Sunday, July 31, 2016

የኤጲስ ቆጶሳቱ ዕጩዎች ጉዳይ እንደገና እንዲጤን እየተጠየቀ ነውየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከግብጽ ጥገኝነት ተላቃ ራስዋን በራስዋ ማስተዳደር ከጀመረችበት ከ1951 ዓ.ም. ወዲህ 6 ፓትርያርኮችን 121 ጳጳሳትን ሾማለች፡፡ በ5ቱ ፓትርያርኮች ዘመን የተሾመው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደዚህ ከፍተኛ ማዕረግ ሲደርሱ በተቻለ መጠን ቅዱስ ሲኖዶስ አስቦበት መክሮበት ይሾም ነበር፡፡
ባለፉት 10 ውስጥ ዓመታት በሞት፣ በእርጅና ያለፉትና መሥራት ያልቻሉትን ለመተካት ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ነገሩን በማንከባለል ብቻ ጳጳሳትን መሾም ሳይቻል በመቅረቱ እስከ 4 ሀገረ ስብከት በድርብ በመያዝ የቤተክርስቲያንን ካዝና በማራቆትና በማን አለብኝነት የተመደቡበትን ሀገረ ስብከት በቅጡ ሳይመሩ ተደርቦ በተሰጣቸው ሃገረ ስብከት ላይ ስማቸው ብቻ እየተጠራ ብዙ ክፍተቶችና የአስተዳደር በደሎች ሲደርሱ ዓመታት አልፈዋል፡፡
በዘንድሮው የርክበ ካህናት ስብሰባ ላይ ኤጲስ ቆጶሳት መሾም እንዳለባቸው ተወስኖ ይህን የሚያከናውን አስመራጭ ኮሚቴ ቢሠየምም የተጣለበትን ኃላፊነት ወደኋላ በመተው በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሚያሳዝንና አንገት የሚያስደፋ በደል ተፈጽሟል፡፡ ከኮሚቴው አባላት መካከል አንዳንዶቹ እነርሱ በተሾሙበት መንገድ ሌሎችን ለመሾም ባደረጉት እንቅስቃሴ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊት ፈጽመዋል፡፡ ከተፈጸሙት አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊቶች መካከል የሚከተሉትን እነጠቅሳለን፡፡ 

Sunday, July 24, 2016

“ወያነሥኡ እደዊሆሙ ለእከይ፣ ወመልአክኒ ይስእል፣ ወመኰንንኒ ይየውኅ ከመ ይርከብ ፍትወተ ነፍሱ” (ሚክ. 7÷3)“አለቃውና ፈራጁ ጉቦ ይፈልጋሉ፣ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጎነጉናሉ”(ሚክ. 7÷3)
ለጵጵስና የሚታጩ አባቶችን እንዲለይ በቅዱስ ሲኖዶስ ኃላፊነት የተሰጠውና በብዙ መልኩ የተዛባና አሳፋሪ ሥራ ሲሠራ የቆየው ኮሚቴ እጅግ አስተዛዛቢ በሆነ መንገድ ለጵጵስና የተገቡ አንዳንድ አባቶችን መጣሉንና ለጵጵስና የማይገቡ አንዳንዶቹን ደግሞ በዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ አካቶ ማቅረቡን ከሰሞኑ ሰምተናል፡፡ በዚህ እጅግ ፍትሐዊነት በጎደለውና የቤተክርስቲያን ጥቅም ሳይሆን የግል ጥቅም በቀደመበትና በጳጳሳት ደረጃ ከፍተኛ ሙስና የተፈጸመበትን የማጨት ሂደት ያዛቡት በተለይ ሁለት ጉዳዮች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ አንደኛው “እኔ እንድታጭ አድርጉ” ወይም “አንተን እንድትታጭ አደርጋለሁ” በሚል ከሚታጩ አንዳንድ መነኮሳት ከፍተኛ የሆነ ጉቦ በተቀበሉ ጳጳሳት ምክንያት ለጵጵስና ያልተገቡ ሰዎች እንዲታጩ ተደርገዋል፡፡ ለጵጵስና የተገቡ አንዳንዶቹ ደግሞ ከዕጩነት እንዲወጡና በሐራ ብሎግ ላይ ስማቸው እንዲጠፋና ቅስማቸው እንዲሰበር የማድረግ እኩይ ሥራም ተሠርቷል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከታጩት ውስጥ ለማኅበረ ቅዱሳን ሐሳብ ተገዢ ያልሆኑና እርሱን ሥርዓት ያስይዛሉ ተብለው ከወዲሁ የተፈሩ መነኮሳት በዕጩው ዝርዝር ውስጥ እንዳይካተቱ፣ ተካትተው ከሆነም ስማቸው እንዲጠፋና ከእጩነቱ እንዲወጡ የማድረግ ሥራ ተሠርቷል፡፡      
በዚህ ውስጥ ዋና ተዋናይ ከሆኑት ጳጳሳት የኮሚቴው አባላት መካከል አንዱ የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም ይገኙበታል፡፡ አባ አብርሃም ራሳቸው እጅግ በሚያሳፍርና እንኳን ለጳጳስ ለአንድ ተራ ሰውም በማይመጥን የዠቀጠ ሕይወት ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን አገር ያውቀዋል፡፡ የአመንዝራነትና የጠንቋይነት ሕይወታቸው ከቤተሰባቸው ይጀምራል፡፡ አባታቸው መሪጌታ እውነቱ ትውልዳቸው ጐጃም እንዳልሆነ የታወቀ ነው፡፡ ከሀገራቸው ጉንደ ወይን የወንድማቸውን ሚስት ደፍረው ተደብድበው ወደ ደቡብ ተሰደው ኖረው ሳሉ፣ ደቡብ አካባቢም የሰው ሚስት ሲያማግጡ እዚያው በድብደባ ሕይወታቸው ማለፉን በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡ አባ አብርሃምም በዚሁ ሕይወት ተጠምደው ፊልሞን የተባለ ልጅ በምንኩስና ውስጥ ወልደው በሹፍርና እያገለገላቸው ይገኛል፡፡

Thursday, July 21, 2016

ቤተክርስቲያንን አንገት ያስደፋ አስመራጩ ኮሚቴና አሳፋሪ ሥራዎቹየጵጵስና አስመራጭ ኮሚቴው የተሰጠው የጊዜ ገደብ ሐምሌ 30 ቢሆንም የ15 ቀን የጊዜ ገደብ ይሰጠኝ ማለቱን ተከትሎ በርካታ ነገሮችን እየታዘብን ነው፡፡ በዋናነት እጩ ሆነው ከገቡትና እጅግ ጠንካራ ከተባሉት አባቶች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን አያሠሩኝም፣ አብሬያቸው መጓዝ አልችልም በማለቱ ምክንያት፣ ከኮሚቴዎቹም አንዳንዶቹ የእነዚህ አባቶች መታጨት ስላሳሰበው የጊዜ ገደቡ ካለቀ በኋላ የ15 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ጠይቆ ማቅ የዘረዘረውን የእነዚህን አባቶች ኃጢአት በሐራ ላይ ማስዘርዘሩን ተያይዞታል፡፡
በተለይ በተጨመረው ጊዜ በኮሚቴው ስም እየተሠራ ያለው ዋና ሥራ ከኮሚቴው አባላት አንዳንዶቹ እና ማቅ በመተባበር የእጩዎችን ኃጢአት በማቅ ብሎግ በሐራ ላይ መዘክዘክ ሆኖአል፡፡ በምእመናን ስም ተሰጠ የሚባለውን በማቅ ሰዎች ተቀነባብሮ የሚቀርብለትን “የምእመናን አስተያየት” ማንበብና እነዚሁ አንዳንድ የኮሚቴው አባላት የፈሯቸውንና ማቅ ስም የለጠፈባቸውን ሰዎች በሐራ በኩል እያሰደበ ይገኛል፡፡ ይህንን ይዞም እነዚህ ሰዎች በርካታ ችግር አሉባቸውና ከዕጩነት መውጣት አለባቸው ብሎ ከዕጩነት ውጪ እያደረጋቸው ነው፡፡

Wednesday, July 13, 2016

ስለ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የነገራችሁን የምታውቁትን ወይስ እንዲሆን የፈለጋችሁትን?


