Tuesday, December 20, 2016

የድርሳነ ሚካኤልና የድርሳነ ገብርኤል የታሪክ ሽሚያና መዘዙ

Read in PDF

“በደቡብ ሀገር መኖር መልካም ነበረ። ግን የደቡብ ሀገር ሰዎች ከእውነተኞቹ ሐሰተኞቹ ይበዛሉ።” እንዲህ ሲሉ የጻፉት ለአማርኛ ስነ ጽሑፍ መሠረት ተጥሏል ተብሎ በሚታመንበት ከ1900-1928 ዓ.ም ድረስ ባለው ዘመን  ተነሠተው  “የአማርኛን ስነ ጽሑፍ መሠረት ከጣሉና ካጠበቁ ደራስያን መሃል እውቁ የፖለቲካ ሰውና ዲፕሎማት ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ ናቸው፡፡” ከላይ የተጠቀሰው አረፍተ ነገር የሚገኘው ወዳጄ ልቤ በተሰኘው አሊጎሪያዊ ልቦለድ መጽሐፋቸው ውስጥ ገጽ 46 ላይ ነው። በመጽሐፉ መጀመሪያ ላይ “መሪ” ባሉት መግለጫ ውስጥ “ደቡብ ሲል አዋልድ መጻሕፍት ማለቱ ነው” የሚል ጠቋሚ አስቀምጠዋልና፥ ከአዋልድ መጻሕፍት መካከል ከእውነተኞቹ ይልቅ ሐሰተኞቹ ይበዛሉ የሚል ትዝብታቸውን የገሃዱ እውነታ ነጸብራቅ በሆነው ወዳጄ ልቤ መጽሐፍ ውስጥ አዋልድ መጻሕፍት በአብዛኛው ዋሾዎች መሆናቸውን መስክረዋል።
ሌሎች ግን ስለ አዋልድ መጻሕፍት ምስክርነት ሲሰጡ አዋልድ መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስን የሚያብራሩና ከመጽሐፍ ቅዱስ የወጡ ወይም የተወለዱ ናቸው ይላሉ፡፡ ይሁን እንጂ አዋልድ መጻሕፍት በተለይም ድርሳናትና ገድላት ይዘዋል ከሚባለው እውነት ይልቅ እንደ ተባለው ውሸታቸው ይበዛል። አዋልድ መጻሕፍት በአብዛኛው በልቦለድ ታሪክና በተጋነኑ ገለጻዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚቃረኑ ብዙ የስሕተት ትምህርቶችንም በውስጣቸው ይዘዋል። አንዳንድ ጊዜም አንድን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሠፈረ ታሪክ በመሻማት እርስ በእርሳቸው ይጣላሉ፡፡ በዚህ ጽሑፍ በድርሳነ ሚካኤልና በድርሳነ ገብርኤል መካከል ስላለው ውዝግብና የታሪክ ሽሚያ በታኅሳስ ድርሳን ላይ የተገለጸውን እንመልከት፡፡ 

