Wednesday, August 3, 2016

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ ሊቃውንት አለቆች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል አስመራጭ ኮሚቴውን በመቃወም ለፓትርያርኩ ደብዳቤ አቀረቡብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስድርጊቱ በግሌ በጣም አሳዝኖኛል፣ በዚህ ጉዳይ የማያዝን የሲኖዶስ አባል አለ ብዬ አላምንም
ባለፈው ሰኞ (በ25/11/2008 ዓ.ም) የኤጲስ ቆጶሳትን አስመራጭ ኮሚቴ ኃላፊነት የጐደለው ሥራ በመቃወም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የአድባራትና የገዳማት አለቆች፣ ጸሐፊዎች ሰባክያነ ወንጌል በተገኙበት በቅዱስነታቸው /ቤት ብስለት የሚታይበት፣ ከበድ ያለ መልእክት ያዘለና ቤተክርስቲያንን ማእከል ያደረገና ከአንድ ሺሕ አምስት መቶ በላይ ሰዎች የፈረሙበት የተቃውሞ ደብዳቤያቸውን በንባብ አሰሙ፡፡ አስተያየትም ተሰጥቶአል፡፡  
 ደብዳቤው በተነበበበት ሥነ ሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ ዲዮስቆሮስ፣ ፀሐፊው አባ ሳዊሮስ ተገኝተዋል፡፡ ቅዱስነታቸውድርጊቱ በግሌ በጣም አሳዝኖኛል፣ በዚህ ጉዳይ የማያዝን የሲኖዶስ አባል አለ ብዬ አላምንምያሉ ሲሆን፣ ሥራቸውን የሚያውቁት አባ ዲዮስቆሮስና አባ ሳዊሮስ ግን አንድም ቃል ትንፍሽ ማለት አልቻሉም፡፡

አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር፣ አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቋልናበሚል መሪ ጥቅስ የሚጀምረው ደብዳቤው “… ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የወደቀችበትን አዘቅት ስንመለከት ትንቢቱ ደርሶ ሊቃውንቱን፣ ካህናቱንና ምእመናኑን በብዙ መንገድ አንገት ያስደፋ ተግባር ተከስቷል፡፡ እየተከሰተም ይገኛል፡፡ በሁሉም ስፍራ በመንፈሳዊው አሰራርና አኗኗር ደግ ሰው አልቋልና አቤቱ አድነኝ የሚለው ዝማሬ የሁሉም እንጉርጉሮ ከሆነ ቆይቷል፡፡ካለ በኋላ ቤተ ክርስቲያኗከጥቂት ዓመታት ወዲህ ያለው ጊዜ ቁልቁል የወረደችበት፣ የነበረው ክብርዋ ጥላሸት ተቀብቶ አኩሪ ታሪኳ ተቀብልሶ መብቷንና ኃላፊነቷን ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ አሳልፋ ለማይመለከታቸው አካላት ያስረከበችበት፣ ዶግማና ቀኖናዋ ፈተና ላይ የወደቀበትጊዜ መሆኑን ገልጿል፡፡ በማስከተልም አስመራጭ ኮሚቴው የፈጸማቸውን ስሕተቶችና ጥፋቶች በሚከተሉት ስድስት ነጥቦች ሥር በዝርዝር አቅርቧል፡፡
1.      ፍትሕ መንፈሳዊንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መጣሱ
2.     በምንኩስናና በመነኮሳት ህልውና ላይ የፈጠረው አደጋ
3.     የቤተ ክርስቲያንን ዓላማ በሚጻረር መልኩ ጵጵስናን በብሔርና በጎጥ እንዲሆን ማድረጉ
4.     ኮሚቴው የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ የሆነውን ጵጵስናን ለገንዘብ ፍጆታ ማዋሉ
5.     ያለ ብሔራቸው የተቀመጡትና በአገልግሎት ላይ ያሉትን ሊቃነ ጳጳሳት የሚያፈናቅል ተግባር መሆኑ፣
6.      በሀገር ደኅንነትና ሰላም ላይ ሥጋትን የሚያመጣ መሆኑ በሚሉት ነጥቦች ስር በማስረጃ የተደገፈና ምክንያታዊ የሆነ አስተያየትና ሐተታ አቅርቧል፡፡
በመጨረሻም በደብዳቤው ኮሚቴው ስለፈጸመው ስሕተት በሕገ ቤተክርሰቲያን እንዲጠየቅና የሄደበት የተሳሳተ መንገድ ያቀረበው የተጭበረበረ ጥቆማም እንደገና እንዲመረመርጠይቋል፡፡ ፓትርያርኩና ብፁዓን ጳጳሳት ጉዳዩን በቀላሉ እንደማያልፉት እምነት አለን ያሉት የተቃውሞ ድምጻቸውን ያሰሙት ሊቃውንቱ፣ የደብር አለቆቹ፣ ካህናቱና ሰባክያነ ወንጌሉበምንም ምክንያት እንዲሆን ከተደረገ ግን ከታሪክ ተወቃሽነት ለመዳንና ቤተ ክርሰቲያንን ለመታደግ ሲባል በአደባባይ ተቃውሞአችንን ለመግለጽ የምንገደድ መሆኑን ስናሳስብ በትሕትና ነው፡፡ብለዋል፡፡ 
ደብዳቤው ከተነበበ በኋላ ከተቃውሞ ድምጽ አሰሚዎቹ የተሰጡ አስተያየቶች የነበሩ ሲሆን ከአስተያየቶቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
·         ጵጵስናውን ላያገኙት ነገር ተደብቀው ያሉ ሁሉ ተሰድበዋል
·         አስመራጭ ኮሚቴው ሙያ ተኮር ምሁራንን አላካተተም ቢያንስ ላወጣው የቤተክርስቲያን  መስፈርት ተጠያቂ መላሽ ጳጳሳትን አላካተተም፡፡
·         የቀረቡት ማስረጃዎች ፎርጅድ ለመሆናቸው ማረጋገጫ አለን፣ የሐዲሳት፣ የቅኔ፣ የመጻሕፍት መምህራን ነን ብለው ያቀረቡ ሰዎች በዚህ ሙያ እንዳላለፉ ማረጋገጫ አለን፡፡
·         ገንዘብ ተጠይቀን ሰጥተናል ያሉ ገጥመውናል
·         በሐራ ተሰድበው የወጡ መነኮሳት ታሪክ እውነት ከሆነ ከዚህ በፊት በሌሎች ብሎጐች የተሰደቡ ጳጳሳት ታሪክም እውነት ነው ማለት ነው፡፡
·         ጥሩ የዘሩ ተገልብጠው አሁን ኮሚቴው ጓያ ዘራበት
·         ሂደቱ አስከፊ ከመሆኑ የተነሣ የአብነት መምህራን፣ የቆሎ ተማሪዎች፣ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን ይህ ጉዳይ መፍትሔ ካላገኘ ብለን እንወጣለን ሲሉ በኮሚቴው ላይ የነበራቸውን ቁጣ ገልጸዋል፡፡ 
    
    ደብዳቤው እነሆ
       

3 comments: