Thursday, September 29, 2016

ቤተ ክርስቲያን የማን ወኪል ናት?ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት አምባሳደር እንደ መሆኗ በዚህ ምድር ላይ ሳለች የምትወክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ያለችው የምትታየዋ ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳን በዚህ ዓለም ጉዳይ ውስጥ በተለይም በፖለቲካ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊ ባትሆንም ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ተከትሎ በአገር ላይ በሚፈጠሩ ችግሮች የማስታረቅና ሰላምን የመስበክ የማይተካ ሚና አላት፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን በመንግሥትና በሕዝብ መካከል የተፈጠሩትን ግጭቶች ለመፍታት በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚናዋን መወጣት ተስኗት ታይታለች፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ በፓትርያርኩ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኩል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠችው መግለጫ ሲፈተሽ በተፈጠረው ችግር ተዋናይ የሆኑትን ሁሉ ሳይሆን አንድን ወገን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ ብቻ መሆኑ ሚዛናዊነት የሚጎድለውና ለመንግስት የወገነ ገጽታ ያለው ሆኖ አልፏል፡፡ ነሐሴ 3/2008 ዓ.ም. የወጣው መግለጫ በውስጡ የቤተ ክርስቲያኗን ሚና በተመለከተ “በአገር ውስጥ አለመግባባት ሲፈጠር አንዱን ከአንዱ ሳትለይና ሌላውን ሳታገል ሁሉንም በእኩልነትና በልጅነት መንፈስ በማየት ስትመክር ስታስተምርና ስታስማማ የነበረች አሁንም ያለች ለወደፊትም የምትኖር የቁርጥ ቀን እናት ቤተ ክርስቲያን ናት” ቢልም እዚያው ላይ ግን የሕዝብን ወገን እንጂ የግጭቱ አካል የሆነውን መንግስትን የሚገሥጽም ሆነ የሚመክር ቃል አልተጠቀሰበትም፡፡ ይህም ከላይ የተጠቀሰውንና ስለ ራሷ የሰጠችውን የራሷን ምስክርነት የሚቃረን ሐሳብ መስጠቷ ትዝብት ላይ እንድትወድቅ ከማድረጉም በላይ በተግባር የወገነችው ወደማን እንደሆነ አመላክቷል፡፡ በመግለጫው ውስጥ ከተጠቀሱት ነጥቦች መካከል ሁለቱን እንመልከት፡፡