ድርሳነ ሚካኤል የታህሳስ 12 ንባብ ላይ “አመ ዐሡሩ ወሰኑዩ ለወርኀ ታኅሳስ ተዝካረ በዓሉ ለመልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት። እስመ በዛቲ ዕለተ ፈነዎ እግዚአብሔር ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ኀበ ሀገረ ባቢሎን ወኮነ ራብዓየ ገጽ ምስለ ሠለስቱ ደቂቅ አናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውስተ እቶነ እሳት ሶበ ገደፎሙ ናቡከደነፆር ንጉሠ ባቢሎን። ወተለዓለ ነበልባለ እሳት መጠነ አርብዓ ወተስዓቱ በእመት ወአውዓዮሙ ለእለ ያነድዱ እሳተ። ወሚካኤል ዘበጦ በበትረ ዚአሁ ለነበልባለ እሳት ወአጥፍኦ እምላዕለ ሠለስቱ ደቂቅ ወኢለከፎሙ እቶነ እሳት ግሙራ።”  ይላል፡፡ ትርጉሙ፦ “በታህሳስ በዐሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያ በዓል ነው፡፡ በዚህች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካአልን ባቢሎን ወደምትባል አገር ልኮታልና። አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ከሚባሉ ከሦስቱ ጐልማሳዎች ጋር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሚነድ እሳት ውስጥ በጨመራቸው ጊዜ አራተኛ ሆኖ ታየ፡፡ የእሳቱ ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ከፍ ከፍ አለ፤ እሳት የሚያነዱትንም አቃጠላቸው፡፡ ሚካኤልም የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሦስቱ ጐልማሳዎች ላይ አጥፍቶ አዳናቸው፤ የሚነደው እሳት ፈጽሞ ምንም አልነካቸውም።”  ይህንኑ ታሪክ ድርሳነ ገብርኤልም ለገብርኤል ሰጥቶት እናገኛለን። ይልቁንም የታኅሣሥ ገብርኤል በዓለ ንግሥ በዚህ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አብዛኛው ሰው ይህ ታሪክ የገብርኤል ታሪክ እንደሆነ ነው የሚያምነው። ነገር ግን ድርሳነ ሚካኤል ታሪኩ የእኔ ነው እያለ ነው።
ሁለቱ ድርሳናት የተጣሉበትን ይህን ታሪክ ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው የወሰዱት፡፡ ነገር ግን ሲወስዱ በትክክል አልወሰዱትም፡፡ ስም ለውጠውና መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለው ውጪ አንዳንድ የራሳቸውን መገር ጨምረው ነው እየተናገሩ ያሉት፡፡ ታሪኩ በተጻፈበት በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 3 ላይ እንደ ተገለጸው ሦስቱ ወጣቶች አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል አንሰግድም ባሉ ጊዜ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፥ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው እርሱም ተናገረ፥ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ። ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ፥ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ። የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ። የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፥ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው። እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ። የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም። ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ። የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ። እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች፥ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም፥ ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው። ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ።መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፥ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች፥ ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፥ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ። ናቡከደነፆርም መልሶ፦ መልአኩን የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ።” ትንቢተ ዳንኤል 3፥19-28፡፡
በዚህ ታሪክ ውስጥ ሦስቱን ወጣቶች ከሚነደው እሳት ያዳናቸው ሚካኤል ነው ወይም ገብርኤል ነው የሚል አልተጻፈም፡፡ እንዲያውም ናቡከደነጾር የመሰከረው “የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል” በሚል እንዲሁም “መልአኩ” ተብሎ ነው የተገለጸው እንጂ በስም አልተጠቀሰም፡፡ እንደሚታወቀው ሚካኤል ወይም ገብርኤል ተልከው የፈጸሙትን አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱስ ስማቸውን ጠቅሶ ይህን አደረጉ እንዲህ አሉ እያለ ይገልጻል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል 3 ላይ ግን የሁለቱም ስም አልተጠቀሰም፡፡ በዚህ ጊዜ ዝም ማለት ሲገባ በድፍረት ሚካኤል ነው ወይም ገብርኤል ነው ማለት በእግዚአብሔር ቃል ላይ የራስን ሐሣብ የመጨመር ትልቅ ድፍረት ነው፡፡
ከስማቸው በተጨማሪ በዚህ ታሪክ ውስጥ የሚነደው እሳት ሰለስቱ ደቂቅን እንዳላቃጠላቸው እንጂ ሚካኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሦስቱ ጐልማሳዎች ላይ አጥፍቶ እንዳዳናቸው አልተጻፈም። ይህን የሌለ ድርጊት ደራሲው በታሪኩ ውስጥ ጨምሮ ያቀረበውም አዳኝነቱን ከአምላክ ላይ ወስዶ ለሚካኤል ለመስጠት ነው፡፡ ድርሳነ ገብርኤልም ስሙንና ድርጊቱን ለገብርኤል ሰጥቶ ይህንኑ ነው የሚናገረው፡፡ ታዲያ የቱ ይታመናል? መጽሐፍ ቅዱስ ወይስ ድርሳነ ሚካኤልና ድርሳነ ገብርኤል? በዚህ ዓይነት ገድላትና ድርሳናት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወለዱ ናቸው የሚለው ውሸት ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት በተሳሳተና በተዛባ መንገድ የሚጠቀሙ ናቸው የሚለው ደግሞ ትክክል ነው፡፡
እነዚህ ድርሳናት ልቦለዶች ናቸው፡፡ ደራሲዎቻቸው ግን እንደ ለመዱት በሚካኤልና በገብርኤል ስም ከልባቸው አፍልቀው የልባቸውን ሐሳብ መጻፍ ሲችሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታሪኮችን በተዛባ መንገድ እየወሰዱና በሚካኤልና በገብርኤል ስም እያቀረቡ ሕዝብን ለማሳሳት መሞከራቸው ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ደራሲዎች መጽሐፍ ቅዱስ በሰው ሁሉ እጅ ባልገባበትና በጥቂቶች እጅ ብቻ በሚገኝበት ዘመን ማንም አይደርስብንም ብለው ይሆናል ገብርኤልና ሚካኤል ባልተጠቀሱበት ቦታ ላይ አንደኛው ሚካኤል ሌላኛው ገብርኤል ነው ሲሉ የጻፉት፡፡ አክለውም ሚካኤል ወይም ገብርኤል በበትራቸው ሲመቱት እሳቱ ጠፋ የሚል የፈጠራ ወሬ የጨመሩት፡፡
ለመሆኑ የእነዚህን ድርሰቶች ልቦለድነት አልቀበል የሚሉ ሰዎች፣ አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ያዳናቸው ማነው ይሉ ይሆን? ይሀ ታሪክ በስፋት ሲነገር የኖረው በገብርኤል ስም በመሆኑ ገብርኤል ነው እንደሚሉ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ድርሳነ ሚካኤል በበኩሉ ብዙ ሰሚ ባያገኝም ሚካኤል ነው ይላል፡፡ መቼም ሚካኤል ገብርኤል ነው ገብርኤልም ሚካኤል ነው ካልተባለ በስተቀር ሁለቱም ናቸው እንዳይባል በእሳቱ ውስጥ ከሶስቱ ወጣቶች በተጨማሪ ሲመላለስ የታየው አራተኛ እንጂ አምስተኛ የለም፡፡ ስሙም በግልጽ ባይጠቀስም የአራተኛው መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ነው የተባለው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሚካኤልም ሆነ ስለ ገብርኤል የተጻፈ አለ፡፡ በእዚያ ክፍል የተከናወነውን ሥራ ከእግዚአብሔር ተልከው የሠሩት እነርሱ መሆናቸው ተገልጾአል፡፡ ከዚያ ውጪ ግን ስማቸው ካልተጠቀሰ እነርሱ ናቸው ለማለት ምንም ማስረጃ የለንም፡፡ በዚህ ጊዜ በተጻፈው መሰረት የቃሉን ሐሳብ መረዳት ይገባል እንጂ በተሳሳተ መንገድ መሄድ የለብንም፡፡ ማንንም ቢሆን በእውነት እንጂ በሐሠት ለማክበር ማሰብ የለብንም፡፡ ስለዚህ በታህሳስ 12 ወይ 19 የሚከበረው በዓል በሐሰተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፡፡
ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ዘመናትን ያስቆጠሩ ውሸቶች ይዛ መቀጠል ትልቅ ኪሳራ ላይ የሚጥላት ነውና ቆም ብላ ልታስብ ይገባል፡፡ ዛሬ ብዙው አገልጋይና ምእመናን እውነትና ሐሠቱን እየለዩ ስለሆነ ይህን ውሸት ይዞ መዝለቅ አይቻልምና በጊዜ ተሐድሶ ማድረግና በገድላትና በድርሳናትም ጭምር ከመመራት ባለሥልጣን በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ወደ መመራት መሸጋገር አለባት፡፡

