Tuesday, August 23, 2016

ግመሉን በዝምታ ትንኙን በጫጫታ


Read in PDF
ከአሸናፊ በላይ
ትንሹ ነገር ያለ ቅጥ ሲጐላና ሲጋነን ትልቁንና ዋናውን ነገር ይሸፍናል፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋናውንና ትልቁን የእግዚአብሔርን እውነታ ቸል ብለውና ትተው ለማይረባውና ኢምንት ለሆነው በአንዳንድ ሁኔታም የእግዚአብሔርን ቃል ለሚቃረነው የወግና የሥርዓት ጉዳይ ብርቱ ጥረት ሲያደርጉ ለተመለከታቸው ግብዞች ፈሪሳውያን ፣ «እናንተ ዕውሮች መሪዎች፤ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ» በማለት በብርቱ ገስጾአቸዋል፤ ማቴ. 23÷24፡፡
ይህንን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለግብዞች ፈሪሳውያን የተናገረውን ትምህርት ያነሳሁት ማኅበረ ቅዱሳን ሊወቀስበትና ሊወገዝበት የሚገባው ዋናውና ትልቁ የኑፋቄ ሐሳብ እያለ ማኅበሩ ለሚፈጥራቸው አንዳንድ ችግሮች ያለቅጥ ትኩረት በመስጠት ዋናውና ትልቁ ጉዳይ ቸል እንደተባለ ለማመልከት ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን አለቆች (ቅዱስ ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባኤ) ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ዋናውን የኑፋቄ ጉዳይ ወደ ጐን ትተው /ቸል ብለው/ ማኅበሩ በሚፈጥራቸው አንዳንድ ችግሮች ላይ ወቀሳ ሲያሳሙ ቆይተዋል፡፡ ማኅበሩ በአስተዳደር ጉዳዮች ጣልቃ እየገባ እንዳስቸገራቸው፤ በቤተ ክርስቲያን ደንብና ሥርዓት ላይ እንዳመፀ፤ ገንዘብ ያለ አግባብ ሰብስቦ እንደተጠቀመ፤ የቤተ ክርስቲያን አለቆችን አላሠራም እንዳለ ፈራ ተባ እያሉ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ አንዳንዶችም «የታመነ ምስክር አይዋሸም»፤ ምሳሌ 14÷5 የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመተላለፍ ስለ መናፍቁ ማኅበር «የቤተ ክርስቲያን ልጅነት፤ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት» ሲለፍፉና ጥብቅና ሲቆሙ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሲቃወሙ ቆይተዋል፤ አልፈው ተርፈውም በተሰጣቸው ሥልጣን የእርሱን እኩይ ፈቃድ በማስፈጸም የማኅበሩ ቀኝ እጅ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ 

