Thursday, July 7, 2016

ከደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ህዝብ ለኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ የቀረበ አስተያየትከደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ኢጲስ ቆጶሳት ተጠቁመዋል። እንደ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ነዋሪነታችን ከኛ ሀገረ ስብከት ሰዎች መጠቆማቸው አስደስቶናል። በተለይም ሶስቱ አባቶች ማለትም የሀይቁ አባት አባ ፍቅረ ዩሀንስ የደሴ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ጽጌ ስላሴ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ አባ ገብረስላሴ መጠቆም አስደሳች ነው። እነዚህ አባቶች በምንኩስናም ሆነ በገዳማዊ ህይወታቸው የተመሰገኑ ናቸው። በአስተዳደር ችሎታቸውም የተመሰከረላቸው ናቸው። ሥርዓተ ቤተክርስቲያንንም ሆነ የክህነነት አገልግሎትን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ መጠቆማቸው ተገቢ ነው።
አባ ገብረስላሴ የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እያሉ አስተዳዳሪነቱን ለቀው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ይሁኑ ሲባል የደብሩ ህዝብ አይነሱብን ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ እንደነበር ይታወቃል። አሰራሩ ግድ ይላል አማራጭ የለም ስለተባለ ብቻ ነው። ህዝቡ የሳቸውን መነሳት የተቀበለው። አባ ገብረሥላሴ በመንፈሳዊ ህይወታቸው እንከን አይገኝባቸው። በንዋይ ፍቅርና በሌላው ነገር አይታሙም። ትህትና ያላቸው እና አስተዳደራዊ ብቃታቸውም የተመሰከረለት ነው። አስተዳደር ብቃት ባይኖራቸው ኖሮ ህዝቡ አይነሱብን ብሎ ሰልፍ አይወጣም ነበር።
አባ ጽጌ የደብረ ቤቴል ቅድስት ስላሴና ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ ሲሆኑ በአስተዳደር ብቃታቸው ከፍ ያለ ደረጃ የደረሰ ነው። አባ ጽጌ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ህዝብ የታወቁ የልማት አርበኛ ናቸው። መኪናዎችን ለቤተክርስቲያን ያስገዙ ሲሆን ለቤተክርስቲያንዋ መገልገያ የሚሆን ህንጻም እያስገነቡ ናቸው። እኚህ አባት 42 ሰው የሚያስተናግድ ሽንት ቤት ያስገነቡ ሲሆን ለአብነት ተማሮዎችም ተጨማሪ ቦነስ በመስጠት ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ትልቅ አስተዋጽዖ አድርገዋል። የኑሮ ውድነቱን ከግምት በማስገባት ለካህናቱ ደሞዝ ያስተካከሉ ሲሆን የስብከተ ወንጌል አዳራሾችንም አስገንብተዋል። አባፍቅረ ዩሀንስም ቢሆኑ በመንፈሳዊ ህይወታቸው የተመሰከረላቸው እና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላው ናቸው።
የእነዚህ ሰዎች ብቃትና መንፈሳዊነት እንዳለ ሆነ በምን መመዘኛ እና ብቃት እንደተጠቆሙ ያልገባን ሰውም በጥቆማው ላይ ስላሉ ተገርመንም ተደንቀንም አለን። እኚህ ሰው አባ ኤልያስ ታደሰ ናቸው። አባ ኤልያስ ለመመንኮስ እንኳ በአስተዳዳሪነት ተደራድረው እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ነው። በሕይወታቸውም ምንም አይነት የምንኩስና ህይወት ፍሬ አይትባቸውም። የደሴ ገብርኤል ሰባኬ ወንጌል በነበሩ ጊዜ ሚስት ለማግባት እየተዘጋጁ በነበረ ጊዜ አለቃ ትሾማለህ መንኩስ ተብለው የመነኮሱ ሰው ናቸው። አለቃ ትሆናለህ የሚለው ቃል አስደስቶዋቸው ከተሾምኩማ በማለት በግንቦት ወር መንኩሰው በሰኔ ወር 40 ቀን እንኳ ሳይሞላቸው አለቅነት የተሾሙ ግለሰብ ናቸው። የተሾሙበትም ደብረ ደሴ መድኃኔዓለም ነው።ግለሰቡ የምነከስናም ሆነ የገዳሚ ሕይወት ባለቤት ሳይሆኑ ለሹመት ብቻ የገቡበት ሕይወት እንዴት ለጵጵስና እንዳስጠቆማቸው ለደሴ ህዝብ ግራ ነው። እሳቸውም ቢሆኑ በአንደበታቸው ምንኩስናን የት አውቀዋለሁ ብለው መናገራቸው የቅርብ ወዳጆቻቸው ሁሉ የሚያውቁት ነው።

ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ጠንቅቀው የማያውቁ መሆናቸው የደብሩ ካህናት የሚመሰክሩት እውነት ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን በጣም የሚያሳዝነው አባ ኤልያስ በጥንቆላ መንፈስ የተጠቁ መሆናቸው ነው። በተሾሙበት ደብር ያለው ህዝብ ሁልጊዜ በሚፈጥሩት የአስተዳደር ችግር ተማሮ የይነሱልን ጥያቄ ባቀረበ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከሥልጣኔ ሊያወርዱኝ ነው እባካችሁ ነገረ በትን(መድፍነ ጸር) የሚባል መተት አድርጉብኝ ብለው ይማጸኑ እንደነበር የታወቀ ነገር ነው። አባ ኤልያስ አስተዳደር የሚባል ነገር ፈጽመው የማያውቁ በመሆናቸውም ታላቁን ደብር የደሴ መድኃኔዓለምን እያተራመሱት ይገኛሉ። ታድያ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የማያውቁትን፣ የተገለጠ የምንኩስና ሕይወት የሌላቸውን፣ ከምንፍቅና ህይወት ያልጸዱትንና በጥንቆላ መንፈስ የተያዙት ግለሰብ በምን መስፈርት ነው ለጵጵስና እጩ የሚሆኑት?
በመንፈሳዊ ሕይወት የበለጸጉ በዓለም አቀፍ እውቀት ሳይቀር የማይታሙ እና የቤተክርስቲያንዋን ሥርዓት ጠንቅቀው የሚያውቁ አባቶች እያሉ አባ ኤልያስን በእጩነት መያዝ ከእብደት የማይተናነስ ነው። ስለዚህም አባ ኤልያስ በምንም መንገድ ለኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ መሾም መቅረብ የለባቸውም። አንድ የደሴ መድኃኔዓለምን ማስተዳደር ያቃታቸው ግለሰብ ጭራሽ ሀገረ ስብከት ይዘው ምን እንደሚያደርጉት መገመት አያዳግትም። በሚያስተዳድሩት ደብር ሰንበት ተምህረት ቤቱ ከካህናቱም ሆነ ከአብነት ተማሪዎች ጋር ተጣልተው እያለ እነርሱን ለማስታረቅና የቤተክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ የረባ ሥራ እንኳን መስራት ያልቻሉ ሰው ናቸው። በእሳቸው አመራር ታላቁ የመድኃኔዓለም ደብር በልማት ወደ ኃላ የቀረ እና በብጥብጥ የሚታወቅ ደብር ሆኗል።
ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠስዋ እንደተባለው እንደመነኮሱ 40 ቀን እንኳን ሳይሞላቸው አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ኤልያስ አሁን ደግሞ ጳጳስ ከሆኑ ነገሩ ሀሉ ከድጡ ወደ ማጡ ስለሚሆን አስመራጭ ኮሚቴው ነገሩን በትኩረት እንዲያየው እንጠይቃለን።
የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ህዝብ


9 comments:

 1. አባሰላማዎች ለቤተክርስቲያን መቀደስ ለምታደርጉት አገልግሎት እግዚአብሔር ይባርካችሁ

  ReplyDelete
 2. AY TEHADISOWOCH! KETEMERETU INDET LITHONU NEW? KEWEDIHU TEQBEZEBEZACHIHUSA? YABATACHU YE DABILOSIN KISS ASTEGABACHIHU!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 3. እነ አይቅርብኖች

  ReplyDelete
 4. የምትሏቸውን አባቶች ባላውቃቸውም በእናንተ መወደሣቸው ግን የሚነግረን ሁለት ነገር አለ
  አንደኛው ከሦሥቱ አባቶች መካከል በጣም ጠንከራ እና በሃይማኖታቸው የማይደራደሩ አባት አሉ ማለት ነው :: ምክንያቱም ከተመረጡ የእናንተን እኩይ መግባር የተሐድሦ እንቅሥቃሤ አደጋ ላይ ሥለሚጥለው እናንተ ደጋፊ መሥላችሁ እናንተ ካቀረባችሁ አባቶቻችን ሢሠሙ ተጠራጥረው እንዳይመርጧቸው ለማድረግ ነው:: ምክንያቱም እናንተ ጸረ ቤተክርድቲያን እንጂ ለቅድሥት ኦርቶዶክሥ ተዋህዶቤተክርሥቲያን መልካም ሥላልሆናችሁ::
  ሁለተኛው ከጠቀሣችሃቸው መካከል የእናንተን አላማ ለማሣካት ይሆናል ያላችሁት ካለምንአልባት የሚሠማን ካገኝን ቅሥቀሣ እናካሂድ ብላችሁ ነው:;ለማንኛውም አባቶቻችን በዚህ ትልቅ ጉዳይ የሚታለሉ አይምሠላችሁ

  ReplyDelete
 5. እናንተ የምትደግፉትን እቃወማለሁ የምትቃወሙትን እደግፋለሁ!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 6. እነ አያ ጅቦ አያችኋቸው አደል አይናማውን ሊቅና የመጽሐፍ መምህር ምንም ስርዓተ ቤ/ክ የማያውቅ? የማታውቁ ደንቆሮስ እናንተ ግብዞች። እኔ ባወደሳችኋቸው አባቶች ላይም ቅሬታ የለኝም ግን የደሴ " ህዝብ" ማለት ምን ማለት ነው? ኦርቶዶክስ፡ ሙስሊሙ፡ ፕሮቴስታንት፡ እናንተ(ተሃድሶውያን)፡ ካቶሊክ ወይስ ማን ነው? ሞኝ ባገኝ ናችሁ ግን ሞኝ የለም እነ አያጅቦ!!!!!

  ReplyDelete
 7. Tesadabiwoch.enantem ahun mengestesemayat engebalen blachu tasebu yehonal yemahber buchlawoch.

