Wednesday, October 26, 2016

የአትላንታ የኖርዝ ካሎራይና እና የቴነሲ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ከአገልግሎት ተባረሩ። በአትላንታ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ረጅም ጊዜ አገልግለዋል። በቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመርቀው በናዝሬት ቅድስት ማርያም አስተዳዳሪ ሆነው በርካታ መንፈሳዊ ሥራ የሰሩ አባት ናቸው። በባሕርያቸው እጅግ የዋህና ትሑት ክፋት የሌለባቸው ሲሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ከቅንነት ጋር ተጨምሮ መንፈሳዊ ውበት የሚታይባቸው መልካም ምሳሌ የሚሆኑ አባት ናቸው። ዓይናቸው ያልተገለጠ እና ሃይማኖትን በጥቅም በዘረኝነት በፖለቲካ ብቻ የሚተረጉሙ ጥቂት የቦርድ (በአሜሪካ ካህናት አጠራር የደርግ) አባላት ጥቃት ደርሶባቸዋል።
   በነዚህ የቦርድ አባላትና በማሕበረ ቅዱሳን ሴራ አባ ኃይለ ሚካኤል የሚባሉ ትቢተኛ መነኩሴ ከኢትዮጵያ ሄደው እንዲቀጠሩ ሆኖ ከአቡነ ያዕቆብና ሌሎች አገልጋዮች ጋር ጦርነት እንዲያደርጉ ተደርጎ ነበር። ፍየል ከመድረሷ ጎመን መቀንጠሷ እንዲሉ ይህ ቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክስ አይመስልም እያሉ ወሬ መንዛት ጀመሩ። ከዚያም ግሪኮች እና ግብፆች በሚጠቀሙበት በሥርዓት በተዘጋጀ ወይን ይሰጥ የነበረውን የጌታ ደም ይህ ምንፍቅና ነው በማለት ወደ ወይን ጭማቂ እንዲመለስ አደረጉ። ንጹሑን ወንጌል ዘወር አድርገው በተረት የተሞሉ ገድላትን እና ልብ ወለድ ድርሳናትን መስበክ ጀመሩ። መነኩሴው ዜማ አዋቂና ብሉይ ኪዳን የተማሩ ናቸው ነገር ግን እውነት ከውሸት ጋር ተቀላቅሎባቸው ጠላና አረቄ ደባልቆ እንደጠጣ ሰው ነው ስብከታቸው። 

