Friday, July 1, 2016

ሰበር ዜና፡ አባ አፈወርቅ ላይ የመግደል ሙከራ ተደረገ። በጩቤ ተወግተው ሆስፒታል ተኝተዋል።


Read in PDF
 • ·         ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ተብሏል
 • ·         ማኅበረ ቅዱሳን የትጥቅ ትግሉን አፋፍሞታል

ዛሬ በአባ አፈወርቅ ላይ በጩቤ በመውጋት የግድያ ሙከራ ተደረገ፡፡ የግድያ ሙከራው የተደረገው አባ አፈወርቅ በቀድሞው ቢሯቸው የኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ ቤተክህነት በር ላይ ሲሆን ግድያው በተቀነባበረ መንገድ መፈጸሙንና ጥቃት አድራሾቹ አባ አፈወርቅን ሽንጣቸው ላይ በጩቤ በመውጋት በሞተር ሳይክል ማምለጣቸው ታውቋል፡፡ አባ አፈወርቅም በሕክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን ቅዱስነታቸው እንደጎበኛቸው አንዳንድ ምንጮች ተናግረዋል፡፡በአባ አፈወርቅ ላይ የመግደል ሙከራ የተደረገው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምክትል ስራ አስኪያጅ ከሆኑ ሳምንት እንኳ ሳይሞላው ነው።
ከአባ አፈወርቅ የማቅን እኩይ ሥራ በመቃወም የሚታወቁና ማቅ በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ ያደረገባቸው የቤተ ክርስቲያን አባት ናቸው፡፡ ማቅ ግን እኩይ ዓላማውን ስለተቃወሙ ብቻ ከዚህ ቀደም ከማቅ ዋና ሰዎች አንዱ የሆነው ባያብል በመኪና ሊገጫቸው ሙከራ አድርጎ ሳይሳካ መቅረቱ፣ በቅርቡም ሌላ የማቅ ሰው በመኪና የመግደል ሙከራ በማድረጉ ተይዞ እንደተፈረደበት የሚታወስ ነው፡፡ አባ አፈወርቅ ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው መመደባቸው የእግር እሳት የሆነበት ማቅ  በሐራ በኩል ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶባቸው የነበረ ሲሆን ይህ በቅጥር ነፍሰ ገዳዮች የተፈጸመው የግድያ ሙከራ ያን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ ወገኖች እየተናገሩ ነው፡፡ የግድያ ሙከራውም ቀደም ብሎ የታሰበበትና ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ማቅ አዲስ አበባ ላይ በአንድ መነኩሴ ላይ እንዲህ ማድረግ ከቻለ በገጠርማ የስንቱን ሕይወት እንደቀጠፈና ስንቱን አካለ ጎደሎ እንዳደረገ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርገው ግን በሃይማኖቱ ስም መሆኑ ለቤተክርስቲያኗ ማፈሪያ ነው፡፡ መቼም በወንጌል ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት ስለሃይማኖታችሁ ሙቱ እንጂ ግደሉ አይልም፡፡ የማቅ አካሄድ  በምን ላይ እንደተመሰረተ ከዚህ ማወቅ ይቻላል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪና በኦርቶዶክስ ስም የሚነግድ ጸረ ክርስቶስ ቡድን መሆኑ ሲነገር ብዙዎች ውሸት ነው ይሉ ነበር፡፡ ወይም ደግሞ በጣም ጨለምተኛ በመሆንና ዓይንን በመጨፈን የሚፈጽማቸውን እኩይ ሥራዎች እንደ ሃይማኖታዊ ገድል ለመቁጠር የሚሞክሩም አይጠፉም፡፡ ዛሬ በመልአከ ገነት አባ አፈወርቅ ላይ የፈጸመው የግድያ ሙከራ ግን የማህበሩን ትክክለኛ ማንነት በገሃድ አሳይቷል፡፡ በአንድ መነኩሴ ላይ የተቃጣ የግድያ ሙከራ ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ሁሉ ላይ የተቃጣ ግድያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ እንዲህ የማያስብ አባት ካለ ትልቅ ታሪካዊ ስሕተት ይሠራል፡፡ ከቤተክርስቲያን ይልቅ የራሱን ጥቅም ያስቀድማል፡፡ ከእውነት ይልቅ በጊዜያዊ ጥቅም ታውሯል፡፡ 
ይህ ቤተ ክርስቲያኒቱን አንገት የሚያስደፋ ወንጌልን በፍቅር መስበክና ስለ ወንጌል መገደል ሲገባ የግል አጀንዳን በሃይማኖት ካባ ሸፍኖ ለእኩይ ዓላማው እንቅፋት የሆኑበትን አባቶች ማስወገድ ዓላማው አድርጎ እንደሚንቀሳቀስ በአባ አፈወርቅ ላይ ያደረሰው ጉዳት በቂ ምስክር ነው፡፡ ይህን የግድያ ሙከራ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሳይሆን በአንድ መነኩሴ ላይ የተቃጣ የግድያ ሙከራ አድርጎ መውሰድ ትልቅ ጥፋት ነው፡፡ ነገ በሌሎች አባቶች ላይ እንዲህ ያለው ግድያ ላለመፈጸሙ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም፡፡ ይህን አባቱን የሚያገለግል ሳይሆን የሚገድል ትውልድ እያፈራ ያለውን ማቅን እዚህ ላይ ማስቆም ካልተቻለ ነገ በቤተክርስቲያን ላይ ብዙ ጥፋት እንደሚደርስ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