27 comments:

 1. መቼም የሚገርም ዘመን ነው እናንተማ ጌታ ካአንቺ ጋር አሳደረኘ እያያላችሁ ሰው ጨርሱ እንጂ መቼ ስለ መላእክት እና ስለቅዱሳን ክብር መናገር ትደፍራላችሁ ንጉስ ናቡከደፆርን ጠፍቶ ያናገረ እናንተንም ማናገሩ ዐይቀርም እና አትቸኩሉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ናቡከደነጾርማ የአራተኛው መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ነው ያለው እንጂ እንደ ድርሳነ ሚካኤል ሚካኤል ነው እንደ ድርሳነ ገብርኤል ደግሞ ገብርኤል ነው አላለም፡፡ ቅዱሳን መላእክት ደግሞ በተጻፈው እንጂ በውሸት አይከብሩም የዚህ ጽሁፍ መልእክትም ይህው ነው፡፡ ታዲያ እውነቱ ሲነገርና እንስተካከል ሲባል የጥሁፉን ፍሬ ነገር ትቶ መዘላበድ ምን ይባላል፡፡

   Delete
 2. Dear Brother,

  We are not sola scriptural Churches like you.

  Tewahedo has Tradition . This is a headache only for you and your fellow brethren, protestants.

  It is not a right decision to you to discuss on this subject.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያላት ቢሆንም አንድን ትውፊት የምትቀበለው ትውፊት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የተስማማውን ነው፡፡ አሁን ጥያቄው በቀረበው ጽሁፍ የተገለጸው ከቃሉ ጋር ስለማይስማማ ተቀባይነት የለውም የሚለው ለእኔ ትክክል ነው፡፡ የሚሻለው የተሳሳተውን ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ማረም እንጂ ትውፊት ስለሆነ ብቻ ልክ ነው ማለት አይመስለኝም፡፡ በተለይ ድርሳኖቹን እርስ በእርስ እንዴት ማስታረቅ ይቻላል? ከመጽሐፍ ቀዱስ ትምህርት ጋራስ እንዴት ተስማምተው ሊቆሙ ይችላሉ በሚለው ላይ መወያየቱ ጥሩ ነው እላለሁ

   Delete
  2. memhr dr
   say the truth truth and say the false the false
   it is irrelevant who the angle was God saved his beloved believers. The enemy is now overshadows the glory of God that was manifested by the story. The enemy in the name of Gabriel and michael takes credit for clearly written story about glorious God.

   Delete
 3. you are really stupid and paganism.
  you are always against true heavenly symbolic church.

  please do to ex-host your energy and time.

  ReplyDelete
 4. የጌታ ትንሳኤ ጊዜ ለሀዋርያትና ለመቅደላዊት ማርያም የታዩት መላእክት አንድ ቦታ አንድ መላክ ሲሆን ሌላ ቦታ ሁለት መላእክት ይላል ስለዚህ መጽሃፍ ቅዱስ ተሳስቱል ማለት ነው; ሰለስቱ ደቂቅ የየራሳቸው ጠባቂ መላክ አላቸው አሳት ውስጥ ሲጨመሩ መላእክቶቹ አብረው ይገባሉ ለናቡከደነጾር የተገለጸለት አንድ መላክ ነው

  ReplyDelete
 5. we are at the edge of end of the world for that peoples are lying like this blog,love is frozen and one attack the other by force and word like Aba selama blog but the thing is that you receive payment you did falsely no more time for that?????

  ReplyDelete
 6. ልክ ብለሃል ፀሐፊው ፣ ጌታ ይባርክህ ፣ አላዎቂ

  ኦርቶዶክሳዊያን እባካችሁ በእግዚአብሔር ስም የእግዚአብሔርን ነገር መርምሩ

  ReplyDelete
 7. Dear Anonymous of Dec 21 (3:10 AM)

  Why don't you answer the question straight and tell us which DIRSAN is correct?. . . well at least according to Tewahido tradition?

  God Bless You!

  ReplyDelete
 8. Dear Brethren,

  This is still a headache only for you and your brethren.

  What is the meaning of "against" for you?

  And, what is the meaning of "supporting" for you?

  If you can not understand those words critically, all will be misleading for you.

  If you were really children of Tewahedo, first you would ask and include in your text what the Ethiopian Church Fathers and other Orthodox ( Both Eastern and Oriental) Church Fathers say on this issue. Unless you are protestant, you need to accept what they all agreed on for the last 2ooo and plus years.

  This because, their interpretation is in context of the Holy Church, not in the context of personal feelings like protestants, probably you.

  If you lack such mind on Tradition like protestants, how you can discuss about Tradition?

  Try the above suggestions.

