Wednesday, August 17, 2016

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የምናከብራት እንዴት እና እስከ ምን ድረስ ነው?ክርስቲያኖች ሁሉ ድንግል ማርያምን ያከብሯታል፤ አለማክበር አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ጌታቸውን አምላካቸውንና መድኃኒታቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ የወለደች እርሷ ናትና፡፡ ይህ እርሷን ለማክበር ከበቂ በላይ ምክንያት ነው፡፡ ለነገሩ ክርስቲያን እንኳና የጌታን እናት ማንንም በአርኣያ ሥላሴ የተፈጠረን ሰው መጥላት አይችልም፡፡ ወንጌልም እኮ እንኳን ወዳጅን ጠላትን ውደዱ ነው የሚለው?
አሁን ጥያቄው ማርያምን የምናከብራት እንዴትና እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለው ነው፡፡ መልሱ ከባድ አይደለም፤ ቀላል ነው፡፡ ማርያምን ልናከብራት የሚገባው እኛ በመሰለንና በታየን መንገድ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር ቃል በሚለው መሠረት መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ሲባልም በእግዚአብሔር ቃል የታዘዘውን መሠረት አድርገን በተገቢው መንገድ ማክበር የሚገባ ሲሆን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከሚለው አልፈን በአክብሮት ስም ያልተገባ ነገር አለማድረግንም ያካትታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የዘንድሮውን ጾመ ፍልሰታ ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት ውስጥ መጀመሪያው ላይ ያስቀመጡት መርሕ ክርስቲያኖች ሁሉ የሚስማሙበት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኗም አቋም ነው፡፡ ስለዚህ ማርያምን ስለማክበር መርሑ በተገቢው መንገድ መከበር አለበት፡፡ ቅዱስነታቸው ያስቀመጡት መርሕ እንዲህ የሚል ነው፡፡

“‹ቃለ እግዚአብሔር ንጹሕ ወያሐዩ ለዓለም፤ የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ነው፤ ለዘላለሙም ያድናል› (መዝ.18፡9)፡፡
ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ስለቃለ እግዚአብሔር አስመልክቶ በዘመረው መዝሙር ሲናገር ‹የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ነው› ይላል፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቃል የተለያዩ ፍጡራን ከሚናገሩዋቸው ቃላት ልዩ፣ ንጹሕ፣ ቅዱስና ክቡር ነው፡፡
የፍጡራን ቃል ከሐሰት፣ ከወላዋይነት፣ ካላዋቂነት፣ ከጥርጣሬ፣ ከአስመሳይነት፣ ከአታላይነትና ከዓቅም ውሱንነት ጋር ተቀላቅሎ ስለሚነገር ንጹሕ ነው ብሎ መናገር አይቻልም፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ከዚህ ሁሉ የተለየ በመሆኑ ፍጹም ንጹሕ ነው፤ እውነትም ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ብቻ ሳይሆን ኃያልም ነውና በተናገረው መሠረት ከሚፈጸም በቀር ፍጹም የማይቀለበስ ነው፡፡
‹የእግዚአብሔር ቃል ከሚወድቅ፣ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል› የሚለው የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይለ ትምህርት፣ የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉም በላይ የሆነ ክብር፣ ኃይልና ጽናት ያለው መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ በመሆኑም ንጹሕና እውነት የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል በማጣመም፣ ወይም በመሸራረፍ፣ ወይም በመቀናነስ ወይም ለራስ ፍላጎት በሚያመች ሁኔታ እያዛቡ መናገርና ማስተማር በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉ ይልቅ ታናሽ የሚያደርግ መሆኑን በቅዱስ ወንጌል ተጽፎአል፤ (ማቴ. 5፡19)፡፡
የእግዚአብሔር ቃል እውነተኛና ንጹሕ የመሆኑን ያህል ሕያውና ዘለዓለማዊ ነው፤ በሁለት ወገን ስለት ካለው ሰይፍም ይልቅ የሚቆርጥና የሚለይ ኃይል አለው፤ (ዕብ.4፡12)፡፡ ይህም ማለት የእግዚአብሔርን ቃል እንዳለ ተቀብለው የሚጠብቁትንና የሚታዘዙለትን ለዘለዓለሙ ሕያዋን የማድረጉን ያህል፣ የሚሸራርፉትንና የሚያጣምሙትን ደግሞ የመቅጣት ሥልጣን ያለው መሆኑን ያሳየናል፡፡ በመሆኑም የሰው ልጅ ድኅነት፣ ቃሉን በመጠበቅና ባለመጠበቅ ሚዛን ላይ ተቀምጦ እንዳለ መገንዘብ አለብን፡፡”

በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ የማይለወጠውና ተአማኒነት ያለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ መሆኑን፣ ለራስ ጥቅም ሲባል ቃሉን ማጣመም፣ መሸራረፍ፣ መቀናነስና እያዛቡ ማቅረብ ትልቅ ፍርድ ያለበት ኃጢአት መሆኑንና የእግዚአብሔርን ቃል እንዳለ ተቀብሎ መጠበቅና መታዘዝ ለዘላለም ሕያው ማድረጉ ሁሉ ሊያውቀው የሚገባ መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ በቅዱስነታቸው አማካይነት የቀረበው የቤተ ክርስቲያናችን መልእክት በመርሑ መሠረት የእግዚአብሔር ቃል ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚናገረውን በተመለከተም እንዲህ ይላል፡፡      

“ንጹሕና ሕያው የሆነው፣ ሰዎችንም ለዘለዓለሙ በሕይወት እንዲኖሩ የሚያደርገው የእግዚአብሔር ቃል፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከተ የተናገረው እውነት አለ፤ በቀጣዮቹ ሁለት ሱባኤያት የቅድስት ድንግል ማርያምን ነገረ ፍልሰት ምክንያት በማድረግ የምንፈጽመው አምልኮተ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔር ቃል ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተናገረውን በማስታወስና ለቃሉ ተገዥ በመሆን ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብዙ ተናግሮአል፤ ከተናገራቸውም መካከል፡-

- ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤
- እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፤
- ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤
- በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻል፤
- መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑልም ኃይል ይፀልልሻል፤
- የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
- ብፅዕት ነሽ፤ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
- እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ፤ የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡
እነዚህ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ይልቁንም አብዛኛው በሉቃስ ወንጌልና አንዱ በዮሐንስ ወንጌል የተነገሩ ናቸው፡፡ የተጠቀሱት ሁሉ ስለእርሷ የተነገሩና የተጻፉ ናቸው፡፡ ይህን ሊክድ የሚችል ክርስቲያን ከቶ የለም፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች መነሻነት ለማርያም ይቅረብ የሚባለው አክብሮት በውን ሊጤን ይገባዋል፡፡ መልእክቱ ሲቀጥል እንዲህ ይላልና፡፡  
ስለሆነም እግዚአብሔር ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም የተናገረውን ቃል ጠቅለል አድርገን ስንመለከት በዋናነት የሚያሳየው ቅድስት ድንግል ማርያምን የጌታ እናት መሆኗን አምነው በመቀበል ‹‹ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ›› እያሉ እንዲያከብሯት በእግዚአብሔር መታዘዙ ነው፤ ምክንያቱም የድንግል ማርያም ክብር፣ ከእግዚአብሔር ክብር ጋር የተያያዘ ባህርይ አለውና ነው፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልእተ ጸጋ፣ ሙኃዘ ፍሥሐ፣ ምልእተ በረከት፣ የእግዚአብሔር ባለሟል፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለች፣ ብፅዕት፣ ባትሆን ኖሮ ጌታን ለመውለድ የሚያስችል ንጽሕናና ቅድስና አይኖራትም ነበር፤ እግዚአብሔር ንጹሐ ባህርይ እንደ መሆኑ መጠን በንጹሐንና በቅዱሳን አድሮ ይኖራልና፡፡
በዚህ ውስጥ “ … ቅድስት ድንግል ማርያምን የጌታ እናት መሆኗን አምነው በመቀበል ‹‹ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ›› እያሉ እንዲያከብሯት በእግዚአብሔር መታዘዙ ነው፤ ምክንያቱም የድንግል ማርያም ክብር፣ ከእግዚአብሔር ክብር ጋር የተያያዘ ባህርይ አለውና ነው፤ …” የሚለው ገለጻ ጥያቄ የሚያስነሱ ሐሳቦች አሉበት፡፡ ማርያምን በጌታ እናትነት “አምኖ መቀበል” ምን ማለት ነው? መጽሐፍ ቅዱስን ያነበበ ማንም ሰው ማርያም የጌታ እናት አይደለችም ብሎ ሊክድ አይችልም ምክንያቱም ሥጋ የሆነውን ቃልን በሥጋ ወልዳለችና፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠውን ይህን እውነት ማንም ሊያስተባብል አይችልም ቢባልም ማርያምን የጌታ እናት መሆኗን አምኖ መቀበል የሚል የሚያሸልምም ሆነ የሚያስቀጣ ትእዛዝ ግን የለም፡፡ ይህን ትእዛዝ በመፈጸም የሚገኝ ዋጋ ስለመኖሩም አልተጻፈም፡፡ ይህ ምናልባት ኢየሱስን ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ማመንና መቀበል የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ሥልጣንን እንደሚያሰጥ ከተጻፈው ቃል የተወሰደ ነው፡፡ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡” (ዮሐ. 1፥11-12)፡፡ ኢየሱስን ክርስቶስና የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ ማመንና መቀበል የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ሥልጣንን ያሰጣል፡፡ አለማመንና አለ መቀበል ግን የእግዚአብሔር ቁጣ የሆነ የዘላለም ሞትና ፍርድን ያመጣል፡፡ ማርያምን የጌታ እናት ብሎ ማመንና መቀበል የሚል ትምህርት ግን እርሷን ከክርስቶስ ጋር ለማስተካከል ከሚፈልግ ልብ የተገኘ እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም፡፡ ከላይ ስለ እርስዋ ከተጻፉት ውስጥ የተጠቀሱት ሐሳቦችም ቢሆኑ ወደዚህ ድምዳሜ የሚያደርሱ አይደሉም፡፡
