Thursday, July 21, 2016

ቤተክርስቲያንን አንገት ያስደፋ አስመራጩ ኮሚቴና አሳፋሪ ሥራዎቹየጵጵስና አስመራጭ ኮሚቴው የተሰጠው የጊዜ ገደብ ሐምሌ 30 ቢሆንም የ15 ቀን የጊዜ ገደብ ይሰጠኝ ማለቱን ተከትሎ በርካታ ነገሮችን እየታዘብን ነው፡፡ በዋናነት እጩ ሆነው ከገቡትና እጅግ ጠንካራ ከተባሉት አባቶች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን አያሠሩኝም፣ አብሬያቸው መጓዝ አልችልም በማለቱ ምክንያት፣ ከኮሚቴዎቹም አንዳንዶቹ የእነዚህ አባቶች መታጨት ስላሳሰበው የጊዜ ገደቡ ካለቀ በኋላ የ15 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ጠይቆ ማቅ የዘረዘረውን የእነዚህን አባቶች ኃጢአት በሐራ ላይ ማስዘርዘሩን ተያይዞታል፡፡
በተለይ በተጨመረው ጊዜ በኮሚቴው ስም እየተሠራ ያለው ዋና ሥራ ከኮሚቴው አባላት አንዳንዶቹ እና ማቅ በመተባበር የእጩዎችን ኃጢአት በማቅ ብሎግ በሐራ ላይ መዘክዘክ ሆኖአል፡፡ በምእመናን ስም ተሰጠ የሚባለውን በማቅ ሰዎች ተቀነባብሮ የሚቀርብለትን “የምእመናን አስተያየት” ማንበብና እነዚሁ አንዳንድ የኮሚቴው አባላት የፈሯቸውንና ማቅ ስም የለጠፈባቸውን ሰዎች በሐራ በኩል እያሰደበ ይገኛል፡፡ ይህንን ይዞም እነዚህ ሰዎች በርካታ ችግር አሉባቸውና ከዕጩነት መውጣት አለባቸው ብሎ ከዕጩነት ውጪ እያደረጋቸው ነው፡፡

የኮሚቴው አንዳንድ አባላትና ማኅበረ ቅዱሳን እየተናበቡ ለመሥራታቸው ብዙ ማሰብ አያስፈልግም፡፡ ማቅ በምእመናን ስም ለኮሚቴው የሚሰጠውን “መረጃ” ኮሚቴው ጠዋት ተቀበልኩ ካለ በኋላ ከሰዓት እነ አባ አብርሃም፣ አባ ዲዮስቆሮስ፣ ወዘተ… አማካይነት ወደሐራ ይልኩታል፡፡ በትናንትናው ዕለት መርጠናል ያሉትን የ32 ሰዎች ስም ዝርዝር 9፡00 ሰዓት ላይ በመጀመሪያ የላኩት ወደ ሐራ ሲሆን ፓትርያርኩ ጋር የደረሰው ግን 11፡00 ሰዓት ላይ ነው፡፡ ይህም ከኮሚቴው አባላት መካከል ይህን ስራ የሚሰሩት አንዳንዶቹ ከማቅ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሲሰሩ መቆየታቸውንና በብዛት ለማቅ ይጠቅማሉ የተባሉትን ለማካተት ሲሰሩ መክረማቸውን ነው የምንረዳው፡፡   
የእኛ ጥያቄ ከዕጩዎቹ መካከል ኃጢአታቸው የተዘረዘረውና ከዕጩነት እንዲቀሩ የተደረጉት መነኮሳት ወደፊት ምን ሊሆኑ ነው? ማቅ በዘረዘረው ኃጢአታቸው መሰረትስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በማገልገል ሊቀጥሉ ይችላሉ ወይ? ወይስ ሌላ እርምጃ ይወሰድባቸዋል? ነው ወይስ የተዘረዘረው ኃጢአታቸው ጳጳስ ከመሆን ብቻ ነው የሚያግዳቸው? ይህ መረጃውን እያሾለከ ለሐራ የሚልከው የአባ አብርሃም አንጃም ሆነ ማኅበረ ቅዱሳንን ትዝብት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ለመሆኑ እነዚህን ዕጩዎች እንዲህና እንዲያ ናቸው ብሎ ለመበየን እነ አባ አብርሃም ሞራሉን ከወዴት አገኙት ይሆን? የሚገርመው እስከ አሁን ይህንና ያንን ናቸው፣ እንዲህና እንዲያ ሰርተዋል ተብለው የተወነጀሉት እጩዎች፣ ከተባሉትና ከሰሩት በላይ ከኮሚቴው አባሎች ከጳጳሳቱ በአንዳንዶቹ የተሠሩት በደሎች በርካታ ናቸው፣ ለዚያውም በጵጵስና ውስጥ ሆነው፡፡ ታዲያ እነርሱ በዐይናቸው ውስጥ የተጋደመውን ግንድ ሳይመለከቱ በዕጩዎቹ ዐይን ውስጥ ጉድፍ ለማየት እንዴት ደፈሩ?
ለምሳሌ፡- አባ አብርሃም ሁሌ መስከረም ወር ለርኩሳን መናፍስት በግ ያርዳሉ ከዓመት በፊት አንድ ቀን ያስለመዱትን ዘለውት በተሳሳተ መንገድ መስዋእት አቅርበው አፋቸው ተጣሞ እንደነበር የታወቀ ነው፡፡ በሴት በኩልም ብዙ ችግር ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡
አባ ሣዊሮስ ሰበታ ቤተ ደናግል ጠባባት ገዳም የምታድግ ልጅ፣ እንደገና ምስካየ ሕዙናን ወንድማቸው ጋር የሚያድግ ልጅ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ አቃቂ ውስጥ ባለግሮሠሪ ሴት እንደገና በሰበታ አማኑኤል የሰበካ ጉባኤ ሊቀመንበር የሆነች ሴትን በውሽምነት ይዘዋል፡፡ ከዚህ ሌላ የሙስና ቅሌትም አለባቸው፡፡
አባ ዲዮስቆሮስም አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ዓይነ ውሃው ቁርጥ እርሳቸውን የመሰለ የታወቀ ልጅ አላቸው፡፡ በፍቅረ ንዋይ የሰከሩ መሆናቸውም ይታወቃል፡፡ ሚስቶቻቸውንም ሲያደባድቡ ጭምር የነበሩት እነዚህና መሰሎቻቸው ጵጵስና ሲሾሙ እኮ መንፈሳውያን አባቶች በወቅቱ እነዚህን ጳጳስ ከምናደርጋቸው ብንድራቸው ይሻላል ብለው ነበር፡፡
ዛሬ ታዲያ በምን ተሽለው ነው ማኅበረ ቅዱሳን ያቀረበባቸውን ክስ እያደመጡ፣ እየፈረዱ፣ ብሎም ከጵጵስናው ይውጡ እያሉ ለሐራ ስማቸውን አጥፉልን ብለው መረጃ የሚሰጡት? እንዲህ ሲባል እንዲህ ያለ ነውር ያለባቸው ሰዎች ይሾሙ እያልን አይደለም፣ በፍጹም! ነገር ግን ዕጩ በመምረጡ ሂደት በአንዳንድ መነኮሳት ላይ የቀረበው ክስ መነኮሳቱ በተባለው ነውር ስለተገኙ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ለማቅ የማይመቹና ማቅን ሥርዓት ሊያስይዙ የሚችሉ መሆናቸው ከወዲሁ ስለታወቀ ነው፡፡ 