34 comments:

 1. በጣም የሚያሳዝን ዜና ነው። ሰሚ አጡ እንጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በተደጋጋሚ በአደባባይ ማህበረ ቅዱሳን የሚባል ሰለፌ ነፍሰ ገዳይ ቤተክርስቲያን አቅፋ ይዛለች አቡነ መርሃክርስቶስ፡ አቡነ ሚካኤል፡ አቡነ ጳውሎስ ያስገደሉ ማህበር ነዉ። አባቶች ጥንቃቄ ያስፈልጋል በማለት በስብሰባ ትኩረት ይሰጥበት ብለው ተናግረው ነበር። አባ አፈወርቅ ያባታቸውን የአቡነ ሳዊሮስን ሀሳብ በመደገፍ ከማቅ ጋር ተላተሙና ለሶስተኛ ጊዜ የመግደል ጥቃት ተደረገባቸው። ብፁእ አቡነ ሳዊሮስ ምን ተሰማዎት? እኝህ ደሀ መንኩሴ ለርሶ ሲሉ ነበር እራሳቸውን አሳልፎ የሰጡት። ብፁእነትዎ ፍርዱን ለእርሶና ለህሊናዎ ትተንዋል። ምን ቀረብኝ ብለው ወይስ ምን እንዳይቀርብዎት ብለው ባንድ አፍ ሁለት ምላስ የሆኑት።

  ReplyDelete
 2. ጉድ ጉድ ትላንት እሳቸውን በጩቤ ካስወጋ በኋላ መትረፋቸውን ሲሰማ ማቅ አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው። ክርስትና መግደል መደብደብ መርዝ ማጠጣት ስም ማጥፋት ወንድምን መክሰስ አባቶችን ማዋረድ ነው ኦርቶዶክስ ማለት። ለዚህ መልስ ከቤተክርስቲያኗ እንጠብቃለን።

