Sunday, July 31, 2016

የኤጲስ ቆጶሳቱ ዕጩዎች ጉዳይ እንደገና እንዲጤን እየተጠየቀ ነውየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከግብጽ ጥገኝነት ተላቃ ራስዋን በራስዋ ማስተዳደር ከጀመረችበት ከ1951 ዓ.ም. ወዲህ 6 ፓትርያርኮችን 121 ጳጳሳትን ሾማለች፡፡ በ5ቱ ፓትርያርኮች ዘመን የተሾመው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደዚህ ከፍተኛ ማዕረግ ሲደርሱ በተቻለ መጠን ቅዱስ ሲኖዶስ አስቦበት መክሮበት ይሾም ነበር፡፡
ባለፉት 10 ውስጥ ዓመታት በሞት፣ በእርጅና ያለፉትና መሥራት ያልቻሉትን ለመተካት ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ነገሩን በማንከባለል ብቻ ጳጳሳትን መሾም ሳይቻል በመቅረቱ እስከ 4 ሀገረ ስብከት በድርብ በመያዝ የቤተክርስቲያንን ካዝና በማራቆትና በማን አለብኝነት የተመደቡበትን ሀገረ ስብከት በቅጡ ሳይመሩ ተደርቦ በተሰጣቸው ሃገረ ስብከት ላይ ስማቸው ብቻ እየተጠራ ብዙ ክፍተቶችና የአስተዳደር በደሎች ሲደርሱ ዓመታት አልፈዋል፡፡
በዘንድሮው የርክበ ካህናት ስብሰባ ላይ ኤጲስ ቆጶሳት መሾም እንዳለባቸው ተወስኖ ይህን የሚያከናውን አስመራጭ ኮሚቴ ቢሠየምም የተጣለበትን ኃላፊነት ወደኋላ በመተው በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሚያሳዝንና አንገት የሚያስደፋ በደል ተፈጽሟል፡፡ ከኮሚቴው አባላት መካከል አንዳንዶቹ እነርሱ በተሾሙበት መንገድ ሌሎችን ለመሾም ባደረጉት እንቅስቃሴ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊት ፈጽመዋል፡፡ ከተፈጸሙት አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊቶች መካከል የሚከተሉትን እነጠቅሳለን፡፡ 

