Wednesday, January 25, 2017

ፓትርያርኩ የቀረበላቸውን አቤቱታ አገረ ስብከቱ እንዲያጣራ አዘዙመ/ር ጎይትኦም የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ከተሾሙ ወዲህ ቀደም ሲል በተለይ በአገልጋዮች ላይ በሕገ ወጥ ዝውውርና ቅጥር ይፈጸም የነበረው ሙስናና አድሎአዊ አሰራር ወደ መስመር ገብቶና ተስተካክሎ ከነበረበት ሁኔታ ወደ ባሰ አቅጣጫ በመሄዱ ብዙዎች የችግሩ ሰላባ በመሆናቸው ጉዳዩን ለፓትርያርኩ ማቅረባቸውን ተከትሎ በፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት በኩል ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ደብዳቤ ተጻፈ፡፡ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የቀረቡትን አቤቱታዎች አባሪ በማድረግ ነው ሀገረ ስብከቱ በአስተዳደር ጉባኤ ነገሩን መርምሮ መፍትሔ እንዲሰጥ ደብዳቤ የተጻፈው፡፡ 

“ከህግና ከስርአት ውጪ የአስተዳደር በደል ደርሶብናልና ዳኝነት ታይቶ ፍትሐዊ ውሳኔ እንዲሰጥልን” በማለት በግልና በጋራ የቀረቡ 20 አቤቱታዎች በደብዳቤው ላይ የተዘረዘሩ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ አቤቱታዎች ከ3 ገጽ እስከ 35 ገጽ ድረስ የደረሰ ደጋፊ ማስረጃ አያይዘው ያቀረቡ መሆናቸውን ደብዳቤው ያስረዳል፡፡ ከአመልካቾች አቤቱታ መረዳት የተቻለውም ደመወዝና አበል እንዲሁም የሥራ ደረጃን በሚቀንስ ደብዳቤ የሥራ ዝውውር ማድረግ፣ ባልተጠራና ባልተወሰነ የስራ ግድፈት ምክንያት ሰራተኞችን ከሥራና ከደመወዝ ማሰናበት የሚሉትና የመሳሰሉት የአቤቱታዎቹ ጭብጦች መሆናቸው በደብዳቤው ላይ ተመልክቷል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት በሊቀ ማእምራን የማነ ሥራ አስኪያጅነት ጊዜ ይህን መሰሉ አሰራር ተስተካክሎ የነበረና የሰራተኞች ዝውውር በምክንያትና በውድድር ሲካሄድ የነበረ መሆኑን አስታውሰው የመ/ር ጎይትኦም አስተዳደር ግን ያን አሰራር ወደኋላ መልሶታል ይላሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ በሀገረ ስብከቱ ጩኸት እየበረከተ መምጣቱንና አቤቱታ ያቀረቡት ሰራተኞችም ወደ ፓትርያርኩ አቤት ለማለት መገደዳቸውን ይገልጻሉ፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ደብዳቤው የደረሳቸው መ/ር ጎይትኦም ጉዳዩን በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ምልአተ ጉባኤ ከመመልከት ይልቅ ከምልአተ ጉባኤው ጥቂት ሰዎችን በማዋቅር ጉዳዩ እንዲታይ እያደረጉ መሆናቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በማጣራቱ ስራ ውስጥ የሀገረ ስብከቱ ጸሀፊ ቀሲስ ሀይሉ፣ የትምህርት ክፍሉ ሊ/ማ ብርሃነ መስቀል፣ የሕግ ክፍሉ መ/ሥርዓት ብርሃነ ሕይወትና መ/ር ባሕሩ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ መ/ር ጎይትኦም ይህን አካሄድ የመረጡትም እስካሁን የተሠራው ልክ ነው እንዲሉላቸው ለማድረግ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡  ሆኖም በጥቅም ተሳስረው በሙስናው ውስጥ የተዘፈቁ ካልሆኑ በቀር ከመካከላቸው አንዳንድ መልካም ስም ያላቸው ሰዎች ስላሉ ጉዳዩን በማጣራቱ ሂደት እነርሱ ለእውነት የሚቆሙ አሊያም እውነትን በጥቅም የሚለውጡ መሆናቸው የሚፈተንበት አጋጣሚ እንደሚሆን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡     

