Tuesday, July 5, 2016

ለጵጵስና እነማን ይመረጡ ይሆን?

 Read in PDF
ለጵጵስና የሚታጩትን ለማቅረብ የተወሰነው የጊዜ ገደብ እየተጠናቀቀ ነው፡፡ በቅርቡ ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የጳጳሳት ሹመት እስካሁን ድረስ ለጵጵስና የታጩት መነኮሳት ብዛትና ማንነት ከቤተ ክርስቲያኒቱ በኩል በይፋ ያልተገለጸ ቢሆንም በማቅ ብሎግ በሐራ በኩል ተዛብተውና ተጋነው፣ በዚህ ውስጥ ማቅ ምን ትርፍ ሊያገኝ እንደሚችል በውል ባይታወቅም፣ ለእርሱ እንደማይመቹት ከወዲሁ ያወቃቸውን አባቶች ስም በልዩ ልዩ መንገድ ማጥፋቱን ተያይዞታል፡፡ ይህም በአስመራጭ ኮሚቴው ላይ ጫና ለመፍጠር ነው፡፡       
በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተሰየመው ኮሚቴ አማካኝነት እስከ ሰኔ 30/2008 ዓም ድረስ ለጵጵስና የሚመረጡትን አባቶች በተመለከተ የእጩዎች ሥም ዝርዝር በሚል በሀራ በኩል ወጥቶ ታይቶአል፡፡ ሀራ በመጀመሪያ ያወጣችው ስም ዝርዝር ብዛት 1ዐ8 ሲሆን ከኮሚቴዎቹ አንዳንዶቹ እንደመሠከሩት በወጣው ስም ዝርዝር ውስጥ በእነርሱ እጅ የሌሉ የመነኮሳት ስም በብዛት መውጣቱን ሲናገሩ ተደምጧል፡፡ ይሁን እንጂ ከ108 በአንድ ጊዜ ወርዳ 74 ናቸው ማለቷ ሐራ በጳጳሳቱ ምርጫ ላይ ሆነ ብላ እየሰራችው ያለ ነገር እንዳለ ያሳያል፡፡ 