አሁን እያየን ያለው የቀሩት እጩዎች አስተዛዛቢ አሳዛኝ አሳፋሪ ነገር ያለባቸው ቢሆኑም የማህበሩ ደጋፊ ስለሆኑ ብቻ እየተተቹ አለመሆናቸውን ነው፡፡ ለምሳሌ ማቅ የእኔን ጥቅም ያስጠብቁልኛል ብሎ ዕጩ ውስጥ እንዲገቡ ከተሟሟተላቸው መካከል፡-
1. መነኩሴ አግብተው እየኖሩ ያሉ
2. የትውልድ ቦታቸውን አስቀድመው አፍረውበትና የዚያ አገር ልጅ ነኝ ማለትን ሲጸየፉ የነበሩና አሁን  ግን ኮቦታው ሲገኝ እዚህ ነው የተወለድኩት ብለው እየተወዳደሩ ያሉ፣
3. በምንኩስና ውስጥ ወልደው ልጆቻቸውን በዘመዶቻቸው ቤት የሚያሳድጉ
4. ከቤተክርስቲያን አካውንት ውስጥ ገንዘብ አውጥተው ለነጋዴ በአራጣ የሚያበድሩ
5. የእነሱ አልበቃ ብሎ ለጓደኞቻቸው መነኮሳት ሴት የሚያቃጥሩ፣
6. ድንግልናን በብር የሚያፈላልጉ፣
7. ሀገሬ ሸዋ ሃይማኖቴ ማቅ ብለው አፋቸውን ሞልተው የሚናገሩ በእጩዎች ስም ዝርዝር ውስጥ አይተናል፡፡ ስለእነዚህ ግን ብዙ ነውር እያለባቸው እንኳን የተባለም ሆነ የተፃፈ ነገር የለም፡፡ እነዚህን የማቅ ምልምሎች ከዕጩነት ወጡም አለፉም ማን መሆናቸውን ወደፊት እንመለስበታለን፡፡
ኮሚቴው እነዚህን ገና ሲጠቆሙ ለዕጩነት አይመጥኑም ብሎ ማባረር ሲገባው፣ ደገኞቹን፣ እምነት፣ ሕሊና፣ ሕይወት ያላቸውን ለማስወጣት ሲሉ ብቻ በገፍ የሚቀርብላቸውን የማቅ “መረጃ” መልሰው ለማቅ ብሎግ ለሐራ በመስጠት ከዕጩነት እንዲወጡ አድርገዋል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ የኮሚቴው አንዳንድ አባላት የእብድ ሥራ ነው የሠሩት፡፡ አንድ ሰው አብዷል የሚባለው ሦስት ነገር ሲጐድለው ነው ይባላል፤ ይኸውም
1.     ቀና ብሎ አይቶ እግዚአብሔርን ካልፈራ
2.    ግራና ቀኝን ተመልክቶ ሰውን አይቶ ካላፈረ
3.    የራሱን ህሊና ማዳመጥ ከተሳነው አብዷል ይባላል፡፡
አንዳንድ የኮሚቴው አባላት አሁን እየሠሩ ያለው ሥራ ይህን የእብደትን መንገድ የተከተለ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት ትተዋል፤ ሰውንም አይተው አያፍሩም፤ የሚገርመው ራሳቸው ይከሰሱበት የነበረውን ነውርና እየቀረበባቸው የነበረውን ክስ እነርሱም በተራቸው እየሰሙ ሲፈርዱ ሲያስፈርዱ መኖራቸው ህሊናቸውን ማዳመጥ እንደተሳናቸው ያሳያል፡፡ እንደዚህ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሳፋሪ ነገር እየሠራ ያለ ኮሚቴ ያለ አይመስለንም፡፡
በሙሴ ዘመን ኮሚቴ ቢኖር ኖሮ እስራኤላውያን ከግብፅ አይወጡም ነበር ይባላል፡፡ በዚህ ኮሚቴ አስመራጭነት እውነት ጵጵስና ወደ ቀደሞ ክብሩ ይመለሳል? የሚለውም አጠያያቂ ነው፡፡ የካህናትና የምእመናን አስተያየት የተሰጠበት መሆኑ መልካም ጅምር ቢሆንም ምእመናንና ካህናት በተገቢው መንገድ እንዳልተሳተፉበትና ማኅበረ ቅዱሳን በምእመናንና በካህናት ስም በታጩት አባቶች ላይ እርሱ የሚፈልገውን እንዳደረገ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ መንገድ በታጩት በብዙዎቹ ቤተ ክርስቲያን እረፍት ታገኝ ይሆን? ፍልሰቱንስ የሚገታ ጳጳስ ያስመርጡልናል? ወንጌልን የሚያስፋፋ አባት ይሾሙልናል? ወይስ የቤተ ክርስቲያንን ሀብትና ንብረት የሚቀራመት፣ የአባትህ ቤት ሲወረር አብረህ ውረር የሚል ጳጳስ ያመጡብናል? ወይስ ሀብትዋ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ብቻ ይዋል የሚሉ አባቶችን ይሰይሙልናል? ቤተ ክርስቲያንን ከማቅ ቅኝ አገዛዝ ነጻ የሚያወጣ አባት ወይስ ቤተ ክርስቲያኒቱ መኖር ያለባት ለማቅ ጥቅም ብቻ ነው የሚል ምንደኛ አባት ያመጡብን ይሆን? ለባከነው ምእመን እረፍት፣ ለባዘነው መንጋ መሰብሰብ፣ የነገን እያሰበ በፍርሃት ተውጦ ያለውን ምእመን በወንጌሉ የሚያሳርፈውን አባት ያሳዩን ይሆ? ወይስ ደግሞ ይህን ጵጵስና ያገኘሁት ወይዛዝርትን አስቸግሬ የቤተክርስቲያንን ካዝና አራቁቼ መቶ ሺህዎች ከፍዬ ነውና ስለዚህ ይህን መመለስ ይጠበቅብኛል የሚልና ለዚህም ተግቶ ዝርፊያን የሚያሳድድ አባት ይሾሙብን ይሆን?