ውድድሩ ጥሎ ማለፍ እንዲሆን አድርገዋል
የዕቹዎቹ ወድድር ጥሎ ማለፍ እንዲሆን በዋናነት ያገለገለው ገንዘብና ለማኅበረ ቅዱሳን ያለ ታማኝነት እንደሆነ በገልጽ ታይቷል፡፡ በእጩ ውስጥ የቀረቡት አንዳንድ አደገኛ መነኮሳት ይበልጠኛል ያሉትን በሙሉ ለእነ አባ አብርሃም ባቀረቡት ገንዘብ ጥለው እንዲያልፉ ዕድሉ ተመቻችቶላቸዋል፡፡ ለዚህም የተጠቀሙበት ዘዴ ገንዘብ ከፍለው በማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ በሐራ ላይ የተቀናቃኞቻቸውን ስም የማስጠፋት እኩይ ሥራ ሠርተዋል፡፡ ይህን እኩይ ተግባር ካስፈጸሙ የስም መነኮሳት መካከል አባ ገብረሥላሴ ጐበና ይጠቀሳሉ፡፡ እኚህ ግለሰብ ከዚህ በፊት ከተጠቀሰው ክፉ ሥራቸው በተጨማሪ በምስካየ ሕዙናን መድኃኔ ዓለም፣ በኬንያ፣ በአውስትራሊያ፣ በሱዳን፣ በጅቡቲ የፈጸሙት ወንጀል ከባድ ነው፡፡ ግለሰቡ ከምስካየ ሕዙናን ገዳም 20 ሚሊዮን ብር ተበድረውና የባንክ ባለእዳ ሆነው ነበር ወደ አውስትራሊያ የሄዱት፡፡ ከጅቡቲ ምዕመናን ተጻፈ የተባለው ደብዳቤ ምንም እንኳን ኮሚቴው እጅ ባይገባም አዲስ አበባ ውስጥ አቧሬ በተባለው አካባቢ በግልጽ ሐናና ወርቄ የተባሉ ሴቶች በሚስትነት ይዘውና ሱቅ ከፍተው ሲያደባድቡ እንደነበር እማኞች ይገልፃሉ፡፡ ግለሰቡ በከፈሉት ከፍተኛ ጉቦ ምክንያት እጩ ውስጥ “ሀ” ተብለው ሲጠቆሙ በማግስቱ ከካርቱም አዲስ አበባ በመግባት ይኸው እስከ አሁን ደብራቸውን ትተው በሌሎች አባቶች ላይ ሸፍጥ እያሠሩ ይገኛሉ፡፡ ኬንያ እያሉም የሱማሌ ተወላጅ የሆነች ሴት ይዘው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቸርችል ጐዳና ቤት ተከራይተውላት እንደነበር ይታወቃል፡፡ እኚህን እንኳን ለጵጵስና ለትዳርም የማይመጥኑ ስመ መነኩሴ ወደ ጵጵስና ማምጣት ለቤተ ክርስቲያን ወዮታ ማቆየት ነው የሚሆነው፡፡
የኮሚቴው ምስጢር አባካኝነት
በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በመጋረጃ ተከልለው ምእመናን ንስሐቸውን ለካህን ሳይታዩ መናዘዝ የተጀመረው ካህናቱ ምስጢር ማውጣት በመጀመራቸው እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ይህን ታላቅ ኃላፊነት የተቀበለው አስመራጭ ኮሚቴ በተጠቋሚዎች ላይ ችግር ካለ ንገሩኝ ባለው መሠረት ችግር አለባቸው እየተባለ የቀረቡለትን “ማስረጃዎች” ተቀብሎ ችግሩን በትክክለኛና ፍትሐዊ መንገድ ማጣራትና (ይህ ችግር አለባቸው የተባሉትን መነኮሳት ማነጋገርንም ይጨምራል) ጉዳዩን በጥብቅ ምስጢር ይዞ ወደሰየመው ቅዱስ ሲኖዶስ ማቅረብ ሲገባው ከጳጳሳት በማይጠበቅ ሁኔታ አሳልፎ ለሐራ ብሎግ ሰጥቶ የተጠቆሙትን መነኮሳት እንዳያይድኑ እንዳይሞቱ አድርጎ ከፍተኛ በደል አድርሶባቸዋል፡፡ ይህ ለጊዜው ስማቸው በብሎግ እንዲጠፋ በተደረጉት መነኮሳት ላይ ከፍተኛ ሐዘንና የልብ ስብራት ቢሆንም  በቤተ ክርስቲያኒቱ የክህነት ሕይወት ላይም ከፍተኛውን ጥላ አጥልቶ አልፎአል፡፡ ከዚህ በኋላ ለእነ አባ አብርሃም  ንስሐውን የሚናዘዝ ማን ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኖአል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ የዚህን የኮሚቴ አሳፋሪ ተግባር በዝምታ ያልፈውን ይሆን? ወይስ ይጠይቃል? መሆን የነበረበትማ ሲኖዶስ ይህን ትውልድን አንገት ያስደግፋውን የአባ አብርሃምን እንጃ ማውገዝና ክህነታቸውን መያዝ ይጠበቅበት ነበር፡፡
በኮሚቴው ውስጥ ያሉ ሲሞናውያን