ይህን ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቀውን ምስጢራዊ የሰዎች ዝርዝር ለማቅ ብሎግ ለሐራ ያቀበሉት የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም መሆናቸው ታውቋል፡፡ ሁኔታውን የተከታተሉ አንዳንዶች አሁን በእውነት ለአባ አብርሃም ንስሐውን የሚናዘዝ ኦርቶዶክሳዊ ይኖራል ወይ? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ጥብቅ ምስጢር ሆኖ መቆየት ያለበትን ጉዳይ ያለ ጊዜው ለዚያውም ኮሚቴው ከሚያውቀው ቁጥር በላይ የሆነ ቁጥር በመጨማመር ከጊዜው ቀድሞ መውጣቱ፣ ሰውዬው በቅዱስ ሲኖዶስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው ምሥጢር ሆኖ መቆየት ያለበትን ጉዳይ እንድታወጣ ለሐራ በመስጠታቸው ታማኝነታቸው ለሲኖዶስ ሳይሆን የአደባባይ ምሥጢር የሆነውን ጉዳቸውን ሸፍኛለሁ እያለ ለሚያስፈራራቸው ማቅ መሆኑን በገቢር አሳይተዋል፡፡
የማቅ ብሎግ ሐራ 108 ብሎ ከዘረዘራቸው መነኮሳት መካከል አንዳንዶቹ ጳጳስ ቢሆኑለት የተመኛቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ለምሳሌ በቅርቡ አሜሪካ ሄደው ከውጭው ሲኖዶስ ጋር ለመቀላቀል እና ጵጵስና ለማግኘት የሞከሩ ግን ልጅ እንዳላቸው ተነግሮአቸው ተመልሰው አ.አ. መጥተው ወደ ደብር እልቅና የተመለሱ “መነኩሴ” ይገኙበታል፡፡
በዚህ አጋጣሚ “እጩ ውስጥ አስገቡን እንጂ ጵጵስናውን እንደማናገኝ እናውቃለን” ብለው በዚህ ግርግር የእጅ መንሻ ገበያውን ላደሩት ለእነ አባ ዲዮስቆሮስ ዳጎስ ያለ ብር የሰጡም አሉ፡፡ አባ ዲዮስቆሮስ ዕጩ ውስጥ እንድትገቡ አደርጋለሁ ከተቻለም ትመረጣላችሁ እያሉ ከአንዳንድ መነኮሳት እጅ ጉቦ እየተቀበሉ እንደሆነ አንዳንድ እማኞች ይናገራሉ፡፡ እጩ ውስጥ ስማቸው ስለተገለጸ ብቻ በከፍተኛ ሩጫ ልመረጥ ነው ብለው የድግስ ብር የተቀበሉ የግል መኪና እንዲገዛላቸው የጠየቁ፣ ውድ የሆነ የግሪክ መቀደሻ ልብስ ግዙ ያሉ በዚች አጋጣሚ ከፍተኛ ብር ከሃብታም ንስሐ ልጆቻቸው ለማግበስበስ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህን እየሠሩ ያሉ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ እጩ የተባሉና በ108ቱ ውስጥ ስማቸው ከተጠቀሰው መነኮሳት አንዳንዶቹ አሁን ውሎአቸው የማቅ ሕንፃ ላይ ሆኖአል፡፡
ይህን ታላቅ ኃላፊነት የተቀበለው ኮሚቴ ከውጪው ሲኖዶስ መማር አለበት፡፡ የመጀመሪያው መማር ያለበት ነገር በማንኛውም መስፈርት ለጵጵስናው ይመጥናሉ ያላቸውን አባቶች ያለማንም ተጽዕኖ መምረጥ ነው፡፡ የውጪው ሲኖዶስ ማቅና መሰሎቹ ባለማወቅ ኑፋቄ ብለው በሚጠሩት መንገድ እግዚአብሔርን ብቻ የሚያመልኩትን (የሐዋርያት ሥራ 24፥14) በዕውቀታቸው፣ በኑሮአቸው በአገልግሎታቸው የተመሰከረላቸውን አባቶች ነው በአብዛኛው የሾመው፡፡ የሀገር ውስጡ ግን በዚህ ረገድ የተሳካለት መሆን አለመሆኑ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ በዚህ ውስጥ ጉቦ የተበላባቸው አንዳንዶች አሳብረው እንዳይገቡና ከዚህ የከፋ ነገር ቤተክርስቲያን ላይ እንዳይደርስ አስበው መስራት ያለባቸው ዛሬ ነው፡፡ ሐራ ስማቸውን ይፋ ካደረገችውና ዕጩዎች ተብለው ከተዘረዘሩት መካከል አንዳንዶቹ ለዚህ የሚመጥኑ ናቸው፡፡
