Monday, June 6, 2016

ለጠቅላይ ቤተክህነት ስራአስኪያጅነትና ጸሐፊነት የተሾሙት ለቤተክህነቱ መፍትሔ ያመጡ ይሆን? ወይስ?

Read in PDF

ፓትርያኩ እንደ ርእሰ መንበርነታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ችግርና የሕዝበ ክርስያኑን ጥያቄ ያገናዘበ መልእክት በማስተላፍ የተጀመረው የሲኖዶስ ስብሰባ እርሳቸው ካቀረቡት ሐሳብ በተቃራኒው መጓዙና አሁን ላለው የቤተ ክርስያኒቱ ወቅታዊ ችግር መፍትሔ የሚያመጣ አጀንዳ ላይ መነጋገርና ተገቢ ውሳኔ መስጠት ተስኖት የጳጳሳቱን የግል ጥቅም በሚያስጠብቁና ሥልጣን ላይ ባተኮሩ አጀንዳዎች ነው የሰነበተው፡፡
ፓትርያኩ “ሕዝቡ በርካታ መሠረታዊ ጥያቄ እየቀረበ ነው፤ የገንዘብ ብክነት የወንጌል አገልግሎት እጦት የምእመናን ፍልሰት ምሳሌ ያለው አገልጋይ ማጣት ወዘተ መስተካከል አለባቸው እያለ ነው” ለሚለው ንግግራቸው ትኩረት መነፈጉ ከዚህ የበለጠ ለቤተክርስቲያን የሚበጅ አጀንዳ አልነበረምና ሲኖዶሱ መንፈስ ቅዱስ እንደ ተለየው አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ስለዚህ ሲኖዶሱን እያሽከረከሩ ያሉት አንዳንድ ጳጳሳት ለግል ጥቅማቸው ብቻ እንጂ ለቤተክርስቲያን እያሰቡ እንዳይልሆነ አመልካች ሆኗል፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ የግላቸው ጉዳይ የሥልጣንና የመሳሰለው የግል ጥቅማቸው ጉዳይ ነው በርካታ ቀናትን የወሰደው፡፡

መንፈስ ቅዱስ ከራቀው እንደ ሰነበተና የሥጋ የደም ሐሳብ እንደሚመራው ተግባሩ እየመሰከረ ያለው የሲኖዶስ ስብሰባ ባለፈው አርብ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅነት አባ ዲዮስቆሮስን ለጸሀፊነት ደግሞ አባ ሳዊሮስን ሾሟል፡፡ ሁለቱ ጳጳሳት እንዲሾሙ በታጩ ጊዜ ፓትርያርኩ እንደማይቀበሏው ተናግረው የነበረ ቢሆንም ከብዙ ድርድር በኋላ ከበጣም መጥፎ መጥፎ የሆነውን ለመምረጥ በመገደዳቸው ሹመቱ በሲኖዶስ ተወስኗል፡፡


