Tuesday, December 13, 2016

ቤተ ክርስቲያንስ በጥልቀት መታደስ የለባትምን?ተሐድሶ የተሰኘው የግእዝ ቃል የቤተ ክርስቲያን ቃል ነው፡፡ ወይም ቤተ ክርስቲያን ስትጠቀምበት የነበረ ቃል ነው፡፡ “የነበረ” የተባለው ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ቃሉን እንዳትጠቀምበት ስለ ተደረገና ቤተ ክርስቲያን የጣለችውን ወንጌል ማንሳትና ወንጌልን መስበክ ስሕተቶቿንም ማረም አለባት ብለው ለተነሱ ልጆቿ ክፉ ስም አድርጋ በመስጠት በአሉታዊ መንገድ እየተጠቀመችበት ስለሆነ ነው፡፡ ተሐድሶ አሉታዊ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ፀረ ወንጌል ቡድኖች ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ያለ የሌለ ኃይላቸውን ተጠቅመዋል፡፡

በእነርሱ ተሐድሶ የተባሉትም ወገኖች ሳይታክቱ የተሐድሶን ትክክለኛ ምንነት ለማስረዳት ጥረት አድርገዋል፡፡ ለዚህም ነው ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ የሚለውን ስም አዎንታዊነት ወደ መግለጽ የመጣው፡፡ በሐመረ ተዋሕዶ የጥር 2008 እትም ገጽ 120 ላይ ተሐድሶ ስለሚለው ቃል እንዲህ ብሏል “ስለ ተሐድሶ የቃል በቃል ትርጉም ነጋሪ አንፈልግም፡፡ ዕድሜ ለአባቶቻችን ዛሬ እናንተ የምታደናግሩበትን ግእዝ አምልተውና አስፍተው ጽፈውልን አልፈዋልና፡፡ ቃሉ አዎንታዊ ትርጉም እንዳለውም አላጣነውም፡፡ ስማችሁ “ተሐድሶ” ይባል አይባልም ለእኛ ጉዳያችን አይደለም፡፡ በእርግጥ ቃሉ ጤነኛ ቃል ስለሆነ ለእናንተ ግብር የሚስማማ አይደለም፡፡”


ይገርማል! ቃሉ ጤነኛ መሆኑን እያወቃችሁ በአሉታዊ መልኩ እንዲታይ ማድረጋችሁ ከምን የመነጨ ነው? ቃሉ ጤነኛ ቃል መሆኑን እያወቃችሁ ቤተ ክርስቲያን ስሕተቶቿን ታርምና ወደ ወንጌል እውነት ትመለስ የሚሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ክፉ ስም አድርጋችሁ ጥቅም ላይ ማዋላችሁስ ምን ለማግኘት ይሆን? ተሐድሶ ጤናማ ቃል ከሆነ ቃሉንም ተግባሩንም ቤተ ክርስቲያን የማትጠቀምበት ለምንድነው?

መንግሥት በቅርቡ ተከስቶ ለነበረው የሕዝብ ዐመፅ መንስኤው በመንግስት በኩል ከነበሩት ክፍተቶች የተነሳ መሆኑን በማመን በጥልቀት መታደስ አለብኝ ብሎ በመጀመሪያ ደረጃ የአመራር ለውጥ የማድረግ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ተሐድሶው ጥልቅ መሆን ያለበት ከመሆኑ አንጻር በአመራር ለውጥ ብቻ የሚቆም ከሆነና አንዳንድ ፖሊሲዎች፣ ሕጎችና መመሪያዎች ላይም ፍትሻ ተደርጎ የማስተካከያ እርምጃ ካልተወሰደ በጥልቀት መታደስ አለብን የሚለው ውሳኔ ትርጉም ያጣል፡፡
መንግሥት ይህን የመሰለ ውሳኔ ሲያስተላለፍና አንዳንድ ፖሊሲዎችን ሲነድፍ ቤተ ክርስቲያን በመሪዎቿ በኩል በበዓላት ላይ በምታስተላልፈው መልእክት መጨረሻ ላይ ለሕዝቡ መልእክቱን ስታስተላለፍ እንደቆየች የሚታወቅ ነውና “በጥልቀት መታደስ አለብን” የሚለውን የመንግሥት አቋም ከዛሬ ነገ ታስተጋባዋለች የሚል ተስፋ አለ፡፡ 

