Sunday, November 13, 2016

በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ

1ኛ ሳሙኤል 16 ፥ 1
 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው ? በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ፤ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ አለው ይለናል ይህ ትዕዛዝ ሳሙኤል ለሳኦል እያለቀሰለት ያለ ስለሆነ እግዚአብሔር ደግሞ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው ? ያለበት ጉዳይ ነው በመሆኑም ይህንን ሁኔታ በእርግጠኝነት መናገር ቢያስፈልግ ለሳሙኤል እጅግ ከባድ ነው እንደገናም ሳኦል ለእግዚአብሔር ሰገድኩ እያለ ነው ሳሙኤል ደግሞ ምንም እንኳ ሳኦልን አግኝቶ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ በማለት የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ያስተላለፈለት ፣ ሳኦልንም እስከሞተበት ቀን ድረስ ዳግመኛ ለማየት ያልሄደበት ጉዳይ ቢሆንም የሳኦል ነገር ግን ከሳሙኤል ጨርሶ ያልቆረጠለትና ከልቡም ያልወጣለት ሰው በመሆኑ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተቀብሎና በቀንዱም ዘይቱን ሞልቶ ቅባልኝ ወደተባለው ሰው መሄድ ለሳሙኤል የሞት ያህል አዳጋች ነበር 
ለዚሁ ለእግዚአብሔር ትዕዛዝም ይሄው ሳሙኤል ምላሽ በመስጠት ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል ማለቱ አሁንም የሳኦል ነገር በሳሙኤል ሕይወት ውስጥ የሚያስከትለውን የስጋት ሃይልና የክብደት መጠን በጉልህ የሚያሳይ ነው ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ እያለ በመለማመጥ የልብስን ጫፍ ይዞ የሚቀድን ሰው ፣ አልፎም ሄዶ ለእግዚአብሔር ሰገደ የተባለን ሰውና የተለቀሰለትን ሰው ትቶ የተዘጋጀውን አዲስ ንጉሥ ለመቀባት በቀንድ ዘይትን ሞልቶ መሄድ ለሳሙኤል አሁንም ፍጹም የማይታሰብና ድንገተኛም ዱብዳ ነው ታድያ በዚህ ጉዳይ ላይ ሳሙኤል እንዲህ ከሚጨነቅ ይልቅ ይህንን ሁኔታ እግዚአብሔር ባየበት ዓይን ለማየት ዓይኑን ቢከፍት እንዲህ ባልተቸገረ ነበር ታድያ ይህንን በሳኦልና በሳሙኤል ዘመን የነበረን አጀንዳ ወደ እኛም ዘመን ስናመጣው ዛሬም በዘመናችን አቅም አግኝተው ንስሐን በሚመስሉ የማግባብያና የለበጣ ቃሎች ተውጠንጥነውና እና ተቀምመው እንደ ሳኦል ዘመን የቀጠሉ የሚመስሉ አምልኮዎች ፣ አገልግሎቶች ፣ የክህነት ሥራዎች እና ክህነቶችም ጭምር በእግዚአብሔር ዘንድ ያበቃላቸው ሆነው የተናቁና የተነወሩ ተቀባይነትም የሌላቸው ናቸው 