  ReplyDelete
 9. ሰለስቱ ደቂቅን ያዳናቸው ማን ነው በሚል በዲያቆን ብርሀኑ አድማስ የተሰበከውን ዩቲዩብ ላይ ፈልጎ የተከታተለ ሰው በቂ ና አትጋቢ መልስ ያገኛል አድራሻው https://www.youtube.com/watch?v=Av22-MC77Ww

  ReplyDelete
 10. Do not worry. It is not God, S word. No one cares about dirsab

  ReplyDelete
 11. ሠለስቱ ደቂቅንም ጠባቂ መላእክቶቻቸው የሚያድኗቸው ቢኾንም ‹‹ለናቡከደነፆር የታየው አንድ መልአክ ኾኖ ሳለ ሦስቱ መላእክት እንዳዳኗቸው ተደርጎ ለምን ይገለጻል?›› የሚል ጥያቄ ልናነሣ እንችላለን፡፡ እንዲህ ያሉትን ምሥጢራት መረዳት የምንችለው በቅዱሳት መጻሕፍት ያሉትን ተመሳሳይ ታሪኮችና ይህ የሚኾንበትን ምክንያት ስናውቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የጌታችንን ትንሣኤ አራቱም ወንጌላውያን መዝግበውልናል፤ አራቱም የመዘገቡበት መንገድ ተቃርኖ ባይኖረውም ልዩነት ግን አለው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ፡- ‹‹እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ኾነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ኾኑ። /ማቴ.፳፰፥፪-፯/፣ ቅዱስ ማርቆስ፡- ‹‹ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ …›› በማለት መዝግቦታል /ማር.፲፮፥፭/፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ‹‹እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ እነሆ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ ፤›› ብሎ ጽፎታል /ሉቃ.፳፬፥፬/፡፡
  ቅዱስ ዮሐንስም ስለ ትንሣኤው ብዙ ነገር ካተተ በኋላ ‹‹ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች፤›› ሲል መዝግቦልናል /ዮሐ.፳፥፲፩-፲፪/፡፡ እነዚህን አገላለጾች ስናያቸው የአዘጋገብ ልዩነት ቢታይባቸውም ተቃርኖና የእውነታ ልዩነት ግን የላቸውም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስና ቅዱስ ማርቆስ ስለ አንድ መልአክ ሴቶችን ማነጋገር ቢገልጹም ሌላ መልአክ እንዳልነበረ ግን አላመለከቱም፡፡ ወንጌላውያኑ ስለ አንድ መልአክ መታየት ይመዝግቡልን እንጂ የተናገሩት ግን ስለ ተለያዩ መላእክት ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ከመቃብሩ ወጭ ድንጋዩን አንከባሎ ስለ ተቀመጠው መልአክ ዘግቦ ከመቃብሩ ውስጥ በቀኝ በኩል (በራስጌ ወይም በግርጌ) ስላለው መልአክ አልመዘገበም፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ደግሞ ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ስላለው መልአክ መዝግቦ ከውጭ በኩል ስላለው ወይም የመቃብሩ ድንጋይ ላይ ስላለው መልአክ አልመዘገበም፡፡ ሁለቱም ግን ‹‹ሌላ መልአክ አልነበረም›› በሚያሰኝ መንገድም አልገለጹልንም፡፡
  ቅዱስ ሉቃስና ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሁለቱም መላእክት መኖራቸውንና በግርጌና በራስጌ መኾናቸውን ገልጸውልናል፡፡ ስለዚህ ዅሉም ትክክል ናቸው ማለት ነው፡፡ የተለያዩትስ ለምንድን ነው ስንል ደግሞ አንድ መሠረታዊ መልእክት እናገኛለን፤ ይኸውም ስለ መላእክቱ የተለያየ ዓይነት መገለጥ የገለጹት ለተለያዩ ሰዎች በትንንሽ የጊዜ ልዩነት የታየውን መገለጥና ለአንዳንዶችም በተቀራራቢ፣ ነገር ግን በተለያየ ጊዜ የተገለጠውን ስለ መዘገቡ ነው፡፡ ስለዚህ የሠለስቱ ደቂቅ ድኅነትን በተመለከተ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል፤ በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል፤ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ደግሞ ሩፋኤል አዳናቸው ተብሎ መገለጹ ከላይ በወንጌል እንዳየነው ትውፊቱን ለያይቶ መዘገብ እንጂ ተቃራኒ ነገር አይደለም፡፡ በዚሁ መሠረት ሦስቱን ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልንም ያዳኗቸው ጠባቂ መላእክቶቻቸው፤ እነዚህም ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሩፋኤል ናቸው፡፡ እንኳን ሰዎቹ ሦስት ኾነው ይቅርና አንድም ሰው ቢኾን ሦስትና ከዚያ በላይ መላእክት ሊገኙ ይችላሉ፡፡