አንዳንዶችም ለሥልጣናቸው በመስጋትና በመፍራት፤ አንዳንዶችም ለጥቅም፤ አንዳንዶችም በማኅበሩ የኑፋቄ ትምህርት ተጠልፈው በመወሰድ በማኅበሩ የኑፋቄ ጉዳይ ላይ ምንም ነገር ሳይተነፍሱ ቆይተዋል፡፡ በዚሁ ምክንያት መናፍቁ ማኅበር ያለቅጥ በመፋነን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕይወት እየጐዳ ይገኛል፡፡ በተለይም በወንጌል ሰባኪዎች ላይ የሚያደርሰው ችግር ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ መጥቷል፡፡
እንዴትም ይሁን በምን ሁኔታ፤ በየትኛውም የሥልጣን እርከን ይቀመጡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እግዚአብሔርን ወክለው በሥልጣን ወንበር ላይ በመቀመጣቸው ሃይማኖትን መጠበቅና አድሎ የሌለበት ፍርድ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የወንጌልን እውነት በቁርጠኝነትና በትጋት መጠበቅ ከማንም በላይ  የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዋና ተግባር ነው፤ ገላ. 2÷5፡፡ «ክፋውን ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድንም ለማጥመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመሰክር፤ በፍርድ ነገርም ለድሃው አታድላ»፤ ዘፀአት 23÷2-3 በሚለው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት የቤተ ክርስቲያን አለቆች ትክክለኛ ዳኝነት መስጠት ግዴታቸው ነው፡፡ ይህን ባያደርጉና ለመናፍቁ ማኀበር የሐሰት ምስክርነታቸውን ቢሰጡ፤ በአጋርነታቸውም ቢቀጥሉ ወይም ጉዳዩን እንዳላዩ ሆነው በቸልታ ቢያልፉት የኋላ የኋላ እግዚአብሔር በረጅዎችም በተረጂዎችም ላይ መፍረዱ አይቀርም፡፡ «በደለኛውን ስለጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፤ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው» መባሉን ማስተዋል ይጠቅማል፤ ኢሳይያስ 5÷23፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ሆኑ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ትኩረት አድርገው ሊዋጉትና እርምጃ ሊወስዱበት የሚገባው ዋና የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ኑፋቄ ነው፡፡ የማህበሩ ክፉ ግብሮች ምንጭ የማህበሩ ኑፋቄ ነው፡፡ ማኅበሩ በኑፋቄ ውስጥ ተዘፍቆ እያለ መልካም ሥራ መጠበቅ ከሰይጣን ጽድቅ ከእባብ እንቁላል ርግብ እንደመጠበቅ ይቆጠራል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ስለተዘፈቀበት ኑፋቄ ተፀፅቶ በእውነተኛ ንስሐ ካልተመለሰ ወይም በውግዘት ከቤተ ክርስቲያን ካልተለየ ከመራራ ዛፍ ጣፋጭ ፍሬ አይጠበቅምና አሁን እንደሚታየው በክፋቱ እየባሰና እየደነደነ ይሄዳል፤ 2ጢሞ 3÷13፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ያወጣቸውን ጽሑፎች ብንመረምር ማኅበሩ በድርብርብ ኑፋቄ ውስጥ መዘፈቁን ለማስተዋል አንቸገረም፡፡ ማኅበሩ በምሥጢረ ሥላሴና በምስጢረ ሥጋዌ ላይ የገባበትን ኑፋቄ የሚያመለክተውን ጽሑፍ መነሻ በማድረግ በጥቂቱ እንመልከት፡፡
«መርከቢቱ የእምቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ ኖህ የጌታችን ምሳሌ ነው፡፡ መርከቢቱ ባለ ሦስት ክፍል መሆኗ እመቤታችን የሥላሴ ማደሪያ ለመሆኗ ምሳሌ ከመሆኑም በላይ ተጨማሪ የድንግል ማርያምን ንጽሐ ሥጋ፤ ንጽሐ ነፍስና ንጽሐ ልቡና ያጠይቃል»፤ ሐመር መጽሔት መጀመሪያ ዓመት ቁጥር 1 ጥር 1985 ዓ.ም ገጽ 18፡፡ ምሳሌውና በምሳሌው የተገለጸው ሐሳብ የተሳሳተ ነው፡፡ በጽሐፉ ውስጥ ያሉትን የኑፋቄ ሐሳቦች በአጭሩ እንመልከት፡፡