  እረፍት ልውጣ እያሉ በሰሜን አሜሪካ የሚካሄዱ የማህበሩ ጉባኤዎችን በስውር ተካፍለው ስውር ተልእኮ ይዘው ይመጡና ሕዝቡን መከፋፈል አቡነ ያዕቆብ መናፍቅ ናቸው ተሃድሶ አራማጅ ናቸው በማለት ሲከሱ ኖረው። በመጨረሻ አቡኑ ካልተባረሩ እዚህ አልኖርም ብለው ስውር ተልእኮ ወደ ሰጣቸው ወደ ማህበሩ ቤተ ክርስቲያን ከሄዱ ቆይተዋል። በዚህ ምክንያት የክፋታቸው ሰለባ የሆኑ አንዳድ ምእመናን እና ፖለቲካዊ ተልእኮ ያላቸው የቦርድ አባላትን በስልክ በመቀስቀስ የቤተ ክርስቲያን መሪና ኃላፊ የሆኑ ሊቀ ጳጳሱን ከአገልግሎት አሳግደዋል።
 በመሠረቱ አንድን ጳጳስ በአድማ ከቤተ ክርስቲያን ማባረር ሥርዓት አልበኝነትን ለዚህ ትውልድ ማስተማር መሆኑን መታወቅ አለበት። ትላልቅ ሰዎችን አለማክበር ሽምግልናን አባትነትን ማዋረድ መሪነትን መናቅና ትልቅነትን አለመቀበል አገርንም ሆነ ትውልድን የሚያፈርስ አደገኛ ነገር ነው። የዛሬዎቹ የኢሕዴግ መሪዎች በወጣትነታቸው እንደፈለጋቸው የሚናገሩ ትላልቅ ሰዎችን የማያከብሩ ለሽምግልና ዋጋ የማይሰጡ መካሪዎችን የማይሰሙ ነበሩ። እንግዲህ ሰው በቆፈረው ጉድጓድ መግባቱ አይቀርምና ዛሬ የነርሱን ታላቅነት የማይቀበል፤ ሽምግልናን የማያከብር ትውልድ በመፍጠራቸው ምክራቸውን የሚሰማ የለም፤ እነሱም አይሰሙም ነበርና እነሱንም የሚሰማ ስለጠፋ ግራ ተጋብተው እናያቸዋለን። አባ ኃይለ ሚካኤል ጳጳሱን ማክበር ከማስተማር ይልቅ አመጽንና ትቢትን አስተምረው ሁከትን ፈጥረዋል። ግን የክርስቶስ አገልጋይ ለመምሰል የሚያሳዩት መቅለስለስ ግብዝነት ስለሆነ ነገ ዋጋውን እንደሚከፍሉት ጥርጥር የለንም። እርሳቸውም ጳጳስ የመሆን ምኞት ይኖራቸው ይሆናልና።
 አቶ አየለና አቶ ዘውዴ ዛሬ የሚያደርጉት ነገር መልካም መስሎ ሊታያቸው ይችላል። ጊዘያዊ ጥቅም ወይም የፖለቲካ ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል የሰይጣንም ግፊት ሊሆን ይችላል። ግን ጊዜ ይስጠን እንጂ መጨረሻቸውን እናያልን። ይህን የሕሊና ቁስላቸውን የሚፈውስ መድኃኒት አይገኝላቸውም። ከክፋትና ከክህደት ከሴራና ከተንኮል የሕሊና እርካታ የሚያገኝ የሰው ልጅ የለም። "ወፍኖቶሙሰ ለኃጥአን ትጠፍእ‚ መዝ 1፥7 ትርጉም፦ የኃጥአን መንገድ ትጠፋለች እንዳለ የአምላካችን ቃል የጥቅም የዘርኝነት የክፋት የተንኮል መንገድ መጨረሻው የሕሊና ጠባሳና የጌታን ፍርድ ማምጣት ነው። አንዳድ ሰዎች የሠሩት ክፋት በልጆቻቸው ላይ ሲገለጥ እናያለን ባንዳዶች ደግሞ በራሳቸው ላይ፤ ምክንያቱም ለክፋት የሚከፈል ዋጋ እርግማን እንጂ በረከት ሊሆን አይችልምና፤ ንስሐ የገቡት ብቻ ናቸው ራሳቸውንም ትውልዳቸውንም የሚያስመልጡት።
 ሻቢያ ወያኔ ደርግ ኢሓፓ መኢሶን ኦነግ ኢድዩ ወዘተ የተባሉ ድርጅቶች ሁሉ መመሪያቸው ቅናት እንጂ ቅንነት አልነበረም። የነዚህ ድርጅቶች አባላት ሁሉ እግዚአብሔር የለም የሚለው ፍልስፍና፤ ሥጋ ብቻ የመሆን ንቅናቄ፤  ትልቅነትን የሚንቁ፤ መንፈሳዊነትን ኋላ ቀርነት አድርገው የሚያዩ ትውልዶች እንደነበሩ ታሪካቸው ያስረዳል። መጨረሻቸውም ይኸው ጥፋት ነው የሆነው። የኃጥአን መንገድ ትጠፋለች የሚለውን የጌታ ቃል በማስረጃ እያየነው ነው። ለኢትዮጵያና ለኤርትራ የነዚህ ትውልዶች መንገድ ያመጣው ምንድን ነው? ውጤቱ ስደትና ውድመት፤ አለመደማመጥ ዘርኝነት ውድቀትና አለመተማመን አይደለምን? ይህን ያነሳንበት ምክንያት ያ ትውልድ ዛሬም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ እየበጠበጠ ስለሚገኝ ነው። ቤተ ክርስቲያንን በፖለቲካ መንገድ ለመምራት ለዚያውም የክፋት እና የተንኮል ፖለቲካ ለማስኬድ እየሞከረ ሰላም እንዳይኖር አድርጓል።
   አንድና ሁለት ግለ ሰብእ ጳጳሱን ከቤተ ክርስቲያን የሚያባርሩበት ምክንያት ምን ይሆን ብሎ መመርመርና እልባት ማበጀት ተገቢ ነው። ሥርዓት አልባ አገርና ስርዓት አልባ ቤተ ክርስቲያን ትቶ ለማለፍ የሚደረገው ጥረት በሚመጣው ትውልድ ላይ ፈንጅ ጠምዶ እንደማስቀመጥ ነው። ልጅ የሚያደርገው አባቱ ሲያደርግ ያየውን ነውና ማስተዋል ያስፈልጋል። ማህበረ ቅዱሳን የሐሳብ ልዩነትን በጉባኤ በሚደረግ ውይይት ለመፍታት ከመጣር ይልቅ አድማና ሁከት በመቀስቀስ ተቀናቃኝን መምታት የሚለው ያለፈውን ትውልድ የፖለቲካ መንገድ ከመከተል መመለስ አለበት። ቤተ ክርስቲያንን እንሠራለን ብሎ ቤተ ክርስቲያንን ማፍረስ እየተካሄደ ነው። ትልቅ ሰውን አለማክበር፣ በአድማ መንገድ ሰውን ማዋረድ ቤተ ክርስቲያንን ማፍረስ መገዛትን መደማመጥን ማፍረስ አይደለምን? ቤተ ክርስቲያን ማለት እንጨትና ድንጋይ አይደለም። ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል እሪ እንላልን እየወደመ ያለው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በዚህ ከቀጠለ ድንጋይና እንጨት ብቻውን እንደ አውሮፓ አብያተ ክርስቲያናት ሱቅና ቲያትር ቤት ከመሆን አያመልጥም። አንድ ሰው መናፍቅም ቢሆን እንኳ ከዚያ ሰው በሰላም መለየት እንጂ አድማና ሁከት አማኝ ሊያደርገው አይችልምና አስቡበት። በፈጸምነው በደል ሁሉ ንስሐ እየገባን መልካም ነገር ማስቀመጥ ርስትን ከማስቀመጥ በላይ እንደሆነ ማሰብ አለብን እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን።        

14 comments:

 1. Enter your comment...አይ እናንተ ምትሉት አታጡ እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ!!!!

  ReplyDelete
 2. LEMEJMRYA GEZE KENA ASAB TSTENAGEDEBACHU BZIHU KETLU EGZEABEHER YEMIWDEW YHEN NEW .

  ReplyDelete
 3. ENANTE KEGZIABEHER SELAYDLACHHU MELEKAMUN MELEKT COMMENT BALMEKEBEL SEW EDYANEBEW TDEMSSUTALCHU .

  ReplyDelete
 4. ይህ ድህረ ገጽ ደንበኛ የተሀድሶ መድረክ መሆኑን ማጋለጥ ከጀመረ ቆይቷል አሁን ግን አትላንታ በተደረገው ቅዳሴ ላይ በክበሮ መዝሙር:ጭፈራ :ኡኡታ:ይባስ ብለው እጅን በማጠላለፍ ወደላይ ማንሳት በመቅደሱ ላይ?በስጋ ደሙ ላይ? ይሄ ሁሉ የተደረገው በነ አባወልደትንሳይ: በነ ልዑለቃል: ዶክተር ጳጳስ ሲፈልጋቸው ፓለቲካ በደሜውስጥ ነው ያለው እያሉ በየአደባባዩ የሚያናፉት ስማቸውም አያዘኝም ለምልክት አንዳንዴም እንደ እብድ ያደርጋቸዋል አባ ምናምን ሌላውና ትልቁ በቀዳማዊ ሐይለ ሥስላሴ ግዜ ጵጵስና እምቢ ብለው በደርግ ግዜ ጵጵስና አምሮቸው የጰጰሱ አቡነ መልክ ፃዲቅ እራሳቸው ያውቁታል ምን ያህል ካቶሊክነት እንደሚይስቸግራቸው ባጠቃላይ አባ ያቆብ ይሁንልህ አቡነ ያቆብን ሊያድኗቸው የጠረባ ቡድን ልክው ቅዳሴውን ያስረበሹ እነዚሁ ከላይ የተጠቀሱት ሰዋች ድራማ ነው።እርግጠኛ ነኝ አንተም ብትሆን ከነሱ ጋር ጎጠኛ ነህ። ደሞ መንፈሳዊ ኴሌጅ የተማሩ ስትል ትንሽ አታፍርም 20 አመት ተናግረው የማያውቁትን እርግጠኛ ነኝ አስደንግጠሀቸዋል ለነገሩ እሳቸውም ካንተ የባሱ ውሸታም ናቸው አትላንታ የምታውቃቸው በውሽት ነው ሌላው አለቃ ታፊ ይባላሉ።

  ReplyDelete
 5. ቤ ክር ሀማኖት ሳይኖራት አለኝ በማለት እርስ በርስ
  ስትናኮር ሰው ይዛ ትጠፋለች በውስጥም በውጭም
  ሥርዐተ አልበኝነት ምግባረ ብልሹነት የዘር ልዩነት ሰፍኖባታል

  ReplyDelete
 6. በመጀመሪያ ይህን ጽሁፍ የጻፍህ ጸሃፊ ክርስቲያን ነህ ለማለት አልችልም አጠቃላይ የአንት ምንባብ ስድብ ነው። ምንም ልብ አድርገን ልናገናዝብ የምንችለው ነገር አላየንም ከመጀመሪያው ስትጀምር የአራት ስቴት አባት ብለሃል አይንህን ጨፍነህ በጭፍን የምታወራ ነህ አቡነ ያቆብ አሁን ስይመህ የሰጠሃቸው አንዱም ምግባር የላቸውም ሌላው ይሁ ሁሉ አንተ የሾምካቸው ምግባር ቢኖራቸው ኖሮ ለአራተኛ ጊዜ ባልተባረሩ ነበር አንተን መሳይ አላማ ስላላቸው ማለት ነው አንተም አንዱ የመናፍቅ አቀንቃኝ ስለሆንህ ወንድሜ ወይም እህቴ ውሽት ለማንም አይጠቅምም አትዋሽ ዝም ብለህ ጸልይላቸው የኔም ስራይህ ነው መሆን ያለበት

  ReplyDelete
 7. nasty nasty nasty.