አዲሶቹ ተሽዋሚዎች እንደ ቀደሙት አባ ማቴዎስና አባ ሉቃስ የአንድ ማኅበር ጉዳይ ፈጻሚዎች ሳይሆኑ የቤተክርስቲያንን ተልእኮ ፈጻሚዎች ሊሆኑ እንደሚገባ እየተጠቆመ ነው፡፡ በተለይም አባ ሳዊሮስ በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ እያደረጉ ያለውን አሁን በሚገኙበት ስልጣን ላይ ሆነው ቢፈጽሙት በቅድሚያ የሚጣሉት ከራሳቸው ጋር ነው፡፡ በመቀጠል ደግሞ ከቤተክርስቲያን ሕግ ጋር ነው፡፡ በመጨረሻም ከፓትርያርኩ ጋር መጋጨታቸው አይቀርም፡፡ የጸሀፊነቱ ሹመት የተሰጣቸው አባ ሳዊሮስ ከዚህ በፊት በሲኖዶስ የታገደውን የማኅበራት ፈቃድ በሀገረ ስብከታቸው በመፍቀድ የሲኖዶስን ሕግ ጥሰዋል፡፡ ይኸውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሆኑ የኦሮሞ ተዋላጆች የሆኑ የማቅ አባላትን “ማኅበረ ሐዋርያት” በሚል ተደራጅተው በእርሳቸው ቲተር ፈቃድ መስጠታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የዚህ ማኅበር አላማው ምንድነው? የሚለው ጥያቄም እያየለ መጥቷል፡፡ በዚህ ሁኔታ በጸሀፊነታቸው ደግሞ ሌሎችንም ጥሰቶች እንደማይፈጽሙ ምንም ማስተማመኛ የለም፡፡
ጠቅላይ ቤተክህነት አካባቢ ያለው መንገድ እየተሰራ በመሆኑ ምክንያት የበዓለ ሲመቱ ድግስ ወደ ሰአሊተ ምህረት ቤተክርስያን መዞሩን እንደ አንድ ትልቅ አጀንዳ ይዞ በመነጋገሩ ክብሩን ዝቅ ያደረገውና ራሱን ያስገመተው ሲኖዶስ አባ ሳዊሮስን የታገደውን የማኅበራት ፈቃድ በገዛ ሥልጣናቸው በመጣሳቸው ይጠይቃቸዋል ወይስ አይጠይቃቸውም? የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ነው፡፡   
አዲሱ ስራ አስኪያጅ አባ ዲዮስቆሮስ ከወለዱት ልጅና ከፍተኛ በሆነ የገንዘብ ፍቅር ጋር በተያያዘ ስማቸው ይነሳል፡፡ በዚሁ ሁኔታቸው የቀድሞው ሥራ አስኪያጅ አባ ማቴዎስ ይመኩበት የነበረውንና ቤተክህነቱን በበጀት እጥረት ወጥረው ከ39 ሚሊዮን ወደ 239 ሚሊዮን ብር አድርሼዋለሁ የሚሉትን ገንዘብ የመጠበቅና ለተገቢው አገልግሎት ማዋል፣ በአባ ማቴዎስ ክፉኛ የተበደለውን የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ እንቅስቃሴና የበጀት እጥረት መቅረፍ ይኖርባቸዋል፡፡
እነዚህ ተሽዋሚዎች በብዙ ችግር ተጠላልፋ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ማረጋጋት ለባዘነው ምእመን በሲኖዶስ ደረጃ የመፍትሔ አቅጣጫ ማፈላለግ፣ አድሎአዊ አሰራርንና የማኅበር አስተሳሰብን ከህሊናቸው ማራገፍ ለስብከተ ወንጌል ከፍተኛ ትኩረትና በጀት መመደብ  አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሹመት በፊት በየሀገረ ስብከታቸው እያደረጉት ያለውን ጎጂ ድርጊት እዚህም በበለጠ ስልጣን የሚደግሙት ከሆነ መጥኔ ለቤተ ክርስቲያን መጥኔ ለፓትርያኩ ነው የሚባለው፡፡           

5 comments:

 1. ገና ምኑን አይተሽ ትጠበጠቢያለሽ!!

  ReplyDelete
 2. Menew Kemegebaw Belay Tewashalachehu?

  ReplyDelete
 3. ስለ ብፁዕ አቡነ ዲስቆሮስ የምታወሩት ሁሉ ውሸት ብቻ ነው። እንዲሁም ስለ አቡነ ሣዊሮስም የምትቀባጥሩት እናንተና ማቅ ግንባር ፈጥራችሁ ቤተክርስቲያን ልታወድሙ እንደሆነ ተነቅቶባችሁዋል። እንግዲያውስ አልሰማንም እንዳትሉ እንጂ አሁን እዉነተኛ አባቶች፡ የተጣሉትን አስታርቀው የጠፋውን ፈልገው ሕዝቡን አንድ ሊያደርጉ የሚያስችሉ አቅምም ብቃትም ያላቸው በአስተዳደር በአስተሳሰብ የነቁና ብቃት ያላቸውን አባቶች ናቸው በትእግስት ጠብቆ ማየት ይሻላልና እባካችሁ አፋችሁን ሰብስቡ።።።።።

  ReplyDelete
 4. ጽፋችሁ ሞታችኋል

  ReplyDelete
 5. Whatever you judge me I'm done!that is it I don't want to lose my self any more.

  ReplyDelete