ቤተክርስቲያንን አንገት ያስደፋ አስመራጩ ኮሚቴና አሳፋሪ ሥራዎቹ
የጵጵስና አስመራጭ ኮሚቴው የተሰጠው የጊዜ ገደብ ሐምሌ 30 ቢሆንም የ15 ቀን የጊዜ ገደብ ይሰጠኝ ማለቱን ተከትሎ በርካታ ነገሮችን እየታዘብን ነው፡፡ በዋናነት እጩ ሆነው ከገቡትና እጅግ ጠንካራ ከተባሉት አባቶች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን አያሠሩኝም፣ አብሬያቸው መጓዝ አልችልም በማለቱ ምክንያት፣ ከኮሚቴዎቹም አንዳንዶቹ የእነዚህ አባቶች መታጨት ስላሳሰበው የጊዜ ገደቡ ካለቀ በኋላ የ15 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ጠይቆ ማቅ የዘረዘረውን የእነዚህን አባቶች ኃጢአት በሐራ ላይ ማስዘርዘሩን ተያይዞታል፡፡

19 comments:

 1. የሚሾሙት ለኦርቶዶስ ቤተክርስቲያን እናንተ ምን አገባችሁ?

  ReplyDelete
 2. እኔ በበኩሌ አያገባኝም።ቤተከርስቲያን ክብሯን ካጣች ሰነበተች።መፅሀፍ እንዳለ የእራሳችሁን መዳን ፈፅሙ።ዘመኑ ከፍቶአል።መምጫው እንደደረሰ እናስተውል።የሚፈርደው ይመጣል።ተዘጋጅተን እንጠብቅ።

  ReplyDelete
 3. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ያሸንፋል። እናንተ የቅዱሳን እና የመቤታችን ጠላቶች። ደግሞም የተደበላለቀባችሁ ውሸትን በማውራት ነገር ለማስቀየር የምትሹ። ደግሞም በዚሁ ብሎግ ታምረ ማርያምን ገድለ ቅዱሳንን አቡነ ተክለሐይማኖትን እየነቀፋችሁ ጽፋችሁ አስነበባችሁን። ዛሬ ደግሞ አዛኝ መስላችሁ ስለ ቤተክርስቲያን እንደሚያስብ ያቀረባችሁት የነቀፌታ ጽሑፍ አያስገርምም። ምክንያቱም በቅዱሳኑ ነቀፌታን ለመጻፍ ያነሳሳችሁ መንፈስ በኮሚቴው ላይ ጸያፍን ቢያጽፋችሁ አይገርምም። ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ሆይ ለተክለሃይማኖት ለእመቤታችን በክፋቱ ያልተኛ የዚህ መንፈስ ቢያመሰግኖት እንኲን ከልቡ እንዳልሆነ በመንፈስ ቅዱስ እንደሚመረምሩት እርግጠኛ ነኝ። ያልተሳካለት አባ ሰላማ ብሎግ።