  ReplyDelete
 3. ያሳዝናል። አረመኔነት ነው።

  ReplyDelete
 4. እንዴ ምነው ዘንድሮ ማኅበረ ቅዱሳን እንዳበደ ውሻ ተቅበዝብዟል። ለምን አባ አፈወርቅ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ምክትል ሥራ ኡስኪያጅ ሆኑ ብሎ ነፍሰ ገዳይ ቀጥሮ ለማስወገድ መሞከር ምን ማለት ነው። መንግሥት የለም እንዴ፡ ኡኡታ በዛ እረ የመንግሥት ያለህ!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ስጋት ላይ ወድቆ ይገኛል።
  ጉዱ እየተጋለጠ ውሸቱ እየተነቃበት ስለሔደ ተርበትብታል። የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫም አስፈርቶት የአባቶቻችንን ስም ማጥፋት እንደገና ተነስቶበታል።።።።
  እስቲ ማኅበረ ቅዱሳን ስማቸውን ያጠፋቸውን አባቶች ወደ ሁዋላ መለስ ብለን እናስታውስ፡ ተሀድሶ ያላቸው ፖትርያርኮች ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ። ከአበው ሊቃነጳጳሳት ብፁዕ አቡነ መርሀክርስቶሰ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ብፁዕ አቡነ ዘካሪያስ ብፁዕ አቡነ ባርናባስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፡ በነውርና በዝሙት ስማቸውን ያጠፋው አባቶች፡ ብፁዕ አቡነ ሣሙኤል ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ብፁዕ አቡነ ዲስቆሮስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ብፅዕ አቡነ ሉቃስ ይገኙበታል። ማህበረ ቅዱሳን ለመሆኑ እነኝህን ሁሉ አባቶች የተለያየ ሥም እየሰጠ እና እያጐደፈ ምን ሊያደርግ ቤተክርስቲያን ይቆያል እነኝህ ሁሉ አባቶች ተሀድሶ እና ርካሾች ከሆኑ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን ለቆ ለምን አይወጣም።
  ስማቸውን እያጠፋ ሰድቦ ለሰዳቢ አዋርዶ ላዋራጅ አሳልፎ የሚሰጥ ማህበር አሁን ደግሞ ባለዉ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚያሠጉትን ሊቃውንት እንዳይመረጡ እየጣረ ይገኛል። በብሎግና በአድማ ከመሾም የሚቀር ከስልጣኑም የሚወርድ ማንም የለም።። ለዚህም ምስክሩ ስማቸውን ያጎደፋቸው በክብር ግን ያሉት ሊቃነ ጳጳ

  ReplyDelete
 6. ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ስጋት ላይ ወድቆ ይገኛል።
  ጉዱ እየተጋለጠ ውሸቱ እየተነቃበት ስለሔደ ተርበትብታል። የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫም አስፈርቶት የአባቶቻችንን ስም ማጥፋት እንደገና ተነስቶበታል።።።።
  እስቲ ማኅበረ ቅዱሳን ስማቸውን ያጠፋቸውን አባቶች ወደ ሁዋላ መለስ ብለን እናስታውስ፡ ተሀድሶ ያላቸው ፖትርያርኮች ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ። ከአበው ሊቃነጳጳሳት ብፁዕ አቡነ መርሀክርስቶሰ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ብፁዕ አቡነ ዘካሪያስ ብፁዕ አቡነ ባርናባስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፡ በነውርና በዝሙት ስማቸውን ያጠፋው አባቶች፡ ብፁዕ አቡነ ሣሙኤል ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ብፁዕ አቡነ ዲስቆሮስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ብፅዕ አቡነ ሉቃስ ይገኙበታል። ማህበረ ቅዱሳን ለመሆኑ እነኝህን ሁሉ አባቶች የተለያየ ሥም እየሰጠ እና እያጐደፈ ምን ሊያደርግ ቤተክርስቲያን ይቆያል እነኝህ ሁሉ አባቶች ተሀድሶ እና ርካሾች ከሆኑ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን ለቆ ለምን አይወጣም።
  ስማቸውን እያጠፋ ሰድቦ ለሰዳቢ አዋርዶ ላዋራጅ አሳልፎ የሚሰጥ ማህበር አሁን ደግሞ ባለዉ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚያሠጉትን ሊቃውንት እንዳይመረጡ እየጣረ ይገኛል። በብሎግና በአድማ ከመሾም የሚቀር ከስልጣኑም የሚወርድ ማንም የለም።። ለዚህም ምስክሩ ስማቸውን ያጎደፋቸው በክብር ግን ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ይኽ ሁሉ የስድብ ናዳና እርስ በርስ መናናቅ ማሀበረ ቅዱሳን ያስለመደው ክፉ መርዝ ነው ።

  ReplyDelete
 7. Ayehi wendime sira fet silhonkina gizehin bekentu matfat minim silemaindqhi bicha tsihuf aistafim. Minim mizan yemaidefa tsihuf...

  "No one will argue with your argument with out realiable evidence."

  ReplyDelete
 8. ማህበረ ቅዱሳን የሚባል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስም የሚንቀሳቀስ ሌላ ነፍሰ ገዳይ አልቃይዳ ወይም አይሲስ በምድራችን ተቋቋመ ማለት ነውን?

  መንግሥትስ ቢሆን ምን እየሠራ ነው? በፖለቲካው ላይ የሚነሳበትን ብቻ ነው እንዴ ጥብቅ ክትትል የሚያደርገው? ኧረ ጌታ ሆይ አስበን?
  እስከ መቼ ድረስ ነው በጸረ ወንንጌል ቡድን
  የቤተ ክርስቲያናችን ምእመን እየታመሰ የሚኖረው?
  ኧረ የእውነት ወዳጅ የሆናችሁ ሁሉ የመንፈስን አንድነት ጠብቀን በፍቅር ጨክነን እንነሳ?

  ReplyDelete
 9. ማቅ ነፍሰ ገዳይ ነው።

  ReplyDelete
 10. NFESE GEDAYU MK LEFERDE MEKREB ALEBET

  ReplyDelete
 11. MAHEBERE KIDUS MAHEBERE AGANENETE MEHONU KETAWEKE KOYE. enerseu yihen madregache baheriyachewe new.

  ReplyDelete
 12. እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው እጅግ በጣም ያሳዝናል

  ReplyDelete
 13. የውሾች ጩኽት ነው፤ ማኀበረ ቅዱሳንስ ዝም ብሎ ሥራውን እየሠራ ነው! እውነት እያሸነፈች፤ የእናንተ ብሎግ ነጭ ውሸት ግን እየቀለለች ለመምጣቷ እስካሁን የነበረው የፈጠራ ወሬአችሁ አሳይቶናል!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማኀበረ ቅዱሳንስ ዝም ብሎ ሥራውን እየሠራ ነው ምን አይነት ስራ በሉኝ ነብሰ ገዳይነት ፣ተሳዳቢነት ፣ስም አጥፊነት በአለም ላይ ያሉ ተንኮልና አጋንንታዊ ተልእኮን እያራመደ ነው

   Delete
 14. የውሾች ጩኸት ነው ያልከው ግዴለከም መልሱን እኮ ከእውነተኛው ዳኛ ከመድኀኒአለም ይገኛል። ዛሬ በባዶ ሜዳ እንዲህ የሆነ ነገ የሚመኛትን ሥልጣንን ቢጨብጥ እንደ ጌታው እንደዘርአያቆብ ዘር እንደሚያጠፋ አልገባህም።
  ስለ ብሎግ ማውራቱን ተወውና ስለ ማህበሩ ስለ ውነት ተናገር። የአባ ሠላማ መፈጠር ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሄር የተላከ ይመስለኛል። ማቅ ብቻውን እየፋለለ እውነት ተሸፍና ትቀር ነበር። አባ ሠላማዎች በርቱ ከጉናችሁ ነን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አድር ባይ የሉተር ልጅ ባንዳ!!