Read in PDF 
ታዛቢ ከአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ አባ ሰላማ ብሎግ ጨለምተኛ አስተያየት ማስተናገድ ከጀመረች የቅርብ ጊዜ ጽሁፍ ሶስተኛዋ ነው። የሀገረ ስብከቱን ሥራ ለመተቸት የሀገረ ስብከቱ ባለሥልጣናት በስልጣን ላይ የቆዩበትን ጊዜ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ባለሥልጣናት ሥልጣን ላይ የቆዩበት ያለፉት 4 ወራት ያቀረባችሁትን ያህል ትችት ለማስተናገድ በቂ ነው ብዬ አላስብም። አንድ ሰው በአዲስ ኃላፊነት ሲሾም የነበረውን አሰራር ለማወቅ የሚፈጅበት የራሱ ጊዜ አለው። አሰራሩን ካወቀ በኃላ ደግሞ የራሱን ሥልት ለመንደፍና ያሉትን የአሰራር ክፍተቶች ለማስተካከል የሚፈጅበት ተጨማሪ ጊዜ አለ። እነዚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ሙገሳም ነቀፋም ማስከተል ተገቢ ይሆናል።
በመሰረቱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በባህሪው ከሌሎች ሀገረ ስብከትም ለየት የሚያደርገው ብዙ ነገሮች አሉት።
·        በርካታ ሰራተኞችን ማስተዳደሩ
·        ሰፊ ምጣኔ ሀብት አንቀሳቃሽ መሆኑ
·        ኋላ ቀር የአስተዳደር ሥርዓት መከተሉ
·        የእርስ በእርስ መጠላለፍና መከፋፋት የሞላበት መሆኑ
·        መንፈሳዊነት በሌላቸው ሰዎች መወረሩ
·        የተለያየ ፍላጎት ባላቸው ቡድኖች መታጠሩ
·        በርካታ ደጅ ጠኚዎችን ማስተናገዱ
·        እያንዳንዱ ደብር ራሱን የቻለ የአሰራር ክፍተት ያለበት መሆኑ
·        መምሪያዎች ከኋላ ቀር አሰራር አለመላቀቃቸው
·       
እነዚህን እና መሰል ውስብስብ ችግሮችና ጫና እያለበት የሀገረ ስብከቱ ችግሮች በቀላሉ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊስተካከሉ ይችላሉ ተብሎ አይታሰብም።
አባ ሰላማ ስለ ሀገረ ስብከቱ አዲስ አስተዳደር ለዘብተኛ ተቋውሞ ማስተናገድ የጀመረችው አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ሥራ ከጀመሩ ወር እንኳን ሳይሟላቸው ነው። ይህ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም የብሎግዋ ኢዲተሮች የተላከላቸውን ጽሁፍ ሁሉ (አንዳንዴ ራሳቸውን ሙልጭ አድርጎ የሚተችም ጭምር) ዝም ብሎ ከመልቀቅ ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ መዝነው በሚያወጡት ጽሁፎች ላይ ማስተካከያ ለማድረግ ቢሞክሩ ጥሩ ነው። ብሎግዋ ግለሶበች የፈለጉትን ጽኁፍ ከራሳቸው ስሜት አንጻር ጽፈው ሲልኩ የምታስተናግድበት መስፈርት ቢኖራት ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ። የምትለቁዋቸው ጽሁፎችም ሆነ አስተያየቶች በሰው ሰብእና ላይ የሚፈጥሩት ችግር እስከምን ድረስ እንደሆነ አጢናችሁ  ሥራችሁን በአግባቡ ብትሰሩ የተሻለ ይሆናል።