  ReplyDelete
 5. ስማ አንተ ተጠራጣሪ ቤተ ክርስቲያንን ለመውረር ይህንን ያክል ሃጢአት የሌለባቸውን እነ አቡነ አብርሃምን አቡነ ዲዮስቆሮስንና ሌሎችንም ብትሳደብ የሚደንቅ አይደለም ቅዱሳንን የምትሳደብበት የዘንዶው አፍ ተሰጥቶሃልና አረ ራሱን የክብር ባለቤት እግዚአብሔርን ክብሩን ስትነካ መቼ አፈርክና..... ያልካቸው አባቶች ያለ ነውራቸው ነውር አወጣህላቸው እንጂ እንዲህስ አይደሉም...... አይደሉም እንጂ ቢሆኑ እንኳን ከመናፍቅ ይልቅ ኃጢአተኛ ይሻላል..... ደፋሩ አረ መናፍቃንን በጨለማ ስትመለምል የከረምከው ማንም ሳይቃወመኝ አስሾማለሁ ብለህ ኖሯልን............

  ReplyDelete
  Replies
  1. I accept your comment on ABA selama

   Delete
 6. kikikikikikikikikikikikikikikikikikikiki aba selamawoch yebeg lemide lebsachihu yekidusan abatochachinin sim atatifu. kezaw kadarashachihu hidachihu chefiru.mahibere kidusan wuste new

  ReplyDelete
 7. ገና አንጀታችሁ ያራል.... የእናት ጡት ነካሸች፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትክክል ገና ድብን ይላል መናፍቅ ሁሉ

   Delete
 8. በጣም የሚገርምም የሚያሳፍርም ስራ ነው እየተሰራ ያለው።

  ReplyDelete
 9. Kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
 10. አያ በሬ ሆይ አያ በሬ ሆይ፤ ሣሩን አየህና ገደሉን ሳታይ፤
  ዘመኑ ሾላ በድፍኑ፤ ሥጋውያንም መንፈሳዊያንም ሁሉም አንድ ሆኑ፤
  ኩሉ ዐረየ ወኅቡረ ዐለወ ያልታደለ ዱቄት ከነፋስ ይጠጋል፤
  ጥቅሙ ይቅርና በኖ በኖ ያልቃል።

  ReplyDelete
 11. እኔ በበኩሌ በተቀደሰው ቦታ ርኩሰትን እያየሁ ነውና በቃኝ ብዬ ትቻለሁ የቤተክርስቲያንን ነገር፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሃድሶ ዓላማ እንዳንተ አይነት ሰው ማፍራት ነው:: የነሱ ፍሬ በመሆንህ በጣም አዝናለሁ!!!!!!!!!!

   Delete
 12. Tehadiso will be screened since it is hertic

  ReplyDelete
 13. ከመናፍቅ ሀጥያት ይሻላል አልክ?ሁለቱም አይሻሉም እይታህን አስተካክል !!

  ReplyDelete
 14. ወሬኛ። ወሬኛ።

  ReplyDelete
 15. Dirom ke kurnchit kurnchit ,ke amekala amekala,..yitebekal enji woyn aytebekim silehone ke enante ekuy migbarna ekuy andebet enji melkam negern antebikm .ye abiyen ekek wode emiye lekek endilu.......

  ReplyDelete
 16. My gut was telling me that Aba Abraham had no grace at all when he visited my church. I am waiting for him to come back and expose him in front of the vongregation.

  ReplyDelete