ይህ ኮሚቴ እንደተሰየመ ነው እነ አባ አብርሃም፣ አባ ሳዊሮስ ደላላ አሰማርተው ገንዘብ አላቸው ብለው ያስገቡአቸውን መነኮሳት አምጡና እጩ ውስጥ እናስገባችኋለን ብሎም ጵጵስናውን እናሰጣችኋለን በማለት የዘረፏቸው፡፡ ለዚህም በደላላነት ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊው ፋንታሁን ሙጪ እንደሆነ ብዙዎች ይመስክራሉ፡፡ በተለይም ከጀርመን ከታጩት ከአባ ብርሃነ መስቀል ጋር በተያያዘ ስሙ በስፈጽ ይነሣል፡፡
ይህ የጀርመኑ አባ ብርሃነ መስቀል ኮሜርስ ተማሪ እያለ ጀምሮ ሜሮን የምትባል የሴት ጓደኛ የነበረችው ሲሆን አሁን ለቡ አካባቢ በሠራው ቤት በሰርቪስ ውስጥ አስቀምጦ ዋናውን አከራይቶታል፡፡ ኪራይ ቤቶች ውስጥ ሲሰራም ዘውዲቱ ህንፃ ላይ ክፍል ተሠጥቶት ሲኖር ወደ ጀርመን የመሄድ ዕድል ሲገጥመው ክፍሉን ለአባ አብርሃም ጠንቋይ ያስተላለፈው እርሱ ነው፡፡
ፋንታሁን ሙጩ ከጀርመኑ እጩ አባ ብርሃን መስቀል ከፍተኛ ገንዘብ ተቀብሎአል፡፡ ከአባ አብርሃም ጋርም አንድ ውለታ ተዋውሏል፡፡ ፋንታሁን ለጥቅምት የተቀጠረው የእንደራሴነቱ ኮሚቴ ውስጥ ስላለበት ከጀርመኑ ሰውዬ በደላላነቱ በወሰደው ገንዘብ አባ አብርሃምን እርስዎን ለእንደራሴነት ለማቅረብ ማኅበረ ቅዱሳን የቤት ሥራ ሰጥቶኛል፣ ኮሚቴው ፍላጐቱ ነው፡፡ ስለዚህ ከእርስዎ የሚጠበቀው አባ ብርሃነ መስቀልን ለጵጵስና ማብቃት ነው ብሎ እየወተወተ ይገኛል፡፡ ስለዚህ የአባ አብርሃምንና የፋንታሁን ሙጬን ተግባር ቅዱስነታቸው ሊያስቡበት ይገባል፡፡
ስለዚህ በኮሚቴው ውስጥ ለግል ጥቅማቸውና ለዓላማቸው ተግተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ እንደ አባ አብርሃም ያሉ ሲሞናውያን ቤተ ክርስቲያኒቱን ትተው ጵጵስናን በብር የሸጡትበት ሁኔታ በግልጽ ስለሚታይ በዚህ መንገድ የቀረቡት ዕጩዎች ጉዳይ እንደገና ሊጤን ይገባል፡፡ ምርጫውና ሹመቱም በዚህ ሁኔታ መከናወን የለበትም፡፡ አሁን እየታየ ያለው እንደ ጀርመኑ አባ ብርሃነ መስቀል፣ እንደ ካርቱሙ አባ ገ/ሥላሴ ዶላር በአቁማዳ ያቀረቡትን ለማሳለፍ፣ ዳር ዳር ሲባል፣ እንደ አባ ኅሩይ አይነቱ ደግሞ ካቀረቡት አነስተኛ ገንዘብ የተነሣ ቤትህን ሽጥ ተብለው እየተገፋፉ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ብር ከፍለው እርግጠኛ የሆኑትና አሁን ግን ከምርጫው የተገለሉት የጐፋ ገብርኤል አለቃ አባ ገ/ሥላሴ ጠባይ ሁለት ነጭና ጥቁር የጳጳስ አስኬማ አስፍተው የነበረ መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን?
ካህናቱና ሕዝቡ ያዘነበት ኮሚቴ መሆኑ
ካህናቱና ሕዝቡ አሁን እያለ ያለው በተለይ የኮሚቴው አንዳንድ አባላት በምስጢር የተሰጣቸውን አስተያየት አሳልፈው ለብሎግ በማውጣታቸው በደለኞች ናቸው ከተባሉ እጩዎች በላይ ይህ ከፍተኛ ኃጢአት ነውና ኮሚቴው በሕገ ቤተክርስቲያን ሊጠየቅና ሊበተን ይገባል፡፡ እርሱ ያቀረባቸው እጩዎችም በምን መስፈርት እንደቀረቡ፣ የጣላቸውን ዕጩዎችንም በምን መስፈርት እንደጣላቸው መጠየቅ አለበት በሚል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጥብቅ ሊያስብበትና ብሎም ሊሠርዘው እንደሚገባ እየተወያዩ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህን ድርጊት የፈፀሙት ተራ ሰዎች ሳይሆኑ በጳጳስ ደረጃ የሚገኙ ናቸውና፡፡
በተለይ አባ አበርሃምን በተመለከተ ከራጉኤል አካባቢ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቀሙት የራጉኤል ሱቆዎች በቀድሞው አባ ቃለ ፅድቅ በአሁኑ አባ አብርሃም ሲገነቡ በርካታ ቁልፎች ከመሸጣቸውም በለይ በእርሳቸው ፈራሚነትና ውል ተዋዋይነት ለእድሜ ልክ የተሰጠ የሱቅ ሰነድ ተገኝቷል፡፡ ይህንንም ለአንዲት ሴት ነበር የሰጡት፡፡ የራጉኤል አካባቢ ምእመናን ይህንና ሌሎችንም ማስረጃዎች በመያዝ የኮሚቴውን ሕገወጥ አሠራርና በተለይም የአባ አብርሃምን ሲሞናዊነት እየተቃወሙ ይገኛሉ፡፡
የገዳማትና የአድባራት አለቆች ተቃውሞ
የኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫ ጉዳይ አሁን አሁን እያነጋገረና ነገሩ እየገፋ መጥቶአል፡፡ በተለይ ዕውቀቱ፣ ጠንካራ አቅምና ክርስቲያናዊ ሕይወት፣ መንፈሳዊም አላማ ያላቸው፣ በልምድ የካበተ ሥራ ያላቸው ቆሞሳት በምርጫው አለመካተታቸው፣ በዚያው አንፃር ወሮበሎች፣ ቦዘኔዎች፣ ከሴት ውጪ አላማ የሌላቸው ቢያንስ በእልቅናና በግብዝና ያላለፉ ሰዎች ተካተው መገኘታቸውን የተመለከቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ኮሚቴው አሳፋሪ ሥራ ከመሥራቱም በላይ፣ እንደ ሀገር ደግሞ ማቅ በሲኖዶስ ውስጥ አባላቱንና ደጋፊዎቹን ለማብዛት ያመቻቻቸውን ሰዎች ያካተተ በመሆኑ አለቆች በጽኑ እየተቃወሙት ይገኛል፡፡
ፍፁም ከተሰጠው አላማ ውጪ የሄደው ይህ የአስመራጭ ኮሚቴ ሌላው ቢቀር በጫት ንግድ ላይ ሳይቀር የተሰማሩትን እኮ ነው ያካተተው፡፡ ስለዚህ ኃላፊነቱን የሰጣቸው ምልአት ጉባኤው ዝም እንደማይል ከሁኔታዎች መረዳት ይቻላል፡፡ የማይፈልጉትን ቀን አራዝመው አንዳንድ በማኅበረ ቅዱሳን የማይፈለጉትንና ጉቦ ያልሰጡትን አሰድበውና አላሟሉም ብለው ከምርጫ ውጪ እንዳደረጉአቸው ሁሉ አሁን ከያቅጣጫው በራሱ በኮሚቴው ላይ የፍትሐዊነት ጥያቄ አለን የሚሉ አካላት ብቅ ሲሉ፣ ነገሩን አጣድፈው 31 እጩዎቹን ማቅረብ ባልተገባም ነበር፡፡
ከታጩት ጥቄቶቹ እነሱ 1ኛ ለመውጣት የሌላውን ሹራብ ጐትተዋል፣ እነሱ ለመክበር ሌላውን አዋርደዋል፣ እነሱ የጵጵስና ልብስ ለመልበስ ሌላውን በሐራ ላይ አራቁተዋል፣ እነሱ ቆመው ለመሄድ ሌላውን ወንድማቸውን ጥለዋል፤ እነሱ ተተክለው ለመኖር ያድጋል ያሉትን በወሬ ቆርጠውታል፡፡ ስለዚህ ኮሚቴው ይበተን የእጩዎቹም ምርጫ ይሰረዝ እየተባለ ነው፡፡
የኮሚቴው አንዳንድ አባላት ከራሳቸው ጋራ የሚመሳሰሉትን መምረጣቸው
ይህ አስመራጭ ኮሚቴ ጥሩ ሰዎችን መምረጥና ማካተት ለምን አስጠላው? የሚል የሁሉም ሰው ጥያቄ ሆኖአል፡፡ ዝሙት በምንኩስናቸውም በጵጵስናውቸው መውለዳቸው፣ ጉቦኝነት፣ የኮሚቴው ጥቂት ጳጳሳት መለያ ነው፡፡ አሳዛኝ ነገር በየተመደቡበት ሀገረ ስብከት ከቀድሞ ቅምጣቸው አልበቃ ብሎአቸው እንደ ባንክ ቤት ገንዘባቸው በአደራ የሚያስቀምጡአቸው ቅምጦቻቸው በርካታ ሆነዋል፡፡
ከዚህ አስከፊ ሕይወታቸው የተነሣ እነሱም ልክ እንደ እነሱ ያሉትን በቁመናቸውና በመልካቸው የተሰፉትን “ቆሞሳት” የሲኖዶስ አባል ለማድረግና አመፀኞቹን ለማብዛት ተግተው ሠርተዋል፡፡ በጨለማ ውስጥ ያለ ሰው ብርሃንን ይጠላል ሲል ጌታ እንደተናገረው በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ እነርሱን የመሰለ እንጂ ጥሩ ሰው መካተት የለበትም ብለው የተማማሉ ይመስላል፡፡ ከዚህ የተነሣ በሕይወት በአላማ የሚመስሉአቸውን ለማካተትና ሌሎችን ለመግፋት ተገደዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ንቀዋል፣ ትተዋል፣ ረስተዋል፡፡ በእነሱ የተነሣ በዮዲት፣ በግራኝ፣ በጣሊያን ወረራ ከደረሰባት ግፍ የበለጠ ቤተክርስቲያንን በቁመናዋ ቀብረዋታል፡፡ እነሱም በምን አይነት መንገድ ወደዚህ ማዕረግ እንዳመጡ ከሥራቸው የተነሣ መገንዘብ ተችሎአል፡፡ በተለይም በዚህ አቅጣጫ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን የተፈጸመው ስሕተት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዘመን እንዳይደገምና ጨለማው የበረታ እንድሆን ቅዱስነታቸውና ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ ብፁዓን አባቶች በዚህ ጉዳይ ላይ ሊያስቡበት ይገባል፡፡