   Delete
 15. መጀመሪያ ባያብል የሚባል ሰይጣን እኝሁ አባ አፈወርቅን በግቢያቸው በቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በመኪና ገጭቶ ሊገላቸው ሲል ሮጠው ተርፈዋል።
  በቅርቡ እንዲሁ የማቅ አባል የሆነ ከኮሌጅ ሲወጡ ጠብቆ
  በመኪና ገጭቶ ሊገላቸው ሲሞክር ቱቦ ላይ ወድቀው ተረፉ
  ወደ ህግ ሄደው ይህን ያደረገው አሥር አመት ፅኑ እሥራት እና አምስት አመት ከማንኛውም ምርጫ እንዲገለል ተፈርዶበት ዘብጥያ መውረዱን እናውቃለን። አሁን ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ መንግሥት ባለበት አገር ወደ ሥራ ሲገቡ በጩቤ ወግቶ ለመግደል የተደረገው ሙከራ የብፁእ አቡነ ሳዊሮስ እጅም እንዳለበት ይጠረጠራል። ብፁዕ አባታችን ዲቃላ የወለዱዋቸው ልጆች ለአባ ፍቅረማሪያም አደራ ብለው በድቁና ምስካየ ህዙናን እንዳስቀጠሩ አስተዳዳሪው ለሰው ሹክ ብለው ወሬው እንደሆነ ያደባባይ ሚሥጥር ሆኖአል። ማቅም የሰማው ከኝሁ አባት ነው። ታዲያ እዚህ ላይ አባ አፈወርቅ ምን አደረጉ? መሰል ልጅዎን ራቅ ማድረግ ነበረብዎት እንጅ ለአባ ፍቅረማርያም ቅጠሩልኝ ብለው ህፃናት ልጆች በድቁና ማስቀጠርን ምን አመጣው እንደ ኤግዚቢት መልኩን እዩ እያሉ እየሳቁ ሲያስቁ ነበር።
  አባ ፍቅረማሪያም እንኳን ለርሶ ቀርቶ አቡነ አብርሃም ባቀኑትና በለፉት ራጉኤል ቤተክርስቲያን ያባረረ አድር ባይ ነው። ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንደ ድመት 7 ነብስ ነው ያላቸው
   የውሸት አንባሳደሮች ውሽት ውሽት ውሽት ውሽት ውሽት ውሽት ውሽት ውሽት ብቻ ይህንን ትምህርት ከአባታቹ ከዲያብሎስ ነው የተማራቹት የውሸት እባት ልጆች

   Delete
 16. woregn menafik nachu

  ReplyDelete
 17. በወንጌል ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት ስለሃይማኖታችሁ ሙቱ እንጂ ግደሉ አይልም፡፡

  ReplyDelete
 18. ከድያብሎስ ወገን እውነት አይጠበቅም፡፡ አይደለም የሰውን ልጅ ፈጣሪውን ሳይቀር በውሸት ከሶታል፡፡ ደጋግሞ በማውራት እና በመጮህ ውሸት ከውሸትነቱ አያልፍም፡፡ ይልቅኑ በማኅበሩ ላይ የውሸት ወሬ ከማስወራት እርሻቸው በሰዎች የሠሩት በደል ካለ አጢኑት፣ ወንጀሎችንም ለሕግ ለማቅረብ ጥረት አድርጉ፡፡ እግዚአብሔር ነፁህ ሕሊና ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 19. ዜናው እውነት ከሆነ/በዚህ ብሎግ እውነት ማግኘት እጅግ ከባድ ቢሆንም/ አባ አፈወርቅን ያስደበደባችኋቸው እናንተ ትሆናላችሁ የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬ አለኝ። ከዚያ ስሙን በማቅ ለማላከክ ትፍጨረጨራላችሁ። ሃይማኖት ስለሌላችሁ ይህን ከማድረግ ወደኋላ እንደማትሉ የታወቀ ነው። ማቅን ለማስጠላት፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ከዚህም በላይ ለማድረግ እንደምትተጉ እናውቃለን። ለነገሩ ማቅንስ ቢሆን የምትጠሉት ይህን መሠሪ ተልእኳችሁን ስለሚያውቅባችሁና ስለሚያጋልጣችሁ አይደል። ብቻ እግዚአብሔር የሥራችሁን ይሰጠችኋልና ወዮላችሁ!