ለጌታ እናትነት የተመረጠች መሆኗ ለእርሷ ብቻ የተሰጠ ጸጋ ቢሆንም ከዚህ ጋር ተያይዘው የተነገሩት፣ ለምሳሌ፡- ጸጋን መሞላት፣ የእግዚአብሔር አብሮነት፣ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን ማግኘት፣ ብፁዕ፣ ብፅዕት መባል ወዘተርፈ ለእርሷ ብቻ የተነገሩ አይደሉም፡፡  ቃል ሥጋ ሲሆን ጸጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ ይላል ዮሐንስ ወንጌላዊው፡፡ አክሎም እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።”  (ዮሐ. 1፥16-17)፡፡ በዚህ መሠረት በክርስቶስ ያመኑ ምእመናን ሁሉ ከሙላቱ ተቀብለው በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቷቸዋል ማለት ነው፡፡ ስለ ሐዋርያት አገልግሎት በተጻፈበት በግብረ ሐዋርያት ውስጥም ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።” ይላል (4፥33)፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስም ሲናገር እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።” (6፥8) በማለት ይመሰክራል፡፡
የእግዚአብሔር አብሮነትም ለአማኞች ሁሉ የተነገረ ነው፡፡ በብሉይም በሐዲስም እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር መሆኑን ደጋግሞ ተናግሯል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለደቀ መዛሙርቱ በሰጠው ተስፋ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ብሏል፡፡ ከላይ እንዳየነው በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ ማግኘትም ለአማኞች ሁሉ የተሰጠ ነው፡፡   
ብፁዕ ብፅዕት መባልም ለጌታ እናት ብቻ ሳይሆን ጌታ ኃጢአታቸውን ከማይቆጥርባቸው በጸጋው ካዳናቸው ኃጢአተኞች አንሥቶ በክርስትና ሕይወት በታማኝነት እስከኖሩት ቅዱሳን ድረስ የሚጠሩበት “ደስተኛ” የሚል ትርጉም ያለው ቃል ነው (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት)፡፡ ለምሳሌ ሐዋርያው ያዕቆብ የሚለውን እንመልከት እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።” (ያዕ. 5፥11)፡፡  በአጠቃላይ እነዚህ ለእመቤታችን የተነገሩት ቃላት ማርያምን አክብሩ ወደሚል ትእዛዝነት የሚመነዘሩበት ምክንያትና ሁኔታ የለም፡፡ ከምንም በላይ ማርያምን የምናከብራት የጌታችን እናት ስለሆነች ነው፡፡
“የድንግል ማርያም ክብር፣ ከእግዚአብሔር ክብር ጋር የተያያዘ ባህርይ አለውና” የሚለው አነጋገር  ማርያምን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስተካከል በማሰብ የቀረበ አስተያየት ነው፡፡ ነገር ግን ምንም ቢሆን የማርያም ክብር ከእግዚአብሔር ክብር ጋር የሚያያዝ ባህርይ ሊኖረው አይችልም፡፡ የማርያም ክብር ሌላ የእግዚአብሔር ክብር ሌላ ነውና፡፡ በአክብሮት ስም ሁለቱን ማቀላቀል ማርያምን ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ማድረግ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ አጼ ዘርአ ያዕቆብ በተአምረ ማርያም መቅድም ላይ “የእመቤታችን ማርያም ሐሳብ እንደ አምላክ ሐሳብ ነው” ያለውን፣ እንዲሁም በመስተብቁእ ዘመስቀል ላይ “ለእሉ ክልኤቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተአረዩ በክብሮሙ” ማለትም ለእነዚህ ለሁለቱ ፍጡሮች የፈጣሪ ክብር ይገባቸዋል የሚለው አምልኮ ባእዳዊ ትምህርት እንጥፍጣፊ ነው፡፡ እውነቱ ማርያም እግዚአብሔር ባከበራት ክብር የምትከብር ናት እንጂ ከእግዚአብሔር ክብር ጋር የሚያያዝ ክብር የላትም፡፡ ይህ ማርያምን ከፍ ለማድረግ ሲባል እግዚአብሔርን ዝቅ የሚያደርግ አስተሳሰብ ስለሆነ በቶሎ ሊታረም ይገባዋል፡፡
“ቅድስት ድንግል ማርያም ምልእተ ጸጋ፣ ሙኃዘ ፍሥሐ፣ ምልእተ በረከት፣ የእግዚአብሔር ባለሟል፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለች፣ ብፅዕት፣ ባትሆን ኖሮ ጌታን ለመውለድ የሚያስችል ንጽሕናና ቅድስና አይኖራትም ነበር፤ እግዚአብሔር ንጹሐ ባህርይ እንደ መሆኑ መጠን በንጹሐንና በቅዱሳን አድሮ ይኖራልና፡፡” በሚለው ገለጻ ውስጥም ማርያም የጌታ እናት መሆን የቻለችው በራሷ ብቃት እንደሆነ አስመስሎ የሚያቀርብ ነው፡፡ እርሷ ከሴቶች መካከል ተለይታ በእግዚአብሔር ተባረከች እንጂ በራሷ ብቁ ስለነበረች አይደለም ለጌታ እናትነት የተመረጠችው፡፡ ካልሆነ ግን ይህ የእግዚአብሔርን የጸጋ አሠራር የሚጻረር አስተሳሰብ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለተለያየ ዓላማውና ተግባሩ መፈጸሚያነት የተለያዩ ሰዎችን የመረጠው በጸጋው ነው፡፡ እዚህ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረውን ልብ ማለት ይጠቅማል ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤”   (2ቆሮ. 3፥5)፡፡
“ቅዱስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ሳንል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ወሰብእ ብለን ማመንና መዳን አንችልም፤ ቅድስት ድንግል ማርያምን ምልእተ ጸጋ፣ ምልእተ በረከት፣ ሙኃዘ ፍሥሐ፣ ብፅዕት፣ ንጽሕት፣ ቅድስት ስንል ነው ከእርስዋ የተወለደውን ጌታ የባህርይ አምላክ ነው ማለት የምንችለው፣ ምክንያቱም የቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ ጸጋና ቅድስና ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት አስረጅ በመሆኑ ‹‹ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ›› እያልን እመቤታችንን እንድናከብር የእግዚአብሔር ቃል አዞናልና፤ (ሉቃ.1፡45-48)፡፡”
በዚህ ውስጥም ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት የማርያም ወላዲተ አምላክነት ወሳኝ መሆኑ አጽንኦት ተሰጥቶታል፡፡ ቅዱስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ሳንል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ወሰብእ ብለን ማመንና መዳን አንችልም፤ ከማለት የበለጠ ስሕተት ያለ የለም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ያደረገው ከእርስዋ መወለዱ አይደለም፤ ይልቁን እርሷን ወላዲተ አምላክ በሥጋ ያሰኛት እርሱን በሥጋ መውለዷ ነው፡፡ እርሱን የባሕርይ አምላክ ያሰኘው ከእርሷ መወለዱ ነው የምንል ከሆነ ግን ማርያምን ወላዲተ አምላክ የምንልበት አግባብ ስሕተት ያለበት ይሆናል፡፡ እርሷንም አምላክ ናት ወደሚል የስሕተት ገደል ውስጥ ይጨምረናል፡፡ እርሷን ምልእተ ጸጋ፣ ምልእተ በረከት፣ ሙኃዘ ፍሥሐ፣ ብፅዕት፣ ንጽሕት፣ ቅድስት ስንል ነው ከእርስዋ የተወለደውን ጌታ የባህርይ አምላክ ነው ማለት የምንችለው፣ የሚለውም ተመሳሳይ ስሕተት ያለበት ማብራሪያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ኃይለ ጊዮርጊስ ማርያምን ያከበረ መስሎት ክርስቶስን ወዳዋረደበት ስሕተት የሚወስድ ነው፡፡ ማርያምን ያከበረው ክርስቶስ እንጂ ክርስቶስን ያከበረች ማርያም አይደለችምና ቦታቸው መዘዋወር አለበት፡፡ በጥቅሉ እመቤታችንን አስመልክቶ ያለገደብ እየተነገረ ያለው ዘመን አመጣሽ ትምህርት በአግባቡ ሊመረመርና በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ገደብ ሊበጅለት ይገባል፡፡   
ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱና በቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለው ግንኙነት የእናትነትና የልጅነት እንደሆነ ሁሉ፣ በምእመናንና በድንግል ማርያም መካከል ያለው ግንኙነትም በእናትነትና በልጅነት ደረጃ እንዲሆን አዞአል፤ (ዮሐ. 19፡26-27) ፡፡ የተባለውም ሌላው ዘመን አመጣሽ ትምህርት እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳችን የሚለው አይደለም፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ብትሆንም፣ ልጄ እያለች ስትጠራው የነበረ ቢሆንም ግንኙነታቸው በእናትና በልጅ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ በሥጋ የወለደችው ልጇ ቢሆንም፣ አምላኳም መድኃኒቷም ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1 ውስጥ መቶ ሃያ በሚያህሉት ሰዎች መካከል አንዷ ሆና በጸሎት ስትተጋ የነበረው በእናትና ልጅ ግንኙነት ሳይሆን አምላኳና መድኃኒቷ በሆነበት መስመር ነው፡፡ እርሱ ጌታችንም የመጣው በእናትና ልጅ ግንኙነት ተወስኖ ለመኖር ሳይሆን የመጣበትን ዓለምን የማዳን ተልእኮ ለመፈጸም ነውና በዐስራ ሁለት ዓመቱ ወደ ቤተመቅደስ ወጥቶ ሳለ ጠፍቶባቸው እናቱና እጮኛዋ ዮሴፍ እየፈለጉት ባገኙት ጊዜ ስለምን ትፈልጉኛላችሁ? በአባቴ ቤት እኖር ዘንድ እንዲገባኝ አታውቁምን? ማለቱ፣ እንዲሁም በሌላ ስፍራ እናትህና ወንድሞችህ በውጪ ቆመው ይፈልጉሃል ባሉት ጊዜ እናቴ ማናት? ወንድሞቼስ እነማናቸው? እነሆ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ እህቴ እናቴም ነው ማለቱም ይህንኑ ያሳያል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በምእመናንና በድንግል ማርያም መካከል የእናትና ልጅ ግንኙነት እንዲኖር ጌታ አዝዟል የሚለው ለዮሐንስ ብቻ የተነገረውን ለምእመናን ሁሉ በመስጠት እየተተረጎመ ያለ እንጂ የጌታ ትእዛዝ አይደለም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከዚህ ቀደም በዚሁ ብሎግ ላይ Thursday, April 28, 2016ጌታ በመስቀል ላይ እናቱን የሰጠው ለዮሐንስ ነው ወይስ ለእኛም ጭምር?” የወጣውን ጽሑፍ መመልከቱ በቂ ነው፡፡       