  ReplyDelete
 12. ‹‹ይህ ከኾነ ታዲያ በሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ገብርኤል ጐልቶ ለምን ይወጣል? ዕለቱ (ታኅሣሥ ፲፱ ቀን) በዓል ኾኖ የሚከበረው ለቅዱስ ገብርኤል፤ በሥዕልም ላይ ‹አራተኛው ሰው› ተብሎ በናቡከደነፆር የተገለጸው የቅዱስ ገብርኤል ሥዕል የሚሣለው ለምንድን ነው?›› ለሚለው የብዙዎቹ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ይኾናል፡፡
  ይህ የኾነበት ምክንያት ዝም ብሎ ወይም በአጋጣሚ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሥጋዌውን አስቀድሞ የገለጸው መላእክትንም በሰው አምሳል እንዲገለጹ በማድረግም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ ለሙሴ መጀመሪያ የተገለጠለት በዚሁ መንገድ ነበረ፡፡ ‹‹የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾኽ ቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድ፣ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ፤›› ተብሎ ተጽፏልና /ዘፀ.፫፥፪/፡፡ ይህም ነገረ ተዋሕዶን ወይም ምሥጢረ ሥጋዌን የሚያስረዳ መገለጥ ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱን በመላእክት አምሳል ሲገልጥ ደግሞ ቅድሚያውን ስፍራ የሚይዘው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ምክንያቱም ገብርኤል ማለት ‹‹ቃለ እግዚአብሔር›› እንደዚሁም ‹‹ሰውና አምላክ›› ማለት ስለ ኾነ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹አራተኛ ሰው አያለሁ›› እስኪል ድረስ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር ሥጋዌውን (ሰው መኾኑን) ገልጦ ያሳየው ከሦስቱ ሊቃነ መላእክት መካከል ይህን የተዋሕዶ ምሥጢር በስሙም በተልእኮውም ቅዱስ ገብርኤል የተሸከመው በመኾኑ ነው፡፡
  ስለዚህም ሦስቱም ሊቃነ መላእክት በጠባቂ መላእክትነታቸውና ረቂቃን ኃይላት በመኾናቸው በአዳኝነት ቢጠቀሱም እግዚአብሔር ሊገልጠው ለፈለገው ታላቅ ምሥጢር ተስማሚ የኾነውን መልአክ (ራሱ ገብርኤል መኾኑ ትርጕምና መልእክት ያለው ነውና) ፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን የተዋሕዶ ምሥጢር መሠረት አድርጋ በዓሉ በቅዱስ ገብርኤል ስም በታላቅ ሥርዓት እንዲከበር፣ ነገረ ሥጋዌውንም፣ የሕፃናቱን ተጋድሎም፣ የመላእክቱን ጠባቂነትም ስትገልጽበትና ስታስረዳበት ትኖራለች፡፡

  ReplyDelete
 13. መጀመሪያውንም መጽሐፍ ቅዱሱ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያወጣቸው ‹‹ገብርኤል ነው›› አይልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ የሚለው የሚከተለውን ነው፤ ‹‹የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም፡- ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፡- ‹ንጉሥ ሆይ እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፡- ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ፤›› /ዳን.፫፥፳፬-፳፭/፡፡ በዚህ አገላለጽ መሠረት አራተኛውን ሰው ያየው ንጉሡ ናቡከደነፆር ሲኾን የጨመረበት ቃል ቢኖር ‹‹አራተኛው የአማልክትን ልጅ ይመስላል›› የሚለው ነው፡፡
  ለመኾኑ አራተኛውን ሰው እርሱ ብቻ ለምን አየው? ሌሎቹ ለምን አላዩትም? የጥያቄው ቍልፍ ምሥጢር ያለው ከዚህ ላይ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ይህ ሰው ጥንቱንም ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እሳት የጣላቸው ሕዝቡን ለራሱ ምስል በማሰገድ ራሱን አምላክ አድርጎ ሊያስመልክ አስቦ ነበር፡፡ ታዲያ ራሱንና እርሱን የመሰሉትን አማክት አድርጎ የሚቈጥር ከኾነ የሚያየውን አራተኛውን ሰው ‹‹የእኛን ልጅ ይመስላል›› ወይም ‹‹እኛን ይመስላል›› ለምን አላለም? ከዚያ ይልቅ አርቆ ሌሎች አማልክትን የሚያመልክ አስመስሎ ‹‹የአማልክትን ልጅ ይመስላል›› ያለበት ምሥጢር ምንድን ነው? ንጉሡ ይህን ያለበት ምክንያት እነርሱ ሳያዩት ከሠለስቱ ደቂቅ ጋር አራተኛ ሰው ወደ እሳቱ ገብቶ ሳይኾን ነገሩ የወልደ እግዚአብሔርን በሥጋ መገለጥ የሚያመላክት ምሥጢር ሳለለው ነው፡፡