የአገር ቤቱ ሲኖዶስ ከውጪው ሲኖዶስ መማር ያለበት ሌላው ነገር የዕጩዎችን ስም ዝርዝር በምስጢር እንዲያዝ ማድረግ ነው፡፡ የውጪው ሲኖዶስ እንኳን እጩዎች ቀርቶ ተሹአሚዎችን ሕዝብ ያወቀው ለበዓለ ሲመቱ ዋዜማ ነው፡፡ እስከ መቼ በእነ አባ አብርሃም፣ በነአባዲዮስቆሮስ በነአባሳዊሮስ ቤተ ክርስቲያን ትዋረዳለች? ለዚህ እኮ ነው የእነሱን ምሥጢር ራሳቸው መደበቅ አቅቶአቸው ለአደባባይ ላይ የሚሰጡት፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ጠንካራ አባቶች ቢመረጡ የሚያስመሰግኑ የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና የሚጠብቁ ከሙስናና ከነውር የፀዱ፣ በቤተክርስቲያን ሙያ የበለፀገ እውቀት ያላቸው ዝርዝሩ ውስጥ አይተናል፡፡ በአጠቃላይ ግን ዝርዝሩን እንደ ተመለከትነው “ብፁአን እነማን ናቸው?” ብሎ ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር አሁን ያሉትን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንደገለፃቸው “አንዳንድ ሰዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከትምህርት ብቃት አኳያ ሲመዘኑ ከፊሉ ብስልከፊሉ ጥሬከፊሉ የላመ ከፊሉ የተሸረከተአንዳንዶች ዓይናማዎች ሌሎች ተመሪዎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ …” ብሎአል (ገፅ 3ዐ)፡፡ አሁንም የእጩዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ያሉት በዚህ መልኩ የሚታዩ ናቸው፡፡ ነገር ግን ለማንም ሲባል ሳይሆን ለቤተክርስቲያን ጥቅም ሲባል ከጥሬው ብስሉን፣ ከተሸረከተው የላመውን፣ ከተመሪዎች ይልቅ ዓይናሞችን መምረጥ የተዋረደውን የጵጵስናን ክብር ወደ ቦታው ለመመለስ ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡  
በአንድ በኩል ለጵጵስና መመረጡ ቀርቶ መታጨት ካማራቸው መነኮሳት ጉቦ ሲቀበሉ የታዩት አባ ዲዮስቆሮስ ምርጫውን እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ቆጥረው ቢዝነሱን አጧጡፈውታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአቡነ ጳውሎስ አማካይነት ወደ አሜሪካ ተልከውና ኢትዮጵያ ለእርሳቸው እንዳሻቸው የሚወጡባትና የሚገቡባት ሀገር ሆና እያለ፣ ከዚህ ቀደም ግሪን ካርድ ለማግኘት ሲሉ የኢህአዴግ ወታደሮች ቤተሰቦቻቸውን እያስጨነቋቸውና በተለይ ወንድማቸውን ጌታቸውን እየተከታተሉት መሆኑን ጠቅሰው 33 ገጽ ደብዳቤ የጻፉት የቀድሞው አባ መላኩ የአሁኑ አቡነ ፋኑኤል ወደጵጵስና የመጡበት መንገድ በእውቀትና ለጵጵስና በተገባ ማንነት ባለመሆኑ ምክንያት በጊዜው አባ ፋኑኤልን አይደለም ያጰጰሰ ያመነኮሰ ነፍሱን አይማረው፣ እንዲሁም ጵጵስና እንደእርሳቸው ከሆነ በአፍንጫዬ ይውጣ ሲባል እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በዚህ መንገድ ጳጳስ የሆኑት አባ ፋኑኤል አሁን እንደሚታጩ ከሚነገርላቸው መካከል በጎ ራእይ ያላቸውና ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙ አባቶች እንዳይመረጡ ለማድረግ ጵጵስናቸውን መከታ በማድረግ የቻሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው፡፡ ለሁሉም አስመራጭ ኮሚቴው ጉቦ ሰጥተው ለመሾም የቋመጡትን ወደ ጵጵስና ቢመጡ በቤተ ክርስቲያን ላይ ምን ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ከወዲሁ በመገመት፣ እንዲሁም ጉቦ በልተው የበሉባቸውን መነኮሳት ለማሾም ጵጵስናቸውን ሊጠቀሙበት የተዘጋጁትን፣ ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለበሉት ገንዘብ የቆሙ ምንደኞች በመሆናቸው የእነርሱን ጥቆማ ውድቅ በማድረግ፣ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ አባቶች ወደጵጵስና እንዳይመጡ ተግተው እየታገሉ ያሉትን የቤተክርስቲያን ሸክሞችን ማግባባት ባለመቀበል፣ ለእግዚአብሔር፣ ለሰየማቸው ሲኖዶስ፣ ለቤተክርስቲያንና ለኅሊናቸው ታማኝ በመሆን ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡና በትክክለኛው መስፈርት ለጵጵስና ይበቃሉ ያሏቸውን አባቶች እንደሚሰይሙ ሁሉም ተስፋ ያደርጋል፡፡