መልእክቱ በመቀጠል እንዲህ ይላል፦ በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው አንድን ልጅ አቅፋ፣ አዝላ፣ አጥብታ፣ መግባ፣ ንጽሕናውን ጠብቃ፣ በእንክብካቤ የምታሳድግ እናት ታስፈልገዋለች፤ እናትም የሚያከብራትና የሚያስከብራት ልጅ ያስፈልጋታል፤ እንደዚሁም ሁሉ ጌታችን እመቤታችንን የምእመናን እናት እንድትሆን ሲያደርግ፣ በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ተጎሳቁለን እንዳንጎዳ በጸሎቷ፣ በልመናዋ፣ በአማላጅነቷ እያገዘችና እየደገፈች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ልታደርሰን ብሎ እንደሆነ ልብ ብሎ ማስተዋሉ ተገቢ ነው ፡፡

ይህ በተፈጥሮም በባህላችንም ውስጥ የዳበረውን የእናትና ልጅን ግንኙነት መሠረት በማድረግ የቀረበ የሰው ሐሣብ እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም፡፡ እኛ እንዳንጎሳቆልና እንዳንጎዳ የሚያስብልንና የሚጠነቀቅልን አምላካችን እንጂ ፍጡር የሆነችው የጌታችን እናት ማርያም አይደለችም፡፡ ካልሆነ ግን ይህ የአምላክን ስፍራ ፍጡር ለሆነችው ለጌታችን እናት ለቅድስት ድንግል ማርያም መስጠት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ይህን እንዳናደርግ ያስጠነቅቀናል፤ አድርገን ብንገኝ ደግሞ ርጉም እንደምንሆን ይናገራል፡፡እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል። በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።”  (ኤር. 17፥5-8)፡፡
ከሁሉ የከፋው ገለጻ ግን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹እነኋት እናትህ›› ከተባለበት ሰዓት ጀምሮ እመቤታችንን ወስዶ በቤቱ አኑሮአታል፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እመቤታችን በእያንዳንዱ አማኝ ልጇ ቤት በመንፈስ እየገባች ትኖራለች፡፡ የሚለው ነው፡፡ ማርያም በመንፈስ በእያንዳንዱ አማኝ ልጇ ቤት ትገኛለች ማለት ምን ማለት ነው? እርሷ የጌታችን እናት በመሆኗ ጌታ እጅግ ያከበራት ብትሆንም በባሕርይዋ ከፍጡርነት ወደ ፈጣሪነት ከፍ ልትልና በሁሉ ቦታ ልትገኝ አትችልም፡፡ ይህ እርሷን ምሉእ በኩለሄ የሆነውን የአምላክ ባሕርይ ማላበስና “ምልእት በኩለሄ” ወደማለት መድረስ ይሆናል፡፡ በሁሉ ቦታ መገኘት የፍጡራን ሳይሆን የፈጣሪ ብቻ ባሕርይ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ ማርያም በእያንዳንዱ ሰው ቤት በመንፈስ ትገባለች ማለት ማርያምን ወደ ፈጣሪነት ደረጃ ከፍ ማድረግ ነውና ይህም ስሕተት እርማት ያሻዋል፡፡   
እግዚአብሔር በቅድስት ድንግል ማርያም በኩል የሰጠን ትልቁ ስጦታ ፍጹም ፍቅር ነው፤ ይኸውም በእናትና በልጅ መካከል ያለውን ፍቅር ነው፤ ያ ፍቅር ነው እስካሁን እመቤታችንንና እኛን አስተሳስሮ የሚገኘው፤ ከዚህ ፍቅር ሊለዩን የሚሞክሩትን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል፣ በኦርቶዶክሳዊና በኢትዮጵያዊ መንፈስ ልንቋቋማቸው ይገባል፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምን ብፁዕት ነሽ እያለ የሚያመሰግን ሁሉ፣ እንደ ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላና የእግዚአብሔርን ቃል በምልአት የያዘ መሆኑን እርግጠኛ ይሁን፡፡

ይህም አነጋገር ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም፡፡ እግዚአብሔር ትልቅ ስጦታ የሆነውን ፍጹም ፍቅር የሰጠን በአንድያ ልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ነው እንጂ በማርያም በኩል አይደለም፡፡ በማርያም በኩል የሰጠን ትልቁ ስጦታ ፍጹም ፍቅር ነው የሚለው አነጋገር ከእግዚአብሔር የሆነ ሐሳብ አይደለም፡፡ አንዳችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትም ሆነ ድጋፍ የሌለው ነው፡፡ ማርያምን በክርስቶስ ለመተካት የሚደረግ ጥረትም ነውና ሊታረም ይገባዋል፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠን ፍቅር በክርስቶስ በኩል የተገለጸ ነው፡፡ ይህ ፍቅር ነፍስን በመስጠት የተገለጸ ታላቅ ፍቅር ነው፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም፡፡ የዚህን ፍቅር ታላቅነት ስፋት፣ ጥልቀትና ርዝመት በተመለከተ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር እንዲህ ይላል፤ “ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካሁ፤ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባጠግነት መጠን ይስጣችሁ፡፡ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።” (ኤፌ. 3÷18-19)፡፡ ይህን ፍቅር መቼ ተረዳነውና፣ መቼስ ጠገብነውና ነው የማርያም ፍቅር የሚባል ልዩ ወንጌል የሚሰበክልን? እመቤታችን ራሷ በእዚህ ፍቅር ውስጥ የተያዘች እንጂ ከዚህ ፍቅር ውጪ አይደለችም፡፡ እስከ ሞት ድረስ የወደደንን ክርስቶስን ብቻ እንጂ ሌላ በእርሱ ደረጃ የምንወደው የለም፡፡ እንዲያ የማናደርግ ከሆነ ግን ወደ ጣኦት አምልኮ መሸጋገራችን ነው፡፡ ጣኦት ተጠርቦ ወይም ተቀርጾ ወይም ተሥሎ የሚቆም ምስል ወይም ሥዕል ብቻ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔርን ክብርና ስፍራ የሚሻማና በእግዚአብሔር ቦታ የተቀመጠ ማንኛውም ነገር ጣኦት ነው፡፡
ይህ የተሳሳተ አመለካከት ስሕተት ነው ማለት ተገቢ ነው፡፡ ቅዱስነታቸው ያስተላፉትን ይህን መልእክት ያዘጋጀው አካል እምነት ሊፈተሽ ይገባል፡፡ ይህን ስሕተት ማረም ሲገባ ከዚህ ስሕተት መውጣት አንፈልግም በሚል መንፈስ፣ ከዚህ ፍቅር ሊለዩን የሚሞክሩትን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል፣ በኦርቶዶክሳዊና በኢትዮጵያዊ መንፈስ ልንቋቋማቸው ይገባል፡፡ የሚለው መንፈሳዊ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል መቋቋም አንድ ነገር ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊና በኢትዮጵያዊ መንፈስ መቋቋምስ ምንድነው? ስለ ፍቅር የሚናገር ሰው ስለ እውነተኛ ፍቅር ራሱን አሳልፎ ይሰጣል እንጂ፣ ሌላ እርምጃ ልውሰድ አይልም፡፡ ስለ ፍቅር ከፍቅር ውጪ የሚሰጥ ማንኛውም ምላሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ ክርስቲያናዊም አይደለም፡፡ የጦር ዕቃችን መንፈሳዊ ብቻ እንጂ ሥጋዊም ሊሆን አይገባም፡፡ ስለዚህ ለመቋቋም የእግዚአብሔር ቃል አልበቃ ብሎ ኦርቶዶክሳዊና ኢትዮጵያዊ የተባለውን መንፈስ መጨመር ከትክክለኛው መንፈሳዊነት ውጪ ማሰብ ነው፡፡ 

በአጠቃላይ ስለ እመቤታችን ያለን አመለካከትና ለእርሷ መስጠት ያለብን ክብር በመልእክቱ መጀመሪያ ላይ በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሕ መሰረት መሆን አለበት፡፡ ከዚህ መርሕ ውጪ ከሆነ ግን እግዚአብሔርን እናሳዝናለን፡፡ ስለዚህ ከተጻፈው በማለፍ ለማርያም እየተነገረ ያለው የተሳሳተ ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ መርሕ መሠረት ሊታረምና በእውነተኛው አምልኮተ እግዚአብሔር ብቻ መጽናት አለብን፡፡   

20 comments:

 1. አሜን ወአሜን !!!!

  ReplyDelete
 2. በመማር ማወቅን፡ ፡ በመስማት መገንዘብን፡ በማየት ማረጋገጥን፡ እያገኘን ስንሄድ ወላዲተአምላክን
  እያከበርን በአምላካችን ፍቅር ህያዋን እንሁን። በየአቅማችን የእውቀት አእምሮ ሰጥቶን ብትክክለኛው አምልኮተ እግዚአብሄር ፀንተን ለመኖር ያብቃን። አሜን!!!

  ReplyDelete
 3. እባካችሁን አታድክሙን ፤ እግዚአብሔር ለአክብሮት መስፈርት አላበጀም ። አባትና እናትህን አክብር ሲል እስከዚህ ድረስ ነው የምታከብረው ፤ ከዚህ እንዳታሳልፍ የሚል የለም ። እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ስለሆነች እናከብራታለን እንጂ አናመልካትም ። ከዚህ ያለፈ ሁሉ ድካም ነውና ተዉን ፤ አለበለዚያም እንደምርጫችሁ ።

  ReplyDelete
 4. የጌታዬን፣ የመድሃኒቴን እናት፣ ቅድስት፥ ድንግል ማርያምን (ከእርሷ በነሳው ሥጋና ደም ዓለሙን ሊዋጅ የመረጣት፥ የአምላክ ምርጥ! እመቤቴን!)እስከ ሞት ድረስ እወዳታለሁ! አከብራታለሁ!በምልጃዋ ተማፅኜ ድኅነትን አገኛለሁ!አላፍርባትም። ያፈረ ቀረበት።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Enter your reply...ለአክብሮት ገደብ የለዉም

   Delete

 5. ባነተ ቤት ቅድስት ድንግል ማርያምን ያቃለልህ መስሎሃል የሰይጣን ባርያዎች እኛ ማርያምን እናከብራታለን እንወዳታለን ከኛጋር ትኖራለች ፡፡ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም

  ReplyDelete
 6. No point at all. You do not have a single piece of knowledge on early Church history, particularly on Ecumenical Counsels. You do not have a single piece of knowledge on Chiristology. Simply talking for nothing.

  Please... first study and then later
  you will have a wisdom for writing.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hey!
   “You do not have a single piece of knowledge on early Church history, particularly on Ecumenical Counsels''
   By the way, what does it say and how do you support this with Biblical references?
   I think this writer has clearly explains facts from the Bible and compared how the practice is wrongly looking like in the so called under the ‘religious’ people in Ethiopia. I want you to make points with reference to the Bible so that we do have the chance to compare and then to take position.
   Or you may share as a link if you could wish for there might be lack of enough space to write or support your evidences from the perspective of the Bible.
   Saying ‘’you do not have knowledge’’ is just none sense. The word of God, the Holy Bible, the only governing book in the spiritual world, is all about Jesus Christ, the Messiah. Jesus is the center for true Christians. Holy Bible is the book where True Christians must fully depend up on. Let’s stop our argument in standing about our religious and come back to the word of God. The word of God strongly and clearly puts Jesus as the way to eternal life. We are created in his own image, we’re here to give all the Glory, worship and honor only for Him.
   በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። ……. አትስገድላቸው…….(Exoduse 20:4-5)

   Delete
 7. GETA YIBARKACHEHU!