  በብሉይ ኪዳን ከተገለጹት ታላላቅ ሦስት የእግዚአብሔር መገለጦች ውስጥ ሦስተኛው ይህ የሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ነው፡፡ አንደኛው መገለጥ በመምሬ የአድባር ዛፍ ሥር እግዚአብሔር ለአብርሃም በሦስት ሰዎች አምሳል የተገለጠው መገለጥ ሲኾን /ዘፍ.፲፰/፣ ሁለተኛውም እግዚአብሔር ለአባታችን ለያዕቆብ በጐልማሳ አምሳል ተገልጾ ሲታገለው ያደረበት ታሪክና ያዕቆብም መጀመሪያ ‹‹ካልባረከኝ አልለቅህም›› ብሎ ከተባረከ በኋላ ‹‹‹እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ድና ቀረች› ሲል የዚያን ቦታ ስም ‹ጵንኤል› ብሎ ጠራው፤›› ያሰኘው መገለጥ ነው /ዘፍ.፴፪፥፳፭-፴፪/፡፡ ሦስተኛው መገለጥ ደግሞ አላዊው የባቢሎን ንጉሥ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶነ እሳት በጣለበት ወቅት ያደረገው መገለጥ ነው፡፡
  ሦስቱም መገለጦች የሚያመሳስሏቸው ሁለት ጠባይዓት አሏቸው፡፡ የመጀመሪያው በሦስቱም መንገድ እግዚአብሔር በሰው መልክና አምሳል መገለጡ ሲኾን ሁለተኛውና ዋነኛው ቃለ እግዚአብሔር በሥጋዌ (ሰው በመኾን) ተገልጦ ለሰው ፍጹም ድኅነት የሚሰጥ መኾኑን አስቀድሞ በምሳሌ መግለጥ ነው፡፡ መሠረታዊ መልእክቱ ደግሞ አምላክ ሰው ከኾነ በኋላ የሚያድነው የተስፋውን ዘር እስራኤልን ብቻ ሳይኾን አሕዛብንም ጭምር መኾኑን ለማሳየትና አሕዛብም የሥጋዌው ነገር ቀድሞ የተገለጠው ለእስራኤል ብቻ ስለ ኾነ እኛ ልናምንበት አይገባም እንዳይሉ ለዚህ ደንዳናና ጨካኝ ናቡከደነፆርም ጭምር ተገለጠለት፡፡
  በዚህ በሠለስቱ ደቂቅ ድኅነት ውስጥ የታየው መገለጠጥ ዋነኛው ምሥጢርና መልእክትም የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና አዳኝነት፤ እንደዚሁም እንደ ሠለስቱ ደቂቅ እሳትና ስለት፣ ሰይፍና ጐራዴ፤ እስራትና ግርፋት የሚቀበሉ ሰማዕታትን ዅሉ የሚያድናቸው እርሱ መኾኑን መግለጽ ነው፡፡ ታዲያ ዋነኛው መልእክቱና ምሥጢሩ ይህ ከኾነ ገብርኤልም ኾነ ሌሎቹ መላእክት ለምን ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት አወጡ (አዳኑ) ይባላሉ? በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት መሠረት ለሰዎች ከጊዜያዊና ምድራዊ አደጋና ሰዎች ከሚያመጡባቸው መከራ ድኅነት ሲደረግላቸው ድኅነታቸውን የሚፈጽሙላቸው ቅዱሳን መላእክት ማለትም ጠባቂ መላእክቶቻቸው ናቸው፡፡
  ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ ላይ ቅዱስ ያዕቆብን ያስገደለው ሄሮድስ ቅዱስ ጴጥሮስንም ለመግደል ባሰረው ጊዜ በዚያ ወቅት እንዲሞት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ መልአኩ እንዲያድነው አድርጓል፡፡ ‹‹እነሆም የጌታ መልአክ ቀረበ፤ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፡፡ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና ‹ፈጥነህ ተነሣ› አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። መልአኩም፡- ‹ታጠቅና ጫማህን አግባ› አለው፤ /ሐዋ.፲፪፥፯፲፩/፡፡
  ጌታችንም በወንጌል ‹‹ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና፤›› በማለት የተናገረው ስለ ጠባቂ መላእክቶቻችን ነው /ማቴ.፲፰፥፲/፡፡ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችንና ፈተናችን ላይ ወደ እግዚአብሔር እያመለከቱ የሚጠብቁን፣ የሚያድኑን፣ የሚያስፈርዱልን ወይም የሚያስፈርዱብንም እነርሱ (ቅዱሳን መላእክት) ናቸውና፡፡ እንደናቡከደነፆር ያለውን አስፈርደውበት አውሬ አድርገው ሣር ያስግጡታል፡፡ እርሱ ራሱም ‹‹አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤›› ብሎ አሁንም እውነቱን አረጋግጧል /ዳን.፬፥፲፫/፡፡ እንደ ሄሮድስ ያለውን ደግሞ ‹‹ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈው /ሐዋ.፲፪፥፳፫/፣ በእግዚአብሔር አስፈርደው ይቀሥፉታል፡፡

