Wednesday, July 13, 2016

ስለ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የነገራችሁን የምታውቁትን ወይስ እንዲሆን የፈለጋችሁትን?


Read in PDF 
ታዛቢ ከአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ አባ ሰላማ ብሎግ ጨለምተኛ አስተያየት ማስተናገድ ከጀመረች የቅርብ ጊዜ ጽሁፍ ሶስተኛዋ ነው። የሀገረ ስብከቱን ሥራ ለመተቸት የሀገረ ስብከቱ ባለሥልጣናት በስልጣን ላይ የቆዩበትን ጊዜ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ባለሥልጣናት ሥልጣን ላይ የቆዩበት ያለፉት 4 ወራት ያቀረባችሁትን ያህል ትችት ለማስተናገድ በቂ ነው ብዬ አላስብም። አንድ ሰው በአዲስ ኃላፊነት ሲሾም የነበረውን አሰራር ለማወቅ የሚፈጅበት የራሱ ጊዜ አለው። አሰራሩን ካወቀ በኃላ ደግሞ የራሱን ሥልት ለመንደፍና ያሉትን የአሰራር ክፍተቶች ለማስተካከል የሚፈጅበት ተጨማሪ ጊዜ አለ። እነዚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ሙገሳም ነቀፋም ማስከተል ተገቢ ይሆናል።
በመሰረቱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በባህሪው ከሌሎች ሀገረ ስብከትም ለየት የሚያደርገው ብዙ ነገሮች አሉት።
·        በርካታ ሰራተኞችን ማስተዳደሩ
·        ሰፊ ምጣኔ ሀብት አንቀሳቃሽ መሆኑ
·        ኋላ ቀር የአስተዳደር ሥርዓት መከተሉ
·        የእርስ በእርስ መጠላለፍና መከፋፋት የሞላበት መሆኑ
·        መንፈሳዊነት በሌላቸው ሰዎች መወረሩ
·        የተለያየ ፍላጎት ባላቸው ቡድኖች መታጠሩ
·        በርካታ ደጅ ጠኚዎችን ማስተናገዱ
·        እያንዳንዱ ደብር ራሱን የቻለ የአሰራር ክፍተት ያለበት መሆኑ
·        መምሪያዎች ከኋላ ቀር አሰራር አለመላቀቃቸው
·       
እነዚህን እና መሰል ውስብስብ ችግሮችና ጫና እያለበት የሀገረ ስብከቱ ችግሮች በቀላሉ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊስተካከሉ ይችላሉ ተብሎ አይታሰብም።
አባ ሰላማ ስለ ሀገረ ስብከቱ አዲስ አስተዳደር ለዘብተኛ ተቋውሞ ማስተናገድ የጀመረችው አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ሥራ ከጀመሩ ወር እንኳን ሳይሟላቸው ነው። ይህ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም የብሎግዋ ኢዲተሮች የተላከላቸውን ጽሁፍ ሁሉ (አንዳንዴ ራሳቸውን ሙልጭ አድርጎ የሚተችም ጭምር) ዝም ብሎ ከመልቀቅ ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ መዝነው በሚያወጡት ጽሁፎች ላይ ማስተካከያ ለማድረግ ቢሞክሩ ጥሩ ነው። ብሎግዋ ግለሶበች የፈለጉትን ጽኁፍ ከራሳቸው ስሜት አንጻር ጽፈው ሲልኩ የምታስተናግድበት መስፈርት ቢኖራት ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ። የምትለቁዋቸው ጽሁፎችም ሆነ አስተያየቶች በሰው ሰብእና ላይ የሚፈጥሩት ችግር እስከምን ድረስ እንደሆነ አጢናችሁ  ሥራችሁን በአግባቡ ብትሰሩ የተሻለ ይሆናል።

ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ፣ የሀገረ ስብከቱ አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ከዚህ በፊት በኃላፊነት በሰሩባቸው በአዲግራት ሀገረ ስብከት፣ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስና በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በአስተዳደር ችሎታቸው የተመሰገኑ በሥነ ምግባራቸውም የተወደሱ ለመሆናቸው በሶስቱም ቦታዎች አብረዋቸው የሰሩ ሰዎች ምስክር ናቸው። አሁን ያሉበት የኃላፊነት ቦታ ከችግሩ ውስብስብነትና በቦታው የተለያዩ ቡድኖች ካላቸው ፍላጎት አንጻር ነገሮች በተፈለገው መንገድ ያለምንም ኮሽታና ግርግር ሊፈጸሙ ይችላሉ ተብሎ አይጠበቅም። የሀገረ ስብከቱ ችግሮች ውስብስብነትና ዘርፈ ብዙነት ችግሮቹን በየትኛውም መንገድ ለመፍታት ሲሞከር የሚቃወሙ ቡድኖች መኖራቸው የማይታበል ሀቅ ነው።
እሰካሁን ድረስ እንኳን ሀገረ ስብከቱ ከእናንተም ሆነ ከሀራ ተቃውሞዎች እያስተናገዱ መሆኑ ላነሳሁት ሀሳብ በቂ ማጠናከሪያ ነው። ተቃውሞቹ ከእውነታና ከምክንያተኛነት የራቁ በመሆናቸው ትክክለኛው ነገር ሣይሆን የቡድኖች ፍላጎት እስዲጠበቅ ብቻ የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉም በቂ ማሳያዎች ነው። በባለፈው ቀን ጽሁፍ ሀገረ ስብከቱ ፈጸማቸው የሚባሉት ስህተቶች ለመጠቆም፣ ጸሀፊው፤ ከጥላቻና የአንድን ወገን ፍላጎት ከማስጠበቅ ባለፈ ያቀረበልን ጠንካራ ማስረጃ የለም።  
በእኔ እምነት ሊቀ ማዕምራን የማነ የሰሩዋቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እንዳሉ ባልክድም እሳቸውን የትክክለኛነት ጥግ አድርጎ መውሰድም ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። መምህር ጎይቶም ሊቀ ማዕምራን የማነን የትክክለኛነት መለኪያ አድርገው መነሳትም አይጠበቅባቸውም። ነገር ግን የነገሮችን ትክክለኛ አካሄድ መዝነው ሊቀ ማዕምራን የማነ የሰሩትን ትክክለኛ ሥራ ባለበት ማስቀጠልና ስህተቶቻቸውንም በተገቢው ሁኔታ ማረም ይጠበቅባቸዋል።
ሌላው እጅግ አሳዛኝ ነገር በመጋቤ ብሉይ እዝራ ላይ የቀረበው ሥርዓት አልበኛ ትችት ነው። ጉቦ ተበልቷል ለማለት መጋቤ ብሉይ እዝራን የጽሁፉ አቅራቢ ያቀረበበት መንገድ አስተዛዛቢ ነው። ከአሉባልታ ባለፈ ምንም አይነት ማስረጃ ባልቀረበበት ጽሁፍ የእሳቸውን ሰብዕና የሚነካ  ቅኔ ማቅረብ በፍጹም በፍጹም ተገቢ አይደለም።
መጋቤ ብሉይ እዝራ በሀገረ ስብከቱ ጉቦ ለመቀበልም ሆነ ለማቀባበል የሚመች አንዳች አይነት የስራ ኃላፊነት የሌላቸው መሆኑን ያለፈው ጽሁፍ አቅራቢ አጥቶት አይደለም። አንድ ማየት የተሳነው ሰው የአካባቢን ሁኔታ ማጥናት የሚጠይቀውን የጉቦ ማቀባበል ሥራ እንዴት ሊሰራ ይችላል? ጉቦ ሰጪው ከምስክር ጋር መምጣት አለመምጣቱን ፓሊስ መያዝ አለመያዙን ድምጽ እየቀረ      ጸ መሆን አለመሆኑን  ሳያጣራ ጉቦ የሚቀበል ሰው በዚህ ጊዜ ይኖራል? አይመስለኝም። መጋቤ ብሉይ እዝራ እሳቸውን የሚያውቅ ሰው ሁሉ እንደሚገነዘበው እንደዚህ ያለውን ሥራ ሊሰሩ አይችሉም።  
የጉቦ አቀባባይነቱን ሥራ ለመስራት ፍላጎቱም እውቀቱም ዝግጁነቱም የላቸውም። የሳቸው የሥራ ሁኔታ እና የሀገረ ስብከቱም መዋቅር የሚገናኝበት ምንም አይነት ቀጥተኛ የግንኙነት ሰንሰለት የለውም። ይልቁንም ማየት የተሳናቸው መሆኑ ሳይበግራቸው እና በማህበረሰቡ  የሚፈጠረውን ከፍተኛ ተጽእኖ ተቋቁመው ራሳቸውን በመንፈሳዊ ትምህርት አበልጽገው የሊቃውንት ጉባኤ አባል እስከመሆን በመድረሳቸው ሊመሰገኑም ሊበረታቱም ይገባል። በተረፈ መምህር ጎይቶምና እና መጋቤ ብሉይ እዝራ አብረው ስለታዩ ብቻ፤ የራስን የሀሳብ ድር አድርቶ፣ በመሰለኝ ነገሮችን ፈትሎ እና ገምዶ፣ በደሳለኝ ድምዳሜ ላይ መድረስ፣ አግባብነት የሌለው ነገር ነው።
የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ችግሮች ለመምህር ጎይቶም ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑ ያምናል። መምህር ጎይቶም አሁን ያሉበትን ኃላፊነት ክብደት እስካሁን ድረስ ባላቸው የሥራ ቆይታ የተረዱት ይመስለኛል። ሀገረ ስብከቱ ላይ ያለው ችግር ያለ ሥር ነቀል ማስተካከያ በቀላሉ ይስተካከላል ማለት ይከብዳል። ሥር ነቀል ማስተካከያ የማድረግ ጥረት ደግሞ ከደጋፊ ይልቅ ተቃውሞን ማስተናገዱ የማይቀር ነው። ቢሆንም መምህር ጎይቶም ራሳቸውን አዘጋጅተው ተገቢውን የአሰራር ለውጥ ለማድረግ መትጋት ይኖርባቸዋል። በየደብሩ የተሰሩ ሕንጻዎች፤ የአስተዳዳሪ፣ የጸሀፊና የሰበካ ጉባኤ አባላት የግል መጠቀሚያ ከመሆን ወጥተው ለቤተክርስቲያን ጥቅም የሚውሉበትን መንገድ መፈለጉ የግድ ይሆናል። ሰዎች በቅርርብና በዝምድና ያለ በቂ ችሎታና ሙያ የሚቀጠሩበት መንገድ መቀጠል የለበትም። ትክክለኛ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሳይሰጥ ቀርቶ ህዝባችን ወንጌልን ከቃና ቲቪ አሳንሶ የሚያይበት መንፈሳዊ ማንነት መቀጠል አይኖርበትም። በየደብሩ ያሉ ካህናት ቃና ቲቪን ሰይጣን ከማለት ከመካከላቸው ያለውን ሰይጣን በጾምና በጸሎት አስወግደው ለስብከተ ወንጌል ስራ የሚሯሯጡበት አሰራር የግድ ያስፈልጋል።
በየደብሩ የሚሰበሰበው ገንዘብ ሙዳይ ምጽዋት እየተገለበጠ ለግል ጥቅም የሚውልበት አሰራር መቅረት ይኖርበታል። ለዚህም የሚረዳ ሲስተም መዘርጋቱ የግድ ይሆናል። በሀገረ ስብከቱ የሚሰሩ ሥራዎች መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች እንዲጎሉ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። የተለያዩ ጠቃሚ ትምህርቶችንና ስብከቶችን መስጠት ሊያደርጉት የሚችሉት ለውጥ አንድ ጅማሬ ነው። ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በተሻለ አቅም አደራጅቶ ከአንድ ቡድን ስሜት ወጥተው ለትልቅዋ ቤተክርስቲያን እንዲያስቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ሥራዎችን በተገቢ እና ብቃት ባላቸው ሰራተኞች ማሰራት ይጠበቅባቸዋል። በሙስናና በደላላነት የሚታሙትን ሰዎች ከአካባቢው ማራቅ ያስፈልጋል። ግልጽ የሆነ የሠራተኛ ቅጥርና የዝውውር መመሪያዎችን ማውጣት ይጠበቅባቸዋል። ለአብነት መምህራን ተገቢውን ትኩረት መስጠትም ያስፈልጋል። ደጅ ጠኚዎች የሚስተናገዱበት ግልጽ የሆነ አሰራር ሊኖር ይገባል። ሰዎች በግል ቂምና ጥላቻ ከሥራ ገበታቸው የሚፈናቀሉበት አሠራር ሊወገድ ይገባል።
መጋቤ ብሉይ እዝራ የተጻፈብዎት ሰብዕናዎን የሚነካ ጽሁፍ ፍጹም ተገቢነት የሌለው መሆኑን እገነዘባለሁ። የሰው ሀሳብ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር የማይገጥምበት በርካታ ነገሮች እንዳሉ ከእርስዎ በላይ ምስክር ይኖራል ብዬ አላስብም። ሰዎች ሁሌም ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም የማይለወጥ ቅን ጌታ ነው። ከእርሱ የሆነው መልካም ነገር ሁሉ ስላልጎደለብዎት ደስ ይበልዎት። የሰውን ተራ ጥላቻ እና ማጥላላት ግን ንቀው ይለፉት። እርስዎ ለብዙዎቻችን በብዙ መንገድ አርአያ መሆንዎት ጥርጥር የለውም። እንዲህ ያለው ተቃውሞ በዓላማዎና በሥራዎ ይበልጥ እንዲያጠነክርዎ እጸልያለሁ።
መምህር ጎይቶም ትከሻዎትን ያስፉ። የጀመሩት ጉዞ ቀላል አይደለምና ከየአቅጣጫው ተቃውሞና ድጋፍ ማስተናገድዎ አይቀርም። ምንጊዜም ግን ትክክለኛውን ሥራ ለመስራት ይሞክሩ። በየብሎጉ የሚሰሙት ተቃውሞ ተስፋ ሊያስቆርጦት አይገባም። ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃውሞ የማይቀርብቦት እጅዎን አጣጥፈው ከተቀመጡ ብቻ ነው። ለመስራት ይንቀሳቀሱ ሥራ ይስሩ። ነገር ግን ነገ ኅሊናዎት የማይወቀስበትን ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም እና ሰዎችን ለቤተክርስቲያን የሚያተርፍ ሥራ ይስሩ። ለዚህም ታላቁ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር እንዲረዳዎት እጸልያለሁ።
ለአባ ሰላማ ብሎግ
ራስና ጅራት የሌለውና ለሚዲያ የማይመጥን ጸሁፎችን ማስተናገድ እንድታቆሙ ላስገነዝባችሁ እወዳለሁ። ዓላማችሁ ከእኔ ከጸሀፊው ዓለማ ጋር እንደማይገጥም አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ እንደማስበው አንድታስቡ አላስገድዳችሁም። ግን ምንም አይነት ጽኁፍ ስታወጡ ተዓማኒነትን በማይሸረሽር መልኩ ብታደርጉት መልካም ነው። የሚዲያ ፓሊሲ ቢኖራችሁና የዘገየንም የተላከላችሁን ሁሉ ጽኁፍ ከማውጣት እውነተኛነቱን በተለያየ አቅጣጫ መዝናችሁ ብታወጡት መልካም ይሆናል። ሙያና ልብ ካላችሁም ስለተላከላችሁ ብቻ ባወጣችሁት ጽኁፍ ላይ የፈጸማችሁትን ስህተት አምናችሁ ይቅርታ ጠይቁ።