መልእክቱን ማስተጋባት ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን በጥልቀት መታደስ ከሚገባቸው ተቋማት መካከል አንዷ መሆን አለባት፡፡ ምክንያቱም በብዙ አቅጣጫ በስሕተት ትምህርትና አሠራር ውስጥ ተዘፍቃ ትገኛለችና፡፡ ፍጡርና ፈጣሪን መለየት ሳይቻል ቅይጥ የሆነ አምልኮ እየተፈጸመ ነው፡፡ የጥንቱ የጌታችን የነቢያትና የሐዋርያት ትምህርት በልዩ ልዩ ዘመን አመጣሽ የስሕተት ትምህርት ተበርዟል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሙስናና ዘረኝነት ከመጠን በላይ ተንሰራፍቷል፡፡ የምትገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ ተመልክተው ወደ ተሐድሶ እንድትመጣ የሚተጉ ልጆቿን የተለያየ ስም እየሰጠች ትገፋቸዋለች፡፡ ሌሎቹም ሁኔታዎችን እያዩ በየጊዜው ወደሌሎች እየፈለሱ ነው፡፡ በአጠቃላይ ለሌላው መፍትሔ ታመጣለች የምትባለው ቤተ ክርስቲያን የችግሩ አካል ሆናለች፡፡ ስለዚህ ተሐድሶን ከምትገፋው በጥልቀት በመታደስ ለራሷም ለምድራችንም መፍትሔ እንድትሆን የጌታ ፈቃድ ይሁን፡፡

12 comments:

 1. Dear Brethren,

  Please read the conclusion of the passage.

  Your deeds and aims are not what you have mentioned here.

  Your works and objectives are clearly revealed for all the faithfuls of Tewahedo.

  It is advisable to you not to waste your time.

  ReplyDelete
 2. kikiki mk eko yemilachihu gibrachihu ye Luther new new. yeleba aynederek alu

  ReplyDelete
 3. I want to ask one is it spiritual OE secular? Because most of the time mixing the two and for me you are babilon stands for benefiting to deviel and please open your eye??

  ReplyDelete
 4. እውነቱ ይነገርDecember 15, 2016 at 7:28 AM

  ወገኖች እባካችሁ በበሬ ወለድ አሉባልታ ወሬ ከመታመስ ወደማይሻረው የእግዚአብሔር ቃል ሁላችንም እንመለስ??? የሳተ እንዲመለስ፣ የቆሸሸ እንዲነጻ፣ አሮጌው አዲስ እንዲሆን፣ አዳማዊ ማንነት በአዲሱ ሰው/በኢየሱስ ክርስቶስ ከልተለወጠ፣ በአጠቃላይ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳንን የማያመጣ ከሆነና በቃሉና በመንፈሱ መታደስ ከሌለ:1/ የክርስቶስ ሰው መሆንና በመስቀል መሰቀል 2/ዳግም መወለድ 3/በራእይ መጽሐፍ ለተጠቀሱት 7ቱ ቤ/ክርስቲያናት ጥንካሬያቸውና ድካማቸው ተገልጾ የተመለሱ ደብዳቤ መጻፉ ለምን አስፈለገ??? ወገኖቼ! ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ በ2ኛ ጢሞ 3 ላይ ከቁ 12 ጀምሮ የክፉ ሰዎችን ክፋት ከዘረዘረለት በኋላ በቁ 14 ላይ አንተ ግን በማለት እንዳስጠነቀቀው በመጀመሪያ ሁላችንም ቆም ብለን በማሰብ ቃሉና መንፈሱ የሚለንን በመስማት አምልጠን ሌላውን የዋህ ወገናችንን እናስመልጥ??? ማስተዋል ለጎደላቸውና የጠላት ዲያብሎስ መሳሪያ ለሆኑ ወገኖቻችን ማስተዋል ይስጣቸው!!!

  እውነቱ ይነገር
  ካለሁበት

  ReplyDelete
  Replies
  1. The truth is that orthodox preach always for the follower that Jesus is God not Pledged(amalaje) and to tell you the truth we received from the bible not lutter or other evil messenger. Open eye world goes to gay marriage they call bible but they don't believe be careful being to be them ?

   Delete
 5. ግድ ነው እንጂ ትታደስ

  ReplyDelete
 6. አዎን ትታደስ ኢየሱስን በማወቅ ትታደስ

  ReplyDelete
 7. kikiki...kentu lifat! gizehn sayders wede tikikleng menged temeles!..

  ReplyDelete
 8. "ፍጡርና ፈጣሪን መለየት ሳይቻል ቅይጥ የሆነ አምልኮ እየተፈጸመ ነው" ፈጻሚው አንተና መሰሎችህ ትሆናላችው የተዋሕዶ አማንያን እንዲህ ላለው ውዠምብርህ ቦታ የለንም፡፡

  ReplyDelete
 9. ባለ ራዕይ ና በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ ብቻ በአገልግሎቱ ቢሳተፍ መልካም ነው ብዬ አስባለሁ!የተቃዋሚዎችን ተቃውሞ መፍራት ና ማስታመም ግን አያስፈልግም

  ReplyDelete
 10. Let stand with God this is the time for EOC to back to Jesus.

  ReplyDelete