Thursday, July 7, 2016

ከደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ህዝብ ለኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ የቀረበ አስተያየትከደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ኢጲስ ቆጶሳት ተጠቁመዋል። እንደ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ነዋሪነታችን ከኛ ሀገረ ስብከት ሰዎች መጠቆማቸው አስደስቶናል። በተለይም ሶስቱ አባቶች ማለትም የሀይቁ አባት አባ ፍቅረ ዩሀንስ የደሴ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ጽጌ ስላሴ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ አባ ገብረስላሴ መጠቆም አስደሳች ነው። እነዚህ አባቶች በምንኩስናም ሆነ በገዳማዊ ህይወታቸው የተመሰገኑ ናቸው። በአስተዳደር ችሎታቸውም የተመሰከረላቸው ናቸው። ሥርዓተ ቤተክርስቲያንንም ሆነ የክህነነት አገልግሎትን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ መጠቆማቸው ተገቢ ነው።
አባ ገብረስላሴ የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እያሉ አስተዳዳሪነቱን ለቀው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ይሁኑ ሲባል የደብሩ ህዝብ አይነሱብን ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ እንደነበር ይታወቃል። አሰራሩ ግድ ይላል አማራጭ የለም ስለተባለ ብቻ ነው። ህዝቡ የሳቸውን መነሳት የተቀበለው። አባ ገብረሥላሴ በመንፈሳዊ ህይወታቸው እንከን አይገኝባቸው። በንዋይ ፍቅርና በሌላው ነገር አይታሙም። ትህትና ያላቸው እና አስተዳደራዊ ብቃታቸውም የተመሰከረለት ነው። አስተዳደር ብቃት ባይኖራቸው ኖሮ ህዝቡ አይነሱብን ብሎ ሰልፍ አይወጣም ነበር።
አባ ጽጌ የደብረ ቤቴል ቅድስት ስላሴና ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ ሲሆኑ በአስተዳደር ብቃታቸው ከፍ ያለ ደረጃ የደረሰ ነው። አባ ጽጌ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ህዝብ የታወቁ የልማት አርበኛ ናቸው። መኪናዎችን ለቤተክርስቲያን ያስገዙ ሲሆን ለቤተክርስቲያንዋ መገልገያ የሚሆን ህንጻም እያስገነቡ ናቸው። እኚህ አባት 42 ሰው የሚያስተናግድ ሽንት ቤት ያስገነቡ ሲሆን ለአብነት ተማሮዎችም ተጨማሪ ቦነስ በመስጠት ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ትልቅ አስተዋጽዖ አድርገዋል። የኑሮ ውድነቱን ከግምት በማስገባት ለካህናቱ ደሞዝ ያስተካከሉ ሲሆን የስብከተ ወንጌል አዳራሾችንም አስገንብተዋል። አባፍቅረ ዩሀንስም ቢሆኑ በመንፈሳዊ ህይወታቸው የተመሰከረላቸው እና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላው ናቸው።
የእነዚህ ሰዎች ብቃትና መንፈሳዊነት እንዳለ ሆነ በምን መመዘኛ እና ብቃት እንደተጠቆሙ ያልገባን ሰውም በጥቆማው ላይ ስላሉ ተገርመንም ተደንቀንም አለን። እኚህ ሰው አባ ኤልያስ ታደሰ ናቸው። አባ ኤልያስ ለመመንኮስ እንኳ በአስተዳዳሪነት ተደራድረው እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ነው። በሕይወታቸውም ምንም አይነት የምንኩስና ህይወት ፍሬ አይትባቸውም። የደሴ ገብርኤል ሰባኬ ወንጌል በነበሩ ጊዜ ሚስት ለማግባት እየተዘጋጁ በነበረ ጊዜ አለቃ ትሾማለህ መንኩስ ተብለው የመነኮሱ ሰው ናቸው። አለቃ ትሆናለህ የሚለው ቃል አስደስቶዋቸው ከተሾምኩማ በማለት በግንቦት ወር መንኩሰው በሰኔ ወር 40 ቀን እንኳ ሳይሞላቸው አለቅነት የተሾሙ ግለሰብ ናቸው። የተሾሙበትም ደብረ ደሴ መድኃኔዓለም ነው።ግለሰቡ የምነከስናም ሆነ የገዳሚ ሕይወት ባለቤት ሳይሆኑ ለሹመት ብቻ የገቡበት ሕይወት እንዴት ለጵጵስና እንዳስጠቆማቸው ለደሴ ህዝብ ግራ ነው። እሳቸውም ቢሆኑ በአንደበታቸው ምንኩስናን የት አውቀዋለሁ ብለው መናገራቸው የቅርብ ወዳጆቻቸው ሁሉ የሚያውቁት ነው።

Tuesday, July 5, 2016

ለጵጵስና እነማን ይመረጡ ይሆን?