  ReplyDelete
 14. ሠለስቱ ደቂቅንም ጠባቂ መላእክቶቻቸው የሚያድኗቸው ቢኾንም ‹‹ለናቡከደነፆር የታየው አንድ መልአክ ኾኖ ሳለ ሦስቱ መላእክት እንዳዳኗቸው ተደርጎ ለምን ይገለጻል?›› የሚል ጥያቄ ልናነሣ እንችላለን፡፡ እንዲህ ያሉትን ምሥጢራት መረዳት የምንችለው በቅዱሳት መጻሕፍት ያሉትን ተመሳሳይ ታሪኮችና ይህ የሚኾንበትን ምክንያት ስናውቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የጌታችንን ትንሣኤ አራቱም ወንጌላውያን መዝግበውልናል፤ አራቱም የመዘገቡበት መንገድ ተቃርኖ ባይኖረውም ልዩነት ግን አለው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ፡- ‹‹እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ኾነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ኾኑ። /ማቴ.፳፰፥፪-፯/፣ ቅዱስ ማርቆስ፡- ‹‹ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ …›› በማለት መዝግቦታል /ማር.፲፮፥፭/፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ‹‹እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ እነሆ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ ፤›› ብሎ ጽፎታል /ሉቃ.፳፬፥፬/፡፡
  ቅዱስ ዮሐንስም ስለ ትንሣኤው ብዙ ነገር ካተተ በኋላ ‹‹ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች፤›› ሲል መዝግቦልናል /ዮሐ.፳፥፲፩-፲፪/፡፡ እነዚህን አገላለጾች ስናያቸው የአዘጋገብ ልዩነት ቢታይባቸውም ተቃርኖና የእውነታ ልዩነት ግን የላቸውም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስና ቅዱስ ማርቆስ ስለ አንድ መልአክ ሴቶችን ማነጋገር ቢገልጹም ሌላ መልአክ እንዳልነበረ ግን አላመለከቱም፡፡ ወንጌላውያኑ ስለ አንድ መልአክ መታየት ይመዝግቡልን እንጂ የተናገሩት ግን ስለ ተለያዩ መላእክት ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ከመቃብሩ ወጭ ድንጋዩን አንከባሎ ስለ ተቀመጠው መልአክ ዘግቦ ከመቃብሩ ውስጥ በቀኝ በኩል (በራስጌ ወይም በግርጌ) ስላለው መልአክ አልመዘገበም፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ደግሞ ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ስላለው መልአክ መዝግቦ ከውጭ በኩል ስላለው ወይም የመቃብሩ ድንጋይ ላይ ስላለው መልአክ አልመዘገበም፡፡ ሁለቱም ግን ‹‹ሌላ መልአክ አልነበረም›› በሚያሰኝ መንገድም አልገለጹልንም፡፡
  ቅዱስ ሉቃስና ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሁለቱም መላእክት መኖራቸውንና በግርጌና በራስጌ መኾናቸውን ገልጸውልናል፡፡ ስለዚህ ዅሉም ትክክል ናቸው ማለት ነው፡፡ የተለያዩትስ ለምንድን ነው ስንል ደግሞ አንድ መሠረታዊ መልእክት እናገኛለን፤ ይኸውም ስለ መላእክቱ የተለያየ ዓይነት መገለጥ የገለጹት ለተለያዩ ሰዎች በትንንሽ የጊዜ ልዩነት የታየውን መገለጥና ለአንዳንዶችም በተቀራራቢ፣ ነገር ግን በተለያየ ጊዜ የተገለጠውን ስለ መዘገቡ ነው፡፡ ስለዚህ የሠለስቱ ደቂቅ ድኅነትን በተመለከተ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል፤ በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል፤ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ደግሞ ሩፋኤል አዳናቸው ተብሎ መገለጹ ከላይ በወንጌል እንዳየነው ትውፊቱን ለያይቶ መዘገብ እንጂ ተቃራኒ ነገር አይደለም፡፡ በዚሁ መሠረት ሦስቱን ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልንም ያዳኗቸው ጠባቂ መላእክቶቻቸው፤ እነዚህም ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሩፋኤል ናቸው፡፡ እንኳን ሰዎቹ ሦስት ኾነው ይቅርና አንድም ሰው ቢኾን ሦስትና ከዚያ በላይ መላእክት ሊገኙ ይችላሉ፡፡
  ‹‹ይህ ከኾነ ታዲያ በሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ገብርኤል ጐልቶ ለምን ይወጣል? ዕለቱ (ታኅሣሥ ፲፱ ቀን) በዓል ኾኖ የሚከበረው ለቅዱስ ገብርኤል፤ በሥዕልም ላይ ‹አራተኛው ሰው› ተብሎ በናቡከደነፆር የተገለጸው የቅዱስ ገብርኤል ሥዕል የሚሣለው ለምንድን ነው?›› ለሚለው የብዙዎቹ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ይኾናል፡፡
  ይህ የኾነበት ምክንያት ዝም ብሎ ወይም በአጋጣሚ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሥጋዌውን አስቀድሞ የገለጸው መላእክትንም በሰው አምሳል እንዲገለጹ በማድረግም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ ለሙሴ መጀመሪያ የተገለጠለት በዚሁ መንገድ ነበረ፡፡ ‹‹የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾኽ ቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድ፣ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ፤›› ተብሎ ተጽፏልና /ዘፀ.፫፥፪/፡፡ ይህም ነገረ ተዋሕዶን ወይም ምሥጢረ ሥጋዌን የሚያስረዳ መገለጥ ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱን በመላእክት አምሳል ሲገልጥ ደግሞ ቅድሚያውን ስፍራ የሚይዘው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ምክንያቱም ገብርኤል ማለት ‹‹ቃለ እግዚአብሔር›› እንደዚሁም ‹‹ሰውና አምላክ›› ማለት ስለ ኾነ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹አራተኛ ሰው አያለሁ›› እስኪል ድረስ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር ሥጋዌውን (ሰው መኾኑን) ገልጦ ያሳየው ከሦስቱ ሊቃነ መላእክት መካከል ይህን የተዋሕዶ ምሥጢር በስሙም በተልእኮውም ቅዱስ ገብርኤል የተሸከመው በመኾኑ ነው፡፡
  ስለዚህም ሦስቱም ሊቃነ መላእክት በጠባቂ መላእክትነታቸውና ረቂቃን ኃይላት በመኾናቸው በአዳኝነት ቢጠቀሱም እግዚአብሔር ሊገልጠው ለፈለገው ታላቅ ምሥጢር ተስማሚ የኾነውን መልአክ (ራሱ ገብርኤል መኾኑ ትርጕምና መልእክት ያለው ነውና) ፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን የተዋሕዶ ምሥጢር መሠረት አድርጋ በዓሉ በቅዱስ ገብርኤል ስም በታላቅ ሥርዓት እንዲከበር፣ ነገረ ሥጋዌውንም፣ የሕፃናቱን ተጋድሎም፣ የመላእክቱን ጠባቂነትም ስትገልጽበትና ስታስረዳበት ትኖራለች፡፡