  ReplyDelete
 8. ወገኖቼ ለመጨረሻ ጊዜ ይህን ልበላችሁ ስሙ!ጌታ ኢየሱስ ከማርያም ተወልዶ ለ3 ዓመት ሲያስተምር ጴንጤ ወይም ኦርቶዶክክስ ወይም ካቶሊክ .... ካልሆናችሁ መንሥተ ሰማይ አትገቡም ብሎ ስለሃይማኖት አሰተምሯል እንዴ?ኧረ እናስተውል?እሱ ያስተማረው ይህን ብታውቁና ብታደርጉ /ዮሐንስ 13፡17/ በማለት፡
  1/ አዳም በኃጢአት ምክንያት ከገነት ወጣ = ከእግዜር ተለየ = ሰው ሁሉ /አንተም አንችም እኔም አባም ፓስተርም / ኃጢአትን ሠርተዋልና /ሮሜ 3፡23/ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን /1ኛ ዮሐንስ 1፡10/
  2/ የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው /ሮሜ 6፡23/ = ከገነት መውጣት ነው /ዘፍጥረት 3፡24/ = ራቁትነትና በፍርሃት መደበቅ ነው /ዘፍ 3፡10/ = በመርገም ውስጥ መሆን ነው /ዘፍ 3፡15_17
  3/ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም /ዕብራውያን 9፡22/ በብሉ ኪዳን ዘመን የእንሳሳት ደም ይፈስ የነበረው ለዚህ ነበር፤ ግን በጥላነት አገለገለ እንጂ ዘለቄታ መፍትሄ አላመጣም።
  ስለዚህ የሁላችን ዋና ጥያቄ መሆን ያለበት ከዚህ ኃጢአት ካመጣብን የሞት በሽታ እንዴት መዳንና ከእግዜር ጋር እንታረቅ?መልሱን ከቃሉ አብረን እንይ:
  ሀ/ ወንድም ወንድሙን አያድንም፣ ሰውም አያድንም /መዝ 49፡7/
  ለ/ እግዚአብሔር ሰውም እንደሌለ አየ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት/ኢሳ 59፡15-17/
  ሐ/ ልጅም ትወልዳለች እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ /ማቴ 1፡21/ የተመረጠች እናቱ ማርያምም ይህን ተረድታ መድሐኒቴ /ሉቃ 1፡47/አለችው!
  መ/ መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና! የለምና! የለምና! የለምና! የለምና! /ሐዋ ሥራ 4፡12/።
  ሠ/ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል /ዮሐ 3፡14 እና 15/ ፍቅሩ የገለጠበት መንገድ /3፡6/
  ረ/ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም ስላለ /ዕብ 9፡22/ በደሙ ከኃጢያታችን ሊያነጻን /1ኛ ዮሐ 1፡7-9 / ቃል ሥጋ ሆነ /ዮሐ 1፡14/
  ስለዚህ ክርስትና በልጁ የመስቀል ሥራ ከሞት መዳን /1ቆሮ 1፡18/ እና የህይዎት ጉዳይ ነው እንጂ /ዮሐ 10፡10/ እና 1ኛ ዮሐ 5፡12/ ሰው ሠራሽ የሆነ የድርጅት ወይም የሃይማኖት ጉዳይ አይደለምና ቆም ብለን ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰማይ የመጣበትንና በመስቀል ላይ ለሁላችን የከፈለውን የህይወት ዋጋ እናስተውል?
  ክርስትና በክርስቶስ የደም ዋጋ የተገኘ ሕይወት እንጂ በፍጹም ሃይማኖት አይደለም!!!
  በሰማይ ፍቅር የተሸነፍኩና
  በጸጋው ቃል ሁለንተና ማንነቴ የተማረኩ
  ብቸኛ አዳኝ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ብቻ ብቻ /ሌላ መጨመር በመስቀሉ ሥራ ላይ ብቃት የለኸም ማለት ስለሚሆን / መሆኑ በመጠኑ የገባኝ!ግን ቃሉን በመብላት ወደ ሙላቱ በመገስገስ ላይ ያለሁና ጨለማየ በብርሃኑ የተገፈፈልኝ!!!
  ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጠን!
  ያለወንጌል /ሮሜ 1፡1-4/ ክርስቲያን ያስባለንንና
  በመርገም ውስጥ እንድንሆን ያደረገን /ገላት 1፡6-9 /
  እና እንደ ሳውል/ጳውሎስ /ሐዋ ሥራ 9፡1-9 /
  ፎካሪና ገዳይ ሃይማኖተኛ ብቻ ያደረገን ክፉ
  የደበተራ መንፈስ በቃሉ ሰይፍ ከሕዝባች ላይ የተሰየፈ ይሁን! አሜን።
  የቀደመችው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታማኝ ልጆች አንዱ!
  እ ው ነ ቱ ይ ነ ገ ር !!!

  ReplyDelete
 9. enant enmanachu selam ortodocxs tewhaedo yemtawerut enda anfelgachum tebal eko yalbelachun atekku

  ReplyDelete