5 comments:

 1. Enter your comment...በጎይቶም ላይ ደግም ተነሳችሁ ኧይ እናንተ ደግሞ ስለ ሀገረ ስብከቱ ይመለከታችሁዋል እንዴ መናፍቆች

  ReplyDelete
 2. ወይ ቤተክርቲያናችን እ/ር በምህረቱ ያስብሽ! በጉዳዩ ላይ ለተሳተፋችሁ እ/ር ንፁሁን ልብ ይስጣችሁ! የቀናውን መንፈስ በውስጣችሁ ያድስ!!!

  ReplyDelete

 3. ሞተች ብለው ምንም
  ቢቀሯት
  አትሞትም፤
  አትሞትም፤
  አትሞትም
  እውነት፤
  እውነት
  የግዜር
  ገንዘብ
  እንደግዜር
  ባሕርይ
  ዘላለም ሕያው
  ናት በምድር
  በሰማይ፡፡” [1]
  የዚህ ጽሑፍ ዋና ዐላማ በትምህርተ ሃይማኖት
  ኦርቶዶክስ ሳይሆኑ ኦርቶዶክስ ነን በማለት
  በልዩ ልዩ መንገድ ቤተ ክርስቲያናችንን እያወኩ
  ያሉ ማኅበራት እነርሱ እንደሚሉት
  ኦርቶዶክሳውያን አለመሆናቸውን ለምእመናን
  ማሳወቅ ነው፤ በተለይ ወጣቱ በትምህርተ
  ሃይማኖት ዕጥረት ምክንያት ቤተ ክርስቲያኑን
  በተገቢው መንገድ ስለማያውቅ
  በየዩኒቨርሲቲው በግቢ ጉባኤያት ስም
  ላጠመደው ማኅበር ምርኮኛ ሆኖ ይታያል፡፡
  ስለዚህ ወጣቶች ከማኅበር ፍቅር ይልቅ
  የአንዲት፣ ቅድስት፣ ከሁሉ በላይ የሆነችና
  ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ፍቅር
  እንዲያድርባቸው በዚህ ተከታታይ ጽሑፍ
  ለመርዳት እንሞክራለን፤ የእውነት አምላክ
  ልባችንን ለእውነት ብቻ ማስገዛት እንድንችል
  ይርዳን፤ አሜን፡፡
  በዚህ ዘመን ኦርቶዶክስ ነን ባዮች ኦርቶዶክስ
  ለመሆን ባይቻላቸውም ለመባል ብዙ
  አማራጮችን በመጠቀም ላይ ናቸው፤ እነዚህ
  አማራጮችም በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
  አጥር ግቢ ውስጥ መሰባሰብ፥ ከኦርቶዶክስ
  ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
  በተሰጠ ሕግ እንመራለን ማለት፥ የኦርቶዶክስ
  ተዋሕዶ የቊርጥ ቀን ልጆች ነን በማለት
  በየመጽሔቱ፣ በየጋዜጣውና በኢንተርኔት
  መስበክ፥ ከቅዱስ ሲኖዶስና ከአባላቱ ከብፁዓን
  አበው ሊቃነ ጳጳሳት በላይ ለኦርቶዶክስ
  ሃይማኖት ተቈርቋሪዎች ለመምሰል መሞከር፥
  የእነርሱ ማኅበር አባላት ለመሆን የማይፈልጉ
  ኦርቶዶክሳውያን አባቶች፣ አገልጋዮችንና
  ምእመናንን ተሐድሶ ናቸው በማለት መክሰስና
  ማሳደድ፥ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያኒቱን
  መዋቅሮች ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ
  አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ ተሐድሶ
  እንደ ወረራቸውና ያልተወረረ የእነርሱ ማኅበር
  ብቻ ስለ ሆነ ሕዝቡ ቅዱስ ፓትርያርኩንም ሆነ
  ሌሎች አባቶችንና የቤተ ክርስቲያን
  አገልጋዮችን እንዲጠራጠር ማድረግና ብቸኛው
  የኦርቶዶክስ አለኝታ የማይጠረጠር ድርጅት
  የእነርሱ ማኅበር ብቻ መሆኑን መስበክ እንደ