7 comments:

 1. reseneable enough.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Good reseneable idea .

   Delete
 2. በመጀመሪያ ደረጃ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ግዛት ነው፣ በመሆኑም ፓትርያርኩ ካሉበት ጎሳ ሥራ አስኪያጅ መመደቡ አዲስ ነገር አይደለም፤ ጎይቶምም ቢለቅ የሚመደበው ገ/መድህን ነው፤፤ ግን በጣም ያሳፍራል፡፡ በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የጎጠኞች መነኃሪያ መሆንዋ!! ወዳጆቻችን ዋናውን የጎጠኝነት ችግር ሳትኮንኑ እነ የማነን ስትጥሉ ስታነሱ ብትውሉና ብታድሩ አይገባንም ፡፡ የጎጠኝነት መንፈስ በቅድሚያ ይነቀል!! አለበለዚያ አዘሉም አንጠለጠሉም ያው ተሸከሙ ነው፡፡የእናቴ ልጅ እናቴ ጎጠንነትን ተሸክማ እስከመቼ››››››

  ReplyDelete
 3. በየደብሩ የተሰሩ ሕንጻዎች፤ የአስተዳዳሪ፣ የጸሀፊና የሰበካ ጉባኤ አባላት የግል መጠቀሚያ ከመሆን ወጥተው ለቤተክርስቲያን ጥቅም የሚውሉበትን መንገድ መፈለጉ የግድ ይሆናል። ሰዎች በቅርርብና በዝምድና ያለ በቂ ችሎታና ሙያ የሚቀጠሩበት መንገድ መቀጠል የለበትም። ትክክለኛ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሳይሰጥ ቀርቶ ህዝባችን ወንጌልን ከቃና ቲቪ አሳንሶ የሚያይበት መንፈሳዊ ማንነት መቀጠል አይኖርበትም። በየደብሩ ያሉ ካህናት ቃና ቲቪን ሰይጣን ከማለት ከመካከላቸው ያለውን ሰይጣን በጾምና በጸሎት አስወግደው ለስብከተ ወንጌል ስራ የሚሯሯጡበት አሰራር የግድ ያስፈልጋል።
  በየደብሩ የሚሰበሰበው ገንዘብ ሙዳይ ምጽዋት እየተገለበጠ ለግል ጥቅም የሚውልበት አሰራር መቅረት ይኖርበታል። ለዚህም የሚረዳ ሲስተም መዘርጋቱ የግድ ይሆናል። በሀገረ ስብከቱ የሚሰሩ ሥራዎች መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች እንዲጎሉ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

  ReplyDelete
 4. I was sad about the previous article. Thank you for this one.

  ReplyDelete
 5. አስተዋይ፡ መካሪ፥ ዘካሪ፥ አበራታች፣ በመልካም ገሳጭ አባቶችን አኑርልን። አሜን!!!

  ReplyDelete
 6. ETHIOPIA has been established international standard constitution. Thanks to TPLF (EPRDF) on the contrary an enemy of peace terrorist MK demolished the credibility and the moral ethics of our church father with out any eviedence just simply creating alleged and attacking those candidate of bishops falsehood accusation. Why they are not sue MK ?

  ReplyDelete