  ReplyDelete
 8. በኣቡነ ያዕቆብ ላይ የደረሰው ያሳዝናል። ቻርለት ሄደው ፖለቲከኞች በክረምት ከኣጥር ውጭ ሁለት ሰዓት ሙሉ ኣስቁመው ኣባረው መለሱዋቸው። ለዛ ሁሉ ሃዋርያዊ ግልጋሎታቸው ያገኙት ነገር ይህ መሆኑ ያሳዝናል። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ ላለችበት ችግር ኣቡኑ ማንም ላይ ጣታቸውን መቀሰር ኣይችሉም። የችግሩም ኣካል ናቸውና። ኣባቶቻችን "ፊት ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ---" እንዲሉ። ያሳዝናል ያሳምማልም።ኣገራችንም ቤተ ክርስቲያናችንም በስድሳ ስድስቱ ትውልድ እየጠፉ ናቸው። እግዚኣብሄር ይርዳን።

  ReplyDelete
 9. man neh ante silematawkat bete Christian yemitawera

  ReplyDelete
 10. የአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ኢኦተቤ/ክንም በነበረው የጎሳና የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ለሁለት ተከፍላ ከፓለቲካውና ከጎሳ ችግር ሳትጸዳ አገልግሎትዋን ቀጠለች ቤ/ክን ከማንኛውም የፖለቲካና ከመሳሰሉት ውዥንብሮች ጸድታ ከማንም ሳትወግን የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች ለእዚአብሔር መንግሥት ወራሾች ማድረግ ሲገባ ያ ሳይደረግ በመቅረቱ አሁንም ለፕሮቴስታንቱ ዓለም ሌላ በር ተከፈተለት
  ለጥቂት ሳምንታት የተለያዩ መነኮሳት ካህናት ከኒውዮርክና ሎስ አንጅለስ እየመጡ ህዝቡን ማረጋግጋትና ማገልገል ሲጀምሩ ተገልጋዩ ምእመን ለረጅም ጊዜ ከቤ/ክን የተለየና ጠለቅ ያለ የቤ/ክን እውቀትም ስላልነበራቸው የሚመጡትን ካህናት ከየት ናችሁ? የት ቤ/ክን አገልግላችሁ ነበር? ምን መረጃ አላችሁ ነበር? ብሎ የሚጠይቅ እምብዛም አልነበረም ከበሮ የመታ ሁሉ ዲያቆን፣ ቀሚስ የለበሰ ሁሉ መነኩሴ ተደርጎ ይቆጠር ነበር የተጠናከረ ኮሚኒቲ ስላልነበረ ሁሉንም አጠቃላ የመገናኛ ማእከል ሁሉ ( የፖለቲካው፣ የሃይማኖቱ፣ የማህበራዊው) ሆና ሁሉንም የያዘችው ቤ/ክኗ ነበረች
  በዚህ ወቅት ነበር በአባ ገብረ ሥላሴና አባ ወልደትንሳዔ ጠቋሚነት ቤ/ክኗ አባ ገብረ መስቀል የሚባሉ መነኩሴ አስተዳደር ላይ ወደቀች ለከተማዋ የነበረው መንፈሳዊ አገልግሎት ለየት ያለ ስለነበረ ይህን ያህላል የማይባል ቁጥሩ የበዛ ምእመን በዕለተ ሰንበት ወደ ቤ/ክኗ ይጎርፍ ጀመር በተለይም ይሄ አግልግሎት ለአንድ ዓመት ያህል ሲሰጥ ቆይቶ የአገልግሎቱ መስፋትና የምእመናን ቁጥር መበርከት በኪራይ ቤት ውስጥ በጥቂት ሰዓት ውስጥ ሙሉ አገልግሎት ማከናወን ስላልተቻለ ሌላ የራስ የሆነ ቦታን መፈለግ ግዴታ ስለሆነ አንዲት አነስ ያለች አሮጌ ቤ/ክን ዲኬተር ከተማ ውስጥ ተገኝታ በምእመናን ትብብር ጸድታ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁእ አቡነ ይስሀቅና በእንግደነት ወደ አሜሪካ በመጡ ሌሎች ጳጳሳት ተባርካ ተከፈተች
  በዚህ ቤ/ክን ውስጥ ለጥቂት ወራት ከሞላ ጎደል አገልግሎቱ እየተሰጠ ሳለ አንዳንድ ችግሮች መታየት ጀመሩ ከላይ እንደተጠቀሰው በወቅቱ አግልግሎቱን የሚሰጡት ካህናት አንድ ካህን እና አንድ ዲያቆን ስለነበሩ ምእመኑም ከጥቂቶች በቀር የጠለቀ የተዋህዶ ሃይማኖት ዶግማና ቀኖና እውቀት ስለሌለው በአገልግሎቱ ላይ ስህተት ቢታይም ለምን ብሎ የሚጠይቅ አልነበረም ከምእመኑም ሲሻው ጴንጤ ቤ/ክን ሲመቸው ደግሞ ወደዚህ የሚሉም ነበሩ ምክንያቱም ፕሮቴስታንቱ ቤ/ክን ውስጥ የሚጠቀሙበት ኦርጋን ወይም ፒያኖ ካህኑ ከቅዳሴ በህዋላ መዘምራኑን ስለሚያጅቡበት እንዲሁም አንዳንድ የፕሮቴስታንት መዝሙሮችም ስለሚዘመሩ ነበር በ እንደዚህ ሁኔታ ለተወሰኑ ወራት በአዲሱ ቤ/ክን እንደተቆየ ምእመኑ በሶስት መከፈል ጀመረ አንዱ ክፍል የፓለቲካ፣ አብዛኛው የጎሳ እና በጣም ጥቂቱ ሃይማኖቱን የሚሉ ሲሆኑ ካህኑም ከአንዱ ክፍል (የጎሳ) ወግነው የክርስቶስ ወንጌል በአውደ ምህረቱ ላይ የውጊያ መሳሪያ ሆነ ባጠቃላይ በከተማው ውስጥ ትልቁ መወያያ የቤ/ክኗ ችግር ሆነ