ኑፋቄ አንድ፡- እመቤታችን የሥላሴ ማደሪያ መሆንዋ
ይህና ሌሎችም የኑፋቄ ሐሳቦች በየአጋጣሚው በማኅበረ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ በስልት እንደሚቀርቡ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ይህንን በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የቀረበውን ሰባልዮሳዊ ኑፋቄ በሌላ ጽሑፍ ከቀረበ ተመሳሳይና የተሳሳተ ሐሳብ ጋር በማስተያየት ለማየት እንሞክር፡፡ በቅድሚያ ስለ ባስልዮስ ጥቂት መግለጫ ልስጥ፡፡ ሰባልዮስ የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት የካደ መናፍቅ ነው፡፡ ትምህርቱ የአካልን፤ የግብርንና የስምን ሦስትነት በማፋለስ አንዱን አካል አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ለዋውጦ የመጥራት ጉዳይ አድርጎ የሚመለከትና በአንዳንዶች ዘንድ በዚህ ዘመን «ኢየሱስ ብቻ only Jesus» እየተባለ የሚጠራ ኑፋቄ ነው፡፡ ይህ ኑፋቄ አብ÷ ወልድ÷ መንፈስ ቅዱስ የሚሉት ስሞች የአንዱ አካል መጠሪያ ሆነው የሚያገለግሉ እንጂ ሦስት የተለያዩ አካላትን የሚያመለክቱ መሆናቸውን አይቀበልም፡፡ ሰባልዮስ በአጭሩ ምሥጢረ ሥላሴን የሚክድ ኑፋቄ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሰውና በሐመር መጽሔት ሰፍሮ የሚገኘው እመቤታችን የሥላሴ ማደሪያ እንደሆነች የሚገልጸው ጽሑፍ ዕንቁ በሚባል በሌላው የማኅበረ ቅዱሳን መጽሔት (አሁን ከሕትመት ውጭ ሆኖአል) ቁጥር ዐ48፤ ነሐሴ 2ዐዐ3 ዓ.ም ገጽ 18 ላይ ተጽፎአል፡፡ ጸሐፊው ሊቀ ትጉሃን ዘርይሁን ሙላት የሚባሉ የማኅበሩ ኑፋቄ ተጋሪ ሰው ናቸው፡፡ የኑፋቄው ሐሳብ በመጽሔቱ እንዲህ ቀርቧል፡፡ ጽሑፉ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ድንግል ማርያምን እንዳበሰራት ከገለጸ በኋላ፤ «ይህ ማለት ሥላሴ ዓለምን ሲያድኑ ድንግል ማርያም የሥላሴ ማደሪያ ለእኛ ደግሞ የመዳናችን ምክንያት ነች ማለት ነው፡፡» ይላል፡፡ ቀጥሎም አብ÷ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ እንደማይከፈል ከገለጸ በኋላ «ስለዚህ ድንግል ማርያም የአብ÷ የወልድ÷ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናት ማለት ነው፡፡» ይላል፡፡ ጽሑፉ ሥላሴን የማይከፈል አንድ ጥቅል አካል አድርጐ ያቀርባል፡፡ እንደገናም ሥላሴ በአብርሃም ድንኳን እንደተስተናገዱ ሁሉ በድንግል ማርያም ማህፀንም ተስተናግደዋል» ማለት ነው በማለት ከ18 ዓመት በኋላ በሐመር መጽሔት ቀርቦ የነበረውን ኑፋቄ  ደግሞ ያነሳል፡፡
በሁለቱም መጽሔቶች የተገለጹት እነዚህ ሐሳቦች በምሥጢረ ሥላሴና በምስጢረ ሥጋዌ ላይ ያነጣጠሩ ኑፋቄዎች ናቸው፡፡ መጽሔቶቹ አብ÷ ወልድ÷ መንፈስ ቅዱስ ሦስት አካላት መሆናቸው ቀርቶ አንድ አካል ሆነው ሥጋ መልበሳቸውን ወይም ሰው መሆናቸውን ይዘው ቀርበዋል፡፡ በመጽሔቶቹ የቀረበው ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ትምህርት ጋር የብርሃንና የጨለማ ያህል ተቃራኒ ናቸው፡፡
እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው፡፡ «እግዚአብሔር፤ መለኮት፤ አምላክ» የሚለው መጠሪያ አንድነቱን ሲገልጽ፤ አብ÷ ወልድ÷ መንፈስ ቅዱስ የሚሉት ስሞች ደግሞ ሦስትነቱን ያመለክታሉ፡፡ አብ÷ ወልድ፤መንፈስ ቅዱስ በፈቃድ፤ በአገዛዝና በሥልጣን አንድ ናቸው፡፡ አብ እውነተኛ አምላክ ነው፤ ወልድ እውነተኛ አምላክ ነው÷ መንፈስ ቅዱስ እውነተኛ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሦስት አካላት የተገለጸ አንድ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሦስትነቱ ባለሦስት ስሞች፣ ባለሦስት አካላትና ባለሦስት ግብሮች ነው፡፡
ሦስቱ አካላት በየራሳቸው ስም ይጠራሉ እንጂ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም፡፡ አብ፤ አብ እንጂ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም፡፡ ወልድ ወልድ እንጂ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ እንጂ አብ ወይም ወልድ አይባልም፡፡ አብ÷ ወልድ÷ መንፈስ፤ ቅዱስ በየራሳቸው አካል አላቸው፡፡ አብ በራሱ አካል አለው፡፡ ወልድም በራሱ አካል አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስም በራሱ አካል አለው፡፡ አብ የራሱ ግብር አለው፡፡ ወልድም የራሱ ግብር አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስም የራሱ ግብር አለው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት ሐሳብ «ሠለስቱ ገጻት፤ አሐዱ አምላክ» በማለት ይገልጹታል፡፡
እነዚህን ሐሳቦች እንያዝና አሁን ሥላሴ በድንግል ማህፀን ሥጋ ስለመልበሳቸው ወይም ሰው ስለመሆናቸው እንነጋገር፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስና እንደ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ትምህርት ሥጋ መልበስና ሰው መሆን፤ በመስቀል ላይ መከራ ተቀብሎ መሞት፤ ከሞት መነሣት፤ ሊቀ ካህናትነት ክርስቶስ በተለየ አካሉ ያከናወነው የክርስቶስ የብቻው ግብር ነው፡፡ አብና መንፈስ ቅዱስ በድንግል ማርያም ማህፀን አድረውና ሥጋ ለብሰው ሰው አልሆኑም፡፡ ያለ ወንድ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ተፀንሶ ኃጢአት የሌለበት እውተኛ ሰው ሆኖ የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ነው፡፡ ስለሆነም፤ «ሥላሴ» (አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ) በድንግል ማሕፀን ሥጋ ለብሰው ሰው ሆነዋል» የሚለው ሐሳብ ሰባልዮሳዊ ኑፋቄ ነው፡፡
ይህንኑ ሰባልዮሳዊ ኑፋቄ የሚያሳይ ሌላውን ሐሳብ ደግሞ እንመልከት፡፡
«ልክ እግዚአብሔር የሚለው ስም በውስጡ የአብ÷ የወልድ÷ የመንፈስ ቅዱስን እንደያዘ ኢየሱስ የሚለውም ስም አብ÷ ወልድ÷ መንፈስ ቅዱስ የሚለውን ይዟል፡፡» ይህ ደግሞ «ሥላሴ» በስም ሦስት ናቸው የሚለውን እውነት በማፋለስ የቀረበ ኑፋቄ ነው፡፡ እንዲህ እንዲህ እያልን የኑፋቄውን ሐሳብ መመልከታችንን እንቀጥል፡፡
«ስለዚህ ኢየሱስ የሚለው ስም የፈጣሪ የእግዚአብሔር፤ ወልድ የሚለው ደግሞ ሰው በሆነበት ዘመን የተጠራበት ሲሆን እግዚአብሔር ሊመለክበትና ሊጠራበት ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ያዘጋጀው ስሙ ነው» ይህ ሐሳብ ምን ያህል የተሳከረና የተምታታ እንደሆነ አንባቢያን በቀላሉ ማስተዋል ስለሚችሉ ማብራሪያ መስጠት እምብዛም አስፈላጊ አይደለም፡፡