“በየአካባቢው የሚገኘው አዛውንቶች ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና አባወራዎች እንዲሁም እማዎራዎች ልጆቻቸውንና የአካባቢው ወጣቶችን በመምከርና በማስተማር የሰው ሕይወት ከጥፋት፣ የሀገር ሀብትን ከውድመት እንዲታድጉ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች፤”
በዚህ ነጥብ ሥር የሰው ሕይወት እንዲጠፋና የሀገር ሀብት እንዲወድም ምክንያት የሆኑት ልጆችና ወጣቶች እንደሆኑ ብቻ ነው የጠቀሰው፡፡ ነገር ግን መግለጫው በወጣ ጊዜ መንግሥትን ስሙን ጠቅሶ እርሱም በበኩሉ እንደ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ምክር መስጠት ለምን ከበዳት? በኋላስ በሕዝቡ በኩል ለደረሰው ጥፋት አጸፋዊ ምላሽ ሲሰጥ ለጠፋው የሰው ሕይወት የመንግስትስ እጅ የለበትም ወይ? ምነው ታዲያ መንግሥትም ችግሩን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታና የሃይል እርምጃ እንዳይወስድ መልእክት ማስተላለፍ ተሳናት? ይህ ሁሉ የሚያሳየው ቤተ ክርስቲያን ሕዝቡን ብቻ እንጂ መንግስትን ለመገሰጽ አቅም እንዳነሳት ነው፡፡  
የመግለጫው ሌላ ነጥብ እንዲህ የሚል ነው “ሁሉም ወገኖች አለን የሚሉትን ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ በውይይትና በምክክር እንዲሁም በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ በመጓዝ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ያደርጉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች፡፡” ይህም ነጥብ ችግሮች ሕጋዊ መንገድን በመከተል መፈታት አለባቸው የሚል ቢሆንም መፍትሔው የእርሷ ሐሳብ ወይም ከቤተ ክርስቲያኗ የተገኘ ሳይሆን የመንግስት አካላት በተለያዩ አጋጣሚዎች በመንግስት ሚዲያዎች ተቀባብለውና ደጋግመው ያሰሙት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የቃላት ለውጥ እንኳን ሳታደርግ ያንኑ ሐሣብ እንዳለ መድገሟ ወገናዊነቷ ለማን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን የራሷ የሆነ መልእክት የሌላት መሆኑን ያሳየ ሆኖ አልፏል፡፡
ይህን ተከትሎ ብዙዎች የእምነቱ ተከታዮች እንደተከፉና ችግሩ በተከሰተባቸው በጎንደርና በጎጃም አካባቢ ብዙዎቹ የካህናትና የምእመናን ወገኖች ከፍተኛ ቅሬታ እንደገባቸው፣ ግጭት ካሳደረው ተጽዕኖና ለብዙዎች መታሰርና የሕይወት ጥፋት ምክንያት መሆኑ እስካሁን ድረስ ጉዳዩ ሳይፈታ በእንጥልጥል እንዲቆይ አድርጎታል፡፡ በጎንደር የመስቀል በዓል እንደከዚህ ቀደሙ ባለ መንገድ በመስቀል አደባባይ አለመከበሩም የችግሩን ትልቅነት የሚያሳይ ነው፡፡ ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ለቤተ ክርስቲያኗ ትልቅ ችግር ነው የሚሆነው፡፡
በሕገ መንግስቱ መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆኑ ቢደነገግም እንደዚህ ባለ አጋጣሚ የሚንጸባረቁ አንዳንድ ሁኔታዎች ግን መንግስትና ሃይማኖት ተለያይተዋል የሚለውን ድንጋጌ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ለልጆችና ለወጣቶች ምክር የለገሰችውን ያህል መንግስትን መምከርም ሆነ መገሰጽ ያልቻለችው ከምን የተነሳ ነው? መንግስት መመከርና መገሰጽ ስለሌለበት ነው? ቤተ ክርስቲያን እንዲህ እንዳይባል መንግስት ራሱ ራሴን ገምግሜያለሁ ካለ በኋላ ጥልቅ ተሐድሶ ያስፈልገኛል ሲል እርሱ የሚገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ መስክሯል፡፡ መቼም ጥልቅ ተሐድሶ ያስፈልገኛል ያለው ችግሮቹ ጥልቅ በመሆናቸው ነው፡፡ ታዲያ በጥልቅ ችግሮች ውስጥ እንደሚገኝ ራሱን የገመገመውን መንግስት መምከርና መገሰጽ አይገባትም ነበር ወይ?
መገሰጽና መምከር ያልቻለችው ይህን የሚከለክል የመንግስት እጅ በቤተ ክህነቱ ውስጥ ስላለ ነው? ወይስ የቤተ ክህነቱ ሹማምንት አድርባይ ሆነውና መንግስትን ደስ ለማሰኘት ካላቸው ፍላጎት በመነጨ ነው? ወይስ ቤተ መንግስትና ቤተ ክህነት ከ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ በይፋ የፈጸሙት ጋብቻ በደርግ መንግስት አማካይነት የፍቺው ወረቀት ቢቀደድም ፍቅራቸው ከልባቸው ስላልወጣ የዚያ ውጤት ይሆን?
ቤተ ክርስቲያኗ አቋሟን እንደገለጸችው ለሁሉም ወገን በእኩል መቆም፣ ሁሉንም እኩል መምከርና መገሰጽ የሚገባት መሆኑን በተግባር ማሳየት አለባት፡፡ በዚህ ወቅት እንዲህ ባለማድረጓ ያዘኑትን ሁሉ ይቅርታ መጠየቅና ለመካስ ራሷን ማዘጋጀት ይገባታል፡፡ በቀጣይም ሚዛናዊነትን የተሞላና ሁሉንም ወገን የሚጠቅም ወደ ሰላም የሚያመጣ ሥራ መሥራት አለባት፡፡ በተለይም በየጊዜው የሚሰጡ መግለጫዎችና የሚተላለፉ መልእክቶች ከቤተ መንግስት ሳትዋስ ከራሷ የመነጩና በራሷ መንገድና ቃላት ጭምር የተዘጋጁ መሆን አለባቸው፡፡ መንግስት የሚለውን በመከተልና እንዳለ በማስተጋባት ሳይሆን መንግስት የሚለውን በእግዚአብሔር ቃል ፈትሻ የተሻለውንና በጎ የሆነውን ለአገር የሚበጀውን ለመንግስት ጭምር በሚጠቁም መልኩ መንፈሳዊ መልእክት ማስተላለፍ ይኖርባታል፡፡ ካልሆነ ግን አምባሳደርነቷ ለምድራዊው መንግስት እንጂ ለሰማያዊው መንግስት መሆኑ ይቀራል፡፡
ሰሞኑን ባሕርዳር ከተማ ለደመራ በዓል ለተሰበሰበው ሕዝብ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ያስተላለፉት መልእክት ከአንድ ሊቀ ጳጳስ የሚጠበቅ ነው፡፡ ሆኖም ንግግራቸው ሙሉ በሙሉ ስሜት የተጫነው አልነበረም ማለት ባይሆንም መወቀስ ያለባቸውን ክፍሎች በተገቢው መንገድ መውቀሳቸው ተገቢነት ያለውና ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ሌሎቹም አባቶች ደጋፊም ተቃዋሚም ሳይሆኑ በሃይማኖት አባትነታቸው ከዚህ በበለጠ ከስሜት ነጻ የሆነ ሚዛናዊነትን የጠበቀና ለሁሉም አካል ተደራሽ የሆነ መልእክት ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና አትዮጵያውያት የምትሆን ኢትዮጵያ እንድትኖር በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚኖሩ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ እውነተኛ ብሔራዊ እርቅ እንዲወርድና ሰላም እንዲፈጠር በሃይማኖት አባትነታቸው ጥሪ ማስተላለፍ አለባቸው፡፡

