው፡፡ ይልቁንም በአሁኑ ጊዜ ካሉት ሀገረ ስብከቶች ሲሶው ያህል ያለ ሊቀ ጳጳስ ነው ያለው፡፡ ክፍተቱንም ለመሙላት በሚል አንዳንድ ጳጳሳት እስከ 4 የሚደርሱ ሀገረ ስብከቶችን ደርበው እንዲሰሩ እየተደረገ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ስሙ በሀገረ ስብከቱ የሚጠራ ጳጳስ ከመሰየምና በተሾመባቸው ሀገረ ስብከቶች ለምሳሌ 4 ሀገረ ስብከት የሚያስተዳድር ጳጳስ ከ4ቱ ቦታዎች ደመወዝተኛ ይሆናል ደሞዙን ከማሳደግ ውጪ የተፈጠረውን የአገልግሎት ክፍተት የሚሸፍን መፍትሔ አይደለም፡፡ ለምሳሌ  የጅማ የኢሉ አባቦራ እና ጋምቤላ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት አባ እስጢፋኖስ ደቡብ ሱዳንን ደርበው እንዲያስተዳድሩ ተደርጓል፡፡ ምንጊዜ ሊያዳርሷቸው ነው? በተለይም ጋምቤላ ከሙቀቱ የተነሳ አንድም ቀን ማደር የሚፈልግ ጳጳስ የለም፡፡ ነገር ግን ሙቀቱን ተቋቁመው 3 የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት ወደ 53 ያደረሱ፣ (ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ገዳማት ናቸው) በደቡብ ሱዳን 6 አብያተ ክርስቲያናትን የተከሉ፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማጥመቅ የቤተክርስቲያን አባል ያደረጉ፣ በርካታ ልማታዊ ስራዎችን የሰሩ በሀገረ ስብከቱ እያሉ ደመወዙን አባ እስጢፋኖስ እንዲበሉት መደረጉ ፍትሐዊ አይደለም፡፡ ይህ ሳያንስ አሁን ደግሞ ደቡብ ሱዳንን ደርቦ መስጠት ይበልጥ ኢፍትሐዊ ነው፡፡  

የአሶሳ፣ የምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከቶች ጳጳስ የሆኑት አባ ሄኖክ ደግሞ የአውስትራሊያ ጳጳስ ሆነው ተመድበዋል፡፡ ለአባ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ጸሀፊነቱ ተሀድሶን በሀገረ ስብከታቸው ተዋግተዋል ተብሎ ስለ ታመነበት የተሰጣቸው ማበረታቻ እንደሆነ ሁሉ ለአባ ሄኖክም አውስትራሊያ ተደርቦ የተሰጣቸው በተመሳሳይ ተሐድሶን ተዋግቻለሁ ስላሉ ነው፡፡ ነገር ግን አባ ሄኖክ በሀገር ውስጥ ሶስት ሀገረ ስብከቶችን እንደገና አውስትራሊያን ማስተዳደር የሚችሉት እንዴት ነው? ከላይ ለማለት እንደሞከርነው ስማቸው እንዲጠራበትና ተቀምጠው ደሞዝ እንዲበሉ ካልሆነ በቀር ለቤተክርስቲያኒቱ በጳጳሳት በኩል ላለው ክፍተት መፍትሔ የለውም፡፡ እንደሚታወቀው አብዛኞቹ ጳጳሳት ብዙ ጊዜያቸውን በሀገረ ስብከታቸው ሳይሆን በሰበብ በአስባቡ በአዲስ አበባ ነው የሚያሳልፉት በዚህ ሁኔታ ላይ ሌላ ሀገረ ስብከት መደረብ የእነርሱን ጥቅም ከማሳደግ በስተቀር ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም ውሳኔ አይደለም፡፡

ተጨማሪ ጳጳሳትን ለመሾም አጀንዳው ፓትርያርኩ ከተሾሙ ጊዜ ጀምሮ ሲነሣ ቢቆይም እስካሁን ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ይህን የሚስኑት ጳጳሳት ስለሆኑና ደርቦ መያዙ ለእነርሱ እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ስለሆነላቸው ይህ እንዲቀር ባለመፈለግ ነው፡፡ ዋናው ምክንያት ግን ማኅበረ ቅዱሳን የማይፈልጋቸውና ማኅበሩን ሥርዓት ለማስያዝ ቆርጠው የተንቀሳቀሱና የማኅበሩን እኩይ ሥራ በመግለጥ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከማኅበሩ ቅኝ ግዛት ነጻ ለማውጣት የተንቀሳቀሱ፣ በዕውቀታቸውም በሕይወታቸውም በአመራራቸውም ለቤተ ክርስቲያን ልማትና እድገት ተጨባጭ ሥራ በመስራት የተመሰከረላቸውን አባቶች ማኅበሩ ቢካተቱ ለእኔ አይታዘዙም ብሎ ስለሰጋ ነው፡፡ አንዳንድ ጳጳሳትም ከግል ጥቅም አንጻር እነዚሁ አባቶች በምንኩስናቸው እንዲህ ያደረጉ ጳጳሳት ሆነው ቢመረጡ አንችላቸውም በሚል ፍርሃት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዕውቀታቸውም ሆነ ሕይወታቸው፣ ለቤተክርስቲያን ያበረከቱት አስተዋፅኦ ወደር የማይገኝለት ስለሆነ እነዚህ አባቶች በጥላቻና የአንድን ማኅበር ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር ካልሆነ በስተቀር የአሁኑ ሹመት እነርሱን ሳያካትት ሊያልፍ የሚችልበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡

ይህ ያሰጋው ማኅበረ ቅዱሳን ጉዳዩን ከሃይማኖት ጋር ለማያያዝ እየሞከረ መሆኑን በልሳኑ በሐራ በኩል እየተናገረ ነው፡፡ ሰዎችን የሚከስበት ነገር ሲያጣ ከዚህ ቀደም የሚጠቀምበት ስልቱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህም ለህልውና ሥጋት መስለው የታዩት አባቶች ወደ ጵጵስና እንዳይመጡ ለማድረግ የከፈተው ዘመቻ አካል ነው፡፡ ይህ የእርሱ ዘመቻ ለእኛም ስጋት ናቸው በሚል እነዚህን ለጵጵስና ይታጫሉ ተብለው የታሰቡትን አባቶች ከሚፈሯቸው አንዳንድ ጳጳሳት በኩል ድጋፍ ስላለው ሴራው ጠንክሮ እስካሁን ተጨማሪ ጳጳሳት ሳይሾሙ ለመዘግየቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡ ይህ ግን ጥቂቶችን ጠቅ ብዙዎችን ይልቁንም ቤተ ክርስቲያንን የጎዳ ተግባር ነው፡፡  
  
ከዚህ በፊት በአቡነ ጳውሎስ ዘመን የተሾሙ 17 ጳጳሳትን ከሁለት ክፍሎ 2 ለ 15 በማድረግ ዜና ቤተክርስቲያን “መንፈስ ቅዱስ የሾማቸው” እና “ሲኖዶስ የሾማቸው” በማለት ጳጳሳቱን የመደባቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ አሁንም እየሆነ ያለው የአስተዋይ አባቶች ምክርና ተጽዕኖ ካላረፈበት ሙሉ በሙሉ ሲኖዶሱ የሾማቸው ብቻ እንዳይሆኑ ያሰጋል፡፡ ውጤቱም ቤተክርስቲያኒቱን በዚህ አቅጣጫ ከአሁን በባሰ ወደጥፋት የሚወስዳት ነው የሚሆነውና አስተዋይ የሆኑ ብፁዓን አባቶች ሊያስቡበት ይገባል፡፡ 
ይህ ጉዳይ እስካሁን ዘግይቶም ቢሆን በአሁኑ ሲኖዶስ ስብሰባ ውሳኔ አግኝቶ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲሰየምና እስከ ሰኔ 30/2008 ዓ/ም ድረስ የእጩዎች ዝርዝር እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡ ኮሚቴው ለማንም ጥቅም ሳይሆን ወይም አንድን ወገን አስደስቶ ሌላውን ለማሳዘን በሚል ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የሚሰጡ አባቶችን ያለማንም እጅ ጥምዘዛና ማባበል በነጻነትና በእግዚአብሔር ፊት በመሆን ሊያጩ ይገባል እንላለን፡፡ ሁሉም ሰው “ሲኖዶስ የሾማቸው“ ሳይሆን “መንፈስ  ቅዱስ የሾማቸው” ማለት እንዲችል ሁሉ ነገር በጥንቃቄ እንዲሆን ሁሉም ተስፋ ያደርጋል፡፡      
    
    

15 comments:

 1. የምትገርሙ ጉዶች!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 2. በአንድ ነገር ታስደሰቱኛላችሁ የላካችሁን አላማውን ለማስፈጸም እንቅልፍ የላችሁም ለዚህም ነው የላካችሁ ስራውን ጨርሶ አርፉአል እናንተ ግን ከተሰጣችሁ በላ አብዝታቸሁ ለመስራት የምትጥሩት ምን ያደርጋል ያዘዛችሁ ከመንፈስቅዱስ ሳይሆን ከዲያቢሎስ መሆኑን ለማወቅ ምምም አይነት መረጃ ማገላበጥ አየስፈልግም ጽሁፎቹን ማንበብ በቂ ነው፡፡ የሰውልጅን ለማቀራረብ ሳየሆን ለማራቅ ???? እንደምትሰሩ ከህሊናችሁ መጣላታችሁ ለዚህ ማስረጃ ነው ግን አስከ መቼ ከሕግዚአብሔር ጋር ተዋግቶ ይቻላል ሳይመሽ ማሰቡ የተሸለ ነውና ብታስቡበት የላካችሁን ብታውቁት ይገርመኛል ከተጫናችሁት በላይ እየዋሻችሁ ሕዝብን ለማናቆር ህሊና ይስጣቸሁ ብቻ ከጽሁፉ አንድ ነገር ልበል ሲነዶስ የሾማቸው ሳይሆን መንፈስቅዱስ የሾማችው ማለት እንደቻል ምን ማለት ነው በመንፈስቅዱስ ተመርተው የሚያደረጉት ጉባኤ ለማቃለል እና ኦርቶዶክሳውያን መንፈስ ቅዱስ የላቸውም ለማለት ሳታውቁት የምትጽፉት ሓሰት እውነቱን እንድናውቅ እንዳደረግን ብትረዱ ስልታችሁን ትቀይሩ ነበር ግን በጫት የደነዘዘ አምሮ በካቲካለ የናወዘ ናላ ይዛችሁ መቼ??? ትውለዱንን እንደናንተው ለማድረግ እንደምትሰሩ በደንብ እናውቃለን ልብይስጣችሁ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. የራስህን መልክ ነው አይደል የሳልከው። ጅል

   Delete
  2. አይ እናንተ ሰዎች፤ ሌባ እናት ልጇ አታመነውም ይባላል እናንተ እዚህ ብሎግ ላይ እንኳን ስትጽፉ ስለምታገኟት የሳንቲም ሽርፍራፊ እንጂ ስለሃይማኖት ግድ ስለሌላችሁ ሁሉም የሚንቀሳቀሰው ለገቢው ነው ብላችሁ ነው የምታስቡት መድኃኒዓለም ልቦና ይስጣችሁ ነገር ግን በናንተ መፈተን አዲስ አይደለም የገሃነም ደጆች አይችሏትምና የትም አትደርሱም የሴጣን ዝናሩ ያልቃል እንጂ ቤተክርስቲያን ምንም አትሆንም፡፡ ስለመንፈስ ቅዱስ ለማውራት ምን ሞራል አላችሁ ምነው ቤትህ ስላለው መንፈስ ቅዱስ ወርዶብናል ብለው በልሳን እየተናገሩ እለት እለት በዝሙት ስለሚወድቁት ፓስተሮችህ ብታወራ እኮ አንተ እውነተኛ ነበርክ እውነት ስለወንጌል መሰበክ ስለጌታ የሚገድህ ቢሆን የመድኃኒዓለም ስም የማይታወቅበትና የማይጠራበት/ነብይ የሚባልበት/ ለመስራት ትመክሩ ነበር ግን የሴጣን አላማ ይህ አይደለም አንድ እና አንድ እንደሁሌም እቺን ንጽሕት የሆነች ቤተክርስቲያንን እውነተኛ መንገድን ሃይማኖት የሚመስል ግን ያልሆነውን በሪፎርም እየተሻሻለ ለዓለም በሚመች የተመቻቸውን እና በአፍ ጌታ ጌታ በሚባልበትና በቃ በፀጋው ድነናል እየተባለ ኃጢያት እንኳን ምእመኑ እንዲለማመዱ የሚደረግባት ከተፈለገ ጳጳስ መሆንን አይደለም አንዱ ተነስቶ እኔ ሐዋርያ ነኝ ነቢይ ነኝ እያለ የሚፈነጭባት እምነት ለማስፋፋት ነው ይህቺ ቤተክርስቲያ እነ ፓስተር እከሌ የሚመሰርቷት ሳይፈልጉ የሚያፈርሷት ድርጅት አይደለችም በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ናት መጀመሪያዋ በክርስቶስ ደም እንደሆ ፍጻሜዋም እንደዛ ነው እባክህ የዚህ ብሎግ ጸሐፊ አስብ ሌላ ሥራ ሥራ ተማር ከዚህ ቆሻሻ ሥራ ውጣ ወንድሜ በነፍስ መቃጠል ምንም አይበጅም እባክህ ንቃ፡፡

