Sunday, August 28, 2016

ነጻነትነጻነት የሰው ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የሰው ተፈጥሮውም ነው። ነጻነት ስለፈለግን አይደለም ስለ ነጻነት የምንጮኸው ነጻ ሆነን ስለተፈጠርን ነው። ያለተፈጥሯችን እንድንሆን የሚፈልጉ ሁሉ ተፈጥሮን ለማበላሸት የሚደክሙ ናቸው። እግዚአብሔር በነጻነት ውስጥ ያስቀመጠው ታላቅ ምሥጢር አለ ይህ የእግዚአብሔር ጥበብ እጅግ በጣም አስደናቂ ነው። ማነኛውም የሰው ልጅ እውቀትና ችሎታ በሥራ ላይ ውለው ለሰው ጥቅም የሚሰጡት በዚህ በነጻነት ምሥጢር ነው።
ነጻነት በእግዚአብሔር መንፈስ የተሰጠ የሰው ማንነት ነው። ሰው ነጻ ፍጡር መሆኑን የሚያንጸባርቀው ገና ሲወለድ ጀምሮ ነው። ሕጻናት አቅም ካላነሳቸው በቀር ዝም ብለው መቀመጥ አይችሉም መሮጥ መጫወት ይፈልጋሉ እናት እና አባት እነርሱን ለመቆጣጠር ሲሞክሩ ተቃውሞአቸውን በለቅሶ ይገልጣሉ። ይህ ሁኔታ የነጻነት ፍላጎት በትምህርት ወይም በአካባቢ ሁኔታ የሚገኝ ሳይሆን በተፈጥሮ በውስጣችን ያለ የእግዚአብሔር ምሥጢር መሆኑን የሚያመለክት ነው። ነጻነትን በአግባቡ ማስተዳደር እንጂ መገደብ አደጋ አለው። ለመርከስም ሆነ ለመቀደስ ነጻነት አለን። ምርጫው የራሳችን ነው። እግዚአብሔር በጉልበት አይቀድሰንም። በኃይልና በግዴታ ቅድስና የለም። እግዚአብሔርን በመምረጥና ለቃሉ በመታዘዝ እንጂ። ይህን ሐሳብ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እናገኘዋለን።

Thursday, August 25, 2016

ግመሉን በዝምታ ትንኙን በጫጫታ
ከአሸናፊ በላይ

ኑፋቄ ሁለት ፡- ማኅበሩ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ መንገዶች የክርስቶስ ተቃዋሚ መሆኑን በግልፅ አሳይቷል፡፡ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እየሠራበት እንደሆነ ወደፊት በዝርዝር ማስረዳት የሚቻል ቢሆንም ለዛሬው ጥቂት ሐሳቦችን ብቻ መጠቆም የማኅበሩን ምንነት የበለጠ ለመረዳት ይጠቅማል፡፡ ቀጥሎ የተጠቀሱት ጥቂት ነጥቦች ማኅበሩ የኢየሱስ ክርስቶስ ተቃዋሚ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡

«ኢየሱስ» የሚለውን ስም አጥብቆ መቃወሙ
ማኅበሩ በግልፅ ይህንን ስም መቃወሙን ባይናገርም የጌታን አዳኝነት የሚያሳየውን «ኢየሱስ» የሚለውን ስም የሚጠሩትን የቤተ ክርስቲያን ልጆች «መናፍቃን ናቸው» ብሎ በክፉ ስማቸውን በማጥፋት እንዲሳደዱ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳ እንዳሰበው ባይሳካለትም የጌታ ስም እንዳይጠራ ለማድረግ ብርቱ ጥረት አድርጓል፡፡ አንዳንድ ዘማርያን
«ማልደራደርበት ማልቀብረው እውነት
አንገት የማያስደፋ የማላፍርበት
ኢየሱስ የሚለው ስም እስትንፋሴ ነው
እውነቱ ይኸው ነው»
በማለት ግሩም ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ኢየሱስ የሚለው ስም እንዳይጠራ ማኅበሩ መቃወሙ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በግልፅ እየሠራበት መሆኑን ያመለክታል፤ (1ቆሮ 12÷3)፡፡

የጌታን የማዳን ሥራ ለፍጡራን መስጠቱ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤዛነትና ብቸኛ የአዳኝነት ሥራ ለፍጡራን በመስጠትና የተለያዩ የደኅንነት /የመዳን/ መንገዶች እንዳሉ በማስተማር ብዙዎች እንዳይድኑ ማኅበሩ እንቅፋት ሆኖአል፡፡ ከተጠቀሱት ሐመርና ዕንቁ መጽሔቶች አንዳንድ ሐሳቦችን እንመልከት፡፡

Tuesday, August 23, 2016

ግመሉን በዝምታ ትንኙን በጫጫታ


Read in PDF
ከአሸናፊ በላይ
ትንሹ ነገር ያለ ቅጥ ሲጐላና ሲጋነን ትልቁንና ዋናውን ነገር ይሸፍናል፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋናውንና ትልቁን የእግዚአብሔርን እውነታ ቸል ብለውና ትተው ለማይረባውና ኢምንት ለሆነው በአንዳንድ ሁኔታም የእግዚአብሔርን ቃል ለሚቃረነው የወግና የሥርዓት ጉዳይ ብርቱ ጥረት ሲያደርጉ ለተመለከታቸው ግብዞች ፈሪሳውያን ፣ «እናንተ ዕውሮች መሪዎች፤ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ» በማለት በብርቱ ገስጾአቸዋል፤ ማቴ. 23÷24፡፡
ይህንን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለግብዞች ፈሪሳውያን የተናገረውን ትምህርት ያነሳሁት ማኅበረ ቅዱሳን ሊወቀስበትና ሊወገዝበት የሚገባው ዋናውና ትልቁ የኑፋቄ ሐሳብ እያለ ማኅበሩ ለሚፈጥራቸው አንዳንድ ችግሮች ያለቅጥ ትኩረት በመስጠት ዋናውና ትልቁ ጉዳይ ቸል እንደተባለ ለማመልከት ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን አለቆች (ቅዱስ ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባኤ) ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ዋናውን የኑፋቄ ጉዳይ ወደ ጐን ትተው /ቸል ብለው/ ማኅበሩ በሚፈጥራቸው አንዳንድ ችግሮች ላይ ወቀሳ ሲያሳሙ ቆይተዋል፡፡ ማኅበሩ በአስተዳደር ጉዳዮች ጣልቃ እየገባ እንዳስቸገራቸው፤ በቤተ ክርስቲያን ደንብና ሥርዓት ላይ እንዳመፀ፤ ገንዘብ ያለ አግባብ ሰብስቦ እንደተጠቀመ፤ የቤተ ክርስቲያን አለቆችን አላሠራም እንዳለ ፈራ ተባ እያሉ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ አንዳንዶችም «የታመነ ምስክር አይዋሸም»፤ ምሳሌ 14÷5 የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመተላለፍ ስለ መናፍቁ ማኅበር «የቤተ ክርስቲያን ልጅነት፤ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት» ሲለፍፉና ጥብቅና ሲቆሙ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሲቃወሙ ቆይተዋል፤ አልፈው ተርፈውም በተሰጣቸው ሥልጣን የእርሱን እኩይ ፈቃድ በማስፈጸም የማኅበሩ ቀኝ እጅ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ 

Wednesday, August 17, 2016

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የምናከብራት እንዴት እና እስከ ምን ድረስ ነው?ክርስቲያኖች ሁሉ ድንግል ማርያምን ያከብሯታል፤ አለማክበር አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ጌታቸውን አምላካቸውንና መድኃኒታቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ የወለደች እርሷ ናትና፡፡ ይህ እርሷን ለማክበር ከበቂ በላይ ምክንያት ነው፡፡ ለነገሩ ክርስቲያን እንኳና የጌታን እናት ማንንም በአርኣያ ሥላሴ የተፈጠረን ሰው መጥላት አይችልም፡፡ ወንጌልም እኮ እንኳን ወዳጅን ጠላትን ውደዱ ነው የሚለው?
አሁን ጥያቄው ማርያምን የምናከብራት እንዴትና እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለው ነው፡፡ መልሱ ከባድ አይደለም፤ ቀላል ነው፡፡ ማርያምን ልናከብራት የሚገባው እኛ በመሰለንና በታየን መንገድ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር ቃል በሚለው መሠረት መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ሲባልም በእግዚአብሔር ቃል የታዘዘውን መሠረት አድርገን በተገቢው መንገድ ማክበር የሚገባ ሲሆን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከሚለው አልፈን በአክብሮት ስም ያልተገባ ነገር አለማድረግንም ያካትታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የዘንድሮውን ጾመ ፍልሰታ ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት ውስጥ መጀመሪያው ላይ ያስቀመጡት መርሕ ክርስቲያኖች ሁሉ የሚስማሙበት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኗም አቋም ነው፡፡ ስለዚህ ማርያምን ስለማክበር መርሑ በተገቢው መንገድ መከበር አለበት፡፡ ቅዱስነታቸው ያስቀመጡት መርሕ እንዲህ የሚል ነው፡፡