6 comments:

 1. " Amarna orthodox betkerstyanen akerkarewn sebernew" eyalu sedenefu yet neberachehu!!!

  ReplyDelete
 2. ሰሞኑን ባሕርዳር ከተማ ለደመራ በዓል ለተሰበሰበው ሕዝብ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ያስተላለፉት መልእክት ከአንድ ሊቀ ጳጳስ የሚጠበቅ ነው፡፡

  ReplyDelete
 3. Aba Abraham advise was one sided. Isn't he the one who creates trouble in the EOTC by working secretly with Mahibere kidusan to fulfill their hidden political agenda. How come he didn't condemn the destruction of property and the chasing of EthiopiAn citizens to Sudan from Gonder just because they were not Amhara. Aba Abraham ideas were biased and not expected from a religious person.

  Oromo people are the majority in Ethiopia. I think they have the capacity and brain to lead Ethiopia in the right direction. Why do Amahara oppose to Oromo's leadership all the time but now try to include them in their protests with hidden Agendas? Oromo people know The true character of Amhara people. I think Amhara people will benefit more if Oromo leads the country.

  ReplyDelete
 4. ሂድ የብጥብጥ ሰልፍ ውስጥ ግባና ድንጋይ ለማቀበልና ለመወርወር ሞክር አከርካሪህ ሲሰበርና ያላደግከውን ቁልቁል ስትሽመደመድ ያኔ እጅህን እያርገበገብክ የሃይማኖት አባቶች አላስጣሉኝም በል፤ ለፍላፊ፤ ቀባጣሪ ሁላ። የመስፍን ፡ የመራራ ፡ የቀርቃራ የአጉራራ ፍልፍል ሁላ፤ ውርደ ወሬኛ የመሀራ መክፈልትና የቤተክርስቲያን ሙዳየ ምጽዋት ሰብሮ ለቃቃሚ ሁላ፡፡ የቤተክርስቲያን ግድግዳና የምዕናን ውስጥ ዘመሚቶች። ደርሶ አዛኞች ቅቤ አንጓቾች። ለመሆኑ አንተ ማንህና ነው የሃይማኖት አባቶች እንዲህ አላሉም እንዲህ አልተናገሩም እያልክ የምትቀበጣጥረው አሸርጋጅ ሁላ የዶላር ሙዳየ ምጽዋት ፍርፋሪ ተላከልህ መሰለኝ። የእናት ቤተክርስቲያን አባቶች በጸሎት በስግደት ወደአምላካችን ያመለክታሉ እንጂ ብየድረገጹና አደባባይ ላይ እየወጡ እንዳንተና እንደ አባቶችህ መቀባጠር አይኖርባቸውም እባክህን ሰውና አምላክ በግልጽ የሚያውቁብህን ኑሮህን ከዲያብሎስ አባትህ የወረስከውን እየቃረምክ ኑር ሌሎቻችንን አትቀባጥርብን በቅቶናል..>>>

  ReplyDelete
 5. Whether U approved it or not eat it that is u. u and ur very mach called vilifiers የማይረባ ቁራ ጯሂዎች.....>>»

  ReplyDelete
 6. ለምን ድንነው በትክክል ስለምታምነው ወይም ስላለህበት የእምነት መሪዎች የማታወራው መቼም ምእመን ውስጥ ጥሩ ነገር ለመፍጠር ነው አይደል በርግጥ የገቢ ምንጭህ እነሱ ናቸው ተኩላው ተው ለምድህ ይገፈፍ ጌታ የእውነት አምላክ ነው፡፡

  ReplyDelete