   Delete
  3. የእናንተ እና የተሃድሶ ግበአተ ምሬት እንዲፈጸም ለማድረግ ሲባል ነዋ! አታውቅም እንዴ አባ ሰለሜ(አባ ሰላማ ማለት ስለማልችል ነው)፡፡ እናንተ ምን አለባችሁ ዘንጡ ለኢየሱስ(ዘንጥ ለኢየሱስ የሚል ኃይማኖት አለ አይደል!) ምድረ ግሪሳ አለ ዘመድኩን አባቶችም ነቅተውባችኃል፡፡ እግዚአብሔር ይስጣቸሁ ጠላት ያበረታል እንጂ አያሰንፍም አጥራችንን ለማጥበቅ ምክንያት ሆናችሁን፡፡ ወይ ፍንክች ቤሳቤስቲን የለም አሁንም ተሃድሶ የሆነ ጳጳስ አይሾምም( አረ የምን መሾም አይታሰብም) ምክንያቱም ‹‹ትጉህ ዘኢይነውም/የማያንቀላፋ ጠባቂያችን›› እግዚአብሔር ስላለ( ውይ ተሳስቻለሁ ለካ የእናንተ አምላክ የሚያንቀላፋ ነው)***

   Delete
  4. "በአንድ ነገር ታስደስቱኛላችሁ" "በጫት የደነዘዘ አምሮ በካቲካለ የናወዘ ናላ ይዛችሁ መቼ" እንዲህ ያለ ጥበብ የተሞላበት እውቀት እንዴት አድርጎ ነው የዘለቀህ? የዲያብሎስ ልጅነትህ ከጽሁፍህ ቁልጭ ብላ አይኗን አፍጣ ትነበባለች። ክህደት የአባትህ ስለሆን እሱን ብትክደው ምን ገዶት እግዚአብሔርንና ልጆቹን እስካንጓጠጥክለት! የዘረዘርከው በሙሉ በህልምህም በውንህም የምታደርገው ስለሆነ ምን ያስደንቃል። ሰይጣን ዝም በልና ውጣ ነው የተባለው፤ አንተስ አባትህን ተከትለህ ወደ ሲኦል ጉብኝት ብትወርድ ምን ይመልሃል? ጥያቄው የቀረበልህ ስጋ ለባሽ ስለሆንክ እንጂ እንዳባትህ ርኩስ መንፈስ ብትሆን ኖሮ ውጣ እንጂ ጥያቄ ድርድር ማን ባደረሰህ? ህሊና እንኳን የለህም እግዚአብሔር አእምሮ ይስጥህ።

   Delete
 3. አዪ እንደዚህ አይነት ማሰተዋል ቢኖርማ ኖሮ ቤተክርሰቲያኒቱ የት በደረሰች? ማፈሪያ ሁሉ ተሰብስቦ ይግል ጥቅሙን ያሳድዳል እንጂ

  ReplyDelete
 4. Enante ayelu lebetekrestiyan asabi sinka enkuan atafrum menafkoch

  ReplyDelete
 5. እኔ እምለው እናንተ እነማን ሆናችሁ ነው ሲኖዶሱንም ሆነ ማህበሩን የምትወቅሱት ያልተጨበጠ ትንታኔ የምትሰጡት? ተሃድሶን መዋጋት ሹመት ቢያሰጥ ቢያንስ እንጂ አይበዛም። እናንተ ከምተሰራምዱት አቋም አንጻር ማየታችሁ አስገርመኝም ለማንኛውም ቢቻላችሁ መሰላችሁን አሽሉኮ ለማስገባት የማትፈነቅሉት ድንጋይ እንደማይኖር ግልጽ ነው። ለማንኛውም ለሁላችንም እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን።

  ReplyDelete
 6. ስራ ፈቶች........ከተነቃ በቃ ወደ አዳራሹ ብቻ ሂዱ...የሰውን ጓዳ ለመበጥበጥ እና ለመዝረፍ ሰው እንደናንተ ሲሯሯጥ አላየሁም.