  ReplyDelete
 11. የአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ኢኦተቤ/ክንም በነበረው የጎሳና የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ለሁለት ተከፍላ ከፓለቲካውና ከጎሳ ችግር ሳትጸዳ አገልግሎትዋን ቀጠለች ቤ/ክን ከማንኛውም የፖለቲካና ከመሳሰሉት ውዥንብሮች ጸድታ ከማንም ሳትወግን የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች ለእዚአብሔር መንግሥት ወራሾች ማድረግ ሲገባ ያ ሳይደረግ በመቅረቱ አሁንም ለፕሮቴስታንቱ ዓለም ሌላ በር ተከፈተለት
  ለጥቂት ሳምንታት የተለያዩ መነኮሳት ካህናት ከኒውዮርክና ሎስ አንጅለስ እየመጡ ህዝቡን ማረጋግጋትና ማገልገል ሲጀምሩ ተገልጋዩ ምእመን ለረጅም ጊዜ ከቤ/ክን የተለየና ጠለቅ ያለ የቤ/ክን እውቀትም ስላልነበራቸው የሚመጡትን ካህናት ከየት ናችሁ? የት ቤ/ክን አገልግላችሁ ነበር? ምን መረጃ አላችሁ ነበር? ብሎ የሚጠይቅ እምብዛም አልነበረም ከበሮ የመታ ሁሉ ዲያቆን፣ ቀሚስ የለበሰ ሁሉ መነኩሴ ተደርጎ ይቆጠር ነበር የተጠናከረ ኮሚኒቲ ስላልነበረ ሁሉንም አጠቃላ የመገናኛ ማእከል ሁሉ ( የፖለቲካው፣ የሃይማኖቱ፣ የማህበራዊው) ሆና ሁሉንም የያዘችው ቤ/ክኗ ነበረች
  በዚህ ወቅት ነበር በአባ ገብረ ሥላሴና አባ ወልደትንሳዔ ጠቋሚነት ቤ/ክኗ አባ ገብረ መስቀል የሚባሉ መነኩሴ አስተዳደር ላይ ወደቀች ለከተማዋ የነበረው መንፈሳዊ አገልግሎት ለየት ያለ ስለነበረ ይህን ያህላል የማይባል ቁጥሩ የበዛ ምእመን በዕለተ ሰንበት ወደ ቤ/ክኗ ይጎርፍ ጀመር በተለይም ይሄ አግልግሎት ለአንድ ዓመት ያህል ሲሰጥ ቆይቶ የአገልግሎቱ መስፋትና የምእመናን ቁጥር መበርከት በኪራይ ቤት ውስጥ በጥቂት ሰዓት ውስጥ ሙሉ አገልግሎት ማከናወን ስላልተቻለ ሌላ የራስ የሆነ ቦታን መፈለግ ግዴታ ስለሆነ አንዲት አነስ ያለች አሮጌ ቤ/ክን ዲኬተር ከተማ ውስጥ ተገኝታ በምእመናን ትብብር ጸድታ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁእ አቡነ ይስሀቅና በእንግደነት ወደ አሜሪካ በመጡ ሌሎች ጳጳሳት ተባርካ ተከፈተች
  በዚህ ቤ/ክን ውስጥ ለጥቂት ወራት ከሞላ ጎደል አገልግሎቱ እየተሰጠ ሳለ አንዳንድ ችግሮች መታየት ጀመሩ ከላይ እንደተጠቀሰው በወቅቱ አግልግሎቱን የሚሰጡት ካህናት አንድ ካህን እና አንድ ዲያቆን ስለነበሩ ምእመኑም ከጥቂቶች በቀር የጠለቀ የተዋህዶ ሃይማኖት ዶግማና ቀኖና እውቀት ስለሌለው በአገልግሎቱ ላይ ስህተት ቢታይም ለምን ብሎ የሚጠይቅ አልነበረም ከምእመኑም ሲሻው ጴንጤ ቤ/ክን ሲመቸው ደግሞ ወደዚህ የሚሉም ነበሩ ምክንያቱም ፕሮቴስታንቱ ቤ/ክን ውስጥ የሚጠቀሙበት ኦርጋን ወይም ፒያኖ ካህኑ ከቅዳሴ በህዋላ መዘምራኑን ስለሚያጅቡበት እንዲሁም አንዳንድ የፕሮቴስታንት መዝሙሮችም ስለሚዘመሩ ነበር በ እንደዚህ ሁኔታ ለተወሰኑ ወራት በአዲሱ ቤ/ክን እንደተቆየ ምእመኑ በሶስት መከፈል ጀመረ አንዱ ክፍል የፓለቲካ፣ አብዛኛው የጎሳ እና በጣም ጥቂቱ ሃይማኖቱን የሚሉ ሲሆኑ ካህኑም ከአንዱ ክፍል (የጎሳ) ወግነው የክርስቶስ ወንጌል በአውደ ምህረቱ ላይ የውጊያ መሳሪያ ሆነ ባጠቃላይ በከተማው ውስጥ ትልቁ መወያያ የቤ/ክኗ ችግር ሆነማን ያውራ የነበረ እንዲሉ የተዋኅዶ ሃይማኖት በተለያየ ጊዜ መናፍቃንና ፓለቲካው በሚፈጥሩት ውሽንፍር መፈተን የግድ ነበር እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ውስጥ ፕሮቴስታንቱ በውጭ ሆነው ቤ/ክናችንን መኮርኮም እንደማያጣ ተረድተው ስትራቴጂያቸውን ለውጠው ውስጧ ገብተው በሯሷ ልጆች ምዕመናን ማወክ ሲጀምሩ የአትላንታ ቤ/ክንም የመከራው ገፈት ቀማሽ ነበረች