  ReplyDelete
 8. አዎ !!! እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታችንና ፈጣሪያችን እናት ትወደዳለች በልጦም ትፈቀራለች ትከበራለች ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዶ አክብሮ ባርኮ ቀድሶ ለሁላችን ድህነት ብሎ በውስጧ አድሮ ተወልዷልና በዚህ ማንም ማንም ማንም!!! አይደራደርም፡ ተምሮና አውቆ ብሎም አገናዝቦ በጌታ ቃልና አስተምህሮ መሆን ይገባዋል በሚልው ስስማማ ስሚታውያንን እባካችሁ ብጽሞና ሁኔታዎችን በትክክለኛው የአባቶች አስተምህሮ ተገንዝባችሁ በእውነኛው የተዋህዶ እምነት ጽኑ እላለሁ። በአባቶች ግልጽ ተምሣሌያዊ አባባል እባካችሁ የጭቅጭቅ ቤት ሳይዘጋ ያድራል አታድርጉት።

  ReplyDelete
 9. ለassssssss እባክህን ጽሁፉን መልሰህ መልሰህ አንብበህ አይንህን ከፈት አእምሮህን ጨመቅ አድርገህ ተረዳው በጽሁፉ አስተምህሮ ሃተታዊ ጽሁፍ መስመር ውስጥ አንድም ቅድስት ድንግል ማርያምን ያቃለለ ቃል አይነበብበትም እንዲያውም በሚገባት አክብሮት፡ አፍቅሮት፡ ፈጣሪዋና ጌታዋ እንዲሁም ልጇ አክብሮ ወዶ ባርኮ በሰጣት ከብሯ አስከብሮ ሁላችንም አንብበን ተምረን አውቀን እንድናከብራት ያደረገ መሆኑን ሊገባህ ካልቻለ የሚያደነቁሩህን ዝባዝንኬ ትምህርት የሚያስተምሩህን በማህበር ተደራጅተው ተፈጥሮዋዊ አዕምሮህንና ገንዘብህን ከሚበዘብዙህ ቀሳጮች ርቀህ እስካሁን ጠብቅው ያኖሯትን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ትክክለኛ ትምህርት ቀስመህ ራስህም ተመራምረህ ጸንተህ አምነህ ኑር እልሃልሁ። ለዚህም ፈጣርያችን ብሩህ አዕምሮህን ያጠንክርልህ። አሜን!

  ReplyDelete
 10. እግዚአብሔር ሆይ ንስጥሮስን እንደ ገሰጽክ ዛሬም እነዚህን
  የድንግል ማርያምን ጠላቶች ገስጽልን

  ReplyDelete
 11. Euciminical council of churches had declared a creed called "The Nicean Creed" which in fact annexed the holly spirit as integral part of the trinity; and the decree had assumed mother Marry as the mother of GOD (theotokos);through this, we give her the respect which is utterly her glory that she had blessings from the almighty; any thing which would make her closr to divinity is a hersey and will also make alterations in the trinity.what does it mean when it says that he(christ) becomes as one of us?
  ( እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለስጋ ወእንቲአሁእና ስጋ ኮነ ለቃል) ድህነትም፣መፍጠርም፤ህይወትም፣ፍጹም ምሉእነትም፣ገዥነትም ስልጣንም፣አለቅነትም ውዘተረፈ የመለኮት ብቻ ነው፤ በቀራንዮ የተገኘው ድህነት ከስላሴ እንደሆነ(ስጋ መከራ የክርስቶስ ብቻ ነው)ርቁም ምልጃውም ከራሱ ከአብ እና ከመንፈስቅዱስ ጋር እንደሆነ ያወቀ እንዲሁ ዝም ብሎ ፍጡር እና ፈጣሪን እየቀላቀለ አይኖርም። ፈራጅም ጠበቃም መካከለኛም የሚማልፍም ኢየሱስ ከርስቶስ ነው።

  ReplyDelete
 12. For the truth Orthodox follower, please leave them. The writers of this blog are full of devilry. Why we waste our time with devil? No need to talk and discuss with cloot.