ይህ ኑፋቄው ማኅበሩን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ብቻ ሳይሆን «መንፈሳዊ አባቴ» ከሚላቸው ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ጋርም ያጣላዋል፡፡ ይህንን የኑፋቄ ሐሳብ የሚያፈርሱ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ተመልክተን ወደ አባ ጎርጎርዮስ ሐሳብ እንለፍ፡፡
«መልአኩም እንዲህ አላቸው፡- እነሆ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ እነግራችኋላሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡ … ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” ሉቃ. 2÷1ዐ-11፤ ገላ 4÷4፡፡
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የቤተ ክርስቲያንን የሃይማኖት ትምህርት በመጥቀስ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፡፡
«ቃል በማይመረመር መግቦቱ ሰው ኸኖ፤ ሥጋ ለብሶ ከኃጢአት በቀር ሰው የሚሠራውን ኹሉ ሠራ» (የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ ገጽ 136)፡፡
«በምሥጢረ ሥጋዊም ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ በፍጹም ባሕርያዊ ተዋሕዶ ከቅድስት ድንግል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሰዋ ነፍስ ነስቶ እኛን ለማዳን መወለዱን፤ ጥምቀቱን፤ በጲላጦስ ዘመን መሰቀሉን፤ መሞቱንና መነሣቱን፤ ወደ አብ ማረጉን፤ ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን መላኩንና ኋላም ለፍርድ መምጣቱን ታስተምራለች፡፡  (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ 1986፤ ገጽ 1ዐዐ- 1ዐ1፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እንጂ ሦስቱም አካላት በማርያም ማህፀን እንዳላደሩና ሥጋ ለብሰው ሰው እንዳልሆኑ ታስተምራለች ፡፡
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የግብር መፋለስንም በሚከተለው ሁኔታ ገልጸዋል፡፡
«የሥላሴን አንድነት የሚያመለክተውን ‘መለኮትን’ ለአካል ግብር ቅጽል አድርጐ ማቅረብ ሦስቱንም ወላድያን፤ ሦስቱንም ተወላድያን÷ ሦስቱን ሠራጺያን ማለት ነው፡፡ ስምንና ግብርን ያፉልሳል አንድነትን ሦስትነትን ያጠፋል፤ ያደናግራል» (እንዳላይኛው ገጽ 1ዐ6)፡፡ ዕንቁ መጽሔት አብ፤ ወልድ÷ መንፈስ ቅዱስን የማይከፈል አንድ ጥቅል አድርጐ ያቀረበበት ሐሳብ ደግሞ እንሆ፡-
«አልአዛርን አብና መንፈስ ቅዱስም ጭምር እንጂ ኢየሱስ ብቻ ከሞት አስነሣው ማለት አይቻልም፡፡»
ተወላዲ የሆነው እግዚአብሔር ወልድ በተወላዲ ግብሩ ኃጢአት የሌለበት እውነተኛ ሰው ሆኖ በየቦታው እየዞረ ወንጌልን እንዳስተማረ፤ ድንቅና ታምራትን እንዳደረገና ሕሙማንን ራሱ እንደፈወሰ አራቱም ወንጌላት ጽፈዋል (ለምሳሌ ዮሐ 2ዐ÷3ዐ)፡፡ የአልአዛር ከሞት መነሣት ጌታ ካደረጋቸው ድንቅና ታምራት አንዱ ነው፤ ዮሐ 11÷11 እና ቁጥር 43-44፡፡ ይህንን በመጽሔቱ የቀረበውን ሐሳብ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ፈጽሞ ያፈርሰዋል፡፡ «ብዙ ድንቅ ድንቅ ታምራትን ያደረገው እሱ ተራበ፤ ተጠማ፤ አዘነ፤ አለቀሰ፡፡ በጌቴሴማኒ የጸለየው በጐልጐታ መራራ ጩኸት ያሰማው እሱ የዕለት ሬሳ ወልደ መበለትን፤ ወለተ ኢያኤሮስን ፤ የአራት ቀን ሬሳ አልአዛርን ያስነሳው ራሱ ሥግው ቃል ነው»፤ (የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፤ 1978 ዓ.ም ገጽ 1ዐ3)፡፡
ይቀጥላል