9 comments:

 1. ሃሃሃ እንደናንተ አይነት ደደብ ደብተራ ጴንጤ አይቼም አላውቅም። የመጨረሻ ደደቦች ናችሁ። ትናንት ስለ አባ ፋኑኤል ምን ስትሉ ነበር? ዛሬ የምትፈልጉትን አላደርግም አሏችሁ? መሃይሞች።

  ReplyDelete
 2. enante degemo sele orthodox tewahdo mene agabachu

  ReplyDelete
 3. Thanks guys for your great educated articles. Why do not keep secret what they are doing or the process how select new bishops for our church.We all now the issues because of pool acknowledges leaders in our bishops and they weren't educated in administration system. Due that ever-times their information is leaking or they are not keep it secret. Too bad, weak leader killing our church members faith. They have to learn from exile snodos (sedetgn snodos) and from catholic church leaders how to keep all info secret.

  ReplyDelete
 4. ምነው በኢትዮጵያ ያሉት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሰኖዶስ ለእጩ ጳጳሳት ምርጫ በምስጥር መያዝ አቅቶዋቸው በየድህረ ገጹ በይፋ መለቀቃቸው እጅግ በጣም ያሳዝናል። እስከ መቼ ይሆን በኢትዮጵያ የሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት ምስጥር ከማውጣት የምቆጠቡት? ምስጥር መያዝ የአንድ መንፈሳዊ አባት ትልቁ የመንፈሳዊ ችሎታው መመዘኛ ነው። ወቅቱና ግዜው ስደርስ ለህዝቡ ወይንም ለድህረ ገጾች ይለቀቃሉ። በእኛዎቹ አባቶች ዘንድ ይህ ዓይነት ህይወት አልተለመደም። ለምን ከሌሎች አባቶች አይማሩም ይሆን? ለምሳሌ ከውጪው ስኖዶስ አባቶች፣ ከሌሎች ሀገራት ኦርቶዶስ አባቶች ግብጽ፤ ራሽያ ፤ አርመኖች፤ ግርኮች ፤ አርመን እና ካቶልክ አባቶች ምጥር አያያዝን መማር አለባቸው። በየግዜ የስኖዶስ ስብሰባ ስደረግ አጀንዳው አስቀድም ለማቅ ድህረ ገፆች አንዳንድ ደካማ አባቶች ምስጥሩ አሾልከው ያወጡታል እጅ አሳዛኝ ነው። ለዚህም ነው አብዛኛው የተዋህዶ ህዝብ ንስሀውን ለአባቶች መናገር ያቆመው። ይህ ሁሉ ከእውቀት ድክመት የመነጨ በሽታ ነው።

  ReplyDelete
 5. sile ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ke siltan mebarer altsafachihum satisemu kertachihu new yediablos ageligayoch aba selama

  ReplyDelete
 6. ጽሑፋችሁ ተራ የመንደር አሉባልታ ነው። ኧረ ከዚያም የወረደ ነው

  ReplyDelete
 7. በዘመኑ ዕውነትን የሚቀበል የለም እንጂ ቢኖር ማንም ወደ ሹመት ባላንጋጠጠም ነበር፡፡
  ሥርዓተ አልበኝነት ምግባረ ብልሹነት የዘር ልዩነት የሰፈነበት ዘመን በመሆኑ ነው። ካናት የፈሰሰ እስከ እግር ደረሰ እንደሚባለው ቤተ መቅደሱ ከላይ እስከ ታች የሌባ ዋሻ የቀማኛ ጋሻ ሆኗል፤ ይህም ይታወቅ ዘንድ ሰዉ ከዕውነት ውሸትን ከትኅትና ትዕቢትን ከእምነት ክህደትን መረጠ። በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ከመታረቅ መጨቃጨቅ ከመደጋገፍ መነቃቀፍ ታክሎበታል
  የበላችው ያገሳታል በላይ በላይ ያጐርሳታል። ያሉት እየተናኰሩ አላምርባቸው ብሏል እንደገና ሌላ አዬ ጉድ!ዕጹብ ዝንቱ ነገር ወመኑ ይክል ሰሚዖቶ ይህ ከባድ ነው ማን ሊቀበለው ይችላል ዮሐ.፮ ፷ (6.60)ዕውነት ወደ ጎን ካልተተወ በስተቀር፤

  ReplyDelete
 8. Ante Sim zirzirun keyet agegnehew?

  ReplyDelete
 9. Min chegeregne mania bimeret.yemiyadenege be wengel mamene bicha new.

  ReplyDelete