  ቀደም ሲል እንደገለጽነው ፕሮቴስታንቱ ዘማሪ ነኝ በማለት ሰርጎ በመግባት ሊበርዝ ሞክሮ ስላልተሳካለት ጥሎ ከሄደ በኋላ ለጥቂት ጊዜ ምዕመናኑ በሰላም አምላካቸውን እያመለኩ እያለ ሌላ ፈተና ደግሞ ተደቀነ የደርግ መንግሥት ወጥቶ የኢሀደግ መንግሥት ሲገባ የፓለቲካው ውዥንብር ቤ/ክኗንም አናወጣት የአቡነ ጵውሎስ ፓትርያርክ ሆኖ ለመጎብኘት ወደ አትላንታ መምጣት በዚች ቤ/ክን ላይ ትልቅ ቀውስን አመጣ ቤ/ክኗም ለሁለት ተከፈለች አቡነ ጵውሎስን በመቃወም ምእመናኑ ቤ/ክን እንዳይገቡ ሲያደርግ የቤክኗ አገልጋይ የነበሩት ካህን በጎሳ ችግር ከጳጳሱ ጋር በማበር ቤ/ክኗን ለሁለት ከፈሏት ለመጀመሪያ ጊዜ በጎሳ እና በፖለቲካ ምክንያት በአትላንታ የተዋኅዶ ቤ/ክን ውስጥ መከፈል መጣ የዚህ ችግር መፈጠር ለፕሮቴስታንቱ ዓለም ታላቅ የምስራችም ነበር በሀገር ቤት እንደፈለጉ የተሀድሶ እምነትን ለማስፋፋት ያልተመቻቸው አንዳንድ ዲያቆናት፣ካህናት፣ መነኮሳትና ጳጳሳት ከሀገር እየወጡ ወደ ምዕራቡ አህጉር መጓዝ ጀመሩ “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልኩ. . .” ዘፀአት 20፡3-6
  በዚህ ሁኔታ ለጥቂት ወራት ያህል ቤ/ክኗ በነዚህ ችግሮች ተወጥራ ብትቆይም የአበጠ ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ መፈንዳቱ ስለማይቀር ቤ/ክኑ ተገዝቶ ገና አንድ ዓመት እንኳን ሳይሞላው ለከፍተኛ ችግር ተዳረገ መሠረቱ በአሸዋ ላይ ስለነበረም ጎርፉን ለመቋቋም አቅም ስላልነበረው በከፍተኛ ሁኔታ ተናወጠ ፖለቲከኛው፣ ጎጠኛው ወይም ዘረኛው፣ ነጋዴው፣ ዝና ፈላጊው፣ በጣም ጥቂት ደግሞ እግዚአብሔርን ፈላጊዎች እና ሌሎችም የራሳቸው የሆነ የተለያየ አጀንዳ ያላቸው ሁሉ በዕለተ ሰነበት መሰባሰብያቸው ይህችው ቤ/ክን ነበረች ካህኑም ሥራየ ብለው የያዙት ወሬ አቀባዮቻቸው ከተማ ውስጥ ምን ተወራ ምን ተባለ በማለት ቃርመው ያመጡላቸውን መቼ ሰንበት ደርሶ አውደ ምህረቱ ላይ ወጥቼ መልስ ሰጥቼበት እንጂ ለቅዳሴው ለቤ/ክኑ አገልግሎት እምብዛም አልነበሩም ትልቁ የቤ/ክናችን አገልግሎት ኪዳን ፣ ቅዳሴ፣ በበዓላት ዋዜማ መቆም፣ ሰዓታት፣ ቤ/ክን በእመቤታችን ስም ከተሰየመ የማርያም ዕለት መቀደስ (ቅዳሴ ማርያም) እና በፍልሰታ ጾም ሊኖር የሚገባው አገልግሎት ሁሉ ቀርቶ በዚች ቤ/ክን ውስጥ በዕለተ ሰንበት ትልቁ አገልግሎት ቅዳሴ መቀደስ ከዛም ዋናውን ቦታ የሚይዘው የካህኑ ፒያኖ (ኦርጋን) መጫወት እና ስብከት ብቻ ነበሩ በጣም የሚገርመው ከመድረኩ ግራና ቀኝ የሚቀመጠው ስፒከር ፒያኖ (ኦርጋን) መጫወት ሲጀመሩ ድምጹ በጣም ከፍ ስለሚደረግ ለመዘምራኑ እና ከፊት ለሚቀመጡ ምእመናን የጆሮ ህመም ስለሆነባቸው የስፒከሩን ድምጽ ለመቀነስ ሁለት መዘምራን ካህኑ ሳያውቁ ከፊቱ በቆም ድምጹን ለመቀነስ ይሞክሩ ነበር ይሄን ሁሉ ጉድ ተሸክማ በውጥረት የቆየች ቤ/ክን ጊዜው ሲደርስ በእለተ ሰንበት ነበር እንደተለመደው ቅዳሴው እንዳለቀ ትምህርት አይሉት ውግዘት ወይም ሌላ ብቻ ምኑም ያልታወቀ ነገር ተናግረው ሲጨርሱ እፊታቸው የሚገኙ ሶስት ምእመናንን (ሁለት ወንድ እና አንድ እናት) ወደ መድረክ ጠርተው የቤ/ክኑን ቁልፍ ለነሱ ሰጥተውና አንድ ለረጅም ጊዜ አትላንታ ውስጥ የኖሩ፣ ከኢትዮጵያውያኑ በሀብታቸው ላቅ ያሉ፣ ቤ/ክኗንም ከመሠረቱት አባላት አንዱ የሆኑና በገንዘባቸውም ለቤ/ክኗ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጉ የነበሩትን ምእመን እየዘለፉ፣ የእመቤታችንን ጽላት ያለበትን፣ የጌታ ሥጋውና ደሙ የተፈተተበትን መንበር ያለ ጠባቂ ጥለው እኔን ያላችሁ ተከተሉኝ እያሉ ቤ/ክኗን ዘግተው የሄዱት አባት ብሎ የሚንከባከባቸው፣ የሚታዘዛቸው እና ቤቱን ትቶ ደፋ ቀና የሚለውን የዋህ ምእመን ሲያዩ ጠላት በልባቸው ትእቢትና ማን አለብኝነትን ስላሳደረባቸው ምእመኑ ሁሉ የእመቤታችንን ጽላት ትቶ ሁሉም ርሳቸውን የሚከተል መስሏቸው ነበር ሆኖም ጥቂት ያልገባቸው የዋሆች እና በጎሳ በሽታ የተተበተቡ ብቻ ተከተሏቸው ሲሄዱ መዘመራኑም ለሁለት ተከፈሉ የቤ/ክኗም ጸሎትና ሥርአተ ቅዳሴ በዕለተ ሰንበት ተጓጎለ ቤ/ክኗም ተዘጋች….. ይቆየን