  ሆነ ካደረግነው ክትትል ለመረዳት ችለናል፡፡
  ኦርቶዶክስ ለመሆን የሚያስፈልጉ
  መሠረታውያን ነገሮች፥
  (1) የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን
  ቅዱስ መጽሐፍን ሳይቀንሱና
  ሳይጨምሩ መቀበልና
  ትምህርትንና ሕይወትን
  በቅዱስ መጽሐፍ ላይ
  መመሥረት፥ ማለትም
  የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ራስ
  ፍላጎት መጠምዘዝ ሳይሆን
  ፍላጎትንና አመለካከትን
  በእግዚአብሔር ቃል ማረም፥
  (2) በአኃት የኦርቶዶክስ አብያተ
  ክርስቲያናት ዘንድ ተቀባይነት
  ያላቸውን የሃይማኖት
  መግለጫዎች መቀበልና
  ማስተማር፥
  (3)አኃት የኦርቶዶክስ አብያተ
  ክርስቲያናት የተቀበሏቸውን
  የኒቅያ፣ የቊስጥንጥንያና
  የኤፌሶን ጉባኤያትንና
  ውሳኔዎቻቸውን መቀበልና
  ማክበር፥
  (4) በቅዱስ መጽሐፍ ላይ
  የተመሠረተ መሆኑን
  እያረጋገጡ የቀደምት
  ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንትን
  ትምህርት መቀበል ናቸው፡፡
  ከተራ ቊጥር (2)-(4) የተጠቀሱት
  እውነተኛነታቸው የሚረጋገጠው
  በቅዱስ መጽሐፍ የተመሠረቱ
  በመሆናቸው ይሆናል፤ የቅዱስ
  መጽሐፍን ትምህርት የሚቃረን
  ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን
  ትምህርትና ሥርዐት መስተካከል
  ይኖርበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ማረም
  የማትችለው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ
  ነው፡፡ ሁሉንም ነገር በመጽሐፍ
  ቅዱስ ሚዛንነት ማስተካከል
  ትችላለች፤ ይገባታልም፡፡
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
  ኦርቶዶክስም፣ ተዋሕዶም፣ ቤተ ክርስቲያንም
  የተባለችው በክርስቶስ ላይ ባላት እምነትና
  ትምህርት ነው፤ ያለ ክርስቶስ ያገኘችው ቅጽል
  “የኢትዮጵያ ” የሚለው ቃል ብቻ ነው፤ ያለ
  ክርስቶስ ኦርቶዶክስም፣ ተዋሕዶም፣ ቤተ
  ክርስቲያንም መሆን አትችልም፤ ለመባል ግን
  የሚከለክላት አይኖርም ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው
  በማንኛውም መለኪያ ተለክተው ኦርቶዶክስ
  መሆን የማይችሉ ማኅበራት ኦርቶክስ ነን
  ከማለት አልፈው እውነተኞችን የኦርቶዶክስ
  አገልጋዮችና ምእመናን በማሳደድ ሥራ
  ተጠምደው ያሉት፡፡ ለእነርሱ ኦርቶዶክሳዊነት
  መከሰስ ሳይሆን መክሰስ፣ መሰደድ ሳይሆን
  ማሳደድ፣ መገፋት ሳይሆን መግፋት ነው፡፡
  አብንና ልጁን ኢየሱስን ስለማያውቁ
  እውነተኞችን ሲገድሉ ለእግዚአብሔር
  መሥዋዕት ያቀረቡ ይመስላቸዋል፡፡ [2]
  የማኅበረ ቅዱሳንን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ
  ትምህርት ለማሳየት የተጠቀምንባቸው
  ምንጮች በራሱ በማኅበሩ ልሳናት በስምዐ
  ጽድቅ ጋዜጣና በሐመር መጽሔት የሚወጡ