11 comments:

 1. የተዋጣልህ የልብ ወለድ ደራሲ ትሆን ነበር።
  የሌለ ታሪክ ትተርካለህ።
  ይህ የሚያመለክተው ተሐድሶዎች የማይፈልጓቸው አባቶች እንዳይገቡ ስም ለማጥፈት ሆን ተብሎ የተፈበረከ የሐሰት ወሬ ነው።

  ReplyDelete
 2. ‎ምነው የአባ ቀለሜንጦስንና የኄኖክንስ ጉዳይ ዝም አላችሁ ነው መረጃው አልደረሳችሁም

  ReplyDelete
 3. ፋንታሁን ማለት ስሙም ሰውነቱም ስራውም የገማ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ቢኖራት ኖሮ ለእርሱ የኃላፊነት ቦታ ባልተሰጠው ነበር፡፡ ምን ይደረግ ሁሉም እንትን ብቻ ሆነ አሉ የሚባሉትም እስትንፋስ አጡ!

  ReplyDelete
 4. Aba Mathias will be reject the fake candidates.

  ReplyDelete
 5. ይህቺ ጽሑፍ ከአባ ሀይለ ኢየሱስ የሽሮ ሜዳ አለቃ የተጻፈች ትመስላለች።
  ምክንያቱም ከእጩዎች መታወቅ ጀምረው ለእኔ በእጩዎች ዝርዝር በ31 ውስጥ አልመግባት የአባ ብርሃነ መስቀል መኖር ነው ብለው ሲናገሩ የሰሙና ስም ለማጥፋትም መዘጋጀታችውን ጭምር የሚቀርቧቸው ጓደኛቸው ሲናገሩ ስለስማሁ ነው።
  አባ ብርሃነ መስቀልን ወደ ጀርመን እስከሚሄዱ ድረስ በሚገባ አውቃቸዋለሁ። የተባለውን የሀሰት ወንጀል የአነበበ ሰው ሲነግረኝ ስቄ ነው ያለፍኩት። ቆይቼ ሳስበው የማያውቃቸው ሀሰቱ እውነት ሊመስለው ስለሚችል ይህን አስተያየት ለመጻፍ አሰብኩ።

  ኮሜርስ ሲማሩም ሆነ በቤተ ክህነት ሲሠሩ ረውቃቸዋለሁ።
  እንኳን እርሳቸው የተባለውን ሀጢያት ሊያደርጉ ሁላችንንም እንዴት ከሀጢያት እንድንሸሽ ሲመክሩን እንደነበር አድታውሳለሁ።
  ጀርመን ከሄዱ በኧኋላ ስላልው በቅርብ የሚያውቋቸ ምስክርነት ቢሰጡ ይሻላል።
  ሌላው የጠፋችሁት ደግሞ የስው ስም ሳታጣሩ ባታጠፉ ጥሩ ነው።

  ReplyDelete
 6. Why Mk do not wanted to provide any information about Yegude Mudaye Abaabrham Yetenkulla history?

  ReplyDelete
 7. Helo, Aba Selama. I dont like both you ,Menafikan, and Mahibere Kidusan because I am a member of Eth Orthodox Church. Association is not a way to save our soul. But Jesus saves us.Aba Selamawech, I completely accept your criticism on the 31 candidates, out of them 16 would be ordained as bishops.Honestly,let alone bishops some dont deserve to be a true husband because they make intercourse with more than one woman. This shows that orthodox religion is on the verge of collapse.

  ReplyDelete
 8. the other candidates like aba g/egziabher from Mekelle are recur-ted to be led by Mk like rho bot.

  ReplyDelete
 9. ስም ማጥፋት ሳይሆን መረጃውን በትክክል እየቃበላችሁን እንጂ እነ ቲጂ ግዜ

  ReplyDelete
 10. Mk an element of terror in Eotc, why not proof their allegations that damaged the immage of our church servant which was blatantly hurting our beloved father slept with women's? When? Where? Who? The alegation must have supported and proved with concise and clear bilogical evidence or DNA test, otherwise simply called falsehood.

  ReplyDelete