  ReplyDelete
 12. "በተቀደሰዉ ስፍራ ርኩሰት ቁሞ ስታዩ አንባቢዉ ያስተዉል"ማቴ ፳፬
  በቤተ ክርስቲያን እየተደረገ ያለዉ ያለመደማመጥ ያለመከባበር የስራተ አልበኝንት ሁኔታ በጣም የሚያሳዝን ነዉ።
  ፩ኛ ቅዳሴ እየተቀደሰ ተደርጎ በማያዉቅ ሁኔታ መዝሙር መዘመሩ በፍጹም በፍጹም ተገቢ አይደለም መወገዝ ያለበት ጉዳይ ነዉ።
  ጳጳሱን ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ ከልክሎ ጳጳሱን ከልክሎ ቅዳሴ መቀደስስ ከየት የመጣ ስራት ነዉ? ይገባል ወይ ? ክርስትናችንስ ይፈቅዳል ወይ ? የካህናቱን ሥልጣነ ክህነትስ አያስይዝም ወይ? የሚያምን ካለ ማለቴ ነዉ። ቤተ ክርስቲያን ወደየ እያመራች ነዉ?ለልጆቻችን የምናወርሳቸዉ ይህን ነዉ ?
  በጣም ያሳዝናል አሁንም ብቢሆን መፍትሔዉና በይቅታ መሆን አለበት እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን።