12 comments:

 1. Glory to God the Father, God the Son, and God the Holy Spirit! God bless our brother! keep such beautiful theological analysis which is the foundation of Christianity.

  ReplyDelete
 2. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 3. With your endless and senseless heretic accusations, You keep proving that MK is doing right.

  ReplyDelete
 4. weregna hula enant wedetach sitadigu mahibere kidusan wedelay eyadege eyetemenedege hede enante gena kene akatachihu titefalachihu esu ynoral

  ReplyDelete
 5. ሲጀመርም የማህበረ ቅዱሳን (እርኩሳን) መሥራቾች ለእውነትኛዋ ቅድስት ቤተክርስቲያን መዕመናን ለመሆን ሳይሆን መሠሪ የሃገር አፍራሾች ጭፍን ፖለቲካ ኣራማጆች በመሆን የብፁዑን ኣባታችን እቡነ ጎርጎርዮስን የሰላ የእግአብሄርን ትምህርት በአቋራጭ አግኝተው በየማስታወሻ ደብተራቸው በእጅ ጽፈው በመያዝ በአገር ቤት ስለሚታወቅባቸው በውጭው ዓለም ከኪሳቸው በማውጣት ሰባⷋን ነን የአስተማሩን አቡነ ጎርጎርዮስ ናቸው እያሉ ትምህርተ ኑፋቄያቸውንና የጭፍን ፖለቲካ ዓላማቸውን የሚረጩ፡ በዚህም የክርስቶስን ትምህርት ተከትሎ የወጣትነት ዕድሜውን በየቤተክርስቲያኑ አገልግሎት በመስጠት በሥረዓት ለመኖር የሚዋትተውን እያወናበዱ አዕምሮውን፡ ገንዘቡን፡ ጉልበቱን፡ እየበዘበዙ የመሠሪ አመፃቸው አድማ መተግበሪያ ፈጻሚ እያደረጉት መሆኑን ሁላችንም ተገንዝበነዋልና መንግሥትም ይህን ድርጊታዊ ዝግጅታቸውን ህዝብን የማበጣበጥ ጉዳይ አድርጎ በመውሰድ ሳይቃጠል በቅጠልን ሥራ ላይ አውሎ መንፈሳውያን ብፁዓንና ቅዱሱን አባቶች በህግ ከለላና ፍትህ በመታደግ መሠሪያውያን (ማቆች) ተመካሪ ሆነው የሚመለሱ ከሆነ እንዲመለሱ ካልሆነ መንጋውን እንደዘመሚት ኩይሳ ከመከመራቸው በፊት እንዲዘበጡ አሳሳባለሁ። እዚህ ላይ ሳላልፈው የማሳስበው ቢኖር አባቶችም ራሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና ብቃት አባት ሆነን የእግዚአብሄርን መንጋ እናገለግላለን ብለው በገቡት ራስን ገዝተው ምዕመኑን ለአምላክ ሥርዓት እናስገዛለን በማለት ነውና መንፈሣዊ አባትነት ያገኙት በማቅና ሌሎችም ጋጠ ወጥ ድረ ገጾች ላይ የእምነታችን ዓምድ በሆኑት አባቶቻችንና በዚሁ ምክንያት እምነታችንንና ቤተክርስቲያናችንን የሚኮስስበት ስድብ ተሳዳቢዎችንንና መድረኩንም የሰጧቸውን ሃላፊዎች ህግ ፊት በማቅረብ ይህ ሁኔታ ተጠያቂነት ኖሮት ፍትህ እንዲደረግበት ለማድረግ የመንፈስ ቅዱስ ህግ አዋቂ ልጆቻችሁን እርዳታ በመጠየቅ እንዲቆም ይኖርበታል እላለሁ ለአሁኑ ይብቃኝ በአማኝነት አቋሜ መሠሪዎችን ለመታገል አልደክምም ሁላችንንም ህያው አምላክ ይርዳን አሜን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኃራጥቃ የማይጠቅም እቃ

   Delete
 6. really!!! yemyen wed abey mhonu naw

  ReplyDelete
 7. የማቅ ካድሬ ታደሰ ከበደ ምን ፤ በበላበት ይጮኻል አሉ- ማቆች አንተንና መሰሎችህን የዋሃን ስሜታችሁን በሚሸጡት ዘቢብ እያሰከሯችሁ ጃስ ጩህ ስለሚሏችሁ አንብበህ ሳትረዳ ባልገባህ ትምህርት ደርሶ ተሳዳቢና ተራች ያደርጉሃልና ሂድ ተናከስ ሳይሉህ በዕውቀት ራስህን አስገዛና እባክህ ወንድሜ ብዬ እንድጠራህ ሁን።

  ReplyDelete
 8. To Thee Anonymous ኩርምባጥ of Aug.24,2016 at 5:50 PM
  Please try to grub some GOD forbid Accusation comes out from your ጨቅላ mentality.

  ReplyDelete
 9. Tadese Kebede ersun be kerstos fit lefred setkom tayewalh.ya yeferahew yetelahew sim balbet eyesus new ferajju. Mahber keza yeferd ken ayasmeltehim .selemahberu Yemtemesekerewon gemash sele kerstos mesker.yemiyadnhim Yemikonenim esu bich new.

  ReplyDelete