  ReplyDelete
 15. ሁለተኛ የላኩትን አውጡት

  ReplyDelete
 16. Mመልስ የሌለው ጥያቄ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የሌለ ነገር መጨመር ያስቀጣል።የጌታ መላእክ ከእግዚአብሄር ተልኮ እግዚአብሄርን የሚፈሩትን ሶስት ህፃነት ከእሳት ያዳነበት ቀን ተብሎ ቢከበር ።ገብርኤል ተብሎ አልተፃፈም የትም ቦታ ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እስቲ እናንተ የኦርቶዶክስ ተዋህዶን የበአል አከባበር ተዉና እናንተ የጌታ መላእክ ከእግዚአብሔር ተልኮ ሦሥቱን ህፃናት ያዳነበት ቀን ብላችሁ አክብሩ ነገሩ ቀኑንስ እንዴት ታስማሙታላችሁ።

   Delete
 17. የ ተዋህዶ ልጆች መለያ ስድብ ነው።የተም ቦታ በአለማዊውም በመንፈሳዊው ጉዳይም ደውን በመልካም ቃል ከማረም ይልቅ ስድብ የሚቀናቸው መምህሮቻቸው በእግዚአብሄር አውደ መረህረት ላይ ቆመው ስድብና መለየያየት ጥላቻን የሚሰብኩ ወንጌል እንደሰይሰበክ ተግተው የሚሰሩ ከእግዚአብሄር ሀሳብ ይልቅ ለሰው ሀሳብ የሚያደሉ ወንጌል የሚቀላቅሉ።ስድብ የዘመኑ በሽታ የተወህዶ ልጆች መለያ።አንገቱ ላይ ክር አስሮ የሚደንስ የሚሰድብ የሚሰክር ብቻ ከወንጌል ይልቅ ማን እንደፃፋቸው እንኳ ለማይታወቁ መፃህፍት አድልተው የሚከራከሩ።ክረስቶስ ሲመጣ ይህ ሁሉ ከንቱ ነው ።

  ReplyDelete
 18. የመጽሐፍ ቅዱስ ምንጭ ትናንሾቹ መጻሕፍት ናቸው እንጁ መፅሀፍ ቅዱስ ለእነርሱ መሰረት አይደለም።መፅሀፍ ቅዱስ የ16 ከፍለ ዘመን እትም ነው ።የመላእክት ስም ቢቀያየር ምነም ችግር የለውም።መላእክ ና እግዚኣብሔርም ተነጻጻሪ ይሆናሉ ።ለምሳሌ ሥላሴ ሰዶምን ለማጥፋት እንሄዳለን ብለው ከአብርሀም ገር ከተነጋገሩ በሁዋላ ሎጥ ደጃፍ ከደረሱ በሁዋላ መላእክት ተባሉ ።የመላእክትና የእግዚአብሔር መንግሥት አንዲት ናት።እርሱፈቀደ

  ReplyDelete
 19. ሁሌ የመናፍቃን አመለካከታቸው ዞሮ ዞሮ አንድ ናት። ይህቺ ትንሽ መፃሃፍ ቅዱስ አንብቢያለሁ ባይ ናት። ጌታን የሰቀሉት ስቀለው ስቀለው ብለው የጮሁ በመጨረሻም ድርጊቱን የፈፀሙ ብሉይ ኪዳን አንብበናል ባዮች ናቸው። ሃይማኖት ሁሌ በሚጨበጥ ሎጂክ ሳይሆን በቃል እና በድርጊት የሚተላለፍ ነው። በተለያየ ጊዜ ከቤተክህነት የጥፋት ሰዎች ጥቂትም ቢሆኑ ወጥተዋል። you are one of them . እናም ንሰሃ ግባ። የሰው አእምሮ የሴጣን መጫወቻ ሜዳ ሲሆን ማየት እንዴት ያሳዝናል። ነፍስ ይማር።

  ReplyDelete
 20. መናፍቅ = ከፍሎ አማኝ

  ReplyDelete
 21. ይህ ሁሉ ክርክር ምን ይረባል/ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን ብቻ ለማምለክ ለማመስገን ለ እርሱ ብቻ ሊዘምር ነው እንጂ ለፃድቃን ለደማእታት ለቅዱሳን ሲከራከር ለመኖር አይደለም ።ሁል ግዜ በማይረባ ነገር ስንከራከር ዘመኑ ሊያበቃ ነው።ከክርስቶስ ወንጌል ይልቅ ለመይረባ ክርክር ገዜ አይባክን።ገብርኤል ሆነ ሚካኤል እግዚአብሄር ካላካቸው አይመጡም።ስለዚህ ቅርንዘጫፍ ላይ አትንጠልጠሉ።

  ReplyDelete
 22. ጌታችን ስለሐሰተኞች መምህራን በማስጠንቀቂያ መልክ ለቅዱሳን ሐዋርያት እንደ ነገራቸው በቅዱሳን ሐዋርያት አንጻርም በ21ኛው ክ/ ዘመን ላለነው ክርስቲያኖች ራሳችን እንድንጠበቅ “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂ ተኩላዎች ከሆኑ ሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ (ማቴ 7÷15) ሲል ነግሮናል፡፡

  የዘመናችን መናፍቃን ትውልዱን የሚያጠምዱበትና ወደ ገደል አፋፍ የሚጥሉበትና የኑፈቄ እንክርዳድ የሚዘሩባቸው መንገዶቻቸው አጅግ በጣም ብዙዎች ናቸው ፡፡

  ከሚጠቀሙበት መንገድ መካከል ዛሬ ብሎጎቻቸውንና ፌስ ቡካቸውን ( blogs& Face bOOK ለጥንቃቄ ይጠቅማችሁ ዘንድ እንጠቁማችኋለሁ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ክፉ ሠራተኞች እንቅልፍ የሌላቸው ናቸውና እውነቱን ማጋለጥ ትውልዱ እንዲነቃባቸው ማድረግ ይገባናል፡፡” እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም “ ( የሐዋ.ሥራ 4÷22

  ReplyDelete