  ReplyDelete
 13. "ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኃጥአንም እርሻ ኃጥያት ነው!" መ.ምሳሌ 21÷4
  ይህን ቪዲዮ ለተመለከታችሁ የመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆናችሁ ልብ ልትሉት የሚገባችሁ ጉዳይ ዛሬ ላይ በድፍረት ሀጥያት የቤተክርስቲያናችን ታላቁ የፅድቅ ማሳረጊያ የቅድስናችን እንዲሁም የአምላክ ቸርነቱ የሚገለፅበት ታላቁ የፀሎት ስርዓተ ቅዳሴ ሀይማኖቷን ለማንቋሸሽ በሚጥሩ ግለሰቦሽ ሲታወክ እና ሲበጠበጥ ማየት እጅግ የመጨረሻውን የመድህን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፃሜ ዓለማት ብሎ ከተናገራቸው ምልክቶች ከፊሎችን መፈፀማቸውን እየተመለከትን ነው። ቅዳሴ ስርዓት በቅዳሴ ፀሎት ምን አይነት ክንዋኔዎች እንዳሉት ማንም ኦርቶዶክስ ክርቲያን የሚያጣው ጉዳይ አይደለም። በየትኛውም የቅድስና መንገድ የፅድቅ ትሩፋት ጎዳና እንደዚህ ያለህ ድፍረት ታይቶ አይታወቅም።በትዕቢት የቅዳሴን ስርዓት መበጥበጥ በፌዘኝነት ከስርዓት ውጭ መሆን የሀጥያት እርሻ ላይ ከሚገኙ ምግባሮች ውስጥ ይካተታሉ። ለዚህ ነው የድፍረት እና የትዕቢት ዓይን ተግሳፅን ትሸሻለች ብሎ ጠቢቡ ሶሎሞን የተናገረው። ቅዱስ ስጋው ክቡር ደሙ በሚፈተትበት ታላቅ የፀሎት ስርዓት ላይ እንዲህ ማድረግ ምን ይሉታል? ይህ ከሰነፎችና ፌዘኞች የሚጠበቅ ምግባር ውጤቱ ምን እንደሆነ አሁንም ጠቢቡ ሶሎሞን ሲናገር"ለፌዘኛ እግዚአብሔር የማይጠገን ስብራት ይሰጠዋል" በማለት በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ፅፎታል።በአንድ ወቅት በእስክንድሪያ ተፈፅሞ የታየ የድፍረት እና የእብሪት ሀጥያት በዚህ ዘመንም ከቶ መምጣቱ አይገርምም። የፖለቲካን ሀሳብ ለፖለቲከኞች መተው እንዲገባ...መድህን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር"የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የቄሳርን ለቄሳር!" በማለት ድርሻዎችን በመንፈሳዊ ምልከታዎች ተፅህኖ እንዳያሳድሩ ለያይቶ ነግሮናል።ሆኖም እኔ እስከማውቀው ዘመናዊነት ከሚጎትተው በደል አንዱ ልብን በትዕቢት መሙላት ነውና ሁላችንም "አቤቱ አፈር መሆናችንን አስብልን" በማለት በትህትና እና በፍፁም አምልኮ በጌታ እግር ስር እንውደቅ።ስለዚህ በደል እናሳስብ።ኢትዮጵያን በምህረቱ እንዲጎበኝልን የሀይማኖታችንን ፅናት እንዲያጠብቅልን በፅድቅ መንገድ እንዲመራን እንፀልይ። ፈፅሞ የአባቶችን ካህናት ምክር ግሳፄ የማይሰማ በሰማይም ድርሻ እንደሌለው ይህን እወቁ። በሰለጠነ ሀገር መኖር ለመንግስተ ሰማይ ቅርብ መሆን አይደለምና ህዝቡ መንቃት አለበት። ይህን ስርዓተ ቅዳሴ የመሰረተልን እራሱ ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና የዚህን ስርዓት መበጥበጥ ትርፉ ክርስቶስን አሳልፎ ከሰጠው ከቅዱስ ማዕዱ ቢካፈል እንኳ መጨረሻው ንሰሀ የሌለው የይሁዳ ሞት ነውና እንዳይደርስብን አቤቱ ማረን እንበል።

  ReplyDelete
 14. Enezih yederg poletikegnoch nachew betecrstiyanwan yemiyawoku.haymanot yeleshoch.abatochin yemayakebru.papa's yet yehidu Hager yelachewo yet yedresu?habesha malet gefegna lesewom le amlak yemaymech fitret malet new.bordochun terargo wede ethiopia memeles neber.habeshanet ergeman new.period.

  ReplyDelete