ሳሙኤልንም በመሠሉ የእግዚአብሔር ማላጆችና የእንባ ሰዎች ሊስተካከሉና ማሻሻያም ሊሰጥባቸው የማይፈለጉ ስለሆኑ እግዚአብሔር አሁንም ሳሙኤልን ለመሰሉ ታማኝ ባርያዎች ጊዜን ሳያባክኑ ለቀጣዩ እርምጃ የተዘጋጁ እንዲሆኑ እስከመቼ ? ………ሂድ ………..አዘጋጅቻለሁ የሚል ቃል አውጥቶባቸዋል ጌታ እግዚአብሔር እስከመቼ ? ባለበትና ባንገሽገሸው ነገር ሲያለቅሱም ሆነ እንባን ሲያፈሱ መገኘት ራስን እንደ ማሞኘት በሳኦልና በመሰሎቹም ዘንድ እንደ መሞኘት ያስቆጥራልና አይሆንም ከዚህም ሌላ ሳኦልንም ሆነ ሳኦልን ለመሰሉ የዘመናችን ሰዎች የሚጠቅም አይደለም እግዚአብሔር በማይቀበለው ነገር እንዲህ ላሉ ሰዎች ሲደክሙ መገኘት መልካም አይደለም ስለዚህ ለዚሁ ለሳሙኤል በመጣው መልዕክት መሠረት በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ ማለት ከተናቀውና ከተነወረው የሳኦል አምልኮና አገልግሎት የንግሥናም ዘመን ጭምር ውጣ እንደማለት ነው ሳሙኤል ከዚህ የሳኦል የንግሥና ፣ የአምልኮና የአገልግሎት ዘመን ካልወጣ በቀንዱ ዘይቱን መሙላት እንደገናም በቀንዱ ዘይቱን ሞልቶ እግዚአብሔር ወዳዘጋጀው ንጉሥ መሄድ አይችልም ነበርና ይህንኑ ለማድረግ ሳሙኤል ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ ወጣ እግዚአብሔር የተናገረውንም አደረገ ወደ ቤተልሔምም መጣ ይለናል ይህ ነው 
እርምጃ ማለት እንግዲህ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በአዲስ መንፈስና በአዲስ አሠራር የሚያምን ስለሆነ በዚሁ አሠራራየሚነሱ አዳዲስ ዳዊቶች ዛሬም አሉትና በቀንዱ ዘይቱን ሞልቶ እንደሄደው እንደ ሳሙኤል ለእኛም እንዲሁ ወደነዚህ ሰዎች መሄድ ይሁንልን ሳሙኤል በዚህ ጉዳይ በብዙ ያቅማማና የተቸገረ ቢሆንም ግን ከምንም በላይ እግዚአብሔር ያለውን በመታመን ለእግዚአብሔር ሊታዘዝ ፈቃደኛ በመሆኑ እግዚአብሔር የተናገረውን ማድረግ ቻለ ለእኛም ይሄ ይሁንልን ሌላው ከምታለቅስበት ነገር ወጥተህ በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ የሚለው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ለሳሙኤል እጅግ ከባድና ፈታኝ የሆነበት ምክንያት ሳሙኤል ይህንን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ታዘዘና አደረገው ማለት የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ራቀ ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው ማለት ስለሆነ ለሳኦል እጅግ ከባድና የከፋ ነገር ነው ታድያ አሁንም በዚህ ጉዳይ ሳሙኤል ለእግዚአብሔር የታዘዘ በመሆኑ ይህም ስቃይ በሳኦል ሕይወት ሆነ በመሆኑም የሳኦል ሕይወት ያላቸው ሰዎች ዛሬም ከዚህ ሕይወት ያመለጡ አይሆኑም 
ነገር ግን አሁን ላይ ባለ ሕይወታቸው ሳኦል እንዳላሰበ ይህ ይሆንብናል ይመጣብናልም ብለው አያስቡም ነገር ግን ውሎ አድሮ በሕይወታቸው ይህ ከመሆን አይቀርም የእግዚአብሔር መንፈስ በሐዲስ ኪዳን ከኛ ጋር ሊኖር የተሰጠን ቢሆንም ከተመረረ ግን ምን ሊፈጠር እንደሚችል እኔ መናገር አልችልም ለዚህም ነው ለቤዛ ቀን የታተምንበትን ቅዱሱን መንፈስ እንዳናሳዝንና እንዳናስመርር ጌታ በቃሉ የተናገረን እንደ ሳኦል ዓይነት ሰዎች ዛሬ ላይ ባለ ንስሐን በማይፈልግ ሕይወታቸው ይህንን ቢያደርጉም የነገው የሕይወት ምልልሳቸው ግን የጌታ አብሮነት የሌለበት በመሆኑ በሕይወታቸው የሚሆነው ከዚህ የከፋ ነው ጌታ እግዚአብሔር ከእንዲህ ዓይነቱ የከፋ ነገር ይጠብቀን
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

3 comments:

  1. ebakachu ebakachu Ethiopian bemulu leb gizu abba tebarere besraw new leba hulu genzeb wodad akefafay menafikan balege' aba haylemikail tikikle yecha abba kristian haimanot awake selamawie E.T.C yehe leba yakob tennasi bla bla bla tifram Goneder hulu. shewa yetemare kongo clean E.T.C.tetenkeku shewa enanten ayflegim leg atabi duket hulu.

    ReplyDelete
  2. አባ ሰላማዎች ምነው ጠፋችሀ

    ReplyDelete