Saturday, August 13, 2016

ሕይወት የሆነን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ብቻ ነው! ምንጭ፦ dejebirhan.blogspot.com
ቅዱሳንን ማክበር እንደሚገባ ምንም ጥያቄ የለንም። መታሰቢያን በተመለከተም የድርጊቶቻችን አፈፃፀም የሁሉ ነገር ባለቤት የሆነውን እግዚአብሔርን ስምና ክብር እስካልጋረደና  እስካልተካ ድረስ የሚደገፍ ነው። ነገር ግን  «ጥቂት አሻሮ ይዞ፤ ዱቄት ወዳለው መጠጋት» የሚለውን ብሂል ለመተግበር መሞከር ግን አደገኛ ነገር ነው። በተለይም በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ወቅት ወንጌል እንደዚህ ስለሚል፤ እኔም እንደዚህ ብል ችግር የለውም የሚለውን ራስን መሸሸጊያ ምክንያት በማቅረብ ለመከለል መሞከር ፀረ ወንጌል ነው። በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ሥር ኑፋቄና ክህደትን ማስተማር በአምላክ ፊት ያስጠይቃል። እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ስለሚችል የኛን ተረት ሁሉ ይሰራልናል ማለት አይደለም። ብዙ ጥያቄዎች የሚነሱትና እነዚህ የመሳሰሉ የስህተት ችካሎች አልነቀል ያሉት በምክንያት ስር በመደበቃቸው ነው። ቅዱሳንን በማክበርና በመውደድ ሽፋን ወደአምልኮና ተገቢ ያልሆነ ሥፍራ ወደማስቀመጥ ያደገው መንፈሳዊ በሚመስል ማሳሳት ተሸፍኖ ነው።

ለክርስቲያኖች ድኅነት ዋናው ቁልፍ የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው የማንም ሰው ሞትና ትንሣኤ ለመዳናችን ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። አይጨምርልንም፣ አይቀንስልንም። ማዳን የእግዚአብሔር ነውና ኢሳይያስ 4311 "እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም"
ይህ የተሠጠን የቃሉ እውነት እንደተጠበቀ ሆኖ የጌታ እናት የድንግል ማርያም ሞትና ትንሣኤ ለክርስቲያኖች ዘላለማዊ ድኅነት መስጠት ይችላል? ወይ ብለን ብንጠይቅ መልሱ አይችልም ነው። ታዲያ በድንግል ማርያም ሞትና ትንሣኤ ላይ ጥንታዊያን የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናት የተለየ ሃይማኖታዊ ትኩረት የሚሰጠው ለምንድነው? ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ትርጉምና ትረካ የሚገልፁበትስ ምክንያት ለምን ይሆን? እንኳን እኛ ጠያቂዎቹ ራሳቸው በትክክል ምክንያቱን የሚያውቁ አይመስለንም። የሆኖ ሆኖ ትርክታቸውን ለመዳሰስ እንሞክራለን።

Wednesday, August 3, 2016

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ ሊቃውንት አለቆች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል አስመራጭ ኮሚቴውን በመቃወም ለፓትርያርኩ ደብዳቤ አቀረቡብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስድርጊቱ በግሌ በጣም አሳዝኖኛል፣ በዚህ ጉዳይ የማያዝን የሲኖዶስ አባል አለ ብዬ አላምንም
ባለፈው ሰኞ (በ25/11/2008 ዓ.ም) የኤጲስ ቆጶሳትን አስመራጭ ኮሚቴ ኃላፊነት የጐደለው ሥራ በመቃወም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የአድባራትና የገዳማት አለቆች፣ ጸሐፊዎች ሰባክያነ ወንጌል በተገኙበት በቅዱስነታቸው /ቤት ብስለት የሚታይበት፣ ከበድ ያለ መልእክት ያዘለና ቤተክርስቲያንን ማእከል ያደረገና ከአንድ ሺሕ አምስት መቶ በላይ ሰዎች የፈረሙበት የተቃውሞ ደብዳቤያቸውን በንባብ አሰሙ፡፡ አስተያየትም ተሰጥቶአል፡፡  
 ደብዳቤው በተነበበበት ሥነ ሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ ዲዮስቆሮስ፣ ፀሐፊው አባ ሳዊሮስ ተገኝተዋል፡፡ ቅዱስነታቸውድርጊቱ በግሌ በጣም አሳዝኖኛል፣ በዚህ ጉዳይ የማያዝን የሲኖዶስ አባል አለ ብዬ አላምንምያሉ ሲሆን፣ ሥራቸውን የሚያውቁት አባ ዲዮስቆሮስና አባ ሳዊሮስ ግን አንድም ቃል ትንፍሽ ማለት አልቻሉም፡፡