  ጽሑፎች፣ በማኅበሩ የሚዘጋጁ መጻሕፍት፣
  በግለሰቦች ተዘጋጅተው በማኅበሩ ኤዲቶሪያል
  ቦርድ ታይተውና ተፈቅደው የሚታተሙና
  የሚሠራጩ መጻሕፍት፣ በኢንተርኔትና በልዩ ልዩ
  የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች የሚሠራጩ
  የማኅበሩ ትምህርቶች ናቸው፡፡ በዚህ ጽሑፍ
  የማኅበሩን ስሕተቶች ለማሳየት ማኅበሩ
  ኀላፊነት ያልወሰደባቸውን ጽሑፎች
  በማስረጃነት አንጠቀምም፡፡
  ለእውነት ባልተሰጠ ልብ ሲመዘን ማኅበረ
  ቅዱሳን መናፍቅ ነው ቢባል በራሱ አባላትም
  ሆነ በምእመናን ዘንድ ከዚያም ዐልፎ በጳጳሳት
  ሳይቀር ድንጋጤና አግራሞት እንደሚፈጥር
  እንገምታለን፤ ሆኖም ርግጠኞች የሆንንበት
  እውነት ቢኖር ማኅበረ ቅዱሳን የመናፍቃን
  ስብስብ እንጂ ኦርቶዶክሳዊ አለመሆኑ ነው፡፡
  ይህንም እውነት ዐብረውን ለሚዘልቁ
  አንባቢዎቻችን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት
  በተከታታይ በሚወጣው በዚህ ጽሑፍ
  እንደምናረጋግጥላቸው ርግጠኞች ነን፡፡
  በመሠረቱ ማኅበረ ቅዱሳን ከእውነት በመራቅ
  ገንዘብና ሥልጣን ላይ ብቻ ትኲረት ባደረጉ
  አንዳንድ ጳጳሳትና አገልጋዮች ዘንድ አይነቀፍ
  እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ቢነቅፈው ጒዳዩ
  አይደለም፤ ምክንያቱም የተቋቋመበት ዋና
  ዐላማ ቤተ ክርስቲያንን በመንፈሳዊ ኀይል
  የሚያስታጥቀውን የእግዚአብሔርን ቃል
  ለመስበክና ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትንሣኤ
  እንድታደርግ መርዳት ሳይሆን፥ የእግዚአብሔርን
  ቃል በተረታ ተረት በማሰር ትንሣኤዋን
  ማዘግየት፥ እንዲሁም የተመሠረተበትንና
  የቆመለትን ሐሰተኛ ታሪክ ለመጠበቅ ነውና፡፡
  የማኅበሩን የስሕተት ትምህርቶች ምንጭ
  ለማወቅ ባደረግነው ጥናት ማኅበረ ቅዱሳን
  አሁን ከገባበት የክሕደት ገደል ውስጥ
  የገባውና ለመውጣትም የተቸገረው በመጽሐፍ
  ቅዱስ ላይ ካለው የተሳሳተ እምነት የተነሣ
  እንደ ሆነ ተገንዝበናል፤ ጌታችን ኢየሱስ
  ክርስቶስ “መጸሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል
  አታውቁምና ትስታላችሁ” [3] ሲል
  የሰዱቃውያንን የምንፍቅና ትምህርት ምንጭ
  እንደ ገለጠልን፥ ማኅበሩም በእግዚአብሔር
  ቃል ላይ ባለው የተሳሳተ እምነት ምክንያት
  ስሕተቱን የማረምና ንስሓ የመግባት ዕድል
  ያላገኘው ከዚህ መሠረታዊ ችግር የተነሣ ነው
  ማለት እንችላለን፡፡ በዚህ ጽሑፍም ማኅበሩ
  በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ከፈጸማቸው
  ስሕተቶች አንዱን እናያለን፡፡
  1.

  ReplyDelete
 4. Aba selama wer alefew Zem kale tezega weys azegajohu yet hedu?

  ReplyDelete
 5. Ere tefachu beselam new

  ReplyDelete