  ReplyDelete
 13. አንድ መሰረታዊ ስህተት አለበት በፅሁፉ ውስጥ። ለመዳን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ ነው ብሎ ማመን እንደሚያስፈልግ ሁሉ በእኩል ደረጃ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውም ልጅ ነው ብሎ ማመን ያስፈልጋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሰው የሆነው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከስጋዋ ስጋ፤ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ነው። ይህ እርሷን ከፍጥረት ሁሉ ይለያታል። እግዚአብሔር በማንም ያልሰራውን ወደፊትም በማንም የማይሰራውን ስራ በእርሷ ሰርቷልና። ይህንን ልናስተውል ይገባል። የእርሷ ብፅዕና እና የሌሎች ብፅዕና የተለያየ ነው። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ጋር ካደረኩት ውይይት የተረዳሁት ኦርቶዶክሳዊያን እና እነርሱ የምንለያየው መሰረታዊ በሆነው የክርስቶስ ማንነት ትምህርት ላይ ነው። በክርስቶስ ማንነት ላይ ስል የመዳናችን መሰረት በሆነው በክርስቶስ ሰው የመሆን ሚስጢር ላይ ማለቴ ነው። ለአንዳንድ ኦርቶዶክሳዊያን ከፕሮቴስታንት ጋር የምንለያየው በቅዱሳን አማላጅነት ወይም በሌሎች ጉዳዮች ይመስለናል ፤ ስለዚህ እንዲሁ ጉንጭ አልፋ ክርክር ስናደርግ እንስተዋላለን። እውነቱ ግን ይሄ አይደለም። እነዚህ ወግኖች ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ እንጅ የሰው ልጅ መሆኑን አያምኑም ማለትም የእመቤታችን የማህጽኗ ፍሬ እንደሆነ አይቅበሉም፤ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋህዶ የተገለጠ የእግዚአብሄ ልጅ፤ የሰው ልጅ ነው ብለን ነው የምናምነው። ፕሮቴስታንት ወገኖቻችን ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ስጋ ይዞ እንደመጣ ነው የሚያምኑት። ይህ ደግሞ የሃሰተኛው ክርስቶስ ትምህርት እንደሆነ መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽ ያስቀመጠው ጉዳይ ነው። ክርስቶስ እኛን በነፍስም በስጋም ያዳነን በተዋህዶ ፍጹም ሰው ሆኖ ነው ማለትም መጽሃፍ ቅዱስ እንደሚል የዳዊት ዘር ሆኖ ነው ፤ የኢየሱስ ክርስቶስን ፍፁም ስው እና ፍፁም አምላክነት ካላመንን ድህነትን አላገኘንም ማለት ነው። ጌታም በዮሃ 8:24 ላይ “እኔ እንደሆንኩ ባታምኑ ከነሃጢያታችሁ ትሞታላችሁ” እንዳለ ማለት ነው። ቅዱስ ዮሃንስ ሰለዚህ የስህተት ትምህርት ሲያስጠነቅቅ በ 1ኛ ዮሃ 4 ፡ 1 -3 ላይ "ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና። የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ። " በማለት ይናገራል። " ሰለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ስው መሆኑን ይህንንም የሰው ባህሪያት ደግሞ በጠቅላላው ከእመቤታችን እንደወሰደ ካላመንን የሃሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ ሰለባዎች ነን ማለት ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከሁሉም በፊት"በርሱ ያመኑ የዘልአለም ህይወት እ ንዲኖራቸው እንጅ እብዳይጠፍእግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወደደ" የተባለው አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መሆኑን ለማስገንዘብ ነው፤ በዩርዳኖስም " በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጀ" እንዳለ ሁሉ ይህንን አሁን በምናስበው ታቦር ተራራ ላይም እንዲሁ በርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጀ እርሱን ስሙት ማለቱ "ኢየሱስ" ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ ማለት ምንጩን ሲያስረግጥ ነው። አሁን ክትስቶስ ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ማለቱን ስናስብ ስጋ መልበሱን መግለጽ እንደሆነ የማይጠየቅ ነው። ይህ በማን ሆነ በአምላክ ፈቃድ በድንግል እንዲጸነስ እና ተወልዶ በስጋ መከራን ከፍሎ እንዲያድነን። አዎን የአምላክ እናት ናት። ችግሩ እናታችን ማርያምን ውደ መለኮትነት ለማሽጋገር የሚመስል ስብከት፣ ከስላሴ በአነስ(እጅግ) ለዛውም፤ የዘወትር ትኩረት መኖሩ የመጽሀፍ ቅዱስ እውቀት የሌላቸውን ሁሉ ማርያምን አዳኝ አድርገው እንዲያዩ እያስገደዳቸው ነው፤ የልዩነትም በር ከፍቱዋል፤ክርስቶስንም ወደ ስው ባህሪነቱ ብቻ እንዲያተኩሩ እያደረገ መምጣቱን መገንዘብ ያስፈልጋል።

   Delete
 14. Listen;I am for sure part and parcel of the Tewahido orthodox denomination for I know that it has the blief derived from the gospel and apostles; but not willing yo embrace preachings and acts which are noy biblical and created by human.I belive in the hypostasis union (ausia); yhat Jesus christ is full human and full devine; knowing that he came from the heavens; it was known early that the Godhead(father) loves the world to the extent of handing his only son to misery(he suffered)-which is GOD's love and likewise the son(Jesus) dare to remain humble that leaving his throne and wanted to become like one of us(human flesh); this is his gift for us and the hollyspirit is also part of this love of the Godhead.እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለስጋ ወእንቲአሁ ስጋ ኮነ ለቃል ይለዋል ይህ መስረታዊ ነው። The main issue is now right at this time those of us who understands the denomination and are attempting to read the bible, are focused on the trinity,we wanted to see all songs, prayers; worship, thanksgiving and liturgy and the likes go to the creator of the universes; the name Jesus is the only name above all names not only for now, but also in the heavens and worlds to come; so glorifying this name has to remain consistant as oftentimes without alterations.Now, the divid here is between who wanted to give every thing for the trinity and those who wanted to place curtain on the trinity. Once every one understands this fact, renewal through the hollyspiriy will takeoff( blast off);and like scribbes and chief prirsts condemn Jesus but he ressurected; those chief priests and scribbes who have occupied the minds of worshipers with their false teachings will be embarrased when the minds of worshipers are renewed by the hollyspirit.I believe that Saint Mary is the mother of GOD( theotokos); I have respect ofcourse;GOD as the sole omnipotent and omnipresent creater is simeltneously everywhere; my connections goes to him in all aspects and situations; the reason why christ die for me is for salivation and redeemption;so why would I need some one to intercede? If I am doing that that means I am devaluating the redeemtion thay has been achieved in Jesus Christ.for all of these;the trinity without division; separation; alteration and without addition is in the divinity that will remain for ever and those of us who are lucky to be part of his beloved heavenly children will aldo be given heavenly renewed life.

  ReplyDelete
 15. ከ እመበፀታችን የነሳው ስጋና ደም ስለሆነ የምነቀበለውም የሷን ስጋ ና ደም ነው ብሎ አንድ ሰባቂ ሲሰብቅ ሰማሁ።እራሱ ከጭቃ ያበጃጀውም አይደል የእመቤታችን ስጋና ደም።ፈጣሪን ከፍጡር እኩል አናድርግ አናወዳድር።ክህደትና የሀሰት አስተማሪዎች ይገሰፁ።እስከመቼ እየተሸቃቀጠ ።አውቆ አጥፊዎች ከእግዚአብሄር ይልቅ ለሰው ፊት የሚያደሉ እግዚአብሄር ልብ ይስታቸው።

  ReplyDelete