  ReplyDelete
 20. የውሾች ጩኽት ነው፤ ማኀበረ ቅዱሳንስ ዝም ብሎ ሥራውን እየሠራ ነው! እውነት እያሸነፈች፤ የእናንተ ብሎግ ነጭ ውሸት ግን እየቀለለች ለመምጣቷ እስካሁን የነበረው የፈጠራ ወሬአችሁ አሳይቶናል!!!

  ReplyDelete
 21. እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን

  ReplyDelete
 22. Kakakakaka... Ayi Aba Selamawoch.... Yihichin Wushet Mefiter ayitakitachihum??? Seyitanim endenanite behaset Fetera Alitekanebetim. leMin Siol hidachihu ataseletinutim Diablosin beWushet?????

  ReplyDelete
 23. Well, if this is true, regardless of who did it, an action of this kind should be condemned. However, imaging "Maheber kidusan" in the image of demon worse than those good for nothing members of the "Synod" including the patriarch is nonsense or highly cynical itself. Who keeps blessing the killing machine of TPLF/EPRDF?? Is it not the so-called patriarch who is the leading conspirator in the history of the church? Do you realty believe that doing this is better than what you are talking about mahibere kidusan? I do say that some of your critical comments on certain traditions of the Church that should be reviewed and wisely removed and kept in museums is quite right. Unfortunately, your allegiance or sympathy to the so-called Holy Synod which is nothing more than being the de facto player of dirty and deadly politics of Tplf/eprdf totally dismisses your claim what ypu stand for, and that is really worse than heretics .

  ReplyDelete
 24. woi Diskur? Medre Diskuram!!

  ReplyDelete
 25. የውሾች ጩኸት ነው ያልከው እኔ የማህበረ ቅዱሳን ወይም የአባ ሰላማ የሁለቱም ደጋፊ አይደለሁም ግን የሁለቱም ተቃዋሚ ነኝ። ማንበብ ግን የሁለቱንም በደንብ አነባለሁ ግን እስቲ ልጠይቅህ የትኛው ፅሁፍ ላይ ነው አባ ሰላማ የዋሸው? የውሸት ቛት እንኳ ማቅ ነው። ስለዚህ ጨለምተኞ አስተሳሰብ ጥሩ አይደለም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሳትደግፍ ሞተሃል የማን እንደሆንክማ ጽሁፍህ አሳበቀብህ!!!!

   Delete
 26. Why those members try to attack and want to kill non their members? Our orthodox church has getting crazy news everyday now.It is very sad to be part of this kind of faith. We lost, what we are going to believe. Now we are working against of Lord God words. Shame on us in this 21st century to heard stupid devil task.

  ReplyDelete
 27. ተባለ ተብሎ ኣይወራም፡፡

  ReplyDelete
 28. ሉተርና ሰራዊቱ ስም ማጥፋት እንጂ ሌላ ምን ስራ አለው ማእበረቅዱሳን ማለት ስራ የበዛብበት ትልቅ በር ነው እናንተ
  Computer ላይ ተጎልታችሁ ወሬያችሁን ከኩ ምድረ ሀራ ጥቃ የእናት ጡት ነካሾች ልቦና እሱ ቸሩ መድሃኒት አለም ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 29. ይሄ አረመኔና ነፍሰ ገዳይ ማህበር በጊዜ ካልተቆነጠጠ ልክ እንደ እስልምና አክራሪዎች በየቦታዉ ቦምብ ማፈንዳቱ አይቀርም፡፡የነጠላ ለባሾችና የጨዋወች ማህበር፣ በመንፈሳዊም ሆነ በስጋዊ ትምህርት ባልበሰሉ ጥሬዎች ተሞልቷል፡፡ ሁሉም በጭፍን ይመራሉ፣ ለነሱ ክርስትና ማለት ሰዎችን ማሳደድ ነዉ፡፡ ያሳዝናሉ፡፡

  ReplyDelete