 Read in PDF
ለጵጵስና የሚታጩትን ለማቅረብ የተወሰነው የጊዜ ገደብ እየተጠናቀቀ ነው፡፡ በቅርቡ ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የጳጳሳት ሹመት እስካሁን ድረስ ለጵጵስና የታጩት መነኮሳት ብዛትና ማንነት ከቤተ ክርስቲያኒቱ በኩል በይፋ ያልተገለጸ ቢሆንም በማቅ ብሎግ በሐራ በኩል ተዛብተውና ተጋነው፣ በዚህ ውስጥ ማቅ ምን ትርፍ ሊያገኝ እንደሚችል በውል ባይታወቅም፣ ለእርሱ እንደማይመቹት ከወዲሁ ያወቃቸውን አባቶች ስም በልዩ ልዩ መንገድ ማጥፋቱን ተያይዞታል፡፡ ይህም በአስመራጭ ኮሚቴው ላይ ጫና ለመፍጠር ነው፡፡       
በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተሰየመው ኮሚቴ አማካኝነት እስከ ሰኔ 30/2008 ዓም ድረስ ለጵጵስና የሚመረጡትን አባቶች በተመለከተ የእጩዎች ሥም ዝርዝር በሚል በሀራ በኩል ወጥቶ ታይቶአል፡፡ ሀራ በመጀመሪያ ያወጣችው ስም ዝርዝር ብዛት 1ዐ8 ሲሆን ከኮሚቴዎቹ አንዳንዶቹ እንደመሠከሩት በወጣው ስም ዝርዝር ውስጥ በእነርሱ እጅ የሌሉ የመነኮሳት ስም በብዛት መውጣቱን ሲናገሩ ተደምጧል፡፡ ይሁን እንጂ ከ108 በአንድ ጊዜ ወርዳ 74 ናቸው ማለቷ ሐራ በጳጳሳቱ ምርጫ ላይ ሆነ ብላ እየሰራችው ያለ ነገር እንዳለ ያሳያል፡፡ 

Friday, July 1, 2016

ሰበር ዜና፡ አባ አፈወርቅ ላይ የመግደል ሙከራ ተደረገ። በጩቤ ተወግተው ሆስፒታል ተኝተዋል።


Read in PDF
  • ·         ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ተብሏል
  • ·         ማኅበረ ቅዱሳን የትጥቅ ትግሉን አፋፍሞታል

ዛሬ በአባ አፈወርቅ ላይ በጩቤ በመውጋት የግድያ ሙከራ ተደረገ፡፡ የግድያ ሙከራው የተደረገው አባ አፈወርቅ በቀድሞው ቢሯቸው የኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ ቤተክህነት በር ላይ ሲሆን ግድያው በተቀነባበረ መንገድ መፈጸሙንና ጥቃት አድራሾቹ አባ አፈወርቅን ሽንጣቸው ላይ በጩቤ በመውጋት በሞተር ሳይክል ማምለጣቸው ታውቋል፡፡ አባ አፈወርቅም በሕክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን ቅዱስነታቸው እንደጎበኛቸው አንዳንድ ምንጮች ተናግረዋል፡፡በአባ አፈወርቅ ላይ የመግደል ሙከራ የተደረገው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምክትል ስራ አስኪያጅ ከሆኑ ሳምንት እንኳ ሳይሞላው ነው።
ከአባ አፈወርቅ የማቅን እኩይ ሥራ በመቃወም የሚታወቁና ማቅ በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ ያደረገባቸው የቤተ ክርስቲያን አባት ናቸው፡፡ ማቅ ግን እኩይ ዓላማውን ስለተቃወሙ ብቻ ከዚህ ቀደም ከማቅ ዋና ሰዎች አንዱ የሆነው ባያብል በመኪና ሊገጫቸው ሙከራ አድርጎ ሳይሳካ መቅረቱ፣ በቅርቡም ሌላ የማቅ ሰው በመኪና የመግደል ሙከራ በማድረጉ ተይዞ እንደተፈረደበት የሚታወስ ነው፡፡ አባ አፈወርቅ ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው መመደባቸው የእግር እሳት የሆነበት ማቅ  በሐራ በኩል ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶባቸው የነበረ ሲሆን ይህ በቅጥር ነፍሰ ገዳዮች የተፈጸመው የግድያ ሙከራ ያን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ ወገኖች እየተናገሩ ነው፡፡ የግድያ ሙከራውም ቀደም ብሎ የታሰበበትና ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