  ReplyDelete
 7. ምን ነካችሁ ምነው ዘገየ የሚል ጥያቄ ምንድር ነው?እነ ዘገየ ተሰብስበው ፍጥነት ከየት ሊመጣ

  ReplyDelete
 8. የታህድሶ ኑፋቂያችሁን ያፋጥኑልናል በማለት ለማሾም ደፋ ቀና ለምትሉላቸው የታህድሶ መናፍቃን መነኮሳት ማጣራት፤ የኃላታሪካቸውን ማየት... የሚሉ የአባቶቻችን ቁርጠኛ አቅዋም ስጋት ላይ የጣላችሁ ይመስላል አትልፉ በምትጠሉት ነገር ግን የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀንልጅ በሆነው ማኅበረ ቅዱሳን አድሮ እግዚአብሔር ስላጋለጣችሁ ታህድሶ በሊቀጳጳስነት አይሾምም ስለዚህ ዝባዝንኬው ሳይበዛ በማደነጋር ሹመቱ ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያስቀምጥ በችኮላ እንዲካሄድ እና የማይመጥኑ መነኮሴ መሳዬች የእናንተ ያላነሰ የቤተክርስቲያን ራስ ምታት እንዲሆኑ የምታደርጉት ጥረት የቤክርስቲያን ተቆርቀወዋሪ መስላችሁ ይህንማለታችሁ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. የሰውልጅን ለማቀራረብ ሳየሆን ለማራቅ ???? እንደምትሰሩ ከህሊናችሁ መጣላታችሁ ለዚህ ማስረጃ ነው ግን አስከ መቼ ከሕግዚአብሔር ጋር ተዋግቶ ይቻላል ሳይመሽ ማሰቡ የተሸለ ነውና ብታስቡበት የላካችሁን ብታውቁት ይገርመኛል ከተጫናችሁት በላይ እየዋሻችሁ ሕዝብን ለማናቆር ህሊና ይስጣቸሁ ብቻ ከጽሁፉ አንድ ነገር ልበል ሲነዶስ የሾማቸው ሳይሆን መንፈስቅዱስ የሾማችው ማለት እንደቻል ምን ማለት ነው በመንፈስቅዱስ ተመርተው የሚያደረጉት ጉባኤ ለማቃለል እና ኦርቶዶክሳውያን መንፈስ ቅዱስ የላቸውም ለማለት ሳታውቁት የምትጽፉት ሓሰት እውነቱን እንድናውቅ እንዳደረግን ብትረዱ ስልታችሁን ትቀይሩ ነበር ግን በጫት የደነዘዘ አምሮ በካቲካለ የናወዘ ናላ ይዛችሁ መቼ???

  ReplyDelete
 10. እውነት በጎደለበት እምነት ውስጥ ትክክለኛ አመራር መጠበቅ ሞኝነት ነው። እግዚአብሄርን ከማምለክ ሌሎች አማልክት ፈጥረን ከእግዚአብሄር በላይ መምለክ ከጀመርን ቆይተናል። ለመሆኑ በጽላት ላይ ከተጻፈው እና መጽሐፍ ቅዱስ የትኛው ይበልጥ ይሆን? ለአስርቱ ትዕዛዛት መስገድና ማምለክ ከተቻለ ለምን ቅዱሰ መጽሀፍኑ ማምለክ አልቻልንን? ለዚህ መልስ መስጠት ከቻል በእውነት አምልኮታችንን በትክክል እየኖርንበት ነው።ሁሉም የገንዘብ ሰው ሆኖዋል። እግዚአብሕርን መፍራት ትተናል። ጉድ ነው የሀገረ ሰው አሉ እናታችን በእደሜ ገፋ ያሉት አያታችን።ኢትዮጵያ ቁጪ ብለው በውጭ ሀገር ያሉት አብያተ ክርስትያናት መምረት ተጀመረ። የጳጳሳት ችግር ስለተፈጠረ። ኤረ አንድ በሉኝ ወገኖቼ።ከአስፈለገም እኮ በቆሞሳት መምራት ይችል የለም። ምነው ስኖዶሳችን ማስተዋል አጡ። መጠቃቀም በእግዝአብሔር ቤት ውስጥ አይደለም።

  ReplyDelete
 11. አባ ሰላሳዎች የስው ቤት ከመቀላወጥ ስለ ፓስተሮቻችሁ ሹመት አውሩ። የኛን ጷጳሳት ጉደይ ለኛ ለኦርቶዶክሳዊያን ተዉልን።

  ReplyDelete